#ምልክት
ላጣሽ አካባቢ
ልብሽ እግር አውጥቶ ፥ ከመሔዱ በፊት
ስለ መሸፈትሽ ፥ ሲሰጠኝ ምልክት
“እንዴት ነህ? " ስትዪኝ
"አጥቼሽ አልኖርም” ፥ ብዬ የመለስኩት
ምልክት ይሁንሽ!
ያን ጊዜ እንደነበር ፥ መሞት የጀመርኩት፡፡
እንጂማ የሚኖር...
“እንዴት ነህ? " ስትዪው
"አጥቼሽ አልኖርም” ፥ እንዴት ይላል ፍቅሬ?!
መልስና ጥያቄ
የተጣጡ ቀን ነው ፥ የመሞት ጅማሬ፡፡
እዪው ጥያቄሽን ፥ ተመልከችው መልሴን
ምልክት ይሁንሽ!
መሔድሽን ሳውቀው ፥ እኔ ማነከሴን፡፡
*
ላጣሽ አካባቢ...
ፀሎት ማላውቅ እኔ ፥ መፀለይ ጀመርኩኝ
ከፀሎት ቤት ቆሜ
አላውቅም ነበረ ፥ ምን እንደፀለይኩኝ፡፡
እፀልያለሁ ስል ፥ ምፀልየው ሳጣ
ምልክት ይሁንሽ!
የህይወት ቤት ሔጄ ፥ ወደ ሞት ስመጣ፡፡
እንጂማ ለሚኖር...
ለመፀለይ ሔዶ ፥ አይጠፋውም ፀሎት
የመሞት መንገድ ነው!
የሚሉት እያለ ፥ ምንም አለማለት።
ውይ ! ውይ! ውይ
ሞት ይርሳኝ ፥
ግርምቴን ሳልነግርሽ ፥ ረስቼው ነበር
ሞት ባይረሳም እንኳ ፥ መሞቱን ለሚኖር
ምን መሠለሽ ፍቅሬ
አሁን ረስቼው
አሁን ያስታወስኩት ፥ የምነግርሽ ነገር ?
ላጣሽ አካባቢ
ከፀሎት ቤት ስሔድ ፥ ፀሎቴን ላደርሰው
ሞቶ ነው መሰለኝ ፥ አንድ የማላውቀው ሰው
ማላቃቸው ሰዎች ፥ ከበውት ሲያለቅሱ
"ሰው ሁለት ሞት አለው.
አንድም በስጋው ነው ፥ አንድም ነው በነፍሱ
ሌላም ሌላም ነገር ፥ ሲል ነበረ ቄሱ፡፡
ከሁሉም በላይ ግን
ስጋ ለበስ ሁሉ ፥ በስጋ ሞት ያልፋል
በነፍስ መሞት ግን ፥ ከመሞት ይከፋል”
እያለ አልቃሹን
ሲያፅናና ገረመኝ ፥ አልቃሽ ፊት አሳቀኝ
እኔ አንቺን አጥቼ...
ብዙ ሞት እንደሞትኩ ፥ ቄሱ መች አወቀኝ?!
* * *
ካጣሁሽ በኀላ...
እስካጣሽ ቀን ድረስ
“አጥቼች አልኖርም” ፥ ስልሽ የነበረው
ውሸት ሆኖ አይደለም ፣ አጥቼሽ ምኖረው።
በእርግጥ እንዳሰብሽው
አጣኋትኝ ብዬ
ራሴን አጥፍቼ ፥ ሞቼ ባልቀበር
ካጣሁሽ በኋላ
ስኖር የምታዪው ፥ አሟሟቴን ነበር።
*
ሳጣሽ የሞትኩት ሞት
ሲኦልም ገነትም ፥ እኩል ሳ'ት መገኘት
ሁለቱንም ሞቶች ፥ ብዙ ጊዜ መሞት
በግማሽ ረክሶ ፥ በግማሽ መቀደስ
እያዘኑ መሣቅ ፥ እየሳቁ ማልቀስ
ሬትና ማርን ፥ እኩል ሰዓት መቅመስ
የቁም ሞት ያልሆነ
ወይ ደሞ የስጋ ፥ ወይም ደሞ የነፍስ
በማይነጥፍ ሞት ውስጥ ፥ እንጀረት መፍሰስ
ሞቶ ሞቶ ሞቶ ፥ መሞቻ ላይ መድረስ!
እንዲያ ነው የሞትኩት!
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
ላጣሽ አካባቢ
ልብሽ እግር አውጥቶ ፥ ከመሔዱ በፊት
ስለ መሸፈትሽ ፥ ሲሰጠኝ ምልክት
“እንዴት ነህ? " ስትዪኝ
"አጥቼሽ አልኖርም” ፥ ብዬ የመለስኩት
ምልክት ይሁንሽ!
ያን ጊዜ እንደነበር ፥ መሞት የጀመርኩት፡፡
እንጂማ የሚኖር...
“እንዴት ነህ? " ስትዪው
"አጥቼሽ አልኖርም” ፥ እንዴት ይላል ፍቅሬ?!
መልስና ጥያቄ
የተጣጡ ቀን ነው ፥ የመሞት ጅማሬ፡፡
እዪው ጥያቄሽን ፥ ተመልከችው መልሴን
ምልክት ይሁንሽ!
መሔድሽን ሳውቀው ፥ እኔ ማነከሴን፡፡
*
ላጣሽ አካባቢ...
ፀሎት ማላውቅ እኔ ፥ መፀለይ ጀመርኩኝ
ከፀሎት ቤት ቆሜ
አላውቅም ነበረ ፥ ምን እንደፀለይኩኝ፡፡
እፀልያለሁ ስል ፥ ምፀልየው ሳጣ
ምልክት ይሁንሽ!
የህይወት ቤት ሔጄ ፥ ወደ ሞት ስመጣ፡፡
እንጂማ ለሚኖር...
ለመፀለይ ሔዶ ፥ አይጠፋውም ፀሎት
የመሞት መንገድ ነው!
የሚሉት እያለ ፥ ምንም አለማለት።
ውይ ! ውይ! ውይ
ሞት ይርሳኝ ፥
ግርምቴን ሳልነግርሽ ፥ ረስቼው ነበር
ሞት ባይረሳም እንኳ ፥ መሞቱን ለሚኖር
ምን መሠለሽ ፍቅሬ
አሁን ረስቼው
አሁን ያስታወስኩት ፥ የምነግርሽ ነገር ?
ላጣሽ አካባቢ
ከፀሎት ቤት ስሔድ ፥ ፀሎቴን ላደርሰው
ሞቶ ነው መሰለኝ ፥ አንድ የማላውቀው ሰው
ማላቃቸው ሰዎች ፥ ከበውት ሲያለቅሱ
"ሰው ሁለት ሞት አለው.
አንድም በስጋው ነው ፥ አንድም ነው በነፍሱ
ሌላም ሌላም ነገር ፥ ሲል ነበረ ቄሱ፡፡
ከሁሉም በላይ ግን
ስጋ ለበስ ሁሉ ፥ በስጋ ሞት ያልፋል
በነፍስ መሞት ግን ፥ ከመሞት ይከፋል”
እያለ አልቃሹን
ሲያፅናና ገረመኝ ፥ አልቃሽ ፊት አሳቀኝ
እኔ አንቺን አጥቼ...
ብዙ ሞት እንደሞትኩ ፥ ቄሱ መች አወቀኝ?!
* * *
ካጣሁሽ በኀላ...
እስካጣሽ ቀን ድረስ
“አጥቼች አልኖርም” ፥ ስልሽ የነበረው
ውሸት ሆኖ አይደለም ፣ አጥቼሽ ምኖረው።
በእርግጥ እንዳሰብሽው
አጣኋትኝ ብዬ
ራሴን አጥፍቼ ፥ ሞቼ ባልቀበር
ካጣሁሽ በኋላ
ስኖር የምታዪው ፥ አሟሟቴን ነበር።
*
ሳጣሽ የሞትኩት ሞት
ሲኦልም ገነትም ፥ እኩል ሳ'ት መገኘት
ሁለቱንም ሞቶች ፥ ብዙ ጊዜ መሞት
በግማሽ ረክሶ ፥ በግማሽ መቀደስ
እያዘኑ መሣቅ ፥ እየሳቁ ማልቀስ
ሬትና ማርን ፥ እኩል ሰዓት መቅመስ
የቁም ሞት ያልሆነ
ወይ ደሞ የስጋ ፥ ወይም ደሞ የነፍስ
በማይነጥፍ ሞት ውስጥ ፥ እንጀረት መፍሰስ
ሞቶ ሞቶ ሞቶ ፥ መሞቻ ላይ መድረስ!
እንዲያ ነው የሞትኩት!
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘