#መልክአ_ሰዋሰው
መንገድ የሚያበጁ
አቅጣጫ 'ሚያስቱ
ብኩን አመልካቾች ፣
ጎዳና አሳምረው
መኼጃን ያጠፉ
እልፍ ባለጸጎች ፣
ሰዉን ቤት ከልክለው ፤
በድንኳን ያኖሩ ከጎጆ ነጥለው
እንደ ጲላጦስም
እውነትን የሸሹ ፣ እጃቸውን ታጥበው
ፍርድን የሚያዛቡ ፣ ዙፋን ተከልለው።
“ከደሙ ንጹሕ ነኝ. . .
እያሉ በድፍረት ፣ በደም የረጠቡ ፣
ስንቶች ስንት ናቸው . . . ?
ለሞት ጥቀር ወተት! ሕይወት የሚያጠቡ።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
መንገድ የሚያበጁ
አቅጣጫ 'ሚያስቱ
ብኩን አመልካቾች ፣
ጎዳና አሳምረው
መኼጃን ያጠፉ
እልፍ ባለጸጎች ፣
ሰዉን ቤት ከልክለው ፤
በድንኳን ያኖሩ ከጎጆ ነጥለው
እንደ ጲላጦስም
እውነትን የሸሹ ፣ እጃቸውን ታጥበው
ፍርድን የሚያዛቡ ፣ ዙፋን ተከልለው።
“ከደሙ ንጹሕ ነኝ. . .
እያሉ በድፍረት ፣ በደም የረጠቡ ፣
ስንቶች ስንት ናቸው . . . ?
ለሞት ጥቀር ወተት! ሕይወት የሚያጠቡ።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘