አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
578 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሐዘን_እና_ዘፈን

ማሞና ማሚቱ . . .
የሚገዙት ቆሎ ጠፋና ባ'ገሩ ፣
ፍቅራቸው ቀነሰ ፤
ጭራሽ ተባብሶ መቃቃር ጀመሩ።

ቆሎ ሻጫ እሜቴ ከገበያ ጠፍታ
የምትሠፍረውን ገብስ ከጎተራ 0ጥታ፣
መደቧ ተራቁቷል ፤ የስፍር ቁናዋ
የገብስ ዘር ጠፍቶ ከትልቅ ማሳዋ።

ቆሎ ቆርጣሚ ሰው ሥንቁ ጥራጥሬ
“ለምን? እኽል ጠፋ ካ'ገሬው ገበሬ”
እያለ 'ሚጠይቅ . .
“በየምልክቱ ገብስ እየለጠፉ
እኮ ለምንድነው? ከማሳው ያጠፉ
ብሎ የሚጠይቅ . . .

ሰበበኛ ቀዬ ፤
ገብሱን እየጠጣ ገብስ ቆሎ 'ሚያልም
ፈጭቶ ከመጋገር በጥሬ የሚልም።
ከእንክርዳዶች መኻል እኽልን ያለየ
“ገብስ ነው!” ይልኻል ፣ ገለባ እያሳየ
ገለባ ሕይወቱን ሰፍሮ እየመዘነ
በሥጋ ውቂያ ላይ ፣ ትልሙ ተበተነ።

የተበተነው ሕልም .
ዘፈን ይዞ መጣ ግልብ ኾኖ ነፋሱ ፣
ማሞ ዳቦ ናፍቆ . . .
የሚቀምሰው ቢያጣ ቢቆም እስትንፋሱ ፣
የጓዳቸውም ሐቅ . .
በሰነፍ ቆሎ ዕጣ ወድቆ ከመቅደሱ።

(. . . አዜሙ ዘፈኑ . . . )
ዘፈን ነው መፍትሔ? . . .

በተቃርኖ ስሌት ሲኾን ሱሪ ባ'ንገት
ዳቦ የበላና . . .
ቆሎ የሚናፍቅ ሲወድቅ በድንገት
በድንገቴ ሐሳብ የድንገቴ ኹነት
የዳቦ እሥረኛ ቆሎ ዕላሚ ኑረት !
መሠረት የሌለው ቤቱ ዐጥር አልባ ፣
በገል ምንነቱ . . .
ማዕበል ተማምኖ የሚዋዥቅ ጀልባ፡፡

የ'ንእሜቴ ጎጆ . .
እንዲኽ ባ'ንድ ጊዜ ገብስ ጠፋ ሲሉ
የ'ነማሞ ፍቅር መፍረስ ነው ሽመሉ።
በጥሬ ሕይወቱ . .
ቆሎ ቆርጣሚ ሰው ፣ ዳቦ እየናፈቀ
ከሥጋ መደብ ላይ በሆዱ ወደቀ
ከግብሩ ሲራራቅ ዘፈኑ ደመቀ።

‹‹ማሞና ማሚቱ ገዙ ዳቦ ቆሎ
ሮጠው ወደቁ ተነሡ በቶሎ!››

በየወደቁበት እየተዋወቁ
በየቦረቁበት እየተዋደቁ
በየዘገኑበት እየተሣለቁ ፣
የጓዳቸውም ሐቅ .
ከግዙፉ ማሳ መደቡ ተለቀ ፤
ዳቦቆሎ ኾኖ . . .
የጥንዶች ቅኔ በዘፈን ዐለቀ።

🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
👍1