አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ልነግርሽ_ከቻልኩኝ

ልነግርሽ ስሻ አንደበቴ ዝግ ነው
መራመድ አቅቶኝ ሽባ እሆናለው
ብዕሬ ይደርቃል ወረቀቴን ንፋስ
ይዞብኝ ይሄዳል
ዘዴና ብልሃት አጋጣሚ ጠፍቷል፤
ቃላቶች አላውቅም ጥሩ ቅኔም አላውቅ
በጥበብ ለመግለፅ ስኳትን ስጨነቅ
ፍቅሬ ብዙ ሆኖ ከሰማይ የላቀ
ሁሉም ያንሳብኛል ልቤ እየማቀቀ፤
በየት በኩል ሄጄ በየት ዘዴ ልቄ .
ፍቅሬን ልግስፅልሽ በቃላት ጨምቄ
ከፊቴ ስትመጪ ልሳኔን አጣለው
በቆምኩበት መድረቅ እጅ እግሬ ሽባ ነው፤
ቀናትን ስቆጥር ነገን እየናፈኩ
በተስፋ ስኳትን ህመሜን እያሰብኩ
ይህው ክረምት ገባ ፀደይም አለፈ
ላንቺ ያልኩት እንቡጥ በነፋስ ረገፈ
ዕድል እያለፈ መያዝሽ ቀረበ ፤
በየት በኩል ሄጄ በየት መንገድ ልምጣ
ዙሪያው ገደል መስሎ ሞትን የሚያመጣ
በፍቅርሽ ስዋትት መላው ቢጠፋብኝ
ዝምታን ታቅፌ ህመሜን ደበኩኝ፡፡