#ለኔ_ሲል_አይነጋም
ኢያሱ የሚሉት
በገባኦን ሰማይ ፥ ሲያቆማት ፀሀይን
እጋርድሽ ብዬ
እከልልሽ ብዬ ፥ አንቺን ከሰው ዐይን
ማንም እንዳያይሽ
አይቶ እንዳይመኝሽ ፥ ልቤ ስለሰጋ
እኔ ነኝ እመኚኝ !
በሀገሬ ሰማይ ላይ
ጨለማን ያቆምኩት ፥ መቼም እንዳይነጋ ።
ይኸው ከዛ ወዲህ
ህዝብሽና ህዝቤ
በብርሃን ናፍቆት ፥ ተሰብሮ እየታሽ
በተስፋ መንገድ ላይ ፥ እድሜው እየሸሽ
ጨለማን አቁሜው
“ይነጋል " ነው ቃሉ ፥ ሁሌም እየመሽ፡፡
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
ኢያሱ የሚሉት
በገባኦን ሰማይ ፥ ሲያቆማት ፀሀይን
እጋርድሽ ብዬ
እከልልሽ ብዬ ፥ አንቺን ከሰው ዐይን
ማንም እንዳያይሽ
አይቶ እንዳይመኝሽ ፥ ልቤ ስለሰጋ
እኔ ነኝ እመኚኝ !
በሀገሬ ሰማይ ላይ
ጨለማን ያቆምኩት ፥ መቼም እንዳይነጋ ።
ይኸው ከዛ ወዲህ
ህዝብሽና ህዝቤ
በብርሃን ናፍቆት ፥ ተሰብሮ እየታሽ
በተስፋ መንገድ ላይ ፥ እድሜው እየሸሽ
ጨለማን አቁሜው
“ይነጋል " ነው ቃሉ ፥ ሁሌም እየመሽ፡፡
🔘በላይ በቀለ ወያ🔘