#ለቃልህ #ታምኜ
በአንዲት እርጉም ቀን ልቤ ፅድቅ ሻተ
ከመፅሐፍህ መሃል “ግራህን ቢመቱ ቀኝ ስጥ” የሚል ቃል ለነብሴ ሸተተ
እልፍ ጠላቶቼ መንገዴን ተረዱ
በእፀድቃለሁ ሰበብ መስከኔን ወደዱ
መጡ ተሰልፈው
ግራዬን ነገሉ
ከቀኙም አንድ አሉ
ወገሩኝ ደጋግመው ክንዳቸው እስኪዝል
ሁሉን ዝም አልክዋቸው ፅድቅህ ይበልጣል ስል
እነሱ ቀጠሉ
የሩቅ ጠላቶቼም እየተጠራሩ
የድል ፈገግታና ቡጢ ሰነዘሩ
በዚህ ሁሉ መሀል አንተ ዝም ብለሀል
በልቤ መሀል ላይ ቃልህ ይንገዋላል
…ቡጢያቸው በረታ ዝምታህ አየለ
እልቦናዬ ውስጥ ትዕዛዝህ ዋለለ
‘…ቀኝህን ስጣቸው’ ይል ቃልህ ተነቅሮ
ግራህን ሲመቱ ቀኛቸውን አንግል ሆነ ተቀይሮ
ዝም ብሎ መጠፍጠፍ መነረቱን ትቼ
እጥፍ ቡጢዎችን ሰነዘሩ እጆቼ
በዙሪያዬ ሆነው ሲያሹኝ የነበሩ
ጠላቶቼ ሁሉ ደንብረው በረሩ
ታዲያ ይህን ጊዜ አንድ ነገር ገባኝ
እፀድቃለሁ ብሎ ፊትን ከመሰዋት
ቀድመው እየመቱ መቺን ካገር ማጥፋት
🔘በ አገኘሁ አሰግድ🔘
በአንዲት እርጉም ቀን ልቤ ፅድቅ ሻተ
ከመፅሐፍህ መሃል “ግራህን ቢመቱ ቀኝ ስጥ” የሚል ቃል ለነብሴ ሸተተ
እልፍ ጠላቶቼ መንገዴን ተረዱ
በእፀድቃለሁ ሰበብ መስከኔን ወደዱ
መጡ ተሰልፈው
ግራዬን ነገሉ
ከቀኙም አንድ አሉ
ወገሩኝ ደጋግመው ክንዳቸው እስኪዝል
ሁሉን ዝም አልክዋቸው ፅድቅህ ይበልጣል ስል
እነሱ ቀጠሉ
የሩቅ ጠላቶቼም እየተጠራሩ
የድል ፈገግታና ቡጢ ሰነዘሩ
በዚህ ሁሉ መሀል አንተ ዝም ብለሀል
በልቤ መሀል ላይ ቃልህ ይንገዋላል
…ቡጢያቸው በረታ ዝምታህ አየለ
እልቦናዬ ውስጥ ትዕዛዝህ ዋለለ
‘…ቀኝህን ስጣቸው’ ይል ቃልህ ተነቅሮ
ግራህን ሲመቱ ቀኛቸውን አንግል ሆነ ተቀይሮ
ዝም ብሎ መጠፍጠፍ መነረቱን ትቼ
እጥፍ ቡጢዎችን ሰነዘሩ እጆቼ
በዙሪያዬ ሆነው ሲያሹኝ የነበሩ
ጠላቶቼ ሁሉ ደንብረው በረሩ
ታዲያ ይህን ጊዜ አንድ ነገር ገባኝ
እፀድቃለሁ ብሎ ፊትን ከመሰዋት
ቀድመው እየመቱ መቺን ካገር ማጥፋት
🔘በ አገኘሁ አሰግድ🔘