አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
566 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮዛ_2


#ክፍል_ሀያ_አንድ(🔞)


#ቺቺንያዊው_ፍቅሮቭስኪ


እግር ጥሎኝ ጆሲ ባር ገብቼ ስዝናና ሄለን ፒንክን አገኘኋት። ሄለን አሁንም ኩል ክለብ ውስጥ እንደምትሰራ ነገረችኝ። ማርቲ እዚሁ አዲሳባ መሆኗን እስክትነግረኝ ድረስ እንደሌሎቹ ጓደኞቻችን ዱባይ የገባች መስሎኝ ነበር። ከሄለን ጋር እየጠጣን የሆድ የሆዳችንን ተጫወትን። ሁለታችንም መጀመሪያ ስለተዋወቅንባት ቺቺንያ አንስተን ብዙ የጋራ ትዝታዎቻችንን አነሳን-ጣልን። ሄለን ፒንክ ጥቂት የድሮ ወዳጆቻችን አሁንም እዚያው ቺቺንያ እንዳሉ ስትነግረኝ ዛሬውኑ ሄደን እንድንጠይቃቸው
በሞቅታ ሀሳብ አቀረብኩ። እውነትም ሞቅ ብሎኝ ነበር። ሄለን ፒንከ አላቅማማችም።

ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ሲል ጆሲ ባርን ለቀን ጥቂት የድሮ ወዳጆቻችንን ለማግኘት ወደ ቺቺንያ አመራን።
እንዲሁ ሳንተኛ ሌሊቱ ይነጋታል እንጂ ሄለንን ብዙ ክለቦች ልወስዳት እዚያው ጆሲ ባር ውስጥ እያለን አስቀድሜ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር። ምን ጣጣ አለው?! ሲነጋ እኔ አፓርታማ ሙሉ ቀን ተጋድመን
እንውላለን ብዬ አሰብኩ። የዛሬን አያድርገውና ሄለን ፒንክ ባለውለታዬ ነበረች። ሁላችንም በራሳችን
የህይወት ሀዲድ ላይ ፋታ አጥተን ስንጣደፍ በተለያየ ወቅት መልካም የዋሉልንን እንረሳለን።

ሰአቱ ገና ስለነበር እዚያው ቺቺንያ ትልቁ ክለብ ዉስጥ ገብተን በዲጄ ሙዚቃ ወለሉ ላይ በዳንስ እየሾርን ስንጠጣ እስከ ሌሊቱ 9፡30 ቆየን። እንደ ጆሲ ባር ሁሉ እዚህም የከለቡን ለፍዳዳ ወንዶች
ለከፋ እና ጅንጀና እንዲሁም የአብረን እንዝናና ጥያቄ መቋቋም ነበረብን ወንዶች መለፋደድ ከጀመሩ ደግሞ ቶሎ አይፋቱም፡ እምቢ ሲባሉ ይብስባቸዋል። እንደዉሻ ከቂጣችን ስር መርመስመስ ጀመሩ።በዚህን ጊዜ ክለቡን ጥለንላቸው ከትልቁ የቺቺንያ ክለብ ወጥተን ወደ ትንሿ ቪቪያን Tብ አመራን።ከዋናው የቺቺንያ አስፋልት የተወሰኑ ሜትሮችን ገባ ብሎ ነው የሚገኘው፡ ገና እግራችን ከመግባቱ ብሌን በጩህት ተቀበለችን።

"ሮዛ!!! እኔ አላምንም፤ በአገሩ አለሽ? ማርቲ ነግራሻለች? ብዙ ጊዜ ያለሽበትን ሁኔታ እጠይቃት ነበር፤ ከሄሊ ጋር እንኳን አልፎ አልፎ እንገናኛለን፤ ሄሊ ፒንክ እንዳንቺ አልረሳትንም ፤ እየመጣች ትጠይቀናለች ወይ ሮዚና እንዳጠፋፍሽ ግን አላማረብሽም ጥፍጥፍ..."

ብሌን ከባንኮኒው ውስጥ ወጥታ በደስታ ተጠመጠመችብኝ፤ ለደቂቃዎች አለቀቀችኝም። ከብሌን ጋር በጣም ነበር የምንዋደደው። ብሌን አልተለወጠችም፤ ውበትዋ፣ ፍልቅልቅነቷ፣ ሸንቃጣነቷ፣
ተጫዋችነቷና ማራኪ ለዛዋ አሁንም እንዳለ ነው። በህይወቷ ውስጥ የቱንም ያህል ሀዘን፣ ስቃይና መከራ ሲደርስ ብሌን እንደ አይሁዶቹ ቀልድ ፈጥራ ትዝናናበታለች። ይሄ የብሌን ልዩ ተሰጥኦ ነው። ምንም ቢደርስባት ሁሌም ሳቂታ፣ ቀልደኛና ተጫዋች ስለሆነች ሀዘን ለቅጽበት እንኳን ነክቷት የሚያውቅ አይመስልም።

እኔና ሄለንን በአሪፉ ለማስተናገድ ሽር ጉድ ስታበዛ አስቆምናት፡ ብሌን አሁንም ድረስ ያልተወጋና ንጹህ ውስኪ ከሚሸጡ እጅግ ጥቂት ታማኝ የቺቺንያ የባርና የፐብ ባለቤቶች ቀዳሚዋ ነች።

ከብሌን ባሻገር ባንኮኒው አጠገብ አንገቱን ደፍቶ በፍጹም ተመስጦ ጠርሙስ ጎርደን ጂን ወደ ሚጠጣው
ጎልማሳ ማተረች። በቪቪያን ፐብ ውስጥ ከሱ ሌላ ሰው የለም። ጂኑ አልቆ የጠርሙሱ ቂጥ ላይ ሊደርስ
ትንሽ ይቀረዋል፤

“ፍቅሮቭስኪን ልሸኝና ፐቤን ዘግተን ቤቴ እወስዳችኋለሁ፣ አሪፍ ኮንዶሚንየም ገዝቼያለሁ ደሞ።ሄልዬን አሳይቻታለሁ፤ ሮዝ ግን ዛሬ ትመርቂልኛለሽ እሺ!”

ብሌን ጉንጩን በለስላሳ መዳፏ መታ አድርጋኝ ያን ደማቅ ፈገግታዋን ለገሰችኝ፤ ፈገግታዋ አለም ሁሉ በጨለማ ቢዋጥ ለመላው አለም ብርሃን የመለገስ ሃይልና ጉልበት አለው። አይ ብሌን! ሁሌም
ፍልቅልቅ ናት። ግራና ቀኝ ከጉንጮቿ መሀል የተሰደሩት ዲምፕሎቿ በምትስቅበት ወቅት ፈገግታዋን
አድምቀውት የልእልት ገጽታን ያላብሷታል። ከበፊት ጀምሮ ከምትሀታዊ ፈገግታዋ ጀርባ አንድ ከባድ ሀዘን ወይም የማይሽር የህይውት ቁሰል እንዳለ ባስብም ያን ደፍሬ ሳልጠይቃት ነበር ከበርካታ አመታት በፊት ቺቺንያን የለቀቅኩት። በጨዋታ በጨዋታ እድርጌም ቢሆን ከደማቅ ፈገግታዋ አድማስ ማዶ የተደበቀውን የህይወት ስንክሳር ባውቅ ደስተኛ ነኝ። ከአንዳንድ ዝነኛ ኮሜድያን ህይወት ጀርባ ስፍር ቁጥር የሌለው ሀዘንና መከራ እንዳለ ሁሉ፣ የብሌን ውብ ምትሀታዊ ፈገግታ ምናልባትም በህይወት የደረስነባትን አንዳች ከባድ ስብራት መሸፈኛ ጭምብል ሊሆን ይችላል። በፊት የማውቀው ባህሪዋ አሁንም እንዳለ ነው።

ሰብለን ከቀልድና ጨዋታዋ ሌላ ልብ አንጠልጣይ የትርጉም ልቦለድ መጻህፍት መለያዎቿ ነበሩ።መጽሐፍ በማንበብ ከጓደኞቼ ብቸኛዋ ሳትሆን አትቀርም። ነገር ግን ልብ አንጠልጣይ ካልሆነ
አታነብም። የሳንድራ ብራውንን፣ የጃኪ ኮሊንስን፣ የኤሪካ ዮንግን፣ የዳኔላ ስቲልን፣ የአጋታ ክሪስቲን፣የሲድኒ ሼልደንንና የኬን ፎሌትን ስራዎች እንደዉስኪ አንጠፍጥፋ ነው የምትጠጣቸው።

ብሌን ከመደርደሪያው ላይ ሙሉ ሬድ ሌብል አውርዳ ለኔና ለሄለን ከዚያም ለሷ በብርጭቆ ቀዳች።ብርጭቆዎቻችንን አጋጭተን እየጠጣን መጨዋወቱን ቀጠልን። ደሞ ለጨዋታ! ብሌን ጋ ቀልድ፣
ጨዋታና ሳቅ በሽ ነው።

ብሌን እንደገና ወደ ጎልማሳው ጠጪ ማተረች፤

“ሮዝ! አላወቅሽውም እንዴ?”

ጎልማሳውን ገና አሁን ነበር በሙሉ አይኔ የተመለከትኩት። ፊቱን እንደ ሃምሌ ደመና አጨፍግጎታል፣ዝምታው የመርግ ያህል ይከብዳል። በራሱ አለም ውስጥ ነው ያለው። ባዶ ሊሆን ጥቂት የቀረው
የጎርደን ጠርሙሱ ላይ አፍጥጧል። ከገባንበት ቅጽበት ጀምሮ እይታውን ከጠርሙሱ ላይ አላነሳም።
በዙሪያው ያለውን ትእይንት ከነመኖሩም እስኪረሳ ድረስ በራሱ የሀሳብና የትካዜ አለም ተሳፍሮ ሩቅ የነጎደ ይመስላል።

አውቅኩት፤ ብረት አስመጪው ፍቅረዝጊ ነው። ተክለሀይማኖት አካባቢ ትልቅ መጋዘን እንዳለው ይወራ ነበር። አመታቱ የቱንም ያህል ቢረዝሙ ድሮ የሚያውቁት ሰው መሰረታዊ ገጽታ አይጠፋም።
ካልሰከረ እሱም እንደሚያውቀኝ እርግጠኛ ነኝ።

"ፍቅረዝጊ ነው አይደል ብሌን?"

ብሌን እንደ ድሮ አስካካች

ሮዝ ሰፈራችንን ከለቀቅሽ ብዙ ጊዜ ስለሆነሽ የስሙን ለውጥ አላወቅሽም ማለት ነው፡፡ ፍቅረዝጊን
| 'ፍቅሮቭስኪ' ብለን የቺቺንያን የክብር ዜግነት ሰጥተነዋል እኮ። ላለፉት አስር አመታት ዊከ ኤንዶችን ከቺቺንያ ርቆ አያውቅም፤-በተለይ ከዚህ ከቪቪያን ፐብ። በርካታ የቺቺንያ ቆነጃጅት በተገኙበትና ድል ባለ ድግስ ነበር የቺቺንያ ዜግነቱን ያቀዳጀነው”

የማስካካቱና በሳቅ የመንከትከቱ ተራ የኔ ተራ ሆነ። እንዲህ እንዲህ እያለ ጨዋታችን ደራ። ድንገት ብሌን ያልጠበቀችውን ጥያቄ አስከተልኩ፤

“የኔ ውብ! ትዳር መሰረትሽ?”

ብሌን እንደገና በሳቅ ተንከተከተች፤

“አይ ሮዝ፤ አላወቅሽም እንዴ?! ትዳር ማለት እኮ ሾርት ወይም አዳር ገብቶ እንደመውጣት ሆኗል።ባለትዳሮቹ ራሱ ሚስታቸውን እያስተኙ እኛ ጋር አይደል እንዴ የሚያመሹት? ለአንድ ለስድስት ወር ያህል ሞክሬው ነበር-ባል ተብዬው አስካሉ የተባለች ሰራተኛዬን በገዛ አልጋዬ ላይ ሲያንከባልል እጅ ከፍንጅ ይዤው በቀይ ካርድ አሰናበትኩት…” ጣሪያው እስኪሰነጠቅ በራሷ ንግግር ሳቀች።

ሶስታችንም በሞቅታ ውስጥ ነን፤ ብሌንን በሳቅ አጀብናት። ሆኖም የፍቅሮቭስኪ ጎርናና ብሶተኛ ድምጽ ከሳቅና ከጨዋታችን መለሰን። ፍቅሮቭስኪ ከባድ ሀዘን ባረበበበት ጨፍጋጋ ፊቱ ሶስታችንንም በየተራ ገረመመን።ቡናማ ኮቱን በንዴት መሬት ላይ ወረወረው። ባንኮኒውን በግዙፍ ቡጢው በተደጋጋሚ
ነረተው። ጨርቁን ሊጥል ቅጽበት የቀረው
👍2