አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
566 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ስንት #ጊዜ #ሆናችሁ?

መሃል አዲስአባ…ሸገር ላይ እያላችሁ..
የእንቁራሪቶች ድምፅ በደንብ ከሰማችሁ
በክር የታሰረ ጢንዚዛ ካያችሁ
የማርያም ፈረስን መንገድ ካገኛችሁ
በእፉዬ ገላ ‹‹ያዘኝ አትያዘኝ›› ከተጃጃላችሁ…

#ስንት #ጊዜ #ሆናችሁ ?

ሱዚ የሚዘሉ
ፔፕሲ የሚራገጡ
ሸክላ እየፈጩ በርበሬ ነው የሚሉ
ሙሽራ ሙሽራ – እቃ እቃ እቃ እቃ የሚጨዋወቱ
ጢቢ ጢቢ ሰርተው- እየተጫወቱ- የሚፈነድቁ -ሴት ልጆች ካያችሁ

#ስንት #ጊዜ #ሆናችሁ ?

በኮባ ጠመንጃ የሚተኳኩሱ
ኳሷን ከስልክ እንጨት ድብን አርገው አስረው ቴዘር የሚመቱ
በሽቦ መኪና የሚወዳደሩ
መሬትን ቆፋፍረው ብይ የሚጫወቱ
ልጆችን ካያችሁ
ዛፉን ተፈናጥጠው ሆምጣጤ የሚያወርዱ
ከአመት እስከ አመት እርግብ የሚያረቡ
በሌሊት ተነስተው ለእግር ኳስ ቡድን ስፖርት የሚሰሩ ፈርጣማ ጎረምሶች
ሰፈር ውስጥ ካያችሁ

#ስንት #ጊዜ #ሆናችሁ ?

አዲሳባ መሃል የአሞራ ክንፍ ቪላ
የቀይ ሸክላ ውብ ቤት በአይናችሁ ካያችሁ
ሰንሰልና ሃረግ አጥር ሆነው ቆመው በጎን ካለፋችሁ
ላላ ያለ ጉንጉን ሁለት ቦታ ከፍላ የተሰራች ጉብል ከገጠመቻችሁ…
‹‹አትሸኟትም ወይ መሄዷ አይደለም ወይ›› እያሉ ሲዘፍኑ ካንጀቷ ምታለቅስ ሙሽራ ካያችሁ
ፅዋ ተሸክመው እያሸበሸቡ ወይ እየዘመሩ የሚጓዙ ሴቶች
መንገድ ካገኛችሁ

#ስንት #ጊዜ #ሆናችሁ ?

በድፎ ዳቦና በሚሪንዳ ብቻ ልደቱን የሚያከብር ትንሽ ልጅ ካያችሁ
‹‹በሙሽራ ቀሚስ›› እየፈነደቀች ወዲህ ወዲያ የምትል ትንሽ ልጅ ካያችሁ
በሚያበራ ጫማ- ወይም በ‹‹ኦክስጅን ባግ›› ጓደኛ የሚያቀና ህፃን ልጅ ካያችሁ

#ስንት #ጊዜ #ሆናችሁ ?

በውይይት ታክሲ በረድፍ ተቀምጣችሁ ከተጓጓዛችሁ
ለአንዲት ነገር ብቻ መርካቶ ሸመታ ጎራ እንኳን ካላችሁ
አምስት ሳንቲምና ስሙኒ ካያችሁ
እሱ እንኳን ቢጠፋ የአንድ ብር ወረቀት ከኖረ በእጃችሁ

#ስንት #ጊዜ #ሆናችሁ ?

በናና የተፈላ ሻይ ፉት ካላችሁ
ሽልጦን ከወዳጅ ከተካፈላችሁ
አሹቅ አነባብሮን መክሰስ ካረጋችሁ
ቤት የተዘጋጀ- የሰነፍ ገብስ ቆሎ ዝግን ካረጋችሁ
ከጎረቤት ጋር ሰብሰብ ብላችሁ ቡና ከጠጣችሁ…

#ስንት #ጊዜ #ሆናችሁ ?

🔘በህይወት እምሽዉ🔘
👍4
#ሮዛ_2


#ክፍል_አስራ_አንድ(🔞)



#ሀያ_ዘጠነኛው_የሸዊት_ልደት_ለ3ኛ
#ጊዜ_ #ተከብሮ_ዋለ!

ሸዊት እድሜን እንደምትፈራው ፈጣሪን ብትፈራ መንግስተ ሰማያትን ትወርስ ነበር። ስለ ዕድሜ ሲነሳ ትበረግጋለች። ቴሌቪዥን የማታየውም አብዛኛዎቹ ዜናዎች እድሜዋን ስለሚያስታዉሷት
እንደሆነ ነግራኛለች። ለምሳሌ፡-
ባለፉት 20 ዓመታት ባስመዘገብነው ልማት…

ባለፈው 20 ዓመታት ባስመዘገብነው ልማት...

17 ዓመታት በፈጀ መራር ትግል የመጣውን ሰላምና ዲሞክራሲ..

የ5 ዓመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ…

ከ5 ዓመታት በኋላ የሚደረገው ይህ ምርጫ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ፍጹም ነጻ፣ሰላማዊና...

ቲቪውን ትዘጋዋለች።

የዛሬ ስድስት ወር መስታወት ፊት ቆማ ሊፒስቲክ እየተቀባች ነበር። በጆሮ ግንዷ ስር በኩል አንዲት
ቅንጣት ነጭ ጸጉር በመስታወት አየች። ልክ አይጥ እንዳየች ቀበጥ ቤቱን በጩኸት አናጋችው።

ሦስት ቀን ከአልጋዋ ሳትወጣ ዋለች። እኛ “ፔሬድ” ላይ ሆና መስሎን፤ አጅሪት ለካስ ሀዘን ላይ ናት። የምሯን።

እናንተ ለቅሶ ደረሳችኋት”

“ማንን?”

"ሸዊትን ነዋ"

"ውይ! ምን ነው? ምን ሆነች? ማን ሞተባት?"

"አንዲት ፀጉር"

"ምን?"

"አንዲት ፀጉር አልኩሽ እኮ!"

አንድ በአንድ ሄደን ለቅሶ ደረስናት። አንዲት ጸጉር ስለሞተችባ ት ጠብ እርግፍ ብለን አስተዛዘናት።
ለቀስተኛው ሁሉ መካሪ ሆነ። ግማሹ” ቀለም ተቀቢው” ሲላት፣ ግማሹ “አትነጪውም እንዴ፤ ምን
ታካብጃለሽ” ሲላት፣ ሌላዋ ተቀብላ ኤ.ኤ.ኤ…መንጨት አይታሰብም…ከነጨሽውማ ራሱን በሺ ያባዛልሻል” ስትላት፣ ነገሩ ያልተዋጠለት ደግሞ ሸዊት የሸሌ ቀበጥ ብሎ በሆዱ ሲሰድባት ብቻ
የምታደርገው ጠፍቷት ስትብሰለሰል ቤቷ ሰነበተች። እውነት ለመናገር ቤቷ ደምበኛ ለቅሶ ቤት ለመሆን ድንኳንና ንፍሮ ብቻ ነበር የጎደለው።

"ከለቅሶው” ስትነሳ ሁሉም ሰው ሸበቷን የሚያይባትና ስለሽበቷ የሚያወራ ስለመሰላት ሻሽ ማሰር ጀመረች።

አንቺ ሰለምሽ እንዴ? ምነው መጠምጠም አበዛሽ” የሚላት ሲበዛ ደግሞ ሻሽዋን አወለቀችው።
ስለእድሜዋ ማሰብ ማቆም ግን አቃታት።

እና ይህ በሆነ በስድስት ወሩ ዛሬ ሚያዚያ 18 ቀን የሸዊትን 29ኛ ዓመት ለ3ኛ ጊዜ እያከበርነው ነው።
“31 ዓመት ሞላኝ ማለት ፈርታ ነው በዚህ አቆጣጠር የቀጠለችው።

"ዶናልድ ዱርዬው"

ሲስ ራስታ እንዲህ አለ

እናንተ ስሙኝማ፡ የሸዊትን ታናሽ እህት መቼ ለታ አግኝቻት ስንት ነው ዕድሜሽ ስላት 28 አለችኝ፤
እንዴ አንቺ ሁልጊዜ 28 ነሽ እንዴ፣ የዛሬ ዓመትም ስጠይቅሽ 28 ብለሽኝ ነበር እኮ ስላት… ምን

ብትለኝ ጥሩ ነው። በየት በኩል ልለፍ፡ ሸዊት ከፊት ቆማብኝ ሃሃሃሃ....ሃሃሃ”

አዲስ ጆክ የህም? ይሄን ሰምተነዋል! ሌላ የለህም” አለችው ሸዊት። ሲስና ሸዊት ሁልጊዜም እንደተበሻሸቁ ነው የሚኖሩት። ደሞ ይዋደዳሉ። “ሲስተርሊ ብራዘርሊ” ይዋደዳሉ ። እሷ ግን ከዚያም
በላይ ነው የምትወደው ይባላል።

ልደቷን ለማከበር ሁላችንም “ሴቶች ቤት” ተሰብስበናል። የሚቅመው ይቅማል፣ የሚያጨሰው ያጨሳል፣ እኔና ሲስ ግን እንደተለመደው ከወደ ሺሻው ነን። ሪች ክልስ፣ ትምኒት፣ ትዝታ፣ ዉቢት
ከወንዶች ደግሞ ሲስ ራስታና ዶናልድ” የሚባል ዱርዬ ፈረንጅ ተገኝተዋል።

ዶናልድ የገባው የሰፈራችን ልጅ ነው። የሰፈር ልጅ ብቻም ሳይሆን ጓደኛችንም ነው። ብዙ ሰው ዶናልድ ዱርዬው እያልን ነው የሚጠራው። ይህ ስም የወጣለት ፈረንጅ ኾኖ ሳለ ነገር ግን ብዙ ጊዜው
ባልተለመደ ሁኔታ ከኛ ጋር እየቃመ ስለሚያሳልፍ ነው። ከኛ ጋር ካልሆነ ደግሞ ከጎዳና ተዳዳሪዎች ጋር ነው የሚያሳልፈው። ሁልጊዜም ነጠላ ጫማ ነው የሚያደርገው። አለባበሱ የፈረንጅ አይመስልም። አማርኛ ጽድት አድርጎ ይሰማል፣ መናገር ላይ ግን እስከዚህም ነው። ስሎቬኒያ ከምትባል አገር ነው
የመጣው።” ለ3ኛ ዲግሪ ማሟያ የማኅበረሰብ ጥናት እያካሄድኩ ነው ይላል። እኛ ግን ምንም ይስራ ምን ግድ አልነበረንም በጣም ስለቀረብነው ከሲስ ራስታ ለይተን አናየውም።

ገንዘብ ላይ ጠንቃቃ ስለሆነ ሸዊት ዶናልድ ጉራጌው እያለች ነው የምትጠራው። አንድ “ሾርት አዉጥቷት ቢዝነስ በሀበሻ ዋጋ ካልከፈልኩ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ ድርቅ ስላለባት ነው ዶናልድ ጉራጊው እያለች የምትጠራው። ብዙ ሰው እሱን ይበልጥ የሚያውቀው ግን ዶናልድ ዱርየው” በሚለው ስሙ ነው።

ፕሮግራማችን ሞቅ ሞቅ እያለ ሲሄድ የድሮ ጓደኛችን ሀና የቢሎስ ኬክ ይዛ ገባች። ሁላችንንም ሳመችንና ከዶናልድ ጎን በነበረው ፍራሽ ቁጭ አለች። ትንፋሽዋን ሰብስባ ስታስቃ፣ ስለሞቃት ጃኬቷን እያወለቀች - "ደግሞ ይሄን ነጫጭባ ከየት አግኝታችሁት ነው?” አለችን፤ ዶናልድ አማርኛ የማይሰማ
መስሏታል።

እዚህ መስቀል ፍላወር ፊትለፊት ካለው የቆሻሻ ገንዳ ወድቆ አግኝተነው ነው” አላት ሲስ ራስታ

ፈጠን ብሎ።

ዶናልድን ጨምሮ ሁላችንም ሳቅን፡፡

Nice meeting you! ሰሜ ዶናልድ ዱርዬ ነው እኔ፤ አንቺ ማን ኢባላል” አላት። ሃና ቅጽል ስሙም አማርኛውም ከጠበቀችው በላይ አስቋት ነው መሰለኝ ያን ረዥም ሳቋን ለቀቀችው።

ሳቋ ሲበርድላት እኔ ደግሞ ሃና ዱርዬ” እባላለሁ!” ብላ እየሳቀች ተዋወቀችው። ከዚያ በኋላ ማን ያላቃቸው። እኛን ሁሉ ረስተው አፍ ለአፍ ገጥመው ማውራት ጀመሩ። አያያዛቸው ያስፈራ ነበር።

ሲስ መደርደሪያው ጋ ሄዶ ቴፑን ይጎረጉራል። ለልደት በዓል የሚኾኑ ሙዚቃዎችን እየመራረጠ ነበር።
ድንገት ሲዲ ለማስገባት ቴፑን ሲነካካው በአጋጣሚ ኤፍ ኤም ላይ “የወባ ቀን በአገራችን ለ8ኛ ጊዜ ተከብሮ ዋለ” የሚል ዜና ሰምቶ በሳቅ መንፈራፈር ጀመረ። “ምን ሆንክ ስንለው?” የሬዲዮኑን ድምጽ ከፍ አድርጎ “ስሙማ፣ ስሙ በናታችሁ ይሄን ዜና” አለን። ምንም አዲስ ነገር አልሰማንም። እንዳጋጣሚ
ዜናው አልፎ ነበር መሰለኝ ተናደደ። የሰማውን ሲነግረን ግን አጋጣሚው እኛንም በጣም አሳቀን።

ሸዊት እንኳን ደስ አለሽ! የዘንድሮውን ልደትሽን ልዩ የሚያደርገው ከወባ ትንኞች ጋር በአገር አቀፍ
ደረጃ አብረሽ ማክበርሽ ነው…ሃሃሃ…ሃሃ” እንደተለመደው ሊያበሽቃት ሞከረ። የሲስ አሳሳቅ ሰውን ለማብሸቅ በትዕዛዝ የተሰራ ነው የሚመስለው። ሁላችንንም መተረብ ነው የትርፍ ጊዜ ሥራው።

"ሂ እዛ ሞዛዛ! ሲያስጠላ! በናትህ እስኪ አትሟዘዝ! ….ቢያንስ በዛሬው ቀን አከብረኝ እስኪ ፤ ልደቴ አይደል? አላሳዝንህም ሲስ” አለችው።

“ሸዊት ቆንጆ! ምን አልኩሽ እኔ፤ ሬዴዮኑ እኮ ነው ዛሬ የወባ ቀን በመላ አገሪቱ ተከብሮ ዋለ ያለው።
እኔ ነኝ?”

ፈገግታ መገበችው። ሸዊት ሲስ ራስታን ትወደዋለች። ለነገሩ ሲስን ማን የማይወደው አለ።

29 ቁጥር ያለበት ትልቅ ሻማ አምጥተን፣ ከሱ ስር ደግሞ ሦስት ትንንሽ ሻማዎችን ለኩሰን፣ ሃና ይዛው
የመጣቸውን የቢሎስ ኬክ ቆርሰን Happy birthday to you!” ብለን ዘመርንላት። ድንገት ሸዊት

እምባዋ መጣ! ሸዊት እንዲሁ ናት። አትችልም፤ በሆነ ባልሆነው እምባ ይቀድማታል።

ቴንኪው ሲስ! ቴንኪው ጓደኞቼ። ሁላችሁንም ዉድድድድ ነው የማረጋችሁ” ብላን ዱብ ዱብ እያሉ የነበሩ እንባዎቾን ጠረገች።እሷ ስታለቅስ ሁላችንም ሆዳችን እርብሽብሽ አለብን።

ቤቱ ለአፍታ በዝምታ ተዋጠ።

“አንቺ ገገማ! በልደትሽ ቀን ይለቀሳል?.የማትረቢ! " ብሎ ሲስ ተቆጣት። እንደዚያ ሲላት ደግሞ ባሰባት።
ከተቀመጠበት ተነስቶ ሄዶ አቀፋትና እምባዋን ጠረገላት።

እንደገና ቤቱ በዝምታ ተዋጠ።

"What is going on guys? Is that some kind of Ethiopian
👍72