አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ከሰፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///
የዝዋዩን ስብሰባ ተሳትፈው በተመለሱ በማግስት ዋና አቃቢ ህጉና አለም በቢሮቸው ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀምጠዋል፡፡

እሱ እጁ ላይ አንድ ደብዳቤ በትኩረት እየተመለከተ ትካዜ ውስጥ ገብቷል …

‹‹ክብሩ አቃቢ ህግ…ምነው ችግር አለ እንዴ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ወደስራ ስትመጪ ከተማው ውስጥ የታዘብሽው ነገር የለም?››

‹‹ምንን በተመለከተ…?››

‹‹የምታሳድጃቸውን ሰዎች በተመለከተ፡፡››
‹‹እ..የጁኒዬር ፍሰሀ ምስል የያዘ የምርጫ ቅስቀሳ ፖስተር ከተማውን ሞልቶታል፡፡ገዢውን ፓርቲ ወክሎ ለተወካዬች ምክር ቤት መወዳደሩ እርግጥ ሆኗል….ያንን ነው የታዘብኩት›››

‹‹አዎ…የዚህ ትርጉም ገብቶሻል ብዬ አስባለው….ጠላቶችሽ ከቀን ወደቀን የማይነኩ አይነት ኃያል እየሆኑ ነው፡፡››

"ምንም ሆነ ምንም …እኔ የጀመርኩትን ወደፊት ከመቀጠል አያስቆመኝም››
‹‹አይ የግድ ለማቆም ትገደጂያለሽ…..››

‹‹ለምን ተብሎ››

እጁ ላይ ያለውን ደብዳቤ ወረወረላት፤ግራ ከመጋባት ውስጥ ሳትወጣ ተቀበችውና አነበበች..ማመን ነው ያቃታት….ከመቀመጫዋ ተነሳች…ተወራጨች…

‹‹ምንድነው ይሄ…››

‹‹ታላቅ እድል ነው….እንደኦሮሚያ ይህንን እድል ካገኙ ሁለት የህግ ባለሞያዎች መከካል አንዷ አንቺ ነሽ…ቀጣዩን ስድስት ወር ቻይና ሄደሽ ይህንን ስልጠና ትወስጂያለሽ…ከዛ ስትመለሺ እርግጠኛ ነኝ….ወይ እዛው ክልል ዋናው ቢሮ ካለበለዚያም ሌላ ዞን በዋና አቃቢ ህግነት ትመደቢያለሽ››

‹‹እኔ መች ፈለኩና…?በምን መስፈርት ነው እኔ የተመረጥኩት….?››

‹‹እሱን እኔ አላውቅም..››

‹‹አወቅክም አላወቅክም ..ይህ እኔን ከእዚህ ገለል ለማድረግ የተሸረበ ሴራ ነው..ለስድስት ወር ከሀገር ወጣሁ ማለት… እስከዛ ጁኒዬር ምርጫውን አሸንፎ ምክርቤት ይገባል…ስመለስም ወደእዚህ ከተማ ስለማይልኩኝ የእናቴ ገዳይ ነፃ እንደሆነ ይቀጥላል ማለት ነው…ይህን መቀበል አልችልም፡፡››

‹‹መቀበልማ የግድ ነው….በዚህ ስራ ላይ ለመቆየት ያለሽ እድል ከ15ቀን አይበልጥም……እሱም ምን አልባት ነው፡፡ደብዳቤውን አንብበሻል አይደል?ይሄ ደብዳቤ ከደረሰት ቀን አንስቶ እጇት ላይ ያለውን ስራና የመንግስት ንብረት ለተተኪው ሰው አስረክበው ለጉዞው ይዘጋጁ ነው የሚለው፡፡››

በንዴት ተንዘረዘረች‹‹አየህ የሰዎቹን ተንኮል….ይህንን ያቀናጁት አቶ ፍሰሀ እና ገመዶ እናም ዳኛው እንደሆኑ እርግጠኛ ነኝ…በዘዴ እኔን ለማስወገድ የሄዱበትን ርቀት የማይታመን ነው››

‹‹አይ የእነሱ እጅ የለበትም ብዬ ልከራከርሽ አልፈልግም….እንደውም ሁኔታውን በደንብ አንድትረጂ ነው የምፈልገው…የሰዎች አቅምና ኃይል ክልል እና ፌዴራል ድረስ ምን ያህል የተዘረጋ እና ስር የሰደደ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው፡፡አንቺ በማትጎጂበት መንገድ ከጀመርሽው መንገድ ዞር ለማድረግ የቀየሱት ጥበብ የተሞላበት ዘዴ ነው፡፡ያ ማለት እኔ እፈራው እንደነበር ቀጥታ አንቺ ላይ ምንም አይነት አካላዊ ጉዳት ሊያደርሱብሽ ፍላጎቱም ሆነ እቅዱ የላቸውም ማለት ነው….ይሄንን በማወቄ አፎይታ ተሰምቶኛል፡፡››

"አንተም እንድሄድ ነው የምትፈልገው?"

"አዎ፣ ሳስበው ለአንቺም የሚበጅሽ እንደዛ ማድረጉ ነው።" በለሆሳስ መለሰላት፡፡
ዋና አቃቢ ህጉ ለእሷ ከአለቃ ይልቅ እንደ ጓደኛ ነው። ስለዚህ እሷ ደህነንት ያሳስበዋል፡፡ " እንደምንም አንድ ወር በስራዬ ላይ እንድቆይ አድርግ"ተማፀነችው፡፡

" እንደዛማድረግ አልችልም.. አልፈልግም."
‹‹እባክህ››

"አንድ ሳምንት አለሽ…ልክ የዛሬ ሳምንት የቢሮሽን ቁልፍ አስረክበሽ ወደ አዲስ አበባሽ ጉዞ ትጀምሪያለሽ።"

" አታስበው…የመጣሁበትን ከግብ ሳላደርስ ከዚህች ከተማ ንቅንቅ አልልም››

‹‹እንዳዛ ከሆነ ስራሽን ታጪያለሽ››

‹‹ስራውን በስራነቱ እንደማልፈልገው ታውቃለህ….የእናቴን ገዳይ እንዳገኝ ካረዳኝ ስራው ምን ያደርግልኛል?››

‹‹የውጭ እድሉም ይቃጥልብሻል››

‹‹አልፈልገውም …ለሌላ ሰው ስጡት፡፡››

‹‹ይሄንን ስራ ከለቀቅሽ…በራስሽ ብቻሽን ነው የምትቆሚው…የቢሮው እገዛና ጥበቃ አይኖርሽም::እንደአንድ ተራ ግለሰብ እነሱን መጋፈጥ እትችይም….››

‹‹ያንን ስሞክር ነው የማውቀው››

"በእግዚያብሄር ስም …ምን አይነት ግትር ሴት ነሽ?"

‹‹ይህ ግትርነት አይደለም…እዚ ከተማ ስመጣ አሁን እናቴን ገድለዋት ይሆናሉ ብዬ የምጠረጥራቸው ሶስት ሰዎች ነበሩ ..ወደዚህ መጥቼ ምርመራዬን ከጀመርኩ በኃላ ተጠርጣሪዎች ወደአምስት አድገዋል፡፡››

‹‹ጭራሽ ተጠርጣሪዎችሽን ቁጥር እያጠበብሽ መሄድ ሲገባሽ እያንዛዛሽው መጣሽ ማለት ነው…ለመሆኑ እነማን ናቸው የተካተቱበት?››

‹‹የአቶ ፍሰሀ ባለቤት ሳራ እና የጁኒዬር የቀድሞ ባለቤት ስርጉት››

ሲጋራውን ከፓኮው አወጣና ለኮሰ ፣ አንዴ ማገና ጭሱን በአየሩ ላይ በተነው ‹‹እንሱ ደግሞ ለምን ብለው ነው እናትሽን የሚገድሏት?››ሲል ከመገረም ውስጥ ሳይወጣ ጠየቃት፡፡

እንደውም ከወንዶቹ በተሻለ እናቴን ለመግደል በቂ ምክንያት እና ጥላቻ ያላቸው ሴቶቹ ናቸው፡፡ወ.ሮ ሳራ ልጇ ጁኒዬር እናቴን እዳያገባ ስትጥር ነበር ቆየችው....በዚህ ጉዳይ ከአያቴ ጋር ሁሉ እንተጨቃጨቁ በገዛ አንደበቷ ነው የነገረቺኝ፡፡በእሷ እምነት እናቴ በሁሉም መስፈርት ለአንድዬና ብቸኛ ልጇ ሚስት ለመሆን እንደማትመጥን ነው የምታስበው፡፡እና ልጇም ተመሳሳዪን እንዲያስብ ብዙ ጊዜ ሞክራ እንዳልተሳካላት ነግራኛለች..ይታይህ ታዲያ ድንገት እኔን ወልዳ አራስ የሆነችውን እናቴን ሊያገባ እየተዘጋጀ ነው ብለው ሲነግሯት እሷን አስወግዳ ልጇን ነፃ ለማውጣት ብትሞክር ምን ይገርማል…?በሌላ በኩል የዳኛው ልጅ የሆነችው ስርጉት ደግሞ ጁኒዬርን ለአመታት ስታፈቅረው እና የራሷ እንዲሆን ስትመኘው የነበረ ሰው ነው….እሱን የራሷ እንዳታደርገው እንቅፋት የሆነቻት እናቴ ነች..ይባስ ብሎ ከአንድ ዲቃላ ልጇ ጋር ሊያገባት እንደሆነ ስትሰማ ምንድነው የሚሰማት….?ደግሞ እናቴን እንዴት አምርራ ትጠላት እንደነበረና መሞቷን እንደግልግል እንደወሰደችው እዛ ድግስ ላይ
የተገናኘን ቀን ምንም ሳትደብቅ ነግራኛለች፡፡እና በአጠቃላይ ከእናቴ ሞት ይበልጥ ተጠቃሚ የሆነው ማን ነው? ብለን ሰንጠይቅ ለጊዜው ሁለቱ ሴቶች የሚል መልስ ነው ምናገኘው…ሳራም ልጇ የማትፈልጋትን ሴት ከማግባት ተገላገለ..ስርጉትም እናቴ ሞታ ብዙም ሳይቆይ ለአመታት ስታፈቅረው የነበረውን ሰው አሳምና ማግባት ቻለች….ምንም እንኳን ጋብቻው ረጅም እድሜ መቆየት ባይችልም ለጊዜው ግን ተጠቃሚ ነበረች፡፡››
በጥሞና ሲያዳምጣት የቆየው አቃቢ ህግ ጭንቅላቱን እየነቀነቀ‹‹ጥሩ መላ ምት ነው››አላት
፡፡
"በዚህ ጉዳይ እኔን የገረመኝን አንድ ነገር ታውቃለህ? ዳኛው። የእናቴን ግድያ በተመለከተ ተጠርጣሪዎች በጠቅላላ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ከእሱ ጋር ትስስር ያላቸው ናቸው..ታዲያ እንዴት አድርጎ ነው ትክክለኛውን ፍርድ ሊፈርድ የሚችለው?።"

በማግስቱ የአለም የመጀመሪ ስራ የዋና አቃቢ ህጉን ቢሮ ማንኳኳት ነበር፡፡ ባልተሟሸ የጥዋት ሻካራ ድምፅ፡፡‹‹ይግቡ››አላት፡፡
በራፉን ገፋ አድርጋ ገባች

‹‹የመጀመሪያ ባለጉዳይ አንቺ ትሆኜያለሽ ብዬ አልጠበቅኩም ነበር››
ለቀልዱ ምንም መልስ ለመስጠት ፍላጎት አልነበራትም…ጠረጴዛውን ተጠጋች እና ከቦርሰዋ ውስጥ አንድ ወረቀት አውጥታ ፊቱ አስቀመጠችለት፡፡ጠቅላላ አቃቢ ህጉ በሁኔታዋ ግራ ተጋብቶ‹‹ምንድነው?›› ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ስራ መልቀቂያ ነው››

‹‹ማለት ?አልገባኝም››
44👍6👎1👏1