አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
566 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮዛ_2


#ክፍል_ስድስት(🔞)


#ከዶር_ቃልአብ_ጋር_ያደረግነው_ነገር

ዶ/ር ቃልዓብ የሐረር ሰው ነው።
መሆንም አለበት። ዶክተርነት እንደሱ ከሆነ ብቻ ይምጣብኝ
ምከንቱም በጣም ነጻ ሰው ነው። ዶክተርነቱ የሰጠው አንድ ነገር ቢኖር እንደብዙዎቹ መቆለልን ሳይሆን ነጻነትን ነው። ወላ እሱ ዶክተር ሊሉት እንኳን አይደላውም አቦ። እኔ የማውቃቸው ዶክተሮች(የበዳኝም፣ ግቢ ያስተማሩኝንም ጨምሮ ማለቴ ነው) ዶክተር ካልተባሉ ለጸብ የሚጋበዙ ናቸው።ጓደኛዬ የነበረችው ሰሚራ Introduction to Macroeconocmics"C" "ያመጣችው አስተማሪዋን በስሙ ስለጠራቸው ነው። ወዲያውኑ ነበር « ዋጋሽን ታገኚያታለሽ!» ብሎ የዛተባት። እንደዛተ።አደረገው። ዶክተር ብላ ስላልጠራቸው ብቻ። ዶክተር መሆን ከንደዚህ አይነት ጠባብነት ካላወጣ
ባፍንጫዬ ይውጣ!

ዶክተር ቃለአብ ከትምህርት ሚኒስቴር ወደላይ በሚገኙ ኪሎ ዩኒቨርስቲዎች በአንዱ የሚያስተምር
የተጨበጨበለት ፕሮፌሰር ዶክተር ነው። የቺቼንያ ሕይወት ላይ Research በሚሰራበት ወቅት የተዋወቅነው። ለሁላችንም በረዳቶቹ በኩል እንድንሞላው በሰጠን Questionaire ላይ የጻፍኩት ነገር ማመን ከብዶት በባትሪ ፈልጎ አፈላልጎ ተዋወቀኝ። መጀመርያ አካባቢ ዶክተር እያልኩ
የምጠራው። እሱ ግን ከመቼው ተግባብቶኝ እንደዚያ እንዳልጠራው እንዳደረገኝ ሳስበው ይገርመኛ።
« አቦ እናሸንና!» ሁለተኛ አንቱ ብለሽ እንዳትጠሪኝ ብሎ በአንድ ጊዜ በመሐላችን የነበረውን ግንብ
አፈረሰው።

«ኸረ ዶክተር ካንተ አይጠበቅም አልኩት እየሳቅኩ።

Shut up bitch! I am here looking for my freedom!” አለኝ።

አልከፋኝም፤ ምክንያቱም ዶክተር ያራዳ ልጅ ነው በዚያ ላይ ከእግዚያአብሔርም ጋ ጀለስ ሳይሆኑ አይቀርም። ለምን ቢባል ከሱ ጋር አስር ደቂቃ ያወራ ማንኛውም ሰው ወዲያውኑ በፍቅሩ ይነደፋልና
ነው። እንደዚህ አይነት ሰዎች ለፈጣሪ የቀረቡ ሳይሆኑ አይቀሩም ሰዎች ራሱ ዶክተር» ብለው ሲጠሩት ብሽቅ ነው የሚለው። አንድ ቀን ብላክ አስወርደን እየጠጣን (ጋባዥ እኔ ነበርኩ) ሞቅ ብሎን ሳለ ለምን ዶክተር ሲሉት እንደሚናደድ ጠየቅኩት።

«ተይ እንጂ ሮዝ! ማንም ሩዝ ነጋዴና አዝማሪ በሚጠራበት ስም ስጠራ እንዴት አይከፋኝም?!»ብሎ ቀለደ።

በሳቅ ልሞት!

ምክንያቱም ያን ሰሞን አንዳንድ ዩኒቨርስቲዎች ለሀብታሙም ለነጋዴዉም፣ለዘፋኙም፣ ለጎሳ
መሪውም የክብር ዶክትሬት ያደሉበት ወቅት ነበር። እና አሽሙሯ በደንብ ገብታኛለች። እውነተኛ ምክንያቱ ግን ያ እንዳልሆነ አውቃለሁ።

ብዙ ጊዜ ስናወራ በዚህ ትውልድ ደስተኛ እንዳልሆነ ለመረዳት ችያለሁ።

“በኛ ዘመን ትምህርት ዋጋ ነበራት፤ እንደናንተ ሸርሙጣ አልሆነችም ነበር፤ ገብቶሻል የምልሽ?
ለምሳሌ በጃ ጊዜ እውቀት ሸቀጥ አልሆነችም ነበር። ብር ስላለሽ ወይም ትዝታ ስላንጎራጎርሽ ማንም
አንስቶ ዶክትሬት አይሰጥሽም፤ በፍጹም። ብቸኛው መንገድ ጠንክሮ መማር ነበር። አሁን ሲ ኤም ሲ ነው ጉርድ ሾላ ለካድሬዎች የተከፈተ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አለ፣ ስሙ ጠፋኝ።
እና ይሄን ዶክትሬት ዲግሪ እንደ ጉድ ለተማሪዎቹ እያደለው ነው»አሉ፤ አንቺም ሳያልቅብሽ ይቺን ብላክሽን ቋ አርጊና ሄደሽ ብትጠይቂያቸው ይሰጡሻል! ሙች እውነቴን ነው!”

ከዚያ ቀን በኋላ ዶክ እያልኩ እጠራው ጀመር።

ዶክ ጓደኛዬ እንጂ ደምበኛዬ የምለው ሰው አይደለም፡፡ ብንባልግም በስንት ጊዜ አንዴ ነው የሆኑ ጊዜያት አሉት፣ ከኔ ጋር ማደር የሚፈልግባቸው ጥብቅ ጊዝያት። ከዚያ ዉጭ ግን ጓደኛሞች ነን
ህይወቱ ላይ የሆነ ያልሻረ ቁስል ያለበት ይመስላል። ግን እሱ ሁሌ ጫወታና ሳቅ ዉስጥ ስለሚዋኝ ከኔ ሌላ ይህን ስሜቱን የሚረዳ ላይኖር ይችላል።

"ዶክ ግን ምንድነው ስታየኝ የርቀት ተማሪ»እመስላለሁ እንዴ?” እልኩት ደሳለኝ ሆቴል በሱዙኪው ይዞኝ እየሄደ።

«እንዴት ማለት?» አለኝ ፊቱን ፊትለፊቱ ባለው ጎዳና ላይ ተክሎ

« የርቀት ትምህርት Exam ይመስል በሴሚስተር አንዴ እየመጣህ ስጪኝ ትለኛለሃ! አይደብርህም እንዴ ጠፍተሃል እኮ?

ያን ምሸት የሳቀው ሳቅ! ትራፊክ ቢያየው “ትርፍ በመሳቅ” ብሎ ይቀጣው ነበር።

“You know what?I wish ሚስቴን ይህን ቀልድሽን በሆነ መልኩ በነገርኳት። በጣም sense of humour ያላት ናት። በዚህ ዓለም ከኔ ሌላ እንደ ጆክ የምትወደው ነገር የላትም፤ ነግሬሼላሁ አይደል?

“ኸረ ዶክ! እንዲያውም ስለ ሚስትህ ትንፍሽ ብለህ አታውቅም?”

“እውነትሽን ነው? How come? ይገርምሻል! ተማሪዎቼ ደግሞ ምን እንደሚሉኝ ታውቂያለሽ?
«ስላንተ ሚስት መስማት ሰለቸን፤ add ያደረግናት ኮርስ ሆነችብን እኮ» ነው የሚሉኝ።

ሳቅኩኝ።

እንዲያውም አስተዋውቃችኃለሁ!

“ኸረ ባክ.ህ?! ተባለንዴ…" የሹፈት ሳቅ ሳቅኩኝ።

እሱ ለካ እያሾፈ አልነረም።

No no! She is not like that! እንዲያውም በተቃራኒው She is open and funny, I am sure you two like each other more than we do! ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም። of course ስለ ግንኙነታችን
ልታውቅ የምትችልበት ምንም መንገድ አይኖርም፡፡ ደሞ we are friends nothing else! አይደለም እንዴ ሮዝ? የቀድሞ ተማሪዬ እንደነበርሽ ቀለል አድርጌ እነግራታለሁ። that is it! I hope አሪፍ ታይም እናሳልፋለን
How about lunch? The coming Sunday. Are you free or what?"

“ዶክ አብደኻል እንዴ? ምንድነው የምትቀባጥረው?”

በሳምንቱ ዕሁድ አንጦልጡሎ ሱዙኪው ውስጥ ከተተኝ። ግሎባል ጀርባ አካባቢ ወደሚገኝ ባለ ሦስት ፎቅ ጸጥ ያለ መኖርያ ቤቱ ይዞኝ ሄደ። መርበትበት ማቆም አልቻልኩም። ላቤ ሲንቆረቆር ይሰማኛል።ብርድ ብርድ ሲለኝ መዳፎቼን ጭኖቼ ውስጥ ወሸቅኳቸው። አንድ ወንድ እንዴት አንዲት የሴክስ
ደምበኛውን ከሚስቱ ጋር ለማስተዋወቅ ይደፍራል? ከዚህ በላይ ምን እብደት ይኖራል? በዚህ ጠራራ ጸሐይ ብርድ ብርድ እያለኝ እንደሆነ ሲገባኝ የፍርሃቴ ጥልቀት ተገለጸልኝ።

“ i really hate you Doc! የእብድ ስራ ለምን ታሰራኛለህ! ማበድ ከፈለክ ብቻህን አታብድም እንዴ!?”

“የኔ ቆንጆ! ምንም ነገር የምትፈሪ አይመስለኝም ነበርኮ! ሃሃሃ! ለካንስ ሸሌዎችም ትፈራላችሁ! ይሄ
በሶሲዮሎጂ መጠናት ያለበት ጉዳይ ነው። ሮዚ! You are such a chicken ! Relax! ምንድነው እንዲህ
መፍራት። you will be fine! ደግሞ ምናባሽ ሆነሽ ነው እንደዚህ እምስ እስክትመስይ ድረስ ቆንጆ ስከርት የለበስሽው፣ ሚስቴን በቅናት ለመግደል እያሴርሽ መሆን አለበት…ሃሃ

እንደሱ ሲለኝ የለበስኳትን ሚኒ ቀሚስ ለመጀመርያ ጊዜ ጎንበስ ብዬ አየኋት፤ ደንግጬ ወደታች መጎተት ጀመርኩ። እውነትም ተራቁቻለሁ፤ ምን ነክቶኝ ነው እንደዚህ ለብሼ የወጣሁት? መኪናው
ውስጥ ስቀመጥ ነው የታወቀኝ። ሚኒ ቀሚሴ ተሰብስቦ ራቁቴን ቀርቻለሁ። ዶክ ሲያጣድፈኝ ምን ላድርግ፣ አጠገቤ ያገኘሁትን ነው የለበስኩት፤ ምናለ ከመነሳታችን በፊት ነግሮኝ በሆነና አለባበሴን በቀየርኩ!

ወደ ግሎባል ሆቴል ጫፍ ስንደርስ ለምን እንደሆነ አላውቅም ዶክ ላይ የሆነ ከወትሮው ቅንዝርነት አስተዋልኩ፤ እንደዚህ በፍላጎት ሲያየኝ ከዚህ በፊት አይቼው አላውቅም ነበር።

ግቢው ሲያምር! አበባ ሞልቶታል፤ ኤምባሲ ነው የሚመስለው። ጋራዥ ውስጥ ጭርጭስ ያለች አንደሸ
የድሮ ቮልስዋገን መኪና ቆማለች
👍8