#ጸዲ
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
ሰው ሁሉ፣ “ጸዲና ሙሌማ ይጋባሉ፡፡ ተጋብተው አራት ልጅ ይወልዳሉ፡፡ አብረው ያረጃሉ፡፡ ተለያይተው መኖር ስለማይችሉ አንዳቸው ከሞቱ፣ በነጋታው ሌላኛቸው ይከተላሉ፡፡” የምንባል
ዓይነት ነበርን፡፡ እኔና ጸዲ ይኸው ከተለያየን ሁለት ወራት ሞላን፡፡
መጀመሪያ መለያየታችንን መቀበል እምቢ አልኩ፡፡ (ለመንኳት፡፡አስለመንኳት፡፡ አስገዘትኳት፡፡ አብረን በነበርን ጊዜ ቅር የሚላትን፣የሚያበሳጫትን ሁሉ ተውኩ፡፡ የሚያስደስታትን ሁሉ አደረግኩ፡፡
እንደ... በሌሊት ተነስቼ ሥራዋ ድረስ መሸኘት፡፡ ቅዳሜ ቅዳሜ
ጓደኞቼን ትቼ ከእሷ ጋር ስንዘላዘል መዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን
ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ማንበብ፡፡ መጸሐፍ ቅዱስን
በየቦታው መጥቀስ፡፡ በየቀኑ ማስቀደስ፡ የማትወዳቸው ሰዎች
እንዳይደውሉልኝ ስልክ ቁጥሬን መቀየር፡፡ የስልኬን ፓስወርድ መስጠት፡፡ የፌስቡክ ፓስወርዴን የእሷን ስምና ስልክ ማድረግ፡፡
መጠጣት ማቆም፡፡ ማጨስ ማቆም፡፡ መቃም ማቆም፡፡ ከእሷ ጋር
ባልተገናኘ ሁኔታ ደስ የሚለኝን ሁሉ መተው፡፡ በአጠቃላይ በእሷ
ብቻ መደሰት፡፡ በእሷ ፈቃድ ብቻ መላወስ፡፡ በእሷ ቀልድ ብቻ
መሣቅ፡፡ በእሷ ዛቢያ ብቻ መሽከርከር፡፡)
ግን አልሆነም፡፡
ጥላኝ ሄደች፡፡
ከዚያ ደግሞ አያዝኑ አስተዛዘን አዘንኩ፡፡
(ቢጃማ አድርጎ ለቀናት ከቤት ያለመውጣት ዓይነት ሐዘን፡ መጠጥ
ውስጥ የመደበቅ ሐዘን፤ በመጠጥ ብዛት ተገፍቶ በወጣ እንባ የመነፋረቅ ሐዘን፡፡ ለእሷ ብዬ የተውኳቸውን ሱሶች ውስጥ ዳግም የመዘፈቅ ሐዘን፡፡ ሰውን ሁሉ የመጥላት ሐዘን፡፡ የምግብ ፍላጎትን
የገደለ ሐዘን፡፡)
ከተለያዩ ይሞታሉ ቢሉንም፣ ይሄው ሁለታችንም አልሞትንም፡፡
አሁን ደግሞ፣ ከዚያ ሁሉ ልመናና ምልጃ በኋላ፣ ከዚያ ሁሉ መሰባበርና መበጣጠስ በኋላ.... እዚህ ጥላው የሄደችው ቤት ውስጥ
ብቻዬን ቁጭ ብዬ ደህና ደህና ነገሯን ሳይሆን ውስጥ ውስጡን
ያስጠሉኝ ስለነበሩ ነገሮቿ አስባለሁ፡፡
ጓደኛዬ ክብሮም ያዘዘልኝ መድኀኒት ነው፡፡
ክብሮም ስለመለያየት ብዙ ያውቃል፡፡ ብዙዎቹ ገርልፍሬንዶቹ
አንድም ልደት አብረውት አክብረው አያውቁም፡፡ እንቁጣጣሽ ላይ
ጀምረው የጥቅምት እሽት ሳይበላ ይቀየራሉ፡፡ ለቅበላ ተዋውቀው
ሁዳዴ ጦም መሀል ይለያያሉ፡፡ ስለዚህ የወደዳትን የመራቅ፣
የመለየት ጥበብን ቀቅሎ በልቶታልና መከረኝ፡፡
....
ምን ብሎ መከረኝ?
“የጓደኝነቴን ልምከርህ፡፡ አትደውልላት፡፡ አታስባት፡፡ ብታስባት
እንኳን አብራችሁ እያላችሁ ያስጠሉህ የነበሩትን ነገሮች ብቻ
አስብ፡፡ መጥፎ መጥፎውን ብቻ... ገባህ? ለምሳሌ፣ ምኗ ይደብርህ
ነበር? ምኗ ያስጠላህ ነበር? ባትነግራትም ምኗ ያናድድህ ነበር...?”
እያለ ፀዲን ከፊተኛው ሕይወቴ የማባረርበትን ጥበብ አቀበለኝ፡፡
ስለዚህ አሁን እዚህ ቁጭ ብዬ አብረን ባለን ጊዜ ቅር፣ ሲዘልም
ቅፍፍ ይሉኝ የነበሩ ባህሪዎቿን፣ ሁኔታዎቿን፣ ግሳንግስ ጓዞቿን፣
ማሰብ ጀምሬያለሁ፡፡
....አለ አይደል... እንደዛ የቺቺኒያ ሴት አዳሪ የሚያስመስላት ክምር
አስጠሊታ ሂውማን ሄሯ:: ምግብ ስታላምጥ በነጠላ ጫማ የምትሮጥ እስከሚመስል ጧ ጧ እያደረገች የምታስጮኸው ነገር፡፡ ታይት ስትለብስ ሦስተኛ እግር ሊያስገባ የሚችል ክፍተት
የሚተዉት ቀጫጫ ብራኬት እግሮቿ፡፡ ምላሷ ላይ ያሉት መዐት ጥቁር ጠቃጠቆዎች፡፡
(ክብሮም እውነቱን ነው.... ይሄ ነገር ሳይሠራ አይቀርም
...
እንደ... ሸራተን በወሰድኳት ቁጥር ብርቅ እየሰራባት የሚያስጠጣኝ፣ የሚያሳፍረኝ ገጠሬነቷ፡፡ ነዝናዛ እናቷ፡፡ ቆንጆ ግን
ነገረኛ እህቷ፡፡ አንድም ቀን ጥሞኝ የማያውቅ ሽሮዋ፡፡ ሆዳም
ጓደኞቿ፡፡ እንግሊዝኛ አለመቻሏ፡፡እንግሊዘኛ ባለሠቻሏ ፊልም
ባየን ቁጥር፣ ምን አላት...? ምን አለው...? ምንድን ናቸው...?
ምኗ ነው? እያለች መጨቅጨቋ፡፡
(ክብሮም ጥሩ ጓደኛዬ ነው፡፡ መድኀኒቱም ፍቱን ነው፡፡)
ከዲፕሎማ ያልዘለለው የትምህርት ደረጃዋ፡፡ ምን ብር ብታፈስበት፣
ሰው ፊት የሚያስቀርብ ልብስ መርጣ መግዛት አለመቻሏ፡፡ ስስማት
የምታሰማው ደስ የማይል እህ.....፣ ፍቅር ስንሠራ እስቲ ከላይ ሁኚ ስላት፣ “ሂድዛ... ሴተኛ አዳሪ አረግከኝ እንዴ...!” የምትለው ፋራነቷ፡፡ አታጭስ ማለቷ፡፡ አትጠጣ ማለቷ፡፡ አትቃም ማለቷ፡፡
በመሸ ቁጥር ስልኬን መበርበሯ፡፡ የሴት ጓደኛ እንዳይኖረኝ በስልት
መከልከሏ፡፡ (ምን ሆኜ ነበር እወዳት የነበረው?)
ለእነዚያ የማያልፍላቸው አመዳም ቤተሰቦቿ፣ ገንዘቤን ሳታባራ
መበተኗ፡፡ ሚጢጢ ደሞዟ ለቀጫጫ እግሯ ከሚሆን ሉሽን በላይ
ምንም ነገር መግዛት አለመቻሏ፡፡ ለመዝናናት ከገዳም ውጪ አለመምረጧ
ደህና ሬስቶራንት ስወስዳት፣በሹካና በቢላ
እንደመብላት ስቴክ እንደ ዐጥንት አንስታ መጋጧ፡፡ ስልክ ሲደወልላት በሄሎ” ፋንታ “ሃሉ” ማለቷ፡፡
(ክብሮም አስማተኛ ነው፡፡ በአንድ ጊዜ ከደም ሥሬ የወጣች፣ ከቤቴ
የተነነች፣ ከሕይወቴ የጠፋች... ላትመለስ የተባረረች መሰለኝ...)
በደስታ እየተንተንተከተከ ለክብሮም ደወዬ ቢራ ካልጋበዝኩህ ሞቼ እገኛለው አልኩት።እየፈነደቀ እሺ አለኝ።
ተነሳሁና ልብስ ልቀይር ወደ ቁምሳጥኑ ሄድኩ።
ከፈትኩት፡፡ ከትርምሱ መሀል ጸዲ ከዕድሜህ ጋር አይሄድም
አትልበሰው ብላ ከልክላኝ የተውኩትን መበታተን የጀመረ ጂንስ ሱሪ
ጎርጉሬ ሳወጣ የረሳችውን ልብሷን አገኘሁት፡፡
ነጭ ረጅም ብዙ ቀያይ አበቦች የፈሰሱበት ቀሚሷ፡፡ ታይላንድ ስሄድ
ምን ላምጣልሽ ስላት ለቤተክርስትያን የሚሆን ረጅም ቀሚስ ብላኝ
ያመጣሁላት ቀሚሷ፡፡ ቤተክርስትያን ስትሄድ የምታዘወትረው ቀሚሷ፡፡ ከቤተክርስትያን መልስ ቡና ስታፈላልኝ የምትለብሰው
ቀሚሷ፡፡ ይሄን ቀሚስ ለብሳ፣ ቤቱን በዚያ ውብ ሣቋና ግሩም ቡናዋ
የምታደምቀው ነገር ትዝ አለኝ፡፡
ይሄን ቀሚስ ለብሳ፣ የማይጣፍጥ ሽሮዋን ካልበላህ ብላ ፊቴን
በፍቅር እየዳበሰች፣ ዐይኖቼን እየሳመች የምታባብለኝ ውል አለኝ፡፡
ይሄን ቀሚስ ለብሳ ውላ፣ ማታ ልንተኛ ስል፣ ራሷ መክፈት እየቻለች፣ ና ዚፑን ክፈትልኝ ብላ ለአልጋ ላይ ድግስ ሰበብ
የምትፈጥረው ነገር ትውስ አለኝ፡፡
ረስታው ነው? እጆቼ ያለፈቃዴ አነሱት፡፡
አሽተትኩት፡፡
ጸዲ ጸዲን ይላል፡፡
ደግሜ አሽተትኩት፡፡
ሳልሰርግ ያገባኋትን፣ ሳልፈልግ ያጣኋትን የዋኋን ፀዲን፣ ፍቅሬን ፍቅሬን ይላል፡፡
ቀሚሱን እንደያዝኩ፣ ቁምሳጥኑ አጠገብ ቆሜ እንደ ሕፃን ንፍርቅ
ብዬ አለቀስኩ፡፡
ጸዲ... አንቺ ጸዲ...!
💫አለቀ💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን። 🙏

👍2