አትሮኖስ
280K subscribers
109 photos
3 videos
41 files
460 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሁቱትሲ


#ምዕራፍ_አስራ_ሦስት


#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች

#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ


#ከዳማሲን_የተላከ_ደብዳቤ


ከትምህርት ቤቱ በስተጀርባ ብቻዬን ሆኜ የዳማሲንን ደብዳቤ ከፈትኩት፡፡ ለማንበብ የሚያስቸግረውን የእጅ ጽሑፉን እንዳየሁ በትምህርት ቤት እንዳለን የጻፈልኝን ደብዳ ቤዎች ሁሉ አስታውሼ ልቤ ታመመ፡፡ ፈጽሞ ግልጽ ስሜት የማይንጸባረቅባቸው፣ ግን ሁሌ በፍቅርና በደግነት፣ በማበረታቻና አድናቆት፣ በግሩም ምክርና ረጋ ያለ ተግሳጽ፣ ስለ ወዳጆቻችን በሚያወሱ ወሬዎችና በብዙ ቀልዶች የተሞሉ ደብዳቤዎቹ ትውስ አሉኝ፡፡ ጀርባዬን በትምህርት ቤቱ ክፍል ግድግዳ ላይ አስደግፌ ተቀምጬ አነብ ጀመር፡፡
ግንቦት 6፣ 1994
ውድ (አባባ፣ እማማ፣ ቪያኒ እና) ኢማኪዩሌ ሁላችንም ከተለያየን አንድ ወር ገደማ ሆነን፡፡ ይሄው የቅዠት ኑሮ እየኖርን ነው፡፡ ሁናቴዎች ከሚያሳዩት ነገር ባሻገር አንድ ዘውግ ሌላውን ፈጽሞ የሚያጠፋው የእግዚአብሔር ፍቃድ ሲሆን ብቻ ይሆናል ብዬ አምናለሁ፡፡ ምናልባት የእኛ ሕይወት ለሩዋንዳ ድኅነት እንዲከፈል ግድ ብሎ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለ አንድ ነገር እርግጠኛ ነኝ - እንደገና እንደምንገናኝ በአእምሮዬ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ የለም፡፡
ከሀገሪቱ ለመውጣት ልሞክር ነው፣ ግን ይሳካልኝ አይሳካልኝ አላውቅም፡፡ በመንገድ ላይ ከገደሉኝ ስለ እኔ አትጨነቁ፤ በሚገባ ጸልያለሁ . . . ለሞትም ተዘጋጅቻለሁ፡፡ ከሩዋንዳ መውጣት ከቻልኩ ሰላም እንደተመለሰ ወዲያውኑ ሁላችሁንም አገኛችኋለሁ፡፡ የደረሰብኝን ሁሉ ቦን
ይነግራችኋል፡፡
የዳማሲን ጓደኛ ቦን በሌላ ጊዜ እንደነገረኝ ወንድሜ ደብዳቤውን እየጻፈ ሳለ እዚህ ሐሳብ ላይ ሲደርስ ዳማሲን ብዕሩን ቁጭ አድርጎ ቀና ብሎ እያየው ‹‹ቦን፣ ወዳጄ እንደሆንክ አውቃለሁ፤ ስሜቴም ሳይጎዳ እንዲቆይ ሞክረሃል፣ አሁን ልትነግረኝ የሚገባህ ሰዓት ላይ ነን - ከቤተሰቤ አባላት የተገደለ አለ እንዴ?›› ቦን ሁቱ ስለሆነ በዘር ጭፍጨፋው ወቅት በነጻነት ይጓጓዝና በአካባቢው ከቱትሲዎች ማንኛቸው እንደተገደሉ ያውቃል፡፡ የወላጆቼንና የቪያኒን ሞት ለራሱ በምስጢር የያዘው ለወንድሜ በጣም ስለሚጠነቀቅለትና ስሜቱን ሳይጎዳ ለመጠበቅ ስለፈለገ ነው፡፡
ዳማሲን በቀጥታ ሲጠይቀው ጊዜ ቦን ከባዱን መርዶ አረዳው፡፡ ጓደኛው የሚወዳቸው የቤተሰቡ አባላት ገና በሕይወት ያሉ እየመሰለው ደብዳቤውን መጻፉን እስኪጨርስ መጠበቅን አልፈለገም፡፡ ስለዚህ ቦን ለዳማሲን አባታችን፣ እናታችንና ታናሽ ወንድማችን እንደተገደሉና እኔ ምናልባት በሕይወት ተርፌ ሊሆን እንደሚችል ይነግረዋል፡፡ ዳማሲን ቀኑን ሙሉ ማለት ይቻላል አልቅሶ እንደነበር የደብዳቤው ቋሚ ምልክት የሆኑት የእንባ ጠብታዎች ይህንን ይመሰክራሉ፡፡
ዳማሲን ኪቩ ሐይቅን ለማቋረጥ ጀልባ ፍለጋ ከመሄዱ በፊት ደብዳቤውን እንደገና አውጥቶ አባባ፣ እማማና ቪያኒ በሚሉት ቃላት ግራና ቀኝ ቅንፎችን አስቀምጦ የሚከተሉትን አረፍተ ነገሮች አከለ፡፡ ኢማኪዩሌ እንድትጠነክሪ እለምንሻለሁ፡፡ እማማ፣ አባባና ቪያኒ መገደላቸውን አሁን ሰማሁ፡፡ በተቻለኝ ፍጥነት ላገኝሽ እሞክራለሁ፡፡ ራስሽን ሳሚልኝ፤ እቀፊልኝም! በጣም የሚወድሽ ወንድምሽ!
ይህ ካነበብኳቸው ነገሮች ሁሉ የሚሠቀጥጠው ነው፡፡ እንባ ባረጠባቸው ቃላት ላይ የጣቶቼን ጫፎች አላወስኳቸውና ይህንን ደብዳቤ ሳላለቅስ ማንበብ እንደማልችል ተረዳሁ፡፡

በኋላ ላይ እንደደረስኩበት ለዘላለም የኔ ጀግና ሆኖ የሚኖረው ቦን ወንድሜን በቤቱ ከቤተሰቡ ፍላጎት በተጻራሪ ሊሸሽገው ሞክሯል፡፡ በዘር ፍጅቱ የመጀመሪያ ቀናት ዳማሲንን በምስጢር ከአልጋው ስር በደኅና በመደበቅ ሊያቆየው ችሎ ነበር፡፡ የቦን ቤተሰብ ግን ያደረገውን ነገር ሲደርስበት ዳማሲንን ለገዳዮቹ እንዲሰጥ ግፊት ያሳድርበታል፡፡
ይባስ ብሎ ቱትሲ ልጆችን በዘውግ ስም ጥሪ ወቅት ማሸማቀቅ የሚወደው ቡሆሮ ከቦን አጎቶች አንዱ ነው፡፡ ቡሆሮ በሀገሪቱ ወስጥ ካሉ ጽንፈኛ ሁቱዎች ውስጥ አንዱ፣ መጥፎና አደገኛ ገዳይ ሆኖ ነበርና ሲጠራጠርበት ጊዜ ቦን ዳማሲንን በጭራሽ ቤት ውስጥ ማቆየት እንደሌለበት ይረዳል፡፡ አንድ ሌሊትም በጣም አምሽቶ በቤተሰቡ መሬት ራቅ ያለ ጥግ ላይ ጉድጓድ ቆፍሮ በዕንጨትና ቅጠላቅጠል ይሸፍነዋል፡፡ ገዳዮቹ በቡሆሮ ተጠቁመው ከመምጣታቸው በፊት ዳማሲንንም በጥንቃቄ ከመኝታ ክፍሉ ያስወጣና በጉድጓዱ ውስጥ ይደብቀዋል ፡፡
ዳማሲን በጉድጓድ ውስጥ ከሦስት ሳምንታት ለበለጠ ጊዜ ያህል ተደብቆ ሳለ ገዳዮቹ በቡሆሮ ውትወታ በተደጋጋሚ የቦንን ቤት አሠሡ፡፡ እነዚህ አራጆች ግን የማይሰለቹ በመሆናቸው የቦንን እያንዳንዷን እንቅስቃሴ ተከታትለው መጨረሻ ላይ ምግብ ወደ ውጪ ይዞ ሲሄድ ያዩታል፡፡ ሸሻጊው ጓደኛውና ተሸሻጊው ዳማሲን ገዳዮቹ ግቢውን ሊያስሱብን ይችላሉ ብለው ሠግተው ዳማሲን የኪቩ ሐይቅን ተሻግሮ ወደ ዛየር እንዲያቀና ይወስናሉ፡፡ (ቦን የቱትሲዎችን ሕይወት ለማትረፍ ሐይቁን የሚያሻግራቸውን አንድ ደግ ሳምራዊ ዐሳ አጥማጅ ሁቱ ያውቃል፡፡) ዳማሲንን ከጉድጓዱ አውጥቶ በየጥላው እየቆዩና ከጥሻ ጥሻ እየተሸጋገሩ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ወደ ሐይቁ ሄዱ፡፡ መንገዱ ብዙ ጊዜ በመፍጀቱ ግን የዚያ ሌሊት ጀልባ ታመልጣቸዋለች፡፡
ነጋባቸው፡፡ በመሆኑም ዳማሲን ወደ ቦን ቤት ረጅም መንገድ ተጉዞ ተመልሶ አደጋ ላይ መውደቅን ስላልፈለገ ንሴንጄ በሚባል በሐይቁ አካባቢ የሚኖር የእርሱና የቦን ወዳጅ ቤት ቆየ፡፡ ንሴንጄ ቤተሰባችንን የሚወድ ለዘብተኛ ሁቱ ነው፡፡ አባቴ የብዙ ወንድሞቹን የትምህርት ክፍያ በመክፈል አግዟቸዋል፡፡ ስለሆነም ዳማሲንን ለዚያን ቀን መሸሸግ በመቻሉ ደስ ተሰኘ፡፡
የንሴንጄ ወንድም ሳይመን ግን የወንድሙን ያክል ቸር አልነበረም፡፡ ዳማሲንን በቤታቸው ሲደርስ በፈገግታና በወዳጅነት ተቀብሎታል … በማግስቱ ከሰዓት በኋላ ግን ወንድሜ በተኛበትና ንሴንጄም የጀልባ ጉዞውን ለማመቻቸት በወጣበት ሳይመን ከቤት ሾልኮ ወጥቶ የገዳዮቹን ቡድን ፈልጎ ዳማሲንን አሳልፎ ሰጠው፡፡
ከእራት በፊት ሳይመን ወንድሜን ቀስቅሶ ወደ ዛየር ከመሄድህ በፊት ልብሶችህን ልጠብልህ ይለዋል፡፡ ዳማሲንም ልብሶቹን ሁሉ አወላልቆ በውስጥ ልብስ ብቻ ይቀራል፡፡ ሳይመንም ልብሶቹን ይወስድበታል፡፡ (በኋላ ላይ እንደተናገረው ይህን ያደረገው ወንድሜን ከመሞቱ በፊት ለማሳፈርና ለማሸማቀቅ ፈልጎ ነው፡፡) ልብሶቹን ከወሰደበት በኋላም ሳይመን ወንድሜን በደርዘኖች የሚቆጠሩ ገዳዮች ይጠብቁት ወደነበረበት ወደ ዋናው ቤት ይጠራዋል፡፡ ወንድሜም ላይ ያለ ምኅረት ተረባረቡበት፤ እየደበደቡ ወደ መንገድ ጎተቱት፡፡ ከውስጥ ልብሱም ሌላ ምንም አልለበሰም፡፡ እኛ ቤት ትሠራ የነበረች አንድ ሴት ነገሩን ሁሉ አይታ የዳማሲንን የመጨረሻ ሰዓት ዝርዝር ሁኔታ ነግራኛለች፡፡ ‹‹ቆንጆዋ እህትህ የት ነች?›› ብለው ገዳዮቹ ወንድሜን ይጠይቁታል፡፡ ‹‹የት ነች ኢማኪዩሌ?›› በቤተሰብህ ያሉትን በረሮዎች አስከሬኖች አይተናቸዋል፤ እሷ ግን ገና አልተደረሰባትም… የት ነች? ንገረንና በነጻ እንለቅሃለን፤ ካልነገርከን ግን ሌሊቱን ሙሉ ስንከትፍህ እናድራለን፡፡ በል ኢማኪዩሌ የት እንዳለች ንገረንና በነጻ ትሰናበታለህ፡፡››
ፊቱ የተሰባበረውና ያባበጠው ዳማሲን የከበቡትን ገዳዮች አየት አድርጓቸው በሕይወቴ ሙሉ እንዳደረገልኝ ሁሉ በመጨረሻዋም ቅጽበት ለኔ ቆመልኝ