አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
461 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሁቱትሲ


#ምዕራፍ_ስምንት


#የወጣቷ_ልብ_አንጠልጣይ_ትውስታዎች

#ትርጉም_በመዝምር_ግርማ


#ቁጣዬን_ስጋፈጥ


በአንጻራዊ መረጋጋት በርካታ ቀናት አለፉ፡፡ አልፎ አልፎ ገዳዮቹ ውጪ ላይ የእብድ መዝሙራቸውን ሲዘምሩ እንሰማቸዋለን፡፡ ቀኑን ሙሉ በጽሞና እንጸልያለን፤ እርስ በርሳችንም በምልክት ቋንቋ እንግባባለን፡፡ ከሞላ ጎደል በየ12 ሰዓታቱ የተወሰኑ ተናፋቂ የሰውነት ማፍታቻዎችን እናደርጋለን፡፡ ከዚያ በስተቀረ ቀንና ሌሊት በአንድ ቦታ በመቀመጥ እንቅስቃሴዎቻችንን በተቻለን መጠን እንገድባለን፡፡ መጸዳጃ ቤቱን በቄስ ሙሪንዚ ትዕዛዝ መሠረት ውሃ እንለቅበታለን፡፡ ይህም ሌላ ሰው በዋናው ቤት ውስጥ ያለውን ሌላውን መጸዳጃ ቤት ውሃ ሲለቅበት መሆኑ ነው፡፡ መጸዳጃውን መጠቀሙ ፈተና ሆነብን፡፡ ስፍራው በቂ ስላልሆነ የምትጠቀመው ሰው ከእብነበረድ በተሰራው መጸዳጃ ላይ ቁጢጥ ለማለት ትገደዳለች፤ ስለሆነም አንደኛችን ስንጸዳዳ ሁላችንም ቦታ መቀያየር አለብን፡፡ ያም ድምፅ የማሰማትና በገዳዮቹ የመገኘት አደጋን ጋርጦብናል፡፡
ባልተለመደ ሁኔታ በመታጠቢያ ቤቱ በቆየንበት ጊዜ ማንም መጸዳጃውን ሲጠቀም ማየቴን አላስታውስም፡፡ መጸዳጃው ከእብነበረድ የተሠራና እላዩ ላይ አስቀምጦ የሚያጸዳዳው ዓይነቱ ነው፡፡ ያለው በዚያች ትንሽ ቦታ መካከል ቢሆንም ሽታው ያስቸገረኝ ወቅት ትዝም አይለኝ፡፡ የወር አበባችንም ይደርሳል፤ ያንዳችን ሲሄድ የሌላችን ከተፍ ይላል፡፡ በመሆኑም ቄሱን ተጨማሪ የንጽሕና መጠበቂያ ወረቀት አምጡ እያልን እናስቸግራቸዋለን፡፡ ማንኛችንም ብንሆን ባለው ሁኔታ አንሸማቀቅም፤ እነዚህን ሁኔታዎች ረስተናቸዋል፤ የብቸኝነትም ጥሩ ጎኖች ትዝ አይሉን፤ በተለይ ይህ ችግር በሕይወት ከመኖራችን አንጻር ሲታይ ከግምት ውስጥ አይገባምና፡፡
ቄሱ ምግብ ይዘው በመጡ ቁጥር እንበላለን - የሚያመጡልን አልፎ አልፎ ቢሆንም፡፡ አንዳንድ ቀንማ ያለ ሌሊት 9 ወይንም 10 ሰዓት አይመጡም፡፡ (ሊያዩን ወይንም ምግብ ሊያመጡልን በፈለጉ ቁጥር ቁምሳጥኑን ገፍተው ይገባሉ፡፡ ሁልጊዜ ግን ሌላ ሰው እንዳይሰማቸው በጣም ይጠነቀቃሉ፡፡ ከቁምሳጥኑ ሲንቀሳቀስ ድምጹን ለማፈን የሚሆን ጨርቅ ከስሩ ተደርጎበታል፡፡ በዚህም እግዚአብሔር እንደገና ይጠብቀን ይዟል፡፡) ተጨማሪ ምግብ ቢያዘጋጁ ሌላ ሰው እንዳያውቅባቸው የልጆቻቸውን ትርፍራፊ ወይንም ሠራተኞቻቸው የሚበሉትን አሸር ባሸር ያመጡልናል፡፡ አንዳንዴ ምንም ብንራብም አንበላም እንላለን - የሚሰጡን የአሳማ ምግብ ይመስላላ፡፡ (እቤቴ ምን ዓይነት ምግብ አማራጭ እንደነበርኩ በማስታወስ በራሴ ላይ እሥቃለሁ፡፡) የምንጠጣውም ውሃ ይመጣልናል፡፡

የማይቻል ቢመስልም ከቀናት ጸጥታ በኋላ ትንሽ ዘና አልን፡፡ ያለንበትን ሁኔታ የሚያስታውሱን ቄሱ ብቻ ናቸው፡፡
አንድ ሌሊት ቄሱ መጥተው ገዳዮቹ ባቅራቢያችን ከቤት ወደ ቤት በመዘዋወር ቤቶችን እየፈተሹ ያገኙትን ቱትሲም እየገደሉ እንደሆነ ነገሩን፡፡ ‹‹በተወሰኑ ደቂቃዎች ውስጥ ሊመጡ ይችላሉ፤ ምናልባትም እስከ ነገ ወይንም ከነግወዲያ ድረስም ላይመጡ ይችላሉ፡፡ በእርግጠኝነት ግን ይመጣሉ፤ ስለዚህም ዝም በሉ›› ሲሉ አስጠነቀቁን፡፡ በዚያች መታጠቢያ ቤት ውስጥ ትንሽ የአእምሮ ሰላም ለማግኘት የነበረን ተስፋ ተነነ፡፡ ስለገዳዮቹ መመለስ ያደረብን ሥጋት አዕምሯዊና አካላዊ ውጋት ሆነብን፡፡ ወለሉ ላይ ድምፅ በሰማሁና ዉሻ በጮኸ ቁጥር አንድ ሰው በስለት እንደወጋኝ ይሰማኛል፡፡ በአንዴ መተኛት የምንችለው ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ስለሆነ ቆዳዬ መድረቅና መላጥ አመጣ፡፡ ሁልጊዜም የማይተወኝ ራስ ምታትም ይዞኝ ተቸገርኩ፡፡ የአእምሮ ሥቃዬማ እንዲያውም በጣም ያይላል፡፡ በሃሳቤ ወጥመድ ውስጥ ብቻዬን እሰቃያለሁ፡፡ ከደረስኩ ጀምሮ የሚያስቸግሩኝ ጽኑ ፍርሃቶችና ቅዠቶች በልቤ ውስጥ እየተመላለሱ የእምነቴን መሠረት አናጉት፡፡ ገዳዮቹ ድምጻቸው ለኛ በሚሰማን ርቀት ሲጠጉ ሐሳቤ ከፈጣሪ ራቀና በአሉታዊው ሐሳብ ተጠመድኩ፡፡ በጸለይኩ ቁጥር ግን ወዲያውኑ ፍቅሩን አገኘዋለሁ፤ ስጋቴም ይቀልልኛል፡፡
ስለዚህ ሌሊት ከ10 ወይም 11 ሰዓት ጀምሬ በማንኛዋም እንቅልፍ ባልያዘኝ ሰዓት ለመጸለይ ወሰንኩ፡፡ ሁልጊዜ የመጀመሪያ ጸሎቴ የቄሱ ቤት ስለተሠራልንና በዘር ጭፍጨፋው ወቅት ስለተጠለልንበት አምላክን ማመስገን ነው፡፡ ከዚያም የቤቱ ንድፍ-አውጪ ከተጨማሪ መታጠቢያ ቤት ጋር እንዲነድፈው ስላደረገው፣ ብሎም ለቄሱ የኛን መደበቂያ ስፍራ መሸፈኛ የሚሆን ልከኛ ቁምሣጥን እንዲገዙ ስለገፋፈ
ወቸው አመሰግነዋለሁ፡፡
ከመጀመሪያው የምስጋና ጸሎቴ በኋላ በመቁጠሪያዬ መጸለይ እጀምራለሁ፡፡ ጸሎቶችን በቀዮቹና ነጮቹ ዶቃዎች አደርሳለሁ፡፡ አንዳንዴ በጣም ስለምጸልይ ያልበኛል፡፡ ሰዓታትም ያልፋሉ… ዶቃዎቹንና ጸሎቴን ስጨርስ የምወዳቸውን
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በማለት ‹‹እረፍት›› አደርጋለሁ፡፡ እምነቴ በአደጋ ላይ እንደወደቀ ስለማስብ ከማርቆስ ወንጌል የማስታውሳቸውን ስለ እምነት ጉልበት የሚያወሱ ሁለት ጥቅሶች በመደጋገም ሰዓታትን አሳልፋለሁ፡፡ መጀመሪያ ይህ ነው - ‹‹ስለዚህም እላችኋለሁ፣ አምናችሁ ብትፀልዩ የምትለምኑትን ሁሉ ታገኛላችሁ፤ ይሆንላችሁማል›› (ማርቆስ 11፡ 24)፡፡ ከዚያም ሌላውን እላለሁ - ‹‹እውነት እላችኋለሁ፣ ይህን ተራራ ተነሥተህ ወደ ባህር ተወርወር ብትሉት፣ በልባችሁም ባትጠራጠሩ፣ ብታምኑም እንደተናገራችሁት ይሆናል›› (ማርቆስ 11፡23)፡፡ ሳልጸልይና ስለ እግዚአብሔር ሳላስብ የማሳልፋት ጥቂት ደቂቃ እንኳን ብትኖር ሰይጣን መንታ ጫፍ ባለው የጥርጣሬና በራስ የማዘን ቢላዋው ይወጋኝ ዘንድ መጋበዝ ይሆናል፡፡ ጸሎት መከላከያዬ በመሆኑ ልቤን አጥብቄ እጠቀልልበታለሁ፡፡

ቄሱ ሁልጊዜ ያልሆነ ስህተት ሰርተን ድምፅ እንዳናሰማ ይፈራሉ፡፡ ስለሆነም ወደ መኝታ ክፍላቸው ሰው የሚያመጡት እጅግ አልፎ አልፎ ነው፡፡ አንዳንዴ ግን ከልጆቻቸው አንዷ ወይንም አስተናጋጃቸው ሊጠይቋቸው ሲመጡ እስኪሄዱ ድረስ እንደነዝዛለን፡፡ እዚህ ከመጣን ከአንድ ሳምንት ገደማ በኋላ ቄሱ ከልጃቸው ከሴምቤባ ጋር ሲያወሩ ሰማናቸው፡፡
‹‹አባባ፣ ስለዚህ ግድያ ምን ትላለህ? ጥሩ አይመስልህም - እኛ ሁቱዎች ማድረግ ያለብን ትክክለኛው ነገር አይመስልህም? ማለቴ በትምህርት ቤት ሲያስተምሩን ከመቶዎች ዓመታት በፊት ቱትሲዎች በእኛ ላይ ተመሳሳይ ነገር አድርሰዋል፤ ስለዚህ እያገኙት ያለው ነገር ይገባቸዋል አይደል?››
‹‹ሴምቤባ ስለምን እያወራህ እንደሆነ አታውቅም፡፡ በል ተወኝ አሁን፤ ልተኛበት›› ሲሉ መለሱ ቄሱ፡፡
‹‹ቱትሲዎች ሲባሉ ሁልጊዜ የበላይ ነን ብለው ያስባሉ… ሁሌ ሁቱዎችን ዝቅ አድርገው ያዩናል፡፡ ዛሬም ድረስ ሥልጣን ላይ ቢሆኑ ኖሮ አሁን እየገደሉን አይሆንም ነበር? ስለዚህ እነርሱን መግደል ራስን መከላከል ነው፣ አይደለም?›› ድምጹ በጣም በመጉላቱ ሴምቤባ ቁምሳጥኑ ጎን እንደቆመ መገመት እችላለሁ፡፡ የቁምሳጥኑንም መንቀሳቀስ ያውቅብናል ብዬ በጣም ተሸበርኩ፡፡ እንደፈራሁም ቢሆን ተነሥቼ ልጩህበት የሚለውን ሃሳቤን መቋቋም ነበረብኝ - ቃላቱ በጣም አናደዱኝ፡፡ ይህን ለቱትሲዎች ያለውን ንቀት የተማረው በትምህርት ቤት እንደሆነ ስለማውቅና እኔም እዚያ ትምህርት ቤት ስለተማርኩ ለድንቁርናው ብቸኛው ተጠያቂ እንዳልሆነ ይገባኛል! ወጣት ሁቱዎች ከልጅነታቸው ጀምሮ ቱትሲዎች የበታችና
👍2