አትሮኖስ
281K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ስራው "የፍቅርና የጋብቻ አማካሪነት ነው።የተማረው ፍልስፍና ነው።ሁለተኛ ዲግሪውን ግን አሜሪካ ሄዶ በስነልቦና መስራት ችሏል፡፡በፍቅርና ጋብቻ አማካሪነት የሰራውም እዛው አሜሪካ ነው….ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ሶስት አመት ተቀጥሮ ሰርቶል፡፡አሜሪካዊያኑ በፍቅርና በጋብቻ ጉዳይ ችግር ሲያጋጥማቸው ባለሞያ ጋር መሄድና ድጋፍ ማግኘት ባህላቸው ነው፡፡በመጀመሪያ ወደትዳር ከመግባታቸው በፊት ማድረግ ስለሚገባቸው ስነልቦናዊ ቅድመ ዝግጅት ለማወቅ ባለሞያው ጋር ይሄዳሉ..ትዳር ውስጥ ገብተው ችግር ሲያጋጥማቸው…እርስ በርስ ያለው ተግባቦታቸው አመርቂ ካልሆነ…የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት የሚያጨቃጭቃቸው ከሆነ…የወሲብ አለመጣጣም በመሀከላቸው ካለ ብቻ ማንኛውንም ችግር በመሀከላቸው ከተፈጠረ ወደ ጋብቻ አማካሪ ሄዶ ሞያዊ ምክር መጠየቅና ከዛም የሚሰጣቸውን ምክርና ትዕዛዝ ለየብቻም ሆነ አንድላይ በመተግበር ችግሩን ለመቅረፍ የሚያደርጉት ጥረት ያስቀናል፤ሌላው ይቅር ጋብቻቸው እንደማይሰራ እርግጠኛ ከሆኑ እንኳን ጤናማና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዴት መለያየትና ጓደኛሞች ሆኖ መቀጠል እንደሚችሉ ምክር ለማግኘት ተያይዘው ወደ ጋብቻ አማካሪ ቢሮ ይሄዳሉ..ይህ ጉዳይ በጣም ነበር የሚያስገርመው፡፡በተለይ በመሀከላቸው ልጆች ካሉ ለየብቻ ሆነው እራሱ
የልጆቻቸውን ስነልቦና ጠብቀው እንዴት ተግባባተው ማሳደግ እንዳለባቸው ዝርዝር መመሪያ ከአማካሪዎች በመስማት ያንን ሳያዛንፉ በመተግበር የልጆቻቸውን ደስታ ሆነ የእነሱን ሰላም ይጠብቃሉ፡፡ያም ሆኖ ግን ምንም እንኳን በስራው በጣም ደስተኛና ጥሩ ገቢ የሚያገኝበት ቢሆንም ከአምስት አመት በኃላ ጠቅልሎ ወደሀገሩ ተመለሰ….ሲሄድ መቼም ላይመለስ ነበር…..ሀገር ቤት ባሉ ነገሮች ጠቅላላ ተስፋ ቆርጦ ነበር…ግን እንዲመለስ የሚያስገድደው ቁራጭ ምክንያት አገኘ……እና ተመለሰ፡፡

ሰለሞን ወደ ሀገር ቤት እንደተመለሰ መጀመሪያ ተቀጥሮ ለመስራት  ስራ ለማፈላለግ ሞክሮ ነበር….።አስቴር ግን የራሱን ስራ መጀመር እንዳለበት በተደጋጋሚ ጊዜ ግፊት ስታደርግበት እራሱን ከተበታተንበት ሰበሰበና እና መኝታ ቤቱ ውስጥ ገብቶ በላዩ ላይ ዘጋና ስብሰባ ተቀመጠ።አስቴር የልጅነት ጓደኛው እናም ደግሞ ፍቅሩ ነች…ወጣት ሲሆኑ ደግሞ እህቱ ሆነች…እስከአሁንም እህቱ ሆና ቀረች..እሱ በልቡ ተመልሳ ፍቅሩ እንድትሆን ነው የሚመኘው….አላማውም እቅዱም ያ ነው..እሷ ግን ያንንን መስመር ጠርቅማ ዘግታበት አባቱን አባቷ እናቱን እናቷ አድርጋ ለእሱ ደግሞ እህቱ ሆናለች፡፡

ከልጅነቱ ጀምሮ ነው የሚያውቃት፡፡ ገና ሰባት ወይ ስምንት አመቱ ላይ…የእናቷን ጠርዙ የነተበ የቀሚስ ጫፍ በትናንሽና ለስላሳ እጆቾ ጨምድዳ ይዛ ስርስሯ ኩስ ኩስ እያለች ስትመጣ ነበር የሚያውቃት…የዛን ጊዜውን የልጅነት መልኳን አሁንም በአእምሮው ሰሌዳ ላይ በጉልህ ተስሎ ይገኛል..በአጭሩ ተቆርጦ እርስ በርሱ ተጠቅልሎ የተንጨፈረረ ወርቃማ ፀጉር…ጎላ ጎላ ብላው በፍርሀት የሚንካባለሉ አይኖች…በእንባና በአቧራ ብራብሬ የሆነ አሳዛኝ ፊት….ልክ የግቢው አጥር ተከፍቶላቸው የፊትለፊቱን ትልቁን የሳሎን በራፍ አልፈው ወደጓሮ ሲዞሩ ከኃላ ተከትሎቸው ይሄዳል…እናትዬውን ተከትላ ማድቤት ስትገባ ተከትሏቸው ይገባል…
‹‹የእኔ ልጅ፣ እስኪ እኔ ስራዬን ልስራበት አንቺ ከሰሎሞን ጋር አብራችሁ ተጫወቱ››እያለች እናትዬው ታባብላታለች…እሷም የእናትዬውን ልመና ተቀብላ ከእሱ ጋር ለመጫወት ፍቃደኛ እንድትሆን በአይኖቹ ጭምር ይለማመጣታል….የተቋጠረ ግንባሯን ሳትፈታ በቀሰስተኛ እርምጃ ወደእሱ ትጠጋለች…በደስታ አጇን አፈፍ አድርጎ ይይዛትና እየጎተተ ወደትልቁ ቤት ይዞት ይሄዳል…ከታላቅ እህቱ ጋር በጋራ ወደሚኖርበት መኝታ ክፍላችው ይዞት ይገባል፣..ያሉትን መጫወቻዎች ሁሉ ከየመደርደሪያዎቹን ከየአልጋ ስሩ እየጎተተ ያወጣና  ፊት ለፊቷ  ወለሉ  ላይ  ይቆልላል፣ለእሱ  የሰለቹትን  መጫወቻዎች  ለእሷ  ብርቅ  ነበሩ….እናትዬው እነሱ ቤት በተመላላሽነት በሳምንት ሶስት ቀን ትሰራለች፡፡እና እነዛን ሶስት ቀናት በናፍቆትና በፍቅር ነበር የሚወዳቸው… ሳምንቱን ሙሉ ለምን እንዳማይመጡ ይገርመው ነበር..ከዛ አባቱ እሱን አንደኛ ክፍል አስመዝግቦ ትምህርት ሲያስጀምረው ለእሷም እንደዛው ደብተርና ዩኒፎርም ገዝቶ እሱ የሚማርበት ትምህርት ቤት እናቷ እንድታስመዘግባት አደረገ…አንድ ትምህርት ቤት አንድ ክፍል መማር ጀመሩ…ይሄ ደግሞ የሚገናኙበትን የቀን ብዛትና አጋጣሚ አሰፋው…..ጓደኝነታቸው አብሮ ዕቃ ዕቃ ከመጫወት የተጀመረ ….ከዛ ኤለመንተሪ ጀምረው እስከ ሀይ እስኩል በተመሳሳይ ጊዜ በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ ነው የተማሩት።

የተወሰኑ ክፍሎችን አንድ ክፍል ጥቂት ክፍሎችን ደግሞ አንድ መቀመጫ ላይም አብረው ተቀምጠው የመማር አጋጣሚዋች ነበሯቸው።ስለዚህ እሷ ልክ አብረውት እንደተወለድ ወንድሞቹ እና እህቱ እድሜ ልኩን ነው የሚያውቃት፡፡
ፍቅር የጀመሩት 8ተኛ ክፍል ሲማሩ ነው።በወቅቱ እሱ 8ተኛ ቢ ሲማር እሷ ደግሞ 8ተኛ ኤፍ ክፍል ነበረች።ግን ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ወደት/ቤት ሲሄድና ወደሰፈር ሲመለሱ ተጠራርተውና ተጠባብቀው ነበር።እና አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ሲወጡ እየጠበቀችው ነበር።አብረው ወደቤት መመለስ ቢጀምሩም ግን አንደበቷ እንደተቆለፈና እንደተበሳጨች ነበር...ምን እንደሆነች ቢጠይቃትም በቀላሉ ልትነግረው አልቻለችም..በኋላ በስንት ጭቅጭቅ ከቦርሳዋ አንድ ወረቀት አውጥታ ሰጠችው።ምንድነው? ብሎ በጉጉት ተቀብሎ አነበበው።
አስቴርዬ የእኔ ቆንጆ..የፍቅርሽ ፍላፃ ልቤ ላይ ነው የተሰካው….እስካሁን ሰንኮፉን
አልነቀልኩትም…ያልነቀልኩት ሲሰካብኝ ከነበረው ጊዜ በላይ ስነቅለው ያመኝ ይሁን በሚል ስጋት ነው…….ምን አልባት አንቺው በትንፋሽሽ አዘናግተሸ በልስልስ እጆችሽ ቀስ ብለሽ ብትነቅይልኝ መልካም ይሆን ይመስለኛል፡፡፡አንቺ እኮ ከአለም ሴቶች ጭምር ተወዳዳሪ
የሌለሽ ውብ ነሽ።እኔ አፍቃሪሽ በአንቺ ፍቅር መንገላታት ከጀመርኩ አመታት አልፈዋል።ግን እስከዛሬ ስቃዬን በውስጤ አፍኜ ህመሜን የቻልኩት ከጓደኛዬ ከሰለሞን ጋር ግንኙነት ያላችሁ ስለሚመስለኝ ነበር።ግን በቀደም ወኔዬን አሰባስቤ ስጠይቀው ጓደኛሞች ብቻ እንደሆናችሁ ነገረኝና ነፍሴን በሀሴት አስጨፈራት።እና ውዴ አንቺስ ምን ትያለሽ...
?መልስሽን በጉጉት እጠብቃለሁ... የአንቺው አፍቃሪ መስፍን ጋዲሳ›› ይል ነበር።

አነበበውና ግራ የመጋባትና የመደነጋገር ስሜት ተሠማው..በደብዳቤው ላይ እንደተጠቀሰው በቀደም በብዙ ጓደኞቻቸው መካከል ስለፍቅር አንስተው ሲያወሩ መስፍን እንደቀልድ ‹‹አስቴርና ሰለሞን ፍቅረኛሞች ናቸው›› አለ ወዲያው ሰለሞን ከአፉ ተቀበለና
‹‹እውነት አይደለም እኔና አስቴር ፍቅረኛሞች ሳንሆን ጓደኛሞች ነን ››ብሎ መልስ ሰጠ ።ነገሩ በዚህ ተደመደመ።ደብዳቤውን ባነበበበት ወቅት ግን መሠፍን ሆነ ብሎ ለገዛ የግል ጥቅሙ ጥያቄውን ጠይቆት እንደነበረና እሱንም ማኖ እንዳስነካው ገባውና በጅልነቱ ተበሳጨ።

ግን ደግሞ የአስቴር ወቅታዊ ኩርፊያ አልገባውም ነበር።‹‹መስፍን ደብዳቤ ለፃፈላት እኔን ለምን ልታኮርፈኝ ቻለች?››እራሱን ጠየቀ
"እና እኔ ምን አጠፋው..የምታኮርፊኝ?"ፈራ ተባ እያለ ጠየቃት፡፡
👍6712🔥2
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰለሞን ለዚህ ነው ከውጭ ከተመለሰ በኃላ ለመደላደል ስራ መጀመር እንዳለበት የወሰነው
‹‹ምንድነው መስራት ያለብኝ?ምን አይነት ዕውቀት ነው ያለኝ?ምን አይነት ጥሪትስ አለኝ?ህብረተሠብስ ምን አይነት ሸቀጥ ወይም አገልግሎት ነው መግዛት የሚፈልገው?። መልሶቹ ቀላል አልነበሩም...ወደ አእምሮው የሚመጣው መልስ ወደግል ስራ የሚያስገባው ሳይሆን እንደውም በተቃራኒው የሚያርቀ ነው የሆነበት።

1/ይሄ የምኖርበት ህብረተሠብ በዚህ ሰአት ግዙፍ ችግሩ ምንድነው...?ወረቀትና እስኪሪብቶ ያዘና ዘርዝሮ መፅፍ ጀመረ

1/ኑሮ ውድነት
2/የሠላም እጦት
3/የፍቅር እጦት
4/ቴክኖሎጂ ቅኝ ግዛት
5/...!!የአየር ፀባይ መዛባት
የፃፈውን መለስ ብሎ አየው ...ለደቂቃዎች ብቻውን ተንከትክቶ ሳቅ ። ዝርዝሩን አንድ አነስተኛ የግል ቢዝነስ ለመክፈት ሳይሆን አዲስ ጠቅላይ ሚንስቴር ሆኖ ተሹሞ በሀገሪቱ ስር ነቀል ለውጥ የሚያመጡ የፓሊሲ አማራጮችን ለማርቀቅ መነሻ ሀሳቧችን እያሰላ ያለ ፓለቲከኛ ነው  የሚመስለው።

‹‹እስቲ የህብረተሠብም የኑሮ ውድነትን የሚቀርፍ ምን አይነት ቢዝነስ ነው የሚኖረው...?ኑሮ ውድነቱ እንኳን ግለሠብ መንግስትስ ለማስተካከል አቅም አለው...?የመለኮት ጣልቃ ገብነት ከሌለስ  መፍትሄ ይኖረዋል?።››ሲል አሰበና በራሱ ድርጊት ዳግመኛ ሳቀ፡፡ ከዘረዘራቸው ሀሳቦች የ3 ተኛው ሀሳቡን ገዛው።‹‹ፍቅር እጦት የእኔም የማህበረሰብም የጋራ ችግር ነው።የፍቅር እጦት ደግሞ የሌሎች ችግሮች ሁሉ መነሻ ምክንያት ነው።ደግሞ በሙሉ አቅሜ መስራት የምችለው ስራ እሱን ነው …ሞያዬም ችሎታዬም እሱ ላይ ነው››ሲል አሰበና ወሰነ፡፡

አሜሪካ እያለ ተቀጥሮ የሚሰረባትን የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ ድርጅት እዚህ ሀገሩ መሀል አዲስ አበባ ላይ በራሱ ለመክፍት ወሰነ…‹‹የራስህን ቢዝነስ ጀምር›› ብላ ስትጨቀጭቀው ለነበረችው አስቴር ነገራት፡፡፡አንገቱ ላይ ተጠምጥማ ጉንጩን እየሳመች በሀሳብ በጣም መደሰቷንና በማንኛውም ነገር ከጓኑ እንደሆነች አበሰረችው…እሷ የተደሰተችበት ነገር ደግሞ በእሱ ህይወት ትልቅ ቦታ ስላለው ወዲያውኑ በደስታ ወደእንቅስቃሴ ገባ……ፍቃድ ለማውጣት ቢሮ ለመከራየትና አስፈላጊ የቢሮ እቃዎችን አሞልቶ ለመክፈት 40 ቀን ብቻ ነበር የፈጀበት፡፡

ይሁን እንጂ ለአንድ ወር ያህል በሰአት ቢሮ እየገባ በሰዓት ቢወጣም አንድም ደንበኛ ማግኘት አልቻለም…ሁሉ ነገር ተስፋ አስቆራጭ የሆነበት፡፡ግራ ገባው ፣በመጀመሪያውም ዝግና ድብቅ ባህል ባለበት ሀገር የጋብቻና የፍቅር አማካሪ ድርጅት ከፍቶ ውጤታማ ሆናለው ብሎ በማሰብ በራሱ ጅልነት ተበሳጨ…የስድስት ወር የቢሮ ኪራይ ባይከፍልና ለፈርኒቸር እና የቢሮ እቃዎችን ለማሟላት ከመቶ ሺ ብሮች በላይ ባያወጣ ኖሮ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ ዘጋግቶ ሌላ የቅጥር ስራ ይፈልግ ነበር..ግን ለጊዜው እንደዛ ማድረግ አይችልም…‹‹አዎ ለአስቴር ምን እላታለሁ….?እንድታፍርብኝማ አላደርግም…እሷ ከምታፍርብኝ አለም ጠቅላላ ብትገለባበጥ እመርጣለሁ….ስለዚህ የሆነ ነገር ማድረግ አለብኝ››በማለት ወሰነና ቀኑን ሙሉ ሲያሰላስል ዋለ… የሆነ ነገር ብልጭ አለለት፡ስልኩን አነሳና ደወለ፡፡
ከአራት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡

‹‹ሄሎ ወንድሜ….›››የሚል ድምፅ በስልኩ እስፒከር አቆርጦ ጆሮው ውስጥ ተሰነቀረ…

‹‹አለሁልሽ››

‹‹ምነው ድምፅህ?››

‹‹ደህና ነኝ….የሆነ ነገር ላማክርሽ ነበር?››

‹‹ይቻላል..ግን ስራ አሪፍ ነው እንዴ?….››

‹‹አሪፍ ነው …አሁን አንድ ደምበኛዬን ወደትዳር ከመግባቷ በፊት ማድረግ ስለሚገባት ቅድመ ዝግጅት ማወቅ ፈልጋ ነበር.. እሷን እንደሸኘሁ ነው የደወልኩልሽ››ዋሻት፡፡

‹‹ደስ ይላል ወንድሜ …ህልምህን መኖር ጀምረሀል ማለት ነው….››

‹‹አንቺ ከጎኔ ሆነሽ እስከደገፍሺኝ ድረስ ምንም ማላሳከው ነገር የለም…..አሁን ለምን መሰለሽ የደወልኩልሽ…ፀሀፊ ብቀጥር ብዬ አሰብኩ…››ያሰበውን ነገራት፡፡

‹‹አዎ አንተ ….እስከዛሬ እንዴት አላሰብንበትም…?ለፕሮቶኮሉ እራሱ አስፈጊ ነው…ባለጉዳዬች እንደመጡ አንተን ማግኘት የለባቸውም በፀሀፊህ በኩል ቀጠሮ ይዘውና ተገቢውን ቅድመ ማሟላት ያለባቸውን ነገር አሟልተው መሆን አለነበት…አሪፍ ነው…››

‹‹እና እንዴት ላደርርግ ?ማስታወቂያ ላውጣ….?››

‹‹አይ እኔ በሶስት ቀን ውስጥ ምርጥ ፀሀፊህ ቀጥርልሀለው….አንተ በዚህ ጉዳይ ምንም አትጨነቅ…..ሶስት ቀን ብቻ ስጠኝ››

‹‹እሺ ማታ እቤት እንገናኝ››

‹‹እሺ ቻው ..ወንድሜ››

‹‹ቻው..››

ወንድሜ የሚለው ቃል ከአንደበቷ በወጣ ቁጥር በአንገቱ የተንጠለጠለ የብረት ሰንሰለት ነው የሚታየው….ሆነ ብላ እሱን ለማጥቃት አስባ ከአንደበቷ የምታወጣው ነው የሚመስለው….‹‹አደራ እኔ እህትህ ባልሆንም ልክ እንደእህትህ ነኝና ሌላ ነገር በአእምሮህ እንዳይበቅል››የሚል ማስጠንቀቂያ ነው የሚመስለው፡፡
የእናትና አባቱ ልጆች የሆኑት እህቱ ወንድሜ የሚለውን ስም በአመት አንዴ እንኳን ሲጠቀሙ አልሰማም….ትዝም የሚላቸው አይመስለውም…እሷ ግን ልክ እንደዘወትር ፀሎት እንደውዳሴ ማርዬም ነው በየእለቱ የምትደግመው፡፡
///.....////...../////

በፀሎት ጥዋት ከእንቅልፏ ስትባንን እቤት ውስጥ ከወ.ሮ እልፍነሽ በስተቀር ሌላ ማንም ሰው አልነበረም፡፡

‹‹እማዬ ሰው ሁሉ የት ሄደ?››እማዬ ብላ መጣራቷን ለራሷም እየገረማት ነው…ደግሞ አፏ ላይ አልከበዳትም…ወላጅ እናቷ…ሌላ ሴት እናቴ እያለች መጥራት መጀመሯን ብትሰማ ልብ ድካም ይዟት ፀጥ እንደምትል እርግጠኛ ነች፡፡

‹‹ወይ ልጄ… ነቃሽ…ልቀስቅሳት ወይስ ትንሽ ትተኛ እያልኩ ከራሴ ጋር ስሟገት ነበር፡፡ በረሀብ ሞትሽ እኮ››ብለው  ወደ ጓዲያ ገብና የእጅ  ማስታጠቢያ  ይዘው መጥተው,ሊያስታጥቧት ጎንበስ አሉ…እንደምንም ከአንገቷ ቀና ብላ ተነሳችና ‹‹ያስቀምጡት እኔ እታጠባለው››

‹‹አረ ችግር የለውም ልጄ ..ችግር የለውም››

‹‹ግድ የሎትም….››.

‹‹እንግዲያው ታጠቢ …ቁርስሽን ላቅርብ ›› ብለው ማስታጠቢያው ስሯ አስጠግተው አስቀመጡላትና ተመልሰው ወደ ጓዲያ ሔድ

…….እግሯ በተንቀሳቀሰች ቁጥር ጥዝጣዜው ነፍሶ ድረስ ይሰማታል…..ፊቷ ላይ አሁንም ተራራ የሚያህል ቁስል የተሸከመች እየመሰላት ነው…እንደምንም ተንፏቀቀችና እጇን ታጥባ የሚመጣላትን ቁርስ መጠበቅ ጀመረች…ጩኮ ከእርጎ ጋር ነበር የመጣላት…ጩኮ መች በልታ እንደምታውቅ አታስታውስም….ቤቷ ቁርስ ሲቀርብ አስር …አስራአምስት አይነት ምግብ ጠረጴዛ ሞልቶ ነው….ከዛ ውስጥ ሶስት ወይም አራት አይነቱን አፕታይቷ የፈቀደላትን መርጣ በልታ ሌላውን ትተዋለች..አሁን የቀረበላት ምግብ ይህን ያህል ግን አስደሳች አልነበረም…….እርቧት ስለነበረ እየተስገበገበች በላች…
ያጋባችውን ሰሀንና ብርጭቆ መልሳ…እጇን ታጠበችና…..‹‹እማዬ ማንም የለም እንዴ?››ስትል ደግማ ጠየቀች፡፡

‹‹ልጄ ለሊሴ ስራ ፍለጋ ብላ ወጥታለች…ፊራኦል ስራ ነው ..አባትሽም እንደዛው››መለሱላት፡፡

‹‹ለሊሴ ምን አይነት ስራ ነው የምትፈልገው?››
👍5412