አትሮኖስ
286K subscribers
121 photos
3 videos
41 files
575 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ዳግም


#በሕይወት_እምሻው


"ሮምዬ...ብዙ ሰዐት ዝም አልሽ እኮ ...!..ጨነቀኝ...አንድ ነገር በይኝ እንጂ .." አላት፣ የደፈረሰ ፊቷን ሁለት እጆቿ ውስጥ ቀብራ በተቀመጠችበት ወደ ፊትና ወደ ኋላ ስትወዛወዝ እያየ። የምትሆነውን አላቆመችም። መልስም አልሰጠችውም። ጭንቀቱ ሳይለቀው፣ ፊት ለፊቱ ጠረፔዛ ላይ የተቀመጠውን ጀምሮት የነበረውን የብርጭቆ ውሃ፣ በአንድ ትንፋሽ ግጥም አድርጎ ጠጣና መልሶ አያት።

የተለወጠ ነገር የለም።

"ሮሚ..." አለና ትከሻዋን ነካት።

መወዝወዟን አቁማ፣ ፊቷን ከእጆቿ አውጥታ ከፊቷ እኩል በደፈረሱ ቁጡ ዐይኖቿ ዐየችው።

"በእናትሽ ለእኔም እዘኚልኝ እንጂ... ወድጄ እኮ አደለም...ያው ማወቅ አለብሽ ብዬ ነው..."

ምንም ሳትናገር ከተቀመጠችበት ተነሳችና የሳሎኑን በር ከፍታ ወጣች። ግራ በመጋባት ዐያትና ትንሽ ቆይቶ ተከተላት።

የበረንዳው መቀመጫ ላይ ኩምትር ብላ ተቀምጣለች።

አጠገቧ ተቀመጠ።

"ሮሚ..." አላት ወደ ጎን እያያት

"ወይ..."

"ባልነግርሽ ይሻል ነበር...? እ?"

"አሁን ሂድ...ብቻዬን መሆን እፈልጋለው ስምኦን...ነገ እደውልልሃለው..."

በመስማማትም፣ በአለሁልሽም፣ ትከሻዋን መታ መታ አድርጎ ተነሳና መራመድ ጀመረ።

የውጭው በር ጋር ደርሶ ከከፈተ በኋላ፣ ዞር ብሎ ዐያት። በተቀመጠችበት እያለቀሰች ነው። ተመልሶ ማፅናናት ትእዛዟን መጣስ፣ ዝም ብሎ መሄድ ደግሞ ጭካኔ ሆኖበት ግራ ተጋብቶ ዐያት። የሚያደርገውን መወሰን አቅቶት እንደቆመ ብድግ አለችና ወደ ቤት ገባች።

"ምስኪን ሮሚ" አለ ለራሱ። ምስኪን።

=========================

"አንቺ በቃ ይሄን ለቅሶ አልተውም አልሽ አይደል?" አለች ሳባ፣ በቁጣ። ስሞኦን ከሄደ ከረዥም ሰዐት በኋላ ሮማን ረጅሙ ሶፋ ላይ ጋቢዋን ለብሳ ስትንፋረቅ አግኝታት ነው።

"ተይኝ በናትሽ አንቺ ደሞ..." አለች፣ አፍንጫዋን በጋቢዋ ጫፍ እየጠረገች።

"ለምንድን ነው የምተውሽ? የምትወጅው ሰው የሞቸብሽ አንቺ ብቻ ነሽ እንዴ? ለእኔም ወንድሜ ነው...ያንን ደግ ሰው በሰላም እንዳያርፍ አታድርጊው። ይልቅ...ተነሽ አሁን ፊትሽን ታጠቢ..." አለች ሳባ ጮክ ብላ።

ሳባ የሮማን ታላቅ ብትሆንም፣ ዲበኩሉ ከሞተ ወዲህ እንደ ታላቅ ትቆጣታለች። እንደ ታላቅ ትወቅሳታለች። በሐዘን ተሽመድምዳ ለቁም ነገር መብቃት ያቃታት ሮማንም የታላቅነት ቦታዋን አምና ስለተቀበለችው እምቢ አትላትም። እህቷ ናትና፣ እንዲህ የሚያደርጋት ፍቅር ነውና በጄ ብላ ትታዘዝላታለች። ባሏን፣ ሁለተናዋን ካታች ደቂቃ ጀምሮ ለሦስት ወር ከመጣው ሰው ጋር ሁሉ ስትንፈራቅ፣ ሌሊት ተነስታ ዐይኖ እስኪጠፋ ስታለቅስ፣ በንዴት ጸጉሯን ስትነጭ፣ ከሰው አልገናኝም ብላ ሐያዥ ለገናዥ ስታስቸግር፣ ነጋ ጠባ የዲበ መቃብር ጋር እየሄደቸ፣ "ልጅ እንኳን ሳልወልድልህ አመለጥከኝ" ብላ ስታነባ፣ "በልክ አድርጊው.... በቃ" እያለች ወደ ሰውነት ልትመልሳት የምትታገለውን ታናሽ እህቷን፣ እሺ ትል ነበር። ዛሬ ግን አልቻለችም።

"ተነሽ እንጂ...ግቢና ታጠቢ!" አለች ሳባ፣ እጇን ይዛ ልታነሳት እየጎተተቻት።

"ውይ ሳባ ደግሞ! ተይኝ አልኩሽ እኮ!" አለች፣ እሷም ጮክ ብላ። "ለመሆኑ ምን ተፈጥሮ ነው ዛሬ ደሞ ደህና የነበርሽው ልጅ እንዲህ ሆነሽ የጠበቅሽኝ?" አለች ሳባ፣ ከሷፋው አልነሳም ብላ ያስቸገረቻትን ሮማን እጆቿን ለቃ እያየቻት።

"ምንም...."

"ምንም አትበይኝ....ማን መጥቶ ነበር?"

"ማንም....ማንም አልመጣም..."

"ሠራተኛውን ጠይቄ ማወቅ እችላለሁ እኮ ሮሚ...ለምን አትነግሪኝም?"

ሮማን ዝም ብላ ቆማ የምታያትን ሳባን ሽቅብ ማየት ጀመረች።

"ማነው የመጣው ሮሚ?"

"ስምኦን...ስምኦን ነው የመጣው ሳባዬ.."

ሮማን ማልቀስ ጀመረች። ሳባ ቶሎ ብላ አጠገቧ ተቀመጠችና።

"እንዴ...ታድያ ስምኦን ከለቅሶው ጀምሮ ከዚህ ቤት ጠፍቶ ያውቃል እንዴ? ምን ተፈጥሮ ነው ዛሬ እንዲህ የሆንሽው?"

አለች።

"ሳብዬ...ስምኦን የሆነ ነገር ነገረኝ..."

"ምን? ምን ነገረሽ?

"ምን ብዬ ልንጠርሽ..."

"ውይ ሮሚ በናትሽ አታስጨንቂኝ..."

"ዲበ.......ዲበ ልጅ አለው..."

"ም....ን?" አለች ሳባ፣ ፍንጥር ብላ እየተነሳች። ሶፋው አንጥሮ ያጎናት ነበር የምትመስለው።

"ዲበ ልጅ አለው..." ሮማን ደገመችላት።

"የት...? ከማን...? መቼ....? ማለቴ እንዴት...? ሳባ በቆመችበት ቅደም ተከተል የሌላቸው ጥያቄዎች አዘነበችባት

"የመስርያ ቤት ልጅ ናት አለኝ..."

"ማን ነው እንዲህ ያለሽ ?"

"ውይ አንቺ ደግሞ ስምኦን ነዋ!"

"እ....ስምኦን...ቆይ ልቀመጥ... አዞረኝ አኮ በናትሽ..." ሳባ ተመልሳ ሮማን አጠገብ ተቀመጠች።

"እና...ማለቴ እርግጠኛ ነው? እንዴት ዐወቀ እሱ..."

"ቤስት ፍሬንዱ አይደል...ነግሮት ነዋ..."
ሳባ እራሷን በታላቅ መገረም ወደቀኝ እና ወደ ግራ ስትወዘውዝ ቆየችና...

"ቆይ...ቆይ ይሄ...ማለቴ ልጁ...ካንቺ በፊት የወለደው ነው አይደል...? ማለቴ የስንት ዓመት ልጅ ነው?"

ሮማን ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ ማልቀስ ጀመረች።

"ሮሚ....ካንቺ በፊት ነው አይደል?"

ሮማን ማልቀሷን ሳታቋርጥ ራሷን በአሉታ ነቀነቀች።

"ወይ ጉድ! ወይ ጉድ! ወይ ጉድ! ወይ ሰው! አለች ሳባ፣ እጆቿን በማጨብጨብ እያማታች።

"ለመሆኑ...የስንት ዓመት ልጅ ነው ያለው አለሽ...? አለች የሮማንን፣ ለቅሶ ለማስቋም ሳትቋጣ።

"ሦስት ዓመቱ ነው አለኝ..."

"ወንድ ልጅ ነው?"

"አዎ..."

"ወይ ጉድ! እኔ መቼስ ማመን አቅቶኛል... ውሸት መሆን አለበት...ዲበ ባንቺ ላይ? ሌላ ሴት? አይመስለኝም...."

"ህም...ሳቢዬ...እኔም ማመን አቅቶኛል ግን..."

"ግን...ምን?"

"ተቆራጭ ሲያደርግላት እንደነበር ነግሮኛል...እሱ ከሞተም ለሦስት ወር ስምኦን ሲከፍላት ነበር...."

"ወይ ጉድ...!"

"የት ነው የምትኖረው? እዚሁ አዲስአባ?"

"አይደለም..."

"እና የት ናት..."

"ናዝሬት"

"ናዝሬት?"

"አዎ....ናዝሬት..."

"እና ቆይ...ቅምጥ ነገር ናት ማለት ነው?"

"አይ...ሳቢ እኔ ምኑን አውቄው...? ስምኦን ግን ሲምል ሲገዘት ነበር..."

"ምን ብሎ?"

"የአንድ ቀን ስህተት ነው....ከዚህ ወዲህ ለልጁ ነው እንጂ እንኳን በፍቅር በሥርአትም አግኝቷት አያውቅ እያለ ሲምልልኝ ነበር....."

"ወይ ጉድ!"

በዚህ ሁኔታ ወሬው በ 'ወይ ጉድ' ታጅቦ፣ ባለማመን ታጅሎ ለሰዓታት ለሰአታት ቆየ። የመኝታ ሰዓት ደርሶ ለስሙ አልጋዋ ውስጥ የገባችው ሮማን ግን ነገር ማውጠንጠን ቀጠለች።

ዲበ? የኔ ዲበ ከሌላ ሴት ጋር ተኛ? እሺ ፊልድ ላይ ነው...እሺ ጠጥቶ ነው...እሺ ተሳስቶ ነው... የኔ ደግ፣ ካለኔ ዓይኑ የማይገለጠው፣ ካለኔ አንደበቱ የማይከፈተው ባል ከሌላ ሴት ተኝቶ ዘር ፈጠረ? ልጅ ሠራ?

የስህተት ልጅ ሰርቶስ አራት ዓመት ሙሉ ባልና ሚስት ሆነን፣ አፍ ለአፍ ገጥመን እያወራን፣ ከጣራ በላይ እየሳቅን፣ ፍቅር እነሰራን፣ ሙዚቃ እየሰማን፣ እስክስታ እየወረድን፣ ሻይ እያፈላን፣ ቡና እየጠጣን፣ ፍርፍር እየበላን፣ ሥራ እየሄድን፣ በመንገድ ጭንቅንቅ እየተነጫነጭን፣ መኪና እየነዳን፣ በኪራይ ቤት እየተማረርን፣ ቤት እየገነባን፣ በአሁኑ እንውለድ ወይስ ቤታችን እስቂያልቅ እንቆይ እየተከራከርን.... ይህን ሁሉ እየሆንን አስችሎት ዋሸኝ? አንጀቱ እሺ ብሎት ደበቀኝ? እኮ የኔ ዲበ....መንገድ ወጥቶ የቀረው
👍4🤔1
#ዳግም (የመጨረሻ ክፍል)


#በሕይወት_እምሻው


==========
"ሳቢ ቅድስትን ነገ ላገኛት ነው..." አለች ሮማን፣ ሳባን ሳይሆን፣ በመብላት ፋንታ በዳቦ አንቃ ሰሃኑ ላይ ወዲህ ወድያ የምታንገላታውን እንቁላል ፍርፍር እያየች።

ሳባ ሻይ ትጠጣበት የነበረውን ወፍራም ብርጭቆ ጠረጴዛው ላይ በኀይል ጓ! አድርጋ አስቀመጠችና፣

"አንቺ ግን ጤና የለሽም በቃ? ደሞ ምን ልሁን ብለሽ ነው የምታገኛት?" አለች።

"ስንቴ ልንገርሽ...አንቺ አይገባሽም..." አለች ሮማን በፍርሃት ካቀረቀረችበት ቀና ብላ እያየቻት።

"ምኑ ነው የሚገባኝ? ባልሽ እላይሽ ላይ ሌላ ሴት ጋር መሄድ ሳያንስ፣ ልጅ መውለዱ ሳያንስ ሄጄ ላገኛቸው ስትይ ምኑ ነው የሚገባኝ!" ሳብ በንዴት መለሰች።

"ሳቢ...እንደሱ አይደለም... ሁለት ሳምንት ተናደድኩ...አለቀስኩ... አሁን ግን ረጋ ቡዬ ሳስበው በሞተ ሰው ለይ መናደድ ድንጋይ መንከስ ምናምን የሚሉት ገባኝ.... ማለት እሱ የለም...ስምኦን ደግሞ ደጋግሞ ነግሮኛል... ስህተት ነበር..."ሳባ አላስጨረሰቻትም።

"ስህተት ቢሆንስ? አንቺ የእሱን ዲቃላ ማሳደግ አለብሽ?" "ሳቢ... እንደሱ አይባልም...ደሞ እኔ ላሳድግ አልኩኝ?" "እና ታድያ ምን ልትሆኚ ነው የምታገኛት?

ሮማን በዝምታ ማሰብ ጀመረች። ለምንድን ነው ቅድስትን የምታገኛት? ራሷ ዐይታ ለማረጋገጥ? የአራት ዓመት ባሏ የተሳሳተባትን ሴት በዐይኗ ለመመልከት ልጁን ዐይታ እሺ ብትለው ኖሮና ቢወልዱ ኖሮ ምን የሚመስሉ ልጆቹን ይኖሯት እንደነበር ለመገመት? አታውቅም። ግን ልታገኛት ፈልጋለች።

"መልሺልኝ እንጂ!" ሳባ በጩኸት ጠየቀች።

"አላውቅም ሳቢ ግን ላገኛት ይገባል... ይቆርጥልኛል...." "ተይ ባክሽ ያንቺ ጅል አንጀት ምንም ቢያደርጉት አይቆርጥም. የራስሽ ጉድይ!" ሳባ ከወንበሯ ተነሳችና ወደ መታጠብያ ቤት መሄድ ጀመረች።

ከሳሎን ልትወጣ ጥቂት እርምጃ ሲቀራት ግን የበላችበት እጇን አንከርፍፋ ዞር አለችና፣

"ልጁን ይዛ ነው የምትመጣው ?" አለቻት።

"እ?"

"ልጇን ታመጣዋለቸሸ ወይ ?"

"እኔ እኮ ነው የምሄደው.... ናዝሬት ነው የምሄደው...."

"ምን....?"

"እሷ ልጅ ይዛ እዚህ ድረስ ከምትመጣ እኔ ብሄድ አይሻልም?"

"አንቺ ለይቶልሻል.... የራስሸ ጉዳይ...!"

ሳባ ምንቅርቅር እያለች ከሳሎን ወጣች።

=============
ሮማን የተቀጣጠሩበት ባለ ሰፊ የአትክልት ቦታ ሆቴል ቀድማ ደርሳ እየጠበቀች ነው። ያዘዘችውን ሚሪንዳ አሁንም አሁንም እየተጎነጨች በትግስት እየጠበቀች ነው። ለሚያያት የናፈቀችውን ፍቅረኛ እንጂ ባላንጣዋንና የባሏን ሕገ-ወጥ ልጅ የምትጠብቅ አትመስልም። ሕገ-ወጥ ልጅ - ሕገ- ወጥ ሰው አለ? ዐሥር ደቂቃ እንዳለፈ ሙሉ ቀይ ቱታ ለብሳ፣ ከእሷ እኩል ለመራመድ የሚታገል ትንሽ ልጅ እጅ ይዛ፣ ወደ ግቢው የምትገባ አጠርና ደልደል ያለች ሴት ዐየች።

ሚሪንዳዋን አንስታ ተጎነጨች። በረጅሙ ተኘፈሰች። እነሱ መሆን አለባቸው።

ሴትየዋ በረንዳው ላይ የተቀመጡ ሰዎችን ሰው በሚፈልግ ሰው ዓይነት ከቃኘች በኋላ ወደ እሷ መምጣት ጀመረች።

ሮማን በተቀመጠችበት ተንቆራጠጠች።

ሊያልቅ አንድ ጉንጭ የቀረውን ሚሪንዳዋን ተጎነጨች። ሴትየዋ ከነልጇ አጠገቧ ደረሰች።

"ይቅርታ...ሮማን ነሽ?" አለቻት ወድያው።

"አዎ...ቅድስት? " አለች ሮማን፣ ከተቀመጠችበት ተነስታ እጇን ለሰላምታ እየዘረጋች - አንዴ አጠገቧ ስትደርስ ከቅድሙ በጣም ያጠረችባትን ሴት፣ አንዴ ደግሞ ድምቡሽቡሹን ትንሽዬ ልጇን አፈራርቃ እያየች።

ቅድስት የልጅ መንቀዥቀዥ የሌለበትን ልጇን አቅፋ ቸቀመጠች። ከምንና በምን ወሬ እንጀምትጀምር ግራ የተጋባችው ሮማን፣ የሳባን ምክር ሰምታ መቅረት እንደነበረባት ማሰብ ጀመረች። ምን ልትላት ነው? ለምን ከባሌ ጋር ተኛሽ? ለምን ከእኔ ሳይወልድ ከእሱ ወለድሽ? ሞቱ እንደኔ ጎዳሽ ወይ?

"ምን ይምጣላችሁ አለች?" በዚህ ሁሉ ፋንታ።

ቅድስት ለራሷ ኮካ ኮላ፣ ለልጇ ደሞ ፋንታ አዘዘች። ሮማን ደግሞ ሌላ ሚሪንዳ ጠየቀች። እንደገና ምቾት የማይሰጥ ዝምታ ሰፈነ። አሁን ደግሞ ለብቻው ወንበር ላይ የተቀመጠው ልጅ በትልቅ ሰው ወግ በስነ- ስርአት ተቀምጦ እናቱ የምታጠጣውን ፋንታ በዝምታ፣ አንዳንዴ በፈገግታ ይጠጣል። እርጋታው ደስ ከማለት ይልቅ ምቾት ይኘሳል።

"በረታችሁ....?" አለች ቅድስት፣ እየሰፋ የመጣውን የዝምታ ክፍተት ለመሙላት በመመኘት።

"እግዜር ይመስገን...ቋሚ ምን ይሆናል... በርትተናል..." አለች ሮማን። "አንቺስ በረታሽ?" ብዬ ልጠይቃት ወይስ ዝም ልበል ፣ በሚል ሐሳብ ተይዛ። "የዲበ ነገር መቼም የሚያሳዝን ነው... እግዜር ነፍሱን ይማር..." አለች ቅድስት።

"እህ... አሜን..." ሮማን መለሰች....

"እኔ ምለው..." አለች ወዲያው መልሳ።

"አንቺ የምትይው..." ቅድስት መለሰች።

"ለቅሶ መጥተሽ ነበር እንዴ?"

ቅድስት ከብዙ ምርጫዎች ውስጥ መልሷን ለመምረጥ እንደፈለገች ሁሉ አሰበችና፤ "እንዴት አልመጣም....ቀብር መጥቼ ነበር....ቤት ግን መረበሽ ስላልፈለግኩ አልመጣሁም..." አለች።

"መረበሽ ማለት? " ሮማን ቶሎ ብላ ጠየቀች። "አይ...እንዳልነገረሽ ስለማውቅ በዚያ ሰዐት ሌላ ነገር...ጭንቀት መጨመር አልፈለግኩም...."

ሮማን በገባኝ ራሷን ነቅንቃ ዝም አለችና ወደ ልጁ ዞር ብላ ዐየችው። አሁንም በትልቅ ሰው ወግ ፈገግ አለላት።

"ዲበን ይመስላል ልበል?" አለች ሳታስበው።

"እ?" ቅድስት በድንጋጤ መለሰች።

"ልጅሽ አይኑ ጋር...ዲበን ይመስላል...."

"ነው ብለሽ ነው...? እንጃ አይመስለኝም... ሰው ሁሉ የእኔን አባት ነው ይመስላል የሚለው...."

"አይ...ዐይኑ ጋር ወደሱ የሚሄድ ነገር አለው..."

ሮማን ሳታስበው ዐይኖቿ በእንባ ተሞሉ።

"ማነው ስሙ?"

"ስሙ?"

"እ...ማነው ስሙ?"

"ዳግም..."

"ዳግም ዲበኩሉ?"

"አዎ..."

"አንቺ ነሽ ያወጣሽለት ወይስ ዲበ ነው?"

"አይ... እኔ ነኝ...."

ዳግም ወሬው እንደከበደው ሁሉ ከወንበሩ ተንሸራቶ ወረደና ወደ አትክልት ቦታው እየተደረደረ መሄድ ጀመረ። እናቱ በዐይኗ እንጂ ተነስታ አልተከተለችውም።

"ኮንዶም አልተጠቀማችሁም ነበር?" ሮማን አሁንም ሳታስበው ጠየቀች።

"ምን?" አለች ቅድስት በድንጋጤ ዐይኖቿን እየተንገዳገደ ከሚሄደው ልጅ ወደ ሮማን መልሳ...

"ማለቴ...መስከራችሁን ስምኦን ነግሮኛል...ግን ኮንደም አልተጠቀማችሁም?"

ይህንን ጥያቄ በዚህ ሰዐት ለምን እንደጠየቀች አታውቅም። ምናልባት የተሳሳተው ባሏ በስካርና በስህተት ሰዐት እንኳን የወትሮው ጠንቃቃነቱ አብሮት ነበር ብላ ለማመን ፈልጋ ይሆናል.... ምናልባት በሽታ ይዞኝ ሚስቴንንም አሲዛለሁ ብሎ ሰግቶ፣ አዝኖልኝ ይሆናል ብላ ልታምን ፈልጋ ይሆናል።

"ወይዘሮ ሮማን... ለምን ልታገኚኝ እንደፈለግሽ አልገባኝም...ግን እሺ ያልኩሽ ለዲበ ብዬ ነው... ጥሩ ሰው ነበር.... ለእሱ ብዬ...ስሞኦንንም አንቺንም አክብሬ ነው...ግን እንዲህ አይነት ጥያቄ...."

"ይቅርታ ቅድስት....."

"እ?"

"ይቅርታ.... እንዲህ አይነት ነገር መጠየቅ አልነበረብኝም....ግራ ገብቶኝ ኘው...."

ቅድስት ምንም ሳትመልስላት ብድግ ብላ ወደ ልጇ ሄደች። ሮማን በተቀመጠችበት ሆና አትክልት ስፍራው ውስጥ የውሸት ስታባርረው ፣ ሲፈነድቅ፣ እፍስፍስ አድርጋ አንስተረ ሁለመናውን ስትስመው ዐየች።