#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ሳባ‹‹ወደ ትምህርትሽ ለመመለስ አልፈልግሺም ነበር….?››መሀከል ገብታ ጥያቄ ጠየቀቻት
ምን ሊያደርግልኝ…ተምሬ ስንት ልቀጠር..ሶስትና አራት ሺ ብር…ምን ላደርግበት.?ነገ ብታመም እንደእናቴ ባዶ ቤት ማቅቄ ልሞት? ነገ ልጅ ብወልድ በድህነት ውስጥ ላሳድገው….?አይ ምንም ሰርቼ ምንም ሀብታም መሆን ብቻ ነው የፈለኩት….ለምሳሌ መስረቅም ቢሆን ፤መሸርሞጥም ቢሆን፤ሀሺሽ ማከፋፈልም ቢሆን… ብቻ ዋናው ጠቀም ያለ ገንዘብ ያስገኝ እንጂ የስራው አይነት ላይ ምንም አይነት ምርጫ እንደማላደርግ ለራሴ ቃል ገባሁ….በአጋጣሚ ያ ያልኩሽ ሰውዬ እቅዴን ስነግረው ከትብለጥ ጋር አስተዋወቀኝና ‹‹እባክሽ እርጂያት››አላት…ተገናኝን..አየቺኝ ልክ አሁን አንቺን እንደወደደችሽ ወደደቺኝ..ታዲያ እኔ እንደአንቺ መወዛገብ ውስጥ አልገባሁም እንዴትስ ልገባ እችላለሁ…? እሺ ብላ ተረከበቺኝ፡፡ ወደስልጠና ገባሁ…ስልጠናው ዛሬ እንደምንሰጠው በጣም የተደራጀ አልነበረም…ግን ለአንድ ወር ሰለጠንኩ…ይበልጥ ወደድኩት…እና ይሄው ስድስት አመት እሱኑ እየሰራሁ ነው፡
ስልኳን ከኪሶ አወጣችና ከፈተች፤ከባንክ የተላከላትን የሂሳብ ዝርዝር.ላይ ያለውን ብር አሳየቻት 6,354,450 ይላል
‹‹6 ሚሊዬን ነው የሚለው?››
‹‹አዎ›› አለችና ጋላሪ ውስጥ በመግባት አንድ ፎቶ አወጣች ‹‹ይሄ በቅርብ እያሰራሁት ያለ ጅምር ቤት ነው..ከሶስት ወር በኃላ ይጠናቀቃል፤ይህቺኛዋ መኪናዬ.ነች፤ቢያንስ ከአስር የሚበልጡ የዘመዶቼን ልጆች አስተምራለሁ…፡፡
‹‹ይገርማል›› አለች ሳባ
‹‹አዎ ይገርማል… .እንግዲህ አስከአሁን የነገርኩሽ መግቢያውንና.መደምደሚያውን ብቻ ነው፡፡ማለቴ እንዴት ስራው ውስጥ እንደገባሁና በመግባቴ ያገኘሁትን ውጤት….››
‹‹አዎ ..››
መሀከሉ የህይወትሽን የአስተሳሰብሽን፤ለሰው ልጅ የምትሰጪውን አጠቃላይ ትርጉም ሙሉ በሙሉ የሚገለባብጥ ተግባርና ስራ ነው የሚያጋጥምሽ…አስር ዲግሪ ብትማሪ የማታገኚውን የህይወት ልምድ ነው የምታገኚው..ሀገር በእነማን አንደምትመራ፤የምናደንቃቸውና.ለአምልኮ በተጠጋ ፍቅር የምንከተላቸው አርቲስቶች እና ዘፋኞች ያላቸው ስብእና..ብር ለሀብታሙና ብር ለደሀው ያለው የትርጉም ልዩነት …ብዙ ብዙ ነገር ትማሪበታለሽ….መማር ብቻ አይደለም…እያንዳንዷን እውቀትም ሆነ እያዳንዷን ገንዘብ ስትቀበይ ለዛ የምትከፍይው ስቃይና ህመም አለ…አንዱ ደንበኛ እንደ አሻንጉሊት ያይሻል፤ ሌላ ንግስት አድርጎ ያንቆጦቁጥሻል አንዱን ሰውነቱን ከላይ እስከታች ታሺለታለሽ፤ ሌላውን ደግሞ አእምሮውንና የውስጥ የስነልቦና ጥዝጣዜውን ውስጡ ገብተሸ እንድታክሚው ይጠበቅብሻል… አንዱን በወሲብ ስታስደስቺው…ሌላውን ደግሞ ለሊቱን ሙሉ ቁጭ ብለሽ እንድታዳምጪው ብቻ ይፈልግ ይሆናል…፡፡
በዚህ የስራ ባህሪ የማያጋጥምሽ ነገር የለም…እርግጥ ከፍላጎትሽ ያፈነገጠ አካላዊ ጥቃት አያጋጥምሽም፤ ድርጅቱ ለዚህ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋል…እዚህ የሚመጡት ደንበኞቻችን ለስማቸው አብዝተው ስለሚጨነቁ በዛ ብዙም አያስቸግሩም፡፡ በተረፈ ግን ዋና ታርጌትሽ በመጪዎቹ አምስትና ስድስት አመታት ለእድሜ ልክሽ የሚበቃሽን ብር ለማግኘት ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ቁርጠኛ ነሽ ወይ…ነው..ለዛ አዎ ቁርጠኛ ነኝ… ከሆነ መልስሽ ያንን እንድታደርጊ የሚያግዝሽ በቂ ስልጠናና ዝግጅት እንዲኖርሽ ወደስልጠና ትገቢያለሽ…አይ እኔ የገንዘብም ችግር የለብኝም.. ቤተሰቦቼ ደህና የሚባል አቅም አላቸው እኔም እየሰራሁት ያለሁት ስራ በቂ ነው የምትይ ከሆነ ግን ልገፋፋሽ አልፈልግም ቢቀርብሽ ይሻላል››
የተወሰነ ደቂቃ ዝም አለች…ሰገንም በዝምታ የማሰላሰያ ሰዓቱን ፈቀደችላት
‹‹ችግሯን አሰበች…ቤተሰቦቿ ያሉበትን ሁኔታ አሰበች…ሁለት እግሮቹን አጥቶ ቤቱ የቀረውን ተወዳጅ አባቷን አሰበች፤የብቸኛ ታናሽ ወንድሟን የወደፊት ህይወቱን አሰበች በወቅቱ በኩርፊያ የተለያየችውን ፍቅረኛዋን አሰበች.. ሰገን ያሳየቻትን በስድስት አመት ውስጥ ሰርቼ አገኘሁት ያለችውን ብር መጠን አሰላች.እያሰራች ያለውን ቤትና የምትነዳውን መኪና አሰበች…በመጎምዠት በአፏ ምራቅ ሞላ ‹‹አይ እሞክረዋለሁ››አለቻት፡፡
‹‹እሞክረዋለሁአይሰራም..አደርገዋለሁ.ወይም ይቅርብኝ..መልስሽ ከሁለት. አንዱ ነው መሆን ያለበት››
‹‹አደርገዋለሁ፡፡››
እጇን ዘረጋችላትና ‹እንኳን ደስ አለሽ… የቤተሰባችን አባል ለመሆን ስለወሰንሽ ደስ ብሎኛል...ከእኔ በተሻለ ብልህ ሆነሽ ስኬታማ እንደምትሆኚ አምናለሁ›በማለት ጨበጠቻትና ፊት ለፊቷ ያለውን ወረቀት አነሳችና ከመካከሉ ሁለት ፎርም በማንሳት ከእስኪርፕቶ ጋር አውጥታ እየሰጠቻት አንብቢውና ፈርሚበት..ያው በእኛ መካከል ዋናው የወረቀት ውል ሳይሆን የደም ውል ነው...አንዴ ቤተሰብ ሆነሽ ወደውስጥ ከገባሽ በህይወት ጭምር እንታመንሻለን ፤በህይወትሽ ጭምር ትታመኚናለሽ ማለት ነው፡፡ ለማንኛውም እስክትጨርሺ መጣሁ ብላ ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደውስጥ ገባች…ሳባም ማንበብ ጀመረች…
አሰሪውና ሰራተኛውን ማክበር የሚገባቸውን ኃላፊነትና ያላቸውን መብት የሚደነግግ ነው፡፡
ለምሳሌ፡
ሰራተኛው..በስራ ሂዳት የሚያጋጥሙትን ሰዎች ማንነት ሆነ ከእነሱ ጋር ያሳለፈውን ማንኛውንም ምስጢራዊም ሆኑ ቀላል ነገሮችን ከማንም ጋር አንስቶ ማውራትም ሆነ መወያየት በጥብቅ የተከለከለ ነው፤ከቤተሰብ ከእናት ጋር ቢሆንም፡፡ ይሄንን መተላለፍ ሚስጥሩ እንደሚያስከትለው ጉዳት መጠን መረር ያለ ቅጣት ያስከትላል፡፡
ህመም ወይም የታወቀ ከባድ ችግር ካልገጠመ በስተቀር ደንበኛ በቀጠሮ በተገኘበት ጊዜ ከስራ ቦታ ላይ አለመገኘትም ሆነ ማርፈድ ፈፅሞ የማይፈቀድና ይቅርታ የማያሰጥ ስህተት ነው፡፡
ከደንበኞች የሚሰጥ ማንኛውንም የብር ስጦታ፤የጌጣጌጥ ስጦታ፤ከዛም ከፍ ያለ እስከ ቤት ስጦታ ድረስ ቢሰጥ ሙሉ በሙሉ የሰራተኛው የግል ሀብት ነው፡፡
ድርጅቱ ሰራተኞቹ በደንበኞች አካላዊ ጥቃት ድብደባም ሆነ መሰል ጥቃት ቢደርስባቸው ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ እስከ ውጭ ሀገር በመላክ ሙሉ ህክምና እንዲያገኙ የማድረግ ጥቃት አድራሹ ደንበኛ ጋር በህግም ሆነ በሌሎች ዘዴዎች በመጠቀም በቂ ካሳ እንዲያገኙ የማስደረግ ኃላፊት ይወስዳል፡፡ቅድሚያ ግን አንደዚህ አይነት ችግሮች እንዳይከሰቱ ደንበኞች መረጣ ላይም ሆነ በሂደት ክትትል ያደርጋል…የራሱን ዘዴ በመጠቀም በስውርና በግልጽ ደህንነታቸውን ይከታተላል፤ ይጠብቃል፤ከስራ ሰዓት ውጭ የፈለጉበት ቦታ መሄድ፤ቤተሰቦቻቸውን የመጠየቅ ከጓደኞቻቸው ጋር መዝናናት ሙሉ መብት ያላቸው ቢሆንም ለደህንነታቸው ሲባል እንቅስቃሴያቸውን በተለያዩ ዘዴዎች ክትትል ይደረግባቸዋል፡፡ የስራቸው ፀባይ ከሀገሪቱ ትላልቅ ሰዎች ጋር ስለሚያገናኛቸው በተቻለ መጠን የሚሄዱበቸው ቦታዎች የተመረጡ የሚያገኟቸው ሰዎች ወደአደጋ የማያስገቡ መሆን እንዳለባቸውም የሚያብራራ አንቀጽ አለበት.በአጠቃላይ እነዚህንና መሰል መመሪያዎች ነው ያሉት
‹‹አንዴ ገብቼበታለሁ የራሱ ጉዳይ፤ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም›› አለችና እስኪሪፕቶውን አነሳችና ሁለቱም ወረቀት ላይ ፈርማ በእፎይታ ከመቀመጫዋ ተነስታ ስትንጠራራ ሰገን ከሄደችበት በፈገግታ መጣች፡፡ የፈረመችውን ወረቀት ከጠረጴዛ ላይ በማንሳት አንዴ በስሱ አየችና ወደቦታው መልሳ በማስቀመጥ ቦርሳዋን አነሳችና ከፈተች….አንድ በካኪ የተጠቀለለ ነገር አነሳችና እጆ ላይ አስቀመጠች
ሳባ‹‹ምንድነው?›› ጠየቀቻት

👍77❤4
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ዛሬ ላይ
ሳባ ሊቱን ሙሉ በትዝታ ከወዲህ ወዲያ ስትዋዥቅ ነው ያደረችው…ለሰከንድ እንኳን እንቅልፍ በአይኗ አልዞረም…አሁን የትዝታ ጉዞዋን መሀከል ላይ ሳትቆጭ
ያቆመችው ታናሽ ወንድሟ ራጂ የተኛችበት ክፍል ደረስ መጥቶ በእናቱና በእሷ መካከል ሰርስሮ መሀከላቸው ሲገባ ነው፡፡
‹‹አንተ ጓረምሳ ሴቶች ክፍል ምን ትሰራለህ?››
‹‹እህቴ ናፍቃኝ ነዋ››
‹‹ወደራሷ ልጥፍ አድርጋ በማቀፍ ግንበሩን ሳመችው፡፡››
‹‹እህቴ ዛሬም ታድሪያለሽ አይደል?›
‹‹ማደር አላድርም …ግን አሁን እንነሳና ከተማህን ዞር ዞር አድርገህ አሳየኝ..ከዛ ትንሽ ዘና ብለን ከሰአት በኃላ እሄዳለሁ፡፡››
ስንዱ(እማሆይ አፀደ) ከአልጋዋ እየወረደች‹‹ ምነው ዛሬ አድረሽ ነገ በጥዋቱ -ብትሄጂ አይሻልም?››ስትል ሀሳብ አቀረበችላት፡፡
‹‹አይ.. ቢያንስ ነገ በጥዋት ሀኪሜ ጋር ተመልሼ በመሄድ ስላቋረጥኩት -መድሀኒት ነገሬው የሚለኝን መስማት አለብኝ፡፡››
‹‹በቃ እንደዛ ከሆነ ተነሱ እስከዛ እኔ ቁርስ ልስራ፡፡››
‹‹አይ አንቺም ተነሺና አብረን ውጭ ነው ቁርስ ምንበላው፡፡››
‹‹ባይሆን እናንተው ሂዱና ስትመለሱ ከእኔ ጋር ሆነን የሆነ ቦታ እንሄዳለን፡፡ ማለቴ ብዙም ጊዜ የሚፈጅ አይደለም፡፡እዚሁ ቅርብ ነው፡፡15 ደቂቃ ቢወስድብን ነው፡፡››
‹‹ሳባም …እሺ በቃ›› ብላ ለባብሳ ከወንድሟ ጋር ተያይዘው ከግቢ ወጡ፡፡ቀጥታ የሄዱት ሻለቃ ደራርቱ ቱሉ ሆቴል ነው፡፡ እዛ እየተዝናኑና ቁርስ እየበሉ እተጫወቱ አራት ሰዓት ሆነ ፡፡ ከዛ ወጡና ወደስጦታ መሸጫ ሱቅ እየሄዱ ሳለ ስልኳ ጠራ፡፡አየችው ..በጣም የምትፈልገው ስልክ ነው፡፡አነሳችው፡
‹‹እሺ ደራሲ ጳውሎስ እንዴት ነህ?››
‹‹አለሁ.. ሰላም ነኝ››
‹‹እሺ እንዴት እየሆነልህ ነው…?›
‹‹ጨርሼለሁ..ዛሬ ወደአዲስአባ ልንመጣ ነው…ከመነሳቴ በፊት ልደውልልሽ ብዬ ነው፡፡››
‹‹በእውነት በጣም አስደሳች ዜና ነው የነገርከኝ…በቃ እኔም አሁን አሰላ ነኝ…ከሰአት እነሳለሁ..ነገ እንገናኛለን፡፡››
‹‹እሺ በቃ ቸው››
‹‹ደግሞ የጉዞውም ነገር መስመር ይዞል..በአስራአምስት ቀን ውስጥ የሚጠናቀቅ ይመስለኛል፡፡››
‹‹ደስ ይላል፡፡በቃ ነገ አንገናኝ፡፡››ብሏት ስልኩን ዘጋው፡፡እሷም ስልኳን ወደኪሷ መልሳ በደስታ ፈጋ ወንድሟን እንዳቀፈች ወደ ሱቅ ገባች፡፡ ትኩስ አበባ ከገዙ በኃላ ቀጥታ ወደቤተክርስትያን ነው ተያያዘው የሄዱት፡፡ ሁለቱም አባታቸው መቃብር ላይ የያዙትን አበባ አስቀመጡና ሀውልቱ ስር ጎን ለጎን ቁጭ አሉ፡፡ ሁለቱም በዝምታ ተሸብበው በየራሳቸው ትዝታ መዳከር ጀመሩ፡፡ሳባ ትዝ ይላታል፡፡የዛሬ ሰባት አመት በፊት የአባቷ አሟሟት፡፡
አዎ ሙሉ በሙሉ በእሷ ጣጣ እንደሞተ ነው የምታምነው፡፡በዛ ምክንያት ደግሞ በቀል በውስጧ በቅሎ ሰው እስከመግደል ደርሳለች፡፡እርግጥ ቀጥታ የሽጉጥ ቃታ ስባ…ወይም ጩቤ በሰው ልብ ሰክታ አልነበረም ግድያውን የፈፀመችው፡፡ግን የአባቴ ዋነኛ ገዳይ ነች የምትላትን ሴት ያላትን ሁሉ አንድ በአንድ እንድታጣ አድርጋ ባዶዋን በማስቀረት በራሷ እጅ አንገቷን ገመድ ውስጥ አስገብታ ከዚህች አለም ህይወት እራሷን እንድትገላግል አድርጋለች፡፡አሁን ሌላ አንድ ትቀራታለች….ለእሷም የመጨረሻውን ቦንብ አጥምዳ ወደማጠናቀቁ ላይ ነች…ከዛ የሴትዬዋ እግሮች ቦንቦቹን ረግጠው ሲነሱ ሁሉ ነገሯ ቡም ብሎ ይበታተናል... ያ ወጥመድ….ደራሲ ጳውሎስ ፅፎ ያጠናቀቀው መፅፈህ ነው፡፡ያ መፅሀፍ ቦንብ ሆኖ ቀሪዋንና ኃያሏን ሴት ያስወግዳታል..‹‹አባዬ አይዞህ ..አንድ በአንድ እበቀላቸዋለሁ››አለች ሳባ፡፡
‹‹ምን አልሽ እህቴ …?አናገርሺኝ?››አላት ታናሽ ወንድሟ፡፡
‹‹አይ…. ከአባዬ ጋር እያወራሁ ነበር፡፡››አለች ደንግጣ፡፡ ራጂም ‹‹እህቴ …አባዬ እኮ በጣም ነው የሚናፍቀኝ፡፡›› አላት፡፡
‹‹እኔም በጣም ነው የሚናፍቀኝ…..በየጊዜው እናንተ ጋር የማልደውለው ለምን እንደሆነ ታውቃለህ ?እንተን ሳወራ አባዬ ትዝ ስለሚለኝና እሱ ትዝ ሲለኝ ደግሞ ሀዘን ውስጤን ስለሚሸረካክተው ነው፡፡አባዬ በጣም ጀግናና ስማርት የሆነ አባት ነበር… ሲሞት አንተ ልጅ ስለነበርክ በደንብ ልብ ላትለው ትችችለህ…በተለይ ከአደጋው በፊት ሮጦ ልረፍ የማይል፤ ሰርቶ ደከማኝ የማያውቅ፤ ለቤቱ ድንቅ አባወራ ለእኔና ለአንተ ድንቅ አባት ፤ለሰፈርና በቄሄው የተከበረ ልዩ ሰው ነበር…አባዬን ሳስብ ሁል ጊዜ ከአደጋው በፊት ስለነበረው ሁኔታ ነው ማሰብ የምፈልገው…››
‹‹እህቴ እኔ አንቺ ከምታስቢው በላይ አባዬን አውቀዋለሁ.እርግጥ አምስት አመቴ ላይ ነው የሞተው…ቢሆንም አምስት አመት ሙሉ እኔን ከማሳደግ ውጭ ሌላ ስራም ሆነ ፍላጎት እልነበረውም…እማዬ እናቴ መሆኗን በትክክል ያወቅኩት እንኳን እሱን በሞት ካጣሁ በኃላ ነው፡፡ከዛ በፊት ምተኛው ከእሱ ጋር
፤የሚያጥበኝ እሱ፤ ምግብ እራሱ የሚያጎርሰኝ እሱ ነበር..እስኪሞት ድረስ በእጆቼ ምግብ ቆርሼ መጉረስ አልችልም ነበር ፡፡እሰከዛ ድረስ በእሱ እጅ ካልሆነ ምግብ ወደአፌ አይገባም ነበር…በየቀኑ የሚነግረኝ ተረቶች የሚያነብልኝ መፅሀፎች ትዝታው ዛሬ የተከወነ ያህል ነው የማስታውሰው ፡፡አንድ አይነት ተረት በቀን
ለ10 ጊዜ ደጋግመህ ንገረኘኝ ስለው አይሰለችም…በደስታ ያደርገዋል፡የአባዬ ጣፋጭ ድምፅ ዛሬም በጆሮቼ ውስጥ ሲንቆረቆር ማደመጥ እችላለሁ፡››
በታናሽ ወንድሟ ልብ የሚነካ ንግግር እንባዋ በጉንጮቾ ተንኳለለ፡፡
ወንድሟ ቀጠለ‹‹…እህቴ የዛን ያህል እያስታወስኩት በዛ መጠን እየናፈቀኝ እንኳን ለምን አንዳማላማርር ታውቂያለሽ?››
መልሱን ለመስማት ተነቃቃች‹‹ለምንድን ነው?››
‹‹አንቺ ስላለሺኝ ነዋ…አንቺ እኮ ልክ እንደአባቴ ነሽ..አይደለም አሁን ላለሁበት ለወደፊት ህይወቴ እንኳን ትጨነቂያለሽ…ጀግና እህት ስላለኝ በአንቺ እፅናናለሁ..አባዬ ሲናፍቀኝ እዚህ እመጣና አንቺ ለእኔ እና ለእናቴ ምታድርጊልን ነገር ሁሉ እነግረዋለሁ…ከዛ ደስ ሲለው አይቼ ወደቤቴ እምለሳለሁ.፡››
ከተቀመጠችበት ተንደርድራ ሄዳ አቀፈችው …ጭምቅ አድርጋ አቀፈችው.. እያገላበጠች ሳመችው…እሱ በእሷ ላይ ያለውን መመካት እሩብን ያህል እሷ በራሷ ላይ ኖሯት ቢሆን እጅግ ደስ ይላት ነበር፡፡ግን እሷ በውስጧ ትንሽነት ነው የነገሰው.. ፤ባዶነት ነው ልቧን የሞላው ፤ስጋት ነው እየናጣት ያለው፤ተስፋ መቁረጥ ነው ዙሪያዋን የከበባት፣
እህትና ወንድም ተመልሰው እቤት ሲደርሱ ስድስት ሰዓት አልፎ ነበር… እናትየው ምርጥ የተባለ ምሳ ሰርታ ቡና አፍልታ ፤እቤቱን አሟሙቃና አጫጭሳ ነበር የጠበቀቻቸው…የተዘጋጀውን ምግብ ከበሉና ከቡናውም አቦሉን ከጠጡ በኃላ ስንዱና ሳባ በተራቸው ተያይዘው ወጡ..
‹‹ስንድ የት እንደምትወስጂኝ ለማወቅ ጓጉቼያለሁ?››
‹‹ትንሽ ታገሽ ደግሞ አስደሳች ቦታ የምወስድሽ እንዳይመስልሽ››
‹‹እናስ..?››
‹‹ያው አስፈላጊ ቦታ ነው…. በተለይ ለእኔ?››
‹ለነገሩ ዝም ብዬ ነው የጠየቅኩሽ…መቼስ መዝናኛ ቦታ ይዘሽኝ ትሄጃለሽ ብዬ አላስብም…›

👍79❤10🔥1😁1