አትሮኖስ
283K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
513 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል አምስት

ይላል ዶጁ እንደገና...

ማሂ ሰላም ጋር ለአንድ ዓመት በአካል አልተያዬንም፤ ስልክም ተደዋውለን እናውቅም፡፡ ብቻ ስለ እርሷ እንዲሁ በወሬ ወሬ፣ የተሟላ ነገር ሳይሆን፣ እዚሀና እዚያ የሚረግጥ ነገር፣ በጋራ ያውቁን ከነበሩ ወዳጆቻችን እሰማ ነበር።አንዳንዶቹ የተለያዬነው በጠብ እየመሰላቼው፣ እኔን ለማጽናናት፣ ስለሷ ክፉ ክፉውን እያመጡ ይነግሩኛል። አስገራሚው ነገር፣ የሚበዙት ጓደኞቼ የሚያምኑት እንደካደችኝ ነበር: ከዳኝ ሌላ ከአሜሪካ የመጠ ወንድ እንዳገባች። አንገት ደፊ አገር አጥፊ! ስትቅለሰለስ እንዲህ የምታደርግ አትመስልም ነበር...ድሮም ሴቶችን ማመን .. እና ሌላም ተረት፣ አባባልና ብሶት ጋር ወቀሳቼውን በእርሷ ላይ _ አዥጎደጎዱ። በመጨረሻም ጥርግ ትበል፣ ወላድ በድባብ ትሂድ ቆንጆ ሞልቷል፡፡ እግዚአብሔር ይክስኻል አይዞህ! ብለው ሊያጽናኑኝ ሞከሩ። የተሳሳተ መሠረት ላይ የቆመ ማጽናናት ማንንም አያጽናናም፡፡ አልተጽናናሁም:: ሲጂምር ተበድዬ ነበር ወይ? ከምኑ ነው ያልተጽናናሁት? የራሴ ቼልተኛ ባሕሪ ገፍትሮ ትዳር ወደሚባል ጥልቅ ዓለም ስለወረወራት ሚስኪን ሴት በደል? የራሴ ቼልተኛ ጥፋት ከፈጠረብኝ ጸጸት? ሕፃናት ክብሪት ሲለኩሱ ድፍን ቤት እንደሚያቃጥል አስበው አይደለም፤ የጅል ድርጊት በአዋቂ ነፍስ የተደበቀ ሕፃንነት ነው፤ ቀጥሎ ያለውን ያለማስተዋል፡፡ የአንዱ ጨዋታ ለሌላው ሕይወት ነው። ባልገባኝ ምክንያት ከተለያዬን በኋላ የማሂን ነገር ሳስብ መበሳጨት ጀምሬ ነበር። ብስጭቴ የቅናት አልነበረም፡፡ እኔ ጋር ትጣላ ወይም በእኔ ተስፋ ትቁረጥ፣ ዓላማ የለውም ፣ ሴት አውል ነው ብላ ትመን ፤ ግን ከእኔ ለመራቅ የግድ ተንቀልቅላ ሄዳ፣ የኾነ የማታውቀውን ሰው ማግባት ነበረባት? እላለሁ፡፡ ቆይቼ ምናገባኝ? እልና በዚያው አፌ ለምን አያገባኝም? በአንተ ምክንያት እንዲህና እንደዚያ ሆንኩ የሚል ወቀሳ አንድ ቀን ይቀራል? ለሰው ባትናገረውም፣ ባለችበት ዕንባዋን እየረጨች እንደ ባልቴት መራገሟ ይቀራል? ብትወቅሰኝም፣ ባትወቅሰኝም ግን ከሰማሁት አጠቃላይ ነገር በመነሳት ከእሷ አስተዋይነትና ትዕግስት ጋር አልገጥም ያለኝን ነገር ያደረገች

ይመስለኛል፡፡ ማነው ለመሆኑ ይህቺን ምስኪን ሥጋ አጥንቴ ናት ብሎ ያገባት? ነፍሷን እዚህ ጣጥላ የሄደች ጠይም ሙዳ ሥጋ። እኔን እንደ ካደችኝ የሚያምኑ ወዳጆቼ፣ የሷ የሆነውን በማጣጣል ሊያጽናኑኝ... “የሆነ ግስላ የመሰለ! ሰው ነው ያገባችው፣ አንተ በእሱ ፊት ልዑል አይደል እንዴ የምትመስለው!?'' አሉኝ፡፡ ግስላ ምን ዓይነት እንስሳ እንደሆነ አላውቅም፡፡ ባላውቅስ? ሰው የሚመስል ሰው በአገሩ ጠፋ? ውጭ አገር (የፈረደበት አሜሪካ) የሚኖር ሰው ነው አሉኝ። ሩ.....ቅ አገር! የሲራራ ትዳር ( የሲራራ ንግድ ከተባለ፣ ለምን የሲራራ ትዳር አይባልም?) ላለፈ ደግነቷ ስል አሁን ላይ ልወዳት እየጣርኩ ነበር። እንዲሁ ለራሴ አፈቅራት ነበር'ኮ አገባች፣ ተለያዬን ለማለት። ውሽታም ቢለኝም ራሴ፤ ለሌሎች አይደለም ለራሴ፡፡ የጥፋተኝነት ስሜት እንዳይሰማኝ ወይም “ይወደኝ ነበር'ኮ፤ ግን ከመተኛት በስተቀር ቁም ነገር ስለማያውቅ ተውኩት'' እንድትል ዕድል ለመስጠት፣ ለሌሎች አይደለም ለራሷ፡፡ በዚህ እንኳን ሰው ሰው ልሽተት። ከሰውነት መንበር አልውደቅ ብዬ፣ እሷን በማጣቴ መቆጨቴን በሆነ መንገድ እንዲደርሳት ፈለግሁ፡፡ ያላገባኋት ንቂያት ሳይሆን፣ ማፍቀር ስላልቻልኩ መሆኑን መናገሪያ መንገድ አወጣሁ አወረድኩ፤ መናቃችን እንደ ውጋት እንደ ልጅነት ስብራት እየከረመ ሕመሙ እንዳይሰማን፣አጠገቤ ሆና ቃሌን እንደ ምጽዓት ስትጠብቅ ያልተነፈስኩትን ዛሬ የሆነ ነገር ልላት ፈለግሁ፡፡ እንደውም የዙሪያ ከመሄድ፣ ለምን ራሴ አግኝቼ ይቅርታ አልጠይቃትም? ብዬ ወስኜ እንድንገናኝ የጽሑፍ መልዕክት ላኩላት “ሃይ! ማሂሰላም! ላገኝሽ ፈልጌ ነበር መቼ ይመችሻል?'' “ላገኝህ አልፈልግም!'' አለችኝ፡፡ ደስ አለኝ፡፡ ቢያንስ ገፋኝ ሳይሆን የመጨረሻዋ ገፊ እሷ እንደሆነች ማሰቧን ወደድኩት፡፡ እውነቱን ለመናገር በጊዜው ይኼ ነው የሚባል የመከፋት ስሜት አልተሰማኝም፤ እንዲያውም የሆነ የማላውቀው የእረፍትና የነፃነት ስሜት ተሰምቶኝ ነበር፤ ጥያቄው ግን ለምን? ነበር። ለምንድን ነው ቆንጆ፣ አፍቃሪ፣ ከልቧ ትሁት የሙዚቃ

ወንዝ ነፍሷን አቋርጦ የሚፈስባት ውብ ምድር የሆነች ልጅ፣ ማፍቀር ያልቻልኩት: ማለቴ የሆነ ዓይነት የአእምሮ ሕመም ቢሆንስ? የሆነ “ዲስ ኦርደር'? ምልክቱ ጠይም ሴቶች ጋር መተኛት እንጂ፣ ማፍቀር የማያስችል “ዲስ ኦርደር'? ነገሩ ማለቴነው እንጂ፤ እሱማ ቀዮቹንስ፣ ጥቁሮቹንስ መቼ አፈቀርኩ? የጎርፍ መንገድ ላይ እንዳበቀለ ሰምበሌጥ፣ በላዬ ላይ በጎረፉ ቁጥር ተኝቼ እያሳለፍኳቸው ተመልሼ ቀና እላለሁ። የተሳሳተ ነገር አለ፡፡ ምንም እንኳን፣ አንዳንዶች ከአሜሪካ የመጣ ሰው ስታገኝ እንደ ካደችኝ በማሰብ ከንፈር ሊመጡልኝ ቢሞክሩም (እንደዚያ አይደለም እባካችሁ! ስል ከአፌ ነጥቀው “በክሀ ሴቶችን አታውቃቸውም'' በሚል ከአንተ በላይ እናውቃታለን መታበይ) እንደኔ እንደኔ ግን ይኼን ባሏን ያገባችው፣ አሜሪካ ስለሚኖር ብቻ አይመስለኝም ከወደቅሁ አይቀር፣ ራቅ ብዬ ያው ተስፋ ያለው ነገር ላይ ልውደቅ ብላ ነው። ነፍሷ ይገባኛል፤ ማፍቀር ነበር ያቃተኝ እንጂ መረዳት አልነበረም'ኮ፡፡ አባቷን ማስደሰት ትፈልጋለች፤ በወግ በማዕረግ ማግባት። ደክመዋል፣ለፍተዋል፣ብቻቼውን አሳድገዋታል፡፡ ቢያንስ ለፍቅር ካልታደለች፣ ለራሷ የጠመመችባትን ደስታ፣ ለምስኪን አባቷ ራሷን ሰውታ ብታበረክታትስ? ወይም “የሰው ልብ ጥልቅ ጉድጓድ ነው” እንዲል መጽሐፉ ልጁን አፍቅራው ቢሆንስ? ፍቅርም ላይ ባይደርስ፣ ወዳው ሊሆን አይችልም?...ለምሳሌ፣ አሳሳቁ ደስ ብሏት...ወይም በሰው አገር ነፍሱን ለማዳን በለመደው እንግሊዝኛ፣ እንደሚያፈቅራት ሲነግራት ደስ ብሏት ቢሆንስ (ከእሜሪካ መቼስ ለክፉ ቀን የሚሆን “ዋትስ አፕም' ቢሆን አያጣ)፣ እኔ እንደሆንኩ የገዘቱኝ፣ ብትናገር ትሰቀላለህ የተባልኩ ይመስል፣ አራት ዓመት ሙሉ ስንኖር፣ አንድ ቀን እንኳን አፈቅርሻለሁ የሚል ቃል ከአንደበቴ አልወጣም፡፡ እና “አፈቅርሻለሁ'' ሲላት የተለዬ ስሜት ፈጥሮባት ቢሆንስ? (ይኼ ቃል እንዴት ውብ ነው!? ብላ) አልያም እንደሷ ዘፈን የሚወድ ሆኖ፣ የሆነ ቀን ባጋጣሚ ጭፈራ ቤት ወስዷት ደንሶ አስደምሟት ቢሆንስ? ማን ምን ያውቃል? አንዳንዴ ሰው ሰውን የሚወድበትን ምክንያት!? እንኳን ሌላ ሰው አፍቃሪው ራሱ ላያውቀው ይችላል፡፡ ፍቅርን የእኔ ብቻ ርስት ያደረገው ማነው?!

ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰው ሆኖ ከመኖር፣ አሜሪካ “ምንትስ'' ሆኖ መኖር ይሻላል፤ በሚል የቀልድ ማሳለጫ፣ እሜሪካ እንድንወድቅ በሩቅ ያነጠፉልን የምናብ ምንጣፍ ጋር ተዳምሮ ለመውደቅ፣ ትንሽ መውደድ በቂ ሊሆን አይችልም? አትውደቁ አይሉንም መቼስ፤ እዚያ ጋ ውደቁ ነው የሚሉን፣ እዚያ ብትወድቁም ነፍሳችሁ አቧራ አይነካም፣ የዶላር ምንጣፍ አለ፤ መውደቅ የትም አለ፤ ያውም በብዙ ዓይነት አወዳደቅ፣ መውደቂያው ነው ዋናው “መውደቂያዬን አሳምረው!” ይባል የለ ከነጸሎቱ። ውድቀትን ተቀብሎ ለመውደቂያው ከሚጨነቅ ማኅበረሰብ የፈለቅን እኛ፣ የተሻለ መውደቂያ ብናማትር ማነው ፈራጁ!? እኔ ግን እላለሁ፣ ቢወደቅ ቢወደቅ እንዴት አሜሪካ ይወደቃል? “ኮንክሪት” ላይ! አገር ቤት ጨፌው አይሻልም? ወድቀው የሚነሱበት! እኔን የሚል ወገን ባለበት? ...ቢበዛ አቧራን ማራገፍ ነው፡፡ የአገር መሬት...
👍42
💥💞#አልተዘዋወረችም💥💞
አሌክስ አብርሃም

ክፍል ስድስት


እስከ አሁን እዚህ ነሽ!?


ከተለያዬን ከዓመት በኋላ (በትክክል ዓመት የሞላው እንኳን አይመስለኝም)፣ አዘውትረን እንሄድበት ወደነበረው የሜክሲኮው ሬስቶራንት ሄድኩ። ለነገሩ ከዚያም በፊት ብዙ ጊዜ ሄጃለሁ፡፡ ብቻዬንም፣ ጓደኞቼም ጋር። ትዝታዬ ደብዝዞ ሌላ ትዝታ ቢጻፍበትም፣ እዚያ ቤት በሄድኩ ቁጥር ግን አስታውሳት ነበር። በተለይ እነዚያን ሳያቋርጡ ዘፈን የሚያንቆረቁሩ “ስፒከሮች” ሳይ፣ ማሂሰላምን አስታውሳት ነበር፡፡ ሳልወድ በግድ የዘፈኖቹን ግጥሞች ለማድመጥ እሞክራለሁ "ሰው ሲደሰት ዜማውን፣ ሲያዝን ግጥሙን ይሰማል" ያለው ማን ነበር!?.... የዘፈኖቹን ግጥሞች ለመያዝ አእምሮዬ ይሰንፋል፤ ያውም እኔ...ግጥም እስትንፋሴ ነው የምል እኔ። የዚያን ቀን ቤቱን ስለምወደው፣ እዚያው ሰው ቀጥሬ ነበር... ሴት ቀጥሬ። በዕድሜና በቁመት የምትበልጠኝን ሴት ቀጥሬ፡ አፏ ሥር ተለግቼ፣ ሳቋንና ወሬዋን ሰምቼ የማልጠግብላት ሴት ቀጥሬ፡፡ ስገባ ማንን አገኜሁ?...ማሂሰላምን _ ከእነባሏ...ደነገጥኩ! የእውነት ደነገጥኩ። መጀመሪያ አራት ዓመት አብራኝ የቆዬች ፍቅረኛዬን (አብሮኝ የቆዬ ጠይም ሰውነት ብል ይቀላል) የሆነ ሌላ ሰው ጋር ማዬት በራሱ ለመልመድ ጊዜ የሚወስድ የመደናገር ማዕበል ያስነሳል፡፡ ቀጥሎ ሰላም ማለት አለብኝ ወይስ የለብኝም? የሚል ጥያቄ ይከተላል....ግራ ተጋባሁ፡፡ ትንሽ ምቾት ነሳኝ- ነገሩ ...አልተነጋገርንም ሰላም አልተባባልንም፡፡ ለምን ሰላም እንዳላለችኝ ገርሞኛል፡፡ እንዲያውም እንደማታውቀኝ ዓይኗን እኔ ላይ ላለማሳረፍ ስትጥር ነበር፡፡ ይኼን ነገሯን ሳይ፣ እኔም ሰላም የማለት ዕቅዴን ተውኩትና ሩቅና ሩቅ ሆነን ተፋጠጥን፡፡ ቢያንስ ለእርሷ ጀርባዬን ሰጥቼ የምቀመጥባቼው ክፍት ወንበሮች ነበሩ፤ ግን ፊት ለፊቷ የምንተያይበት ወንበር ላይ ተጣድኩ፤ ደንብሬ መሆን አለበት፡፡

ድባቡ የሚጨንቅ ነበር፡፡ በመካከላችን እንደ ወተት የነጣ ልብስ የለበሱ ሦስት ከብ ጠረጴዛዎች አሉ። ሁሉም ጠረፔዛዎች ላይ፣ የሚያንጸባርቁ ሹካና ማንኪያዎች ተደርድረው፣ መኸላቼው ላይ፣ ብርጭቆ ውስጥ የቆሙ ደማቅ ጽጌሬዳዎች ተቀምጠዋል። በቀኝ በኩል ባሉት ሰፋፊ ወርደ ሰፊ መስኮቶች ላይ፣ ጣል የተደረጉት ነፋሱ ከውጭ ሲገፋቼው፣ መጋረጃዎቹ የእርጉዝ ሴት ቀሚስ መስለው፣ በአየር ይወጠሩና መልሰው ይረግባሉ፡፡ ነፋስ እያረገዙ ነፋስ የሚያስወርዱ መጋረጃዎች: ለመጀመሪያ ጊዜ ሳገኛት፣ እዚያ አንዱ ነጭ መጋረጃ አጠገብ ያለው ወንበር ላይ ተቀምጣ ነበር ያገኘኋት። በየጥጋጥጉ ከተሰቀሉት ስፒከሮች፣ ለስለስ ያለ ሙዚቃ ይፈሳል፡፡ ከማሂሰላም ኋላ ያለው ግድግዳ፣ በትልቅ “ካንቫስ” ላይ በታተመ ፎቶ ተሸፍኗል፡፡ ስስ ነጫጭ መጋረጃዎች፣ ከውጭ በሚ7ፋቼው ነፋስ ረጋ ብለው ይንቀሳቀሳሉ። የወይን ጠርሙዝ ነው...ዘንበል ብሎ፣ ከውስጡ ወይኑ እንደ ፏፏቴ ቁልቁል ይወርዳል....ቀይ ደም የመሰለ ፏፏቴ...ጨነቀኝ። ቀጥሎ በመጋረጃው በኩል የሚገባው ስስ ነፋስ፣ ወደ አውሎ ነፋስ ተቀይሮ ቤቱን የሚገለባብጠው፣ የጠርሙዙ ወይን ወደ ጎርፍ ተቀይሮ እንደ ባሕር ቤቱን የሚሞላው ...የሆነ እንደዚያ ዓይነት ትርምስ ነገር እንደሚፈጠር ያወቅሁ ያኽል ጨነቀኝ፡፡ ማሂ ሰላም፣ የባሏን እጆች በእጆቿ እያሻሼች በዝምታ ታዬዋለች፤ እሱን ለነካችው፣ የእጇ ልስላሴ እኔን ይሰማኛል፡፡ ባሏ ሳያቋርጥ ያወራል፤ምን እንደሚያወራት እንጃ። ገና በአንድ ዕይታ እንደማታፈቅረው አውቂያለሁ፡፡ዓይኖቼ ሴት ላይ ፈጣን ናቸው። እንኳን አራት ዓመት አብራኝ የቆየች ሴት፣ በታክሲ እየከነፍኩ በቅጽበት የማያት ሴት ፊት ላይ ያለች ተንኮል አልስትም ብል፣ ቢጋነን እንጂ የለዬለት ቅጥፈት አይሆንም፡፡ ማሂሰላምና ባሏ አልተቀላቀሉም ዘይት እና ውሃ ነበሩ፡፡ ስታፈቅር እንደምትሆነው ዓይኖቿ ዙሪያዋን አልረሱም፤ ይቃብዛሉ፤ ዙሪያዋን ትቃኛለች። ስታፈቅር እንደዚያ አይደለችም፡፡ ያፈቀረችው ላይ ብቻ የሚተከሉ ዓይኖች ነበሩ ያሏት። ምስክር ነኝ በእሷ ተፈቅሬ ነበርና፡፡ አንድ ጠባብ ክፍል፣ _ የምታፈቅረው ሰውና ትርኢት የሚያሳይ ዝሆን ተቀምጠው፣ ያንን ዝሆን አየሽው? ብትባል፣

የቱን? የምትል፤ ላፈቀረችው መሰጠት ተፈጥሮዋ የሆነው ማሂሰላም፣ እሱ ላይ ብቻ እልነበሩም ዓይኖቿ።.. አይታኛለች፣ ያውም ገና ስገባ- ከሩቅ፡፡ ከዚያ በኋላ ያለው ድራማ ነበር፡፡ ጥሩ አፍቃሪ እንጂ፤ ጥሩ ተዋናይ አልነበረችም፡፡ ባሏ ጋር በጨረፍታ እያዬኋቼው “ከሩቅ ሲያዩን ይኼን ነበር የምንመስለው?” እላለሁ፣ ለራሴ ...አሁንም ቆንጆ ናት ...አሁንም ቀለል ባለ አለባበስ ነበረች፡፡ከላይ ቀያይ አበባ ጣል ጣል ያለበት፣ ነጭ፣ ሰፊ፣ ስስ ሸሚዝ ለብሳለች ...ጡቶቿ ተለቅ አሉብኝ ...ይኼ ሰውዬ ምን አድርጓቼው ነው!? ...ምናልባት ከአሜሪካ ልኳ ያልሆነ የጡት ማስያዣ አምጥቶላት ይሆናል ማን ያውቃል? መቼስ መተዋወቅ ጊዜ ይፈልጋል፡፡ለማሂ ጡቶች ዓይኔን ጨፍኜ የጡት ማስያዣ ብመርጥ፣ ቁጥሯን አልስተውም፡፡ በዚያ ቅጽበት ያስታወስኩት ነገር፣ በአራት ዓመት ቆይታችን አንድም ስጦታ ሰጥቻት አለማወቄን ነው። በአጋጣሚ ከመደርደሪያው ላይ መጽሐፍ አንስታ ልውሰደው? ካለችኝ ውሰጅው እላታለሁ፤ በቃ። ሸሚዟን ሳይ ድንገት ከስንት ጊዜ በኋላ እቤቴ የረሳችው “የውስጥ ልብስ” ትዝ አለኝ። ከጠረጴዛው ስር እግሯ ይታዬኛል፤ የአንድ እግሯን ጫማ አውልቃ በጫማዋ ትጫዎታለች፤ የቆዬ ልማዷ ነበር። ጸጉሯ ግን ተቀይሯል፣ እንደ በፊቱ በቼልታ አለቀቀችውም፣ በሥርዓት ተሠርቷል። ሲመቼው እንደሚሆነው፣ ጥቁርና የሚያብረቀርቅ ጸጉር፡፡ እንዲህ ጠቁሮ ዓይቼው አላውቅም፤ ዐሥር ጊዜ ጸጉሯን ትነካካለች፡፡ ከሴቶች አጥብቄ የምጠላው ባሕሪ! ሳውቃት እንደዚያ አልነበረችም፡፡ ዓይኖቼ እጅ ሆነው ልስላሴዋ እንዲሰማኝ አድርገውኛል-ሙቀቷም...ሰውነቴ ሲነቃቃ ይሰማኛል፡፡ ፊት ለፊቷ ነው የተቀመጥኩት- ከባሏ ኋላ...መልኩ አይታዬኝም፤ ሁለት ጆሮዎቹ ከርፈፍ ያሉ፣ ከኋላ እንዲሁ ጎልማሳ የሚመስል፣ጸጉሩ ላይ ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት፡፡ በትከሻው ላይ አሻግራ ታዬኛለች፣ እንደምታዬኝ ሳላያት አውቃለሁ፡፡ አስተናጋጁ ሊታዘዘኝ መጣ፤ ፊቱ ላይ የእፍረት ፈገግታ አለ፡፡ ያውቀኛል‐ያውቃታል፣ ያውቀናል፡፡ ትንሽ እንደምቆይ ነገርኩት…“ለምን ትቆያለህ? መጥታለች'ኮ!" አለማለቱም ጨዋ ሆኖ ነው፡፡ እስቲ የሚመጣውን ጉድ ልይ! ብሎ ነው መሰል

ትሪውን አቅፎ የታፈነች ዓይንአፋር ፈገግታው ስትከስም አንድ ጥግ ቆመ (እንዲህ ትርኢት ለማዬት ከጓጓ፣ለምን ረዘም ረዘም ያሉ ቢላዋዎች ከወጥቤት አምጥቶ! አንድ ለእኔ፣ አንድ ለባሏ ሰጥቶ ፍልሚያ ጀምሩ አይለንም?) አስተናጋጁ እኔጋ ደርሶ ሲመለስ፣ ድንገት ማሂሰላም ጋር ዓይንለዓይን ተገጣጠምን፡፡ ፊቷ ብስጭትና ጉጉት ሲያንዣብብበት ታዘብኩ። የተበሳጨችበትን ለመረዳት ትንሽ ደቂቃዎች ነበር የወሰደብኝ። እሷ ጋር እዚህ ቤት ስንመጣ ቀድሚያት ከደረስኩ፣ ምንም ነገር ሳላ'ዝ እንደምጠብቃት ታውቃለች፡፡ ምንም አለማዘዝ የሆነች ሴት የመጠበቅ ምልክቴ ነው። ምክንያት ኖሮኝ ሳይሆን፣ ደመነፍሳዊ ልምድ። ጨራርሰው ስለነበር፣ ባሏ የወንበር መደገፊያው ላይ ያንጠለጠለውን ጃኬት ሊያነሳ ዞር ሲል፣ የሆነ ነገር አለቸውና መልሶ ተቀመጠ፡፡ አስተናጋጁን በምልክት ጠርታ ቡና አዘዘች፤ ከሩቅ በከንፈሯ እንቅስቃሴ ነው ቡና ማዘዟን ያወቅኩት
👍56🤔2