አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የመልስ_ጉዞ
:
ክፍል- #አንድ

:
:
ደራሲ -ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
:
ፍእማዊ መንግስታዊ አስተዳደር ፤ፍፁማዊ ማህበረሳብ አወቀቀር፤ፍፁማዊ የተፈጥሮ ሚዛኗን የጠበቀች ሀገር..በዩቶፕያ ፅንሰ ሀሳብ የታነፀች ማለት ያቺ ነች ፡፡በነብያት አዕምሮ ውሰጥ ከዘመናት በፊት ተፀንሳ ትንቢት የተነገረላት ሰማያዊ የመኖሪያ ስፍራ በነአፍላጦስ ምናብ የተፀነሰችና በምድር ለመገንባት የተመኙላት ምድራዊ እንከን አልባ የሰለጠኑና የበቁ ማህበረሰቦች የሚኖሩባት ፤በፍፅም ፍትሀዊነት እና በጋራ ህግ የሚመራ መንግስት ያላት፤ ለገነት የቀረበ ልምላሜ ኖሯት አንድ ቀን በጋራ ስምምነት ፍፅማዊ ደስታ የምታመነጭ ተደርጋ የምትመሰረት ምድራዊ ከተማ ….
ታዲያ ይህቺ የአለማዊው እሳቤ እና የመንፈሳዊው ትንቢት ቀላቅላ የያዘች ዩቶፐያ ከወዴት ነች?የሀይማኖት ነብያት እንደሚሉት በሰማይ ከሞት ቡኃላ ባለው ህይወት የሚያገኞት ወይስ ሰው የልዕለ ሰብነትን ዙፋን ሲቆናጠጥ ፍፁም ፍትሀዊ፤ ፍፁም ዘመናዊ ብቃት ባገኘ ጊዜ በብቃትና በጥበቡ እዚሁ ምድር ላይ የሚመሰርታት….?
ወደ ዩቶፕያ መሄጂያ መንገዱ በየት ነው…ዩቶፕያስ የት ነው እውን ሊሆን የሚችለው ….?
እግዚያብሄር መላክ በምስራቅ በኤደን የአትክልት ስፍራ አዘጋጀ ያበጀውንም ሰው በዛ አኖረው፡፡እግዚያሄር አምላክ ለዓይን የሚያስደስት ለመብልም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ በምድር አበቀለ፡፡ በአትክልቱ ቦታ መልካም የህይወት ዛፍ ነበር፡፡እንዲሁም መልካምና ክፍውን መለየት ሚያስችል የዕውቀት ዛፍም ነበር፡፡የአትክልት ስፋራ የሚያጠጣው ወንዝ ከዔደን ይፈስ ነበር ፡፡ከዚያም በአራት ተከፍሎ ይፈስ ነበር፡፡የመጀመሪያው በምድሩ ወርቅ የሚገኝበት በሐዊላ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈሰው የፊሶን ወንዝ ነው፡፡ኤውላጥ ምርጥ ሆነ ወርቅ መልካም መአዛ ያለው ከርቤና የከበረ ድንጋይ የሚገኝበት ምደር ነው፡፡ሁለተኛው በኢትዬጳያ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈስው ግዬን ወንዝ ነው፡፡ሶስተኛው ከአሶር በስተምስራቅ ሚፈሰው የጤግሮስ ወንዝ ሲሆን አራተኛው የኤፍራጠስ ወንዝ ነው፡፡ (ዘፍጥረት ም 2 ቁጥር 8-14 )
ለመሆኑ ይሄስ ስፍራ የት ነው?፡፡የአዳምና ሄዋን ቀደምት መኖሪያ ስፍራ ..?የእውቀትና የዘላለም ፍሬ የሚበቅልበት ሚስጥራዊ ስፍራ…?በአዳምና ሄዋና የተወከሉት የመጀመሪያዎቹ የሰው ልጆች በፈጣሪያቸው ላይ ከብልሁ እባብ ጋር የመከሩበት ፤የመከሩበት ብቻ ሳይሆን የዶለቱበትም ስፍራ የት ነው?፡ከዛስ እርቃናቸውን እንደሆኑ የተገለፀላቸው…?ያን ሰፊ እፍረታቸውን የጋረዱበት ቅጠልስ ከየትኛው ስፍራ ከየትኛውስ ዛፍ ላይስ የተገንጥለው ይሆን? …ከዛስ ወደየት ተባረሩ ?እንዚህ መሰረታዊ ጥያቄዎች ናቸው፡፡የመልስ ጉዞው ወደዛ ነዋ ፡፡አያቶቾ አዳምና ሄዋን ወደተባሩበት ስፍራ ወደ ሀገረ ገነት ...
ይህቺ ሀገር ኢትዬጵያ ነች፤ ይህቺ ሀገር የአያቴ ህልም ነች…ህልሙ ግን በከፊል እንኳን እውን ሳይሆን እድሜ እየተጫጫነው ነው፡፡ቢሆንም ለዚህ አንድ ዘዴ ዘይዷል …ህልሙ ህልሜ እንዲሆን አድርጎል…እንደሱ እንድመኝ ….እንደእሱ እንዳስብ…. ግን ይሄን ህልም እውን ለማድረግ እኔ ምን ማድረግ አለብኝ…ከሚስቴ ጋ እስክገናኝ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም..
አሁን ግን ወደ እዛች ስፍራ ጉዞ ጀምረናል ፡፡እኔና ሚስቴ ፡፡ሁለታችንም የተለያየ የግል ዓላማ አለን ፡፡ግን የየግል አላማችን ከተሳካን ቡኃላም የጋራም አንድ አላማ አለን፡፡ አዎ እንብርት የሆነውን ስፍራ ካገኘን ቡኃላ ዩቶፐያችንን በስፍራው ደግመን እንገነባለን..እንዴት አድርገን.? ወደፊት አብረን የምናየው ይሆናል፡፡
አሁን ወደዋናው የታሪኩ ክፍል ጠልቄ ከመግባቴ በፊት እራሴን ላስተዋውቃችሁ …መቼስ ታሪኬን ስትሰሙ አንዳንዶቻችሁ የተዛባ አዕምሮ የፈጠራቸው የእድሜ ልክ የቀን ቅዥቶች ልትሉት እንድምትችሉ እገምታለው፡፡ይሁንና የእኔን እውነት ነግራችሆለው፡፡ ሳልኩልና ሳልቀባባ ጥሬ እወነቱን ብቻ፡፡ማመን ያለማመን የእናንተ ፋንታ ነው፡፡ግን ከእኔ ጋር ወዳጅነት መስርታችሁ የምነግራችሁን ለማድመጥ በጣም ትዕግስተኛ እና አስተዋይ መሆን አለባችሁ፡፡ምክንያቱም የሆነ ርዕስ ተከትሎ የነገሮችን ቅደም ተከለተልን ጠብቆ ታሪኩን ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ያጫውተናል ብላቹ ምትጠብቁ ከሆነ ከአሁኑ እርማችሁን አውጡ ፡፡እና ንባባችሁን እዚህ ጋር አቋርጡ፡፡
የገዛ የራሴን ታሪክ ለሌላ ሰው እንዴት ማውጋት እንዳለብኝ መወሰን ስልጣን ያለኝ እኔ ብቻ ነኝ ፡፡ስለዚህ ዘባራቂነቴን ካልወደዳችሁት ምንም ልረዳችሁ አልችልም፡፡ዘባራቂነቴ የነፃነቴ መገለጫ ምልክት ነው፡፡ምናቤ በማንኛውም የስርዓትና የደንብ ሰንሰለት አለመጠፍነጉን የሚያሳይ ልቅ መጋለቢያ ሜዳ አይነት ነው፡፡ወይንም በሆነ ቦታ የታጠረ የኩሬ ውሀ ሳይሆን የአባይ አይነት ሀገር ተሸጋሪ ወንዝ ፡፡አዎ የእኔ አዕምሮ እንደዛ ነው፡፡ለነፍሴ ማደሪያ በተሰጠኝ አካል ያልተወሰነ እንዳምንበት ከቤተሰቤ በውርስ በተሰጠኝ ሀይማኖታዊ ዶግማ ያልታጠረ.. በተወለድኩበት ሀገር ድንበር ያልተከለለ….በተፈጠርኩበት ምድር የልተገደበ…እንደዛ ነው ምናቤ… እንደዛው ነው ሀሳቤ …..
እና ታዲያ እንዴት ሆኖ ነው ካልከኝ በዘመን ሂደት ሰው ያው ሰው ነውና መጎዝና አዲስ ነገር ማሰስ ተፈጥሮአዊው ባህሪው እንደመሆኑ መጠን አካባቢውን እየለቀቀ ሲያፈገፍግ ሲዋለድ ሲራባ ሲያፈገፍግ በሚሊዬን ዓመት ሂደት ውስጥ መቶች ውስጥ አለመን አዳረሰና በዚህ ሂደት ውስት ከተፈጥሮ እና እርስበርሱ በሚያደርገው ትግልና ፍትጊያ አእምሮውን እያዳበረ አዕምሮ ሲዳብር ደግሞ ለአካባቢውም ሆነ ለራሱ የነበረው እይታ እየተቀየረ የማምረቻ መሰሪያዎችን እየፈለሰፈ ንግድና እየጀመረ ሲመጣ መልሶ ወደ መነሻው ማየት ጀመረ…ኢትዬጵያ የሰው ዘር ተፈጥሮ የተበተነባት ምድር መልሶም አንድ ቀን የሚሰበሰብባት፡፡

💫ይቀጥላል💫

Like 👍👍 ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍5