አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


....የወይዘሮ ዘነቡና የታፈሡ ውይይት በዚህ መልኩ እየተከናወነ ባለበት ሰአት
ሸዋዬ አልጋዋ ላይ ቁጭ ብላ በሁለት እጇ ጆሮ ግንዶቿን ጠፍራ በመያዝና አተርትራ በማሰብ ላይ ናት። ታፈሡንና ወይዘሮ ዘነቡን እያሰበች ልክ በመሀላቸው ቁጭ ብላ እንደምታዳምጣቸው ዓይነት ስለ እሷ ሲያወራ በሀሳቧ "ቀንታ ነው እኮ ተቀጥላ ይስሟታል!
ሰው እንዴት በእህቱ ይቀናል! አረ የሷ የብቻው ነው ። አስቻለውን እንደሆነ አታገኘው ምን ያስለፋታል?» የሚሏት ይመስላታል። ወይዘሮ
ዘነቡ ታፈሡን ሲያሞካሹ!
ለአስቻለውና ለሄዋን ለሔዋን ፍቅር መልካም ሲመኙ እሷ በእሳቸው ፊት የምታሳየውን ድንጋጤና የብስጭት ስሜት ለታፈሡ ዝርዝር አድርገው ሲያወሩባት ሁሉ ይታያታል፡፡ በዚያ ልክ ቅጥል ንድድ ትችላለች፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ ግቢያቸው ውስጥ እንዴግቡ ወደ ቢታቸው ጎራ ሳይሉ
በቀጥታ ወደ ጓሮ ዞረው ወደ ሸዋዩ ቤት አመሩ። ሸዋዬ ድንገት የሰው ኮቴ ሰምታ ከአጎነሰችበት ቀና ስትል ወይዘሮ ዘነቡ ብቻቸውን ሲመጡ አየቻቻው። ወደ
ኋላቸው ዓይኗን ስታማትር ሔዋን የለችም። እንዴ አለችና እማማ ዘነብ! » ስትል ጠራቻቸው ገና ከሩቅ ሳሉ፡፡
«ወይ»
«አልተሳካሎትም?»
ወይዘሮ ዘነቡ ዝም ብለዋት ወደ ቤት ገቡና ዱካ ላይ ቁጭ ካሉ በኋላ ትሰሚያለሽ የኔ ልጅ!» አሏት ቀልብና ስሜቷን ሰብሰብ ለማድረግ፡፡
«እሺ» አለቻቸው በጉጉትና በፍርሀት ስሜት ተውጣ፡፡
ጓደኛሽም እህትሽሃም መልካም ሰዎች ናቸው። እህትሽ ጥፋቷን አምናለች፡፡ጓደኛሽም ተቆጥታለች። አንቺ የፈለግሽውን እርቅ እነሱ የበለጠ ፈልገውታል፡፡
እውነተኛ እርቅ ደግሞ አፍን ሳይሆን ልብን ከፍቶ ስለሆነ፣ ለዚህ ብርቱ ጉዳይ አንቺም ስትዘጋጂ እደሪና ነገ ሁለታችንም አብረን እንሂድና አንቺንም ከጓደኛሽ፣ እህትሽንም ከአንቺ በማስታረቅ ሁሉንም ነገር ፈጥሠን እንመጣለን። ከዚያ በኋላ እህትሽን ይዘናት እንመጣለን፡፡» ከማለት ውጭ ሌላ ምንም ሳይጨምሩ
ከተቀመጠበት ብድግ ብለው በይ ደህና እደሪl» ብለዋት ውልቅ አሉ፡፡
ሸዋዬ ድንግጥ አለች፡፡ እንዴ አለች በሆዷ፡፡ በዓይኗ ወይዘሮ ዘነቡን
እየተከተለች ይቺ አሮጊትና ያቺ ታፈሡ የምትባል መናጢ ምን ተማክረው ይሆን?' በማለት ብቻዋን ታወራ ጀመር። ሄደች በሀሳብ አሁንም ታፈሡ ከኔ ጋር
ታርቀ ሰላ እያለች ወደ ቤቴ በመምጣት የጀመረችውን ልትጨርስ!? እኔ ሳላውቅ
ከዚች አሮጊት ጋር ገጥማ ውስጥ ለውስጥ ሊያርዱኝ? በፍጹም ይህ የማይሆን ነው። ከታፈሡ ጋር እርቅ ብሎ ነገር የለም፡፡ ብቻ ያቺ ሰላቢ እህቴ እንደምንም ብላ
በእጄ ትግባልኝ፡፡ ይህ እንዲሆን የግድ ከታፈሡ ጋር ታረቂ ብባልም ለዚያች ቀን ብቻ በማግስቱ ግን አፈርሰዋለው በቃ።
ሸዋዬ ምሽቱን ሁሉ ስለዚሁ ስታስብ ቆይታ ሌሊቱንም ሳትረሳው መልሳ መላልሳ ስታመነዥገው አደረች። ፍላጎቷ አንድ! ሔዋንን በእጇ ማስገባት፤ ፉከራዋም እንድ፤ ከታፈሡ ጋር ፈጽሞ ከልብ ላለመታረቅ። ሀሳቧ ሁሉ ከዚሁ ሳይርቅ ሌቱ ነግቶ በጠዋቱ ፈረቃ ስራ ገባች፡፡
ከሰዓት በኋላ በታፈሡ ቤት የተያዘው የቀጠሮ ሠዓት ደረሰና ከወይዘሮ ዘነቡ ጋር ወደ ታፈሡ ቤት ጉዞ ጀመሩ።
«እማማ ዘነብ!» ስትል ጠራቻቸው ከጎናቸው ሆና እየተራመደች
«ወይ»
«ለመሆኑ ታፈሡ እኔን ምን አደረገችኝ እለችዎት?»
«እረ እሷ እቴ! ምንም ያለችው ነገር የለም::»
«ታዲያ ከእሷ ጋር መታረቁ ለምን አስፈለገ?»
«በአንቺ ሆድ ውስጥ ያለ ነገር ሊኖር ይችላል ብዬ ነዋ!»
«እሱማ ብዙ አለ። ግን ዝም ነው የምለው፡፡»
«ያማ ቂመኝነት ነው:: የነገር ብዛት ባይጠቅምም የቂም ቋጠሮ ካልተፈታ እርቅ አይኖርምና ቅር ያለሽን ነገር አጠር አርግሽ መግለጥ ይኖርብሻል፡፡»
«እኔና እሷን ያቀያየመን እኮ ይሄው የእህቴ ጉዳይ ነው::»
ወይዘሮ ዘነቡ ድንገት ቁጥት አሉ፡፡ «የእህትሽ ጉዳይ የአንቺና የእሷ ጉዳይ አይደለም የራሷ ብቻ ነው:: በእሷ አታሳቡ፤ ተዋት!! አሉ ጠበቅ ባለ አነጋገር፡፡
«እንዴት እማማ ዘነበ? እኔማ የእህቴ ጉዳይ ያገባኛል::»
«ስለምታበያትና ስለምታጠጫት ተሆነ ተሳስተሻል። ሆድ የትም ይሞላል፡፡
ጭንቅላት ግን ነጣነት የሚያገኝበትን መንገድ ይፈልጋል፡፡ አትሞኚ »
«መረን ልቀቂያት ነው የሚሉኝ!»
«ተይ አንቺ ልጅ! ኋላ እንዳልጠላሽ! እህትሽን እንኳን አንቺ እኔ አውቄአታለሁ፡፡ ሥነስራት ያላት ጨዋ ናት፡፡ የሆዷን አይታ ድንግል ያን የመሰለ ጨዋ ልጅ ሰጥታተለች:: እንደኔ ቢሆን በእነሱ መሀል ባትገቢ ጥሩ ይመስለኛል፡፡»
አሏት ፈርጠም ባለ አነጋገር፡፡
ሽዋዬ ወይዘሮ ዘነቡን ክፉኛ ጠላቻቸው፡፡ ዛሬ ሔዋንን በእጇ የማስገባት ዓላማ ባይኖርባት ኖሮ በዚያ ሠዓት ወደ ቤቷ ምልስ ብትል በወደደች ነበር፡፡ ከዚያ
በኋላ ፀጥ እንዳለች ከታፈሡ ቤት በር ላይ ደረሱ፡፡
የታፈሡ ቤት እንግዳ ለመቀበል ተዘጋጅቷል። ወለሉ ተወልውሎ- ፏ ብሏል::ከሰል ተያይዞ የቡና ዕቃዎች ቀርበዋል። ታፈሡም እምር ብላለች። ቀላ ያለ ጉርድ
ቀሚስ በነጭ ሽሚዝ ለብሳ ሀብሏ በደረቷ ላይ እንደ ፀሐይ ያበራል፡፡ ያን ረጅም የጥቁር ዞማ ፀጉሯን ጎንጉና በጀርባዋ ላይ ለቃዋለች፡፡ ወይዘሮ ዘነቡ ሸዋዬን አስከትለው ወደ ቤት ራመድ ሲሉ ፈልቀቅ ባለ ፈገግታ ተቀበለቻቸው፡፡ በዚያ
ሠዓት ሔዋን ድንግጥ ብላ ወደ ጓዳ ስትሮጥ ወይዘሮ ዘነቡ ተመልክተዋት ኖሯል።
«ዛሬ ፈርቶ መደበቅ፣ እኩርፎ መንጋደድ የለም፡፡» አሉና መሀል ወለል ላይ ቆመው «በሉ እናንተ ቀድማችሁ በይቅርባይነት ያለ ወቀሳ ተሳሳሙ፡፡» አሏቸው
ታፈሡና ሸዋዬን ግራና ቀኝ አየት አየት እያረጉ፡፡ ታፈሡ ሁለት እጆቿን ዘርግታ ወደ ሸዋዬ ጠጋ በማለት «ሸዋዬ!!
ከአጠፋሁ ይቅርታ!» ብላ እንገቷን እቅፍ አድርጋ በመሳም ጨመጨመቻት፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ አጠገባቸው ቆመው «እሰይ እሰይ እልልል…» አሉ፡፡
ወይዘሮ ዘነቡ ታፈሡ በዚያ ዓይነት ፈገግታ እየሳመቻት ሳለች የሸዋዬ
ፊት ግን ፈታ አለማለቱ እያናደዳቸው ነገር ግን የጀመሩትን ለመጨረስ ሲሉ፡ «በይ ያቺንም አበባ ጥሪልኝ፡፡ በእህቷ እግር ላይ ትወደቅ» ብለው ሔዋን ወዳላችበት ጓዳ አይናቸውን ወረወሩ።
«አንቺ ሒዩ» ስትል ታፈሡ ተጣራችና ቀጥላም ነይ እማማ ዘነብ ይፈልጉሻል» ስትላት ሔዋን ሽቁጥቁጥ እያለች ከወደ ጓዳ ብቅ አሉች፡፡ ለአንዴም ቀና ሳትል አቀርቅራ በመራመድ ከመሀላቸው ደረሰችና ከሸዋዬ እግር ላይ ወደቀች፡፡ወይዘሮ ዘነቡና ታፈሡም እልልእልል» በማለት ዕርቁን አደመቁት ።
ወይዘሮ ዘነቡ አሁንም ሆዳቸው በገነ ሔዋን ያን ያህል በእግሯ ላይ
ስትደፋ ሸዋዬ ግን ለመግደርደር ስትል እንኳ ቀና እንድትል አልጋበዘቻትም።በሆዳቸው ምኗ ድንጋይ ናት በማሪያም አሉ፡፡
የእርቅ ስነ ሥርዓት በዚህ ሁኔታ ተጠናቆ ሔዋን ብቻ ወደ ጓዳ ፈጥና ስትመለስ ሶስቱም ሶፋ ላይ ቁጭ አሉ የታፈሡ ሠራተኛ ቡና መቁላት ጀምራለች
«ሰላም ነሽ ሸዋዬ!» አለቻት ታፈሡ ቀድማ ፈገግ ብላ እያየቻት»
«እግዜሔርን አይክፋው»
«ሰሞኑን እንደተበሳጨሽ ይገባኛል ሔዩ አጥፍታለች» አለቻት ታፈሡ
👍131