አትሮኖስ
281K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
479 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ


...ሽዋዬ ከቤቷ ስትወጣ የት መሄድ እንደነበረባት አቅዳ አልነበረም። ሰሞኑን ነገሮች ሁሉ ረገብ ብለው ስታይ ትንሽም ቢሆን ቀዝቀዝ ብላ የነበረ ቢሆንም የዛሬው አስቻለው ቤቷ ድረስ መምጣት ግን እሳት ለኩሰባት ንዴቷን ቀስትሶባታል፡፡
ከወጣችም በኋሳ ጅው ብላ መሄዷ አስቻለውና ሔዋን ብስጭቷን አይተው ለወደፊቱም እንዲፈሩ ማድረግ ነበር፡፡ ያ ሁሉ ሆኖ አሁንም ጉዞዋን ወደፊት
ቀጠለች። የዲላ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱን ወደ ቀኝ በመተው ሂዳ ሂዳ ወደ ኳስ ሜዳው ደረሰች። በሜዳው እሻግራ ፊት ለፊት ስትመለከት የዲላ ሆስፒታል ለጥ ባለ ሜዳ ላይ ተንጣሎ ታያት፡፡ ያኔ ባርናባስ ወየሶ ትዝ አላት፡፡
««አሃ» አለኝ ቀጥ ብላ በመቆም ብቻዋን እየተነጋገረች፡፡ አሁንም ለራሷ
«ለምን ባርኒ ጋ አልሄድም?» አለች። ባርናባስን ስታቆላምጠው ባርኔ እያለች ነው፡፡
ለኳስ ሜዳ ተብሎ የተናደውን ገደል ተንደርድራ ወረደችው፡ ሜዳዋንም አቋርጣት አለፈች። እዚያም አልፋ ከዲላ ወደ ሞያሌ የሚወስደውን የአስፋልት
መንገድ ተሻገረች:: ብላ ብላ የቆፌን የኮረንኮች መንገድ ትውረገረገበት ጀመር፡፡
ደግነቱ ከቤቷ የወጣችው ትምህርት ቤት ስትሄድ የለበሰችውን ልብስ እንደለበስች
ስለሆነ አለባበሷ ወዴትም ብትሄድ አያሳፍራትም፡፡ ከቦርሳ በስተቀር የሚቀራት ነገር የለምና :: አንገቷ ላይ ቀላ ያለ ቡኒ ቀለም ያላት ስካርፍ አጣፍታለች፡፡
ለሆስፒታሉ እንግዳ ናት:: ታማ ልትታከም ወይም ታማሚ ልትጠይቅ እንኳ ገብታበት አታውቅም፡፡ ይሁን እንጂ ሆስፒታሉ አደናጋሪ ሁኔታ የለውም፡፡
ህንፃዎቹ በአንድ አካባቢ ችምችም ብለው የተሰሩ ናቸው። ቀሪው ደግሞ ወለል ያለ
ሜዳ፡፡ ቀጥታ ወደ ህንጻዎቹ ስትጠጋ የተጓዘችበት መንገድ ከድንገተኛ መቀበያ ክፍሎች አካባቢ አደረሳት።
ሰዓቱ ወደ ስምንት ተኩል ገደማ ይሆናል። በርካታ ህመምተኞት በአግዳሚ ወንበሮቻ ላይ ተቀምጠው ወረፋቸውን ይጠባበቃሉ፡፡ የህመምተኞቹ ጀርባ ቆም ብላ ወደ ቀኝ አቅጣጫ ስትመለከት ረጅም የመተላለፊያ ኮሪደር ታያት፡፡ ጎርደድ ልትልበት አስባ ጥቂት ከተራመደች በኋላ አሁን ወደ አስተዳደር አገልግሎት ሃላፊ» የሚል የቢሮ መለያ አነበበች፡፡

«አሃ! የባርኔ ቢሮ ይኸ መሆን አለበት» አለችና ቆም ብላ ወደ በሩ ስትመለከት ከኋላ በል የሰው እጅ ትክሻዋ ላይ ቸብ አደረጋት፤ ባርናባስ ወየሶ፣
ሽዋ'ዩ ድንግጥ አለች ። «እንዴ! አለህ እንዴ?» ስትል ጠየቀችው ምን እያለች እንደሆነ ለሷም ሳይገባት።
«የሸዋ ዛሬ ከየት ተገኘሽን»አለና ባርናባስ እጇን ጨብጦ እንደገና ደረት ልደረት ተሳሳመ።: ባርናባስ ሸዋዬን ሲያቆላምጥ የሸዋ እያለ ነው፡፡
«ጉብኝት መጥቼ::» አለችው ሸዋዬ ሳቅ እያለች።
ጥሩ ነዋ! የሚጎበኝም ሞልቷል የሚያስጎበኝም አለ።» አላት ባርናባስ እጁን ትክሻዋ ላይ ጣል አድርጎ በረጅም ቁመቱ ቁልቁል እየተመለከታት፡፡
«አለፈልኛ! ኪኪኪኪ ……!
እኔ ጋ ነው የመጣሽው?» ሲል ጠየቃት እሷንም ቢሮውንም ተራ በተራ እየተመለከተ፡
«አይ!» ሽዋዬ ተሽኮረመመች።
«ቢሮዬ አጠገብ ቆመሽ ሳገኝሽ ጊዜ እኮ ነወ፡፡ ጎራ በያ፣ ሻይ በና ልበልሽ»
«በዚህ ሙቀት ሻይ ቡና?»
«ለስላሳም ይኖራል»::አለና ባርናባስ እጇን ይዟት ወደ ቢሮው አመራ::
በሽዋዬ ዓይን የባርናባስ ቢሮ ልዩ ነው፡፡ ስፋቱ፣ ጽዳቱ፣ የመስኮቶቹ
መጋረጃዎችና የወለለ ምንጣፍ ዓይን ይማርካሉ፡፡ የመጋረጃው ቀለም ነጣ ያለ ብርቱካናማ ነው ለቢሮው ልዩ ብርሃን ሰጥቶታል፡፡ እንግዳ መቀበያው ጠረጴዛ
ስፋትና የወንበሮቹ ብዛት አስደነቃት፡፡ በቢሮው የግድግዳ ጥግ ዙሪያ ተጨማሪ ወንበሮችም አሉ፡፡ ያቤሎ ጤና ጣቢያ ውስጥ በነበረበት ጊዜ በአንድ ጠበብ ባለች ክፍል ውስጥ ከአንድ ሜትር የማትበልጥ ጠረጴዛውንና የሚቀመጥባትን ደረቅ
ወንበር አስታውሳ ስታወዳድር አሁን ግን ገነት ወስጥ እንደገባ ቆጠረችው::
«አንተ! ቢሮህ ግን እንዴት ያምራል!?» አለችው የቢሮውን ዙሪያ በዓይኗ እየቃኘች፡፡
ከዚህ የበለጠ ስንት ዓይነት ቢሮ አለ እባክሽ! ደሞ ይኸ ቢሮ ሆኖ?» አለና ወንበር ሳብ አድርጎ እንድትቀመጥ ጋበዛት።
«ጡር አትናገር»
ባርናባስ በእንግዳ መቀበያው ጠረጴዛ ላይ ከሸዋዬ ፊትለፊት ቁጭ አለና በደወል ተላላኪ ጠርቶ ለእሱ ቡና ስሸዋዬ ለስላሳ አዘዘ
«ይኸ ሁሉ ወንበር ምን ያረጋል?» ስትል ጠየቀችው፡፡
ህእ! የባለ ስልጣን ቢሮ እኮ ነው፣ ስንት ዓይነት ስብሰባ የሚካሄድበትና ውሳኔ የሚሰጥበት። አለና ባርናባስ በተቀመጠበት ላይ ፈነስነስ አለ።
በምን በምን ጉዳይ ላይ ትወስናለህ?»
«በፖለቲካ በትይ፥ በአስተዳደር ጉዳይ ብትይ፣ በደረጃ ዕድገት፣
በዲስፕሊን.…ወዘተ!» አለና ሽዋዬን ፈገግ ብሎ እያየ በቀልድ ዓይነት አነጋገር፣
«በፍቅር ላይ ብቻ ነው መወሰን ያቃተኝ!» አለና ሃሃሃሃ…» ብሎ ለራሱ ስቆ ሸዋዬንም አሳቃት፡፡
«ስትልን» አለች ሽዋዪ በቅንድቧ ስር እያየችው፡፡
«የምወዳት ሴት እንዳትጠላኝ አድርጌ መወሰን! ሃሃሃሃ….
«ውይ አልቀረብህም»
"ያን ማድረግ ብችል ኖሮ አንቺ መች ታመልጪኝ ነበር» አለና እንደ ቁም ነገር አድርጎ ግን የሸዋ፡ ይህን ያህል ወራት ዲላ ውስጥ ስትኖሪ እንዴት ወደ ቢሮው ሄጄ ልጠይቀው አላልሽም?» ሲል ጠየቃት፡፡
«ሆሆይ! ደሞ የሰው ባል ለአለፈውም ይቅር ይበለኝ፡፡ ያም ቢሆን ሳላውቅ ያደረኩት ስለሆነ ኩነኔው የአንተ ነው፡፡» አለችና የቀረበላትን ሚሪንዳ ጎንጨት
አለች፡፡
ባርናባስ በስጨት እንዳለ ዓይነት እጁን ወንጨፍ እያረገ የሸዋ ደሞ ዝም ብለሽ ነው፣ ይኸን ሚስት፣ ድስት፣ ትዳር ምናምን የምትይውን ነገር ለምን አትተይም? ፍቅር በትዳርና በስማኒያ ይገለጽ መስለሽ እንዴ?” አላት ቡናውን
እያማሰለ፡፡

«ብታርፍ ይሻልሃል» .
«በተለይ በአንቺ ነገር መቼም ቢሆን የምቆርጥ አይመስለኝም።
ግን ባለቤትህ ደህና ናት?»
«ለራሷ ትኖራለች።
«እዚህ ገባህ፣ ከዚያ ወጣህ አትለኝም!»
«መረን ለቃሃለቻ!»
«ኧረ ዛሬ ከየት ተገኘሽ የሽዋ? እስቲ ስለ አንቺ እንጨዋወት?» ብሎ ቡናውን ፉት አለ፡፡
«አንተን ልጠይቅ ኪኪኪኪ...»
«ጎሽ የኔ ወለላ! አንቺ እኮ ዱሮም ቁም ነገርኛ ነሽ ሰውየው እኔ ሆኜ እንጂ» ብሉ ነገሩን ተወት ሲያደርገው ሽዋዬ ቀጠላች።
«ባትሆንስ?»
«ልብ ቢኖረኝ ኖሮ እግርሽ ላይ ወድቄ ይቅርታ መጠየቅ ነበረብኝ። ግን ዛሬነገ ስል» አለና ንግግሩን ቆረጥ አድርጎ አሁንም ቡናውን ፉት አለ፡፡
«ደሞ እንደገና?»
«የቆየ ነገር እኮ ሲታደስ ከበፊቱ ይበልጣል። ሃሃሃሃ…»
«ይልቅስ ስለ መጣሁበት ጉዳይ ልጠይቅህ!»
«ምን ልርዳሽ?»
«አንድ ሴት፣ በተለይ ልጃገረድ ማስወረድ አስማስወረዷን በሀኪም ምርመራ ማወቅ ይቻላል?» ስትል ጠየቀችው፡፡
«ሀኪሞችን አነጋግሮ መረዳት ይቻላል። ግን በዚህ ዙሪያ ምን ችግር ገጠመሽ?» ሲል ጠየቃት።
«በእናትህ ባርኔ ዶክተሮችን ጠይቅና ንገረኝ!»
«ማነጋገር እችላለሁ!»
«ይገርምሃል! በአንዲት እህቴ ገዳይ ተቸግሬአለሁ፡፡»
«አስወርዳ?»
«መሰለኝ፡፡»
«በአገር ባህል ወይስ በሀኪም?»
«አረ የእናንተ ሰራተኛ በሆነ ሰው!»
ደሞ የምን ባህል አመጣህ ያን ቤሆን ራሴ ተከታትዩ ለሕግ አቀርበው አልነበር? ያስቸገረኝ ብላ ሸዋዬ የተበሳጨች ለመምሰል ራሷን ወዘወዘች።
👍2