አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
491 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ያልታበሱ_እንባዎች


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በአሰፋ_በቀለ_ገየሱስ

..የሞተ ተጎዳ እንዲሉ ከአደጋው መድረስ በኋላ ሳምንት እንኳን ሳይሞላ ሀዘን በረድ፤ ቀዝቀዝ እያለ ሄደ። ድንኳኖች ሁሉ ተነቃቅለው ወደ መጋዘን ተመለሱ፡፡ ሀዘንተኛ ሁሉ ወደ ሥራ ገባ፡፡ ከሩቅ የመጣ ሁሉ ወደየመጣበት ተመለሰ፡፡
እንባ ቆሞ በንፈር መምጠጥ ተተካ፡፡ መብረድ ቀርቶ ይባስ
እየተቀጣጠለ የሚሄደው በሽዋዩ ቤት ውስጥ የተነሳው እሳት ብቻ።

ሔዋን ስደት ላይ ነች፥ በታፈሡ ቤት፡፡ አስቻለዉን በተመለከተ
የተፈጠረባት ጭንቅና ሥጋት በልሁ ከወደ አዲስ አበባ የስልክ መልዕክት ካስተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ ቀለል ያለላት ቢሆንም የወደፊት አኗኗሯ ግን ጨለማ
ሆኖባታል። አስቻለው በደረሰበት አደጋ ምክንያት ወድ ክብረ መንግስት ያሰበችውን
ጉዞ ለጊዜው ትተዋለች። ግን ደግሞ ወደ ሸዋዬ ቤት መመለሻው መንገድ ይጨንቃታል። ሸዋዬ ለቤተሰቦቿ የፃፈችባት ደብዳቤም የጎን ውጋት ሆኖባታል።በስጋት እንቅልፍ አጥታ ተቸግራለች፡፡ መንፈሷም ዕረፍት አጥቷል።
ሽዋዬ በበኩሏ በተምታቱ ሀሳቦች ውስጥ ገብታ ራሷም ተምታቶባታል። በአስቻለው መትረፍ ባትከፋም ከመትረፉ ጋር ተያይዞ የሚመጣባትን አደጋ
ስታስበው እንደ ገደል ፈርተዋለች:: ሔዋን አስቻለው ቤት በማደራ ምክንያት የወሰደችባትን ርምጃ ሲመለስ መስማቱ አይቀርምና ምናልባት አስቻለውም
ተናድዶ፤ ሔዋንም ወደ ቤቷ ለመመለስ ፈርታ በዚህ አጋጣሚ ቢጠቃለሉስ? ሽዋዬ ከቅናት በተጨማሪ ያ የምትፈራው የማህበራዊ ህይወት ቀውስ በአቋራጭ ከች ሊልባት ነው:: ከዚህ አደጋ ማምለጫዋ መንገድ አንድ ብቻ ሆኗል! እስቻለው
ህክምናውን ጨርሶ ሳይመለስ ሔዋንን በዚያም በዚህም ብላ ወደ ቤቷ መመለስና በእጇ ማስገባት፡፡ ምንም እንኳ ቀልቧ የጠላቸው ቢሆንም ሔዋንን ከታፈሡ ቤት አምጥተው ለማስታረቅ የሚችሉ ወይዘሮ ዘነቡ ብቻ መሆናቸውን በማመን ተስፋዋን በእሳቸው ላይ ጣለች። ልክ አደጋው በደረሰ ሳምንት በዕለተ ሐሙስ ዓይኗን በጨው
አጥባ ወደ ቤታቸው ጎራ በማለት
«እማማ ዘነብ!» አለቻቸው።
«ወይ የኔ ልጅ»
«መቼም የሰሞኑን ጉዴን ሳይሰመት አይቀሩም»
«የምን ጉድ?» አሏት ሆዳቸው እየጠረጠረ ነገር ግን እሷው ትዘርዝረው በሚል ሐሳብ።
«እህቴን ከቤት እንዳባረርኩ አልሰሙም?»
«መስማቱን ሰማሁ ልጄ! ግን ምን አድርጋ ይሆን?» አሉና ጉንጫቸውን በእጃቸው መዳፍ ደገፍ አድርገው ያዩዋት ጀመር።
«በጣም በጣም ባለገችብኝ፡፡»
«እንዴት?»
ሽዋዬ የነበረውን ሁኔታ ሁሉ ዝርዝር አድርጋ ከነገረቻቸው በኋላ «ታዲያ ይኸ አያናድድም እማማ ዘነብ?» ስትል ጠየቀቻቸው።

ወይዘሮ ዘነቡ ለሽዋዬ ጥያቄ መልስ ከመስጠት ይልቅ በውስጣቸው ይጉላላ ለነበረው ሀሳብ መልስ ለማግኘት ሲሉ «አሁን ታዲያ የት ነው ያለችው!» ሲሉ ጠየቋት።

«አንድ ታፈሡ የምትባል መርዝ አለች፡፡ እሷ ጋር ሳትሆን አትቀርም፡፡»
ወይዘሮ ዘነቡ በሽዋይ አነጋገር ውስጣቸው ቅይም አለ፡፡ ታፈሡን
ያውቋታልና የመርዘኛነት ባህሪ እንደሌላት ያውቃሉ፡፡ ይልቁንም ሲያዩዋትም ሆነ ሲያነጋግሯት ደስ ትላቸዋለች፡፡ የተዋወቁትም እዚያው ሽዋዬ ጋ ስትመጣ በነበረበት ወቅት ነው፡፡ አሁንም የሆዳቸውን በሆዳቸው አድርገው፡-
«ያቺ ደርባባ ጓደኛሽ?» ሲሉ ጠየቋት፡፡
«አንዳች ያንደርባትና ሲያዩዋትማ ትመስላለች፡፡» አለችና ሽዋዬ ከንፈሯን ንክስ አድርጋ ወደ ሰማይ አንጋጣ ማየት ጀመረች። ወይዘሮ ዘነቡ ግን ታፈሡን ….ደርባባ የምትመስሰው፡ በማለት ብቻ ሊረኩ አልቻሉም፡፡ እንደው ጥሎብኝ እወዳታለሁ ልጄ! ከመልክ ቢሉ መልክ፣ ከጠባይ ቢሉ ጠባይ፣ ትትናውንም ሁሉ
አስተካክሎ አንድዬ የሰጣት እመቤት» በማለት ለታፈሡ ያላቸውን ትክክለኛ ስሜት
ከገለፁ በኋላ «ከአንቺስ ጋር ሰላም አልነበራችሁም ነበር እንዴ?» ሲሉ ጠየቋት፡፡
«በዚችው በእህቴ የተነሳ ተጣላን፡፡» አለቻቸው ወይዘሮ ዘነቡ ስለ ታፈሡ የሰጡት አስተየየት ሆድ ሆዷን እየቆጫት፡፡ «እሷ አይደለች እህቴን እንደ ዓይን
እልም አድርጋ ያጠፋችብኝ» ብላ ፊቷን ወደ ወይዘሮ ዘነቡ መሰስ በማድረግ «አሁን ሽማግሌ ሁኑኝ፤» አለቻቸው፡፡
«የምን ሽምግልና?»
ይቺኑ እህቴን ከተወሽቀችበት ጎትተው ቢያወጡልኝ ብዬ ነዋ!
ያለበለዚያማ ትምህርቷም መቋረጡ ነው::»
ወይዘሮ ዘነቡ አሁንም ጉንጫቸውን በመዳፋቸው ደገፍ አድርገው ረጋ ባለ አነጋገር «ሰማሽ ልጄ!» አሏት ከአንገታቸው ዘንበል ብለው እያዩዋት።

«እ»
«ከአንቺም በኩል ጥፋት አየሁ፡፡»
«ምን አደረኩ?» አለቻቸው ሽዋዬ ፊቷን ኮስተርተር በማድረግ እያየቻቸው፡፡
«መቸም ሁላችንም ልጅ ሆነን አድገናል። ልጅነት ደግሞ የተስፋ ዘመን ነው። ልጆች ሁሉን ነገር የሚያዩት በበጎ ነው። መስሎ የታያቸውን ነገር ከመፈጠም አይመለሱም። በተለይ ሴት ልጅ አንዴ እግሯ ከወጣ የልቧን ሳታደርስ አትመለስም::
ስለዚህ ዘመድ ነኝ የሚል ሰው ከፊት ከፊቷ እየቀደመ መንገዷን
ቢያመቻችላት ይሻላል እንጂ ተመለሽ ብሎ ከእሷ ጋር እልሀ መያያዝ… » ብለው ሳይጨርሱ ሸዋዬ አቋረጠቻቸው::
«አልገባኝም!» አለች ቆጣ ባለ አነጋገር፡፡
«ትዳር ሳትይዝ እንዳትጠንስ መላ መላውን መንገር፣ የወደደ ቢጠላት
ተበሳጭታ አንድ ነገር እንዳትሆን ማጥናናትና --» ብለው ሳይጨርሱ ሽዋዬ አሁንም ቀደመቻቸው
«ቁም ነገሩን ብናወራስ እማማ!»
«የማወራሽ ቁም ነገር መስሎኝ!» አሏት እሳቸወም መነፅራቸውን ወለቅ አድርግው አየት እያረጓት።
«ያ ሁሉ የሚሆነው በእጀ ስትገባ አይደል!?» አለቻቸው አስተያየታች
የንዴት መስሏት ደንገጥ እያለች።
«ቁም ነገሩ በእጅ ማስገባቱ ብቻ አይደለም፣ ተመልሳ እንዳትወጣ ማድረጉ ነው።ለነገሩ እህትሽም ዕድለኛ ሳትሆን አትቀርም፤ ከእጅሽ ብትወጣም መውደቂያዋ
ያማረ። ያ ልጅ ደግሞ ባለሙያና ረጋ ያለ የልጅ አዋቂ ነው፡፡ እንዳይለያዩ ድንግል ትርዳቸው እንጂ ሁሉቱም መልካም ልጆች ናቸው:» አሏት፡፡
ሸዋዬ የበለጠ ውስጧ ጨሰ፡ በሆዷ ላይ ይቺ ፈልፈላ አሮጊት አለቻቸው በወይዘሮ ዘነቡ ላይ ዓይኗን ስክት አድርጋ።
«ለመሆን የዚያች ጓደኛሽ ቤት የት ይሆን?» ሲሉ ወይዘሮ ዘነቡ በመሀል ጠየቋት። በዚህ ጊዜ ሽዋዬ ወደ ዋናው ቁምነገር የተመለሰላት መስሏት ልቧ ትንሽ
ተንፈስ አለና እኔ ወስጄ ከሩቅ አሳይዎትና እመለሳለሁ፡፡» አለቻቸው ትንፍሿ በርክቶ አፍንጫዋ ሳብ ረገብ እያለ፡፡
«ይሁን ደግ ልጄ፣ ትንሽ፣ ጠሐዩ በረድ ይበልና ሄጄ እሞክራለሁ::»
«እንደ ምንም ብለው ይዘዋት ይምጡ፣ አደራ!»
የዚያኑ ዕለት ከአመሻሹ አሥር ሰዓት አካባቢ ሽዋዬ ወይዘሮ ዘነቡን ከታፈሡ ቤት አካባቢ አድርሳቸው ወደ ቤቷ ተመለሰች። ነገር ግን የወይዘሮ ዘነቡ
አመለካከት ቅፍፍ አላት፡፡ ሔዋንን በእጇ የማስገባት ዓላማዋ ቢሰናከል ችግሩ የከፋ
እንዳይሆን ፈርታ እንጂ ሽምግልናቸውም ቢቀርባት በወደደች ነበር።
ወይዘሮ ዘነቡ ከታፈሡ ቤት ሲደርሱ ቀኑ አሥር ሠዓት አለፍ ብሏል።
ታፈሡና ሔዋን ሶፋ ላይ ቁጭ ብለው እንጀራ በትሪ አቅርበው ሲበሉ አገኟቸው።
አስቻለውን ለመጠየቅ አዲስ አበባ ሰንብተው ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ነው ከቤታቸው የደረሱት:: ቡናም እየተፈላ ነው፡፡እራት ነው ምሣ የምትበሉት?» እያሉ ወይዘሮ ዘነቡ ወደ ቤት ገቡ።
👍12