አትሮኖስ
286K subscribers
122 photos
3 videos
41 files
578 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የወድያነሽ


#ክፍል_አስራ_ስድስት


#ድርሰት_ኀይለመለኮት_መዋዕል

....የማለዳዋ የጥር ወር ፀሐይ በመሬት ወለል አካባቢ ከየሚዳው! ከየተራራው፣ ከየዛፉ፣ ከየቤቱ፣ ከየጉራንጉሩ ቀዝቃዛ አየር ጋር ትንቅንቅ ገጥማለች። ተፈጥሮ ራሷን በራሷ የምታስተካክልበትና የምትለዋውጥበት ተፈራራቂ ኃይል ስላላት ቀዝቃዛው አየሩ ቀስ በቀስ ተረታ። ለውጥ የተፃራሪ ኃይሎች የግብግብ ውጤት ነው::

በእኔ ሕይወት ውስጥ ግን ጎልቶ የሚጠቀስ ለውጥ ባለመገኘቱ ሕሊናዩ
እየቀዘቀዘ ከመሔድ በቀር የብርታት ለውጥ አልታየብኝም፡፡ ከመኝታዬ ተነሥቼ
ልብሴን ስለባብስ ሰውነቴ ቀነቀነኝ፡፡ እውነተኛዎቹ የሐሳቤ ቅንቅኖች ግን አንጎሌ ውስጥ ይርመሰመሳሉ። የሥራ ቀን ነበር፡፡

መንገዱ የሚያልቅልኝ ስላልመስለኝ ቀደም ብዬ ተነሣሁ፡፡ ወደ ሕጋዊ ፍርድ ቤት ሳይሆን ወደ ግፈኞች የመከራ ሽንጎ የምገሠግሥ መሰለኝ፡፡ ከአራት ኪሎ እስከ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያለውን ርቀት በሁለት ታክሲ አጠቃለልኩት፡፡
ጠበቆች፣ ዳኞች፣ ጸሐፊዎች፣ ነገረ ፈጆችና ወኪሎች፣ ተሟጋቾችና አማላጆች፣ “ጫማ ጠራጊዎችና ሥራ ፈቶች፣ እንደየ ኑሮ ደረጃቸው ለብሰው ተራ በተራ ሁለትና ሦስት እየሆኑ በመምጣት የፍርድ ቤቱን አካባቢ የበጋ ወራት ገብያ
አስመሰሉት፡፡ አንዳንዶቹ ሰዎች የለበሱት ነጠላና ጋቢ በጣም ከመቆሸሹ የተነሣ
ዳግመኛ ታጥቦ የሚነጣ አይመስልም፡፡ ጥለቱ የተንዘለዘለ፣ ዐልፎ ዐልፎ አይጥ
የበላው ይመስል የተቀዳደደ፣ እንደ አረጀ ሻሽ አለቅጥ የሳሳ ልብስ፣ በተለያየ
የጨርቅ ዐይነት የተጣጣፈ ኮትና ሱሪ፣ ከታጠበ ብዙ ዓመታት ዐልፈውት እድፉ
እንደ ማሰሻ የተላከከበት ሱፍ ኮት፣ ከተወለወለ ወራት ያለፉትና የቆዳው ቀለም የተገጣጠባ ከወደ አፍንጫው በእንቅፋት አልቆ ቀዳዳው የደረቀ የዓሣ አፍ የመሰለ፡ ከወደ ተረከዙ ወይም ከወደ ጎኑ ባንድ ወገን ተበልቶ የተንጋደደ ጫማ፣
በፀሐይ ሐሩርና በውርጭ፣ በአቧራና በእንክርት ቀለሙ ጠፍቶ የነተበ ባርኔጣ፣
የለበሱ ያደረጉና የደፉ ሰዎች በተስፋ መቁረጥ ስሜት እዚህም እዚያም
ቆመዋል፡፡ ለአያሌ ወራትና ዓመታት የተንገላቱና የተጎሳቆሉ ባለጉዳዮች ናቸው::በረሃብና በጥማት በርዛትና በንዴት በመጎዳታቸው አብዛኛዎቹ ውርጭ ላይ ያደረ አንጋሬ ይመስላሉ፡፡ ሕይወታቸው በትካዜ በመሞላቱ የገጽታቸው ፈገግታ ደርቋል፡፡

ወዛቸው እንደ ቅቤ ቅል የሚቅለጠለጥ ፊታቸው በዶሮ ጮማ እንደተወለወለ የወይራ በትር የሚያበራ፣ ቦርጫቸው የመንፈቅ ርጉዝ መስሎ ሱሪያቸው መታጠቂያው ላይ የሪቅ አፍ የሚያህል፣ አለባበሳቸው ሁሉ በጣም ያማረና የተዋበ ደንደሳሞች፣ በየደቂቃው በሚረባና በማይረባው ሁሉ የሚሥቁ በጣም መሠሪ ሰዎች ከየቢጤዎቻቸው ጋር ሰብሰብ ከምችት ብለው አፍ ለአፍ
ገጥመው ያወራሉ። የያዙት የሰነዶች መያዣ ኮሮጆ እንደ ባለቤቶቹ የፀዳ ሲሆን
የልፋት እንክርት አልነካውም፡፡ የተሰበሰበውን ሰው በዝርዝር ሲያዩት እያንዳንዱ ብቻውን ቆሞ እጁን እያወራጨ ከራሱ ጋር ይሟገታል።

አብዛኛው ጨርቅ ለባሽ በሌላ ሰው ወረቀት እያስነበበ ይኽ ልክ ነው
የለም ይኽ ሐሰት ነው! ለዚህ በቂ ነቃሽ አለኝ! ያያት የቅድመ አያቴ ነው ይግባኝ እላለሁ፡ ከዳኛው ጋር ተዋውለው ነው። ወላዲተ አምላክን!” እያለ እሰጥ
አገባ ይላል። ሁሉም ከሕይወት ወዲያ ማዶ በውሸት ዓለም ውስጥ የሚንቀሳቀሱ እንጂ በርግጠኛ ሕይወት በእውነተኛ ዓለም የሚኖሩ አልመሰሉኝም

የመጥፎ ነገር ጥቀርሻ በጥብጠው የጋቱኝ ይመስል አእምሮዩ ተጨነቀ፡፡
የማያቋርጠው የጊዜ ጎርፍ እየጋፈረ መጓዙን ቀጠለ። ደቂቃ የደቂቃ ርካብ ረግጣ እየተፈናጠጠች ላትመለስ ትጋልባለች።

ጎነ ረጂሙ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ግዙፍ ሕንፃ ታላቅ የመከራ ተራራ መስሎ ፊት ለፊት ተገትሯል። የማደርገውን ጥንቃቄ አሟልቼ አካባቢዬን ገልመጥ እያልኩ እያየሁ መለስ ቀለስ አልኩ፡፡ ጭንቀቴና ጥበቴ እንደ ሐምሌ ጥቁር ደመና ከብዶ አንጎሌ ውስጥ አንዣሰሰ። በውስጤ የነበረው ሥጋት በድኃ ገበሬዎች አዋሳኝ እንዳለ የከበርቴ እርሻ መስፋቱን ቀጠለ። ረፈደ።

በወታደሮች ታጅበው በእግራቸውና በመኪና የመጡ አያሌ እስረኞች
በተለየ ቦታ ሰብሰብ አጀብ ብለው ቆሙ። ገር ገጭ ገጭ ገጭ፣ ሲጢጢጢጢጢ !
ካካካካካኪ! የሚል ድምፅ የምታሰማ ቮልስዋገን መጥታ አጠገቤ ቆመች፡፡ ጉልላት ነው። የየወዲያነሽ ቀነ ቀጠሮ በመሆኑ እኔና እርሱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት
ለመገናኘት ተነጋግረን ነበር። ድክምክም ባለ እንቅስቃሴ የመኪናይቱን ቋቋቲያም
“በር ከፍቶ ወጣና ጨበጠኝ፡፡

ለአራት ሰዓት ሩብ ጉዳይ እኮ ሆኗል እስካሁን አላመጧትም እንዴ?»
አለኝ፡፡ ከንፈሬ ተጣብቆና ምላሴ አልላወስ ብሎ ቢያስቸግረኝም የለም እስካሁን አላመጧትም» ብዬ ዝም አልኩ። ውካታ በበዛበት አካባቢ ጥቂት ዝም ብለን ቆምን። ትላንት ማምሻዬን ሦስት ባለሙያ ጠበቆች አነጋግሬ ነበር። ሁሉም የሰጡኝ መልስ በጣም ተቀራራቢ ነበር፡፡ ቢበዛ አምስት ዓመት” አሉኝ። እንተስ ምን ይመስልሃል?» ብሎ ዐይኔን ማየት ጀመረ።

«እኔ ምን ዐውቃለሁ፡፡ ማንም ቢሆን ከራሱ ላይ ይልቅ በሌላው ላይ
መፍረድ ይቀልለዋል። የፍርድ ሰጪዎቹን ማንነት ስታየው ግን አምስት ዓመት
የሚበዛ አይመስልም፡፡ ቢሆንም ለእኔና ለእርሷ እያንዳንዱ ደቂቃ የሕይወታችን
ማሻከሪያ ክፍለ ጊዜ መሆኗ ነው» ብዬ ዝም አልኩ፡፡

«መቼም ቢሆን» አለ ጉልላት ወደድክም ጠላህም ምን ጊዜም ቢሆን ሕግ አለ። በሕጉም የሚጠቀሙና ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁ አሉ። አህያና ጅብ
ባንድ ላይ ሕግ አያረፉም፡፡ ለጨቋኝና ለተጨቋት በአንድ ጊዜ በእኩልነት
የሚያገለግል ሕግ የለም፣ አልነበረምም፡፡ ሕግ ስለተፃፈ ብቻ ሕጋዊ አሠራር አለ
ማለት አይቻልም። እኔና አንተ ባለንበት ሥርዓተ ማኅበር ውስጥ እጀግ በጣም
አያሌ ባለሥልጣኖችና አጫፋሪዎቻቸው በልዩ ልዩ የእሠራር ስልትና ሥልጣን
ፈጠር ከለላ ከሕግ በላይ የሆኑበትና የሚሆኑበት ሁኔታ እንዳለ መዘንጋት
የለበትም፡፡ ስለሆነም ሕግ በትክክለኛው መንገድ በሥራ ላይ እስካልዋለ ድረስ
የሌለ ያህል ነው፡፡ ይህ ጉዳይ በስፋት የሚያነጋግግር ስለሆነ አሁን ከመጣንበት
ጉዳይ ጋር በቀጥታ ተያያዥነት የለውም። ወደ መጣንበት ጉዳይ እንመለስ፡፡
ስለዚህ በሚሰጠው ፍርድ እንዳትገረም፡፡ የበዛ ወይም ያነሰ ሊሆን ይሆናል» ብሎ
ወደፊት ተራመደ፡፡ ርምጃዬን ከርምጃው ጋር አስተካክዩ ተከተልኩት።

ከእኛ ትንሽ ራቅ ብሎ አንድ ብረት ሽፍን ባለ ጥቁር ሰሌዳ አረንጓዴ መኪና ቆሟል፡፡ ጉልላት መኪናውን አሻግሮ እየተመለከተ «ለምንድን ነው አልመጣችም ያልከኝ? ያ እኮ ነው የወህኒ ቤቱ መኪና» ብሎ ጥሎኝ ሔደ፡፡
አልተከተልኩትም፡፡

መኪናው ውስጥ ከተቀመጠው ሰው ጋር ምን እንደተባባሉ ባይሰማም ጉልላት ትንሽ ራቅ ብሎ ተነጋገሩ። ወዲያው ወደ እኔ ዞር ብሉ ና ቶሉ በሚል አኳኋን ጠቀሰኝ እና ሄድኩ፡፡ እስረኞቹ ወደሚገኙበት አካባቢ እንደ ደረስን ዐይኔ
ያካባቢው የብርሃን መጠን ያነሣት ይመስል የውበት ሃያ መስኮቶቿ ተሸጎሩ።

አጠርጠር ያሉና በሰፊ የካኪ ጨርቅ ስልቻ ውስጥ የቆሙ የሚመስሉ
የወህኒ ቤት ሴት ወታደሮች እያንዳንዳቸው አጠር ያለ ዱላ ይዘው ቆመዋል። በአቅራቢያቸው አምስት ሴቶች ሰብሰብ ብለው ተቀምጠዋል። የትካዜ እሳት ያነኮታቸው ይመስላሉ። ንዳድ እንደ ተነሣበት ሰው መላ ሰውነቴ ጋየ፡፡

የሕይወቴ ክፋይ የሆነችውና የማፈቅራት የወዲያነሽ አንገቷን ሰበር አድርጋና ጀርባዋን ለረፋዷ ፀሐይ ሰጥታ መሬት ትቆረቁራለች። ጉልላት ከሴቷ ወታደር ትንሽ ራቅ ብሎ በትሕትና እጅ ነሣ ራመድ ብዬ ከጎኑ ቆመኩ

በተከዘ ፊቱ ላይ ለማስደሰት የሚፍጨረጨር ፈገግታ እያሳየ «ከነዚህ
👍31