አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ህመም_ያዘለ_ፍቅር


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#በክፍለማርያም

...ወረቀቱን ፍለጋ ወደ ዉስጥ ተመለሰ
ፍቃዱ ወረቀቱን እያነሳ ድል እንዳረገ ሰው ኮራ እና ጀነን እያለ
"አገኘኋችሁ"
ሲል አጉተምትሞ የወረቀቱን አቅጣጫ ተከትሎ መሄድ ጀመረ።

እማማ ስንቅነሽ ቁርስ ሰራርተዉ ዉጪ ተገትራ የቆመችዉን ቤዛዊትን ወደ ቤት ዉስጥ ገብታ
እንድትበላ ጠሯት አልሰማቻቸዉም ልቧ ከአሁን አሁን መጣ አልመጣም ብላ የምትጠብቀዉ ፍፁም ላይ ነዉ።

ቀረብ ብለዉ እየነኳት
"ልጄ የምትጠብቂዉ ሰዉ አለ እንዴ"
እማማ ስንቅነሽ በሁኔታዋ ተጠራጥረዉ ጠየቋት
"አዎ ግን አሁን አልነግሮትም"
ፈጠን ፈጠን እያለች እያወራች
የእማማን ልብ ለማንጠልጠል አስባ
ነገር ግን እማማ ስንቅነሽ ምንም አልመሰላቸዉም እንደሚያማት ስለሚያዉቁ አብዳ ለይቶላት
ጨርቋን ጥላ ሳይፀየፉ ሰዉ ናት ብለዉ ስላቀረቧት አሁን አሟት ቢሆን እንኳ ሰዉ የምትጠብቀዉ ሊጫኗት አልፈለጉም።

እዉነተኛ ወዳጅም እንደዚህ ነዉ ጥፋትህን ስህተትህን ካወቀ በስህተት በጥፋትህ ተጠቅሞ
ሊጎዳህ አይሞክርም
ያግዝሀል ያበረታሀል እንጂ
እማማ ስንቅነሽም የቤዛዊትን እጅ በፍቅር ይዘዉ ሳብ እያረጉዋት
"በይ ነይና ቁርስሽን በልተሽ ትጠብቂዋለሽ"
ለእሳቸዉ የእሷ ቁርስ መብላት እንጂ ታማ ዉጪ መገተሯ ወይ በጤነኛ አይምሮዋ ሰዉ ቀጥራ
እየጠበቀች መሆኑ ብዙም ትኩረት አይሰጣቸዉም
ቤዛዊት የቀጠረችዉ ሰዓት ሳይደርስ መጨነቋ እየገረማት እና ፍፁምን ምን ያክል እንደምትወደዉ እያሰበች ወደ ቤቱ ዉስጥ ከእማማ ስንቅነሽ ጋር ተከታትለዉ ገቡ።

እጇ ላይ ያሰረችዉ ሰዓት ይቆጥራል እርግጠኛ ስላልመሰላትም በእማማ ስንቅነሽ በር በኩል
የሚያልፉ እና የሚያገድሙ ሰወችን
"ይቅርታ ሰዓት ስንት ነዉ?"
በሚያሳዝን አስተያየት ትጠይቃለች
"ሶስት ተኩል፣አራት ስዓት .."
እያሉዋት የጠየቀቻቸዉ ሰወች ያልፉሉ
እሷም ያሰረችዉ ሰዓት ግን ትክክል ነበር የሚሰራዉ።

ቤዛዊት ስልኳን ይዛ ባለመዉጣቷ ተበሳጨች ይዛዉ ብትጠፋ ቤተሰቦቿ እየደወሉ የሚጨቀጭቋት ስለመሰላት ነበር ትታዉ የወጣችዉ አሁን ግን ብይዘዉ ኖሮ ስትል
ተመኘች የፍፁም መዘግየት እያሳሰባት ስድስት ስዓት ሊሆን ተቃርቧል።
እማማ ስንቅነሽ በጠራራ ፀሐይ ዉጪ የቆመችዉን ቤዛዊትን ቤት እንድትገባ ለመለመን ከጉዋዳቸዉ ወጡ
"አይ ልጄ ፀሀዩ በረታብሽ እንዳያምሽ ወይ ወደ ቤት ግቢ አልያም በረንዳ ላይ ጥላ ቦታ ተቀመጪ"
"ቀረብኝ እኮ ሶስት ሰዓት ተባብለን ስድስት ሰዓት ሞላ"
"እኮ ይመጣል ብቻ ከፀሐይዋ ራቅ በይ"
እንደዚህ ሲልዋት ቤዛዊት በደስታ ፈገግ እያለች
"የሚመጣዉ ማን እንደሆነ ልንገሮት?"
በእሺታ እማማ ስንቅነሽ ጭንቅላታቸውን ነቀነቁ
"ጉዋደኛዬ ፍቅረኛዬ ባሌ"
ቀጠል አድርጋም
"ፍፁም ይባላል ሲመጣ አስተዋዉቃችሁዋለሁ"
እማማ በእሷ ደስተኛ መሆን እየተደሰቱ እና እያዋሩ ቤዛዊትን ከፀሀዩ ወደ ጥላ ወስደዋት ነበር።

(ከሰዓታት በፊት)
ፍፁም ሁለት ስዓት ተኩል አካባቢ ከተባለዉ አድራሻ በታክሲ ተሳፍሮ እንደወረደ እና ባለችዉ አቅጣጫ ጥቂት ከተራመደ በኋላ ቦታዉን ለማረጋገጥ ፈልጎ ቤዛዊት የሰጠችዉን ወረቀት ኪሶቹ ዉስጥ ሲፈልግ ስላጣዉ እየተበሳጨ
የት ሊጥለዉ እንደቻለ ማሰብ ጀመረ።
ቤቱ እየወጣ ለአከራዩ ብር ሲሰጥ ሊሆን እንደሚችል ገምቶ የቦታዉን እርግጠኝነትን ለማረጋገጥ
ጭንቅላቱን መጠየቅ ተያያዘ
አልተሳሳተም ያለችዉ ቦታ ላይ ደርሷል ነገር ግን እሱ ከቆመበት መንገድ ተሻግሮ ነበር
አንገቱን ቀና አርጎ ለማየት ሞከረ ቤዛዊትን በርቀት አያት
በእድሜ ገፋ ካሉ ሴትዮ ጋር ቆማ ታወራለች
ስላያት እየተደሰተ ግዜ ሳያጠፋ መንገዱን ሊሻገር ሲል በቅርብ እርቀት ከቅድም ጀምሮ ከጀርባዉ
የነበረ የመሰለዉ ሰዉ ስላየ መሻገሩን ተቶ የሰዉየዉን ፊት ለማየት በቀስታ ዞሮ በጨረፍታ አይቶት
መሻገሩን ወደ ቤዛዊት መቅረቡን ትቶ ቀጥታዉን መንገድ ይዞ እየተናደደ እያጉተመተመ መራመድ ጀመረ።

"ከቤት ጀምሮ ሲከተለኝ ነበር ወይስ እንዴት እዚህ ድረስ ሊመጣ ቻለ"
ፍፁም እራሱን እየጠየቀ ከኋላዉ የሚከተለዉን ሰዉዬ ለማምለጥ እየሞከረ ነዉ
"አይ ፍቃዱ ምን አርግ ነዉ ግን የሚለኝ ምን በደልኩት ምን አሰቀየምኩት
ይሄን ያህል የጎን ዉጋት የሆነብኝ"
ፍፁም ከፊት ሲራመድ ፍቃዱ አድፍጦ ከኋላው እየተከተለዉ ነዉ ፍፁም እሮጦ ማምለጥ
ተመኘ ነገር ግን እግሮቹ ለመሮጥ ብቁ አደሉም
ፍፁም እያነከሰ ፍቃዱን ለማምለጥ ክራንቹን ተጠቅሞ ፈጠን ፈጠን ለማለት እየታገለ ነዉ
ከጀርባዉ ያለዉ ፍቃዱ ግን ዘና ብሎ እየተራመደ በፍፁም አረማመድ አነካከስ እየሳቀ እየተከተለዉ ነበር።

አንዳንዴ በህይወት መስመራችን ዉስጥም ከእኛ በብዙ እጥፍ የሚበልጡን በብዙ እጥፍ
የተሻሉ ሰወች አሉ
ነገር ግን አብዛኞቹ ስለበለጡን የሚኮፈሱ ስላነስን የሚንቁን ናቸዉ
ህየወትንም ከባድ የመያረጋት መሮጥ የሚችል ሰዉን በታመመ እግር በክራንች ታግዘዉ ማምለጥ መቻል ነዉ።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
2👍1