#የፈሪ_ሰው_ጸሎት
አምላክ ሆይ .
ይግባኝ ዐለኝና አቤት የምልበት
በአርባ አራት ጾሜ ሕግን 'ምሽርበት።
ለምን? የሚል ሐሳብ . . .
በመሸነፍ ብእር ልብ ወለድ ተደርሶ
ይጠይቃል ልቤ ከዙፋንኽ ደርሶ።
እዚኽ . . .
ሕግን እያወጣ ደንብ እያረቀቀ
ሕዝብ እያስከበረ እራሱ እየናቀ፣
ይበይንብኻል . . .!
አያድን ከቅጣት ሕግን ያላወቀ።
( . . . እያለ. . .)
( ፈተና ፩ )
ሠፊው የ'ኔ ዓለም . . .
ስልቻ ላይሞላ ሠርክ ፍዳ ኾነ
ሆድ የሚሉት ዋሻ ለግብሩ ታመነ ፣
ድንጋይን ከዳቦ እያፎካከረ
ኅሊናን ረስቶ ተገዛ ፣ታሰረ።
( ፈተና ፪ )
መከራዬ ኹሉ ዕንገት እያስደፋኝ
መንገዴ በሙሉ 0ጉኖ እያፋፋኝ ፣
ጠረጠርኩኝና ...
በኾነው በቀኑ መድረስኽን ረሳኹ ፤
በማወቅ ጉጉቴ . . .
ከመቅደስ ከፍታ ለመውደቅ ተነሣኹ።
( ፈተና ፫ )
ነባዊ . . .
ልባዊ . .
ሕያዊ . . .
መገመት ጀመሩ ፤ አንሰው ኮሰሱና
እሩጫው ዐየለ ፤ መስገድ እረሱና ፣
ሙዳይ መስፈራዬ አስገምቶኝ ከ'ኔ
ገዛኹ ፣ተገዛኹኝ ፤ በምድራዊው ቅኔ።
እናም . .
ልቤ ቃልን ስቶ
ለሥጋ ተገዝቶ
በዓለም ተመርቶ።
በሰው መኾን ግብር
አልችል ካለች ነፍሴ ፈተናውን ማለፍ፤
ይግባኝ ባሉት ብሂል ይቺ ጽዋ ትለፍ።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘
አምላክ ሆይ .
ይግባኝ ዐለኝና አቤት የምልበት
በአርባ አራት ጾሜ ሕግን 'ምሽርበት።
ለምን? የሚል ሐሳብ . . .
በመሸነፍ ብእር ልብ ወለድ ተደርሶ
ይጠይቃል ልቤ ከዙፋንኽ ደርሶ።
እዚኽ . . .
ሕግን እያወጣ ደንብ እያረቀቀ
ሕዝብ እያስከበረ እራሱ እየናቀ፣
ይበይንብኻል . . .!
አያድን ከቅጣት ሕግን ያላወቀ።
( . . . እያለ. . .)
( ፈተና ፩ )
ሠፊው የ'ኔ ዓለም . . .
ስልቻ ላይሞላ ሠርክ ፍዳ ኾነ
ሆድ የሚሉት ዋሻ ለግብሩ ታመነ ፣
ድንጋይን ከዳቦ እያፎካከረ
ኅሊናን ረስቶ ተገዛ ፣ታሰረ።
( ፈተና ፪ )
መከራዬ ኹሉ ዕንገት እያስደፋኝ
መንገዴ በሙሉ 0ጉኖ እያፋፋኝ ፣
ጠረጠርኩኝና ...
በኾነው በቀኑ መድረስኽን ረሳኹ ፤
በማወቅ ጉጉቴ . . .
ከመቅደስ ከፍታ ለመውደቅ ተነሣኹ።
( ፈተና ፫ )
ነባዊ . . .
ልባዊ . .
ሕያዊ . . .
መገመት ጀመሩ ፤ አንሰው ኮሰሱና
እሩጫው ዐየለ ፤ መስገድ እረሱና ፣
ሙዳይ መስፈራዬ አስገምቶኝ ከ'ኔ
ገዛኹ ፣ተገዛኹኝ ፤ በምድራዊው ቅኔ።
እናም . .
ልቤ ቃልን ስቶ
ለሥጋ ተገዝቶ
በዓለም ተመርቶ።
በሰው መኾን ግብር
አልችል ካለች ነፍሴ ፈተናውን ማለፍ፤
ይግባኝ ባሉት ብሂል ይቺ ጽዋ ትለፍ።
🔘ተስፋሁን ከበደ🔘