አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ጨረሬን


#ክፍል_አንድ


#በአሌክስ_አብርሃም

እማማ ሞቱ !!

ትላንት ልክ ፀሐይ ስትጠልቅ፤ እማማ ይችን ዓለም ተሰናበቱ !

ዘጠኝ ዓመት ሙሉ ከአልጋ ወርደው የማያውቁት ሚስኪን ሴት፣ የሰፈሩን ሰው ሁሉ እንዳኮረፉ ሞቱ። ዘጠኝ ዓመት አስታመን፣ እንደ እናት ተንከባክበን፣ ባለቀ ሰዓት ረግመውን ሞቱ” እያለ የሰፈሩ ሰው በሙሉ አዘነ: አፍ አውጥተው አይናገሩት እንጅ ያስረገምከን አንተ ነህ” የሚል ወቀሳቸውን ከእያንዳንዳቸው ዓይን ላይ እይቻለሁ፡፡እኔም ምነው በቀረብኝ ብዬ በውስጤ ስብሰለሰል ሳምንት አለፈኝ፡፡ የሆነ ሆኖ እማማ
ላይመለሱ ከነኩርፊያቸው አሸለቡ፡፡ ለነገሩ ኩርፊያ ይሁን ሐዘን ማንም አልገባውም:
በኩርፊያና በሐዘን መሃል ያለው ልዩነት ምንድነው? ምንስ ነው በቁጣና የኩርፊያ
መካከል ያለው መስመር? …መዝገበ ቃላት ቃላትን እንጅ ስሜትን አይፈታም፡፡ እማማ፡
በምናውቃቸው ቃላት የገለፅነው የማናውቀው ስሜት ውስጥ የነበሩ ይመስለኛል፡፡ የሕይወት ታሪካቸው ሲነበብ በደፈናው “የሁላችንም እናት ነበሩ” ከሚል የወል ምስጋና ውጭ እምብዛም የተዘረዘረ ነገር አልነበረም:: አስክሬናቸው በአራት የሰፈራችን ወንዶች ትስሻ ላይ ተቀምጦ በቀባሪው አጀብ በቀስታ ወደ መቃብር ቤቱ ጓሮ ሲጓዝ እእምሮዬ ወደትዝታው የኋሊት ነጎደ ፡፡

የዛሬን አያድርገውና ከሊቅ እስከ ደቂቅ መዋያችን እማማ ቤት ነበር፡፡ የእማማ ቤት እንደው ቤት ሆነ እንጅ ነገረስራው ድድ ማስጫ የሚሉት ዓይነት ነበር፣ ሕፃናቱ እማማ ቤት በር ላይ እቃቃቸውን ሲደረድሩና ሲያፈርሱ፣ የእቃቃ ሰርግ ሲደግሱና
ሲጋቡ፡ወጣቶቹ ተሰብስበን ካርታና ዳማ ስንጫዎት፡ ስለሴት ስናወራና ስናውካካ እንውላለን እሁድ እሁድ የሰፈሩ እድር ዳኞች እና የዕቁብ ገንዘብ ሰብሳቢዎች እዚያው እማማ ቤት ተሰብስበው ሲነታረኩ ያረፍዳሉ፤ ያ አንድ ክፍል የቀበሌ ቤት ሁል ጊዜ ከጧት እስከ ማታ በሩ ክፍት ነበር።

በዛ ዕድሜ እንደ እማማ ዓይነት ረዥም እና ቆንጆ ሴት አይቸ አላውቅም፤ በድህነት ተጎሳቁለው እንኳን ጥርት ያለ ጠይም ቆዳቸውና ሽበት ጣል ጣል ያደረገበት ፀጉራቸው አንዳች ሞገስ ነበረው ስለ ረዥም ቁመት ሲወራ ምሳሌ ነበሩ እንደ እማማ ዠርጋዳ ይባላል፡፡ ዠርጋዳ ነበሩ፤ ሲራመዱ የሚንሳፈፉ የሚመስሉ፡፡ በስተኋላ ዘመናቸው እርጅና ተጭኗቸው፣ ትንሽ ከወገባቸው ጎበጥ ብለው እንኳ በቁመት የሚስተካከላቸው
እልነበረም፡፡ ባልም ልጅም አልነበራቸውም፡፡ መተዳደሪያችው ሰርግና ድግስ ሲኖር ወጥ
በመስራት ነበር፤ ታዲያ ወጥ ሳይቀምሱ በሽታው የሚያውቁ ባለሙያ ናቸው ይባላል።
ሴት ልጅ የወጥ ማማስያ ከላሰች ምኑን ሴት ሆነች ኤዲያ !?” ይላሉ፤ውጥ ሲቀመስ ሲያዩ
እይወዱም:

እማማ ለምን ባል አያገቡም? ስንላችው፣

“በልኬ ወንድ አጣሁ፤ ጨርሶ ኩርፋድ አጎንብሸ ላግባ እንዴ…? ይሉና ይስቃሉ፤ ጨዋታ
እዋቂ ናቸው :

ታዲያ ዓመቱን ሙሉ ማድቤት ለማድቤት ከርመው ለጥምቀት ጽዓል ፀጉራቸውን ተሰርተው፣ሰፊ ባለባንዲራ፣ ጥለቱ ጉልበታቸው የሚደርስ ያበሻ ቀሚሳቸውን ይለብሱና፣ በወገባቸዉ ላይ ሶስት አራት ዙር ተጠምጥሞ ጫፉ ወደታች የሚንዘረፈፍ መቀነታቸውን ሸብ አድርገው፣ ክብ ሰርተው የሚጨፍሩ (እሳቸው “የአገሬ ሰዎች የሚሏቸው) ወንዶች መኻል ገብተው ምንጃርኛ የሚባል ዘፈን እያወራረዱ ጭፈራቸውን ያስነኩታል:እማማን ለማየት የማይመጣ ሰው የለም እማማ መጡ ክፈቱላቸውም ይባላል … ክቡ የሰው ቀለበት በመጡበት በኩል ተከፍቶ ይገባሉ… የታወቁ ናቸው !

ቸብ ቸብ ቸብ ሲዴረግ እማማ እጃቸውን ከፍ አድርገው …

“የምንጃር ልጅ …ሽቅርቅር ብለሺ ነይ ነይ ዙረሺ
ይላሉ፣

የከበበው ህዝብ ይቀበላቸዋል፤ ሕዝቡ ድንገት ለጥምቀት የተሰበሰበ ሳይሆን አብሮ ግጥምና ዜማ ሲያጠና የከረመ ነበር የሚመስለው!

ኢሄ የጀግናው አገር
.
እዛው ምንጃር …

ወረዶች ሸንኮራ …

ስንዴ ልትበላ፣

ወረደች ምንጃር ….

የጤፍ አገር፤

ተይ አብሪው ኩራዙን …

ሳትፈጅው ጎዙን፤

“ያዝ እንግዲህ!” ብለው በዛ ቁመት ድንገት ወደላይ እየዘለሉ ሲመለሱ በፀጉራቸው
የግዜርን ዘርፋፋ ቀሚስ ነክተው የሚመለሱ ነበር የሚመስሉት! ጭብጨባው፣ ጩኸቱ፣ሳቁ ይደምቃል ጎን ለጎን የተደረደሩ ጨፋሪዎች በከበበው ሰው ጭብጨባ ፊትም ልክ
በአንድ ላይ ሸብረክ ሸብረክ… ሸብረክ እያሉ ወደፊት ወደኋላ እተራመዱ ሲጨፍሩ
የተለየ ስሜት ነበረው፡፡

እዛ ማዶ፣

አሃ

ከተራራው!"

አሃ.!

ዓይኑ ነው ወይ፤

እሃ፣

የሚያበራው፧ - የሰሌን ባርኔጣ በቀኝ እጃቸው የያዙ ጨፋሪ ወንዶች በአንድ ላይ ባርኔጣቸውን ከፍና ዝቅ እያደረጉ ሲጨፍሩ አቧራው ይጨሳል …እማማ እንደዛ ነበሩ፡፡

በሰፈሩ ሰው ዘንድ እማማ የሚለው ቃል የወል ስምነቱ ቀርቶ የዚቹ ሴትዮ መጠሪያ ከሆነ ዘመን የለውም፡፡ ሰፈራችን ውስጥ የሚኖሩ ሰዕድሜ የገፉ ባልቴቶች ሁሉ እማማ ከሚለው ቀጥሎ ስማቸው ይጠራል፡፡ እማማ ተዋሱ ፡እማማ ዮሃና፣ እማማ ብርነሽ እማማ ግን እማማ ብቻ! የዛሬ ዘጠኝ ዓመት ታዲያ ለማኅበር ድፎ ደፍተው ማድቤት ጉድ ጉድ ሲሉ ራሳቸውን ስተው እሳት ላይ ወደቁ፣ እሳቱ ግራ ክንዳቸውና በግራ
በኩል ያለ የራሳቸው ፀጉር ክፉኛ ተቃጠለ የግራ ጆሯቸውም በከፊል በእሳቱ ተጎድቶ ነበር፡፡ ያ የተረገመ አደገ የእማማ ጠይም ፊት ላይ በግራ በኩል ለማየት የሚያስፈራ የእሳት ጠባሳ ትቶባቸው አለፈ። ይሄም ባልከፋ ነበር፤ከአደጋው በኋላ ሁለት እግሮቻቸውና የቀኝ እጃቸው አልታዘዝ አላቸው… የግራ እጃቸው ብቻ ነበር የሚሰራው፡፡
በቃ እልጋ ላይ ዋሉ ሰው ደግፎ ካላነሳቸው በስተቀር ከአልጋቸውም መነሳት አይችሉም
ነበር፡፡

የሰፈሩ ሰው ደግ ነው እየተቀያየረ እማማን ለዘጠኝ ዓመታት አስታመመ፡፡ ቤታቸው
ሰው አይጠፋም፣ ከጧት እስከማታ የእማማ ቤት አደባባይ ነበር፤ መንደርተኛው ከልጅ እስከአዋቂ እማማን እየረዳ እግረመንገዱን ቤታቸውን መዋያ መቀጣጠሪያው አደረገው፡፡እማማ ትራሳቸውን ደገፍ ብለው ወጣቶቹ ሲጫወቱ እያዩ፣ አዋቂዎቹ ሲያጫውቷቸው እየተጫወቱ (እንደዛም ሆነው ጨዋታቸው ለጉድ ነበር ) ዘጠኝ ዓመታት አለፉ ።

እንድ ቅዳሜ ቀን ከሰዓት አምስት የምንሆን የሰፈር ልጆች ሰብሰብ ብለን እማማ ቤት ካርታ እንጫዎታለን ፡፡ ድንገት ዓይኔ እማማ ላይ ሲያርፍ የቤቱ ጣራ ላይ ባለች ሽንቁር የገባች ጨረር የብርሃን ዘነጓን ዘርግታ እማማ ጠይም ቆዳ ላይ የቀኝ ግማሽ ከንፈራቸውና የአፍንጫቸውን ጫፍ ያካለለች የብርሃን እንጎቻ ሰርታ ተመለከትኩ፡፡ አንዴ የጣራውን ሽንቁር አንዴ እማማ ፊት ላይ ያረፈውን ክብ ጨረር እያየሁ “ይሄ ሽንቁር ዝናብ ሲዘንብ

አልጋቸው ላይ ውሃ ያንጠባጥብባቸው ይሆን? ብዬ አሰብኩ፤ ጣራውን በሙሉ ስመለከተው ጥላሸት ሸፍኖታል፡፡ የጣራ ከዳኑ ቆርቆሮ እዚያና እዚህ ተበሳስቶ ጥቃቅን የብርሃን ነጠብጣቦቹ ጥቁር ሰማይ ላይ የተዘሩ ከዋከብት መስለዋል ።
ጓደኞቼ ጋር ተያይዘን ስንወጣ “ ለምን የእማማን ጣራ አናድሰላቸውም - አይታችሁታል? ጨረር ሁሉ ያስገባባቸዋልኮ” አልኳቸው… እኔም ሳስብ ነበር… እኔም… እያሉ በየአፋቸው ተንጫጩ፡፡ እንዲህ ነበር የተጀመረው፡፡ ለአንድ ሳምንት ቤት ለቤት እየዞርን ብር አሰባሰብን፤ ጎረቤቱ ሁሉ ደስ እያለው ካሰብነው በላይ ብር አዋጣ፡፡ እንደውም
አንዳንዶቹ ለራሳቸው ጉዳይ ገዝተውት ከተረፋቸው ማገርና ኣውራጅ እየቀነሱ ውሰዱ
አሉን ፡ ግርማቸው የሰፈራችን እናፂ ስራውን በነፃ ሊሰራ ቃል ገባልን ደግሞ ለማማ ብር ልቀበል እንዴ!?” ብሎ ::

በሳምንቱ እማማን ለማስደነቅ በማሰብ ሳንነግራቸው ቤታቸውን ለማደስ ወሰንንና አልፎ
አልፎ እንደምናደርገው አንድ ሁለት
👍1