#Re #post
‹‹ ራስህን ከሌሎች ጋር አታወዳድር፡፡ ፀሃይና ጨረቃን ተመልከት፡፡ ሁለቱንም ማወዳደር አትችልም፡፡ ምክንያቱም ሁለቱም በየጊዜያቸው ዓለምን ያበራሉና፡፡ ››
የእኔ፣ የአንተ፣ የእሱ፣ የእሷ እና የሁላችንም የሕይወት ፍሠት፣ የደስታ ስኬት፣ የኑሮ ተዳፋት፣ እጣ ፋንታ እና ዕድል አንድ አይደለም፡፡ እንደየተፈጥሯችን፣ እንደየመልካችን፣ እንደየአስተሳሰባችን፣ እንደየፍላጎታችን፣ እንደየስጦታችን፣ እንደየአካሄዳችን፣ እንደአጠቃቀማችን ሁለነገራችን፣ ዕጣ ፋንታችን፣ ዕድል ገጠመኛችን ፍፁም የተለያየ ነው፡፡ ከአንድ እናት የወጡ መንታ ልጆች እንኳን ስኬታቸውም ሆነ ውድቀታቸው ይለያያል፡፡ ስለዚህ ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር አይቻልም፡፡
ለአንዳንዱ በቀለም ትምህርት በሕይወቱ ስኬትን ለመጎናፀፍ ይቀለዋል፡፡ ለሌላው ደሞ ዳገት ይሆንበታል፡፡ ለእከሌ ንግድ የሚሳካለት ሲሆን ለእንቶኔ ደሞ ንግድ ኪሳራ በኪሳራ ያደርጋታል፡፡ ይሄ ማለት ግን በጥረትና በልፋት ነገሮችን ማሳካት አይቻልም ማለት አይደለም፡፡ በልፋትና በጥረት የሚሳካላቸው ሠዎች እንዳሉ ሁሉ የማይሳካለቸውም እልፍ ናቸው፡፡ ስንት ዓመት ለፍተው ፍሬውን ሊያዩ ትንሽ ሲቀራቸው ገደ-ቢስ ሆነው ልፋታቸው መና የቀረ ጥቂቶች አይደሉም፡፡
ለዚህ ጥሩ ምሣሌ የሚሆነው የጨረቃና የፀሃይን ተፈጥሮ ማየት ነው፡፡ አንዱን ካንዱ ማበላለጥ አይቻልም፡፡ ጨረቃን ከፀሃይ ብናሳንስ በድቅድቅ ጨለማ የምታበራውን ብርሃን መካድ ይሆናል፡፡ ጨረቃንም ከፀሃይ ብናስበልጥ የፀሃይን ውለታ አይቶ እንዳላየ ማለፍ ነው የሚሆነው፡፡ ሁለቱም በየራሳቸው ጠቃሚዎቻችን ናቸው፡፡ ሠውን ከሠው ማሳነስም ሆነ ማበላለጥ የተገባ አይደለም፡፡ ሁሉም ሠው ለሃገሩም ሆነ ለዓለም የሚታይና የማይታይ ቀጥተኛ አስተዋፅኦ አለውና፡፡ ምንም እንኳን ታዋቂ ሠዎች ቢሞገሱም በነሱ ስር ግን ብዙ ተራ ሠዎች ለእነሱ እውቅና የድርሻቸውን አዋጥተዋል፡፡ ለዚች ዓለም በየትኛውም ደረጃ ያለ ሠው አስፈላጊ ነው፡፡ አምላክ የሠው ልጅን ወዶና ፈቅዶ ነው የፈጠረው፡፡ በመሆኑም ሁሉም የራሱን አሻራ ጥሎ ያልፋል፡፡
ስለዚህ አበበን ከከበደ ማወዳደር አይቻልም፡፡ አበበም የሚበረታበት ነገር እንዳለው ሁሉ ከበደም የራሱ ጠንካራ ጎን አለው፡፡ በርግጥ ከበደ የሚደክምበትን አበበ ሊበረታበት ይችል ይሆናል፡፡ ይሄ ደሞ ከበደ ከአበበ ያነሠ ነው ማለት አይደለም፡፡ ከበደም በራሱ አቅምና ተፈጥሮ ብርታቱን የሚያሳይበትና የሚነሳበት ጊዜ አለውና፡፡
‹‹ለሁሉም ጊዜ አለው›› እንዳለው ጠቢቡ ሠለሞን እከሌ በስኬት ፏ ብሎ እኔ እስካሁን እዛው ነኝ ብለህ አትዘን፡፡ አንተም ጠንክረህ ከሠራህ ኑሮህን ታበራ ዘንድ ስኬት ካንተ ጎን የሚቆምበት ጊዜ ሩቅ አይደለም፡፡ ዋናው ነገር በስራ እየተጉ ጊዜውን በትዕግስት መጠባበቅ ብቻ ነው፡፡
💚መልካም 💛ቀን ለሁላችን❤️

👍3
#Re_post
#ያመት_በአል_ማግስት_ትእይንቶች!!
- የተመጠጠ ቤት
የሞላ ሽንትቤት
ጭር ያለ ቤተሰብ
የተጠረገ ድስት -ድርቅ የመታው ሞሰብ!!
-ያደፈ ቄጤማ
በበግ በሰው እግር- የተደቀደቀ
ወዙ ባንድ ሌሊት -ተመጦ ያለቀ
መጥረጊያ ሚጠብቅ -ወድቆ ተበታትኖ
ትናንት ጌጥ የነበር- ዛሬ ጉድፍ ሆኖ!!
-የተወቀጠ ፊት -የነጋበት ድንገት
በዳንኪራ ብዛት-ወለም ያለው አንገት
የዞረበት ናላ -ጌሾ ያበከተው
እንኳንስ መገንዘብ -መጀዘብ ያቃተው
የወለቀ ወገብ -የዛለ ትከሻ
መኪና ይመስል -ብየዳ የሚሻ
-የጠጅና የጢስ- ድብልቅ እስትንፋስ
ከሆድ ሸለቆ ውስጥ -የታፈነ ነፋስ
ባንጀት የታሰረው
እንደተከበበ አመፀኛ ሽፍታ
መውጫ የቸገረው!
-የማይፈካ ሰማይ -የማይዘንብ ደመና
በላባና በፈርስ -ያደፈ ጎዳና
በበግ ራስ ምላስ -የተልከሰከሰ
የጠገበ ውሻ-
በመንፈቅ አንድ ጊዜ አጥንት የቀመሰ::
ሀንጎቨር ያዛገው-መሂና አሽከርካሪ
እግረኛ አስደንባሪ
በከፊል የነቃ -በከፊል የተኛ
ከሱ የማይሻል- የመኪና እረኛ
ካውራ ጎዳናው ዳር -ቁሞ ሚያንቀላፋ
ድብርትን ባናቱ -እንደ ቆብ የደፋ!!
The moral of the story :
የተድላ ማገዶ!!
ላጭር ጊዜ ነዶ
ላጭር ጊዜ ደምቆ
ላጭር ጊዜ ሙቆ
አመዱ ብዙ ነው: አያልቅም ተዝቆ!!
🔘በውቀቱ ስዩም🔘
#ያመት_በአል_ማግስት_ትእይንቶች!!
- የተመጠጠ ቤት
የሞላ ሽንትቤት
ጭር ያለ ቤተሰብ
የተጠረገ ድስት -ድርቅ የመታው ሞሰብ!!
-ያደፈ ቄጤማ
በበግ በሰው እግር- የተደቀደቀ
ወዙ ባንድ ሌሊት -ተመጦ ያለቀ
መጥረጊያ ሚጠብቅ -ወድቆ ተበታትኖ
ትናንት ጌጥ የነበር- ዛሬ ጉድፍ ሆኖ!!
-የተወቀጠ ፊት -የነጋበት ድንገት
በዳንኪራ ብዛት-ወለም ያለው አንገት
የዞረበት ናላ -ጌሾ ያበከተው
እንኳንስ መገንዘብ -መጀዘብ ያቃተው
የወለቀ ወገብ -የዛለ ትከሻ
መኪና ይመስል -ብየዳ የሚሻ
-የጠጅና የጢስ- ድብልቅ እስትንፋስ
ከሆድ ሸለቆ ውስጥ -የታፈነ ነፋስ
ባንጀት የታሰረው
እንደተከበበ አመፀኛ ሽፍታ
መውጫ የቸገረው!
-የማይፈካ ሰማይ -የማይዘንብ ደመና
በላባና በፈርስ -ያደፈ ጎዳና
በበግ ራስ ምላስ -የተልከሰከሰ
የጠገበ ውሻ-
በመንፈቅ አንድ ጊዜ አጥንት የቀመሰ::
ሀንጎቨር ያዛገው-መሂና አሽከርካሪ
እግረኛ አስደንባሪ
በከፊል የነቃ -በከፊል የተኛ
ከሱ የማይሻል- የመኪና እረኛ
ካውራ ጎዳናው ዳር -ቁሞ ሚያንቀላፋ
ድብርትን ባናቱ -እንደ ቆብ የደፋ!!
The moral of the story :
የተድላ ማገዶ!!
ላጭር ጊዜ ነዶ
ላጭር ጊዜ ደምቆ
ላጭር ጊዜ ሙቆ
አመዱ ብዙ ነው: አያልቅም ተዝቆ!!
🔘በውቀቱ ስዩም🔘
👍1