አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///

ከዛ ጉሮሮውን አሟሸና መናገር ጀመረ"ከእድሜሽ በላይ ለማሸነፍ ስጥር ነው የኖርኩት…እናም ቡዙ ነገር አግኝቼ .. ብዙ ነገር አጥቻለሁ፣ ወጣቷ ሴት…ኪሳራ አያስደነግጠኝም። ሀብታም መሆን የበለጠ አስደሳች ነገር ነው፣ ግን ኪሳራም የበለጠ አስደሳች ነው። እራስን የሚያንፁና የሚገነቡ ጥቅሞች  አሉት። ››

‹‹ከከተማዋም አልፎ በሀገሪቱም የተሳካልህ የቢዝነስ ሰው መሆንህን አውቃለው፡፡ገንዘብ ስላለህም የፈለከውን ነገር በፈለከው ሰዓት ማድረግ እንደምትችል እንደምታምንም አውቃለው፡፡››አለችው በልበሙሉነት፡፡

"ታዲያ ካወቅሽ ይህን አስቂኝ ምርመራ ለምን አትተይውም?"ሲል ቀጥታ ወደሚፈልገው ርዕስ ገባ፡፡

"ይህ መቼም የሚሆን አይመስለኝም ..አላደርገውም››

"እናትሽን የገደልኩት እኔ እንደሆንኩ እንዴት ታስቢያለሽ? እሷ ከጁኒየር ምርጥ ጓደኞች መካከል አንዷ ነበረች:: በየእለቱ ከዚህ ቤት ትወጣና ትገባ ነበር::እርግጥ ካገባች በኋላ ብዙም አትመጣም ነበር… እናትሽን ለመጉዳት ጣቴን አንስቼ አላውቅም።››

አለም እሱን ማመን ፈለገች። በወንጀል ጉዳይ ተጠርጣሪ ቢሆንም እሷ ግን በጣም ታደንቀው ነበር። በውይይታቸው ከተገነዘበችው እና ለምርመራዋ ስትል ከሰበሰበችው መራጃ እንደተረዳችው ከምንም ነገር ተነስቶ ኢምፓየር መገንባት ችሏል።በማህበረሰቡ ዘንድ በጣም ተወዳጅ ነበር. አሳማኝ ባህሪ ነበረው። ነገር ግን በቀለማት ያሸበረቀ ስብዕናው ከጀርባ ሚሰራቸውን ቆሻሻ ድርጊቷች በቀላሉ እንዳይገለፁ ምክንያት እንደሆኑ በደንብ ታውቃለች።ቢሆንም ግን ለፍሰሀ ያላት አድናቆት እንደፍላጎቷ ሙሉና ጠንካራ አልነበረም..፡፡

ደገመችና ‹‹ምንም ቢሆን ምንም ምርመራውን ማቋረጥ አልችልም" አለች ።

‹‹ለምን ?››

" ብፈልግ እንኳን ዋና አቃቢ ህጉን በስንት መከራ ካሳመንኩት በኃላ ወደኃላ እንድመለስ መጠየቅ ያሳፍራል ፡፡"

"ስሚ" አለና አይኖቾን በትኩረት እያየ " ስህተት እንደሰራሽ ንገሪው፣ እናም ነገ በዚህ ሰአት እዚህ የመጣሽበትን ጉዳይ እንኳን እንደማያስታውስ ዋስትና እሰጥሻለሁ..ስራውንም ለቀሽ ወደአዲስአበባ መመለስና ቆንጆ የጥብቅና ቢሮ ማቋቋም ትችያለሽ….እናትሽ የልጄ የልብ ጓደኛ ነች…አንቺን ለማቋቋም የሆነ ነገር ማድረግ ለእኔ ያን ያህል የሚከብድ ጉዳይ አይደለም ።"

" አላደርገውም "

"እሺ፣ እንግዲያውስ ዋና አቃቢ ህጉን ለእኔ ተይልኝ..እኔ አናግረዋለው።"

"አቶ ፍሰሀ… ››ጮክ ብላ ተናገረች "የኔ ሀሳብ አልተረዳህልኝም"ትኩረቱን እንዳገኘች እርግጠኛ ስትሆን "ልጅህ በምርጫ ያለውን ተሳትፎ የሚጎዳ ምንም ነገር ለማድረግ እቅድ የለኝም…ያ እንዳይሆን አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንደማደርግና እያንዳንዱን እንቅስቃሴዬንና ምርመራዬን በከፍተኛ ሚስጥር እንደማከናውን ቃል እገባለው…ማድረግ የምችለው ያንን ብቻ ነው፡፡››

"የአንድ ሙሉ ከተማ የወደፊት ዕጣ ፈንታ አደጋ ላይ ቢሆንም ሀሳብሽን አትቀይሪም ማለት ነው?"

"ከተራቡ ህፃናት ዳቦ እየወሰድኩ ነው የሚመስልህ…?ነው ወይስ ያንተ ልጅ ይህቺን ከተማ ወክሎ የተወካዬች ምክር ቤት ከገባ በኩልፎ ወንዝ ወተት እንደሚንዠቀዘቅ እና ህዝቡ በቁንጣን እንደሚሰቃይ ነው የምታስበው?"

" ተይ እንጂ ..እኔ እንደዛ አላልኩም "

" እንግዲያው አቋሜን በግልፅ አሳውቂያለው..እኔ ሁላችሁንም በግል ለማጥቃትና ለማውደም ምንም እቅድ የለኝም…ግን ደግሞ የእናቴን ገዳይ ለፍርድ ለማቅረብ ህይወቴንም የሚያስከፍለኝ ቢሆን ግድ የለኝም..እስትንፋሴ እስካለች ድረስ ወደፊት እቀጥላለው››

‹‹በቃ የመጨረሻ ውሳኔሽ ይሄ ነው?"

‹‹አዎ..እኔን ማስቆሚያ ብቸኛው መንገድ እኔንም እንደእናቴ ማስወገድ ነው….በዛ ጉዳይ ላይ ልታስብበት ትችላላችሁ፡፡››

‹‹ንግግርሽ በጣም….››አቶ ፍሰሀ ንግግሩን አቋረጠ..እንደዛ ያደረገው ልጁ ጂኒዬር በራፉን ከፍቶ ስለገባ ነው፡፡

ጁኒየር በሩን በድንገት ከፍቶ አንገቱን ወደ ውስጥ አሰገገና"ሄይ, በሰላም ነው ..በጣም መሸ እኮ…እራት ሊቀርብ ነው" ፡፡

"በጣም ጥሩ ….ውይይታችን ጨርሰናል…..ግን እራቱ ይቅርብኝ ….ቀጥታ ወደቤቴ ነው መሄድ የምፈልገው››አለች አለም።

አቶ ፍሰሀ ንዴቱን መቆጣጠር አቃተው "እዚህ በቁም ነገር እየተነጋገርን ነበር። ዳግመኛ በግል ቢሮዬ ውስጥ ከሰው ጋር እያለው አንዳታቋርጠኝ፣ ።››
ጁኒየር "ንግግራችሁ በጣም ግላዊ ወይም በጣም ከባድ እንደሆነ አላውቅም ነበር።"ሲል ለአባቱ ቅሬታ ምላሽ ሰጠ፡፡

"አቶ ፍሰሀ.. እባክህ, ምንም አይደለም…በበቂ መጠን ተጋግረናል እኮ..የቀረም ነገር ካለ ሁለተችንም እዚሁ ከተማ ውስጥ ነን..ደጋግመን መገናኘታችን አይቀርም በእውነቱን ለመናገር፣ ጁኒየር ስላቋረጠን ደስተኛ ነኝ። ምን ያህል እንደመሸ አሁን ነው ያስተዋልኩት… አሁን መሄድ አለብኝ።"

ሁሉም ተያይዘው ወደሳሎን ተመለሱ፡፡ሳሎኑ ባዶ ነበር፡፡ገመዶም ሆነ ሳራ አልነበሩም፡፡

‹‹ለራት ብትቆይ ግን ደስ ይለኛል››አቶ ፍሰሀ ናቸው ተናጋሪው

‹‹አይ ይቅርብኝ..ደህና እደሩ››

ጁኒየር  ኮቷን ከያዘላት በኋላ መኪናዋ ድረስ ሸኛት ..ወደ እሱ ዘወር አለችና ።"ጁኒየር አመሰግናለው …ደህና እደር።"አለችው
" እጇን ያዘና ጎንበስ ብሎ ሳመው… ከዛ መዳፏን ወደ ላይ አዙሮ ሳመው። "የምታገኛቸው ሴቶች ሁሉ እንደዚህ ታሽኮረምማለህ?"

የማይገባ ፈገግታ ፈገግ አለላት ፡፡

"ለፍቅር በቀላሉ ተጋላጭ ነህ እንዴ?"ሌላ ጥያቄ አስከተለች፡፡ "እንደዛ ነኝ እንዴ..?አይ አይደለሁም."ፈገግታው እየሰፋ ሄዶ ፡፡
‹‹ለማንኛም መልካም ምሽት››አለችና መኪና ውስጥ ገብታ አካባቢውን ለቃ ተፈተለከች ጁኒዬር ወደቤት ተመለሰና ቀጥታ ወደእናቱ መኝታ ክፈል አመራ እና በስሱ አንኳኳ
‹‹እማዬ ፣ ልግባ?››

" ውዴ እባክህ ግባ" ሳራ ፈቀደችለት… በልጇ ጉብኝት በጣም እንደተደሰተች ግልጽ ነው። ርካሽ የንባብ መነፅሯን አውልቃ እያነበበች የነበረውን መፅሃፉ ከጎኗ አስቀመጠች፡፡

‹‹አትቀመጥም››

‹‹አይ  ይሁን››  አለና  አልጋው  ጎን  በመቆም፡፡ 

"መጽሐፉ  እንዴት  ነው?"  ሲል ጠየቃት፡፡መፅሀፉን ገዝቶ ያመጣላት እሱ ነበር፡፡

"በጣም አስደሳች ነው።››ስትል በአጭሩ መለሰችለት፡፡ "ጥሩ፣ ስለተደሰትሽበት ደስ ብሎኛል"

ሳራ እናቱ እንደመኆኗ መጠን በውስጡ የሚገላበጠውን ጭንቀት ተረዳችና። "ምንድነው ችግሩ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

"ምንም።"

"አንድ የተሳሳተ ነገር ሲኖር ማወቅ እችላለሁ."
"ከተለመደው የተለየ ነገር የለም ከአሌክስ..ማለቴ ከአለም ጋር የነበራቸውን ውይይት በማቋረጤ አባቴን አበሳጭቼዋለው››

"አባትህ የጋራችን በሆነው መኖሪያ ቤታችን ውስጥ ሲኖር ራሱን እንዴት መምራት እንዳለበት እስካሁን አልተማረም። በቤታችን የጋራ እንግዳችን ሆና የመጣችን ሴት ለግል ውይይት ብሎ ክፍል ውስጥ በማስገባት ማዋራት ጨዋነት የጎደለው ተግባር ስለሆነ አንተም ፣ ውይይቱን በማቋረጥ ባለጌ የመሆን መብት አለህ።››አለችው

‹‹እማዬ…››

"ለማንኛውም በግል ምን እየተወያዩ ነበር?"

"ስለ እናቷ ሞት ይመስለኛል….ምንም የሚያስጨንቅ ነገር የለም."

"እርግጠኛ ነህ? ዛሬ ማታ ሁሉም ሰው በጣም የተጨናነቀ ስሜት ላይ እንዳለ መረዳት ችያለው።"

" ችግርም ካለ አባዬ ሁል ጊዜ እንደሚያደርገው ይቆጣጠረዋል። በእርግጠኝነት ምንም የሚያስጨንቅ ነገር አይኖርም።››
38👍4