አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
491 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
//////

ዔሊያስ በፀጋ አልጋ ጥግ ላይ ቆሟል፡፡ማንኛውም ሕፃን ከማሽን ጋር ተጣብቆ ማየት ሁል ጊዜ ጥልቅ ሀዘን ውስጥ ይጨምረዋል ፡፡እንደፀጋ አይነት የሚያውቃትና የሚቀርባት ልጅ ስትሆን ደግሞ ነገሩ ከባድ ነው የሆነበት ..በዛም ምክንያት እሱ ዛሬ ጠፍቷል፣ ግን ለማንኛውም  ከልምዱ ወጥቶ ወደ ተቆጣጣሪ ማሽኖቹ  ተመለከተ። ምንም ለውጥ የለም።በአንድ በኩል ማመስገን ያለበት ነገር ነበር።በሌላ በኩል፣ አሁን ለሃያ አራት ሰአታት ራሷን ስታ ቆየች ማለት ነው። እና ለምን እንደሆነ አላወቀም. ተአምር እስኪፈጠር ድረስ ከመጠበቅ ውጭ  ምን ማድረግ እንደሚችል   ምንም ሀሳብ አልነበረውም።

ከዚያን ቀደም  ብዙ ነገር ሲከሰት አይቷል። ልክ እንደ ራሄል በልጁ አልጋ አጠገብ ሲያንዣብቡ ለነበረሩ ወላጆች አሳዛኝ ዜና አቅራቢ ሆኖ ያውቃል ።የወንድሙ ሚስት  በካንሰር ስትሞት በዛ ምክንያት ወንድሙ ሲሰቃይ ተመልክቶ ነበር።
የፀጋ ወላጅ እናት ትዝ አለችው፡፡ጽጌረዳ፡፡አሁን በዚህች ደቂቃ ልጇ ያለችበትን ሁኔታ ሰምታ ብትመጣና ለመጨረሻ ጊዜ  ብትሰናበታት ደስ ይለው ነበር፡፡ግን አድራሻዋን ካልታወቀ ምን  ማድረግ ይቻላል?፡፡አንድ ቀን ከአመት ወይም ከአስር አመት በኋላ ካለችበት መጥታ‹‹ ልጄስ የት ነው ያለችው? ››ብላ ስትጠይቀው…መቃብር ቦታ ወስዶ ሲያሳያት በአእምሮው ሳለና ዝግንን አለው፡፡‹‹እግዚያብሄር ሆይ እባክህ እርዳኝ››ሲል ለአምላኩ ተማፅኖ አቀረበ፡፡

‹‹እንዴት ነች?›› የራሄል ድምፅ  ነበር ከሀሳቡ የመለሰው።

‹‹ ..ምንም ለውጥ የለም …ነገሮች ባሉበት እየሄዱ ነው.›› ወደ እሷ ዞረ፣ በዓይኖቿ ውስጥ  ፍርሀት ይነበባል፡፡

‹‹ተኝተሻል?››

‹‹ትንሽ ›› ራሄል ፈገግ አለችለት፣
ከዚያም አንገቷን በቀስታ ዞረች፣

‹‹ሴቶቹ ሄዱ?››ሴት ጓደኞቾ  ሊጎበኟቸው መጥተው ነበር፣ እና በእሱ እርዳታ ራሄልን ለጥቂት ጊዜ መተኛት ችላለች ። እሷ በተኛችበት ጊዜ ጓደኞቾ በፀጋ አልጋ አጠገብ ተንበርክከው ሲፀልዩላት አይቶ  ነበር።

‹‹አዎ ሄደዋል…ብዙ ቆዩ እኮ››

‹‹ደህና …በመምጣታቸው በጣም ደስ ብሎኛል….እንደዚህ አይነት ጥሩ ጓደኞች ስላለሽ እድለኛ ነሽ››የሚል አስተያየት ሰጣት ፡፡

ራሄል በቀስታ ጉንጯን እየዳበሰች ‹‹አዎ ልክ ነህ…ለጸሎታቸው በጣም አመስጋኝ ነኝ።››አለችና ወደ ፀጋ ሄደች።
በቀስታ መዳፏን  ግንባሯ ላይ አሳረፈች ‹‹ስነካት ይታወቃታል እንዴ?›› ብላ ጠየቀችው፡

‹‹አንዳንድ የአካላቷ ክፍል ሴንስ ሊያደርግ ይችላል ። ግን ያንን የምንለካበት ምንም መንገድ የለንም።››

‹‹ግን ከዚህ ኮማ ትነቃለች አይደል? ስትነሳ እንደበፊቱ  እራሷን ትሆናለች አይደል?››ጥያቄዎቾ ሁሉ ጭንቀት የወለዳቸው ናቸው፡፡
እሱም ከእሷ ባልተናነሰ በመጨነቅ‹‹ሁሉም ነገር ደህና መሆኑን ብነግርሽ ደስ ይለኝ ነበር››አላት፡፡

በዚህ ሆስፒታል ውስጥ በህፃናት ሀኪምነት ካሳለፈው ከማንኛውም ጊዜ በላይ  አቅመ ቢስነት  ተሰማው።‹‹ፀጋ የራሷ የሆነ ችግር አለባት ፤ ነገር ግን የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነው።››አለና ወደራሄል ተጠግቶ  እጇን በእጁ  ያዘው።

‹‹ዶክተሯ ስለሆንክ ደስ ብሎኛል››አለችው።

‹‹እዚህ በመሆናችሁ ደስ ብሎኛል.››እጇን  ጨመቀ ፣ -ጸጋ በእሱ  እጅ ፈውስ ታገኝ ዘንድ ተመኘ። እሷን ከኮማ እንድትወጣ ለማድረግ ትክክለኛውን መድሃኒት በፀጋ ደም ስር  ማስገባት ይችል ዘንድ  ተመኘ። በራሔል ፊት ላይ ፈገግታ መመለስ ይችል ዘንድ ተመኘ… ያን ሁሉ ነገር ማድረግ ቢችል ተመኘ።ስለ ወላጆቹ ሊነግራት ፈለገ, ለምን እንደገፋት ሊያስረዳት ፈለገ. ነገር ግን ከመናገሩ በፊት አንዲት ነርስ ወደ በሩ መጣች።

‹‹ራሄል ቸርነት? ወላጆችሽ እዚህ ናቸው።››አለቻት፡፡

ድንጋጤ  የተቀላቀለበት ብስጭት በእሱ ውስጥ ፈሰሰ።.ራሄል እጁን የበለጠ ጨመቀች፡፡

ነርሷ ራሔልን ‹‹በአንድ ጊዜ ሁለት ጎብኝዎች ብቻ ናቸው ወደ ውስጥ መግባት የሚችሉት  …ስለዚህ እነሱ ከገቡ መውጣት አለብሽ።››ስትል አስጠነቀቀች።
ወደ ፀጋ ዞር ብላ ተመለከተች እና ‹‹ገባኝ።››አለቻት።

ደ/ር ኤልያስ የአቶ ቸርነት እና የትርሀስ  ጸጥ ያሉ ድምጾችን እና የራሄልን ዝቅተኛ ምላሽ እስኪሰማ ድረስ በአልጋዋ አጠገብ ቆየ።የራሄል እናት  አቶ ቸርነት  እየገፏቸው  በዊልቸር ላይ ነበሩ፣ ። ሀኪሞቹ  ለልጃቸው ምን እየሰሩ እንደሆነ  በአጭሩ አስረዳቸው እና… የተሻለ ዜና ሊነግራቸው ቢችል ደስተኛ ይሆን እንደነበረ በፀፀት ስሜት ነገራቸው፡፡

‹‹በሰው የሚቻለውን ሁሉ እንደምታደርጉ እናምናለን›› አሉ አቶ ቸርነት፡፡የሚያጽናና እጃቸውን በዔሊያስ ትከሻ ላይ ዘረጉና።

‹‹እኛ ከትንሿ ልጃችን  ጋር ስለምንቆይ  ለምን ራሄልን ለጥቂት ሳዕታት ማረፍ ወደምትችልበት ቦታ  አትወስዳትም.››አሉት
እሱም መስማማቱን ጭንቅላቱን በመነቅነቅ አረጋገጠላቸው፡፡
‹‹ይቅርታ እማዬ…አደራችሁን መወጣት እልቻልኩም››አለች እና እንባዋ እርግፍ አለ!! ከዛ እናቷን ለመሳም ጎንበስ አለች፡፡

እናትዬው የልጇን ፊት በእጆቿ አሻሸች‹‹ልጄ እህትሽን በአደራ አልሰጠሁሽም..እሷ ለሁላችንም የእግዚያብሄር አደራ ነች…የተቀበልናት ከእግዚያብሄር ነው….አይ እፍልጋታለው ብሎ  መልሶ ከወሰደብንም ከእሷ ጋር ስላሳለፍናቸው ጣፋጭ ወራቶች ከማመስገን ውጭ ምንም ማለት አንችል ..ብቻ በዚህ አይነት ጉዳይ ዳግመኛ ወደዚህ ሆስፒታል  እንድትመጪ ስላደረኩሽ አዝናለሁ።››

ራሄል እንባዋን ዘረገፈችው‹‹እማዬ እኔ እኮ እምነቴ እንደእናንተ ጠንካራ ቢሆን ደስ ይለኝ ነበር..ግን አልችልም››

ወ.ሮ ትርሀስ‹‹ልጄ፣ትቺያለሽ ልብሽን ብቻ አለስልሺው… ይሄ የእኔ ስህተት ነው ብለሽ ለአንድ ደቂቃ እንኳን እንዳታስቢ…እሷን ለመርዳት በአቅራቢያዋ ስለነበርሽ ደስ ብሎኛል. እግዚያብሄር ይሁን ያለው ነገር  ማንም ከመሆን ሊያግደው አይችልም.››በማለት የራሔልን ጭንቅላት ወደ ታች ጎትተው ግንባሯ ላይ ሳሟት።
ቀጥለው የተናገሩት አቶ ቸርነት ናቸው‹‹ አሁን ሄደሽ ቡና ጠጪ። ትንሽ እርፍት ውሰጂ እኛም ከናፈቀችን ልጃችን ጋር ትንሽ እንቆይ ።››ራሄል ደካማ ፈገግታ ሰጠቻቸውና, ክፍሉን ለቃ ስትቀወጣ  ኤልያስ ከኋላዋ ተከተላት፡፡

‹‹ከእኔ ጋር መምጣት የለብህም››

‹‹አይ መምጣት ስለምፈልግ ነው፣…እንደውም ተከተይኝ ቆንጆ እርፍት የምታደርጊበት ያልተያዘ ክፍል አውቃለው፡፡››አለና ክንዷን ይዞ እየመራ ወሰዳት…ክፍሉን ከፍተው ሲገቡ ግን እንደጠበቁት ባዶ አልነበረም ፡፡ ሲገቡ አንድ ወጣት ባልና ሚስት  ከአልጋው ተነሱ..እና ለመውጣት ወደበሩ ተንቀሳቀሱ።

‹‹እባካችሁ በእኔ ምክንያት አትውጣ››አለችው ራሄል።

ሴትየዋ በከፍተኛ ፈገግታ ‹‹እኔና ባለቤቴ እየሄድን ነበር፣እዚህ ያለንን ቆይታ ጨርሰን ወደቤታችን እየሄድን ነው…››አለች

‹‹ለዚያ አመሰግናለሁ.››ወጣቱ እጁን በሚስቱ ትከሻ ላይ አድርጎ አቀፋት፡፡ እሷን ዘና ብላ ራሷን በትከሻው ላይ አስተኛች።ዔሊያስ የቅናት ስሜት ተሰማው። ደስተኛ ሆነው ይታዩ ነበር። እሱ እና ራሄል እንዲኖራቸው  የሚፈልገው እንዲህ አይነት ፍቅር እና መፈቃቀድ ነው ።በሩ ከኋላቸው ተዘግቶ ሳለ፣ ፊቷ የናፍቆት መልክ ይዞ ራሄልን እያያቸው ያዘ።

‹‹ወደ ቤታቸው መሄድ በመቻላቸው ደስ ብሎኛል››አለች በለስላሳ።
ክፍሉ ውስጥ ግድግዳ ተጠግቶ ካለ ሶፋ ላይ ተቀመጠና በረጅሙ የእፎይታ ትንፋሽ ተነፈሰች፡፡
50👍3🥰1