አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

////

ተደግፋ በተቀመጠችበት   ወንበር ላይ ተኮራምታ ነው ያደረችው፡፡በጥዋቱ ተረኛ ዶክተሮች መጥተው እህቷን ቢመለከቷትም ምንም የተቀየረ ነገር አላገኙም…..ይህ  መሆኑ ደግሞ ራሄልን  ይበልጥ ተስፋ ቢስና ረዳት አልባ ስሜት እንዲሰማት አደረጋት፡፡መፅሀፍ ቅዱሷን አነሳችና …አነስተኛ ወንበር  እህቷ አልጋ አጠገብ በማድረግ የፀጋን ትንሽዬ ጣት ይዛ መፀለይ ጀመረች…አምላክ ለሁለተኛ ጊዜ ልቧን እንደማይሰብራት ተስፋ አድርጋለች፡፡ ድንገት ቀና ስትል ዔሊያስ  የሕፃናት ሕክምና አይሲዩ  በር ላይ ቆሞ ተመለከተችው፣ ልቡ ከብዷል። ስለ ፀጋ እንዳወቀ ወደ ሆስፒታል በፍጥነት ነው የመጣው።

ኤልያስ ወደ ክፍሉ ከመምጣቱ በፊት የህክምና ቻርቱን  አንብቦ መድሃኒቱን ሁለት ጊዜ ፈትሾ ነበር ….የፀጋን  አሁናዊ ሁኔታ እና እየተደረገላት ያለውን እንክብካቤ ከህፃናት ሐኪም ጋር ተወያይቷል. ሁሉም ምርመራዎች ታዝዘዋል እና ረፋድ ላይ ሌላ ሲቲ ስካን ማድረግ እንደሚያስፈልጋት ተወስኗል።ፀጋ ለጊዜው ራሷን ስታለች ግን የተረጋጋች ነበረች።በአሁኑ ጊዜ ኤልያስን  በጣም ያሳሰበው ከፀጋ እጅ ጋር የተጣበቀችው እና የገረጣችው ሴት ሁኔታ ነው፣ በመጋረጃዎቹ ክፍተት መሀል   አልፎ የሚመጣው የጠዋት ብርሃን  ጭንቅላቷ ላይ አርፎ ይታያል .. መጽሃፍ ላይ አቀርቅራ እያነበነበች ነው ። ራሔል  አንድ ጊዜ  ስልክ ለመደወል ከፀጋ ጎን ከመነሳቷ ውጭ  ሌሊቱን ሙሉ  ከጎኗ ሳትንቀሳቀስ እንዳሳለፈች ነርሷ ነግራዋለች፡፡

ለመጨረሻ ጊዜ እሱ ቤት መጥታ በመጥፎ ሁኔታ ካስተናገዳት በኋላ ከእርሷ ጋር የመነጋገር መብት እንደሌለው ተሰማው። በወቅቱ ባለበት ንዴት ተነስቶ በሰራው ስህተት በጣም ተቆጭቶ ስህተቱን ለማረም  በመፈለግ ለእሷን ለመደወል ፈልጎ ነበር ..እሷን ማስቀየሙ እንዴት ህይወቱን እንዳመረረበት ሊነግራት ፈልጎ ነበር ። ለምን በእሷ ላይ እንደዛ እንደሆነ እና ስለወላጆቹ ማንነት ያወቀው አዲስ መረጃ  ውስጡን እንዴት እንደሰባበረው ሊያስረዳትና አዝናለት ይቅር እንድትለው ለመጠየቅ ፈልጎ ነበር…ግን አንዱንም ማድረግ ሳይችል  ነው.. ቆይ በኋላ ..ቆይ ትንሽ ልቆይ ሲል ድንገት ዛሬ ጥዋት ከሆስፒታል ተደውሎለት ስለፀጋ በአደገኛ ሁኔታ መታመም እና ለሊቱን ሙሉ ሆስፒታል እንዳደረች  የተነገረውና ሲሮጥ የመጣው፡፡

አዎ አሁን ትልቅ ሰው ነው… አዎ እሱ የበለጠ ጥበበኛ ነው። አዎን፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ ጠንካራ ቦታ አለው።ያ ሁሉ ቢሆንም ግን ከወላጆቹ የተቀዳ ተመሳሳይ ድክመት  በደም ሥሩ ውስጥ ሊፈስ እንደሚችል  መገመቱ አልቀረም ። ብዙውን ጊዜ አንድ ልጅ ከወላጆቹ የሚወርሳቸው ጥሩም ሆነ መጥፎ የባህሪ ውርሶች  እንደሚኖሩ ለማወቅ በቂ የታካሚ ታሪኮችን አንብቧል.፡፡ራሄል በቤቱ ልትጠይቀው ስትመጣ መረጃውን ለመቀበል እየሞከረ ነበር…በህይወቱ ውስጥም የት ቦታ ሊያስቀምጠው እንደሚችል  ለማወቅ በመጣር ላይ ነበር…. በዛ ምክንያት ነበር እሷን ሊያስቀይማት የቻለው፡፡

በጸጥታ ወደ ክፍሉ ገባ፣ አይኑ ወደ ተቆጣጣሪ  ማሽኖቹ ተመለከተ፣ እየፈተሸ፣ እየለካ። ወደ አልጋው አጠገብ ሲደርስ ራሄል .ተስፋ ቆርጣ ታነብ ከነበረው መጽሐፍ ቀና ብላ ተመለከተችው። ፊቷ እርብሽብሽ ብሏል  እና ስታለቅስ ተመለከተ።

ፊቷ ላይ ያለው ህመም በግልፅ ይነበባል። ለሌሎች ታካሚ  ወላጆች እንደሚያደርገው አይነት በርህራሄ የተሞላ እንክብካቤ ሊያደርግላት ከጎኗ ቆመ። ማድረግ የፈለገው ግን ወደ እቅፉ ጎትቶ ደረቱ ላይ ለጥፎ ግንባሯን ደጋግሞ ለመሳም ነበር፡፡ ሊያበረታታት እና  ሊያፅናናት ነበር ሚፈልገው ።

‹‹ደህና ትሆናለች?››አላት፡፡

ራሔል ቀና ብላ ተመለከተችው፣

‹‹ለአሁን የተረጋጋች ናት›› ሲል አከለበት፡፡ 

በዝምታ እያዳመጠችው ነው፡፡

‹‹ሲቲ ስካን ሰርተንላታል እና ስለ ደም ዝውውሯ ከላቦራቶሪ ውጤት በኋላ እናውቃለን ።››

የራሄል እንባ ዝርግፍ አለ…ከተቀመጠችበት ተነሳችና  ቆመች ፡፡በእጇ ይዛ ነበረውን መፅሀፍ አጠፈችውና ማውራት ጀመረች

‹‹ጉንፋን ብቻ ነበር ያመማት..ድንገት በዚህ ደረጃ እንዴት አቅም ልታጣና እራሷን ልትስት ቻለች?››ስትል ጠየቀችው፡፡

ዔሊያስ ራሱን ነቀነቀ።

‹‹አናውቅም… ከዚህ በፊት እንደነገርኩሽ የፀጋ የጤና ችግር ተደራራቢና የተወሳሰበ ነው….. አንዱ በሽታ ሲጀምር ሌላውም ይከተላል…አሁን በጣም አደገኛ የሆነው በአእምሮዋ ውስጥ የተፈጠረው ችግር ነው፡፡

‹‹ከዚህ ስቃይ  ትወጣለች?››

‹‹በአጠቃላይ ያቺ  ትንሽ ልጅ ሳንባዋ ጥሩ ነው፤ልቧ ጠንካራ ነው። ከዚህ በሽታ እንደምታገግም አምናለሁ።››

ራሄል በሚናገርው ነገር ላይ እርግጠኛ እንዳልሆነ ተረዳች፡፡ ‹‹እግዚአብሔር በእርሱ እንድንታመን እንዴት እንደሚነግረን እና የልባችንን መሻት እንዴት እንደሚሰጠን እያነበብኩ ነበር…ይህን ታምናለህ?››ዔሊ ወደ ፀጋ ከዚያም ደግሞ  ወደ ራሄል እያፈራረቀ ተመለከተ፡፡

‹‹እኔ በዚህ ወቅት  ምን ማመን እንዳለብኝ አላውቅም። ለፀጋ የምንችለውን ሁሉ እያደረግን እንደሆነ አውቃለሁ። እና እሷን በሕይወት ለማቆየት ባለን ቴክኖሎጂ ላይ እምነቴን ማሳረፍ እመርጣለው።››

ራሄል የደከመ ፈገግታ ፈገግ አለችለት‹‹ከዚህ በፊት አንድ ጊዜ እግዚያብሄርን  አመንኩኝ እና አሳዘነኝ. ..ማለቴ ስለ ኪሩቤል እያወራሁ ነው?››ራሷን ነቀነቀች፣ ከዚያም ቀና ብላ ተመለከተችው…በዛ ቅፅበት  ነርሷ ወደ ፀጋ አልጋ መጣች።

‹‹ነርሷ ለሰዓታት እዚህ እንደተቀመጥሽ ነገረችኝ…ሄደን ቡና ብንጠጣ ምን ይመስልሻል? እስክንመጣ እዚህ ያለውን ነገር ነርሷ  ትከታተለዋለች?›› አለና  በቀስታ እጇን ጎተታት።

‹‹እኛ ስንሄድ ፀጋ ደህና ትሆናለች?።››ስትል ጠየቀች፡፡

ነርሷ እያስተካከለችው ያለውን መቆጣጣሪውን ቀና ብላ ተመለከተች..ወደ ዶ/ር ኤልያስ ተመለከተችና ‹‹አንድ ነገር ከተቀየረ ወዲያውኑ አሳውቅሃለሁ››አለችው ።

‹‹ለአሁን ነገሮች ደህና ሆነው ይታያሉ።››ራሄል ወደ ፀጋ  ተመለከተች፣ ፡፡ጥላት መውጣቷ ብዙም ምቾት አልሰጣትም፡፡

በለሆሳሳ‹‹እሺ ..እንዳልክ እንሂድ››አለች ።ኤሊያስ መጽሐፍ ቅዱስን ከእጇ ወስዶ ከፀጋ አልጋ አጠገብ ባለው ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው። ከዚያም ከክፍሉ ይዟት ወደ ካፍቴሪያ ሄደ፡፡ወንበር ስበው ፊት ለፊት እየተዩ ተቀመጡ፡፡የሚፈልጉትን አዘዙ፡፡

አሁንም ከፀጋ ውጭ ምንም ነገር በአእምሮዋ የለም..‹‹ትናንት ከሰዓት ነው፡፡ትንሽ እንደመሻል ብሏት ነበር… ከእኔ በቅርብ ርቀት ሶፋው ላይ ሆና ስትጫወት ነበር…ድንገት አንሸራተታት እና ለስላሳ የቆዳ ሶፋ ላይ ወደቀች እና በጭንቅላቷን ወደኋላ ተኛች… ከዛ ተዝለፍለፈችብኝ..ጮህኩ..ወዲያው አምቡላንስ ተጠራ…ወደዚህ ይዘውን መጡ…..ይሄው እየባሰ ከመሄድ  ውጭ ምንም መሻሻል አላየሁም፡፡››

‹‹አይዞሽ……ሁሉም ነገር ሰላም ይሆናል››

ያዘዙት ነገር መጣላቸው…..እሷ ጥቁር  ቡና ብቻ ነበር ያዘዘችው፡፡

ትኩር ብሎ ሲያያት ያዘችው….ፀጉሯን ከፊቷ ላይ ገፋች እና ‹‹የባቡር አደጋ  የደረሰብኝ መስያለው አይደል?››

ከዚህ በፊት አይቷት ከነበረው በተለየ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ እየተመለከታት ነው ፡፡የለበሰችው ልብስ የተዘበራረቀ እና የተዝረከረከ አይነት ነው… ምንም አይነት ሜካፕ አልተጠቀመችም እና ፊቷ ተጎሳቅሏል እና ደክሟታልል።
59👍1🥰1
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ድርሰት__በዘሪሁን_ገመቹ
……

ከባለፈው ክፍል ተቆርጦ የቀረ

///
ዝግጅቱ በተዘጋጀበት የከተማዋ ግዙፉ ሆቴል የጁኒዬርን እጅ ይዛ ስትገባ ደስ የሚል ስሜት ነው የተሰማት፡፡ ለስለስ ያለ ምርጥ ሙዚቃ እና እዚህማ እዛም በፈገግታ የታጀበ ሳቅ ይሰማ ነበር፡ከበርካታ ሰዎች ጋር አስተዋወቃት…ከብዙ ሰዎች ጋር የማውራት እድል አገኘች፡፡ አንዳቸውም ውይይቶች በእናቷ ግድያ ዙሪያ ያተኮሩ አልነበሩም። ያ በራሱ መንፈስን የሚያድስ ለውጥ ነበር። እረፍት ላይ እንዳለች መስሎ ተሰማት። ጁኒየር በመጠጥ ተፅዕኖ ውስጥ ገብቶ ሚስጥሩን ለእሷ አሳልፎ እንደሚሰጣት ቀድሞውንም አላመነችም። እሷ ምንም አስገራሚ ኑዛዜዎችን የመስማት ዕድል እንደሌለት ገምታ ነበር።ቢሆን ከምሽቱ አንድ ጠቃሚ ነገር ሊወጣ ይችላል የሚል ተስፋ መሰነቋ ግን አልቀረም. ፡፡
ከሁሉም በላይ፣ ከአካባቢው ነዋሪዎች፣ ከአቶ ፍሰሀ እና ከኩማደሩ ጋር በደንብ ከሚተዋወቁ እና ባህሪያቸውንና ድብቅ ተግባራቸው ከሚያውቁ ሰዎች ጋር የመቀላቀል እድል አላት፡፡
እንደተለመደው "ነጭ ወይን"ይዛ እየጠጣች ነው ጁኒዬር ከጎኗ አለ፡፡

"ሙዚቃው የእኔ ጣዕም አይደለም ነገር ግን መደነስ ከፈለግሽ እኔ ታዛዥ ነኝ.››አላት

ጭንቅላቷን በአሉታ ነቀነቀች። "አመሰግናለሁ …እኔ ከመደነስ ይልቅ ማየት እመርጣለሁ።››

ከጥቂት ዘፈኖች በኋላ ጁኒየር ጠጋ ብሎ በሹክሹክታ፣"እናትና አባቴ እዛ ጋር ናቸው….ሰላም እንበላቸው›› አለና..እየጎተተ ይዟት ሄደ፡፡
አለም በዳንስ ወለል ዙሪያ ለመመገቢያ ወደተዘጋጁት የጠረጴዛዎች ስብስብ አብሮት ሄደ። ሳራ ጆ እና አቶ ፍሰሀ በአንድ ላይ ተቀምጠዋል። ደረሱና

"ጤና ይስጥልኝ ወይዘሮ ሳራ ዛሬ ማታ ቆንጆ ሆነሻል።››አለቻት አለም

‹‹አንቺም እንደዛው ….እንኳን በሰላም መጣሽ››ስትል መለሰችላት፡፡

ሰላምታ  ተለዋውጠው  አንድ  ጠረጴዛ  ከበው  የየግላቸውን  መጠጥ  በመጠጣት ጫወታቸውን ጀመሩ፡፡

‹‹የሙስጠፋን የሞተ  አካል ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘሽው አንቺ  እንደሆንሽ  ሰማሁ››።ሲል ኮስተር ባለ ነገር ጫወታውን የጀመረው አቶ ፍሰሀ ነበር፡፡

"አባዬ  ይህ  ፓርቲ  ነው…አለም  ስለ  እንደዚህ  አይነት  መጥፎ  ነገር  ማውራት አትይፈልግም."አለ ጁኒየር።

"አይ፣ ምንም አይደለም፣ ጁኒየር፣ ይዋል ይደር እንጂ እኔ ራሴ አነሳው ነበር።››

"ጥሩ ..ከሱ ጋር የተገናኘሽው በአጋጣሚ ነው ብዬ አላስብም።ያንን ደደብ ሽማግሌ ለምን ነበር ልታገኚ የፈለግሽው?"

"አይ….።››በማለት ከሙስጠፋ ጋር የነበራትን የስልክ ውይይት በዝርዝር ነገረቻቸው፡፡

‹‹ያ ውሸታም ሽማግሌ ሊያታልልሽና አንቺን አጓጉቶ ገንዘብ ሊቀበልሽና ..እግረ መንገዱንም እኔን ለመበቀል ሲያደባ ነበር…ግን ፈጣሪ የልቡን ተንኮል አይቶ ለሌላ ወንጀለኛ አሳልፎ ሰጠው፡፡››
"ኦህ፣ እንዴት በእርግጠኝነት እንደዛ ደመደምክ..?››

‹‹ ሙስጠፋ ከሰሎሜ ጋር ወደዚያ በረት ውስጥ የገባው ማን እንደሆነ አይቶ ሊሆን ይችላል፣ ግን የእውነት እንደሚለው ሰው አይቶ ከሆነ ሊያይ የሚችለው ሊቁን ነው።››ሲል ጁኒዬር አከለበት፡፡
አለም ..ለመናገር የፈለገውን ከተናገረ በኋላ …እንዲከራከር እድል አልሰጠችውም ፣ የሙስጠፋ ርዕስ ለጊዜው ባለበት እንዲቆም አደረገች ።መጠጣቸውን እንደጨረሱ፣ አቶ ፍሰሀ እና ጁኒየር ሴቶቹን ባሉበት ጥለው ሌሎች የቢዝነስ ሰዎችና ለማነጋገር ተያይዘው ሄዱ፡፡
ከሳራ ጆ ጋር ለረጅም ደቂቃዎች መቆየት ከባድ ነው ..ከእሷ ጋር ማውራትም ቀላል እንደማይሆን አሰበች፣ቢሆንም እንደምንም እራሷን አጀግና "ለረጅም ጊዜ የዚህ ማህበር አባል ናችሁ?"የሚል ጥያቄ ሰነዘረችላት፡፡

"ፍሰሀ ከመስራች አባላት አንዱ ነበር" ስትል ሳራ ግድ በሌለው ሁኔታ መለሰችላት ።
በመድረኩ ላይ በርካንታ ጥንዶች እየደነሱ እና እየተጎነታተሉ ይታያሉ፡፡አለም"አቶ ፍሰሀ በእያንዳንዱ የከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ እጁ ያለበት ይመስላል " ስትል አስተያየት ሰጠች.
"ትክክል ነሽ…የከተማዋ ጠባቂ እንደሆነ ነው የሚያስበው… እየሆነ ያለውን ሁሉ ማወቅ ይፈልጋል….በዛ ምክንያት ..ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር ሲል ሁሉም ነገር ውስጥ ይገባል››ሳራ በረጅሙ ተነፈሰች እና ንግግሯን ካቆመችበት ቀጠለች "አየሽ ፍሰሀ በእያንዳዱ የከተማው ኑዋሪ …በባለስልጣናቱም ዘንድ ሆነ በነጋዴዎች ክበብ የመወደድ ፍላጎት አለው
፤ እሱ ሁል ጊዜ ፖለቲከኛ ነው ፣ ››
አለም እጆቿን ከአገጯ በታች አጣጥፋ በክርኖቿ ጠረጴዛው ላይ ተደግፋ። "አንቺ ያ.. አስፈላጊ ነው ብለሽ ታምኚያለሽ?"

"አይ አላንም።" አለችና ለመጀመሪያ ጊዜ አለምን በትኩረት  ተመለከተች።

"ጁኒየር ለአንቺ የሚያሳይሽን እንክብካቤ ብዙም ትርጉም አትስጪው››በማለት አዲስ ርዕስ ከፈተች፡፡

"አቤት…ምን ማለት ነው?"

"ልጄ የሚያገኛት ሴት ሁሉ የማሽኮርመም ልክፍት አለበት እያልኩሽ ነው ››

አለም ቀስ ብላ እጆቿን ወደ ታች አወረደች። ንዴቷ ወደ ውስጥ ገባ፣ ነገር ግን ድምጿን ዝቅ አድርጋና እራሷን እንደምንም ተቆጣጥራ “ወ/ሮ ሳራ አንድምታይው ተናድጃለሁ።››

ሳራ ጆ በግዴለሽነት አንድ ትከሻ ከፍ ዝቅ አደረገች‹‹ግድ የለኝም ››የሚለውን መልዕክት ለማስተላለፍ ፈልጋ እንደሆነ አለም በግልፅ ገብቷታል፡፡

"ሁለቱም ወንዶቼ ቆንጆዎች ናቸው እና እነሱም ያንን ስለሚያውቁ አላግባብ ይጠቀሙበታል..አብዛኛዎቹ ሴቶች ደግሞ የእነሱ ማሽኮርመም ትርጉም የለሽ እንደሆነ አይገባቸውም."

" እርግጠኛ ነኝ ፍሰሀን በተመለከተ ያልሽው እውነት ነው፣ ስለ ጁኒየር ግን አይመስለኝም።
ሶስት የቀድሞ ሚስቶች ስለ እሱ ማሽኮርመም ከአንቺ ጋር ላይስማሙ ይችላሉ።››

"ሁሉም እሱን በተመለከተ ተሳስተው ነበር።"

"እናቴስ? እሷም እሱን በተመለከተ ታሳስታ  ነበር?"ሳራ ባዶ አይኗን አሌክስ ላይ በድጋሚ ተከለች።

"አዎ ተሳስታለች ፤አንቺም እንደሷ  ነሽ ….ታውቂያለሽ አይደል?።"

"እኔ?"

" አዎ!!አለመግባባት መፍጠር ያስደስትሻል። እናትሽ አስጨናቂ ነገሮችን በመፍጠር እርካታ አልነበራትም። ልዩነቱ አንቺ ከሷ በላይ ችግር እና መጥፎ ስሜትን በመፍጠር የተሻልሽ መሆንሽ ብቻ ነው። ብዙውን ጊዜ ብልሀት የሚጎድልሽ ቀጥተኛ ሴት ነሽ።››ዓይኖቿን ከአለም ጀርባ አሻግራ አንድ ሰው ትመለከት ጀመረ፡፡

"ደህና አመሻሽ ሳራ "

"ዳኛ ዋልልኝ" ጣፋጭ ፈገግታ በሳራ ጆ ፊት ላይ ታየ።በዛ ቅፅበት የሚመለከታት አንድ ሰው ከሴኮንዶች ቀደም ብሎ ከፍተኛ ንዴት ላይ እንደነበረች በጭራሽ መገመት አይችልም

‹‹… ሰላም ስርጉት።››አለም በሳራ ያልተጠበቀ ትችት የተናደደ ፊቷን ወደኋላ አዞረች። ዳኛው የእሷን እዛ መገኘት እንደትልቅ ጥፋት የቆጠረ እንደሆነ በሚያሳብቅ ስሜት ትኩር ብሎ ያያት ጀመር።

" ክብርት አቃቢት ህግ "

"ጤና ይስጥልኝ ክቡር ዳኛ " ከሳቸው ጎን የቆመችው ሴት አለምን ከሱ ጋር የሚዛመድ ተግሳፅ ተመለከተች ፣ ዳኛው የሴትየዋን ክንድ ነካ አድርገው ወደ ሌላ ጠረጴዛ ሄዱ

"ሚስቱ ናት?" አለም ለሳራ ጥያቄ አቀረበች ፡፡

ሳራ በመደነቅ "በእግዚያብሄር ስም….አረ አይደለችም..የሱ ሴት ልጅ ነች ስርጉት…የመጀመሪያ እና ብቸኛ  ሴት ልጁ ነች፡››

ከላይ የለጠፍነው ከባለፈው ክፍል ተቆርጦ የቀረ ነው።

#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ

///

"ሰሎሜና ስትሞት ደስ ብሎኝ ነበር."

የጥርጣሬ ብልጭታ በአለም አይኖች ውስጥ ዘለለ፣ ‹‹አልዋሽሽም…የሆነ ተራራ ከጭንቅላቴ እንደወረደ እፎይታ ነው የተሰማኝ ››
56👍3👎1