አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
471 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ



ራሄልም እህቷን ይዛ እቤት እንደገባች ጓደኛዋ  ሜሮን ቤት እየጠበቀቻት ነው፡፡መጀመሪያ ቀጠሮውን ለመሰረዝ ፈልጋ ነበር…በኋላ ስታስበው ግን ሴትዬዋ ለስብሰባው ትኩረት እንዳልሰጠች አድርጋ ልትረዳት እንደምትችል ስላሰበች ለመሄድ ወሰነች፡፡ ከሆስፒታል እንደተነሳች ነበር ደውላ ቤት እንድትጠብቃት የጠየቀቻት፡፡፡‹‹ቀጠሮው በጣም ወሳኝ ስለሆነ  ነው ያስቸገርኩሽ፡፡››

‹‹አረ ችግር የለውም..ያንቺ እህት ማለት እኮ የእኔ እህት ነች››አለች ሜሮን፡፡

‹‹እሱስ እውነት ነው››

‹‹አዎ ደግሞም አሪፍ የምስራች አለኝ…››

‹‹እባክሽ ንገሪኝ ቀኑን ሙሉ ስጨናነቅ ነው የዋልኩት…ፈገግ ማለት አምሮኛል››

‹‹አንድ እምቅ ችሎታ ያላት እና በነርሲንግ የሰለጠነች ሞግዚት አግኝቼልሻለው›› አለቻት….ከሁለት ቀን በፊት ለሁሉም ጓደኞቾ  ስለፀጋ ነግራቸው የሰለጠነች ሞግዚት እንዲፈልጉላት አደራ ብላቸው  ነበር፡፡

‹‹አንቺ እኮ ሕይወት አድን ነሽ›› አለችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ጉንጯን ሳመቻት፡፡

ወደቀጠሮ ቦታ ይዛ የምትሄደቸውን ወረቀቶች ወደ ቦርሳዋ አስገባች።

‹‹ሞግዚት ማግኘት ከቻልኩ የፀጋ ዶ/ር የሰጠውን መመሪያ በሙሉ በጥንቃቄ እንዲተገበር ማድረግ እችላለው። ውዴ  ለአሁን ፀጋን ልትጠብቂልኝ ስለወሰንሽ  ደስተኛ ነኝ። ነገሮች ሁሉ ሰላም  እንደሚሆኑ አምናለው?››

‹‹ሄይ. ታውቂያለሽ እኔ  በጣም ጥሩ ጓደኛሽ  ነኝ.››

‹‹ብቃት ያለው ሞግዚት አግኝተሸልኝማ ያንን መካድ አልችልም…  በጣም ጥሩ ጓደኛ መሆን ብቻ ሳይሆን ህይወት አድንም ነሽ።››

‹‹ጥሩ እንደዛ ከሆነ እስኪ በመጠኑ ዘና ለማለት ሞክሪ….››

ራሄል  ከወ.ሮ ላምሮት ጋር ላላት ቀጠሮ የምትጠቀምባቸውን መረጀጃዎች የያዙ ወረቀቶች እየለየች ‹‹ዘና ማለት እንኳን የምችል አይመስለኝም…ደክሞኛል… በአእምሮዬ ውስጥ ብዙ ነገሮች አሉ,››ስትል መለሰችላት፡፡ቀጥላም‹‹‹‹በፋውንዴሽን ውስጥ ነገሮች በጥሩ መንገድ እየሄዱ አይደለም ፡፡ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሁለት ለጋሾችን አጥቻለሁ አሁን የምሄድባትን ሴትዬ ከዋና ለጋሾቻችን የመጀመሪያዋ ነች….እሷን የግድ ማሳመን አለብኝ ››

‹‹ለምን ሎዛ እንድትሰራው  አታደርጊም?››

ራሄል ነገሩን በማሰብ ትንሽ ቆም ብላ ራሷን በአሉታ ነቀነቀች።‹‹ይህን ከባድ ኃላፊነት በእሷ ትከሻ ላይ መጣል አልችልም››

‹‹ስለዚህ በራስሽ ላይ ትጥያለሽ ..እሱ ችግር የለውም ማለት ነው?››

‹‹ትከሻዬ ከሷ የበለጠ ልምድ ያለው ነው›› አለች ፡፡

‹‹ጓደኛዬ ጥቂት ስራዎችን ለሌላ ሰው  ብታስተላልፊ አለም አትገለባበጥም።እና ደግሞ የህይወት ሸክማችንን የሚያቀልልን ክርስቶስ ነው….በእሱ መታመን ችግራቸንን ያቀልልናል፡፡››

‹‹እና ለምን ያቺን አሁን በስቃይ የምታለቅሰውን  ትንሽ ልጅ  እንዲህ አጎጉል አደረጋት? በኢየሱስ አላምንም ብላ ይሆን ?››በራሄል ንግግር ሜሮን  በጣም ደነገጠች፣

‹‹ራሄል .. አንቺ እኮ ከዚህ የበለጠ አስተዋይ ነሽ ››ራሄል እጇን ወደ ላይ ዘረጋች።

‹‹አዝናለሁ ስለ ኃጢአት እና ክፋት ሁሉን ነገር አውቃለሁ እናም እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር በቁጥጥሩ ስር እንደሆነም አምናለው, ስለዚህ ስብከት አንዳትጀምሪኝ››

ሜሮን  የጓደኛዋን ትከሻው በፍቅር እየዳበሰች‹‹ታውቂያለሽ አይደል …?ማመን ስለማትፈልጊ ብቻ ነው. እንዲህ የምትይው…ግን እወቂ አሁንም በኢየሱስ ጥበቃ ውስጥ ነሽ …አዎ፣ በግንኙነቶች ውስጥ ህመም አለ…በሆነ ግንኙነት ተሰብረን ሊሆን ይችላል፣ ቢሆንም  ልባችንን ሁሌ ለፍቅር ክፍት መሆን አለበት ››

‹‹ደህና፣ አሁን ለልብ ጉዳዬች ጊዜ የለኝም።ደግሞ እስከአሁን ለእኔ የሚሆን ሰው አላጋጠመኝም።›› መስታወት አወጣች እና ሜካፕ እና ፀጉሯን በፍጥነት አስተካከለች።

ሜሮን ‹‹ዶ/ሩ በጣም የሚስብ ይመስለኛል››ስትል አዲስ ድንገተኛ ርዕስ ከፈተች፡፡

ራሄል የጓደኛዋን ሹፈት ችላ በማለት ቦርሳዋን አነሳችና ትከሻዋ ላይ አንጠለጠለች ፡፡

‹‹እሱ ማራኪ ነው…እንዳልኩሽ  ግን ለጊዜው ለማንም ጊዜ የለኝም ።››በማለት መለሰችላት፡፡

ራሄል ወደ በሩ ስትሄድ ሜሮን ‹‹መልካም ጊዜ ይሁንልሽ›› ብላ ጮኸች።

////
ራሄል ከሴትዬዋ ጋር እያካሄደች ያለውን ስብሰባ አንድ ሰዓት በላይ ብታሳልፍም..እስከአሁን ሙሉ በሙሉ ልታሳምናት አልቻለችም፡፡

‹‹ባለቤቴ በዚህ ገንዘብ በጣም ነው የሚያምነኝ… እናም ይህን  በትክክለኛው መንገድ ማድረግ  ነው የምፈልገው፡፡››

‹‹ይገባኛል››አለች ራሄል። ነገር ግን የባለቤቷትን  እምነትን ለመጠበቅ ምርጡ መንገድ ገንዘቡን ለትክክለኛው ዓላማ ብቻ ለሚጠቀም በጎ አድራጎት መስጠት ነው።››
ወ.ሮ ላምሮት ፈገግ አለችላት፡፡

ወ.ሮ ላምሮት ራሄልን በትኩረት አየቻትና ‹‹አባትሽን ትመስያለሽ›› አለቻት። ‹‹እሱ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ የሚሰራ የእግዚአብሔር ፍቅር ሁልጊዜ ምሳሌ ነው.››ስትል አከለችበት፡፡

ራሄል መራራ ህመም ተሰማት። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ከአምላክ ጋር ብዙ ጊዜ አላጠፋችም። የወ.ሮዋ  ቃላት አብዝታ ወደ ጸለየችበት፣ መጽሐፍ ቅዱሷን በሰፊው ታንብበት  ወደ ነበረችበት ጊዜ አመጣት። ቤተክርስቲያን እና እምነት የመተንፈስ ያህል የእርሷ አካል ነበር። እምነቷን መልሶ ለማግኘት እና በአምላክ ላይ መታመን ለምን እንደሚያስፈልጓት አሰበች። ››

በወ.ሮ ላምሮት ፈገግ ብላ ሰዓቷን በጥበብ ተመለከተች። ለመውጣት ጊዜው ነበር፡፡

‹‹እኔ እንዳልኩት፣ እባኮት ይህን በትክክለኛው መንገድ  ለማድረግ ትንሽ ጊዜ ስጡኝ..ያንን ብቻ ነው የምጠይቀው››አለች ራሄል፣

ወ.ሮ ላምሮት ከግዙፉ መኖሪያ ቤቷ ስትሸኛት ራሄል የመጨረሻ የማሳመኛ ንግግሯን ተናገረች‹‹እርግጠኛ ነኝ .. ባለቤቷት በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲቸኩሉ አይፈልግም ››

ነገር ግን ከወ.ሮዋ ፊት ምንም ነገር ማንበብ አልቻለችም  ፡፡ሴትዬዋን ለማሳመን የተቻላትን ሁሉ አድርጋለች..ግን ይሳካላት አይሳካላት መገመት ስላልቻለች በጣም ተበሳጨች ፣ መኪናውን አስነሳችና ወደቤቷ ነዳችው…መኪናዋን አቁማ ወደአፓርታማዋ ተጠጋች… የአሳንሰሩን ቁልፍ ተጫነች እና ገባች፤ውስጥ ያልጠበቀችውን ሰው አገኘች፡፡የቆዳ ጃኬት ለብሶ ነበር። የሞተር ሳይክል ሄልሜት በእጁ ይዟል።

‹‹ሰላም. እዚህ ምን እየሰራህ ነው?››ብላ ጠየቀችው፣ እስትንፋሶ ተቆራረጠባት፡፡

‹‹በቃ ጎራ  ብዬ ከፀጋ ጋር እንዴት እየተለማመድሽ እንዳለሽ ለማየት አስቤ ነበር።››

‹‹ጥሩ አደረክ››አለችው

‹‹ወደ ውጭ ወጥተሽ ነበር?››

‹‹አዎ ጠቃሚ ስብሰባ ነበረኝ›

‹‹እንደ ሁሉም ስብሰባዎችሽ››አለ

‹‹አይዞህ አታስብ ጓደኛዬ በጣም ብቃት ያለት ሞግዚት ነች።እርግጠኛ ነኝ እሷ ከእኔ በተሻለ  ከፀጋ ጋር ትግባባለች።››ሊፍት ሲቆም ወደ ኋላ ዞር አለላት።ራሄል ቀድማ ወጣች..ተከተላት፡፡ ኮሪደሩን እንደረገጡ  የሚያለቅስ የህፃን ድምፅ በሁለቱም ጆሮ ገባ። የመጣው ከራሷ ቤት  ነው።ሁለቱም ርምጃቸውን አፈጠኑና ተከታትለው ወደቤት ገቡ ፡፡ሜሮን የምትጮኸውን ፀጋን  ተሸክማ እቤት ውስጥ ከወዲህ ወዲያ ትሽከረከራለች፣ የልጁቷ ክንዶች በሜሮን  ጀርባ ላይ ተዝለፍልፋው ይታያሉ፡፡

ራሄል ቦርሳዋን ጥላ ወደ ጓደኛዋ ሮጣ ሄደች። ጸጋ ራሄልን እንዳየች ከሜሮን እቅፍ ውስጥ ተስፈንጥራ  እጇን ዘረጋች። እንባዋ በጉንጮቾ እየተንከባለሉ በመርገፍ ላይ ናቸው፡፡
49👍3🥰1😢1