አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
====================
ከአንድ አመት በኃላ በትዳር ውስጥ ወሲብ ብቸኛው አስፈላጊ ነገር አይደለም፡፡ግን ደግሞ ሊቀር የማይችል ከዋነኞቹ አስፈላጊ ነገሮች መካከል አንዱ ነው፡፡በተጣማሪዎች መካከል የሚከሰትን ማንኛውንም የከረረ ነገር የሚያለዝበው፤ የተጣመመ ስሜታቸውን የሚያቃናው፤የጎበጠ ግንኙነታቸውን የሚያቃናው ወሲብ ነው፡፡
የኑሮ ችግር ቢኖር መፅናኛ..አለመመቸት ቢኖር ማስረሻ ነው..ወሲብ፡፡እናም ባለትዳሮች የኑሮቸውን ኢኮኖሚያው ቀዳዳ ለመድፋት በስራ ደፋ ቀና እንደሚሉት ሁሉ የስሜታቸውን ክፍተት ለመድፈን ስለወሲብ ብቃታቸውና ችሎታቸው እኩል ትኩረት መስጠት አለባቸው፡፡ለዛውም ያልተቆራረጠ ቀጣይነት ያለው ትኩረት ፡፡ምክንያቱም ወሲብ ለፍቅር ተጣማሪዎች ልክ እንደምግብ ነው፡፡ምግቡ ቁርስ ላይ  ያበሉት  ሆድ ምሳ ላይ አምጡ ብሎ እንደሚጠይቀው ሁሉ ወሲብም ሰኞ እስኪዝለፈለፉ አድርገው እሮብ ላይ ጭንቅላቶትን እስኪያዞሮት ሊያምሮት ይችላል፡፡ይሄ ለምን ሆነ ተብሎ መጠየቅ የለበትም..፡፡እንደውም የሰውነቶትንም ሆነ የአእምሮትን ሙሉ ጤናማነት የሚያሳይ አንድ ምልክት ተደርጎ መወሰድ ነው ያለበት፡፡
በአላዛርና በሰሎሜ ትዳር ውስጥ ዋነኛውና ብቸኛው ስብራት ይህ ነው፡፡ወሲብ፡፡ታዲያ ወሲብ ብቸኛው ችግራቸው ከሆነ እንዴት በመሀከላቸው ያለን አንድ ችግር መፍታት ያቅታቸዋል? በሌሎች ትዳሮች እኮ ከደርዘን በላይ የታጭቁ ችግሮች እያሉ እንኳን ትዳሩን በፀና መሰረት ላይ ማስኬድ ይቻላል፤ታዲያ የእነሱ እንዴት ? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ግን ነገሩ ከላይ እንደሚታየው ቀላል አይደለም፡፡ወሲብ ማለት የፍቅር መግለጫ ማህተም ነው….ወሲብ ማለት የአብራክ ክፍይን መተኪያ ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ልጆች ደግሞ ለአንድ ትዳር የተለየ ትርጉም የሚሰጡ ፍፅማዊ በረከቶች ናቸው፡፡
ሰሎሜና አላዛር እናትዬውን ለመጠየቅ ኮዬ ፈጬ ከንደሚኒዬም ይገኛሉ፡፡የተለየ ጉዳይ ካልተፈጠረ በስተቀር በ15 ቀን አንዴ እንዲህ እየመጡ እናትዬውን ይጎበኛሉ፡፡ይሄንን በየ15 ቀን የሚደረጉትን ጉብኝት ከእነሱ በላይ እናትዬው ነች የምትናፍቀው፡፡ምክንያቱም እነሱ እንድታገለግላት ከቀጠሩላት አጋዥ ልጅ እግር ሴት  በስተቀር ለብቻዋ ነው የምትኖረው፡፡አላዛርም ሆነ ሰሎሜ አብራቸው እንድትኖር ደጋግመው ለምነዋት ነበር፡፡እሷ ግን ፍቃደኛ አልሆነችም፡፡
አላዛርን ሳሎን እንደተቀመጠ ከጎኑ የተቀመጠችው ሰሎሜ  ከተቀመጠችበት ተነሳችና .‹‹ማሬ እስኪ እማዬን ኪችን ሄጄ ላግዛት፡፡››አለችው፡፡
‹‹ምነው ልጅቷ የለችም እንዴ?››
‹‹ዛሬ  ቤተሰቦቼን ልጠይቅ ብላ ፍቃድ ተሰጥቶት ሄዳለች.. ››አለችው፡፡
‹‹ታዲያ እኮ እቴቴን ይዘናት ወጣ ብለን ውጭ መዝናናት እንችላለን..ኪችን ገብታ ለእኛ ምግብ ማዘጋጀት የለባትም ፡፡››
‹‹አንተ ደግሞ እቴቴን የማታውቃት ይመስላል…ለማንኛውም መጣሁ…እንዳይደብርህ ሪሞቱ ያውልህ ቲቪውን ክፈተው፡፡››ብላው ወደኪችን ገባች፡፡እናትዬው በእስቶቭ ላይ ጎን ለጎን ሁለት ድስት ጥዳ አንዱን ስታማስል ነበር የደረሰችው፡፡
‹‹መጣሽ ልጄ?››
‹‹አዎ አማዬ…ምን ላግዝሽ?››
‹‹ምንም …በቃ እየበሰለ ነው፤ራባችሁ እንዴ?››
‹‹አረ በፍፅም ..አርፍደን ከእንቅልፋችን ስለተነሳን  ቁርስ በቅርብ ነው የበላነው፡፡››
በሰጠቻቸው መልስ ባለመደሰት አፋቸውን ወደጎን በማሽሟጠጥ አጣመው‹‹ጥሩ ነው.. እስከአራት አምስት ሰዓት መተኛቱ ጥሩ ነው..ግን ዝም ብሎ መተኛት ምን ረብ አለው?››ሲሉ መለሱላት፡፡
የንግግራቸውን አቅጣጫ እያወቀች ‹‹እሱ ደግሞ ምን ማለት ነው?..››ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
‹‹ካንቺ በኃላ ያገቡ ጓደኞችሽ ሁሉ እኮ  ወለዱ..ሌላው ይቅር ከአምስት ወር በፊት ያገበችው ቤተልሄም የዛሬ ሳምንት ወልደ ሄጄ ጠየቅኳት፡፡››
‹‹እንዴ እማ …ልጅ በዘጠኝ ወር አይደል እንዴ የሚወለደው?በአምስት ወር እንዴት ማድረስ ቻለች?››
‹‹ቀልጂብኝ…ደግሞ እኮ ስላረገዘች ነው ተካልባ ያገባችወ እያሉ ሲያሟት እኔም አብሬ ማማቴ..ምነው አንቺም ከማግባትሽ በፊት አርግዘሽ ቢሆን ኖሮ…፡፡››
‹‹እቴቴ…. እንተዋወቃለን እኮ..አሁን እደዛ አድርጌ ቢሆን አታዝኚብኝም ነበር..?››
‹‹ልዘና ..የተወሰነ ጊዜ ተነጫንጬ ተወዋለው…ምንም ባዝን አሁን እያዘንኩ እንዳለሁት አላዝንም…ደግሞም  እስካሁን በእግሩ ለመሄድ የሚታገል ወፌ ቆመች ወፌ ቆመች የምለው የልጅ ልጅ ይኖረኝ ነበር፡፡››
‹‹አይዞሽ እማዬ… በተከታይ ሶስት አራቱን አንጠባጥብልሻለሁ፡፡››
‹‹ልጄ እናት መሆን እንዲሁ ተራ ነገር አይምሰለሽ..ለህይወትሽ ጥልቅ ትርጉም የሚሰጥሽ እናትነት ነው፡፡እናት መሆን ማለት በህይወት ውስጥ ስርሽን የህይወት እንብርት ድረስ ዘረጋሽ ማለት ነው፡፡እናት ስትሆኚ ለህመም በቀላሉ እጅ አትሰጪም፤እናት ስትሆኚ ብትቸገሪ እራሱ በቀላሉ ተስፋ አትቆርጪም፤እናት ስትሆኚ ለቀናት እህል ባትቀምሺ ራሱ ተዝለፍልፈሽ ለመውደቅ  አትሞክሪም፤እናት ስትሆኚ  መሞት ብትፈልጊ እንኳን ለመሞት መብት የለሽም፤እኔ አንቺን አጎጉል በሆነ ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ነው የወለድኩሽ..እንደእንቺ በወግ በማአረግ አግብቼ መሰረቱ የፀና ትዳር መመስረት አልቻልኩም፡፡እና ደግሞ አንቺን ስወልድ በደረሰብኝ የማህፀን ጉዳት ሌላ ልጅ ወልጄ ወንድም ወይም እህት እንዲኖርሽ ማድረግ አልቻልኩም…አሁን የምትወልጂያቸው ልጆች ልጆችሽ ብቻ አይደለም የሚሆኑት ወንድምና እህቶችሽም ጭምር ነው የምትወልጂው..ለዛ ነው ቀንና ሌት የምጨቀጭቅሽ፡፡››
‹‹ይገባኛል እቴቴ…አይዞሽ!! ››
ሁል ጊዜ ይሄንን ጥያቄ እናትዬው ባነሳችላት ቁጥር ‹‹አይዞሽ››ከማለት ውጭ ሌላ የምትመልስላት መልስ ኖሯት አያውቅም፡፡አሁን አሁን ግን መልሷ በጣም ከመደጋገሙ የተነሳ ለእናቷ ብቻ ሳይሆን ለእሷም በጣም እጅ እጁ እያላት ነው፡፡ግን ለጊዜው ሌላ ምርጫ የላትም፡፡
እናትዬው‹‹አይዞሽ ብቻ ምንም አይረባኝም…የምትጠቀሚውን መከላካያ መድሀኒት ዛሬውን አውጥተሸ  ሽንት ቤት እንድትጥይው ፈልጋለሁ፡፡፡››አሏት፡፡
‹‹እሺ እኮ አልኩሽ እማዬ..እሺ››
‹‹በይ ወጡ ደርሶል…ታጠቡና ተዘጋጁ፡፡ ››
‹‹እሺ›› ብላ በደፈረሰ ስሜትና በተከፋ ፊት ወደ ባሏ ተመለሰች፡፡ይሄ ጭቅጭቅ ምርር እያደረጋት ነው፡፡ደግሞ የእናቷ ብቻ ቢሆን ምን አለበት..ጠቅላላ የሚያውቋት ሰዎች በተለይ ትንሽ ጠና ያሉ ሴቶች በሙሉ በሆነ አጋጣሚ ፊት ለፊት ሲያገኞት‹‹..እሺ መቼ ነው ገንፎ የምንበላው…?ምነው ሰውነትሽ ጨመረ..?አረገዝሽ አይደል?››በቃ ቋቅ እስኪላት ድረስ ምርር ያደረጎት ጉዳዬች ናቸው፡፡
እናቷ ደጋግማ ስትጠይቃት…‹‹ትንሽ ልቆይ ብዬ ነው..መድሀኒት ስለምጠቀም እንጂ እስከአሁን አረግዝ ነበር ፡፡››የሚሉ መልሶችን ደጋግማ መልሳላቸዋለች፡፡ታዲያ ‹‹አይ እናቴ እስከአሁን ያላረገዝኩት ያገባሁት ባሌ ከእኔ ጋር ወሲብ መፈፀም እምቢ ስላለ ነው፡፡እስከአሁን ድንግል ስለሆንኩ ነው ፡፡››ትበላቸው እንዴት ? የዚህ ነገር መቋጫው የት እንደሆነ መገመት እራሱ እየከበዳት ነው፡፡
ምሳ ቀርቦ በልተው ካገባደዱ በኃላ ይዘው የመጡትን ወይን ለሶስቱም ተቀድቶ እሱን እየተጎነጩ በግማሽ ልብ የተከፈተውን ቴሌቭዥን እያዩ በግማሽ ልብ የባጥ የቆጡን ርእስ እያነሱ ሲጫወቱ ቆዩ ፡፡በድንገት ግን ቀልብ የሚስብ ፕሮግራም ወሬያቸውን እንዲያቆሙና ሙሉ በሙሉ ፀጥ ብለው እንዲያዳምጡ አስገደዳቸው፡፡ጣቢያው ኢቢኤስ ነበር፡፡
👍648😢2👏1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///
ቢንያም እና ዔሊያስ አዲሱ ቤት ውስጥ ሆነው አንዳንድ ነገሮችን እያስተካከሉ ነው፡፡

‹‹እነዚህ ክፍሎች ከተጠናቀቁ በኋላ የሚቀጥለው ፕሮጀክት የሳሎኑን ሴራሚክ ማሰራት ነው›› አለ ዔሊ፡፡

ቢኒያምም ‹‹አዎ..እኔም እንደዛ ነው ያሰብኩት ››ሲል ለሀሳቡ ድጋፍ ሰጠው፡፡
‹‹ሰሞኑን በቤቱ የፊኒሽንግ ስራ ላይ ያለህ ትኩረትና ጉጉት ጨምሮብኛል ..ምነው ?ጉዳዩ ከራሄል  ጋር የሚያገናኘው ነገር አለው እንዴ?››ሲል ጠየቀው፡፡
ዔሊያስ የሚናገረው ማንኛውም ነገር በወንድሙ በተሳሳተ መንገድ እንደሚተረጎምበት ስለሚያውቅ  ዝም ለማለት ወሰነ ። የቀረውን የእንጨት ፍቅፋቂ ጠራርጎ ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ጣላው፡፡

ቢኒያም ወደሌላ ተያያዥ ጥያቄ ተሸጋገረ‹‹በቤተሰቧቾ ግቢ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢ አመታዊ ዝግጅት ላይ  ቆንጆዎቹ ጥንዶች እናንተ እንደነበራችሁ  ሰምቻለሁ።››

‹‹ስለ ቆንጆው ክፍል አላውቅም, ግን አዎ  አብረን ጠቃሚ የሚባል ጊዜ አሳልፈናል.››ሲል መለሰለት፡፡
ቢኒያም መሳሪያዎቹን እየሰበሰበ ‹‹እሷ በጣም የምትስብ ሴት ነች፣ አይመስልህም?›› ሲል አከለበት።
ዔሊያስ ሳጥኑን አነሳና‹‹በአሁኑ ጊዜ ስለእሷ ምንም  ላለማሰብ እሞክራለሁ…ካለበለዚያ ችግር ውስጥ ያስገባኛል.››ሲል መለሰለት ።

የሚናገረው ነገር ሙሉ በሙሉ እውነት አልነበረም። ከዝግጅቱ ቀን  ጀምሮ፣ ብዙ ነገሮችን ከአእምሮው ማውጣት አልቻለም። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እዛው በራሄል ቢሮ ውስጥ፣ ወደ ኋላ የተገፋ.. የተተወ ያህል ተሰምቶታል። በቀጣዮቹ ቀናት ብዙ ጊዜ፣ ወደቤቷ ተንደርድሮ ለመሄድ ስሜቱ ተፈትኗት ነበር።እሱ ግን እንደምንም ተቋቁሞት እራሱን አቅቧል። ለራሄል ልቡን ከፍቶ ነበር፣ እሷም እንዲሁ ያደረገች መስሎት ነበር። ከዚያ በኋላ ግን ስለእሷ ያለውን ስሜት በትክክል ሲነግራት.. ቀዝቀዝ አድርጋዋለች።‹‹እንደዛ ማድረግ  ያለብን አይመስለኝም።›› ነበር ያለችው….ታዲያ ለምን እንዲስማት ፈቀደችለት?እና ለምን አሁንም ስለ እሷ ያስባል? እሷን ከአእምሮው ለማስወጣት ወስኗል። እሱ ትኩረቱን የሚያሳርፍበት የሚሠራው ቤት ስላለው አመሰገነ። እንደ ሞኝ እሷ በቀደደችለት ቦይ  ፈቃደኛ ሆኖ እንዲፈስ  አድርጋዋለች።

‹‹እሷን እንደ ፍቅር ጓደኛ አድርጎ ማሰብ ከመጠን ያለፈ ነው›› አለ ፡፡
ቢንያም ‹‹ከየትኛውም ሴት ጋር ለተወሰነ ጊዜ አላሳለፍክም። ይህችኛዋ የተለየ ምን አላት?››
ዔሊያስ ሱሪው ላይ ያለውን አቧራ ጠርጎ አራገፈው። ‹‹ እርግጠኛ አይደለሁም።››ሲል መለሰላት፡፡

‹‹ወደሀታል?››

ኤሊያስ ቅንነት በጎደለው እንቅስቃሴ እጁን አወዛወዘ። እሱ ካልወደዳት ለምን አብዝቶ ስለእሷ ያስባል ?‹‹የሆነ ሆኖ ..ለጊዜያዊ  ስሜት እንዳልፈለኳት  አውቃለሁ››
ቢንያም ቀጠለ‹‹ስለዚህ ጉዳይ ማውራት ትፈልጋለህ?››

‹‹አይ ..ርዕስ ብንቀይር ደስ ይለኛል››አለው፡፡

ቢንያምን ወንድሙ ስሜት ተረዳና ርእሱን ቀየረ ‹‹በቀደም ለሆነ የስራ ጉዳይ…እኛ የነበርንበት የህፃናት የማደጎ ድርጅት ሄጄ ነበር ..አስተዳዳሪዋ ወይዘሪት ሜላት ስለአንተ ስትጠይቀኝ ነበር፡፡ሰሞኑን ፋይል ሲያደራጁ በአንተ ፋይል ላይ በፊት ካሳየችህ  የተለየ ነገር እንዳገኘች ነገረችኝ፡፡››

ኤልያስ  በሰማው ነገር ደነገጠ ‹‹ታዲያ ለምን  አልነገርከኝም? ስለ ወላጆቼ የበለጠ ለማወቅ እንደምፈልግ ታውቃለህ።››
ቢንያም ‹‹ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደተሰማኝ ታውቃለህ.? አሳዳጊ ወላጇቼ የሚያስፈልገኝን   ሁሉንም ነገር ነው የሰጡኝ … ስለ ወለደችኝ  እናቴ ምንም ግድ የለኝም. አንተም ተመሳሳይ ነገር እንድታደርግ እመኛለሁ  ምክንያቱም ወላጆችህ ሞተዋል..ተመልሰው አይመጡም ..በዚህ ጉዳይ ላይ አእምሮህን እንድትበጠብጥ አልፈልግም..ለዛነው ችላ ያልኩት››

ዔሊያስ በማደጎ ወንድሙ ላይ ያለው ብስጭት አደገ ‹‹የአንተ እናት ‹መቼም ቢሆን ከልጄ ጋር ምንም አይነት  ግንኙነት ለማድረግ አልሞክርም› የሚል ስምምነት ፈርመዋል።የገዛ የስጋ እናትህ መቼም ቢሆን ከአንተ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዲኖራት አልፈለገችም…. የእኔ ግን የተለየ ነው … የወላጆቼ  ትዝታዎች  በልቤ ውስጥ ናቸው… ምንም እንኳን  አንተም ሆንክ አሳዳጊ ወላጆቻቼ  ስለ ወላጆቼ በጭራሽ እንዳውቅ ባትፈቅዱልኝም…..እኔ ግን ፍለጋዬን አላቆምም.››ሲል በቁጣ ተንዘረዘረበት፡፡

ቢኒያም በስክነት ‹‹ ብቻ እንደወንድምነቴ የተሰማኝን ነገሬሀለው….››አለው፡፡
ኤሊያስ  ምንም መልስ አልሰጠውም ። እሱ እና ቢንያምን ከዚህ በፊት  በዚህ ጉዳይ ላይ በተደጋጋሚ ተወያይተው ነበር ግን አንድም ቀን አንድ አይነት አቋም አራምደው አያውቁም። እሱ አሳዳጊዎቹ ከማደጎ ቤት ከተቀበሉት በኋላ በእውነት የቤተሰቡ አካል እንደሆነ ለማመን ብዙ አመታት ፈጅቶበት ነበር፣ እና ከዛም የገዛ ወላጆቹ እና የእነሱ አሳዛኝ ሞት ትዝታዎች ብዙውን ጊዜ ጣልቃ በመግባት በእሱና በአሳዳጊ ወላጆቹ መካከል ክፍተት እንደፈጠረ ነበር፡፡

‹‹ስለ መዛግብት ስላልነገርኩህ ይቅርታ… አስፈላጊ ነው ብዬ አላሰብኩም ነበር. ከዚህ ሁሉ በላይ የሆንክ መስሎኝ ነበር.››
ኤልያስ በሀሳብ ነሆለለ።የሚወዳት ልጅ  ራሔል ትዝ አለችው፡፡እሷ  በሁለቱም በኩል  ወደ ኋላ ዞራ የትውልድ ሀረጓን በኩራት መዘርዘር ትችላለች…ከዛም አልፎ በእናቷ የዘር ግንድ ሔዶ ሄዶ ከሰለሞን ዘር ይመዘዛል ብለው እናቷ  ነገረውታል…. በዚህም ምክንያት እሷ በተጠየቀች ቁጥር ከየት እንደመጣች ለሰዎች በኩራት መንገር ትችላለች። እሱ ግን የዘር ግንዱ በአጭሩ ብጥስ ብሎ መጥፋቱ ከሌሎች ሰዎች ያነሰ እንደሆነ እንዲሰማው አድርጎታል።አሳዳጊ ወላጆቹን  ይወዳቸዋል ። በወጣትነት ዘመናቸው ወደቤታቸው ወስደው… አመፁን እና አስቸጋሪ ፀባዩን ተቋቁመው በፍቅር አሳድገውታል..አሁንም ድረስ ስለእሱ ማሰብና እሱን ከመንከባከብ ሲደክማቸው አይቶ አያውቅም።ልክ እንደእነሱ አማኝ ሆኖ ወደ ቤተ ክርስቲያን መመላለስ አለመቻሉ እንዴት እንዳሰቃያቸው ያውቃል።ግን በተመሳሳይ ስለስጋ ወላጆቹ ያለውን ቁርጥራጭ ትውስታዎቹን ማጥፋት አልቻለም. ….አልፈለገምም ነበር።

ከረጅም ዝምታ በኋላ ቢኒያም ‹‹ኤሊያስ ልነግርህ የምችለው ነገር የበለጠ ማወቅ ከፈለግክ ከወይዘሪት ሜላት ጋር  ሄደህ ራስህ  ብትነጋገር ጥሩ ይመስለኛል››የሚል ሀሳብ አቀረበለት፡፡
ዠቨ
‹‹እንደዚያ የማደርግ ይመስለኛል›› አለ.

ዶ/ር ኤልያስ በማግስቱ አስረአንድ ሰዓት ላይ በህፃናት ማሳደጊያ በጎ አድርጎት ድርጅት ቢሮ ውስጥ ከመዘጋቱ በፊት ተገኘው። ምሳ ሰዓት ላይ ስልክ ደውሎ  ቀጠሮ ይዞ ነበር ። ወ.ሪት ሜሮን ተከትሎ ወደ ቢሮዋ ሲገባ ልቡ ከተገቢው በላይ እየመታ ነበር።

የራሄል ምስል በአእምሮው ውስጥ ድቅን አለና  ለስለስ ያለ ህመም ተሰማው። ‹‹  ዶ/ር ኤልያስ…እንኳን በሰላም መጣህ…ምን እንድረዳህ ትፈልጋለህ?›› ስትል ጠየቀችው ፡፡

‹‹ስለ ስጋ  ወላጆቼ አንዳንድ ነገሮች ሚያስረዳ ፋይል እንዳለሽ ተረድቻለሁ›› አለ ።ወ.ሪት ሜላት ጭንቅላቷን  በአውንታ ነቀነቀች። ‹‹ብዙ መረጃ አልያዘም ነገር ግን ጥቂትም ቢሆን ምን አልባት የምትፈልገውን ነገር ልታገኝበት ትችል ይሆናል::››

‹‹እና አሁን ማየት ብችል ደስ ይለኛል?››

‹‹እላይ ፎቅ ላይ በሚገኝ መዝገብ ቤት ውስጥ ነው ያለው…ትንሽ ታገሰኝ ይዤ ልምጣ  ›› ብላ እዛው የተቀመጠበት ትታው ወጥታ ሄደች፡፡
73👍7
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_አስራ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


///
አለም ወደ አፓርታማዋ  እደገባች የእጅ ቦርሳዋን እና ካፖርትዋን ወንበር ላይ አስቀመጠች
ዛሬ ከሰአት በኋላ ለዋናው አቃቢ ህጉ ደውላለት ነበር። እስካሁን እጇ ላይ ባስገባችው ግኝት ደስተኛ ሆኖ አላገኘችውም፡፡ ስራውና እርግፍ አድርጋ ወደ አዲስ አበባዋ እንድትመለስ ወይም እራሷን ካለፈው ታሪኳ ጋር እንድታስታርቅ ምርጫ አቀረበላት።እስከአሁን በሚጠበቀው ልክ ተጨባጭ ውጤት ማግኘት ያለመቻሏ የሱ ቅሬታ አንዱ ምክንያት ነበር። ዛሬ ማታ ባላት ቀጠሮ መሰረት ለዋናው አቃቢ ህግጉ የአይን እማኙን አግኝታ ያገኘችውን መረጃ ስታቀርብለት ስሜቱ ሙሉ በሙሉ እንደሚቀየር እርግጠኛ ነች።
ወደ መጠጥ ቤቱ የመኪና ማቆሚያ ቦታ በገባችበትን ቅጽበት ብዙም ተስፋ እንደማይሰጥ ማወቅ ነበረባት። አምፖሎቹ ቦግ ብልጭ ድርግም ከሚለው የሸዋ በር መጠጥ ቤቶች መካከል በአንዱ ነው የቀጠራት ። ከደረሰች በላ ወደ ውስጥ አልፋ ለመግባት በጣም አመንትታ ነበር።ግን ይሄ የያዘችውን ምርመራ ከስኬት ለማድረስ መክፈል ከሚገባት መስዋዕትነት መካከል አንዱ እንደሆነ ራሷን በራሷ አሳመነችና እግሮቾን እየጎተተች ወደውስጥ ገባች፡፡በክፍሉ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ሰው ትኩስ ስጋ እንዳየ ጥንብ አንሳ ወደ እሷ ተመለከቷት፡። የተወሰኑ ሴቶች ቢኖርም የእነሱ እይታ እንደውም ከወንዶቹ በተቃራኒ ሻካራ መስሎ ነው የተሰማት ፡፡ወደኋላ ዞራ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጋ ትታ መሮጥ ፈለገች ..ግን ያደረገችው ወደግራዋ ታጥፋ ኮርነር አካባቢ ወንበር ስባ መቀመጥ ነበር፡፡

አስተናጋጆ መጥታ

‹‹ ምን ልታዘዝ ስትላት"

‹‹እባክሽ ነጭ ወይን "ስትል አዘዘች፡፡
በስልክ ያናገራት እና ድምፁን ብቻ የሰማችው ሰው የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ዓይኗን ከአንዱ አቅጣጫ ወደሌላው በማወናጨፍ ለመገመት ሞከረች ።ግን ….አይኗ ሲንከራተት እየተካታተሉ የነበሩ አንዳንድ ወንዶች ሁኔታዋን በተለየ መንገድ ትርጉም ሰጥተውት አስፀያፊ ምልክት ሲሰጦት ነው ያወቀችው። ከዛ በኋላ አይኖቾን አደብ አስገዛችና መጠጧን እየተጎነጨች አቀርቅራ ማሰላሰሏን ቀጠለች፡፡ የምትፈልገው ሰው እዛ ሆቴል ውስጥ ካሉት ሰዎች መካከል አንዱ ከሆነ የምትወደው አይነት ሰው ሊሆን እንደማይችል አሰበችና ተረበሸች፡፡

እያጨሰች ባትሆንም በዙሪያዋ ብዙ ሰዎች የተለያየ አይነት ሲጋር እያጬሱ ስለሆነ በጭስ ደመና ታፍናለች። እና አሁንም ብቻዋን እንደተቀመጠች ነው።በመጨረሻ፣ እሷ ስትመጣ ባለጌ ወንበር ላይ ተቀምጦ የነበረ የተጎሳቆለ አይነት ሰው ከመቀመጫው ተነሳና ወደ እሷ አቅጣጫ መጣ። ከእሷ ጠረጴዛ ጋር ከመድረሱ በፊት ካለው ሌለኛው ጠረጴዛ ላይ ወንበር ስቦ ተቀመጠና ይዞ የመጣውን ቢራ ከፊት ለፊቱ አስቀመጠ…የሁለቱ ወንበር መደገፊያ የተደጋገፈ ስለሆነ ጅርባቸው ተጋጥሟል ማለት ይቻላል..በዛ ላይ ሰውዬው ጥቁር ኮፍያ አድርጎ ፊቱን በከፍል ስለሸፈነ ምን እንደሚመስል በትክክል ልትለየው አልቻለችም፡፡፡

አንገቱን ወደኋላ ለጥጦ"ሰው እየጠበቅሽ ነው?"ሲል ተናገረ…ድምፁ የተለየ ይመስላል፣
"እኔ መሆኔን በምን አወቅክ ?ደግሞስ ይህን ያህል ጊዜ የፈጀብህ ለምንድን ነው?"ብላ በቀዝቃዛ ድምጽ መለሰችለት።

"ድፍረቴን እያሰባሰብኩ ነበር" አለ ከቢራው እየተጎነጨለት።

‹‹ጥሩ….ከእኔ ጋር አንድ ጠረጴዛ ለመጋራት ይሄን ያህል ትፈራለህ እንዴ?››

‹‹ህይወት እኮ ነው የያዝኩት… ለምን አልፈራም?››

"ይሁን እሺ…የምትነግረኝ ነገር እንዳለህ ገምታለው…ምንድነው ?።"

"የምትፈልጊውን ሁሉ ማውራት እንችላለን " የቢራ ጠርሙስ ጠረጴዛው ላይ አስቀምጦ ከኪሱ ብር አወጣና አስቀምጦ ‹‹..ግን መጀመሪያ ከዚህ መውጣት አለብን›› አላት፡፡

‹‹ ጥሩ የእኔ መኪና ውጭ ነው …ነጭ ቪታራ ነች"
‹‹አውቃታለው››

‹‹ሂሳብ ከፍዬ መጣሁ.. እዛ ጠብቀኝ››
ቀድሞ መራመድ ጀመረ፡፡ሹክክ ብሎ ሆቴሉን ለቆ ተሰወረ….እሷም አስተናጋጁን ጠርታ ሂሳብን ዘጋችና ግማሽ የቀረውን የወይን ጠርሙስ ባለበት ጥላ ቦርሳዋን ይዛ ወደውጭ ወጣች ..ወደ መኪናዋ ቀረበች ….ምንም ሰው በአካባቢው አይታያትም…..ወደመኪናዋ ውስጥ ገባችና ..የውስጥ መብረቱን አብርታ መጠበቅ ጀመረች…….ምንም ብቅ የሚል ሰው አልነበረም፡፡ ግራ ተጋባች…ተበሳጨች…ሰሞኑን ይደውልላት በነበረው ስልክ ደወለችለት…እንደተለመደው ይጠራል አይነሳም፡፡ማልቀስ ሁሉ አማራት..እዛው መኪናዋ ውስጥ ኩርምት እንዳለች ከአንድ ሰዓት በላይ አሳለፈች..በመጨረሻ ተስፋ ቆረጠችና አዲስ ወደ ተከራየችው አፓርታማ ነዳችው፡፡ከሀሳቧ ያባነናት የስልክ ጥሪ ድምፅ ነው… ከብስጭቷ ሳትወጣ ከአልጋዋ ተፈናጥራ ተነሳችና አነሳችው።

"ሀሎ።"

"እብድ ነው እንዴ ብለሽ አስበሻል አይደል ?"
የምታውቀውና የምትጠብቀው ድምፅ ነው።

"አንተ የት ነበርክ? ከእኔ ጋር ምን አይነት ጫወታ ነው አየተጫወትክ ያለኸው?መኪናዬ ውስጥ ተጎልቼ አንድ ሰዓት ያህል ስጠብቅህ ነበር.."

"ካንቺ ጋር ድብብቆሽ መጫወት ብፈልግ ኖሮ መልኬን እንድታይው አልፈቅድልሽም ነበር….ኩማንደሩ እዛው ነበር?"

"ምንድን ነው የምታወራው? ገማዶ እዚያ አልነበረም"

"የእኔ እመቤት ነበረ፣ በትክክል ነው ያየሁት። በቀጠሯችን መሰረት በቦታው ተገኝቻለሁ ግን ኩማንደር ገመዶ ከጀርባሽ በቅርብ ርቀት ተቀምጦ እያየሁት በአካባቢው መቆየት እና ከአንቺ ጋር ማውራቱን መቀጠል አልችልም… ፡፡››

‹‹ኩማንደሩ እየተከተለህ ነበር እንዴ?"

"እንዴት እንደዛ ያደርጋል….እኔ ምንም አይነት ህግ እልጣስኩም,…በተለይም ከፍሰሀ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች አንገቴ ስር ሲተነፍሱ. ደስ አይለኝም…ኩማንደሩ ደግሞ ከልጅነቱ ጀምሮ ከፍሰሀ ጋር ያበረ ወፍራም ሌባ ነው. የእሱ ዋነኛ ቀኝ እጁ ነው..ለማንኛውም አንቺን ተከትሎ የመጣ ይመስለኛል!!››

"ኩማንደሩ በአካባቢዬ እንዳለ አላውቅም ነበር. ሌላ ቦታ እንገናኛለን. በሚቀጥለው ጊዜ እሱ እንዳልተከተለኝ እርግጠኛ እሆናለሁ."ስትል ቃል ገባችለት፡፡

" እስቲ እናያለን።"

‹‹እናያለን ማለት ምንድነው…?ነው ወይስ የምትነግረኝ ነገር ያን ያህል አስፈላጊ አይደለም፡፡.››

"ወንጀሉን ማን እንደፈፀመው አይቻለሁ እመቤት"

ተፈላጊነቱን ስታሳንስበት ተበሳጨ፡፡

"ታዲያ የት ነው የምንገናኘው?

እና መቼ?"

‹‹አሁን ህዝብ የተሰበሰበበት ቦታ አይደለም መገናኘት ያለብን ….ከቶታል ማደያ በቀኝ በኩል በምታስገባው መንገድ አንድ ሰማያዊ ቀለም የተቀባ ህንጻ አለ…. ከእሱ ፊት ለፊት
አንድ አሮጌ ሰማያዊ ባጃጅ ውስጥ ቁጭ ብዬ እጠብቅሻለው። እኔ ከኃላ ውስጥ አለሁ..ዝም ብለሽ ትገቢያለሽ።"

‹‹ባጃጁ ያንተ ነው ማለት ነው››

‹‹ከየት አባቴ አምጥቼ…የጓደኛዬ ነው..ሰሞኑን ስለታመመ እኔ ደግሞ ስራ ፈት ስለሆንኩ እየሰራሁለት ነው፡፡››

"በቃ በሰዓቱ እገኛለሁ- ግን እስከዛው ቢያንስ ስምህን ልትነግረኝ አትችልም?"

"አይ አልችልም" ስልኩን ዘጋው። አለም ተሳደበች። ከአልጋው ወርዳ ወደ መስኮቱ ሄደች ፣ መጋረጃዎችን ገለጠችና ወደውጭ ተመለከተች…የጠቆረው እና ኮከቦች የተበተሉበት ሰማይን በትኩረት አየች፡፡መጋረጃዎቹን ዘጋች፣ ወደ ስልኩ ተመለሰች፣ እና በቁጣ ውስጥ እንዳለች ሌላ ቁጥር ላይ ደወለች። የዓይን እማኝን በማስፈራራቱ በኩማንደሩ ላይ በጣም ተናደደች፣ እየተንቀጠቀጠች ነበር።ቀጥታ እሱ ላይ ነበር መደወል የፈለገችው…ግን ደግሞ ቁጥሩን አታውቅም…..የሰዓቱ መምሸት ግድ አልሰጣትም ፡፡ስልኩ ተነሳ፡፡
49👍2🥰2