#የጣት_ቁስል
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ
የተዳፈነ እሳት
ከሁለት አጉል ሆነች፡፡ እንደ ባህር ላይ ኩበት ተንሳፈፈች፡፡ ከባለቤቷ ወይም ከቤተሰቦቿ ሳትሆን ቀረች፡፡ ባለቤቷ ለገበያ እንደሄደ ወደ ውትድርና መግባቱን ሰማች፡፡ የመኖር ተስፋዋ እንደ ተዳፈነ እሳት ውስጧ ተንቦገቦገ፡፡ የጨለማ ተከናነበ፡፡ ከባለቤቷ ጋር ሰርታ የመለወጥ ተሰፋዋ ከማህል ተቀጨ፡፡ የኑሮዋ መሻሻል ከጨለማ የመውጫ መንገድ ሳይሆን የጨለማ መግቢያ ሆናት፡፡ ቤተሰቦቿ ባላወቁት ጉዳይ አይንሽን ላፈር አሏት፡፡
ታዲያ አበበች አስቀድማም እንደሚገጥማት ብገምትም ለሰው መልካም ነገር ማድረግ ግን እንደዚህ የእሳት እረመጥ ይሆንብኛል ብላ አላሰበችም ነበር፡፡ አንዴ ያደላትን የመከራ ፅዋ ተጎንጭታ፡፡ ገና እናትና አባቱን እንኳን በደንብ ካለየ ህፃን ልጇ ጋር ያለ ዘመድና ያለ አይዞሽ ባይ ባዶ ቤት ለመኖር ተገደደች፡፡ ስታለቅስ ውላ ስታለቅስ ብታድርም ከልጅዋ በስተቀር አብሯት የሚያለቅስ ሰው አይደለም ወደ ቤቷ ዝር ብሎ አይዞሽ የሚላት እንኳን አልነበረም፡፡
ከእለታት አንድ ቀን የያሬድ አጎት አቶ አስፋው ከባለቤታቸው ከወ/ሮ የኔነሽ ጋር ቡና አፍልተው እየጠጡ ነው፡፡
"እንዴው ያችን የያሬድ ባለቤት ሳንጠይቃት ምን ትለን ይሆን ? ቤተሰቦቿም እደጃችንም እንዳትደርሽ ብለዋታል አሉ፡፡ ያሬድም ብቻዋን ባዶ ቤት አዳፍኖባት ወዶ ዘማች መሄዱ የሚገርም ነው" አሉ፡፡ አቶ አስፋው ፤ በጉንጫቸው ላይ የወረደውን ረጃጅም ፂማቸውን በእጃቸው እየደባበሱ፡፡
"ምን ተጠየቀች አልተጠየቀች ምን ጎሎባታል፡፡ ያለውን ንብረት ጥሎላት ነው የሄደው፡፡ እሷን ደግሞ ማን ይጠይቃታል፡፡ እቤት ተቀምጣ ባሏን ሳይሞት በቁሙ የገፋች ገፊ" አሉ፡፡ ምንም አዘኔታ እንኳን ሳይታይባቸው፡፡ ግን የአበበችን በደልና ስቃይ ቢያውቁ ኖሮ እንደዚህ ባልተናገሩ ነበር፡፡
አቶ አስፋው በሰል ያሉና ብዙ ውጣ ውረዶችን በትንሹም ቢሆን መከራና ስቃይን ያሳለፉ በመሆናቸው ለተጎዳ ሰው የሚያስቡና ትህትና ያላቸው ማለፊያ የእግዚአብሔር ሰው ናቸው፡፡ የባለቤታቸው ንግግር አልተዋጠላቸውም፡፡
አይ! አንች ከንቱ መሆንሽ ያሳዝናል፡፡ ለነገሩ የችግርን ነገር ስለማታውቂው አይፈረድብሽም፡፡
የአንች ነገር በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት እንደ ሚባለው ነው፡፡ በአንች ላይ ቢደርስብሽ ያኔ በደንብ ታውቂው ነበር አሉ፡፡
ምን የተባለውንና የተወራውን ነው፡፡ የተናገርኩት በእሷም የተነሳ አይደለም እንዴ፡፡ ወንድሟ ያሬድን ለመግደል እያደፈጠ ሲስተው የነበረው፡፡ ታዲያ ይህ አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው አይደለም አሉ፡፡ ስኒ አጣጥበው እረከቦት ላይ እያደረጉ፡፡
"ዝም ብለሽ በማታውቂው ነገር ትዘላብጃለሽ፡፡ ያሬድ የተሳሳተው በራሱ ልክስክስነት እንጂ በአበበች ጥፋት አይደለም፡፡ እሷ ምን አጠፋች ባሌ ዲቃላ ቢወልድም እሱ ይሻለኛል፡፡ ስላለች አይደለም አባቷ አይንሽን ላፈር ያሏት፡፡ ለማንኛውም ምንም ቢሆንዐተዋልደናልና የእሷ ቤተሰቦች እንኳን ቢጠሏት ደግሞ በራሳችን ጥፋት ልንሸሻት አይገባም፡፡
ደግመውም ሌላ ንግግር ሳይነጋገሩ በይ እስቲ አሁን በቁሜ ቢሆን ደረስ ብዬ ልምጣ ብለው ዘንጋቸውን ይዘው ተነስተው ወደ አበበች ቤት ሔዱ፡፡
ቤቱ ተዘግቶ በግቢው ውስጥ ሰው አይደለም ከብትም አላገኙም፡፡ አቶ አስፋው፡፡ ወዴት ሔዳ ይሆን ? ቆይታ ይሆን ከሄደች ? እያሉ ግራ በመጋባት ከራሳቸው ሐሳብ ጋር እየተሟገቱ ወደ መጡበት ተመለሱ፡፡
አበበች ልጇን አዝላ ውሃ ቀድታና ከብቶቿን አጠጥታ ከወንዝ ስትመጣ ከአቶ አስፋው ጋር እመንገድ ላይ ተገናኙ፡፡
"ደህና ዋልሽ አበበች" ? አሏት አቶ አስፋው፡፡
እግዚአብሔር ሰላም ዋሉ ? አለች፡፡ አይኗን ወደ አቶ አስፋው አትኩራ እየተመለከተች፡፡
"እኔ እኮ እቤት ሄጄ ቤቱ ተዘግቶ ሳይ የት ሄደች ብየ ስመለስ ነው ያገኘሁሽ" አሉ፡፡
"ምን ላድርገው አንዴ ያደለኝን ከብት እንኳን የሚያጠጣልኝ ሰው አጣሁ፡፡ ችግር ሲደርስብኝ እንኳን ዞር ብሎ የሚያዬኝ ጠፋ፡፡ እግዚአብሔርም ጨከነብኝ አለች፡፡
"እኔም ዛሬ ነገ እያልኩ ሳልመጣና ሳልጠይቅሽ ቀረሁ፡፡ ብትቀየምም ዛሬ አይቻት ልምጣ ብዬ ነው የመጣሁት፡፡ ሰው በቁሙ ካልተረዳዳ ከሞተ በኋላ ዋይ ዋይ ቢሉት ተመልሶ አይመጣም፡፡ እንዴው ሰራተኛ አላገኝሽም ኖሯል? አሉ፡፡
አይ! ጋሸ አስፋው የት አገኛለሁ ሰራተኛ የሚገኘው ከሰው ሲገናኙ ነው፡፡ እኔ ከሰው አልገናኝ፡፡ ዘመዶቸም ጠልተውኛል፡፡ አሁን ደግሞ አዝመራ እየደረሰ ነው፡፡ ማሳውን ማን እንደሚያርስልኝ ጨንቆኛል፡፡ ብን ብየ እንዳልጠፋ ይሄን ጨቅላ ልጅ አቅፌ መሄዱ ከበደኝ፡፡… ልማደኛው እንባዋ ተናንቋት አለቀሰች፡፡
በቃሽ አታልቅሽ ተይ፡፡ አንች እያለቀስሽ ምንም የማያቀውን ህፃን አታስለቅሽ፡፡ ያሬድም እንደሆነ ይመጣል፡፡ ወዶ ዘማች የሄደ ሁሉ አይሞትም፡፡ ለሁሉም እግዚአብሔር ያውቃል፡፡ ዛሬ ቢጨልምም ነገ መንጋቱ አይቀርም፡፡ አይዞሽ፡፡ አዝመራውም ይዘመራል፡፡ ነገ ወደ ሸንኮራ ዮሃንስ መሄዴ ስለማይቀር ሰራተኛ እዠልሽ እመጣለሁ፡፡
ደግሞም የሚቸግርሽ ነገር ካለ እኔም ቢሆን እየመጣሁ አግዝሻለሁ፡፡ በነጋ በጠባ ቁጥር ማልቀስ ጥሩ አይደለም፡፡ እግዚአብሔርም አይወድም፡፡ እባክሽን ለልጅሽ ስትይ አታልቅሽ፡፡ አንችም ያለ እድሜሽ በሽታ ላይ ትወድቂያለሽ፡፡ ብለው አፅናንተዋት ተነስተው ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡
ትንሽ የነበረባት የጭንቀት ጨለማ ፈገግ ያለ መሰላት፡፡ አቶ አስፋው አይዞሽ ብለዋት ሲሄዱ፡፡ ባለቤቷ ወዶ ዘማች በመግባቱ መልሳ በህይወት የምታገኘው ግን አልመስል አላት፡፡ ፈገግ ብሎ የነበረው የጨለማ ብርሃን መልሶ ይጨልምባታል፡፡
አበበች ሁለተኛ ልጇን መፀነሷን የታወቃት ያሬድ በሄደ በሁለተኛው ሳምንት የወር አበባዋ ሲቋረጥ ነበር፡፡
አቶ አስፋው ለአበበች በገቡላት ቃል መሰረት ሰራተኛ አግኝተው ቀጠሩላት፡፡ ባለቤቷ ያሬድ እንደነበረው ጊዜ የተደላደለ ህይወትን ባትኖርም በባዶ ቤት ሆና ከምታለቅሰው የተሻለ ህይወት መኖር ጀመረች፡፡
የቤተሰቦቿ መጥላት ሳያንሳት የተመስገን እናት ወ/ሮ አሰገደች ሲወጡና ሲገቡ የባልሽን ዲቃላ አሳዳጊ አደረግሽኝ ፡፡ ባልሽም ዲቃላውን እንዳይወስድ የሰራው ስራ አሳፍሮት አገር ለቆ ጠፋ፡፡ እያሉ አላስገባ አላስወጣ አሏት፡፡ አበበች ግን አልቅሳ ዝም ከማለት ውጭ ምንም ምላሽ አልነበራትም፡፡
ጉልላት የተባለው የአበበች ሰራተኛ ትንሽ ጠና ያለና ነብስ አወቅ ያደረገ ነው፡፡ አበበች ስታለቅስና ስትበሳጭ አይዞሽ እያለ እያፅናና ያበረታታል፡፡
ጉልላት ለሁሉ ታዛዥ ቅን ሰው ለመሆኑ ደከመኝ ሰለቼኝ ሳይል ሲያገለግላት ላየውና ለተመለከተው የእናት ልጅ እንኳን እንደሱ አድርጎ የሚሰራ አይመስልም ነበር፡፡
አበበች ባለቤቷ ያሬድ ከሄደ ከዘጠኝ ወር በኋላ አንድ ቀን በእለተ ሐሙስ በጥዋት ተነሳች፡፡ የሚሸጥ ስንዴ ቋጠረች፡፡ ለጉልላት ገበያ ልልከው አስባለች፡፡ ይሔን ስንዴ ሽጥና አንዳንድ ነገሮችን ግዛልኝና ና፡፡ እኔም ቀኔ ደርሷል ብላ የሚገዙትን የእቃ ዓይነቶች ነግራ ቁርሱን አብልታ ወደ ገበያ ላከችው፡፡

👍53❤3
#የጣት_ቁስል
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ
ሚስጥሩ
ከአራት ዓመት ከውጊያ በኋላ፡፡ እንደ ማንኛውም የሰራዊት አባላት ዓመታዊ የወር ፍቃድ ደረሰው፡፡ የታጠቀውን የመንግስት መሳሪያ ለቅርብ አመራሩ አስረከበ፡፡ የፍቃድ ወረቀት ተቀበለ፡፡ የትግል አጋሮቹ ወደ ቤተሰቦቹ ሸኙት፡፡
የወርሃዊ ፍቃድ የተሰጠው እለት አራት አመታትን እንዳልቆየ ባለቤቱንና ልጁን ቶሎ ደርሶ ለማየት አንድ ቀን ሌሊት አልነጋ አለው፡፡ ካሳለፈው አራት ዓመታት በላይ በአይኑ ላይ እንቅልፍ የሚባል እንኳን ሳያልፍ ፍጥጥ ብሎ አነጋ፡፡ የሌሊቱ እንቅልፍ ወደ ቀን ተቀይሮበታል፡፡ ከመኪና ወንበር እያወዛወዘ ያላትመዋል፡፡
ያሬድ ከሁለት ቀን የመኪና ጉዞ በኋላ፤ አመሻሽ ላይ የትውልድ ቀየው ደረሰ፡፡ ሰፈሩ ሁሉ ዓዲስ ሆነበት፡፡ አካባቢው ተቀያይሯል፡፡ ተገረመ ፤ ከቤቱ አካባቢ
ዳገቱ ላይ ሻንጣውን አውርዶ አረፍ አለ፡፡ አይኖቹን በእሱ ቤት ላይ ተከላቸው፡፡ የእሱ ቤት ሰርቶት እንደሄደ አላገኘውም፡፡ የጣራው ሳር እረግፏል፡፡
የግቢውም አጥር ወላልቋል፡፡ በውስጡ ሰው ያለበት አይመስልም፡፡ ቤተሰቦቹን የሚያገኝ አልመስል አለው፡፡ ሆዱ በፍራት ተዋጠ፡፡ አይኖቹ በእንባ ተሞሉ፡፡ ወደ ወላለቀውና ፈራረሰው ቤቱ ተጠጋ፡፡
ከቤቱ ደጅ ላይ ሁለት ወንድ ህፃናት ልጆች እየቦረቁ ይጫወታሉ፡፡ አትኩሮ ተመለከታቸው፡፡ አንደኛው ህፃን ትልቅ እና ሰውነቱ ለወጥወጥ ቢልበትም የራሱ ልጅ ምትኩ እንደሆነ አልተጠራጠረም ነበር፡፡
ሁለተኛው ህፃን ግን የማን እንደሆነ ሊያውቀው አልቻለም፡፡ ወደ ሚጫወቱት ህፃናት ተጠግቶ ልጁን ምትክ ምትኩ? ብሎ ተጣራ፡፡ ህፃኖቹ የራስ የራሳቸውን እየተጨዋወቱ ከስራቸው ተጠግቶ የቆመውን ያሬድን አላዩትም ነበር፡፡ ህፃን ምትኩ መጫወቱን ትቶ ቀና አለ፡፡ በሰውነቱ ግዙፍ የሆነ ሰው አዬ፡፡ አባቱ እንደሆነ አያውቅም፡፡ ፈርቶ የወንድሙን የሁሉባንተን እጅ እየጎተተ ሸሽተው ወደ ቤት ገቡ፡፡
ምን ሁናችሁ ነው የምትሮጡት? ውሻ አባረራችሁ እንዴ ? አለች አበበች፡፡ ልጆቿ እየሮጡ ሲገቡ ደንግጣ፡፡
"ህፃን ምትኩ በተቆራረጠ ትንፋሽ ውሻ አይደለም ፤ መጥቷል" አላት፡፡
"የማን ሰው ነው የመጣው" ?፡፡
"አላውቀውም ሲያዩት ያስፈራል፡፡ ውጭና እይው እውጭ ቁሟል አላት፡፡ ውጭ ውጭውን እየተመለከተ፡፡
አበበች ውጭ እና እይው ሲላት የባሰ ድንጋጤ ጨመረባት፡፡ የሚያስፈራ ሰው ደግሞ ከየት መጣብኝ፡፡ እንዲያው አምላኬ ምን ልታሰማኝ ይሆን? ቤቴን ሰው አያውቀው፡፡ እንዲያው ሰርታ በላች ብለው ሊጨርሱኝ ይሆን? ከሰው ጋርም ባይሆን ከራሷ ጋር ያወራችው ነበር፡፡
ወደ ውጭ ብቅ አለች፡፡ እውነትም የሚያስፈራ ሰው ነው፡፡ የውጩን በር ከፍቶ ገባ፡፡ ሰውነቷ ተርበተበተ፡፡ የሚያስፈራው ሰውየ እየቀረባት መጣ፡፡
ለአራት አመታት የተለያት ባለቤቷ ያሬድ ነው፡፡ ማመን አቃታት፡፡ለመራመድ እግሮቿ ተሳሰሩ፡፡ አይኖቿ ያሬድ ላይ እንደተተከሉ በናፍቆት እንባ ተሞሉ፡፡
አበበች በደረሰባት ስቃይና መከራ ተጎሰቋቁላለች፡፡ የሃያ አምስት አመት ወጣት መምሰሏ ቀርቶ የአምሳ አመት አሮጊት ሆናለች፡፡ ያሬድ አዘነ፡፡ እያለቀሰ ተጠመጠመባት፡፡ ቤቱ ከሃዘን እንባ ወደ ደስታ እንባ ተቀየረ፡፡ አበበች የደረሰባትን ስቃይና መከራ እንዲሁም ባለቤቷ ያሬድ ከሄደ ስለወለደችው ልጅ ሁሉባንተ አጫውታው ልጁም የራሱ እንደሆነ ነግራው አምኖ ተቀብሏት ፡፡ ያሳለፉትን ናፍቆትና ትዝታ እያስታወሱ ሲለቃቀሱና ሲያወሩ ቢቆዩም ስለተደበቀው ሚስጢር ምንም ነገር ሳያወሩ አድረው በማግስቱ ጥዋት ነበር፡፡
ቡና ተፈልቶ "እንዴት አደረግሽው ያንን ነገር ያላት ?
"የቱን ነገር ? አለች ጥያቄው ግራ አጋብቷት፡፡
"ሚስጢሩን ነዋ አላት"፡፡
"አይ! ምነው ሁሉንም ነገር ለማንም እንዳትነግሪ ብለኸኝ በባዶ ቤት ያለቤተሰብና ያለ ዘመድ አዳፍነህብኝ ሄደህ ፤ እንዴት ነው ሚስጢሩ የሚወጣው?፡፡ ይኸው ከዛን እለት ጀምሮ ተመስገን እኔ ደጀም አልደረሰም፡፡ እስካሁንም አላየሁት፡፡ ብላ የነበረውን ሁኔታ ስታነሳሳ ውስጧ ተረበሸ፡፡ የብሶት እንባ አለቀሰች፡፡
ያሬድ የሚለው የሚናገረውን ቢያጣ ግራ ቢገባውም፡፡ ከተመስገን ያልተገናኛችሁት እዚሁ እያለ ነው ወይስ ከሃገር ለቆ ነው? አለ፡፡
በፊቷ ላይ የሚወርደውን እንባ በፎጣዋ ጠረግ ጠረግ እያደረገች "እዚሁ እያለ ሲሸሸኝ ፣ ሲሸሸኝ ቆይቶ እህቱን እድላዊትን ወደ ፀበል ልወስዳት ነው፡፡ ብሎ ቤተሰቦቹን አታሎ ወደ ተባለበት ፀበል ሳይወስዳት ወደ አረብ ሃገር ተሰደው ምን እንደደረሰባቸው እንጃ እድላዊትም ከመጣች አንስታ ከአልጋ ላይ አልተነሳችም አሉ"፡፡
"ማን ነገረሽ ? እነሱ ቤት እንደማትደርሽ ነግረሽኝ ነበር"::
እድላዊት በጠና መታመሟን የነገረኝ ጉልላት ነው፡፡ እኔማ ከቤትም ስወጣ ሰው ሁሉ እንደ ዕብድ ውሻ ይሸሸኛል፡፡ አለች የፈላውን ቡና እየቀዳች፡፡
"ለዚሁ ሁሉ ስቃይና መከራ ያበቃሁሽ እኔ ነኝ፡፡ እንደበደልኩሽም አውቃለሁ፡፡ ግን ወድጀ አይደለም፡፡ የሃገር ጉዳይ ሆኖብኝ ነው፡፡ ጥየሽ የሔድኩት ፤ ብዙ አትፍረጅብኝ ሃገር ሰላም ካልሆነች እኛም ሰላም እንደማናገኝ አንችም ታውቂያለሽ" አለ ፤ ያሬድ፡፡
"እግዚአብሄር እንኳን ከእሳት አትርፎህ ለአይነ ስጋ እንድንገናኝ አበቃን እንጂ ያለፈው አልፏል፡፡ አሁንም አንተ ከመጣህ ጊዜው አይርቅም፡፡ የተደበቀው ሚስጢር ይውጣና እኔም እናቴ ናፍቃኛለች፡፡ ይሄው ካየኋት፤ አራት አመታትን ጨርሰን አምስተኛ አመታችንን ልንይዝ ነው፡፡ ምንም ቢሆን የእናት ክፉ የለውም፡፡ ባላወቀችው ነገር እንደጠላችኝ አውቃለሁ አለች፡፡ የቀሉ አይኖቿን እያሻሸች፡፡
እድላዊት በደረሰባት ጉዳት የተነሳ የአልጋ ቁራኛ ሆናለች፡፡ እህል እንኳን መቅመስ አቅቷታል፡፡
ተመስገን የቁም ስቃይና መከራ እያየ ባለበት ሰዓት ሞቷል እየተባለ የተወራለት ያሬድ መምጣቱን ሲሰማ
ወደ አረብ ሃገር ሲሰደድ ሶስት ሰዓት የፈጀበት የገመሪ ተራራ እፊቱ ላይ የተጋረጠበት ያክል መስሎ ተሰማው፡፡
ከአምስት ቀን እረፍት በኋላ፤ የተደበቀውን ሚስጢር ለማውጣት ይመለከታቸዋል የተባሉትን ዘመድና ሽማግሌዎች ለማነጋገር በጥዋት ተነሳ፡፡ የውጭ በሩን ከፍቶ ሳይወጣ ከቤቱ ማዶ ላይ አንድ ነጭ ጋቢ የለበሰ ሰው አየ፡፡ ወደ እሱ ቤት እየመጣ ይመስላል፡፡ ወደ አሰበበት መሄዱን ተወት አድርጎ ወደ እሱ የሚመጣውን መጠባበቅ ጀመረ፡፡
በጥዋት ጋቢያቸውን ተከናንበው ወደ ያሬድ ቤት የሚመጡት ቄስ አሻግሬ ነበሩ፡፡
"ደህና አደርህ ያሬድ" ? አሉ ቄስ አሻግሬ፡፡ እስሩ ደርሰው፡፡
"እግዚአብሔር ይመስገን ደህና አደሩ ቄስ አሻግሬ"?፡፡
"እንኳን ለሃገርህ አበቃህ" ፡፡
ልጆች ደህና ናቸው ?፡፡
"ደህና ናቸው ፤ እንዲያው አንተ ለጤናህ ደህናነህ ?
ደህና ነኝ፡፡ ወደ ቤት ይግቡ ? ቄስ አሻግሬ አለ፡፡
አይ! አልገባም ቸኮል እላለሁ፡፡ እንዲያው በጥዋቱ ተነስተህ ኖሯል፡፡ የምትሄድበት አለ እንዴ ? አሉ፡፡
አዎ፤ የምሄድበት ነበረኝ፡፡ ከማዶ ስትመጡ ሳይ ጊዜ ነው፡፡ ወደ እኔ መምጣትዎን ሳውቅ የጠበኩዎት፡፡ ብሎ ምን ነው ደህና አይደሉም እንዴ? አለ፡፡
አይ! እኔስ ደህና ነኝ፡፡ እንዲያው እኒያ ቄስ መልካሙ ወደ አንተ ልከውኝ ነበር፡፡ የመጣሁት አሉ፡፡
ምን ነው በሰላም ነው? አለ ያሬድ፡፡ እድላዊት ምን ሆነች ብሎ እየተጠራጠረ፡፡
ልጁን ወይም ማሳደጊያ ይክፈለን እኛም አቅማችን እየደከመ ነው፡፡ እድላዊትም በሽተኛ ሆናለች፡፡ አንድ ነገር ያድርግልን ብለው ነው የላኩኝ አሉ፡፡

👍44❤3🎉2