አትሮኖስ
281K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
481 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ


‹ከሃያ ደቂቃ በኋላ ቢሮዬ እንገናኝ።››

በእሺታ ራሷን ነቀነቀች፣ ከዚያም አልፋው ጥላው ሄደች፡፡

ከግማሽ ሰአት በኋላ ራሄል ቢሮው መጥታ  ከጠረጴዛው ማዶ ተቀመጠች፣ በአንድ እጇ እስክሪብቶ፣ በሌላ እጇ ማስታወሻ ደብተር ይዛለች። ሁኔታዋ አስገረመው ፡፡

ዶ/ር ዔሊያስ መናገር ጀመረ ‹‹ፀጋ በቴክኒካል ተርሙ ሄሚፕሌጂያ ተብሎ የሚጠራ  በሽታ ተጠቂ ነች፡፡በሌላ አነጋገር ሴሬብራል ፓልሲ ታማሚ ነች ማለት ነው፡፡ በሰውነቷ አንድ ጎን በግራ እጇ እና በግራ እግሯ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሮባታል..አጥንቶቾ በጣም ደካማ ስለሆኑ እንደልብ ለመንቀሳቀስ ትቸገራለች…በተወሰነ መልኩ የመስማትና ቃላቶችን አቀላጥፎ የማውራት ችግርም አለባት።የእሷን  ጤና ሁኔታ ለማሻሻል በሚደረገው ሂደት ውስጥ የሚሳተፉትን  - ፊዚዬ ቴራፒስት  ጨምሮ፣ ብዙ ባለሞያዎች አሉ.. እና እያንዳንዱን መቼ መቼ  ማየት እንዳለባት አስረዳት፡፡

‹‹በተጨማሪም የጆሮ ኢንፌክሽንን እየተዋጋች ስለነበረ አንቲባዮቲክ ትወስዳለች።››ዔሊ የራሔልን እይታ በመሸሽ እስክሪብቶውን አንሥቶ መሞነጫጨር ጀመረ።

ራሄል ትዕግስት በማጣት‹‹ዶክተር ሌላ ልትነግረኝ የሚገባ ነገር እንዳለ ይሰማኛል››አለችው.

‹‹ትሁት  ከጊዜ ወደ ጊዜ በንዴት በሽታ እየተሰቃየች ነው ። ስለዚህ ስሜቷን በጥንቃቄ መከታተል እና የሚያበሳጮትን ነገሮች ማስወገድ ያስፈልግሻል ማለት ነው ።ያው እንድትናደድ ከፈቀድሽላት የሚጥል በሽታ ስላለባት ነገሮች ይባባሳሉ… እንደ አለመታደል ሆኖ ይሄንን ጉዳይ በመድኃኒቷን ማስተካከል አልቻልንም።››

‹‹ትሁት ማለት?››ግራ በመጋባት ጠየቀችው

‹‹ይቅርታ..ፀጋ ወደእናንተ ቤት ከመምጣቷ በፊት ወላጅ እናቷ ትሁት ብላ ነበር ስም ያወጣችላት….ከዛ ነው አባትሽ ፀጋ ያለት፡፡እና እኔ ትሁት የሚለውን ስም ለረጅም ጊዜ ስለተጠቀምኩበት በቀላሉ ከአእምሮዬ ላወጣው አልቻልኩም…..››

‹‹አይ ችግር ለውም..ትሁትም ደስ የሚል ስም ነው››

‹‹አዎ…እና እንዳልኩሽ ፀጋ ማለት ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋት ልጅ ነች፣፣በተለይ መናደድ የለባትም….ምክንያቱም ከንዴቷ በኋላ የሚከሰተው የሚጥል በሽታ ሌሎች ብዙ የጤና ችግሯቾን ነው የሚያናጋባት››

በራሔል ፊት ላይ የፍርሃት ብልጭታ ሲያይ ተገረመ።

‹‹የሚጥል በሽታ ሊነሳባት መሆኑን  እንዴት አውቃለሁ እና ምን ያህል መጥፎ ነው?››

‹‹ትለይወለሽ…እጆቿ  ይንቀጥቀጣሉ… የዐይን ሽፋኖቿን ይርገበገባሉ እነዚህን እና የመሳሰሉት ምልክቶችን ታሳያለች፡፡የዛን ጊዜ አጓጉል ወድቃ እራሷን እንዳትጎዳ ጥንቃቄ መውሰድ ይገባሻል፡፡ ማንኛውም አሳሳቢ የጤና ችግር ሲያጋጥማት በአፋጣኝ ወደሆስፒታል ልትወስጂያት የግድ ነው፡፡ በመደበኝነት በሳምንት ሶስት ቀን ሆስፒታል የህክምና ክትትል አለት፡፡በመሀል አስፈላጊ ሲሆን ለእኔ በማንኛውም ሰዓት ልትደውይልኝ ትችያለሽ ፣ ወዲያውኑ ልመጣ እችላለሁ።..›› ዔሊያስ መጀመሪያ ያሰበው ለፀጋ  ነው።‹ራሔል በዚህች ልጅ ላይ ያለውን ችግር  በሙሉ ማወቅ አለባት› ሲል በውስጡ አሰበ፡፡

‹‹ፀጋን  ከተወለደች ቀን ጀምሮ እየተንከባከባት ነበር…እናትዬው ተስፋ ቆርጣበት በሆስፒታል አልጋ ላይ ማሽን እንደተሰካካባት ጥላት ስትሰወርም አንደኛ እናትዬውን ከልጅነት ጀምሮ የሚያውቃት ጓደኛው ስለሆነች ሲሆን ሁለተኛም ከራሱ ህይወት ጋር አያይዞ ሲንከባከባትና እንደወላጅ ስለሚጨነቅላት ነው፡፡በመጨረሻም ከስድስት ወር የሆስፒታል ቆይታዋ በኃላ የራሄልን ወላጆችን በግሉ ፈልጎ በማግኘት  በጉዲፈቻ እንዲወስዷት በማድረግ ሂደት ላይ የአንበሳውን ድርሻ የእሱ ነው፡፡ከዛም በኃላ በቃ በኃላፊነት የሚያሳድጓት እና የሚንከባከቧት ወላጆች አግኝታለች ብሎ አልተዋትም፤ በቆሚነት የእሷ ሀኪም በመሆን እነ  አቶ ቸርነት ቤት ድረስ እየተመላለሰ ሁኔታዋን ይከታተላል፤ ታማለች ብለው ሲደውሉለት ያለምንም ማቅማማት ሞተሩን ተረክ አድርጎ በሮ ይሄድና ያያታል…እናም ይህቺ ልጅ ለእሱ እንደአንድ ታካሚው ብቻ አይደለችም…የህይወቱ አካል ነች….ስቃዮ ያመዋል…ለቅሶዋ ይሰማዋል….ፈገግታዋ ያስቀዋል….ለዛ ነው ራሄልን በትክክል እናቷ በምትንከባከባት መጠን ትንከባከባታለች ብሎ ሊያምን ያልቻለው፡፡

‹‹ራሄል ምን መሰለሽ ፀጋን እንዲህ ስታያት በአካላዊ እይታ ጥሩ ሁኔታ ላይ ያለች ሊመስልሽ ይችላል, ግን ውስብስብ በሆነ የህክምና ሂደት ውስጥ እያለፈች ነው፡፡ ሰውነቷ እየሰጠ ያለው መልስ  በጣም ደካማ ነው. ለሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት በጤና እሷን ማቆየት ከቻልን ትልቅ ድል ነው…በህክምናው ሂደት ከባድ ችግር እያጋጠመን ነው ››

ራሔል በፍጥነት ማስታወሻ እየወሰደች ሲሆን  በእጇ ላይ ትንሽ መንቀጥቀጥ አየ፡፡‹‹ስለ ምን ዓይነት የሕክምና ችግሮች ነው የምታወራው?››

‹‹በአእምሯዋ ውስጥ ፈሳሽ መከማቸት ጀምሮል እና  ተጨማሪ ኢንፌክሽኖች እና ሌሎች ችግሮችም እየተከሰቱባት ነው፡፡››

እሺ፣ ምናልባት ትንሽ አክብዶባት ሊሆን ይችላል ግን ማወቅ አለባት። የበለጠ መረጃ ባላት ቁጥር እሷ ማድረግ የምትችለው የተሻሉ ውሳኔዎች ትወስናለች፣ ።

‹‹ወላጆቼ ግን ፀጋ ያለባትን ይሄን ሁሉ የጤና ችግር ያውቃሉ?››

‹‹አዎ..እንደውም ለአንቺ በጥቅሉ ነው የነገርኩሽ እንሱ ግን እሷን ለማሳደግ ከመወሰናቸው በፊት እያንዳንዱን  በዝርዝር አስረድቻቸዋለው…..ግን ለምን ጠየቅሺኝ?››

‹‹እኔ እንጃ…..በዚህ ሁሉ የጤና እክል ውስጥ ሆኖ ምን አልባትም የመሞቻ ቀኗን እየተጠባበቀች ያለች እና ክፉና ደጉን የማታውቅ ልጅ እንዴት ለማሳደግ እንደፈቀዱ ግራ ስለገባኝ ነው፡፡››

‹‹ትክክል ነሽ….እኔም ወላጆችሽን በጣም የማከብራቸውና ከልቤ ማደንቃቸው በዚህ ውሳኔያቸው ነው…እነሱ ያደረጉትን ማንም ሌላ ሰው ያደርገዋል ብዬ አላስብም..እነሱ ለእኔ የህይወት ዘመን ጀግናዎቼ ናቸው፡፡››አለና ካርዱን ከጠረጴዛው ላይ አንስቶ  ሰጣት። ‹‹ይህ የሆስፒታሉ የድንገተኛ አደጋ ቁጥር፣የቤቴ ቁጥር እና የሞባይል  ቁጥሬ ነው። በፈለግሺኝ ጊዜ  ደዉይልኝ››ራሄል መረጃውን እንደያዘች ረጅም እና ዘገምተኛ ትንፋሽ ወደ ውስጣ ሳበች ከዛ ወደ ውጭ ተነፈሰች፡፡  ወረቀቱን  እና ካርዱን በቦርሳዋ ውስጥ አስገባች።

‹‹ከመሄዴ በፊት ግን አንድ የመጨረሻ ጥያቄ ልጠይቅህ?››

‹‹የፈለግሽውን ጠይቂኝ››አላት በጉጉት፡፡

‹‹ፀጋን ቤተሰቦቼ  እንዲያሳድጓት በግል የጠየቅካቸውና ያሳመንካቸው አንተ ነህ….ለሌሎችም ታካሚዎችህ እንደዛ ታደርጋለህ?››ስትል ያለሳበውን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡

‹‹እውነቱን ለመናገር የፀጋ እናት የልጅነት ጎደኛዬ ነች…አንድ ሰፈር ነው ያደግነው…ህይወት ባልሆነ መንገድ መርታ ያልሆነ ማጥ ውስጥ ጨመረቻት እንጂ  እንዲህ እንደቀልድ ልጇን ጥላ የምትሰወር ልጅ አልነበረችም….እና ፀጋን ዝም ብዬ ችላ ብዬ ማደጎ ቤት ስትገባ ማየት አልቻልኩም…የምተማመንባቸው  አሳዳጊዎች መፈለግ  ጀምርኩ..መጀመሪያ የራሴ ወላጆች ነበር የመጡልኝ..ግን የጽጌረዳ ሰፈር እዛው ስለነበረ ትንሽ ልክ መስሎ አልተሰማኝም….ከዛ ምክንያት ነው ወላጆችሽን ያገኘሁት…እናም ደግሞ ሁሉንም ነገር በግልፅ ነግሬያቸዋለው….ምንም የማያውቁት ነገር የለም፡፡››

‹‹አባቷስ?››

‹‹ምን ያህል እውነት እንደሆነ አላውቅ…አባቷ እንደሞተ ነው የነገረችኝ… ሌላ ጥያቄ ይኖርሻል?››

‹‹ አይ የለኝም..አመሰግናለው…. ››አለች… ቆመች… እጁን ለመጨበጥ ከጠረጴዛው አሻግራ እጇን ዘረጋች፡፡
65👍3