አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ናኦልና ኑሀሚ ብራዚል ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ  ይገኛሉ.. ከኢትዬጵያ ደህንነት መስራቤት ተልእኮ ተሰጥቶችው የመጡ ሁለት የደህንነት ሰዎች አብረዋቸው አሉ…ሁለቱ መንትዬች በኮንክሪት ግግር እንደቆመ ሀውልት ጎን ለጎን ተጣብቀው  ቆመዋል…ከፊት ለፊታቸው በአንድ ሜትር ርቀት አንድ የታሸገ የሬሳ ሳጥን ወለል ላይ ተቀምጦ ይታያል…እሬሳውን ጭኖ ወደኢትዬጵያ የሚበረው አውሮፕላን በሰላሳ ሜትር ርቀት ላይ ይታያል…እዛ ሬሳ ሳጥን ውስጥ ለዘላለም አሸልባ  የተኛችው ምስራቅ ነች፡፡

ናኦል እና ኑሀሚ ከዳግላስ ወጥመድ አምልጠው የሲኦል ወጥመድ ከሆነው ከእዛ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ወጥተው እንሆ አስተማማኝን ቦታ ላይ ቆመዋል…ከአንድ ሰዓት በኃላ በአገራቸው አየር መንገድ ወደሀገራቸው ለመብረር ዝግጅታቸውን ሁሉ አጠናቀዋል…ግን እዚህ ለመድረስ የከፈሉት መሰዋዕትነት ሁለቱንም እስከወዲያኛው ያፈራረሳቸው ነው፡፡አሁን በድናቸው ነው የሚንገዋለለው፡፡እግዚያብሄር በእድሜያቸው መጀመሪያ በዛ በህፃንነታቸው ጊዜ  ሚወዱዋቸውን ወላጆቻቸውን በመንጠቅ አሸማቆቸው ነበር  በእድሜያቸው አጋማሽ ደግሞ በእድሜ ልካቸው አብራቸው የነበረችውን፤ ከጎዳና አንስታ ህይወት የሰጠቻቸውን፤የተዘረፈውን  የወላጆቻቸውን ንብረት ያስለመለሰልችላቸውን.. እናም ከዛም አልፍ እሷን ለማትረፍ አህጉር አቆርጣ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ የገባችላቸውን የዚህችን  ሴት ህይወት ማጣት ለሁለቱም ቅስም ሰባሪ ነው፡፡ለናኦል ደግሞ ነገሩ የተለየ ነው….ይህቺን ሴት ገና የ12 ዓመት ልጅ እያለ እዛ በረንዳ ፤ላይ ካያት ቀን ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ይወዳት ነበር…እዚህ ነገር ውስጥ ያስገባት እራሱ ነው፡፡እህቴ ጠፋችብኝ አፋልጊኝ ብሎ ደወላላት..እሱን ለመርዳ ከጎሬዋ ወጣች..ለብቻው ልትተወው ስላልፈለገች አህጉር አቋርጣ ተከትላው መጣች ..አንድ ወር ሊደፍን ትንሽ ቀን ለቀረው ቀናት በመከራና በስጋት ውስጥ ቢሆኑም እንኳን እጅግ ጣፋጭ የሆነ የፍቅር ህይወት አሳልፈዋል….የህይወትን ጣእም እና የፍቅርን ትርጉም አሳይታዋለች ..አስተምራዋለች፡፡….ከእሷ ጋር የመሰረቱት የውሸት ትዳር ለእሱ በህይወቱ ካጋጠመው ተጨባጭ እውነቶች መካከል ምን እልባትም ዋነኛው  ነው…በሰላም ወደሀገራቸው ሲመለሱ ለምኖና እግሯ ላይ ወድቆ ጋብቻቸው ባለበት እንዲቀጥልና በእሷ እቅፍ ውስጥ ለዘላለም መቅለጥ ነበር የሚፈልገው፡፡እቅዱ እንደዛ ነበር….ብቸኛ ምኞቱም ያ ነበር..፡፡ግን አሁን ሁሉ ነገር እንዳልነበረ ሆኗል….፡፡በሰልም እየሰቀችና እተፍለቀለቀች አብራው የመጣችው ሴት ይሄው ህይወት አልባ በድን እሬሳ ሆነ  በሳጥን ውስጥ ታሽጋ  ወደሀገሯ እየተመለሰች ነው፡፡እና ደግሞ በጣም እያበሳጨው ያለው ነገር  ምንም እንዳልተፈጠረ በህይወት ቆሞ አየር እየሳበ መሆኑን ሲያስብ ነው….ደግሞ እኮ የእሱን ሞት ነው ሞተችው፡፡
ነገሩ እጌት ነው  የተከሰተው  ብለን ወደኃላ ዞረን ስናስታውስ……
..
ከአራት ቀን በፊት  ነው፡፡ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ  የታገቱበት ክፍል ተከፈተ….የመጣው  የተለመደው የዳግላስ ተላላኪ ነው፡፡
ወደኑሀሚ አትኩሮ እየተመለከተ ‹‹ጌታዬ እየጠበቀሽ ነው››አላት፡፡

ኑሀሚ ከ30 ደቂቃ በፊት አምጥቶ የሰጣትን ውብ የራት ቀሚስ ለብሳና ተዘጋጅታ  የጠበቀችው ነበር፡፡ምስራቅንና ወንድሟ ናኦልን ተራ በተራ ጉንጫቸውን ሳመችና በዝግታ እርምጃ ልጁን ተከትላ ወጣች፡፡ቀደም ብሎ የተላከላትን ቀሚስ ለብሳ ወደታባለችው የእራት ግብዣ መሄድ የምርጫ ጉዳይ አይደለም…ግዴታ ነው..፡፡በሰዓቱ እያስጨነቃት የነበረው  ከእራት ቡኃላስ ሚለው ነበር?….ወደአልጋ እንሂድ ቢለኝስ?እንደዛ ስታስብ ዝግንን የሚያደርግ ቀፋፊ ስሜት ነበር የተሰማት፡፡እሷ ግን እኮ እንደዛ አልነበረችም፡፡ለአላማዋ ጥቂትም ጥቅም ይኑረው እንጂ ከማንም ወንድ ጋር ተጋድሞ ወሲብ መፈፀም ልክ እንደካርታ ጫወታ  ዘና ብላ ምትፈፅመው ቀላልና ትርጉም የማይሰጣት ጉዳይ ነበር…ደግሞም በሰላይነት ሕይወቷ እንዲጠቅማት በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ላይ በቂ ስልጠና ወስዳለች…አሁን ግን አንድ ነገር ገብቷታል..ለካ በዛን ጊዜ ነገሩ ቀላልና የማያስጨንቅ ሆኖ የሚታያት  ስለሰለጠነችበት ብቻ አልነበረም…ልቧ ኦናና ባዶ ስለነበረ ነበር እንጂ፡፤አሁን ግን አንድ ሰው ገብቶበታል…ያ ሰው ደግሞ እሷን ለማዳን በቅርብ ርቀት ባለ ጫካ ውስጥ ሆኖ እቅዱን ስለሚያሳካበት ዘዴ እየተጨነቀና እያሰበ ነው…እና  እሷ ካለፍላጎቷም ቢሆን ከሌላ ሰው ጋር ወደአልጋ የመሄድን ጉዳይ በቀላሉ ምታየው አይደለም….ይሄ ነው ያስጨነቃት…የተንጣለለው ሳሎን ውስጥ ስትገባ ግዙፉ ጠረጴዛ በምግብና በመጠጥ ተሞልቶ ተመለከተች፣አንድ ሴትና ሁለት ወንድ አስተናጋጆች ፈንጠር ብለው ግድግዳውን ተደግፈው ትእዛዝ በመጠባበቅ ላይ ናቸው…እንደገባች ዳግላስ ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ተራመደ…ቀለል ያለ አለባበስ ነው የለበሰው…ከላይ ሰማያዊ ሸሚዝ ከዳለቻ ጅንስ ሱሪ ጋር አድርጎል…በፈገግታ ተጠጋትና እጁን ለሰላምታ ዘረጋላት…ፈራ ተባ እያለች እጇን ሰነዘረችና ጨበጠችው፡፡

እጇን ሳይለቅ እየጎተተ ወደ ጠረጴዛው ወሰዳትና  ወንበር ስቦ አስቀመጣት..ከዛ ራመድ አለና  ከፊት ለፊቷ ሄዶ ተቀመጠ፡፡ወዲያው ለአስተናጋጆች በእጁ ምልክት ሲያሳይ ተንደርድረው መጡና ብርጭቆቸውን በመጠጥ ሞልተውላቸው ወደቦታቸው ተመለሱ፡፡
ከተቀዳለት መጠጥ አንዴ ጠቀም አድርጎ ከተጎነጨለት በኃላ‹‹እንዴት ነው ቆይታ ?››ሲል ጠየቃት፡፡
ያለምንም ማስተባበል‹‹በጣም አሰልቺ ነው››ስትል ፍርጥም ብላ መለሰችለት፡፡
‹‹እንግዲህ የአጋጣሚ ጉዳይ ሆነና ለስራ ጉዳይ ወጣ ማለት ነበረብኝ…አሁን ግን ተመልሼለው…ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ፍፅም ደስተኛ እንድትሆኚ የተቻለኝን አደርጋለሁ…ከነገ ጀምሮ የአማዛንን ድንቅ ውበት ጎዲያ ጎድጓዳዋን እያዞርኩ አሳይሻለው..እንስሳቱን ፤ወፎችን ፤ፏፏቴዎችንና ወንዙን ሁሉንም አንድ በአንድ አሳይሻለው..እናም ከቦታው ጋር በፍቅር እድትተሳሰሪ የተቻለኝን እጥራለው..ከቦታው ብቻ ሳይሆን ከእኔም ጋር ፍቅር እንዲይዝሽ እፈልጋለው››ሲል ተናዘዘላት፡፡
‹‹እርግጠኛ ነህ ከአንተ ፍቅር እንዲይዘኝ ማድረግ ትችላለህ?››
‹‹እንግዲህ እቅዴ እንደዛ ነው››
‹‹ጥሩ ነው››ብላ በአጭሩ መለሰችለት
‹‹ምኑ ነው ጥሩ?››በጫወታው እንዲገፉበት ስለፈለገ ጥያቄውን ቀጠለበት፡፡
‹‹እስከማውቅህ ድረስ ሁሉንም ነገር    በጉልበትና በማስግደድ ነው የምታደርገው…..ቡኃላ እንዳፈቅርህ ማድረግ ሲያቅትህ እንዳትተኩስብኝ ነው የምፈራው…፡፡››ስትለው ከጣሪያ በላይ ተንከትክቶ ሳቀ..‹‹በይ በባዶ ሆዴ ከዚህ በላይ መሳቅ አልችልም ..እራት እንብላና ወደበረንዳ ወጣ ብለን መጠጣችንን እየተጎነጨን የጀመርነውን ጫወታ እንጨርሰዋለን…››አለና ሰሀን አነሳ …እሷም እንደእሱ አደረገኝ..እራት በልተው አስኪያጠናቅቁ ሀያ ደቂቃ አካባቢ የፈጀባቸው ሲሆን በዛን ጊዜ ውስጥ ብዙም የረባ  ነገር እልተነጋገሩም…፡፡.እራቱ እንደተጠናቀቀ ዳጋላስ እጁን ሊታጠብ ቀድሞ ወደመታጠቢያ ክፍል ገባ …ወዲያው ከአስተናጋጆቹ አንዱ እቃ የሚያነሳሳ መስሎ ተጠጋት እና ጎንበስ ብሎ‹‹ነገ በዚህን ሰዓት››አላት፡፡፡አልገባትም‹‹ዋት››አለችው፡፡ደገመላት‹‹ነገ በዚህን ሰዓት..ተዘጋጁ››ብሎ የተበላበትን  ሰሀን ሰበሰበና እንዳቀረቀረ ከሳሎን ወጥቶ ሄደ፡፡
👍817👎2🥰1👏1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰለሞንና የበፀሎት ቤተሰቦችን አብዛኛውን ጊዜያቸውን አካባቢውን ያለውን እያንዳንዱን መስህብ በመጎብኘት ነው የሚያሳልፉት….እያንዳንዱ ውይይትና ምክረ-ሀሳብም በመዝናናት ውስጥ ሆነው የሆነ ቦታ አረፍ ሲሉ ወይም ቡና ለመጠጣት የሆነ ካፌ ሲቀመጡ በውይይትና በጫወታ መልክ የሚሰጥ ስለሆነ እንደ ቢሾፍቱ አስጨናቂና ጭንቅላት የሚይዝ አይነት አልነበረም፡፡

በወንጪ ኢኮ ቱሪዝማ ማዕከል ውስጥ ከሚገኙት እና ለጉብኝት ዝግጁ ከሆኑት ዋና ዋና አይን ሳቢና ቀልብ አስደንጋጭ የቱሪስት መስህቦች ውስጥ ጥቂቶቹ
ጎሮ በሚባለው ስፍራ የተገነባው ጎሮ ካልቸራል ሴንተር የወንጪ ኢኮቱሪዘም ፓርክ አንዱ መገለጫና ውበት ነው፡፡ በህንፃው ላይ ባህላዊ ምግቦች የሚገኙበት ውብ የሆነ ሬስቶራንት..ባህላዊ የሆኑ የእጅ ስራ ውጤቶች የሚሸጥባቸው ሱቆች…የተለያዩ ዝግጅቶችን ለማዘጋጀት የሚያገለግል እስከ 3መቶ ሰዎች ማስተናገድ የሚችል ውብ የሆነ አምፊ ትያትር ከአካባቢው ከሚገኙ አገልግሎቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እና አካባቢው ላይ ሆኖ ቁልቁል ወደታች ሀይቁንና ከማዶው ያለውን ተራራ ሲያዩት ልብን ስውር የሚያደርግ የተለየ አይነት አስደማሚ እይታ አለው፡፡

ከጎሮ 2.3 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ነዲ ካልቸራል ሴንተር ደግሞ ሌላው ልብ ሰዋሪ ቦታ ነው፡፡ነዲ ከስሙም መረዳት እንደሚቻለው በአካባቢው የሚመረት የወንጪ ማር እና የማር ውጤቶች እንደብርዝና ጠጅን ጨምሮ መሸጫ እንዲሆን ታስቦ የተገነባ ህንጻ ነው…የህንፃው ጠቅላላ ዲዛይን አገልግሎቱን ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ ስለሆነ ውብ ነው፡፡በማር እንጀራ ቅርፅ የተሰራ ሁለት ሶስት ጓደኛሞች ተቀምጠው ቁልቁል ሚታየውን ውብ እይታ ዘና እያሉ ወሬያቸውን የሚጠረቁበት ውብ ስፍራ አለ፡፡

ሙለታ ወንጪ ሬስቶራንት ሌላው በስፍራው የሚገኝ ውብ ቦታ ነው …በዚህ ስፍራ ሬስቶራንቶችና ሱቆች የፈረስ ማስዋቢያና ባህላዊ እቃዎች የሚሸጡበት ሱቆች ሲኖሩ ኩኪስ ብስኩት የመሳሰሉትም ቀላል ምግቦችን ማግኘት ይቻላል ፡፡
ነዲ ሰስፔንድድ የመስታወት ቴራስ ሌላው በአካባቢው ያለ ውብ ህንፃ ነው፡፡ይህ የመስታወት ወለል ግማሽ ክብ አይነት ቅርፅ ሲኖረው በሶስት ድርብርብ ተደርጎ የተሰራና እላዩ ላይ ወጥታው በመስታወቱ አሻግረው ወደታች ሲመለከቱ ከስር የሚታየው አስፈሪ ገደል መሳይ ግን በአረንጓዴ ሳርና ተክሎች የተሸፈና ውብ ስፍራ በማዶ የሚገኘው የጠራ ሀይቅ …በቃ አስፈሪ ግን ደግሞ አስደሳች እይታ ነው፡፡ይህ የመስታወት ቴራስ በአንድ ካሬ ሜትር ላይ 400 ኪ.ግራማ የመሸከም አቅም እንዳለው ቢታወቅም በርከት ያለ ሰው ከወጣበት ግን ከአሁን አሁን መስታወቱ ተፈርክሶ ሾልከን ወደገደሉ ብንንከባለልስ? የሚል የፍራቻ ስሜት ሰቅዞ የሚያሲዝ አይነት ነው፡፡ከዚህ አስደማሚ የመስታወት ቴራስ ጎን አምፊትያትር ያለ ሲሆን በተያያዥነትም…ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚሰጥ ካፍቴሪያ አለ፡፡ከዚህ ስፍራ ቀጥታ ወደሎጅ የሚወስድ የመኪና መንገድ ከላይ የመስታወት ቴራሱ ላይ ሆነው ከስር ማየት ይቻላል፡፡
ከዛ ደግሞ የተፈጥሮ ፍል ውሀ ያለበት በደን የተሸፈነ ሲሆን በአካባቢው ጉሬዛ ፤ጦጣ አእዋፍት ፤አምቦ ውሀ የተፈጥሮ ፏፏቴ ይገኛል …ጎን ለጎን ያሉ ሙቅና ቀዝቃዛ ኩሬ የኬብል ድልድይ ፤ወንዝ ..ብዙ ብዙ አስደማሚ ተፈጥሯዊ ነገር ይገኛል፡፡የነዲ መዝነኛ ስፍራን እና የተፈጥሮ ፍል ውሀን የሚያገናኝ በብረት የተሰራ እስካይ ብሪጅ አለ፡፡ብሪጁ 72 ሜትር ርዝመትና ኖሮት ሀምሳ ሜትር ከፍታ እንዲኖረው ተደርጎ የተሰራ አስፈሪ ግን ደግሞ የራሱ የሆነ ውበትና የተለየ ስሜት የሚያጭር ልዩ ድልድይ ነው፡፡
እነዚህን ሁሉ ባለፈው አንድ ሰምንት ውስጥ የጎበኞቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ በስምንተኛው ቀን ከቀኑ 9ሰዓት አካባቢ ለበፀሎት ደወለላት
‹‹ሄሎ..እንዴት ነሽ?››
‹‹አለሁልህ…ገነት ገብቼለሁ››
‹‹ወደድሽው ማለት ነው››

‹‹እንዴ ትቀልዳለህ እንዴ …?አካባቢው እኮ እንኳን እንደእኔ አፍጥጠው የሚያዩ ሁለት አይኖች ላሉት ሰው ይቅርና አይነ-ስውር ቢመጣበት እንኳን ውበቱ በሽታ ሳይቀር ይታወቀዋል፡፡››
‹‹ዋው ድንቅ አገላለፅ ነው….በጣም ማርኮሻል ማለት ነው…እኔንም አንድ ቀን ወስደሽ እንደምታስጎበኚኝ ትስፋ አለኝ፡፡››
‹‹በደንብ እንጂ…ለዛውም በቅርብ ነዋ››
‹‹አሁን የት ነሽ…?ላለፉት አንድ ሰዓት ለሊሴ ጋር በሳይክል አካባቢውን ስናካልል ነበር.. አሁን ድክም ብለን ነዲ ካልቸራል ሴንተር የሚባለው ስፍራ ላይ ነን ፡፡
‹‹ምነው…ጠጅ እየጠጣችሁ ነው እንዴ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ ትኩስ ወለላ ማር እየበላን››
‹‹በቃ ..ሰዓታችሁን አልውሰድባችሁ…..ዘና በሉ››
‹‹እሺ ቸው…ለሊሴ ሀይ እያለችህ ነው፡፡››
‹‹ሀይ በይልኝ‹‹ስልኩ ተዘጋ፡፡
‹‹አንቺ ሀለቃዬን ምን ልታደርጊው ነው?››ለሊሴ በመገረም ውስጥ ሆና ጠየቀቻት፡፡
‹‹ምን አደረኩብሽ…?››
‹‹እንዴ እያየሁ…ከተዋወቃችሁ ገና ሳምንት ነው..ግን ይሄውና በየቀኑ ይደውልልሻል፣ ገባሽለት እንዴ?››
‹‹አረ አንቺ ደግሞ…››በፀሎት እንደማፈር ብላ ተሸኮረመመች፡፡
‹‹ምነው..ቢሆን ደስ ይለኛል..ምርጥ ሸበላና የተማረ ሰው ነው..በዛ ላይ ትህትና አለው…እና አንቺን እህቴን ብድርለት በጣም ደስ ይለኛል››
‹‹በይ አንቺ ካዳመጡሽ …ብዙ ታወሪያለሽ››

ለደቂቃዎች ሁለቱም ዝም ተባባሉና በየግላቸው ሀሳብ መብሰልሰል ጀመሩ፣…በፀሎት ድንገት‹‹አካባቢው ግን አያስደንቅም?››ብላ አዲስ የመወያያ ርዕስ ከፈተች፡፡
‹‹ በጣም እንጂ…እያንዳንዱ ስፍራ የራሱ የሆነ እይታ አለው…አሁን ጎሮ ጋር ሆነሽ ቁልቁል ስታይ የተለየ አይነት እይታ..ከሊበን ሆነሽ ስታይው ደግሞ የተለየ አይነት እንደምታይው እዚህ ሆነሽ ስትመለከቾ ደግሞ ሌለ አይነት…በእውነት ይሄ በጣም አስገራሚ ነው፡፡ቦታ በቀየርሽ ቁጥር የምታይውም ነገር ይቀየራል…››
‹‹አዎ እንግዲህ …አምላክ ሲጠበብ ወሰን የለውም….››
‹‹እውነት ነው አምላክ ሲጠበብ ወሰን የለውም››የሚል ጣልቃ ገብ ዓ.ነገር  ሁለቱንም ከተቀመጡበት በርግገው እንዲነሱ አደረጋቸው፡፡ሌላ ሰው ነበር ከጀርባቸው የተናገረው፡፡
‹‹አንተ….እንዴት?››
‹‹ያው እንደዚህ››አለና ሁለቱንም በየተራ ሰላም አላቸው፡፡ተያይዘው ተቀመጡ፡፡
‹‹እዚህ ሆነህ ነበር እንዴ የምትደውልልኝ…?››በፀሎት በገረሜታና ባለማመን ጠየቀችው፡፡
‹‹አዎ…››
‹‹እኔ ደግሞ ምን አይነት ሞኝ ነኝ ..የት ነሽ ስትለኝ ያለሁበትን በየዋህነት መዘርዘሬ››
‹‹ምነው ስለመጣው ከፋሽ እንዴ?››
‹‹አረ በፍፅም››
የሰለሞንንና የበፀሎትን የማያቆርጥ ጥያቄና መልስ በዝምታ እየታዘበች በውስጦ እነዚህ ሰዎች ምንድነው እንዲህ ያቀራረባቸው..?ሰውዬውስ እሷን ፍለጋነው እንዴ እዚህ የመጣው
?እያለች በውስጦ ተብሰለሰለች ፡፡ልክ ልቧን እንዳነበበ ለጥያቄዎቾ መልስ ይሰጣት ጀመር…‹‹ያው ባለፀጋዎቹ ደንበኞቼ እዚህ ካልመጣን ሲሉ ተከትያቸው መጠሁ..ያው አስገድደው ሲያስደስቱኝ ምን ላድርግ..እየመጣሁ ሳለሁ ደግሞ እናንተ እዚህ እንዳላችሁ ትዝ ሲለኝ..የበለጠ ዘና አልኩ››
‹‹እና ታዲያ ሰዎችህ የታሉ?››በፀሎት ከወላጆቾ ጋር ድንገት ፊት ለፊት የመፋጠጥ ስጋት አስጨንቋት ጠየቀች

‹‹አሁን ክፍላቸው አረፍ ብለዋል….ለሚቀጥሉት ሁለት ሶስት ሰዓት እረፍት ነኝ….›› በፀሎት‹‹እና ታዲያ ወደፍል ውሀ ለምን አንሄድም?››የሚል ሀሳብ አቀረበች፡፡
👍6914
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


===============

በሶስተኛው ቀን አለማየሁና ሰሎሜ  ተደዋውለው  ተገናኙ፡፡ማታ አስራሁለት ሰዓት አካባቢ ሆቴል ነው የተገናኙት…ዝንጥ ብላ ነው የመጣችው፡፡በሞቀና በጋለ ሰላምታ ተቀበላት ፡፡ምግብ አዘው በልተው መጠጥ እየተጎነጩ ወሬ ጀመሩ ፡፡
‹‹እሺ እንዴት ነሽ..?ነገሮች እንዴት እየሄዱ ነው?››ሲል ለጫወታ መጀመሪያ የሚሆን አ.ነገር ሰነዘረ፡፡
‹‹ቆይ እስኪ የእኔ ጉዳይ ይቆይ…ለመሆኑ አንተ እንዴት ነህ?››መልሳ ጠየቀችው፡፡
‹‹ማለት..እኔ ደግሞ ምን እሆናለሁ?››ሲል መለሰላት፡፡
‹‹ማለቴ በቀደም ሳልጠይቅህ ….አገባህ እንዴ?››
‹‹አረ..በፍጽም፣ባገባ ኖሮ ቢያንስ ለእቴቴ ነግራት ነበር..ለእሷ ከነገርኩ ደግሞ ያው ልጇ ስለሆንሽ አትደብቅሽም ነበር፡፡››
‹‹አውቄዋለሁ….!!››
‹‹እንዴት .?ምኑን ነው ያወቅሽው?››
‹‹አንተ በቀላሉ የምትጨበጥ ወንድ አይደለህማ..አንድ ሴት አንተን አሳምና ወደ ጋብቻ ለመውሰድ በጣም ነው የሚከባዳት፡፡እርግጠኛ ነኝ ለማንም ሴት ከባድ ነው የሚሆንባት ፡፡››
‹‹እንዴ ያን ያህል አስቸጋሪ ሰው ነኝ እንዴ?››እሱን በተመለከተ በሰጠችው  አስተያየት የእውነት ገርሞት  ነው የጠየቃት ፡፡
‹‹አዎ እኔ እስከማውቅህ ድረስ፣ሀሳብህና ፍላጎትህ በደቂቃ ውስጥ  ነበር የሚቀያየረው…መቀሌም  ሞያሌም በአንድ ጊዜ መገኘት የምትፈልግ ለመረዳት አስቸጋሪ አይነት ሰው ነህ፡፡ማለቴ ነበርክ..አላውቅም ምን አልባት ባለፉት አምስት.. ስድሰት አመታት ተቀይረህ ሊሆን ይችላል..እኔ የማውቀው አሌክስ  ግን እንደዛ ነበር፡፡››
‹‹በእውነትን እንደዛ አይነት ሰው መሆኔን አላውቅም ነበር፡፡ደግሞም አንድ እህት ወንድሟን በተመለከተ ይሄንን የመሰለ አስተያየት መስጠት ያልተለመደ አይነት ነው፡፡፡››
‹‹እንዴት  ..ትክክለኛ ባህሪህን እኮ እየነገርኩህ ነው፡፡ለምሳሌ አስራሁለተኛ ክፍል ጨርሰን ማትሪክ እንደወሰድን  አብረን ተማክረን  ተግባረእድ ተመዝግበን  ነበር፡፡ትምህርት ሲጀመር ግን ብን ብለህ ቤቱንም ከተማውንም ለቀህ ጠፋህ .ፖሊስ  ለመሆን ተመዝግበህ  ማሰልጠኛ መግባትህን እንኳን ለእኔ መንገር አልፈለክም..ከእናቴ ነበር የሰማሁት፡፡ሁል ጊዜ የሆነ ነገር አብረን እናቅዳለን..ትግበራው ላይ ግን ድንገት ታፈነግጣለህ፡፡በዚህ በዚህ ሁሴንና አላዛር ካንተ በጣም የተሻሉ ናቸው፡፡እነሱ በቃላቸው ይፀናሉ…በተለይ አላዛር››
‹‹ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ..ለገዛ ባልሽ እያደለሽ ነው..?ለመሆኑ ሁሴን አሁን የት ነው ያለው?››
‹‹ያው ከመሀካላችን የተሻለ ጭንቅላት ያለው እሱ ነበር ፡፡አሁን  እንግሊዝ ሀገር የህክምና ዶክተር ሆኖ እየሰራ ነው…ግን በቅርብ ሳይመጣ አይቀርም፡፡››
‹‹አዎ ውጭ መሄዱንማ ሰምቼለሁ….ለማለት የፈለኩት ትደዋወላላችሁ ወይ ለማለት ነው?››
‹‹ከአላዛር ጋር እስክንጋባ ድረስ እንደዋወል ነበር፡፡ከዛ በኃላ ግን  ደውሎልኝ አያውቅም፡፡.እኔም አንድ ሁለቴ ልደውልለት ሞክሬ ነበር ስልኩን ቀይሮታል መሰለኝ አልሰራ አለኝ፡፡››
‹‹ተበሳጭቶብሽ ነዋ?››
‹‹ምን ያበሳጨዋል?››
‹‹በጣም  ያፈቅርሽ ነበር እኮ…!!››
‹‹ያፈቅርሽ ነበር ወይስ ይወድሽ ነበር?››
‹አንቺ ደግሞ …ሶስታችንም ነበር የምናፈቅርሽ..ይሄንን ደግሞ አንቺም በደንብ ታውቂያለሽ፡፡›.
የመደንገጥና ግራ የመጋባት ስሜት በፊቷ ላይ ተንፀባረቀባት ‹‹ምን እያልከኝ ነው…? እየቀለድክ ነው አይደል?››
‹‹አንቺ ነሽ እንጂ እየቀለድሽ ያለሽው…፡፡ ሶስታችንም ገና ማፍቀር እራሱ ምን እንደሆነ ሳናውቅ በፊት እናፈቅርሽ ነበር፡፡እድሜያችን በሙሉ ማነው በይበልጥ ሚያፈቅራት እያልን ስንፎካከለርብሽ  ነው ያሳለፍነው፡፡››
‹‹እኔ ትምህርት ጨርሰን እስክንበታተን ድረስ አራታችንም እርስ በርስ የምንዋደድ የልብ ጓደኛሞች እንደሆን ብቻ ነበር የማውቀው፣በተለይ አንተ ወንድሜም ጭምር ስለነበርክ  በዚህ መልኩ ላስብህ አልችልም፡፡ ››
‹‹ይሄን አላዛር እስከአሁን እንዴት ሳይነግርሽ…?ለነገሩ ምን ብሎ ይነግርሻል፤ አውቀሽ እሱ እንዳይከፋ በማሰብ ያላወቅሽ መስለሽ እንደምታስመስይ ነው የሚያስበው፡፡››
‹‹እሺ የሁሴንስ ይሁን ..አንተ የእውነት ታፈቅረኝ ነበር?››
‹‹ለዛውም ልክ በሌለው መጠን ነዋ….ለአንቺ ስል የማላደርገው ምን አለ..ቢያንስ የሞዴሱ ታሪክ ትዝ አይልሽም?››
‹‹አንተ ..ደግሞ ታስታውሰኛለህ እንዴ?ስንት አመት ሙሉ አንተ ምትገዛልኝ እየመሰለኝ አንጀቴን ስትበላው ኖረህ…አለችና በሳቅ ፈረሰች..እሱም ተከተላት፡፡
ሁለቱም በምናባቸው ወደኃላ ተጓዙና ትካዜ ውስጥ ገቡ
ሰሎሜ የወር አበባዋ የመጣው በ14 አመቷ ነበር፡፡ያንን ደግሞ ከግሩፑ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቀው አለማየሁ ነበር፡፡የዛም ምክንያት ከሰሎሜ ጋር አንድ ቤት በመኖራቸው ነው፡፡ወር በመጣ ቁጥር ግን ለሞዴስ የሚሆን ብር እናትዬውን መጠየቅ እያሳቀቃት ስትበሳጭ ይሰማና ..ይሄንን ችግር የሚፈታበትን ዘዴ ማሰላሰል ይጀምራል፡፡
ከዛ ፡አላዛር በዛን ጊዜ   ከትምህር ሰዓት ውጭ የሱቅ ስራ ይሰራ ስለነበረ ወደእዛው ነው የሄደው፡፡
‹‹እሺ ቱጃሩ እንዴት ነህ?››
‹‹ያሄው እንደምታየው ነው....ምነው ብቻህን?››
‹‹ማለት?››
‹‹ሰሎሜን ወይም ሁሴንን አስከትለህ ይምትመጣ መስሎኝ ነበር፡፡››
ከሁለቱን ማንን ይዤ ብመጣ ነበር የምትደሰተው?››ሲል መልሱን እያወቀው ጠየቀው፡፡
‹‹ምን ለማለት ነው…?ሁለቱም ጓደኞቼ ናቸው …ለምን መርጣለሁ?››
‹‹ተው እንጂ …አታስመስል፡፡››
‹‹አንተ ደግሞ…!››ብሎት ዝም አለ
‹‹ቆይ ..ሞዴስ አለህ እንዴ?››
አላዛር ደንግጦ‹‹የምን ሞዴስ?››ሲል ነበር መልሶ የጠየቀው፡፡
‹‹ሞዴስ ነዋ ..ሴቶች የወርአበባ ሲመጣባቸው ሚጠቀሙበት፡፡››ሲል ብራራለት፡፡
‹‹የለኝም፡፡››
‹‹ለምን አታመጣም..ሴቶች አይጠይቁህም?››
‹‹እሱማ አልፎ አልፎ ይጠይቁኛል፡፡››
‹‹እና ለምን አታመጣም?››
‹‹እንዲሁ…ብዙም አስቤበት አላውቅም…ግን አልገባኝም. .እንዴት ልትጠይቀኝ ቻልክ?፡››
‹‹አይ ሰሎሜ እኮ አላዛር ሞዴስ የሚሸጥ ቢሆን እኮ በየወሩ አንድአንድ ይሰጠኝ ነበር…በየወሩ እቴቴን አላስቸግርም ነበር ስትል ሰምቼት ነው፡፡››
በመደነቅ‹‹በእውነት እንደዛ አለች…?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹አዎ ብላለች››ሲል  ነበር ፍርጥም ብሎ የዋሸው፡፡
‹‹ግን የወር አበባ ታያለች ማለት ነው?››
‹‹እንዴ ለምን አታይም ሴት አይደለች?››
‹‹ማለቴ ገና ልጅ ነች ብዬ እኮ ነው፡፡››
‹‹ምነው አንተ መርጨት አልጀመርክም እንዴ?››
‹‹አንተ ደግሞ ታበዛዋለህ፡፡››
‹‹እንደውም ቆየች ..ባይሎጂ ላይ አልተማርክም እንዴ ..?አንድ ሴት እኮ ከ12 ዓመቷ ጀምሮ የወርአበባ ልታይ ትችላለች፡፡››
‹‹እሱማ አውቃለሁ…በቃ አሁን አደገች ማለት ነው?››
‹‹አዎ ..በደንብ እያደገችልን ነው፡፡››
‹‹በቃ…ከነገ ጀምሮ አመጣለሁ፡፡››
‹‹ጥሩ ..ለዚህ ወር ተገዝቶላታል..ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ትሰጣታለህ፡፡››
‹‹አዎ..ምንም አታስቢ በላት፡፡››
‹‹እሺ እላታለሁ..የወር አበባዋ የሚመጣው በ22 ወይም በ23 አካባቢ ነው…ስለዚህ በ20 በ20 እየመጣሁ ወስድላታለሁ፡፡››
‹‹ችግር የለውም..ግን እራሷ መጥታ ለምን አትወስድም፡፡››
👍458