አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የተገላቢጦሽ

እኔ ጎመን ቀቃይ
እቴ ቅቤ አንጣሪ
ምች ምን አግብቶት....
የሆነ አቃጣሪ፣
ወደ'ሷ አደላና....
አጠናግሮ ጣለኝ፣
ላም ባልዋለበት....
ኩበት ሊያስለቅመኝ!!

🔘ሀብታሙ ወዳጅ🔘
😁2
#የተገላቢጦሽ

እህሉን ስናገኝ
ወፍጫችን ደነዘ፣
አልፈጭልን ብሎ
ለግሞ እየፈዘዘ፣
ሌላ ግዜ ደግሞ
አጣንለት መላ፣
እህሉን ስናጣ
ወፍጮው እየሰላ !!

🔘ሀብታሙ ወዳጅ🔘