#አንድነት_ማለት
አንድ እንሁን አለኝ አንድ መሆን ቢሻ
ባንዲራውን ስጠኝ እንድሆን ሀበሻ፤
እኔም መለስኩለት ነገርኩት ስጋቴን
ካሰኘህ ውህደት መርጠህ አንድነቱን
ቋንቋዬን ተምረህ ባህሌን አክብረህ
ችግሬን ተጋርተህ እኔነቴን ወደህ
ፍትህ እኩልነት ስላም የበዛ ለት
ያስብከው ይሆናል የእውነት ውህደት!
እናም ወዳጄ...
ስለውህደት ማውራት ሁ ሉ ም ተክኖታል
ከአንገት በላይ ፍቅር ምን ይሰራልናል?
ገና ብዙ መንገድ ብዙ. ይቀረናል....!
ስለዚህ...
ልባችን ተቋስሎ እኛ ሳንዋደድ
በፍቅር መንገድ ላይ ተሳስበን ሳንሄድ
መሬት ቢቀላቀል ከንቱ ነው መዋሃድ፡፡
አንድ እንሁን አለኝ አንድ መሆን ቢሻ
ባንዲራውን ስጠኝ እንድሆን ሀበሻ፤
እኔም መለስኩለት ነገርኩት ስጋቴን
ካሰኘህ ውህደት መርጠህ አንድነቱን
ቋንቋዬን ተምረህ ባህሌን አክብረህ
ችግሬን ተጋርተህ እኔነቴን ወደህ
ፍትህ እኩልነት ስላም የበዛ ለት
ያስብከው ይሆናል የእውነት ውህደት!
እናም ወዳጄ...
ስለውህደት ማውራት ሁ ሉ ም ተክኖታል
ከአንገት በላይ ፍቅር ምን ይሰራልናል?
ገና ብዙ መንገድ ብዙ. ይቀረናል....!
ስለዚህ...
ልባችን ተቋስሎ እኛ ሳንዋደድ
በፍቅር መንገድ ላይ ተሳስበን ሳንሄድ
መሬት ቢቀላቀል ከንቱ ነው መዋሃድ፡፡
#አንድነት_ማለት
አንድ አካል ማለት
አንድ አምሳል ማለት
እንደ ጎፈርና ሰው ..
ከማርትሬዛ አካል ተጣብቀው እንዳሉት
በድንን መጋራት
አይደለም አንድነት
አንድ አካል ማለት
አንድ አምሳል ማለት
እንደ ሃገሬ ተክል እንደ አክሱም ሃውልት
አካልን ለማቅረብ ለመጓዝ ቢያቅት
በአይን ውሃ ተያይቶ ካለ መግባባት
ይህ ነው አንድነት፡፡
አንድ አካል ማለት
አንድ አምሳል ማለት
እንደ ጎፈርና ሰው ..
ከማርትሬዛ አካል ተጣብቀው እንዳሉት
በድንን መጋራት
አይደለም አንድነት
አንድ አካል ማለት
አንድ አምሳል ማለት
እንደ ሃገሬ ተክል እንደ አክሱም ሃውልት
አካልን ለማቅረብ ለመጓዝ ቢያቅት
በአይን ውሃ ተያይቶ ካለ መግባባት
ይህ ነው አንድነት፡፡