#በእቅፍሽ_ውስጥ_ያለው_ሰላም
በደጃፌ
ያዱኛ ጅረት ይፈስሳል
ሲዘረጋ መዳፌ
አልማዝ አፍሶ ይመለሳል።
ድህነትን አልቀድስም፣ ሀብታም መሆን አልጠላም
ግና ገንዘብ ኪስን እንጂ፣ የልብን ክፍተት አይሞላም
ከሁሉም ግን የሚልቀው፣ እቅፍሽ ውስጥ ያለው ሰላም።
በጉልምስና ዘመኔ፣ ወደ ልጅነት ተዛውሬ
የወይን ፅዋየን ወርውሬ
እልፍ ጡቶችን ብጠባ
ካንዲት ሽንቁር ተመዝዤ፣ ሌላይቱ ውስጥ ብገባ
ብለዋውጥ ማህደር
ብቀያይር ሰገባ
ምን አገኘሁ? ምን አተረፍሁ? ምን ፈየድኩኝ? ምኔ ረባ?
ሥጋ በሥጋ ቢሞረድ፣ የደነዘ ነፍስ አይሰላም
ከሁሉም ግን የሚልቀው፣ እቅፍሽ ውስጥ ያለው ሰላም።
🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
በደጃፌ
ያዱኛ ጅረት ይፈስሳል
ሲዘረጋ መዳፌ
አልማዝ አፍሶ ይመለሳል።
ድህነትን አልቀድስም፣ ሀብታም መሆን አልጠላም
ግና ገንዘብ ኪስን እንጂ፣ የልብን ክፍተት አይሞላም
ከሁሉም ግን የሚልቀው፣ እቅፍሽ ውስጥ ያለው ሰላም።
በጉልምስና ዘመኔ፣ ወደ ልጅነት ተዛውሬ
የወይን ፅዋየን ወርውሬ
እልፍ ጡቶችን ብጠባ
ካንዲት ሽንቁር ተመዝዤ፣ ሌላይቱ ውስጥ ብገባ
ብለዋውጥ ማህደር
ብቀያይር ሰገባ
ምን አገኘሁ? ምን አተረፍሁ? ምን ፈየድኩኝ? ምኔ ረባ?
ሥጋ በሥጋ ቢሞረድ፣ የደነዘ ነፍስ አይሰላም
ከሁሉም ግን የሚልቀው፣ እቅፍሽ ውስጥ ያለው ሰላም።
🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
👍2