#ሚሊዮን_ፀሐዮች_ሚሊዮን_ጨለሞች
ጨረቃ ብቅ አለት፣ ፀሐይ ስትከስም
ያው እንደ ወትሮ ነው
የምሽት የንጋት፣ ፈረቃው አይፈርስም!
የኔ ግን ይለያል
ልቦናየ ቢማስ
ሚሊዮን ፀሐዮች፣ ሚሊዮን ጨለሞች!
ሺ ሰማይ፣ ሺህ አድማስ
ተገልጦ ይታያል።
ስንቴ በጽልመቴ፣ ዙርያየን አዳፈንሁ
ስንቴ በጨረሬ፣ የምድርን ዐይን ወጋሁ
ባንድ ቀን ውስጥ ብቻ
ስንት ጊዜ መሽቼ፣ ስንት ጊዜ ነጋሁ!
ጨረቃ ብቅ አለት፣ ፀሐይ ስትከስም
ያው እንደ ወትሮ ነው
የምሽት የንጋት፣ ፈረቃው አይፈርስም!
የኔ ግን ይለያል
ልቦናየ ቢማስ
ሚሊዮን ፀሐዮች፣ ሚሊዮን ጨለሞች!
ሺ ሰማይ፣ ሺህ አድማስ
ተገልጦ ይታያል።
ስንቴ በጽልመቴ፣ ዙርያየን አዳፈንሁ
ስንቴ በጨረሬ፣ የምድርን ዐይን ወጋሁ
ባንድ ቀን ውስጥ ብቻ
ስንት ጊዜ መሽቼ፣ ስንት ጊዜ ነጋሁ!