አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ባል_ተመኘሁ

አስተዳደጌ ነው የገደለኝ። አስተዳደጌ መጠበቅ እና ማግኘት ነበረበት። አባቴ ሁሌ ቃል ይገባልኛል፣ የሆነ ነገር በጥሩ መልኩ ሳደርግ ይሸልመኛል፣ እናቴ የቤት ሥራ ስሠራ ታመሰግነኛለች፣ ትመርቀኛለች። በምስጋና እና በስጦታ ተንበሽብሼ ነው ያደግኩት፤ ለዛ ነው የጠበቅኩትን ሳጣ የምታመመው ብዬ ሁላ አውቃለሁ፤ ግን በእሱ ብቻም አይደለም!

የማያቸው ሮማንቲክ ፊልሞች እና የማነባቸው መጻሕፍት ናቸው፤ ከፍቅር የሚገኘውን ደስታ እና ሁኔታ ከሚገባው በላይ አጋነው፣ ከቅዱስ የማገኘውን ነገር ሁሉ ያሳነሱብኝ ብዬም አምኜ አውቃለሁ።

ግን እሱ ብቻ አይደለም!

ቅዱስ ራሱ ነው ፍቅረኛሞች እያለን አባቴን መስሎ እና ሆኖ ተንከባክቦ ኑሮ ስንጀምር እርግፍ አድርጎ ትቶኝ የተፈላጊነት ስሜቴን የገደለው።

ኖ በእሱ ብቻም አይደለም!

ገመናዬን፣ ሚስጥሬን፣ ስሜቴን ለሰው ስለማልናገር ነው መፍትሔ ያጣሁት፤ የማይቀለኝ! የሚያብከነክነኝ!

ግን ዋናው ምክንያት ይሄም አይደለም!

ራሴን ከዋናው የሕመሜ ምክንያት፣ የድባቴዬን ምንጭ ለራሴ አልነግር ብዬ ነው።

ቅዱስ አይፈልገኝም። ሲመጣ ባዶ ቤት ቢቆየው ቅር አይለውም። ለስሜቴ ደንታ የለውም። ቆይ ስንት ወራቶች ሞላን ወሲብ እንኳን ከፈጸምን? አልጋ ከለየን ስንት ጊዜ ሆነን? ስንቴ ተዘገጃጅቼ ሊወጣ ሲል፣ ሲገባም ላነሳሳው በሚል አጋጣሚ አስመስዬ ራቁቴን የታየሁት፣ ቀስቃሽ አለባበስ ስንቴ ነው የለበስኩት?

እሱ ግን አያየኝም።

እንዲያዝንልኝ ታመምኩ፤ ኡኡ ነደድኩ፣ ጠዘጠዘኝ፣ ወጋኝ አልኩ፤ ታከሚ ይላል እንጂ አይደነግጥም። ወጣ ብሎ ስልክ ረጅም ሰዓት ያወራል።

መሀላችን ያለው ችግር ቀላል ነው ብዬ አስመሰልኩ... እውነቱ ግን እሱ አይወደኝም።

በመጨረሻ አልፈለግነት ሲጫወትብኝ፣ የድሮ ቦይፍሬንዴ ጋ ሄጄ ተልከሰከስኩ!

እሰይ!! እንኳን ተልከሰከስኩ።

ለሴት ልጅ የአለመፈለግነት ስሜት፣ ለዛውም በእንክብካቤ ላደገች፤ ለዛውም ተለማምጦ፣ ልዕልቴ ናት ብሎ ላገባት፣ ለዛውም መፈለግ እና መውደድ ለምታውቅ ሴት የሚሰማትን የሕመም ስሜት የት ያውቀዋል?!

የምን ጉዝጓዝ፣ ሰበብ፣ ድሪቶ፣ ዝባዝንኬ ነው?!

አለመፈለግ ብቻውን ቀላል ነው?!

ብቻውን ትዳርን መፍታት ብቻ አማራጭ አድርጎ ማሰብ ቀላል ነው?

ብቻውን ወሲብ ማድረግ መፈለግ እና ባል እያለ በፍትወት መቸንከር ቀላል ነው?

ብቻውን ላወራው እየፈለግኩ፣ ስደውልለት ሳያነሳልኝ ሲቀር አያከብረኝም፣ ከምንም አይቆጥረኝም ዓይነት ስሜትስ ቀላል ነው?!

ብቻውን እንዲህ እለዋለሁ ብዬ የሰበሰብኩትን ዓረፍተ ነገር፣ እንዲያዝንልኝ ያጠናሁትን ንግግር፣ እንዲታረቀኝ ያጠራቀምኩትን ቃላት፣ እንዲሳሳልኝ ያከማቸሁትን ሰበብ፣ እንዲረዳኝ የተዘጋጀሁበትን ቃል ፊት ነስቶ ሲያጠፋብኝ ስሜቱ ልብ አይሰብርም??!

ከድሮ ቦይፍሬንዴ ጋር ተንገብግበን፣ ተጠማጥመን ተዋሰብን። ቆንጆ ነኝ ወይ ስለው "ከድሮ በበለጠ” እያለኝ፤ ምኔን ትወድልኛለህ ስለው እያንዳንዱ አካሌን . እየሳመ እያሳየኝ። እየተዟዟርን፣ ቦታ እያማረጥን ተዋሰብን።

ደስስስ አለኝ!!

ለመለምኩ! እየጠወለግኩኝ ነበር።

ያደረግኩት ተግባር ለሌላው፣ ለመንገደኛው፣ ለመርሕ ሰው ሁሉ፣ ለጨዋው ሁሉ፣ ለአማኙ ሁሉ፣ ከዳር ሆኖ ላየኝ ሁሉ፣ ለፈራጅ ሁሉ፣ ለሌባው ሳይቀር ዝሙት ነው!.

ወሲብ ውስጥ ያለውን እፈልግሻለሁ፣ ታምሪያለሽ፣ እወድሻለሁ ሽንገላን መስማት ናፍቆኝ ነበር።

አመሰግንሃለሁ ብዬ አንገቱ ውስጥ ተወሽቄ ሳምኩት። ስለተኛኸኝ አመሰግናለሁ ይባላል? ትዳሬ ላይ ከባለግኩኝ በኋላ ማመስገን ነበረብኝ?

እኔ ግን አመሰገንኩት!

ተሰናብቼው ሳይመሽብኝ ወደ ቤቴ ፈጠን ፈጠን እያልኩ መሄድ ጀመርኩ፤ ቀስ እያልኩ ፍጥነቴን ቀነስኩ፤ እዛ ዱካክ፣ አልፈለግነት የሚበላኝ ቤት መሄድ ፈራሁ። የማይፈልገኝን ባሌን ማየት ሲዖልን የማየት ዓይነት ሆነብኝ፣ የማይናፍቀኝን፣ የማይንከባከበኝ ባሌ ያለበት ቤት መሄድ ጠላሁ፣ ወስልቼበት እንኳን ጸጸት ያልተሰማኝ ባሌ ጋ መሄድ አስጠላኝ።

ለመጀመርያ ጊዜ ልቤን ሰማሁት።

ከእኔ ካልሆነ ሰው ጋር እንድተኛ ያደረገኝ ሰውዬ ጋ ምን አደርጋለሁ??

መሳም እስክናፍቅ ድረስ የገፋኝን፣ መታቀፍን ብርቅ ያደረገብኝን፣ መወደድ እንደሚገባኝ ያሰረሳኝ ሰው ጋ ምን አደርጋለሁ?!

ምን አጠፋሁ? ይቅርታ ለማለት፣ ምን ላድርግልህ እንድለው ትንሽዬ እንኳን ፊት የማይሰጠኝ ሰው ጋ ለመኖር ለምን ወደኋላ ተመለስኩ።

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
38👍4😢1