#ውርስ_ሕይወት
አባቴ ለብዙ ዓመታት ታስሮ ነበር። አስራ አራት ዓመቴ አካባቢ ተፈታ፤ የተወለድኩት ያን ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል፤ አባቴ ሲፈታ እኔም ተፈታሁ። አባቴ አስራ አራት ዓመት ድረስ ሳስብ የነበረውን ቀስ እያደረገ ዳመጠው።
አባቴ የላላ፣ የተቆጠበ ማኅበራዊ ግንኙነት ያለው፣ ረጋ፣ ጀንተል፣ ኮስተር ያለ ግለሰብ ነው። ብዙ ሰዓት ዝም ይላል፤ የስሜት መለዋወጥ አይታይበትም፤ ጺሙ በብዙ ሲያድግ በመቀስ በትንሹ ይከረክመዋል፤ ልብሶቹ፣ የሚጠቀምባቸው እቃዎች ስትር ያሉ ናቸው።
ከእስር እንደተፈታ እኖር ከነበረበት ከእናቴ ቤተሰቦች ቤት ወስዶ ተከራይቶ ከነበረው ሰፊ ግቢ ውስጥ መኖር ጀመርን።
ቤታችን ቅዝቅዝ ያለ ነው። ቅዝቅዝ ያለው ብዙ ወንድም እና እህት ስለሌለን ነው ወይስ እናት ስለሌለኝ ነው፣ አልያም ደግሞ አባቴ ከሰው ጋ በደማቁ ስለማይግባባ፤ ምክንያቱን እርግጠኛ ባልሆንም ውጤቱ ግን ቀዝቃዛ ሰፊ ትልቅ ግቢ ውስጥ ነው የኖርነው።
መቀዝቀዙ የገባኝ፣ በየአገጣሚ የትምርት ቤት ጓደኞቼ ጋ ቤታቸው ስሄድ ይሳሳቃሉ፣ ይጨቃጨቃሉ፣ ይካሰሳሉ፤ በዚህም እቀና ነበር። እጦታችን ያወቅነው ዕለት ጉድለት ይሰማን የለ?!
ስሜ ዋሲሁን ቢሆንም አባቴ ዋሴ ነው የሚለኝ፤ ምንም ነገር ሲያስደርገኝ ሆነ ሳደርግ አምኜበት እንዲሆን አድርጎ ሠርቶኛል። ከፍቶኝ ለምቦጬን ከዘረገፍኩ "ዋሴ ማኩረፍ የአቅመቢስነት ማሳያ ነው፤ መጀመርያ የከፋህን፣ ቅር ያለህን በእርጋታ አስረዳ" እያለ የውይይት ባሕል ልቤ ውስጥ እያኖረ ነው ያሳደገኝ።ያምንብኛል። እንደመታመን አበርቺ እጽ እንደሌለ ያወቅኩት ለራሴ ያለኝ በጎ እና የእችላለሁ ወኔ ከብዙ አቻዎቼ መለየቱን እና ምንጩን ስረዳ እና ሲገባኝ ነው።
በጨዋታ መሀል
“ይሄውልህ ዋሴ ሁልጊዜ እሮሮ የሚዘበዝቡ፣ ሁልጊዜ ሰው ማጣጣል ላይ የተመሰጡ ሰዎች፣ ሁልጊዜም አልተሳካልን ዓይነት ደረት የሚመቱ፤ ለውድቀታቸው ሰው የሚወቅሱ ሰዎች፣ ለመውደቃቸው ኃላፊነት ከማይወስዱ ጋ አትወዳጅ" ይላል።
ይሄ ሰውዬ ጓደኛ የሌለው ለውድቀታቸው ኃላፊነት የሚወስዱ አጥቶ ይሆን እላለሁ አንዳንዴ።
ደግሞ በሌላ ቀን እጅግ ብዙ ቆይቶ
“ዋሴ" ይላል። ልገልጸው የማልችለው አጠራር አለው። ሁሉም ሰው ዋሴ ብሎ ቢጠራኝም በእሱ ዓይነት መንገድ የሚጠራኝ ሰው አልገጠመኝም። የሆነ አለኝታዬ ዋስትናዬ የሚለኝ ነው የሚመስለኝ፤ እወድሃለሁ የሚለኝ በአጠራሩ ውስጥ ባለው ድምጸት በኩል ነው።
"ይሄውልህ ዋሴ ሰው አንተ ላይ ስለሚይዘው . አቋም እንዳትጨነቅ፤ ሰው ለማስደሰት ከዳከርክ የራስህ እውነት ሳይኖርህ ታልፋለህ" ይላል።
አባቴ ጥንቅቅ ያለ ሰውዬ ነው፤ ነፍስ እያወቅኩ ስሄድ ነው ለእሱ ያለኝ ፍቅር እና አክብሮት ያየለው።
ብዙ ዝም ስለሚል ሲያወራ ተስገብግቤ ነው የምሰማው፤ እጦትን የመሰለ ነገሮችን ተፈላጊ አድራጊ ያለ አይመስለኝም እኮ::
"ይሄውልህ ዋሴ"
ወዬ አባቴ
“ስንት ዓመት መቀመቅ ያወረደኝ ሐቀኝነቴ ነው፤ ኃላፊነቴን በአግባቡ ለመወጣት ስዳክር፤ ብልሹ ካልኩት አሠራር ጋ ስታገል፣ መደለያቸውን በጄ ስላላልኩ መቀመቅ ውስጥ ወረወሩኝ።
ብቻዬን ቆምኩ!
በእርግጥ እኔ ቆምኩ ልበል እንጂ ለብዙ ሰው ወድቄያለሁ፤ የወደቀ ከሚለው ጋ ማበር የሚፈልግ ማን አለ? ወደቀ ብለው ተዘባበቱብኝ፤ ስንት ዓመት ለመኖር ነው ግን እንዲህ የከፉት እላለሁ፤ ስለ ተቻለ ብቻ አሳማም ጅብም እንዴት ይኮናል?!
ይኸውልህ ዋሴ
ለእራስህ እውነተኛን መሆን የመሰለ የሕሊና እረፍት የለም፤ ከራስ ጋ ሰላም ከመሆን በላይ ምን ሽልማት አለ? ወድቋል ብለው ሲዘባበቱ እኔ ያልሠራሁት መጥፎ ተግባር ምቹ ትራስ ሆኖኝ ከሰላሜ ጋ ነበርኩ።
አንተ እንዲህ የምትወደኝ እኮ፣ አንተ እንዲህ የጎበዝክልኝ'ኮ ለእውነቴ የተሰጠኝ ሽልማት ነው፤ በዚህ ዕድሜ ጤነኛ የሆንኩት እኮ አምላክ ለመታመኔ የሰጠኝ ስጦታ ነው፤ ሰው ሽልማት ጥሬ ገንዘብ ብቻ ይመስለዋል" ይል'ና በስሱ እንደሁሌው ጥርሱን ገለጥ አድርጎ ፈገግ ይላል፤ አሳሳቁ ሞገስ አለው!!
“እኔን ያሳቀሉኝ እኮ በእስተርጅና የሚመታቸው ልጅ፣ የማይወዳቸው ልጅ ኖሯቸዋል፤ ያመኑት ክዷቸዋል፡፡
“እግዚሃር በሚደግሱት ዝክር የሚሸወድ መስሏቸዋል" እያለ አፉን በትንሹ ከፍቶ ጥርሱን እያሳየኝ ፈገግ ይላል።
አባቴ የሚለኝን ሁሉ እየሆነ ያሳየኝ መምህሬ ነው።
“ይኸውልህ ዋሴ ጥቃቅን ነገር ላይ አታተኩር፤ የምትኖርለት መርሕ ይኑርህ፤ እመቀመቅ ድረስ የምትሄድለት ሕልም እና መርሕ ይኑርህ።"
የሚኖርን እውነት ከመስማት በላይ ምን ሐሴት አለ??
ብቻዬን መቆም አስተምሮኝ፣ ጥቂት ቀን ታሞ ጥቂት ቀን አስታምሜው አለፈ። ብዙ ቆይቼ እስር ቤት ሳለ የጻፋቸውን ሐሳቦችን እና ገጠመኞቹን ሳነብ ከዕድሜዬ በላይ አበሰለኝ።
ሕይወቴ ላይ የብስለቱ ዳና ያረፈብኝ የአባቴ ልጅ እኔ ዋሴ ነኝ!!!
🔘አድኀኖም ምትኩ🔘
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

❤48👏19