#ቅብጥብጡ_ውሻ
የት እንዳነበብኳት ባላስታውስም ከረጅም ጊዜ በፊት ያነበብኳት አንዲት አጭር ታሪክ ትዝ አለችኝ፡፡ አስተምራኝ አልፋለች፣ ዛሬም ባሰብኳት ቁጥር ታስተምረኛለች፡፡ የአንድ ሰውና የውሻው አጭር ታሪክ ነው፡፡
በገጠራማው አካባቢ የሚኖር አንድ ሰው ከቤቱ ወጥቶ ወደ 30 ደቂቃ የሚፈጅ የእግር ጉዞ ካደረገ በኋላ መድረስ ወደሚገባው የወዳጁ ቤት ደረሰ፡፡ ከእሱ ጋር እሱ በሄደበት ሁሉ የሚከተለው በጣም የሚወደው ውሻው እንደተለመደው ተከትሎት መጥቷል፡፡ ሰውየው ወዳጁ ቤት ሲደርስ ከወዳጁ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጡ በኋላ ወዳጁ፣ “ያ ሁልጊዜ በሄድክበት ሁሉ የሚከተልህ ውሻህስ የት አለ?” ብሎ ገና ከመጠየቁ ውሻው እያለከለከና በውኃ ጥም ለሃጩን እያዝረከረከ ከባለቤቱ ጀርባ ከተፍ አለ፡፡
የዚህ ሰው ወዳጅ የሰውየውን አለመድከም ከውሻው ማለክለክ ጋር አነጻጸረና፣ “ውሻህን ምን አድርገኸው ነው እንደዚህ የደከመው፡፡ አንተ ምንም የድካ ስሜት አይታይብህም፣ እሱ ግን በጣም ደክሟል” አለው፣ ልክ በውሻው ላይ እንደጨከነበትና ችላ እንዳለው አይነት ስሜት በሚሰጥ ሁኔታ፡፡
የውሻውም ባለቤት ይህ የለመደውና በሄደበት ሁሉ ሰዎች የሚጠይቁት ጥያቄ በመሆኑ ብዙም ሳይገረም በውስጡ አቀባብሎ ያለውን መልስ መለሰለት፣ “የሚገርምህ ነገር ሁለታችን ከቤት ተነስተን እኩል መንገድ ነው የመጣነው፡፡ በእኔና በእሱ መካከል ያለው ልዩነት እኔ ቀጥ ብዬና ተረጋግቼ ነው የመጣሁት፣ እሱ ግን አንዴ ወደ ግራ፣ አንዴ ደግሞ ወደ ቀኝ ሲባዝን፤ አንዴ አንድን ነገር ሲያባርር፣ እንዴ ደግሞ ቆም ብሎ መሬቱን እያሸተተ አንድን ነገር አገኛለሁ ብሎ ሲቆፍ፣ እኔ ስርቅበት ደግሞ ለመድረስ ሲሮጥ . . . ሁል ጊዜ እሱን የሚያደክመው ይህ ቅብጥብጥ ባህሪው ነው”፡፡
ለካ ያለመጠን የሚያደክመን መንገዳችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ የሚያዝለን ስራችን ብቻውን አይደለም፣ ለካ በቀኑ መጨረሻ ላይ ዝልፍልፍ የሚያደርገን የቀኑ ዋና ዓላማችን አይደለም፣ ለካ በኑሮ ድክም ያልነው በተለመደው የኑሮ ሂደት አይደለም፡፡ እኛን የሚያደክመንና ዝለት ውስጥ የሚከተን በመንገዳችን ላይ በማያገባን ነገር እየገባን ወዲህና ወዲያ የምንለው ነገር ነው፡፡
ይህ እውነት የገባኝ ቀን . . .
ስለማያገባኝ ሰው ማውራት አቆምኩኝ፣ በማያገባኝ ስፍራ መገኘት ተውኩኝ፣ ምንም ለውጥ በማያመጣ ነገር ላይ መከራከርን ጣልኩት፣ ምንም ተጽእኖ ከማላመጣለት ሰው ጋር መነታረክን ተወት አደረኩኝ፣ ድምዳሜ ላይ ስደርስ ምንም ፋይዳ የማያመጣልኝን ጉዳይ ማሰላሰል እርግፍ አደረኩኝ . . . በአጭሩ የማደርገው ነገር ሁሉ ከዋናው የህይወቴ ዓላማና እሴት ጋር የመጣጣሙን ጉዳይ ማሰብ መኖር ጀመርኩኝ፡፡
ይህንን ያደረኩኝ ጊዜ ብዙ ሸክም ከላዬ ላይ የተነሳ ያህል እርምጃዬ ቀለለኝ፣ ምክንያት-የለሹ የድካም ስሜት ተወኝ፣ የጀመርኩትን ግቤን ጥጉ የማድረስ ጉልበት አገኘሁኝ! ለካ እኔንም ልክ እንደ ቅብጥብጡ ውሻ ያደከመኝ ቀጥታው ሳይሆን ግራ-ቀኙ እና መለስ-ቀለሱ ነው!
🔘በዶ/ር እዮብ ማሞ🔘
ዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን እንጂ ትላንት
5 ሰው ብለን ማንም #ሰብስክራይብ አላደረገም እስከ ማታ 5 ሰው #እጠብቃለሁ
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

👍74❤5🥰4
ልጆቹን ከአባታቸው ጋር አገናኝቶ ለጊዜውም
ቢሆን እንዲሻላቸው ማድረግ፤በዘላቂነትም
መሆን ያለበትን ነገር ከአባትዬውም ሆነ
ከኤደን ጋር ተነጋግሮ ሁኔታዎችን ለማስተካከል
አቀደ፡፡..ቢያንስ የቅዳሜና የእሁድ የእረፍት ቀናቸውን አባታቸው ጋር ማሰለፍ እንዳለባቸውና ይሄንንም ማስተካከል የእሱ ኃላፊነት እንደሆነ ወሰነ፡፡
✨ይቀጥላል✨
አሁንም ዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን ቤተሰቦች
ሰብስክረይብ ያላደረጋችሁ በማድረግ ….ያደረጋችሁ ደግሞ ሌሎች እዲያደርጉ በማስተባበር ተባበሩኝ… አመሰግናለሁ፡፡

👍67❤8😢4
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሰባት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ሀዋሳ
ሁሴን ወደ ሲዩዘርላንድ ከበረረ ሀያ ቀን አልፎታል፡፡ያለፉትን ሀያ ቀናት የእሱንም ቦታ ተክታ ለስራው ከላይ እታች በመሯሯጥ ብታሳልፍም ከናፍቆት ግን ማምለጥ አልቻለችም፡፡አዎ ሁሴን ባልተለመደ መልኩ በጣም ናፍቋታል፡፡እራሷን በሌላ ሰው ህልውና ላይ ይሄን ያህል መለጠፍ አትፈልግም ነበር፤ምንም ቋሚና ዘላቂ ነገር እንደሌለ ህይወት ደጋግማ አስተምራታለች፡፡የእኔ የምትለው ነገር ሁሉ አንድ ቀን በሰላምም ሆነ በአደጋ ብቻ በሆነ ምክንያት እንደሚለያትና ለዛም ዝግጁ ሆና መጠበቅ እንዳለባት የዘወትር መፈክሯና መመሪያዋ ነበር፡፡አሁን ግን መልሳ ደከመች፤እናም ባሏ ናፈቃት፡፡እለቱ ሰንበት ስለሆነ የቤቷ ሳሎን ሶፋ ላይ ጋደም ብላ ቴሌቪዢን እየተመለከተች ነው፡፡
አይድል ፕሮግራም..በሀዋሳ የሚካሄድ የማጣሪያ ውድድር እየተመለከተች ነው፡፡
በአብረሀም ወልዴ የሚመራው የዳኞች ቡድን
የዳኝነት ቦታቸውን ይዘዋል፡፡ተወዳዳሪዎች በቅደም ተከተል ወደ መድረክ እየወጡ የተዘጋጁበትን ዘፈን በመዝፈን ተፈጥሮ
የቸረቻቸውን ድምጽና በጥረታቸው ያደበሩትን
ችሎታ በማዋሀድ ዳኞቹንም ሆነ ተመልካቾችን
በማሳመን ለአዲስአበባው ውድድር ለማለፍ ይጥራሉ፡፡ጥቂቶች ይሳካላቸዋል ፤ሌሎቹ ደግሞ አንገት ደፍተውና ፈዘው ከመድረኩ
ይሰናበታሉ፡፡ትንግርት ሁሌ ይህን ፕሮግራም ስታይ ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ነው የሚሰማት፡፡
ዘና የሚያደርገት እንዳለ ሁሉ የሚያሳዝኗትም
ተወዳዳሪዎች አሉ፡፡ከችሎታቸው በላይ
ጉጉታቸው የናረ፣ብዙ ተስፋ አድርገው መጥተው በዳኞቹ ቁርጥ ያለ ሞያዊ
አስተያየት ሽምቅቅ የሚሉ ወጣት ጨቅላዎች፤ ያሳዝኗታል፡፡ችሎታው እያላቸውም ፍራቻቸውን ብቻ ማሸነፍ ተስኗቸው ያላቸውን ነገር መግለጽ ባለመቻላቸው አጉል የሚሆኑም አሉ፤እነሱም ያሳዝኗታል፡፡
...አሁን ግን እያየች ያለቻው ድንቅና የሚያስደምም ችሎታ ነው፡፡አስር ሁለት አመት የማይበልጣቸው ሁለት ሴት ልጆች ናቸው የሚታዩት፡፡አንደኛዋ ጊታሯን ይዛ የተዘጋጀላት መቀመጫ ላይ ተቀመጠችና በጣቶቿ የጊታሩን ክሮች በመነካካት ፈታተሸች፤ሌለኛዋ ከፊት ለፊቷ በሜትሮች ርቀት ማይኩን ይዛ ::
አብረሀም ወልዴ መናገር ጀመረ....
‹‹እሺ እንኳን በሰላም መጣችሁ እያልኩ እራሳችሁን እንድታስተዋውቁ ዕድሉን ልስጣችሁ ፡፡››
‹‹ስሜ ሀሊማ ታዲዬስ ይባላል፡፡ የምጫወትላችሁ የተፈራ ካሳን ‹አባብዬ› የሚለውን ዘፈን ነው፡፡››
‹‹አሪፍ ነው፡፡ባለጊታሯስ ስምሽ ማነው ?››
‹‹ስሜ ሄለን ታዲዬስ ይባላል፤ጊታርና ፒያኖ ተጨዋች ነኝ።
<<እህት አማቾች ናችሁ ?››አረጋኸኝ መሀከል ገብቶ ጠየቀ፡፡
‹‹አዎ እህቴ ናት፡፡››
ይሄ ሁሉ ሲሆን ትንግርት ስትከታተል የነበረው በግማሽ ልቧ ነበር፡፡እህትማማቾች ነን ሲሉ ግን ትንሽ ግር አላት፡፡በእኩል ዕድሜ ላይ ናቸው፡፡የትኛዋ ታላቅ የትኛዋ ደግሞ ታናሽ ትሆን? ስትል እራሷን ጥያቄ ጠየቀች፡፡ ደግሞ ምናቸውም አይመሳሰልም <<የእናት ሆድ ዥንጉርጉር›› ይባል የለ ብላ ለራሷ መልስ ሰጠች፡፡
‹‹በሉ ቀጥሉ..መልካም ዕድል፡፡››ከዳኞቹ ፍቃድ አገኙ፡፡
ሄለን እነዛ ቀጫጭንና ለጋ ጣቶቾን የጊታሩ ክሮች ላይ ማርመስመስ ጀመረች ፡፡ የሙዚቃ መሳሪያውን ምት ተከትሎ የሀሊማ ተስረቅራቂና ማራኪ ድምጽ ይንቆረቆር ጀመር፡፡ በአዳራሹ የሞላው ተመልካች ብቻ ሳይሆን በየቤቱ በቲቪ ፕሮግራሙን የሚከታተለው ህዝብም ፀጥ የሚያሰኝ አደንዛዥ ድምጽ ነበር፡፡በዚህ ዕድሜ በእንዲህ አይነት ችሎታ? እንዴት ነው በዚህ ዕድሜ የሙዚቃ መሳሪያን ስልተ-ምት ጠብቆ ስይደናገሩና ሳይንሸራተቱ በዚህ ልክ መዝፈን የቻሉት?፡፡
ዳኞቹ ሳይቀር አፋቸውን ከፈቱ፡፡ደግሞ በሙዚቃው ሁለቱም ጉንጮች ላይ እንባ እየተንጠባጠበ ነው፡፡ሲጨርሱ የአዳራሹ ሰው ሁሉ አረንጎዴ ካርዱን እያወዛወዘ ከመቀመጨው ተነሳ፡፡ደኞቹም እያጨበጨቡ ቆሙ .. መድረክ ድረስ በመሄድ በየተራ አቅፈው ሳሟቸው፡፡
አስተያየት መስጠት ተጀመረ..የመጀመሪያው ዳኛ
‹‹በእውነት ሀዋሳ እናንተን የመሰሉ ባለድንቅ ችሎታ ሙዚቀኞችን ስላፈራች እድለኛ ነች፡፡
እኛም እዚህ መጥተን እናንተን ስላገኘን እድለኞች ነን፤በቃ ልዩ ናችሁ፡፡››
ሁለተኛው ዳኛ…..
‹‹ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡፡ሙዚቃው ከህይወታችሁ ጋር የሚያይዘው ጉዳይ አለ? ሁለታችሁም ስታለቅሱ ነበር፡፡እኔንም አስለቅሳችሁኛል፡፡ምከንያት ነበራችሁ?››
ሀሊማ መናገር ጀመረች‹‹አዎ ሁለታቸንም አባታችንን በጣም እንወደዋለን፡፡እርግጥ ሁሉም ሰው አባቱን በጣም ይወዳል፡፡እመኑን የእኛ አባት ግን ልዩ ሰው ነው፡፡›› አዳራሹ በሳቅና በጭብጨባ ተናጋ፡፡
ሄለን ቀጠለች‹‹ታዲያ አንተ አባታችን ባትሆን ኖሮ እኛ ዛሬ እንዲህ አምሮብን ሙዚቃ እየተጫወትን እንዲህ አዳራሽ ሙሉ ህዝብ እያጨበጨበልን አንታይም ነበር.፡፡ምክንያም እድሉም ጊዜውም አይኖረንም ነበር፡፡አዎ አባት ባትሆነን ኖሮ ይሄኔ ሁለታችንም አሞራ ገደል
አካባቢ ከሚገኝ ቆሻሻ መጣያ ገንዳ ውስጥ ተበላሽቶ የተጣለ ምግብ ከቆሻሻው በመለየት በመመገብ ላይ ነበርን፡፡…እና ከእንደገና ስለፈጠርከን አመሰግናለሁ ...ታዲ እንወድሀለን፡፡››
ዳኞቹም ታዳሚዎቹም ከልጆቹ ችሎታ በላይ በንግግራቸው ድንግርግር እንዳሉ ፊታቸውን በመመልከት ማወቅ ይቻላል፡፡
‹‹እባክህ አቶ ታዲዬስ እዚህ አዳራሽ ውስጥ ካላህ ወደ መድረክ ወጥተህ አንድ ነገር በለን››ከዳኞቹ መካከል አንድ ተናገረ፡፡ በአዳራሹ ያላው ታዳሚ እርስ በርሱ ዞር ዞር በማለት መተያየት ጀመረ፡፡ከመቀመጫው ተነስቶ ወደ መድረክ የሚወጣ ሰው ለመመልከት፡፡
‹‹ታዲ ና እንጂ››ሄለን ከመድረክ ተማፀነች፡፡
የሁለት ልጆች አባት ሳይሆን ተደባበዳቢ ቦዴ ጋርድ የሚመስል ጠይም ደንዳና ወጣት ወደ መድረኩ ወጣና ሁለቱንም ልጆቹን አቅፎ
ጉንጮቻቸውን ከሳመ በኃላ ማይኩን ተቀብሎ መናገር ጀመረ፡፡‹‹ታዴዬስ ማለት እኔ ነኝ፡፡ልጆቼ
ስለእኔ ያሉት ትንሽ ተጋኗል፡፡እውነታው በተቃራኒው ነው፡፡እነሱ ልጆቼ በመሆናቸው
በአሁኑ ወቅት በአለም በጣም እድለኛው ሰው
እኔ ነኝ፡፡ምን አልባት ችሎታቸውን አይታችሁ
ስታጨበጭቡላቸው ነበር፡፡ግን እመኑኝ መድረክ የመጀመሪያ ቀናቸው ስለሆነ የችሎታቸውን ግማሽም አላሳዮችሁም...እናም
ሁላችሁም እዚህ አዳራሹን የሞላችሁ ሁሉ ብትቀኑብኝ አይገርመኝም፡፡ምክንያቱም እኔ የእነዚህ ዕንቁ ልጆች አባት ነኝ፡፡አመሰግናለሁ፡፡>> ብሎ ወረደ፡፡ፕሮግራሙ ቢያልቅም ትንግርት
ስለልጆቹም ሆነ ስለአባትዬው ልትረሳ
አልቻለችም፡፡የሆነ ያልተለመደ ነገር ነው
የሆነባት፡፡<<አባታችን ባትሆን የቆሻሻ ገንዳ ላይ
ምግብ እንለቃቅም ነበር›› ሲሉ ምን ማለታቸው ነው?ግን የእውነት አባታቸው ነው ?
አልመሰላትም፡፡እንዴት አድርጎ ቢያሳድጋቸው
ነው በዚህ መጠን ሊወዱት የቻሉት?እውነትም
እሱ እንዳለው የሚቀናበት አባት ነው ? አለችና ቲቪውን አጥፍታ አየር ለመቀበል ቤቷን ለቃ ወደ ውጭ ወጣች፡፡
✨ይቀጥላል✨
አሁንም ዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ አበረታቱን ቤተሰቦች እያደረጋቹ አደለም በየቀኑ ለመልቀቅ እየሞከርኩ ነው እናንተም ማበረታታችሁን ቀጥሉ አመሰጎናለሁ።

👍122❤14👏3🔥1
‹‹እንዴ ይሄው፤ አታውቂውም እንዴ?›› በማለት ባላዋቂነቷ ሳቀችባት፡፡ ስለ እዚህ ልጅ ይበልጥ ለማወቅ በጣረች ቁጥር እየራቀባት መጣ‹‹ስንት እህቶች አሉሽ?››
<<አራት>>
‹‹ወንድሞችስ››
«አንድ»
<<እናታችሁስ>>
<< እናት የለንም፤ የሁላችንም ሞተዋል፡፡››
በዚህ ጊዜ አሮጊቷ በትሪ ሙሉ እንጀራ ቆልለው
ልሙጥ ሽሮ በላዩ ላይ ፈሰስ አድርገው ይዘው
በመምጣት መሀከል ላይ አስቀመጡ፡፡ልጆቹ
መብላት ጀመሩ ፡፡ እሷም ልክ እንደነሱ ለራሷም እየጎረሰች እነሱንም እያጎረሰች ተመሳሰለቻቸው፡፡ ያሮጊቷ ሽሮ እንደሚታየው
አይደለም፤ልዩ ጣዕም አለው፡፡ ከአስር አመት
በፊት የሞቱትን አያቷን አስታወሳት፡፡ እሳቸው
ነበሩ እንዲ አይነት ሽሮ ያበሏት የነበሩት፤ ከዛ
በኃላ ግን በአጋጣሚ እንኳን እንደዚህ አይነት ምግብ አግኝታ አታውቅም፡፡ ሆቴል
ከምትበላው ምግብ ጋር ሲነፃፀር ልዩነቱ የትየለሌ ቢሆንም ለእሷ ግን መሰጣት፡፡
ከጨረሱ በኃላ የምግብ ሂሳቡን ልትከፍል ስትል ቀድሟት ከፈለ ፡፡ስለፈራችው ብዙ
አልተከራከረችውም ፡፡ ከምግብ ቤቱ ወጡ…፡፡
‹‹ጨለማው ያስፈራል ልጆቹን ላስገባና እሸኝሻለሁ፡፡››
‹‹እሺ ››ብላ ተከለተለችው፡፡እንደቅድሙ ግን ከአጥሩ ውጭ ቆማ ልትጠብቀው
አልፈለገችም ፡፡ከልጆቹ ጋር ተጋፍታ ወደ ውስጥ ገባች፡፡ግቢው ሰፊ ነው፡፡ አምስት ሰርቪስ ቤቶችና አንድ በጣም ዘመናዊ የሆነ የተንጣለለ ቪላ ቤት አለ፡፡ ከሰርቪሶቹ ውስጥ አንዱን ተከራይቶ እንደሚኖር ገመተች፡፡ልጆቹ ግን ወደ ትልቁ ቤት እየተሯሯጡ ገቡ፡፡በረንዳ ላይ ሲደርሱ ቆመና << እንግዳዋን ሸኝቼያት መጣሁ እግራችሁን እየታጠባችሁ ጠብቁኝ›› ብሎ ፊቱን ሲያዞር እሷ ከህፃናቱ ጋር የቤቱን በራፍ አልፋ ወደ ውስጥ ገባች፡፡ ቤቱ ከስምንት በላይ ክፍሎች ከሰፊ ሳሎን ጋር ከነ ሙሉ ቤት ዕቃው አለው፡፡ ረጅሙ ሶፋ ላይ አንድ የአስር አመት ልጅ ፎጣ ለብሳ ተኝታለች፡፡
‹‹ቅር ካላለህ ትንሽ ብቆይ? ››አለችው፡፡
‹‹በንዴት ፊቱን እንዳጠቆረ ምንም ሳይመልስላት አልፎት ወደ አንደኛው ክፍል ሄደና ከፍቶ ገብቶ ዘጋው፡፡መኝታ ቤቱ እንደሆነ ገመተች፡፡
እሷም በቀስታ እርምጃ ወደ ተኛችው ልጅ በመሄድ ከጎኗ ሶፋው ላይ ተቀመጠች፡፡
‹‹ስምሽ ማነው?››
«ሠላም»
‹‹ሠላም ማን?››ተመሳሳይ መልስ መለሰችላት፡፡
‹‹ምንሽን ነው የሚያምሽ?››
‹‹እግሬን፡፡››
‹‹እኔ ዶክተር ነኝ፤ልይልሽ?››
‹‹እሺ›› ብላ ፈቀደችላት፡፡ቀስ ብላ የለበሰችውን ብርድ ልብስ ገልጣ ስታይ ዝግንን አላት፡፡ የልጅቷ ቀኝ እግር ጥምዝዝ ብሎ እንዳልሆነ ሆኗል ፡፡ ጣቶቿ አቅጣጫቸውን ለውጠው በተቃራኒው ናቸው ፡፡ግን አዲስ ጉዳት አይደለም፡፡እንደተጠማዘዘ የዳነና የቆየ ነው፡፡
‹‹ምን ሆነሽ ነው ሰላም?››
‹‹ልጅ ሆኜ አባቴ ነው እንዲህ ያደረገኝ፡፡››
ደነገጠች
‹‹ታዲዬስ ነው እንዲህ ያደረገሽ?››
‹‹ኧረ አይደለም ..አይደለም>>
ልጅቷ ተንገፈገፈች፡፡
‹‹አይ አባቴ ስላልሺኝ እኮ ነው፡፡››
‹‹ታዲያ ያ ክፉውን የድሮውን አባቴን ማለቴ ነዋ፡፡ሊለምንብኝ ነው እንዲህ ያበለሻሸኝ፡፡አሁን ግን የለም ታስሯል..ታዲ ነው ያሳሰረው፡፡››
‹‹አሁን ታዲያ እንዴት አመመሽ..አልዳነልሽም ነበር?>>
‹‹አይ ድኖልኛል ...ግን ሰሞኑን ወለም ስላለኝ ነው ህመሙ የተነሳብኝ፡፡››
‹‹እኔ ዶክተር ስለሆንኩ ነገ መድሀኒት ይዤልሽ መጣና ትድኚያለሽ እሺ፡፡››
‹‹ታዲ እኮ ሀኪም ቤት ወስዶኝ ነበር.፡፡ መድሀኒትም ተሰጥቶኛል፡፡››
‹‹አይ ጥሩ ነው››ብላ ትኩረቷን ወደ ሌሎቹ ልጆች ስትመለስ ተለቅ ተለቅ ያሉት የትናንሾቹን እግር እያጠቡ ተመለከተች፡፡
‹‹አንቺ የታዲዬስ ምኑ ነሽ?›› ጠየቀቻት ሰላም፡፡
‹‹ጓደኛው፡፡››
<<ጓደኛ እኮ የለውም፤አንቺን ከየት አገኘሽ?››
‹‹ብቻውን ነው እንዴ የሚኖረው?››ሚስት የለውም ወይ ለሚለው የውስጥ ጥያቄዋ መልስ ለማግኘት የተሰነዘረ ጥያቄ ነው፡፡
‹‹አይ አይደለም፤ከእኛ ጋር ነው ሚኖረው፡፡ ብታይ በጣም ነው የሚወደን ፡፡እኛም ውድድ ነው ምናደርገው፡፡››
ወሬዋን ሳትጨርስላት ታዲዬስ ከተከተተበት ክፍል ወጣ፡፡ ወደ ቴሌቨዥኑ ሄደና የህፃናት የካርቶን ፊልም ከፈተ ‹‹ፊልም እያያችሁ ጠብቁኝ ሸኚቼያት ልምጣ፡፡›› ሲላቸው ሁሉም በአንድነት ‹‹እሺ ታዲዬ›› አሉት ፡፡ ከተቀመጠችበት ፍራሽ ተነሳችና ሠላምን ግንባሯን ስማት ሌሎቹን ጉንጫቸውን በመሳም ተሰናብታቸው ወጣች፡፡የውጭ በራፉን ከፍተው እንደወጡ‹‹ታድለህ›› አለችው ምን ብላ ከእሱ ጋር ወሬ እንደምትጀምር ግራ ገብቷት፡፡
‹‹ለምኑ?>>
‹‹ልጆችህ በጣም ይወዱሀል፡፡››
‹‹እኔም በጣም እወዳቸዋለሁ፡፡››
‹‹ግን እነዚህን ሁሉ ህፃናት ያለእናት ማሳደግ በጣም አይከብድም?››
‹‹አይከብድም፡፡ልጆቹ የተንደላቀቀ የቅምጥል ኑሮ የለመዱ አይደሉም፡፡ ይህቺን ህይወት ሀ ብለው ሲጀምሩ በጣም ከከፋ እና ከዘቀጠ የድህነት መንደር ውስጥ ነው ፡፡እኔ ከእዛ ትንሽ የተሻለ ነገር ነው የማደርግላቸው፡፡ከበረንዳ ማደር ወደ ቤት ውስጥ፤ ጆንያ ከመልበስ ብርድልብስ ወደ መልበስ፤ ትርፍራፊ እና የተጣለ ምግብ ከመመገብ ልሙጥ ሽሮም ቢሆን መብላት... ይሄው ነው ብዙ አይጠይቁኝም፤ይሄንን ማድረግ ደግሞ አይከብደኝም፡፡››
‹‹ግን እኮ ብቻህን ከምትቸገር ብዙ በህፃናት ላይ የሚሰሩ እርዳታ ድርጅቶች አሉ ፤ኮምንኬት ብታደርጋቸው ይረዱሀል፡፡››
‹‹እኔ እርዳታ አልፈልግም ፡፡እነሱ ከፈለጉ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ህፃናት በየመንደሩ እና በየጎዳናው አሉ፡፡እነዚህ የእኔ ድርሻ ናቸው፡፡ ምን አልባት በምቾት እያኖርኳቸው መስሎ ያልተሰማሽ ከሆነ የተሳሳትሽ ይመስለኛል፡፡ እነዚህን ልጆች ግን ከምንም ነገር በላይ የሚርባቸው ፍቅር ነው፡፡ደግሞ እነዚህን ልጆች የማሳድጋቸው ደሀ ወይም ወላጅ አልባ
ስለሆኑ ከመሰለሽ ተሳስተሸል፡፡ሚጣ የኔ ልጅ ነች..ሌሎቹ አራቶቹ ደግሞ ወላጅ አልባ ብቻ ሳይሆኑ ጂኒዬሶችም ጭምር ናቸው..ለዛ ነው፡፡››
‹‹አልገባኝም፡፡››
‹‹ተይው በቀላሉ አይገባሽም፡፡››
እውነትም የዚህ ልጅ ነገር በቀላሉ አይገባም፡፡ ሊስትሮ እየሰሩ አምስት ልጆች በተንጣለለ ቪላ ቤት ውስጥ ማሳደግ፤ግራ የሚያጋባ ነገር ነው፡፡ወሬያቸውን እልባት ሳያበጁለት ዋናው አስፓልት ጋር ደርሱ፡፡
‹‹አሁን ታክሲ ወይም ባጃጅ ያዢና ወደ ሆቴልሽ ሂጂ፤እኔም ወደ ልጆቼ ልመለስ፡፡››
‹‹እሺ ስለ እራት ግብዣው አመሰግናለሁ፡፡ ልጆችህን ደግሞ በጣም ወድጄያቸዋለሁ፡፡ አንተም ጥሩ አባታቸው ብቻ ሳትሆን እናታቸውም ጭምር ነህ፡፡ደግሞ ቅድም የተናገርከው ልክ ነው ፤ ለሰው ልጅ ምግብ ብቻ ሳይሆን ፍቅርም መሰረታዊ ነገር ነው ፡፡›.ብላው ተሰናበተችው፡፡ እሱም ፊቱን አዙሮ ጉዞውን ቀጠለ፡፡ታዲዬስን እንዳገኘችው ለአንድ ወር ሙሉ በአዕምሮዋ ሲጉላላ የከረመውን ዕንቆቅልሽ በቀላሉ የምትፈታ መስሏት ነበር የተደሰተችው፡፡አሁን ግን ሌላ ተጨማሪ እንቆቅልሽ ጨምራ በመብሰልሰል ወደ ክፍሏ ተመለሰች፡፡
✨ይቀጥላል✨
አሁንም ዩቲዩብ ቻናል #ሰብስክራይብ #Share እያደረጋቹ ቤተሰቦች በቅንነት እባካቹ👍

👍88❤12😁4👎1🥰1
#ወዳጄ_ሆይ!
🌟ሰውን የሚያስከብረው ጌጣጌጥ ነው ብለህ ጌጥ አታብዛ።የሰው ልጅ ክብሩ እውነተኛ ቃሉ እና ቅንነቱ መሆኑን ተረዳ ።
#ወዳጄ_ሆይ!
🌟ተማረ ተመራመረ ብለህ ሰውን አታድንቀው ።ምንም ቢያውቅ ቢራቀቅ የሞቱን ቀን
አያውቅም ብለህ እዘንለት
#ወዳጄ_ሆይ!
🌟የጋለ ምጣድ አትንካ ትቃጠላለህ።በስሜት ያበደን ሰው እይዛለሁ አትበል ታዝናለህ።
#ወዳጄ_ሆይ!
🌟መንፈሳቸው እንደ ብረት ከቀዘቀዘባቸው ስዎች ጋር መኖር በጣም ከባድ ነው።አንተ እነርሱን
እስክታሞቅ እነርሱ አንተን ያበርዱሀልና ተጠንቀቅ ።
#ወዳጄ_ሆይ!
🌟ፈረስ የፈለግበት ድረስ ያድርስህ እንጂ ፈረሱ የፈለገበት አትድረስ ። እንዲሁም ፍቅር
በሚመስል ነገር ስክረህ በከንቱዎች ምክር አትራመድ ።
#ወዳጄ_ሆይ!
🌟መስማትና መስማማት ይለያያልና የስማህ ሁሉ የተስማማ መስሎህ አትዘናጋ ።
መስማማት ማድረግ ነውና የተስማማ ስውን በተግባር ታየዋለህ። ስዎች በጆሮ ሲስሙህ
ራሳቸውን ይነቀንቃሉ በልባቸው ሲያዳምጡህ ግን ከቀድሞ ስህተታቸዉ ይርቃሉ ::ይለወጣሉ::
ተረድተውሀላ!!
#ወዳጄ_ሆይ!
🌟ንግግርህ ፣አስተሳስብህን ፣ኑሮህን የምትመራበትን መመሪያህን ማሳያህ ነውና ንግግርህን በማስተዋል አድርገው
አፍና በራፍ እኩል ይከፈታል።❤️
ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ እንጂ ለ500 እኮ ትንሽ ነው የቀረው እባካቹ ቤተሰቦች
ሰብስክረይብ እያረጋቹ ያደረጋችሁ ደግሞ ሌሎች እዲያደርጉ #Share እያደረጋቹ አመሰግናለሁ፡፡

👍28👏18❤6🥰1
ትናንት እራሱ ለእነሱ ይሄንን ስጦታ ስገዛ እግረ መንገዴን ለራሴም ሶስት ጥንድ ጫማዎች ገዝቼያለሁ.. እቤቴ ግን ቢያንስ ከመቶ በላይ ጫማዎች አሉኝ ፡፡በእነሱ ግን መርካት ባለመቻሌ እና ተጨማሪ ያስፈልገኛል ብዬ በማመኔ ነው የገዛሁት፤እንጂ ትርፍ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም፡፡አነዚህ አንድ ፍሬ ህፃናት ግን ከምንጠቀምበት በላይ አንሰበስብም ሲሉ እነሱን ተከራክሬ ለማሳመን ምን አይነት ሞራል ይኖረኛል?›› ብላ ንግግሯን ደመደመች፡፡
‹‹በቃ እኔ ላስታርቃችሁ ፤ አሁን እሷ ቅር እንዳይላት ያመጣችውን ስጦታ አመስግናችሁ ተቀበሏት፡፡ከዛ እሁድ ጓደኞቻችንን ልንጠይቃቸው ስንሔድ ለሚያስፈልጋቸው በእሷ ስም እንሰጣቸዋለን..ይሄ ያስማማናል?፡፡››
ሁሉም በፈገግታ ሀሳቡን ተቀበሉት፡፡የእሷን ጉንጭ በማመስገን እየሳሙ መልሰውላት የነበረውን ስጦታ ከያስቀመጡበት በመውሰድ ወደመቀመጫችው ተመለሱ፡፡
በዚህ ጊዜ ሳይንቲስቱ ሙሴ ከመሸገበት ክፍል ፈንደድ ፈንደድ እያለ መጥቶ ተቀላቀላቸው፡፡ታዲዬስ ወደራሱ ስቦ ግንባሩን ሳመው፡፡ዶክተር ሶፊያ የሙሴ ድርሻ የሆነውን ስጦታ ልትሰጠው ስትንቀሳቀስ‹‹ዶ/ር ተይው ….እሱን አስረድቶ ለማሳመን ለሊቱም አይበቃንም፡፡ይልቅ አሁን ሁላችንም ለእራት እንውጣ >> የሚል ሀሳብ አቀረበ፡፡›› ሁሉም በደስታ ተስማሙ፡፡
‹‹እስክትዘገጃጁ ታክሲ ጋር ልደውል?››
‹‹እኔ መኪና ይዤያለሁ›› አለችው ዶክተሯ፡፡
‹‹ውጭ የቆመችው መኪና ያንቺ ነች እንዴ?››
<<አዎ>>
ተያይዘው ወጡ፡፡መኪናው ውስጥ ገቡ፡፡ ውጪው በጣም ጨልሟል፡፡ ከተማዋ መብራት ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል፡፡
‹‹መብራት ጠፍቷል እንዴ..?እናንተ ጋር ጄኔሬተር አለ ማለት ነው ? >> ስትል ጠየቀችው ዶክተር ሶፊያ እነሱ ቤት ለብቻው ተነጥሎ መብራት እየበራበት ሞሆኑ ገርሟት፡፡
‹‹እኛ እኮ ሀገሪቱን በመብራት አናስቸግርም ..እድሜ ለሙሴ እራሳችንን ችለናል፡፡››
<<እንዴት?>>
‹‹ሙሴ በራሱ ፈጠራ ከፀሀይ ሃይል የሚያመነጭ የራሳችንን በቂ ሀይል እንድናገኝ አድርጎናል..ነጻ ከወጣን አንድ አመት ሆነን፡፡ መብራት ኃይል የራሱን ቆጣሪ በብስጭት መሰለኝ ከቆረጠው ቆየ፡፡››
ወደ ግዙፉ ታዳጊ በአትኩሮት እየተመለከተች‹‹ይሄ ሙሴ ነው የሰራው ?>> ስትል ባለማመን ደግማ ጠየቀችው ፡፡
‹‹አዎ ይሄ የእኛ ሙሴ፡፡›› ፍርጥም ብሎ አረጋገጠላት
‹‹ለመሆኑ ስንት አመቱ ነው?››
‹‹አስር ወይም አስራ አንድ ይሆነዋል..ነገሮችን ለመስራት ግን ዋናው ዕድሜ አይመስለኝም ስጦታ እና ጥረት ካለ የእናት ጡት መጥባት ሳያቆሙ በፊትም ተዓምር መስራት ይቻላል፡፡››አለት፡፡
‹‹እሱስ እውነትህን ነው... በእንደ እናንተ አይነት የጉድ ቤት የማይቻል ነገር የለም !! እሺ አሁን ወዴት ልንዳ?›› አለችው፡፡
በከተማዋ የሚገኙ የትልቅ ሆቴል ስም ነገራት፤ ወደዛው አሽከረከረች፡፡‹‹እዛ አካባቢ የሚገኝ ምግብ ቤት ለመጠቀም ፈልጎ ይሆናል፡፡›› ስትል ገመተች፡፡ደረሱ ፡፡መኪናውን ቦታ አሲይዛ አቆመች፡፡
ወርደው ግን ያመሩት እንደጠበቀችው ወደአነስተኛ ምግብ ቤት ሳይሆን ወደ ዋናው ባለኮከብ ሆቴል ነው፡፡ትናንት እራት ከበሉበት የአሮጊቷ ምግብ ቤት ጋር ሲነፃፀር የሲኦል እና የገነት አይነት ልዩነት አለው፡፡ተከትላቸው ወደሆቴሉ ገባች፡፡ሲገቡ አስተናጋጆቹ ሁሉ ተንጋግተው በመምጣት በሞቀ ሰላምታና በደመቀ ፈገግታ ተቀብለው ቦታ ሰጧቸው፡፡ እያንዳንዶቹን ህፃናት በየስማቸው እየጠሯቸው ያናግሯቸው ነበር፡፡ሶፊያ በጣም ነበር የተደመመችው፡፡የቤቱ ቋሚ ደንበኞች እንደሆኑ በእርግጠኝነት አመነች፡፡ለአንድ ሰዓት ያህል እየተጫወቱና እየተዝናኑ ከቆዩ በኃላ መልሳ ቤት ድረስ ሸኘቻቸው፡፡ሲለያዩ‹‹ለእራት ግብዣው አመሰግናለሁ፡፡››አለችው፡፡
<<ችግር የለውም›› መለሰላት ታዲዬስ፡፡
‹‹አንድ ነገር ላስቸግርህ?››
<<ምን ልታዘዝ>>
‹‹ነገ ቁርስ ብጋብዝህ ደስ ይለኛል?››
<< ነገ?>>
‹‹አዎ ነገ ሁለት ሰዓት አካባቢ፡፡››
‹‹ይቻላል ስራ ቦታ ታገኚኛለሽ፡፡››አላትና ልጆቹን ይዞ ወደ ቤቱ ሲገባ እሷም መኪና• አስነስታ በተደመመ ስሜት ወደ ቤርጎዋ ተመለሰች፡፡

👍68🥰4❤3😁2👏1
በጊዜው ታዲዬስ እሷን ከሸኘ በኃላ እረፍት አላገኘም…፡፡በምን ዓይነት መንገድ ይህቺን ልጅ ከገባችበት ችግር እንድትወጣ ሊረዳት እንደሚችል በቀላሉ ሊገለጽለት አልቻለም፡፡ እንዲሁ በሀሳብ ሲባዝን አምሽቶ ከምሽቱ አራት ሰዓት አካባቢ ነበር ምን ማድረግ እንዳለበት መወሰን የቻለው፡፡ሞባይል ስልኩን አነሳና ያሰበውን ወደተግባር ለመቀየር ያግዙኛል ወዳላቸው ሶስት ሰዎች ጋር በተከታታይ የደወለው፡፡እቅዱን ለሁሉም በዝርዝር አስረዳና በእፎይታ እራሱን ለእንቅልፍ አሳልፎ ሰጠ፡፡
በማግስቱ ማለዳ 12 ሰዓት ነበር የአቶ ቂጤሳ ቤት በሶስት ሰዎች የተንኳኳው፡፡ድምፁን ሰምታ በድንጋጤ በመበርገግ በሩን ለመክፈት መኝታዋን ለቃ በራፍ ላይ ቀድማ የተገኘችው መርጊቱ ነች፡፡ ይሄ ያልተለመደ ክስተት ነው ፡፡ በዚህ ሰዓት ማን ነው?ማን ሞተ..…?‹‹ተልባ ቆይዋ እያለች..ጎመን ቀንጣሿ ምች መታት››የሚለው ሀገራዊ ብሄል በአዕምሮዋ ተሰነቀረ፡፡እሷን ማን ቀደማት?የትኛው ዘመድ ነው ከእሷ ጋር ፉክክር የገጠመው…?ማነው ቀድሟት የሞተው?ምን አለ አንድ ቀን ዘግየት ብሎ ቢጠብቋት ወይም ምን አለ አንድ ቀን ፈጠን ብትል? በሰከንዶች ሽርፍራፊ ይሄን ሁሉ እያሰላሰለች በራፉን ስትከፍት ሶስት ጎልማሳ ወንዶች በራፉን ሞልተው ቆመዋል፡፡
‹‹ምንድ ነው? ምን ተፈጠረ?››
‹‹ተረጋጊ ሰላም ነው፡፡››
‹‹በዚህን ሰዓት የምን ሰላም?››
‹‹ኧረ ሰላም ነው ፤ አባትሽን ማናገር ፈልገን ነው፤ቤተክርስቲያን ሳይሄዱ ልንደርስባቸው ስለፈለግን ነው በማለዳ የመጣነው፡፡
በድንጋጤ የሚንቀጠቀጠው ሰውነቷ ሳይረጋጋ ከበራፉ ገለል አለችና እንዲገቡ ፈቀደችላቸው፡፡
‹‹ግቡ ..ይቅርታ ቤቱ ግን እንደተዝረከረከ ነው፡፡››
‹‹አረ ግድ የለም፤ይልቅ አባትሽን ቀስቅሺልን፡፡››
‹‹እሺ ››ብላ ዞር ስትል አቶ ቂጤሳ ተነስተው ከመኝታ ቤታቸው በመውጣት ሳሎን ደርሰው ነበር::
መርጊቱ ትታቸው ወደ መኝታ ቤት ገባችና ጆሮዋን ግድግዳ ላይ ለጥፋ ማዳመጡን ቀጠለች፡፡
‹‹ሰዎች ምነው በሰላም ነው? አረ ቁጭ በሉ፡፡››
በተርታ ተገትራው የነበሩት ሶስት ሰዎች በአክብሮት እጅ እንደመንሳት አሉና ‹‹የመጣንበትን ጉዳይ ሳንናገር መቀመጥ አንችልም፡፡››
‹‹እኮ ቁጭ በሉና ትናገራላችሁ፡፡››
‹‹ኧረ ግድ የለም ቆመን ይሻላል፡፡››
‹‹እሺ ምን እግር ጣላችሁ?››
‹‹ልጃችሁን ለልጃችን እንድትሰጡን ልንጠይቅ ነው፡፡››
‹‹ልጃችሁን ለልጃችን?››አቶ ቂጤሳ ቃሉን መልሰው ደገሙት፡፡መኝታ ክፍል ሆና ስታዳምጥ የነበረችው መርጊቱ የምትሰማው ነገር የተዓምር ያህል አስደነገጣት፡፡ማን ነው
ላኪው? መቼስ እዚህ ቤት ከእኔ ሌላ ሌላ ሴት የለም፡፡የትኛው አፍቃሪዬ ነው እኔን ሳያማክር ለጋብቻ ሚስኪኑ አባቴ ጋር የላከው? በፍቅር የሚጎመዣትና ስትወጣ ስትገባ የሚለክፏትን አንድ ሶስት ወንዶች በምናቧ መጡላት፡፡ከእነሱ መካከል አንድ እንደሆነ እርግጠኛ ሆነች፡፡ አሳቃትም፣ አሳዘናትም፡፡ሁለቱም ስሜት እኩል ነው የተሰማት፤አንድ ላይ ተዋህዶ አንድ ላይ ተጨፍልቆ፡፡መቼስ እርጉዝ መሆኗን እያወቀች ብትፈልግ እንኳን ይሄንን የጋብቻ ጥያቄ መቀበል አትችልም፤በሀጥያት ላይ ሌላ ሀጥያት አትጭምርም፡፡ጆሮዋን የመኝታ ቤቱ በራፍ ላይ እንደለጠፈች ሳሎን የሚካሄደውን ትዕይንት መከታተል ቀጠለች፡፡
‹‹ለመሆኑ ልጁ ማን ነው?››አባቷ ጠየቁ፡፡
‹‹እኮ ማ ነው? የእሱንና የቤተሰቦቹንም ማንነት ንገሩኝ?››
ያው እርሷ ባያውቁም ልጃችንና ልጆት ለረጅም ጊዜ ፍቅረኛሞች ነበሩ፤በጣም ይዋደዳሉ፤ያው አሁን መምጣታችን ነገሩን ሁሉ በእርሷ ፍቃድ እንዲሆን ስለፈለግን ነው፡፡››
‹‹ሰዎች ለምን የጠየቅኳችሁን አትመልሱም..? ልጁ ማን ነው?››ጋሽ ቂጤሳ ትግስት አጠራቸው፡፡
መርጊቱ ደግሞ ከሽማግሌ ተብዬዎቹ የምትሰማው ነገር ግራ አጋባት‹…እንዴ እንዲህ አይነት ውሸት አለ እንዴ?ማነው እንዴህ በድፍረት አይን ያወጣ ውሸት አሲዞ ሽማግሌዎችን የሚልክ?እሱ ተዋርዶ እነሱንም የሚያዋርድ?›› ተንደርድራ ወጥታ ለሽማግሌዎቹም ለአባቷም ምንም አይነት ፍቅረኛ እንደሌላትና ማንንም ማግባት እንደማትፈልግ ነግራቸው ነገሩን ለማሳጠርና ሁሉንም ከድካም ለመገላገል ወሰነችና ወደ ሳሎን ሳሎን ለመግባት መኝታ ቤቱን በራፍ ከፍታ አንድ እግሯን ስታነሳ ‹‹ጌታዬ ልጁ ታዲዬስ ነው፡፡››የሚል ድምጽ ከሽማግሌዎቹ ሰማች... ባለችበት ደንዝዛ ቆመች፡፡
‹‹ታዲዬስ….ታዲዬስ የቱ?››
‹‹ታዲዬስ መሀንዲሱ ..እዚሁ እርሶ ቤት የሚኖረው፡፡››
አቶ ቂጤሳ ከመደንገጣቸው የተነሳ በተቀመጡበት እጆቻቸውን ጭንቅላታቸው ላይ ጫኑና አንገታቸውን ወደ መሬት ደፍተው ማሰላሰል ጀመሩ፡፡‹‹እንዴት እንዲህ ይሆናል?››አንድ ቀን እንኳን የረባ ጫወታ ሲጫወቱ፣ሲቀላለዱ ወይም ሲላፉ አጋጥሞቸው አያውቅም፡፡ሁለቱም እርስ በርስ ከመሳሳብ ይልቅ የመገፋፋት ባህሪ ነበር ዘወትር የሚያታይባቸው፡፡እንዴት ከእሷቸው በዚህን መጠን ግንኙነታቸውን መሰወር ቻሉ?
‹‹እሺ ያላችሁትን ሰምቼያለሁ፤ጉዳዩን ከልጅቷም ከዘመድ አዝማድም ጋር ልማከርበትና መልሱን ለሳምንት ልስጣችሁ፡፡››
በደመነፍስ እግሯን እየጎተተች በጓሮ በር ወጥታ ወደ ታዲዬስ ክፍል አመራች፤አንኳኳች፤ ከፈተላትና ወደ መኝታው ተመለሰ፡፡ ምንም ሳትናገር ወደውስጥ ገባችና በራፉን ዘጋችውና ወደ አልጋው በመውጣት ከውስጥ በመግባት ዝም ብላ ከጎኑ ተኛች፡፡ በአድናቆትና በዝምታ ተመለከታት፡፡ በጣም ደንግጣለች፤ በእንቅልፍ ልቧ እየተጓዘች የመጣች ትመስላለች፡፡ዝም ብሎ አይኖቾ እንባ ያመነጫሉ፡፡ከሃያ ደቂቃ የዝምታ ጊዜ በኃላ << ታፈቅረኝ ነበር እንዴ?››በማለት ያልጠበቀውን አደናጋሪ ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
ግራ ተጋባ‹‹ምን አልሺኝ?››
‹‹ታፈቅረኝ ነበር ወይ ?ሳትዋሽ ንገረኝ፡፡››
‹‹በፍቅር እኮ ውሸትም ይሉኝታም አይገባም፤ፈጽሞ አፍቅሬሽ አላውቅም፡፡››
ሰውነቷ በደቂቃዎች እንደበረዶ ቀዘቀዘባት‹‹ታዲያ ለምን?አስበኸዋል ግን? ሰው ያፈቀረውን እንኳን ለማግባት ሞራል ባጣበት ጊዜ አንተ የማታፈቅራትን ለዛውም እርጉዝ የሆነችን ሴት ለማግባት መስዋዕትነትን ለመክፈል የፈለከው ?ነው ወይስ የውሸት ድራማ እየተጫወትክ ነው፡፡?››
‹‹የውሸት አይደለም፤ የእውነት ነው የማገባሽ..ማለቴ እንጋባለን፤አብረን እንኖራለን፡፡…ያለምንም ግንኙነት፤ልጅሽን ወልደሽ ሁኔታዎች ከተስተካከሉ በኃላ አልተስማማንም ብለን እንፋታና አንቺም የፈለግሽውን ማለት የሚያፈቅርሽንና የምታፈቅሪውን ታገቢያለሽ፤ እኔም እንደዛው፡፡››
‹‹እኮ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ ገብተህ ይሄን ሁሉ ውጣ ውረድ ውስጥ ለምን ለመግባት ፈለክ?እኔ ምን አድርጌልህ አውቃለሁ? አንድ ቀን እንኳን ልብስህን ልጠብልህ ወይም ቤትህን ላፅዳልህ ብዬህ አላውቅ፡፡››
ስለተደረገልሽ ብቻ አይደለም የሆነ ነገር ማድረግ ያለብሽ፡፡ደግሞም ላንቺ ብዬ አይደለም፤ ለአባትሽ ስል ነው፡፡አንቺ እንዳልሽው በዚህ ዕድሜያቸው ጥለሻቸው ብትጠፊ እርግጠኛ ነኝ ለአንድ ወር በህይወት አይቆዩም፤በመጨረሻ ዕድሜያቸው ለእሳቸው ይሄ አይገባቸውም፡፡››
✨ይቀጥላል✨
ዛሬ በጠዋት ተከስተናል ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ እንጂ እስከማታ የተወሰነ ሰው #Sebscribe ካደረገ በክፍል #31 እንገናኛለን #Shareም አይረሳ አመሰግናለሁ፡፡

👍121❤12😱5😢2
አየሽ እኔ ስራን የምሰራው ለብር አይደለም እያንዳንዱን የህይወት ዘርፍ ለማጣጣም እንዲያመቸኝ ነው፡፡ሳይት ኢንጂነር
ሆኜ ሰርቼያለሁ፤የሆቴል ማናጀር ሆኜያለሁ፤ተሸካሚ ሆኜ ሰርቼ አውቃለሁ፤ ዌይተርም ነበርኩ፤ አስተማሪም ሆኜ ሰርቼያለሁ..ብዙ ብዙ ነገር፡፡ይሄንን የማደርገው ከነዛ የስራ ዘርፎች የሚገኘውን የህይወት ልምድ ቀጥታ ለማግኘት ስል ነው፡፡››
‹‹የሚገርም ነው!!!የወደፊት እቅድህን ልትነግረኝ ትችላለህ?››
‹‹የወደፊት ዕቅዴ ህዝብና መንግስትን ማሳቀቅ ነው፡፡››
‹‹አልገባኝም?››
‹‹አየሽ... ሰሞኑን የተዋወቅሻቸው አምስት ልጆቼን በየተሰጥኦዋቸው የመጨረሻው ስኬት ላይ እንዲደርሱ ማገዝ ነው ዋና የህይወት ግቤ፡፡…ያ ሲሆን ደግሞ እነዚህ ልጆች ከበረንዳ ኑሮ ከቆሻሻ ላይ ተነስተው የሀገሪቱ ምርጥ ሰው ሆነው ሲገኙ..መንግስትም ሆነ ማንም ገንዘብ አለኝ የሚል ግለሰብ ስንቱ ምጡቅ
አዕምሮ ያለው ትውልድ በየቆሻሻው ባክኖ እንደቀረ ማሰብና መቆጨት ይጀምራል፡፡ከዛም ከአንድ ሺ መካከል አንድ ሰው እንኳን የእኔን ልጆች ስኬት ተመልክቶ የራሱን ኃላፊነት ለመወጣት ቢነሳ ጎዳና ባክኖ የሚቀር አንድ ህፃን እንኳን አይገኝም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ በአጠቃላይ እኔ ይሄንን አድርጌያለሁ ... እናንተስ ?...ለማለት ነው..፡፡የተግባር ስብከት ለመስበክ፡፡››
ቀጣይ ምን እንደምትጠይቀው እያሰላሰለች ሳለ የእሱ ስልክ ድምፅ አሰማ፡፡
<ሄሎ ሰላም::>>
<<ሄሎ>>
<<ምን?>>
‹‹መጣሁ...በቃ ሄለን ሞባይሉን ስጫትና ከኋላ ትከተለው ..ደውዬላት ያሉበት ድረስ ሄዳለሁ፡፡›› ስልኩን ዘጋው፡
‹‹ምነው? ምን ሆንክ?››
‹‹ሙሴ ከግቢ ወጥቷል ...ሂሳብ ክፈይና እንሂድ፡፡››ከቦርሳዋ ብር አወጣችና ጠረጴዛ ላይ አስቀምጣ በመነሳት ወደመኪናው አመራች ፡፡እሱም ተከትሏታል፡፡ የተፈጠረው ችግር አልገባትም፡፡
ከግቢው ወጥተው መንገድ እንደያዙ‹‹አልገባኝም..ሙሴ ከግቢ መውጣቱ ችግር አለው?››
‹‹አዎ..ሙሴ ትንሽ ክትትል የሚፈልግ ልጅ ነው፤ከግቢ የሚወጣው ብዙውን ጊዜ የሆነ ነገር ለመስራት አስቦ የሆነ ቁሳቁስ ሲያጣ ፍለጋ ነው፡፡››
‹‹ከየት ነው የሚፈልገው?››
‹‹ከየመንገዱ.፤ከየቆሻሻ መጣያው...የፈለገውን እሲኪያገኝ ድረስ ሲባዝን ነው የሚውለው..ካጣ ደግሞ ስለሚ።በሳጭ ያመዋል፡፡››
‹‹ምንድነው የሚያመው?››
‹‹የሚጥል በሽታ አለበት፡፡ሙሴ ተአምራዊ የሆነ የፈጠራ ብቃት አለው፡፡ ይሁን እንጂ በዛው ልክ ታማሚ፤ከሰው የማይግባባ፤የትምህርት ለመማር የሚያዳግተው የተለየ ልጅ ነው፡፡››
‹‹ቆይ ..አንድ የማይገባኝ ነገር እንዲህ የተለየ የፈጠራ ብቃት እያለው ትምህርት ለመማር እንዴት ይከብደዋል?››
‹‹በዚህ አለም የትምህርት ስርዓት ስትማሪ በካሪኩለሙ በተቀመጠው ልክ ካልተጓዝሽ ደደብ ነሽ፡፡››
‹‹አልገባኝም?››
‹‹ማለቴ ሰነፍም ከሆንሽ…በጣምም ከመጠን ያለፈ ጎበዝ ከሆንሽ በተመሳሳይ ‹ደደብ ነሽ >ነው የምትባይው...ምክንያቱም ሰነፍ ስትሆኚ የእውነት አንቺ አታውቂም ...በጣም ጎበዝ ስትሆኚ ደግሞ አንቺ ባወቅሺው መጠን
ካሪኩለሙም አስተማሪዎችሽም አያውቁም፡፡
የዛን ጊዜ ታዲያ መቼስ ማንም ቢሆን አስተማሪው አያውቅም ማለት ስለማይደፍር አንችኑ ደደብ ነሽ ይልሻል..ያሸማቅቅሻል፡፡
ሙሴን ያጋጠመው እንደዚህ አይነት ሁኔታ
ነው፡፡ለምሳሌ ሁለተኛ ክፍል ሆኖ አንድ ዶሮ ሲደመር ሶስት ዶሮ ስንት ይሆናል ? የሚል ጥያቄ ፈተና ላይ ቀረበለት፡፡ለዚህ ጥያቄ
አስተማሪው ከእሱ የሚጠብቀው መልስ አራት
ዶሮ የሚል ነበር፡፡እሱ ግን ‹መደመር አይቻልም> ብሎ መለሰ፡፡ ኤክስ አገኘ፡፡‹ አልተሳሳትኩም›ብሎ ክርክር አስነሳ << ..አንዱ ዶሮሴት..ሌላው ወንድ..አንዱ ጥቁር ሌላው ቀይ..አንዱ 5 ኪሎ ሚመዝን ሌላው 3 ኪሎ
ሚመዝን ሊሆን ይችላል፤ታዲያ እንዲህ በስም ካልሆነ በስተቀር በምንም የማይመሳሳሉ
የተለያዩ ነገሮች አንድ ላይ ጨፍልቆ አምስት ዶሮዎች ማለት ትልቅ ስህተት ነው ብሎ ሀሳቡን አብራራ፡፡ከእኔ በስተቀር ማንም ሀሳቡን
ሊረዳው የፈለገ ሰው አልነበረም፣አስተማሪዎቹ
ሳይቀሩ እንደጅል ነበር የቆጠሩት፡፡››
‹‹እውነትም እንክብካቤ የሚገባው ልጅ ነው››አለች ዶ/ር ሶፊያ በሙሴ ሁኔታ ውስጧ ተነክቶ፡፡ ታዲዬስም ሄለን ጋር ደወለ የሚገኙበትን ቦታ ነገረችው፤ ተቃርበዋል፡፡
✨ይቀጥላል✨
ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ እንጂ በጣም ቀንሳችኋል እስካሁን የተወሰነ ሰው ነው #Sebscribe ያደረገው ከዚ ፖስት በኋላ አንድ 20 ሰው እጠቦቃለው ሃሳባችን ከሞላ ጠዋት በክፍል 33 እንገናኛለን አመሰግናለው።

👍105❤12🥰1😱1
ትንግርት ታዲዬስን ለመጨበጥ በአየር ላይ የዘረጋችው እጇን እንዳንከረፈፈች ፊቷን ሙሉ በሙሉ ወደ ዶ/ር አዞረች፡፡በህይወቷ መቼም ፊት ለፊት አገኛታለሁ ብላ ለሰከንድ እንኳን አስባ የማታውቀውን ሰው ፊት ለፊት ስታይ አፏን ከፈተች.. ለደቂቃዎች ሁለቱም ደንዝዘው በፀጥታ ተፋጠጡ፡፡ ሶስት ወንዶች ግራ ገባቸው፡፡
በመጋባት ጠየቀ::
‹‹እጅግ በጣም እንተዋወቃለን ››ብላ ስትናገር እና ጠረጴዛ ላይ ያለውን የለስላሳ ጠርሙስ አንስታ ዶክተሯ ጭንቅላት ላይ ስትከሰክሰው አንድ ነበር፡፡በሰከንዶች ቅፅበት በአከባቢው ከፍተኛ ግርግርና ድንጋጤ ተከሰተ፡፡.ዶ/ር ሶፊያ መላ ፊቷ በደም ተሸፍኖ እራሷን ስታ ተቀምጣበት ከነበረበት ወንበር ወደ ኃላዋ ተገነደሰች፡፡
<< ምን ነካሽ አብደሻል እንዴ…?››ኤልያስ
‹‹እንዴ ምነካሽ ?እኛን እንኳን አታከብሪም?››ጋዜጠኛው አመነጫጨቃት፡፡ ታዲዬስ ዶ/ር ሶፊያን በክንዶቹ አቅፎ ግራ በመጋባት ትንፋሿን ያዳምጣል፡፡
ከ5 ደቂቃ በኃላ ታዲዬስ እና ኤልያስ ዶ/ር ሶፊያን ለህክምና ወደ ሆስፒታል ይዘዋት ሲሄዱ በአካባቢው የነበሩ ፖሊሶች በአፋጣኝ ደርሰው ወንጀለኛዋን ትንግርትን ይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያ አመሩ፡፡
✨ይቀጥላል✨
ቤተሰቦች የዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ እያደረጋቹ
ነው በጣም አመሰግናለው
አሁንም #Sebscribe ያለደረጋቹ እያደረጋቹ #ትንግርት እስከሚያልቅ 500 ##Sebscriber እጠብቃለሁ በቅድምያ ለሁላችሁሜ አመሰግናለሁ።

👍70❤15🤔6😱6
አይደለችም፡፡ከእሱ በፊት ቀርባቸው የነበሩት ሁለት ወንዶች እንዴት አይነት አስቸገሪ ሁኔታ ላይ ጥለዋት እንደነበረ ዛሬም ትዝ ሲላት ዝግንን ይላታል፡፡
አሁን የምትፈራው ይሄ ልጅ ይሄን ሁሉ ነገር ለምዶ በቃህ ከዛሬ ወዲያ አንገናኝም ብትለው አሜን ብሎ ተሰናብቷት ይሄዳል? እዚህ ላይ ከባድ ጥርጣሬ አላት፡፡ይህንን ጥርጣሬዋን ለማጥራት የቅርብ የሆነ ጓደኛውን በጎን ቀጥራበት ለአንድ ወር ስታሰልለው ነበር፡፡ስለእሷ ምን እንደሚያስብ?እቅዱና ምኞቱን ምን እንደሆነ ?ለማወቅ፡፡በተቀዳ የድምፅ መረጃ ያገኘችው መረጃ ግን ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ የጣላት ነበር ፡፡ፈፅሞ እንዳሰበችው አይነት የዋህና ታዛዥ ብቻ የሆነ ሰው ሆኖ አላገኘችው፡፡እሷ ላይ የሞትና የሽረት የሆነ ሰፊና ጥልቅ እቅድ እንዳለው ደርሳበታለች፡፡ ይሄን ካወቀች በኃላ ሳትበረግግና ስሜቷን ለእሱ በግልፅ ሳታሳውቀው እንዴት ከላዮ ላይ ጉዳት በማያስከትልባት ዘዴ ገለል እንደምታደርገው እቅድ ማውጣት እዳለባት ገብቷት እየሰራችበት ነው፡፡
እሱ ግን እሷ ምንም እንደምታቅ ባያውቅም እንደተባለው ከእሷ በጣም የራቀ እና የተለየ እቅድ ነበረው፡፡ከእሷ ለዘላለምም ቢሆን የመለየት እቅድ በአእምሮዋ የለም፡፡በጣም እንደምታፈቅረው ነው የሚያስበው፡፡እሱም እለት ከእለት በጣም እያፈቀራት ሄዷል ፤ከዛም በላይ ከእሷ ጋር ከተገናኘበት ጊዜ በኃላ ኑሮውን ከሲኦል ወደገነት ቀይራለታለች፡፡በምንም አይነት ሁኔታ ይሄንን እድል ማባከን አይፈልግም፡፡ከውበቷም ከሀብቷም ፍቅር ይዞታል፡፡አሁን ወደቤቷ የሚሄደው ከእዚህ ጋር ለተያያዘ ጉዳይ ቀስ ብሎ በእርጋታ ሊያማክራት ነው፡፡ይሄንን ጉዳይ እስከመጨረሻው በፍቅርና በሰላም መስመር ለማስያዝ እስከመጨረሻው ጠብታ ይለፋል፡፡የሰላሙ መንገድ የማይሳካ ከሆነ ግን በየትኛውንም ሌላ አማራጭ በመጠቀም ሀሳቡን ለማሳካት ቆርጧል፡፡በሰላም ከሆነ ፍቅሯንም ሀብቷንም መቆጣጠር ይችላል፤ ያ ተመራጩና በጣም የሚፈልገው ነው፡ካልሆነ ግን
በየትኛውም መስዋዕትነት እሷን ዞር አድርጎ ሀብቷን ጠቅልሎ የመረከብ ፍላጎቱ ጣሪያ የነካ ነው፡፡
💫ይቀጥላል💫
አሁንም ዩቲዩብ ቻናሉን #ሰብስክራይብ #Share እያደረጋቹ ቤተሰቦች በቅንነት እባካቹ👍

👍68❤4