#የጣሪያ_ስር_አበቦች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
ማደግ፣ ብልህ መሆን
ልክ እንደ መጀመሪያው አመት ሁሉ ሌላኛውም አመት አለፈ እናታችን ልትጎበኘን የምትመጣበት ቀን እየቀነሰ መጣ ከስንት አንድ ጊዜ ስትመጣም
ሁሌም ከዚህ ለመውጣት ጥቂት ሳምንታት ብቻ እንደቀሩን እንድናምንና ተስፋ እንድናደርግ የሚያደርገን ቃል ትገባልናለች። በእያንዳንዱ ምሽት መጨረሻ ላይ የምናደርገው ነገር ቢኖር የቀን መቁጠሪያው ላይ በትልቁ
የኤክስ ምልክት ማድረግ ነው።
አሁን ትላልቅ ቀይ የኤክስ ምልክቶች ያሉባቸው ሶስት የቀን መቁጠሪያዎች አሉን፡ የመጀመሪያው በግማሽ ብቻ ቀይ የኤክስ ምልክት የተደረገበት ነው።
ሁለተኛው ሙሉ በሙሉ ምልክት ተደርጎበታል፡ ሶስተኛው ደግሞ ግማሹ በኤክስ ምልክት ተሞልቷል፡ እየሞተ ያለው አያታችን አሁን ስልሳ ስምንት
አመት ሆኖታል። ሁልጊዜም የመጨረሻ ትንፋሹ ነው እየተባለ እኛ በተረሳ ቦታ እየተጠባበቅን እሱ ግን አሁንም መኖሩን ቀጥሏል ስልሳ ዘጠኝ አመት
እንዲሆነው እየኖረ ይመስላል።
ሀሙስ ሀሙስ በፎክስወርዝ ቤት ውስጥ ያሉ ሠራተኞች ወደ ከተማ
የሚሄዱበት ቀን ነው፡ እኔና ክሪስቶፈር ጥቁሩ ጣራ ላይ ወጥተን ጋደም በማለት የፀሀይ ብርሃን የምናገኘውና ከጨረቃና ከኮከቦች ስር ሆነን አየር
የምንቀበለው እነሱ በሚወጡ ጊዜ ነው በጣም ከፍ ያለና አደገኛ ቢሆንም ንፁህ አየር የተጠማው ቆዳችንን ማስታገስ የምንችልበት ብቸኛ ቦታ ቢኖር ጣሪያው ብቻ ነው።
እግራችንን በጭስ ማውጫው በኩል የሁለቱ ቤቶች ጣራዎች የሚገናኙበት ጥግ ላይ ስናደርግ ደህንነት ተሰማን የተደበቅንበት ቦታ መሬት ላይ ካለው ሰው ሁሉ ይከልለናል: የአያትየው ቁጣ ገና መተግበር ስላልጀመረ እኔና
ክሪስ ግዴለሾች ሆነን ነበር መታጠቢያ ቤት የምንጠቀመው ሁሌ ተጠንቅቀን አይደለም። አንዳንዴ ልብሶቻችንን ሙሉ በሙሉ ላንለብስ እንችላለን አንድ
ክፍል ቤት ውስጥ ውለን እያደርን ሁልጊዜ ውስጣዊ የአካል ክፍሎቻችንን ከተቃራኒ ፆታ ሚስጥር ማድረግ ከባድ ነበር።
እውነቱን ለመናገር ማንኛችንም ማን ምን እንዳየ ግድ አልነበረንም።
ግድ ሊኖረን ግን ይገባ ነበር
መጠንቀቅ ነበረብን መቼም ቢሆን የእናታችንን በአለንጋ የተተለተለ ጀርባ መርሳት አልነበረብንም።
እናታችን የተገረፈችበት ጊዜ እጅግ ሩቅ፣ የዘለአለም ያህል የራቀ ሆኖ
ተሰምቶን ነበር።
አሁን እስካለሁበት አስራዎቹ የእድሜ ክልል ድረስ አንድም ቀን የራሴን እርቃን ሙሉ በሙሉ አይቼው አላውቅም: እርቃኗን የሆነች ሴት በስዕልም
እንኳን አይቼ አላውቅም ከእምነበረድ የተሰሩ እርቃን ሀውልቶች አይቼ የማውቅ ቢሆንም እነሱ ግን ሁሉንም አያሳዩም።
ስለዚህ እርቃኔን ለማየት መስታወት ፈለግኩ። የመድኃኒት ማስቀመጫው ቁምሳጥን ላይ ያለው መስተዋት ከፍ ብሎ የተሰቀለ ስለሆነ በደንብ አያሳይም፡ ስለዚህ ሙሉ በሙሉ እርቃን ሆኜ ራሴን ለማየት ክፍሉ ውስጥ ብቻዬን እስክሆን መጠበቅ አለብኝ ከዚያ ከመልበሻው መስታወት ፊት እርቃኔን ቆሜ እንደፈለግኩ አተኩሬ እመለከታለሁ። በራሴ ሰውነት እደሰታለሁ፣ አደንቃለሁ።
ተሳካልቶልኝ መኝታ ክፍላችን ውስጥ ያለው መስተዋት ፊት ለፊት እርቃኔን ቆምኩ የሆርሞኖች መለወጥ ያመጣው ነገር የሚገርም ነው! በእርግጠኝነት
እዚህ ስመጣ ከነበርኩት በላይ በጣም ቆንጆ ሆኛለሁ። ፊቴን፣ ፀጉሬን፣ እግሮቼን፣ እንዲሁም ደረቴን እያየሁ ነው: ከአንድ ጎን ወደ ሌላ ጎን እየተሽከረከርኩ መስታወቱ ላይ ያለውን ምስሌን እያደነቅኩ ነው። በራሴ
ተመስጫለሁ።
የሆነ ሰው ከጀርባ እየተመለከተኝ እንደሆነ ስለተሰማኝ ድንገት ስዞር ክሪስ ቁም ሳጥኑ የፈጠረው ጥላ ውስጥ ቆሞ ሲያየኝ ያዝኩት: ጣሪያው ስር ካለው
ክፍል እየመጣ ነበር እዚያ ቆሞ የነበረው ለምን ያህል ጊዜ ይሆን? ሳደርግ የነበረውን እርቃንን የማየት ብልግና አይቶ ይሆን? አምላኬ እንዳላየ ተስፋ
አለኝ:
ክሪስ በቆመበት ደንዝዟል፡ ልክ ከዚህ በፊት አይቶኝ እንደማያውቅ ሁሉ ሰማያዊ አይኖቹ ላይ የተለየ ብርሀን ይታይ ነበር፡ ምናልባት እርቃናችንን ሆነን ፀሀይ ስንሞቅ መንትዮቹም አብረውን ስለሚሆኑ ሀሳቡን ወንድማዊና ንፁህ ያደርግ ስለነበረ አፍጥጦ አያየኝም ነበር ማለት ነው።
አይኖቹ በእፍረት ቀልተው፣ ከፊቴ ወደታች ወደ ጡቶቼ ከዚያ ወደ ታች...ወደ ታች ሄደው እግሮቼ ጋ ደረሱና እንደገና በዝግታ ወደ ላይ ተመለሱ።
በፈለገ ጊዜ እንዴት ማሾፊያ እንደሚያደርገኝ ጠንቅቆ በሚያውቀው ወንድሜ
አይን አጉል ስርአት አጥባቂ ሆኜ ላለመታየት ምን ማድረግ እንዳለብኝ እርግጠኛ ባለመሆን እየተንቀጠቀጥኩ ቆምኩ፡ ከዚህ በፊት አይቼው የማላውቀው አይነት እንግዳና ትልቅ ሰው መሰለኝ፡ በሌላ በኩል ደግሞ
ሰውነቴን ለመሸፈን ብንቀሳቀስ ለማየት የተራበውን ነገር የምነጥቀው ይመስል
የደከመው፣ የፈዘዘና ግራ የተጋባ ይመስል ነበር።
እዚያው እንደተገተረ ሰአቱም የቆመ ይመስል ነበር። እኔም አይኖቹ ከኋላ መስታወት ውስጥ የሚያንፀባርቀውን ምስል በውስጣቸው ለማስቀረት ሲሞክሩ
ስመለከት እያመነታሁ “ክሪስ እባክህ ሂድ” አልኩት።
የሰማኝ አይመስልም ዝም ብሎ አፍጥጠጧል በጣም አፈርኩ ብብቴ ስር እርጥበት ተሰማኝ፡፡ ልቤም እንግዳ በሆነ ሁኔታ
መምታት ጀመረ፡ እጁን ስኳር የሚቀመጥበት ዕቃ ውስጥ ሲከት እንደተያዘ ህፃን ልጅ የሆንኩ መሰለኝ፡ ይሁንና አስተያየቱና አይኖቹ ወደ ህይወት
መለሱኝና ልቤ በሚያስፈራ ሁኔታ በከባዱ መምታት ጀመረ፡ በፍርሀት
ተሞላሁ: ለምንድነው የፈራሁት? ክሪስ እኮ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ የምር የሆነ እፍረት ተሰማኝ፡ ከዚያ ፈጠን ብዬ ያወለቅኩትን
ቀሚሴን ብድግ አደረግኩ: በዚህ ራሴን መከለልና እንዲሄድ መንገር እችላለሁ።
“ተይ” አለኝ፡ ቀሚሱን በእጄ እንደያዝኩ
“አንተኮ…” ተንተባተብኩ የበለጠ ተንቀጠቀጥኩ፡
“አውቃለሁ ማየት እንደሌለብኝ፡ ግን ደግሞ በጣም ቆንጆ ነሽ፡ ከዚህ በፊት አይቼሽ የማውቅ ሁሉ አልመሰለኝም: አብሬሽ ውዬ እያደርኩ እንዴት እንደዚህ ቆንጆ ሆነሽ ስታድጊ አላስተዋልኩም?"
እሱን ከመመልከትና በአይኖቼ ከመለመን በቀር እንደዚህ አይነት ጥያቄ እንዴት ይመለሳል? ይሄኔ ከኋላዬ በበሩ የቁልፍ ማስገቢያ መክፈቻ ቁልፉ ሲገባ ሰማሁ። አያትየው! ከመግባቷ በፊት በፍጥነት ቀሚሴን በጭንቅላቴ
አጥልቄ ወደታች ጎተትኩት። አምላኬ! እጅጌውን ማግኘት አልቻልኩም ጭንቅላቴ በቀሚሱ ተሸፍኖ ሌላው ሰውነቴ ግን እርቃን ሆኖ ነበር። እናም አያትየው አጠገቤ ነች! ላያት ባልችልም ግን ተሰምቶኛል!
በመጨረሻ እንደምንም እጅጌውን አስገባሁና ቀሚሴን ወደታች ሳብኩት። ነገር ግን እነዚያ ግራጫ ድንጋይ አይኖቿ ውስጥ እርቃኔን በደንብ እንደተመለከተችኝ
አይቻለሁ አይኖቿን ከእኔ ላይ አንስታ ክሪስን ዘልቆ የሚወጋ በሚመስል አይነት አፈጠጠችበት፡ እንደፈዘዘ ነው። “በመጨረሻ ያዝኳችሁ! ፈጠነም ዘገየም እንደምይዛችሁ አውቅ ነበር!” አለች:
ይህ ልክ ከቅዠቶቼ እንደ አንዱ ነው... ልብስ ሳልለብስ በአያትየውና በእግዚአብሔር ፊት
ክሪስ ከቆመበት ጥግ ወጣና መልስ ለመስጠት ወደፊት ተራመደ። “ያዝሽን?
ምንድነው የያዝሽው? ምንም:”
ምንም...
ምንም...
ምንም...
የሚያስተጋባ ድምፅ፡፡ በእሷ አይን ግን ሁሉንም ነገር ስናደርግ ይዛናለች።

👍39❤1
#ጠላፊዎቹ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#በኬንፎሌት
፡
፡
#ትርጉም_በወንዳየሁ_ንጉሴ
በተቃራኒው ጦርነት
ወደ ተዘፈቀች አገር መመለሱ ራሱ አንድ ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው፡.... እዚህ ነገር ውስጥ በመጀመሪያ ደረጃ ለምን ገባሁ? አለች ልቧ
እየተሰበረ ሁን ለመጸጸት ጊዜ የለም፡ አንዴ ስለወሰንኩ ወደ ኋላ
የምልበት ነገር የለም፡፡ የተተፋ ምራቅ ተመልሶ አይዋጥም አለች መልሳ
በሆዷ ሀሳቧ አንድ ቦታ አልረጋ ብሏት፡
ማርክ እጇን ለቀም አድርጎ ሲይዝ እንዳይለቃት ፈራች፡፡ ‹አንድ ጊዜ ሃሳብሽን ለውጠሻል። አሁንም ደግመሽ መለወጥ ትችያለሽ›› አለ ለማሳመን፡፡
ከኔ ጋር አሜሪካ እንሂድና ላግባሽ፡፡ ልጆቻችንን ይዘን ባህር ዳር እንጫወታለን የምንወልዳቸው ልጆች ቴኒስ እየተጫወቱ፣ እየዋኙ ብስክሌት እየነዱ ያድጋሉ፡ ስንት ልጅ ነው መውለድ የምትፈልጊው?››
አሁን መወላወሉን አቁማለች፡፡ ‹‹ማርክ እያደረኩት ያለሁት ነገር ጥሩ አይደለም፡፡ ተመልሼ ወዳገሬ እሄዳለሁ›› አለች፡፡
ያለችውን የተቀበለ መሆኑን ተረዳች፡፡ ሁለቱም ሀዘን ገብቷቸውና የሚሰሩትን አጥተው ዓይን ላይን ይተያያሉ፡፡ የሚናገሩት ጠፍቷቸው ዝም
ዝም ብለዋል፡
ከዚያም መርቪን ቡና ቤት ውስጥ ዘው ብሎ ገባ፡፡
ዳያና ባሏ ፊቷ መጥቶ ድቅን ሲልባት ዓይኗን ማመን አቃታት፡ ልክ
አንድ የሆነ መንፈስ ፊት የቆመ ይመስል አፈጠጠችበት፡ እንዴት እዚህ ሊመጣ ቻለ? ሊሆን አይችልም
‹‹እዚህ ተገኘሽ አይደል!›› አለ መርቪን በተለመደው አስገምጋሚ ድምጹ
ዳያና ግራ ተጋባች፡፡ መርቪን እዚህ መገኘቱ አስደንቋታል፣ አስፈርቷታል፣ እፎይታ ሆኗታል፣ ቅሌት ውስጥም ከቷታል፡፡ ከሌላ ወንድ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዛ ባሏ ሲደርስባት በደመነፍስ እጇን ከማርክ እጅ መንጭቃ አላቀቀች
ማርክም ‹‹ምንድነው እሱ?›› ሲል ጠየቃት ነገሩ ስላልገባው፡
መርቪን ሁለት እጁን ወገቡ ላይ አድርጎ ፊታቸው ተገትሯል፡
‹‹ማነው ይሄ ፊታችን የተገተረው?›› ሲል ጠየቀ ማርክ፡፡
‹‹ባሌ መርቪን ነው›› አለች በደከመ ድምጽ፡
‹‹ወይ አምላኬ!›› አለ ማርክ፡
‹‹እንዴት እዚህ ልትመጣ ቻልክ መርቪን?›› ስትል ጠየቀች ዳያና የምንተ እፍረቷን፡፡
‹‹ብራሴ አይሮፕላን በርሬ መጣሁ›› አለ ቁርጥ ባለ የአነጋገር ባህሪው:
ቆዳ ጃኬት የለበሰ ሲሆን በእጁ የሞተር ሳይክል ነጂ ቆብ አንጠልጥሏል፡፡
‹‹ኧረ ለመሆኑ እዚህ መሆናችንን እንዴት አወቅህ?›› ስትል ጥያቄዋን
ደገመች፡፡
‹በጻፍሽልኝ ደብዳቤ አሜሪካ እንደምትሄጂ ገልጸሻል፡ ወደ አሜሪካ
የሚኬደው ደግሞ በሰማይ በራሪ ጀልባ ብቻ መሆኑ ይታወቃል›› አለ በድል
አድራጊነት፡፡
የሷን ዱካ ተከታትሎ የምትሄድበትን መንገድ ገምቶ እሷ ጋ በመድረሱ ደስ እንዳለው ከገጽታው ይነበባል፡ በራሱ አይሮፕላን በርሮ ሊደርስባቸው
እንደሚችል ፈጽሞ አልጠረጠረችም፡፡ በዚህ መንገድ ተከታትሎ ስለደረሰባት ደካማ ነኝ ስትል አሰበች፡፡
ከእነሱ ትይዩ ባለው
ወንበር ላይ ተቀመጠና
‹‹እስቲ ዊስኪ አምጪልኝ›› ሲል አዘዘ አስተናጋጇን፡፡
ማርክ ብርጭቆውን አንስቶ ባንዴ ሲጨልጥ ዳያና ታየዋለች::በመጀመሪያ መርቪንን ሲያየው ተርበትብቶ ነበር፡፡ በኋላ ግን መርቪን አምባጓሮ እንደማያነሳ ሲገነዘብ ተረጋጋ ሆኖም ወምበሩን ገፋ አደረገና ከዳያና ፈንጠር ብሎ ተቀመጠ፡፡ የሰው ሚስት እጅ እንደያዝ ባሏ ከተፍ ሲልበት ሳያፍር አልቀረም፡
ዳያና ድፍረት እንዲሰጣት ብላ ከአልኮሉ ተጎነጨች፡ መርቪን በጭንቀት ያያታል። ግራ መጋባቱንና መጎዳቱን ከፊቱ ስታይ ደረቱ ውስጥ
ተወሸቂ! ተወሸቂ! አላት፡፡ ከፊቱ ምን እንደሚጠብቀው ሳያውቅ እሷን ፍለጋ
አገር አቋርጦ መጥቷል፡፡ እጇን ሰዳ በማጽናናት ሁኔታ ክንዱን ያዝ አደረገችው፡፡
ሚስቱ በውሽማዋ ፊት ያዝ ስታደርገው መርቪን ማርክን በእፍረት አየት አደረገው፡፡ ዊስኪው ሲመጣለት አንስቶ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠው::
ማርክ በበኩሉ ዳያናን የሚያጣ መስሎት ወምበሩን ወደ እሷ አስጠጋ
ዳያና በሁኔታው ግራ ተጋባች፡፡ እንደዚህ አይነት ነገር ከዚህ በፊት
ገጥሟት አያውቅም:: ሁለቱም ሰዎች ይወዱዋታል ከሁለቱም ጋር ተኝታለች፡ ሁለቱም ይህን ያውቃሉ፡፡ በጣም አሳፋሪ፡፡ ሁለቱንም ማጽናናት ፈለገች፧ ሆኖም ፈራች፡፡ አሁን ወደ መከላከሉ አዘምብላለች። ከሁለቱም ራቅ ብላ ተቀመጠችና ‹‹መርቪን አንተን ልጎዳ ብዬ አይደለም እዚህ መዘዝ ውስጥ የገባሁት›› አለች
መርቪን ፊቱን ቅጭም አድርጎ ‹‹አምንሻለሁ›› አለ
‹‹ታምነኛለህ? የሆነውን ሁሉ ትቀበለዋለህ?›› አለች ዳያና፡፡
መርቪን ማርክ ላይ አፍጥጦ ነገር ለመፈለግ በሚመስል ሁኔታ
ተጠጋውና ውሽማሽ አሜሪካዊ ይመስላል፤ከአፍ የወደቀ ጥሬ!
የተመኘሺውን አግኘተሻል›› አለ፡፡
ማርክ አፈገፈገ፤ ምንም ቃል ሳይተነፍስ መርቪንን አፍጥጦ ያየዋል ማርክ ጠብ ፈላጊ አይነት ሰው አይደለም፡፡ ሁኔታው ግራ አጋብቶታል፡ ከዚህ በፊት ተገናኝተው ባያውቁም መርቪን ዋና ባላንጣው ነው፡፡ ማታ ማታ ዳያና አቅፋው የምትተኛው ሰው ማን ይሆን?› ሲል ራሱን ሲጠይቅ ከርሟል፡፡ አሁን ማን እንደሆነ አውቆታል። ከማርክ ጋር ሲተያይ መርቪን ስለማርክ ምንም የተጨነቀ አይመስልም፡፡
ዳያና ሁለቱን ባላንጣዎች ተመለከተቻቸው፡ ምንም የሚያመሳስላቸው ነገር የለም መርቪን ዘንካታ፣ ጠብ ያለሽ በዳቦ የሚል፣ ኮስታራና ነርቨስ ነው ማርክ
ደግሞ አጭር፣ ሽክ ያለ፣ ነቃ ያለና ስው ሲናገር ጆሮ የሚሰጥ ሰው ነው ማርክ
አንድ ቀን ይህን ታሪክ በኮመዲ ስራው ውስጥ አካቶ ሳያቀርበው አይቀርም ስትል ዳያና አሰበች፡
አይኖቿ እምባ አንቆርዝዘዋል፡ መሃረብ አውጥታ ንፍጧን ተናፈጠች
«ልክስክስ መሆኔን አውቄዋለሁ›› አለች፡
‹‹ልክስክስ!›› ሲል አሾፈ መርቪን ቃሉ አንሶበት፡፡ ‹‹በጣም የጅል ስራ
ዳያና ባሏ በተናገረው ተሸማቀቀች፡ ብዙ ጊዜ ስድቡ አፏን እንዳዘጋት
ነው፡፡ ዛሬ ግን ከስድብም በላይ ይገባታል፡፡
አስተናጋጇና ጥግ ተቀምጠው መጠጣቸውን የሚኮመኩሙት ሁለት
ሰዎች ሁሉን ነገር ጣጥለው ትእይንቱን በጉጉት ይመለከታሉ፤ ‹‹ምን ይከተል ይሆን?› እያሉ።
መርቪን አስተናጋጇን ጠራና ‹የኔ ቆንጆ ሳንድዊች ብታመጪልኝ›› ሲል አዘዛት እሷም ‹‹እሺ የኔ ጌታ›› አለችው በፍጹም ትህትና፡፡
አስተናጋጆች መርቪንን ይወዱታል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኑሮ እያስጠላኝ መጥቷል ትንሽ ደስታ አገኝ ብዬ ነው አሜሪካ ለመሄድ የወሰንኩት›› አለች ዳያና፡፡
"ትንሽ ደስታ አገኝ ብዬ ነው ያልሽው! አሜሪካ ጓደኛ የለሽ፣ ዘመድ የለሽ፣ ቤት የለሽ. . .አዕምሮሽ ማሰብ አቆመ እንዴ!›› አለ መርቪን፡፡
ዳያና መርቪን ስለደረሰላት አምላኳን ብታመሰግንም እንዳይጨክንባት
ፈርታለች ማርክ በእጁ ትከሻዋን ነካ አደረገና ‹‹ለምንድነው አሜሪካ ደስታ
የማታገኚው፧ እዚያ ለመሄድ ማሰብሽ ስህተት አይደለም›› አላት ድምጹን
ዝቅ አድርጎ፡፡
መርቪንን ከዚህ በላይ ማናደዱ አስፈርቷታል፡፡ ምናልባትም ትቷት
ተመልሶ ይሄድ ይሆናል፡ በማርክና በሉሉ ቤል ፊት ‹‹አልፈልግሽም›› ብሎ
ቢላት እንዴት እንደሚያበሳጫት መገመት አስቸጋሪ ነው፡፡ አያደርግም
አይባልም፡፡ መርቪን ተከትሏት ባይመጣ ጥሩ ነበር፡፡ ይህ ማለት ደግሞ
እዚሁ አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ ይኖርበታል፡፡ ከዚያም ብርጭቆዋን አነሳችና ከንፈሯን አስነክታ ‹‹ይህን መጠጥ አልፈልግም›› ብላ መልሳ አስቀመጠችው
በዚህ ጊዜ ማርክ ‹‹ሻይ ላምጣልሽ?›› አላት፡፡

👍20❤4🥰1
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ነበረ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
////
መቼስ የሀገራችን የሚካሄድ ትንሽም ሆነ ትላልቅ ዝግጅቶች ተሳስተው እንኳን ከመዝረክረክ አያመልጡም።እና ይጀመራል ከተባለበት ሰዓት 40 ደቂቃ አርፈደው ጀመሩ...ዝግጅቱ ከተጀመረ ከአንድ ሰአት በኃላ የሽልማቱ ፕሮግራም ተጀመረ ። እንደአጋጣሚ ሽልማቱ ከታችኛው ክፍል ነው የተጀመረው...
‹‹ አማካይ ውጤት 97.5 በማምጣት ከሁለተኛ-ለ ክፍል እንዲሁም ከአጠቃላዩ ሶስቱም የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች አንደኛ በመውጣት ልዩ ተሸላሚያችን ተአምር እዬብ ..››አካባቢው በጭብጨባ ተነጋ.. ቤተሰቦቼ ሁሉም ከተቀመጡበት ተነስተው አካባቢውን ቀወጡት..፡፡በስሜት ካሜራዬን ደቅኜ ወደፊት ተጠጋሁ .በተቻለኝ መጠን ልጄን በካሜራዬ ለማደን ሙከራዬን ቀጠልኩ...፡፡የእኔ ልዕልት እየተንሳፈፈች ወደመድረክ
እየቀረበች ነው...፡፡
እናትዬውና አክስቶቾ ሰፌድ የሚያካክል አይፓዳቸውን ቀስረው ከኃላ ተከተሏት...፡፡መድረክ ላይ ወጥታ ከክብር እንግዳው ሽልማቷን ስትቀበል ስመለከት እንባዬን ከመርገፍ ላግደው አልቻልኩም...የራስ ልጅ እንዲህ በክብር አደባባይ ላይ ብዙዎችን በአድናቆት ሲያስጨበጭብ ማየት ለአንድ ወላጅ ምን አይነት ልብን በደስታ የሚያጥለቀልቅ መባረክ እንደሆነ እድሉ የገጠመው ወላጅ ብቻ ነው የሚያውቀው።
እኔም በጊዜው እዚህ መድረክ ላይ እስኪሰለቸኝ ድረስ በተደጋጋሚ በመውጣት ተሸልሜበታለሁ...በዛን ወቅት ግን እቤተሠቧቼ አሁን እኔ የተሠማኝን አይነት ልዩ ስሜት እንደሚሰማቸው ገምቼ አላውቅም ነበር...፡፡ልጄ ሽልማቷን በአየር ላይ እያወዛወዘች ህዝብን አስጨበጨበች።ከዛ በእኔ አቅጣጫ ስትደርስ ሽልማቱን ባለበት አቆመችና ትኩር ብላ ወደእኔ ተመለከተች፤ እኔም በደስታ እጄን እስኪያመኝ በአየር ላይ አወናጨፍኩት..ከዛ ለሌላ ተሸላሚ መድረኩን ለቃ ስትወርድ እኔም ፈጠን ብዬ በፊት ወደነበኩበት ቦታ ተመለስኩ…፡፡
ዘመዶቾ ከበዋት ያውካካሉ እያንዳንዱ በየተራ አብረዋት ፎቶ ይነሳሉ…፡፡ቀናሁ… በጣም ቀናሁ…..እኔም ከመሀከላቸው መገኘት ነበረብኝ፡፡.ቁጭ አልኩና በሀሳብ ሰመጥኩ፡፡.አይኖቼ እንባ አግተዋል….፡፡ትንሽ ፊት ሚያሳየኝ ወይ ሚነካካኝ ነገር ባገኝ እዘረግፈዋለሁ….፡፡
አንድ ነገር ተከሻዬን ከኃላዬ ነካኝ…..ከሀሳብ ባነንኩና ዞር ስል ልጄ ነች…፡፡
‹‹አባዬ ተከተለኝ›› ብላ ብን ብላ ወደኃላ ሄደችና ከእኔ ጀርባ ባለ የመማሪያ ክፍል ግድግዳ ኮርነር ተጠመዘዘች፡፡ፊቴን ወደ ፊትለፊት ላኩ ፡፡ወደዘመዶቼ፡፡ በራሳቸው ነገር ተጠምደው ያውካካሉ.፡፡ፈጠን አልኩና ተንቀሳቀስኩ፡፡ ልጄ ወደሄደችበት በፍጥት ሄድኩ ፡፡እንደተጠመዝኩ አገኘኋት፡፡ እጄን ያዘችና በፈጣን እርምጃ ወደፊት መጓዝ ጀመረች.፡፡ዝምብዬ ተጎተትኩላት…፡፡ምን ልታደርግ እንደሆነ አልገባኝም…፡፡ክፍሉን አለፈችና ሌላ ጠባብ መንገድ ውስጥ ይዛኝ ገባች፡፡ጥቂት ተራመድንና በፅድና በአትክልት የደመቀ የት/ቤቱ መናፈሻ ውስጥ ገባን፡፡ ምትፈልግበት ቦታ ከደረሰች በኃላ አዲስ እንዳገኘችኝ ነገር ተጠመጠመችብኝ፡፡
‹‹እንዳያዩን ብዬ እኮ ነው እዚህ ይዤህ የመጣሁት››
‹‹አይፈልጉሽም?››
‹‹ቶሎ እመለሳለሁ… ሽንት ቤት ብያቸው ነው የመጣሁት››
‹‹የእኔ ብልጥ በጣም ነው የኮራሁብሽ….፡፡.በጣም ነው ያስደሰሽኝ ….፡፡እንቺ ይህቺ ያዘጋጀውልሽ ትንሽ ስጦታ ነች›አልኩና በሚያብረቀርቅ የስጦታ ወረቀት አምሮ የተጠቀለ እና በፔስታል ያለ ስጦታዬን ሰጣኋት..
‹‹አባዬ ምንድነው? ልክፈተው?››
‹አይ እቤት ብቻሽን ስትሆኚ ተከፍቺዋለሽ›
‹‹እሺ አበባዬ አመሰግናለሁ…በጣም አስደስተህኛል›ብላ ወደታች አስጎንብሳ ጉንጬን ሳመቺኝና
‹አባዬ ፎቶ እንነሳና ልሂዳ..›
‹‹እሺ …እሺ›› አልኩና የያዝኩትን ካሜራ በራሱ እንዲያነሳ አጀስት በማድረግ አንድ አምስት የሚሆኑ ፎቶዎች ተነሳን፡፡
‹‹አሁን ልሂድ አባዬ››
‹የእኔ ማር ሂጀ …አሁን እኔም ወደአዲስአባ ልመለስ…ማታ ብቻሽን ስትሆኚ ደውይልኝ››
‹‹እሺ አባዬ…ሌላ ጊዜም መጥተህ ታየኛለህ አይደል.?››
‹‹የእኔ ማር ከአሁን ወዲህ አንቺን ሳላይ ብዙ ጊዜ መቆየት ስለማልችል .አዎ መጥቼ አይሻለሁ›
አገላብጬ ሳምኳት.እሷም ሳመችኝና እንዳመጣጧ እየተሹለከለክች ብን ብላ ሄደች.፡፡እኔ እዛ መናፈሻ ውስጥ ለታሪክ ድምቀት የታነፀ በድን ሀውልት መስዬ ለረጅም ደቂቃዎች ቆምኩ፡፡ አሁን እንደቅድሙ የተንጠለጠለውን እንባዬን ገድቤ ማቆየት አልቻልኩም….ዝርግፍ ብሎ ሲንጠባጠብ እኔም ልክ እንደሌላ ሰው በትዝብት እያየሁት ነው፡፡ከዛ በኃላማ ወደዝግጅቱም አልተመለስኩም፡፡ ምን ላደርግ…?ሹልክ ብዬ ግቢውን ለቅቄ ወጣሁና ወደመናኸሪያ ነው ያመራሁት.፡፡ከዛ ቀጥታ ወደ አዲስአባዬ ፡፡
✨ይቀጥላል✨

👍99❤8🥰6😁5🔥2👏2👎1
#ባል_አስይዞ_ቁማር
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///
በእቅዷ መሰረት ኩሪፍቱ ይገኛሉ….ትናንትና ከመሸ ነው የገቡት፡፡ከጥዋቱ ሁለተ ሰዓት አካባቢ ሆኗል..መኝታውን ለቆ ተነስቶ ክፍል ውስጥ ሲንጎራደድ ከጀመረ 30 ደቂቃ ያህል አልፎታል አንዴ መታጠቢያ ቤት ይገባል…አንዴ ወደበረንዳ ይወጣል…እኔ እየሰማው ቢሆንም አንቅልፍ ውስጥ እንዳለ ሰው አድፍጣ ዝም….መታጠቢያ ቤት ሲገባ ፈጠን ብላ ተነሳችና ከቦርሳዋ ውስጥ መከታተያ ካሜራዋን በማውጣት ወንበር ላይ የተንጠለጠለው ጃኬቱ ላይ አንዳይታይ አድርጋ ኮሌታው አካባቢ አጣበቀችውና ቶሎ ብላ ወደመኝታዋ ተመለሰች …በስተመጨረሻ ትግስት አጥቶ ,..ፈራ ተባ እያለው ወደአልጋው ቀረበና ትከሻዋን ይዞ እየነቀቃት…..
‹‹ፍቅር ተኝተሸ ቀረሸ እኮ …በጣም እርቦኛል..ተነሽ ቁርስ እንብላ››አላት
‹‹ተወኝ በናትህ እንቅልፌን አልጠገብኩም…ጊፍቲን ቀስቅሳትና አብራችሁ ብሉ››
‹‹ተይ እንጂ ፍቅር..››
‹‹እየረበሽከኝ አኮ ነው..በፈጣሪ ተወኝ››ተነጫነጨችበት፡፡
‹‹እሺ.ስትነሺ ተቀላቀይን›› ብሎ ዘረጥ ዘረጥ እያለ ክፍሉን ለቆ ለመውጣት ወደበሩ መራመድ ጀመረ…ፍፁም ንቁ ሁና ከአንገቷ ቀና አለችና..
‹‹እንዴ?››አለችው፡፡
በሁኔታዋ ግራ በመጋባት‹‹ምነው ልጠብቅሽ ?ትመጪያለሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹አይ አልመጣም ግን የውጩን ቅዝቃዜ አታየውም እንዴ…?››
‹‹እና ምን ?
ተኝተን እንዋል?››
ምን ለማለት እንደፈለገች አልተገለፀለትም፡፡
‹‹አላልኩም..በኃላ ኩሪፍቱ ወስደሽ ብርድ አስመታሺኝ እያልክ ስትወቅሰኝ እንዳትከርም….ጃኬትህን ለብሰህ ውጣ››
‹‹አረ ተይ… እንዲህ ተመችቶኛል››
‹‹አይሆን …ነገርኩህ እኮ….››
‹‹አንቺ ደግሞ በሚሆነውማ በማይሆነውም መጨነቅ ታበዢዋለሽ…እኔ እኮ እስፖርተኛ ነኝ የምን በርድ ነው››እያለ በማጉረምረም ወደኃላ ተመልሶ ጃኬቱን ከተንጠለጠለበት ወንበር በማንሳት እየለበሰ ወጥቶ ሄደ…ፈገግ አለች…‹‹አይ ወንዶች ነገረ ሰራቸው እኮ የህፃን ነው..በቀላሉ የሚታለሉ ገራገር ፍጥሮች… ሲመጣባቸውም እንደዛው ደንባራ አውሬዎች ናቸው…›አለችና …ከተኛችበት ተስፈንጥራ በመነሳት ክፍሉን ከውስጥ ቆለፈችው…ከዛ ላፕቶፖን አወጣችና ከፈተችው.. በገዛ እጮኛዋ ደረት ላይ የሰካችውን ካሜራ ጋር የሚየገናኝውን አፕ ቁልፍ አበራችው…በዛን ሰከንድ አዲስአባ ቤቱ አልጋ ላይ ተኝቶ የሚገኘው የቃል ስልክ ድምፅ አሰማ …ፈጥኖ ተነሳና ልክ ልዩ እንዳደረገችው ላፕቶፑን አነሳና አበራ…ከፈተውና ልዩ የምታየውን ማየት ጀመረ….
አዎ መድህኒ እየሄደ ነው..ጊፍቲ የተኛችበት መኝታ ክፍል በረንዳ ላይ እየወጣ ነው..አንኳኳ፡፡በራፍ ተከፈተና ጊፍቲ ከውስጥ ወጣች…ለባብሳና ሜካፖን ተቀባብታ ዝንጥ ብላለች…
‹‹እንዲህ ነው ንቁ ሴት..››አለ መድህኔ
እንደመሽኮርም አለችና‹ያው ለስራ ለሊት አይደለ ተነስቼ ምዘጋጀው ልምድ ሆኖብኝ ነው››
‹‹አይ በጣም ጥሩ ነው…በይ ወደ ቁርስ እንሂድ››
‹‹ልዩስ?››
‹‹እሷ እንቅልፍ ይበልጥብኛል ብላ እምቢ አለች›
በራፉን እየቆለፈች‹‹ምነው ማታ አምሽታችሁ ነበር እንዴ?››አለችው
‹‹ማለት? ጎድተሀታል ወይ እያልሺኝ ነው?›ሲል ጥያቄዋን በሌላ ጥያቄ መለሰላት፡፡
ፊቷ ቀላ..‹እረ እኔ…ማለቴ..›ተንተባተበች፡፡
‹‹ግድ የለም ስቀልድ ነው ..እውነታው ግን ልዩ እንዲህ ነች…አንዳንዴ ቅምጥል የሀብታም ልጅ መሆን አጎጉል ያደርግሻል…›ወደቁርስ እየሄዱ ነው ልዩን የሚያሟት፡፡
ጥያቄ አስመስላ በውስጡ ግን አድናቆት እና ልብ ሚያሞቅ ቃል ጨምራበት፡፡‹‹አንተም እኮ የሀብታም ልጅ መሰልከኝ…ግን ይሄው በጥዋት ንቁ ሆነህ ተነስተሀል›› አለችው….
‹‹አይ…የእኔ ስሙ ብቻ ነው…አባቴ እንዲህ የዋዛ ሰው መስሎሻል…እቤት ውስጥ ከ12 ሰዓት በኃላ የአንድ አመት ህፃን እራሱ አይተኛም…እያንዳንዱ የቤቱ ልጅ የየራሱ የስራ ድርሻ አለው….አልጋችንን እናነጥፋለን….አትክልት ዉሀ እናጠጣለን…ግቢ እንጠርጋለን…ከዛ በኃላ ነው ልብሳችንን ቀይረን ቁርሳችንን በልተን ወደ ትምህርት ቤት የምንሄደው….ከዛም ስንመለሰ ተመሳሳይ የተግተለተለ ስራ ይጠብቀናል…. የሚገርመው ደግሞ ይሄን ሁሉ ስራ የምንሰራው እኮ መአት ሰራተኞችና የደረሱ የዘመድ ልጆች ጭምር እቤት ውስጥ እያሉ ነው››
‹‹እና አሁን አንደዛ በመሆኑ እያማረርክ እንዳይሆን?››
‹‹አይ ሙሉ በሙሉ እያማራርኩ አይደለም...የእሱ አስተዳደግ አሁን ስራ ወዳድና ውጤታማ እንድሆነ አደርጎኛል….ግን ደግሞ ልጅነቴን ልክ እንደልጅ ሆኜ አጣጥሜ ተጫውቼ ስላላደኩ አሁንም የሆነ ከፍት ይሰማኛል…መኪና እየነዳሁ በሆነ መንደር ውስጥ በማልፍበት ወቅት ልጆች መንገድ ዳር ተሰብስበው ብይ ሲጫወቱ ካየሁ ወርደህ አብርህችው ተጫወት የሚል ስሜት ይቀስፈኛል..ሌላው ይቀር ጭቃ እያቦኩ ግድብ የሚገድቡ ህፃናት ሳይ ውሰጤ ይቀናል እና አሁንም ያላደገ ህፃን በውስጤ ያለ ይመስለኛል፡፡››
‹‹እና አንተ ከልዩ ምትወልዳቸውን ልጆች እንዴት ለማሳደግ አሰብክ?››ብላ ጠየቀችው፡
በዚህ ጥያቄ ልዩን በጣም ነው ያስገረማት‹‹እኔ እንኳን አስቤ የማላውቀውን ገራሚ ጥያቄ ነው›በማት መልሱን ልትሰማ ቋመጠች…ይህ መገረም አዲስአባ ያለው ቃልም ተጋብቶበታል፡፡
ጊፍቲና መድሀኔ ይሄን በሚያወሩበት ጊዜ ፊት ለፊት ተቀምጠው የሚፈለጉትን ቁርስ ከተደረደረው ቢፌ ላይ ወስደው ቁርስ እየተመገብ ነው፡፡
‹‹ልጅቷ ግን ፀሀፊ ሳትሆን ጋዤጠኛ ነው የምትመስለው፡፡ምን ብሎ ይመስልስላት ይሆን›አለች ልዩ…መድህኔ የጎረሰውን አላምጦ ማውራት እስኪጀምር በጉጉት ትጠብቅ ነበር..
‹‹እንደእኔም ወግ አጥባቂ አስተዳደግ ሳይሆን እንደልዩም መረን የለቀቀ ስንፍና የተጫጫነው ሳይሆን በመካከል ባላ ዘመናዊ አስተዳደግ እንዲያድጉልኝ ነው ምፈልገው››ሲል መለሰላት፡፡
ከትከት ብላ ሳቀች‹‹መረን የለቀቀ›› ስላለኝ የተደሰተች ይመስላል፡፡
‹‹ግን ስንት ልጅ ምትውልደ ይምስልሀል?›
‹‹እኔማ ስድስት ልጆች ብንወልድ ደስ ይለኛል…ግን ከማን?››
በዚህ መልሱ ፊት ለፊት ተቀምጣ ምታዳምጠው ጊፍቲ ብቻም ሳትሆን ከጀርባ ሆነው በሚስጠጥር የሚከታተሎቸው ልዩና ቃልም ጭምር ናቸው የደነገጡት
‹‹እንዴት ከማ…?ከሚስትህ ነዋ..›ጊፍቲ በገረሜታ ተሞልታ ጠየቀችው፡
‹‹ከሚስትህ ማለት ከልዩ?››
‹‹እንዴ ግራ አጋባሀኝ እኮ…ሌላ ሚስት አለህ እንዴ?››
እሱማ የለኝም...ልዩን ሳስባት ግን አንድ ልጅ እንኳን በስርአቱ አምጣ መውለድ የምትችል አይመስለኝም…ምግቧን እንኳን በእጆቾ ጠቅልላ መብላት የሚከብዳት እና በአጉራሽ የምትመገብ ቅንጡ .ልጅ ነች፡፡ታዲያ ልጅን የሚያህል ነገር አርግዛ…. ለዛውም ዘጠኝ ወር….ለዛውም ደጋግማ… ምን አልባት የመጀመሪያውን እንደወረት ልታደርገው ትችላለች.. ከዛ በኋላ ላሉት ግን እርግጠኛ ነኝ መሀፀን ተከራይልኝ ነው የምትለው››
ጊፍቲ ከት ብላ ሳቀች…‹‹ጓደኛዬንማ እንዲህ አትላትም…ይሄን ያህል ምነው?››መቆርቆሮ ሳይሆን የሆነ የሽሙጥና እሷ የተሻለች እንደሆነች በሚያረጋግጥ ስሜት ነው፡፡
እሱ ግን ቀጠለበት‹ባክሽ በጥልቀት ስለማታውቂያት ነው….የእሷ ጉዳይ ከምልሽም በላይ ነው….እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ነው ያማውቃት….ቤተሰብ ነን….አሁንም የማስተዳድረው ካማፓኒ የሁለታችን ቤተሰቦች በጋራ የመሰረቱት ነው››

👍70❤12😁4👏3
#ታምራተ_ኬድሮን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
/
እዚህ አብሬያቸው ከምኖረው የሰው ልጆች የበለጠ እውቀትና የረቀቀ ጥበብ የሰጣችሁ እሱ መሆኑን ታማናለችሁ ወይ? .በመካከላችሁ ያለው ግንኙነትስ እንዴት ነው ?ማለቴ በእናንተ እና በእግዚያብሄር መካከል…አንድ ጊዜ ስለአንተ ከእማዬ የሰማሁትን ለአንድ ቄስ ብነግራቸው….እነሱ ከእግዚያብሄር ተጣልተው ወደምድር ተወርውረው የነበሩ የመላእክት ዘሮች ናቸው ብለው አስረዱኝ...ወደምድር መጥተው ከሰው ልጆች ጋር ተስማምተው እንዲኖሩ ቢፈቅድላቸውም.እነሱ ግን መላውን የሰው ልጅ በከሉት ..ሰላማዊውን ፍጡር ጦር መሳሪያ አሰራርና ጎራዴ አሞረረድ ከዛም አልፎ የጦርነት ጥበብ እና የዘረፋና ግድያ ስልቶችን በማስተማር እርስ በርስ አጫረሱት ..በስርዓትና ይኖር የነበረውን ግብረሰዶምና ሊዚቢያ አደረጉት..እግዚያብሄር በጥበብና በፍቅር በመፍጠር በምድር የበተናቸውን እንስሳትን አንዱን ከሌላው እያዳቀሉ አስፈሪና አጥፊ ፍጥረታትና መፍጠር ጀመሩ..የጥንቆላና የሞርት ጥበብን ለሰው ልጅ በማስተማር አእምሮውን በከሉት ከዛ አምላክ ተቆጣና የጥፋት ውሀ ላከ ..ምድርንም በውስጦ ያሉትን ከእነሱ ጋር የተባበሩትን ትምህርታቸውንና በጥባቸው የተደሙትን ሁሉ አጠፋ…የሰው ለጅና እንስሳቱ ለዘር እንዲሆን ጥንድ እየሆነ በኖህ መርከብ ተጠልሎ እንደተረፈ ሁሉ.አነሱም የተወሰኑት የረቀቀ ጥበባቸው በመጠቀም ምድርን ለቀው በመሰደድ በጥፋት ውሀው ሙሉ በሙሉ ከመጥፋት እራሳቸውን ያተረፉ ይመስለኛል ….
እንደምገምተው ከሆነ አሁን አባቴ የምትይውና በሌላ አለም እንደሚኖር ለእናትሽ የነገራት ፍጥረት ከእነሱ አንዱ ነው አሉኝ…..፡፡ከእግዚያብሄር ጋረ የሚያቀያይምሽና ሀይማኖትሽ የሚያስክድሽ ከይሲ ፍጥረት ስለሆነ ቢመጣ እንኳን እንዳትቀርቢው.በስመአብ፤ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በማለት ደጋግመሽ በማማተብ ከስርሽ አባሪው ብለው መከሩኝ ..አልተከራከርኮቸውም ምን አልባት ያሉት እውነት ሊሆን ይችላል ብዬ አሰብኩ፡፡እንኳን ሙለ በመሉ የእናንተ ዘር መሆነን ተችሎ ይቅርና እኔ እራሱ ያንተ ደም በውስጤ ስላለ በውስጤ የሚንቀለቀለው የክፋት ኃይልና የወሲብ ጥማት እኔ ነኝ የማውቀው፡፡ከቄሱ ጋር ያልተስማማሁበት አንድ ነገር ቢኖር ቢመጣ እንዳትቀርቢው ብለው ያሉኝን ነው..ወይ ብትመጣ እንዴት እንደምጠመጠምብህ ሳስበው እራሱ ውስጤ በደስታ ይነዝራል፡፡
ይቀልዳሉ እንዴ? ሴይጣንም ሆንክ እግዚያሄር አባቴ ነህ…መርጬ አይደለም ካንተ የተፈጠርኩት..
እና ለማለት የፈለኩት እውነትም ቄሱ ያሉኝ ነገር የእውነት ከሆነ በመጀመሪያ በእናንተና በእግዚያሄር መካከል የነበረውንም አለመጋባባት ምክንያትም የሚያስረዳኝ አካል አላገኘሁም…ስለዚህ ማን ጥፋተኛ ማን ትክክል እንደሆነ መወሰን አልችልም…ደግሞ እግዚያብሄር ይሳሳታል እንዴ?አቦ እኔ እንጃ …ለማኛውም እስከአሁን የዘበዘብኩትን ሁሉ እርሳውና ለእናቴ እባክህ ምትችለውን አድርግ…›ሀሳቧን ሳትቋጭ ዝናቡ ዣ ብሎ መርገፈ ጀመረ….በትላልቅ ዕድሜ ጠገብ ዛፎችና በርካታ ቁጥቆጦችና ሰርጎ የሚረግፍ በመሆኑ ዝናቡ ከላይ በሚረግፈው ልክ ሳይሆን በየቅርንጫፎቹ እየተሹለኮለከ በቅጠሎች ላይ የተንኳለለ ነበር እሷ ጋር ሚደርሰው፡፡ እሷ ግን ግድም አልነበራትም…..ቦታም ቀይራ ለመጠለል አልሞከረችም…. ልክ እዛ ደን ውስጥ ዛፎቹ ስር ተተክላ እንደበቀለች ታዳጊ ችግኝ.. በደስታ ቅርንጫፎቾንና መላ አካሏን ወዲህ ወዲያ እያዋወዘች የሚዘንበውን ዝናብ በፍቅር እንደምትመጥ አይነት እሷም ተመሳሳዩን ነበር ያደረገችው..
ከ20 ደቂቃ በኃላ ዝናቡ ቢያባራም እየተንኳለለ ከቅርንጫፎቹ ቅጠሎች የሚንጠባጠበው ውሀ ግን አልተቋረጠም ነበር….ንስሯ እንደአካሄዷ አካባቢውን እየደረማመሰ መጥቶ ከፊት ለፊቷ አረፈ፤በቅርንጫፎቹ ውስጥ እየሾለከ ሲመጣ አካሉ ላይ ካረፉበት የውሀ እንክበብሎች በስተቀር ሲሄድ እንደነበረው ፍፅም ደረቅ አካል ነው ያለው፡፡ያው ይሄ የእሱ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ንስሮች ፀጋ ነው፡ዝናብ ሲዘንብ ደመናውን ሰንጥቀው አልፈው ከበላዩ ይሆኑን ወደታች አዘቅዝቀው በትዝብት ያዩታል..ምድርና በውስጧ ያሉት ሌሎች ፍጥረቶች ሁሉ ግን በሰማይ የሚበሩትን ሌሎች እዋፍቶችም ሳይቀሩ ወደዱም አልወዱም ወይ መሸሸጊያ ዋሻ ይፈልጋሉ ወይ ደግሞ በዝናቡ ይቀጠቀጣሉ፡፡
‹‹እሺ የት ሄደህ መጣህ?››
እምሮውን ከፈተላት.የሄደበትን ቦታ ሳይሆን እናቷ የምትድንበትን ዘዴ ነው የነገራት፡፡መጀመሪያው መድሀኒት ጨካኝ ነፍስ ያላቸው…ከ7 ሰዎች በላይ የገደሉ የሶስት ሰዎችን አንገት ቆርጦ እናትትሽ ቤት ውስጥ መቅበር ነው›የሚል መልዕክት በእምሮዋ ፃፈላት፡
‹‹ምን እያልከኝ ነው….እኔ ሰው ልገድል ነው…?ለዛውም አስፈሪና ጭራቅ የሆኑ ሰዎችን?››
‹‹ለዚህ እኮ ነው….የእናትሽን ሞት በፀጋ ተቀበይ የምልሽ››ሲል በእምሮ መለሰላት፡፡
‹‹አንተ ከእናቴ ነጥለህ ብቻዬን ምን ልታደርገኝ አስበሀል….?ሀዘኔ ያስደስትሀል ማለት ነው..?››
እዕምሮውን በነጭ ቀለም ሞላው …እንዲህ የሚያደርገው ሲያዝንና በንግግሯ ወይም በድርጊቷ ሲበሳጭ እንደሆነ ታውቃለች፡››
‹‹ይቅርታ ላስከፋህ ፈልጌ አይደለም….በቃ አደርገዋለሁ…ሶስት ሰው ጭንቅላት አይደል፡፡ለዛውም የሶስት ጨካኝና ገዳይ የሆኑ ሰዎች ጭንቅላት… .አረ አደርገዋለሁ ደግሞ ለእናቴ››ስትል ፎከረች፡፡
‹‹እንደዛ ከሆነ በ15 ቀን ውስጥ ጭንቅላቱ ተገኝቶ መቀበር አለበት….ይሄ ጉዳይ በትክክል ከተፈፀመ እናትሽን ለአንድ አመት በህይወት ያቆያታል፡፡
‹‹ፈክቶና በተስፋ ተሞልቶ የነበረው ፊቷ በአንዴ ጨለመ››
‹‹ምን ማለት ነው…?እኔ ለእናቴ እኮ መቶ አመት ነው የምመኝላት….ከተቻለም ዘላለም እንድትኖር፡››
‹‹መጀመሪያ ይሄንን ማድረግ ነው የምትችይው ..ከዛ ደግሞ ሌላውን ዕድሜ እናትሽ እንድታገኝ ምን ማድረግ እንዳለብሽ እናወራለን›››
‹‹ለምን ያኔ ?አሁን አትነግረኝም…ምን ያሰደብቅሀል ?››
‹‹የመጀመሪያው ካልተሳካ ሁለተኛውን ማወቅሽ ምንም እርባን የለውም …..››ብሎ ፍቃዷን ሳይጠብቅ ከአካባቢው ለቆ በረረ…ሆዱ ባዶ ስለሆነ የሚበላ ነገር ለማደን ነው ወደ ደኑ በጥልቀት የገባው….እሷም እንዴት አድርጋ ጨካኝና ወንጀለኛ ሰዎችን ጭንቅላት በ3 ቀን ውስጥ ማግኘት እደምተችል እያሰላሰለች ወደቤቷ ጉዞዋን ቀጠለች፡፡
ንስሯ ግን ተከትሏት አልሄደም..በተቃራኒው ሰማዩን ሰንጥቆ በረረ…

👍109❤12😱12👎2🔥1😁1
#ትንግርት
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹዋቤ
ሁሴን ትንግርትን እንደያዘ ቤቱ ሲገባ የገጠመው ከገመተው በላይ የሆነ ዝግጅት ነው፡፡ ለወር ያህል የታሠበበት ይመስል ሁሉ
ነገር ደምቋል፡፡ ሳሎኑ በዲኮሬሽን አሸብርቋል፡፡
ቤቱ ውስጥ ያሉ ሠዎች የጎደሉ ነገሮችን ለሟሟላት ከወዲህ ወዲያ ውር ውር ይላሉ፡፡
የሳሎኑን በር ዘልቀው ወደ ውስጥ ከገቡ በኋላ ግን የቤቱ ድባብ ሙሉ በሙሉ ነበር የተቀየረው፡፡ ሁሉም በያለበት ደንዝዘው ቆሙ፡፡ ፎዚያ፣ ኤደን፣ ሠሎሞን፣ የሠለሞን ሁለት መንታ ልጆች፣ አንድ የጎረቤት አሮጊት፣ እቤቱ ውስጥ የጠበቁት ሠዎች ናቸው፡፡ ሁሉም ፈዞ እንደቆመ ሁሴን የትንግርትን እጆቿን ይዞ
እየጎተተ ወደ ሶፋው ወስዶ አስቀመጣትና ወደ መኝታ ክፍሉ አመራ፡፡
‹‹አልተሳካም ማለት ነው?›› ሠሎሞን ነበር ከደብረ ዘይት ጀምሮ አንደበቷን ተቆልፎ የደነዘዘችውን ትንግርትን የጠየቃት፡፡ሌሎችም መልሱን ለመስማት ወደ እሷ ተጠግተው ቆመዋል፡፡
‹‹ምን ነካችሁ? ምን ተፈጠረ?›› መልስ ስታጣ ዳግመኛ የጠየቀችው ፎዚያ ነች፡፡ከድንዛዜዋ ሳትወጣ ‹‹ባካችሁ ተውኝ እሱኑ ጠይቁት፤ እኔ ምንም አላውቅም፡፡››ብላ መለሰችላቸው፡፡
‹‹አብረሽው አልነበርሽ እንዴ?›› ኤደን ነች ጣልቃ የገባችው፡፡ ትንግርት ቀና ብላ አየቻት፡፡ እስከአሁን መኖሯን አላወቀችም ነበር፡፡
‹‹ነበርኩ.. ግን ለምን እራሱን አትጠይቁትም›› ተበሳጨች፡፡
‹‹ተዋት በቃ.... ለማንኛውም ተረጋጉ መጣሁ፡፡›› በማለት ወደ መኝታ ክፍል ፈራ ተባ እያለ አመራ፤ሰሎሞን፡፡ ዘልቆ ሲገባ ያልጠበቀው ነገር ነው ያየው፡፡ሁሴን በፈገግታ ተጥለቅልቆ.. ለብሶ የመጣውን ልብስ አውልቆ
ቡኒ ከለር ያለውን የጣሊያን ሱፉን እየለበሠ ነበር::
‹‹ምን እየተከናወነ ነው?›› ሠሎሞን በገረሜታ ጠየቀው፡፡
‹‹ሙሽራ አይደለሁ… እየተዘጋጀሁ ነዋ!!››
‹‹አግኝተሀታል ማለት ነው?››
<አግኝቻታለሁ ግን ይዣት አልመጣሁም .. አላናገርኳትም፤ እዛው ጥያት ነው የመጣሁት፡፡
‹‹አንተ ሠውዬ ጭራሽ ለይቶልሀል ማለት ነው?›› ይሄን ሁሉ ጊዜ ቁም ስቅላችንን ስታሳየን ከርመህ አንተም ይሄን ያህል ተሠቃይተህ ካገኘሀት በኋላ ጥያት መጣሁ ስትል ምን ለማለት ፈልገህ ነው?››
‹‹ባክህ አትነጫነጭ .. ድግሳችሁ አይከስርም አንድ እቅድ አለኝ ሂድና ንገራቸው.. ሁሉም ለእራት ዝግጁ ይሁኑ፤ አስር ደቂቃ አይፈጅብኝም መጣሁ፡፡››
‹‹ለነገሩ እውነትህን ነው... የለፋንበትን እራትማ መሬት ላይ ደፍተን አንሄድም፡፡ ሁለተኛ ግን ካንተ ጋር አብሮ የሚያብድ ሠው የምታገኝ አይምሰልህ፡፡ደግሞ ልጆቼን አንከርፍፌ መምጣቴ፡፡›› በማለት እየተበሳጨ ወደ ሳሎን ተመለሠ፡፡
ሁሉም መቀመጫቸውን ይዘው የእራት ድግሱን ለመቋደስ ሲዘጋጁ ሠዓቱ ሁለት ተኩል ሆኖ ነበር፡፡ እንዳንዱ ቤት ውስጥ ካሉት መጠጦች የሚስማማውን እየመረጠ ይዟል፡፡ የሁሴን ፊት በፈገግታ መጥለቅለቅ የቤቱን የቀድሞ ድባብ በተወሠነ ደረጃም ቢሆን አሻሽሎታል፡፡ ትንግርት ግን አሁንም እንደደነዘዘች ነው፡፡
ከጎኑ ብትቀመጥም ሩቅ ኪሎ ሜትሮች በሀሳብ ርቃ ሄዳለች፡፡ ፎዚያ ወደ እራት ዝግጅቱ ለማምራት ፈራ ተባ በምትልበት ቅጽበት ሁሴን እጁን በማጨብጨብ መናገር የሚፈልገው ነገር እንዳለ ሲናገር ሁሉም
በታላቅ ፀጥታ ውስጥ ገባ፡፡ ፎዚያም ክፍት ወንበር ፈልጋ ተቀመጠች፡፡ ሁሉም በአዕምሮአቸው የሚያጉላሉትን ጥያቄዎች መልስ ከንግግሩ ለማግኘት ጓጉቷል፡፡
‹‹ወደ እራት ፕሮግራሙ እንደዚህ በተጨናነቀና በታፈነ ድባብ እንድንገባ አልፈለኩም፡፡ በመጀመሪያ ኤደን ምን አልባት ጥሪዬን አትቀበይም ብዬ አስቤ ነበር ስለተገኘሽ በጣም ደስ ብሎኛል፡፡ መንታዎቹ ዕፀ - ህይወት እና ዕፀ - ፍቅርም ስለተገኛችሁ በጣም አስደስታችሁኛል፡፡ እናታችሁ ብትመጣም ደስ ይለኝ ነበር ግን ምንም አይደል…›› ንግግሩን ገታ አደረገና እጁን ወደ ኪሱ ከቶ አበባ እና ቀለበት ይዞ መጥቶ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠው፡፡
‹‹እንግዲህ የሦስት ቀን ተልዕኮዬን አጠናቅቄ መጥቻለሁ፤ እናንተም ይሄንን በማስመልከት በሞቀ ዝግጅት ተቀብላችሁኛል፡፡ ይሁን እንጂ አንድ የጠበቃችሁት ነገር ማለት የፈለጋችሁት ሠው ለማየት አልቻላችሁም፡፡ የዚህንም
ምክንያት እንዳብራራላችሁ የምትፈልጉ ይመስለኛል፡፡መቶ ፐርሰንት እርግጠኛ ባልሆንም ለሁለት ዓመታት በማይጨበጥ ፍቅር ያሠቃየችኝን ደራሲ ዛሬ ያገኘኋት መስሎኛል ፤ነገር ግን ላናግራት ወይንም በተስማማነው መሠረት ይሄንን እንቡጥ አበባ ላበረክትላት፤ ይሄንን ቀለበትም ላጠልቅላት አልቻልኩም፡፡ እንዲህ ስላችሁ የማትሆን ሴት ሆና ስላገኘኋት እንዳይመስላችሁ ፤እንዳውም ከጠበኳት በላይ ቆንጆ፤ ከአሠብኳት በላይ ውብ ነች፡፡ ጠይም የሆነ ኢትዮጵያዊ የቆዳ ቀለም፤ሞዴሊስት ለመሆን የሚያስችላት የሠውነት ቅርጽ፤ገና ያልተነካ እንቡጥ ወጣትነት፤በቃ አሟልቶ የፈጠራት የምትባል ዓይነት ነበረች፡፡››
‹‹እና መጨረሻው ምን ሆነ?›› ትዕግስት አጥታ ጣልቃ የገባችው ኤደን ነበረች፡፡ ከስምንት ወር በኋላ በአንድ ቤት ውስጥ ከእሱ ጋር ስትቀመጥ ዛሬ የመጀመሪያዋ ነው፡፡አሁንም ታፈቅረዋለች፤ግን በበፊቱ መልክ አይደለም፡፡ ከእሱ ጋር የነበራትን አብሮነት ሙሉ በሙሉ በጥሳዋለች፡፡ሌላ ሕይወት ሌላ የፍቅር መንገድ ውስጥ ገብታለች፡፡ እንዲያም ሆና ታፈቅረዋለች፡፡ስለምታፈቅረውም… ያፈቀራትን፤ለረጅም ጊዜ የተጎዳባትን፤ከእሷ ጋርም የተለያየባትን ልጅ አግኝቶ ጥሩ የፍቅር ስኬት ቢያጋጥመው በዚህን ወቅት ደስተኛ ትሆን ነበር፡፡ አሁን ግን ምኞቷ ሁሉ በመክሸፉ ግራ መጋባት ውስጥ ገብታለች፡፡
ሁሴን ንግግሩን ቀጠለ <<....መጨረሻም ሀሳቤን ቀየርኩ፡፡ ሳስበውና ውስጤን በጥልቀት ሳዳምጠው፤ ከእሷ በላይ ማጣት ማልፈልጋት፤ ከእሷ በላይ የማፈቅራት ልጅ ልቤ ውስጥ አገኘሁ፡፡››
‹‹ማነች?›› ከሦስት ሠው አፍ ነበር የወጣው፡፡
ሠሎሞን፣ ፎዚያ እና ኤደን፤ እንደተማከረ ሠው
በአንዴ አፋቸውን ከፈቱ፡፡ ትንግርት በመጠኑ
እንደመነቃቃት ብላ አይኖቿን አፍጣ
ታስተውለው ጀመር፡፡
ምን እየተካሄደ እንደሆነ ብዙም ያልገባቸው ከጎረቤት የተገኙት አሮጊትና መንታዎቹ የሠሎሞን ልጆች በዝምታ ይቁለጨለጫሉ፡፡
‹‹ማንነቷን ልነግራችሁ አይደል…፡፡›› አበባውን አነሳ ፊቱን ከጎኑ ወደ ተቀመጠችው ትንግርት አዞረ ...‹‹እነሆ ይሄ የሦስተኛና የመጨረሻ ዕድሌን የምሞክርበት የፍቅር መግለጫ አበባ ነው፡፡ ትንግርት አንቺን ከምስጢር በላይ እንደማፈቅርሽ ዛሬ በደንብ ነው የገባኝ፡፡ ዛሬውኑ ላገባሽ እፈልጋለሁ፤ እባክሽ አታሳፍሪኝ፡፡››
የቤቱ ሠው ሁሉ የሚካሄደውን ትዕይንት ማመን አልቻለም፡፡ አንደ ትንግርት ግን ሁሉም ነገር ቅዠት የሆነበት የለም፡፡ ሁሴን አበባውን እንድትቀበለው እጆቹን ለልመና እንደዘረጋ ነው፡፡ እሷ ግን መንቀሳቀስ አልቻለችም፤ ወንበሩን ወደ ኋላ አንፏቆ ክፍት ቦታ ካገኘ በኋላ በጉልበቱ ተንበረከከና አንገቱን በትህትና ወደ መሬት ደፍቶ ‹‹እባክሽ ተቀበይኝ፡፡›› አላት፡፡
‹‹ተቀበይው›› ሠሎሞን ነበር፡፡
<ተቀበይው ተቀበይው ሁሉም...» በመቀባበል ጮኹባት፡፡በደመነፍስ እጇን ዘርግታ ተቀበለችው፡፡ እቤቱ በጭብጨባ ደመቀ፡፡ በማስከተልም ጠረጴዛ ላይ ያለውን ቀለበት አንስቶ ጣቷ ላይ አጠለቀላት፡፡ዳግመኛ ደማቅ ጭብጨባ በቤቱ ተስተጋባ፡፡ የትንግር፦ ጉንጮች በእንባ ራሱ…፡፡ ቀስ ብላ አጠገቧ ያለውን ቦርሳዋን አነሳችና የጎን ኪሱን ከፈተችው፡፡ እጇን ሠደደችና የልብ ቅርፅ ኖሮት መሀከሉ የእሱ ስም የመጀመሪያ ፊደል ያለበት ሀብል መዛ አወጣችና አንገቱ ላይ አጠለቀችለት፡፡ አሁን ደግሞ ግራ

👍107❤14👎2👏1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ዛሬ ላይ…አሁን
ሳባ ከሰመጠችበት የአመታት ትዝታ ወጥታ…ወዳለችበት ስትመለስ ከታላቅ መገረም ጋር ነው፡፡በዛን ወቅት በዛን ለሊት በወሲብ የረካችውን እርካታ በህይወቷ ሙሉ ድጋሚ አግኝታው አታውቅም..እናም ደግሞ ፈፅሞ አትዘነጋውም..እርግጥ ሴት ሆና የመጀመሪያ ቀን የወሲብ ገጠመኟን በመጥፎም ሆነ በክፉ የማታስታውስ የለችም…የእሷ ግን ከነጣዕምና ከነቃናው ዕድሜ ልኳን ይሄው እንዲህ ስብርብር ብላ አቅሏን አጥታ ደንዝዛ እንኳን ምንም የደበዘዘ ነገር የለም፡፡ እንደምንም ከተቀመጠችበት ተነስታ ለመቆም ስትሞክር እግሯ የእሷ መሆኑ እስኪጠፋት ድረስ ደንዝዞ ከቁጥጥሯ ውጭ ሆኗል ..እንደምንም ፈጠን አለችና የበረንዳውን ብረት በመያዝ ቆመች….ከድንዛዜዋ እስክትወጣ ከ5 ደቂቃ በላይ ወስደባት…
ትዝ ይላታል እዚህ ቦታ ስትቀመጥ ከለሊቱ 8 ሰዓት አካባቢ ነበር..አሁን ግን ነግቶ..ወፎች ግቢ ውስጥ ያሉ ሁለት ዛፎች ላይ ሰፍረው ጭጭጭ እያሉ መንፈስ የሚያንሰፈስፍ ሚስጥራዊ መዝሙር አየዘመሩ ነው…ግቢ ውስጥ ከወዲህ ወዲያ ስትንጎራድድ ዘበኛዋ ለኦሎምፒክ እንደሚዘጋጅ አትሌት በዛ ለሊት የስፖርት ቱታ ለብሶ ግቢው ውስጥ ባለ ከፍት ቦታ ስፖርት እየሰራ ነው….በርከት ላሉ ደቂቃዎች ቆማ ተመለከተችው…አንዴ ፑሻፕ ይሰራል፤ደግሞ ክብደት ያነሳል፤ደግሞ ቁጭ ብድግ ይላል፡፡
‹ታድለህ..››አለችና ወደውስጥ ገባች፡፡
…ቀጥታ ወደሻወር ቤት ነው ያመራችው…ሰውነቷን ታጠበች..ለመታጠብ ረጅም ሰዓት ነው የፈጀባት.. ምን አልባትም ከአንድ ሰዓት በላይ....ከዛ ልብሷን ቀየረች..የተወሰነ ሜካፕ በመጠቀም ራሷን አሰማመረችና መድሀኒቷን ወደቦርሳዋ በማስገባት መኝታ ቤቷን ለቃ ለመውጣት ዝግጁ ስትሆን ሁለት ሰዓት ከሩብ ሆኖ ነበር….ቀጥታ ወደሆስፒታል ነው የምትሄደው…እርግጥ ለቀጠሮዋ ሶስት ቀን ይቀረዋል..ግን ደግሞ ላለፉት ሶስት ቀን መድሀኒቷን አልተጠቀመችም..ያንን ለሀኪሟ ተናግራ መፍትሄ የሚለውን እንዲነግራት ትፈልጋለች….እርግጥ ልታገኘው የፈለገችው ለዚህ ብቻ አይደለም…ከእሱ ጋር መነጋገር ሰላም እንዲሰማት ስለሚያደርጋት ነው፡፡ ፎቅ ላይ ካለው መኝታ ቤቷ ወደሳሎን ስትወርድ ፊት ለፊቷ ባለው የምግብ ጠረጴዛ በምግብ ተሞልቶ አየች…ግራ ገባት…ሞባይሏን አወጣችና ሰዓቷን መልሳ አየችው 2.20 ነው፡፡ተመላላሽ ሰራተኛዋ ከ3 ሰዓት በፊት ስትገባ አይታት አታውቅም …እንደዛ አይነት ንግግርም የላቸውም
‹‹…ታዲያ አንዴት ዛሬ ልታደርገው ቻለች?››በማለት ቦርሳዋን ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠችና ወደኪችን ስትሄድ፤ባዶ ነው፡፡ ኪችኑ ሁሉ ነገር ፅድት ብሎ እቃዎች ሁሉ በየቦታቸው ስለተቀመጡ ከነጋ ሰው የገባበትም አይመስልም፡፡ ቀጥታ ወደምግቡ ተመለሰችና እየጣፈጣት የምትፈልገውን ያህል ከተመገበች በኃላ እጇን ተጣጥባ ቦርሳዋን ይዛ ወጣችና ቀጥታ ወደ መኪናዋ ስትሄድ ትናንት ከአሰላ ስትመጣ አልብሷት የነበረውን አቧራና ጭቃ ከላዩ ላይ ተወግዶ ፏ ብላ ፀድታለች፡፡ደስ አላት፡፡ገባችና ቁልፏን አሽከርክራ ሞተሩን ማሞቅ ጀመረች በዚህን ጊዜ የመኪናውን ድምፅ ሰምቶ ከዘበኛ ቤት ወጣና በራፉን ከፈተላት..መኪናዋን አንቀሳቀሰችና .ስሩ.ስትደርስ.አቆመች አንገቷን በመስኮት አወጣችና..‹‹መኪናዬን ንፁህ ስላደረክልኝ አመሰግናለሁ››አለችው
‹‹አረ ችግር የለውም…ቁጭ ከምል ብዬ ነው››
‹‹ሳሎን ቁርስ አለልህ.. ግባና ብላ ››
‹‹እሺ እበላለሁ››
‹‹እሺ ቻው›ብላ መኪናዋን አንቀሳቀሰችና ወዲያው መልሳ አቆመችው፡፡
‹‹ይቅርታ ስምህ አይያዝልኝም››
‹‹ቀናው››
‹‹ያልተለመደ ስም ነው…ቆይ አለም መጥታ ነበረ አይደል.?ታዲያ.የት ሄደች?››
‹‹መቼ? ዛሬ ከሆነ አልመጣችም፡፡››
‹‹ታዲያ ቁርሱን ማን ነው የሰራው?››አቀረቀረ…
‹‹ምነው መልስ የለህም?››ኮስተርተር ብላ ጠየቀችው፡፡
‹‹ምነው የማይሆን ነገር ሰራሁ እንዴ?››
የምትመልሰው ግራ ገባት ‹‹እኔ እንጃ.. ለማንኛውም በጣም ይጣፍጣል›› አለችውና ከመገረም ውስጥ ሳትወጣ መኪናውን አስነስታ ተፈተለከች፡፡
ከዶክተሩ ጋር ተገናኝታ ፊት ለፊት ተቀምጣለች…የሆነውን ነገር ሁሉ ነግራው ምክር እየሰጣት ነው፡፡
ይሄውልሽ ሳባ .ይሄንን ነገር ሲሪዬስ አድርገሽ እንድትወስጂው እፈልጋለሁ››
‹‹እሺ ዶ/ር ሁለተኛ አይለመደኝም፡፡››
‹‹ቤተሰቦችሽም ሊረዱሽ ይገባል፡፡››
‹‹ቤተሰቦቼ አሰላ ነው ያሉት‹‹ያንን ማድረግ አይችሉም፡፡››
‹‹ሳባ ከእኔ በተጨማሪ በቅርብሽ ሆኖ ሁሉን ነገር እየተከታተለ ሊረዳሽ የሚችል ሰው ማግኘት አለብሽ.››.
‹‹አይ ዶ/ር እንዲሁ እድሜ ለመግፋት ካልሆነ በስተቀር የእኔ ነገር ተስፋ.ያለው........ .አይመስለኝም…በአጠቃላይ.መኖርደክሞኛል..መጨረሻ.መዳረሻዬ.
መቃብር ቤት፤
ከዛ ካመለጥኩ በሰንሰለት ታስሬ አማኑኤል…በጣም እድለኛ ከሆንኩ ደግሞ እስር ቤት የሚሆን ይመስለኛል››
‹‹ከእንደዚህ አይነት አሉታዊ አስተሳሰቦች ራስሽን ማራቅ አለብሽ..አሉታዊ ሀሳብ ቀስ በቀስ በመጀመሪያ በአዕምሯችን ስሩን እየሰደደ ይሄዳል.. ከዛ የምናስብበትን መንገድ ይቀይራል፡፡ እኛ ደግሞ የሀሳባችን ውጤት ስለሆንን በሂደት በአላስፈላጊ መንገድ እንድንጓዝ እየቀየረን ይሄዳል፡፡ ቀድሞ የማናውቀው አይነት ሰው ከውስጣችን ይበቅላል››
‹‹.ይበቅላል አልክ…በቅሎ አድጓል እኮ…ብቻ ዶ/ር ሁሉ ነገር ይጨንቃል››
እኮ የምልሽ እሱን ነው.መድሀኒቱ ብቻውን ብዙም ውጤታማ አይሆንም፤ አንቺም በተስፋ መታገል አለብሽ፡፡ ከዚህ ውጥረት በአፋጣኝ እራስሽን ማላቀቅ አለብሽ ምን መሰለሽ ውጥረት ከቁጥጥራችን ውጭ ከወጣ ወደ ስራ ህይወታችን ይሄድና ስህተት የሆነ ውሳኔ እንድንወስን ያደርገናል፡፡ ከዛም አልፎ የቤተሰብ ህይወታችን ላይ ጫና ያሳድራል፡፡ውጥረት ያመጣብንን ችግር በወቅቱና በሰዓቱ ካልተቆጣጠርነው እዕምሯችንና አካላችንን ይቆጣጠርና የጤና ችግር ከማስከተሉም በላይ አካላዊ በሽታና አእምሮአዊ በሽታ ያስከትልብናል..በሂደትም ለባህሪ ለውጥ ይዳርገናል፡፡ የባህሪ ለውጥ ማለት ደግሞ የምናስብበት መንገድ ነገሮችን የምናይበትና የምንመዝንበት ሚዛን እየተቀየረና እየተዛባ ይሄዳል ማለት ነው፡፡ ያ ደግሞ በውሳኔያችን ላይ ለውጥ ያመጣል፡፡ በስተመጨረሻም የሕይወታችንን መስመር ሙሉ ለሙሉ የመቀየር አቅም ይኖረዋል፡፡ስለዚህ በአእምሮችን ላይ የሚከሰት ማንኛውንም ውጥረት በጊዜና በሰአቱ ማከም ይጠበቅብናል፡፡ ለዛ ነው የምጨቀጭቅሽ››
‹‹እሺ ዶ/ር እሞክራለሁ..ማለቴ ለጤናዬ እፋለማለሁ››
አዎ እንደዛ ማድረግ አለብሽ…አየሽ ራሳችን ከውስጣችን ጋር ስናጣምር ህይወት ምን ያህል ንፁህ በደስታ የተሞላችና ህመም አልባ እንደሆነች እንረዳለን፡፡ለአዕምሯችን ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ብናቀርብለት ያለማቅማማት መልስ ይሰጠናል፡፡ ጥያቄው ብዛትም ሆነ ክብደት ችግር የለውም ብቻ ሁሌ መልስ አያጣም፡፡ ችግሩ መልሱ ትክክል ሊሆንም ላይሆንም ይችላል..ስለዚህ እኛም ራሳችንን የምንጠይቅበት ሆነ ሌሎች የሚጠይቁንን ጥያቄዎች መጠንቀቅ አለብን፡፡ ምክንያቱም አዕምሯችን የሚሰጠን መልስ በምናቀርብለት የጥያቄ ይዘት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ለምሳሌ ይህች ሀገር ወዴት እየሄደች ነው? የሚል ጥያቄ ለአዕምሯችን ቢቀርብለት ቀድሞ የሚመጣለት መልስ ስለጦርነት፤ስለኑሮ ውድነትና፤መሰል ነገሮች ነው...መልሱም በዛ ዙሪያ የሚሽከረከር ነው የሚሆነው፡፡ በተለየ መንገድ ደግሞ ኢትዬጵያ ላንቺ ምንሽ ነች? ቢሆን ጥያቄው...ስለውበቷ፤ ስለ

👍56❤7😁2
#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)፡
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ሁለቱም እርቃናቸውን ተኝተው ፊት ለፊት እየተያዩ ማውራት ቀጠሉ?
"የሆነ ነገር ትጠይቀኛለህ ብዬ ስጠብቅ ነበር ግን ማድረግ አልቻልክም"አለችው
እንደመደንገጥ ብሎ ፀጉሯን በእጆቹ እየላገ"ምንድነው የእኔ ፍቅር?ምን ልጠይቅሽ?"
"ከዚህ በፊት የዛሬ ሳምንት አካባቢ ከዚህ ደን በሰላም ከወጣን ደግመህ ጠይቀኝ ብዬህ ነበር...አሁን ሳስበው ግን ጥያቄውን ሙሉ በሙሉ ረስተኸዋል…በፊትም ከልብህ አልነበረም የጠየቅከኝ ማለት ነው "አለች እንደማኩረፍ ብላ።
"አንቺ በጣም ተሳስተሻል...ያንን ጥያቄ ለደቂቃም ረስቼው አላውቅም..አሁን ደግሜ ብጠይቃትና እምቢ ብትለኝ እንዴት ነው የምቋቋመው?"ብዬ ሰግቼ ነበር ...
"እና "
"እናማ...አንቺ ቆንጆ ጠይም ወጣት ወደሀገርሽ ይዘሽኝ ብትበሪ ምን ይመስልሻል?"
"ይዞ መሄድን ይዤህ ሄዳለው።ግን ልመለስ ብትል ማንም አይሰማህም"
"ይሁን ተስማምቼያለው...አልፎ..አልፎ ሀገሬ ሲናፍቀኝ ይዘሽኝ መጥተሽ እንደምታሳይኝ እተማመናለው።››
"እሱን ፀባይህ እየታየ የሚወሰን ነው።"ብላ ከመኝታዋ ተነሳችና እርቃን ገላዋን ለእሱ እይታ አጋልጣ ወረደች..ቀጥታ ወደሰካችው ስልኳ ሄደችና ነቀለችው።ተመልሳ መጣችና አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ ብላ ወደሀገር ቤት ወንድሟ ጋር ደወለች.፡፡ከሰከንዶች በኃላ የወንሟን ተወዳጅ ድምፅ በጆሮዋ ሲንቆረቆር ልትሰማ እንደሆነ ስታስብ ሰውነቷን ሌላ ዙር ሙቀት ወረራት...ግን እንዳሰበችው የወንድሟ ሞባይል ሊጠራ አልቻለም...ደግማ ሞከረች።በሁለተኛ ቁጥሩም ሞከረች ተመሳሳይ ነው።
"ብሽቅ...በዚህ ቀን ሞባይሉን ያጠፍል"ተበሳጨች።ሌላ ተለዋጭ ሀሳብ መጣላት።የምስራቅ ቁጥርን ከሞባይሏ ፈለገችና ደወለች።ልክ እንደወንድሟ ስልክ የእሷም አይሰራም።
‹‹የሰዎቹ ስልክ ሁሉ አይሰራም"በተኛበት አይኖቹን እያቁለጨለጨ እየተመለከታት ለነበረው ካርሎስ ነገረችው። ከተኛበት ተነሳና ከአልጋው ወርዶ አልጋ ልብሱን ከአልጋው ላይ ገፎ እርቃን ሰውነቷን በማልበስ"አይዞሽ ተረጋጊ...አህጉር አቋራጭ ጥሪ እኮ ነው እያደረግሽ ያለሽው፡፡ ኔትወርኩ ችግር ሊኖርበት ይችላል...አሁን ባይሆን ጥዋት ሲነጋ ሊሰራ ይችላል...ካልሆነም ሌላ ዘዴ እንፈልጋለን።››ሲል ሊያፅናናት ሞከረ፡፡
ሌላ ዘዴ ሲላት በአእምሮዋ ተለዋጭ ዘዴ ብልጭ አለባት፡፡ ለወንድሞ...ነፃ እንደወጣችና ከቀናት በኃላ ወደሀገሯ እንደምትመለስ ልትፅፍለት ወሰነችና ኢሜሏን ከፈተች። ከአለም እይታ በተሰወረችባቸው 20 በሚሆኑ ቀናቶች በርካታ ኢሜሎች ተልከውላታል።አብዛኛዎቹ ከወንድሟ.. ከዛም ከመስሪያ ቤቷ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ ግን የተላከላት ከማትጠብቀው ሰው ነበር… በድንጋጤ ከተቀመጠችበት ተነስታ ስትቆም ካርሎስ አልብሷት የነበረው አልጋ ልብስ ከላዩ ላይ ወደቀና እርቃኗን ቀረች...
‹‹ምንድነው ፍቅር...?››
‹‹ሰውዬው ተደጋጋሚ መልዕክት ልኮልኛል?››
ግራ ገባው"የትኛው ሰውዬ?"
"ሀለቃህ...ዳግላስ?"
ከመደንገጡ የተነሳ ተንደርድሮ ወደእሷ ቀረበና ሞባይሉን ከእጇ ተቀበላትና ኢሜሉን ተራ በተራ እየከፈተ አየ...ከዛ በድንጋጤ እግሮቹ ዝሎ ወለሉ ላይ ተዘረፈጠ..ኑሀሚም ድንጋጤው ክፍኛ አዝሏት ስሩ ተንበረከከች፡፡
ስልኩን ተቀብላው ኢሜሉን በማንበብ የሆነውን ለመረዳት የሚያስችል ጥንካሬ ከውስጧ ማግኘት አልቻለችም።ሽው እያለ መጥቶ እርቃን ሰውነቷን የሚገርፋት እርጥብ አየር ነፍሷን ጭምር እያቀዘቀዘው ነው።
"ምንድነው የሆነው?"ጥንካሬዋን አሰባስባ የሆነውን ሁሉ ከእሱ አንደበት ለመስማት ጠየቀችው።ስልኩን መልሶ ከፈተና በኢሜሏ የተላከለትን ፎቶዎች አወጣና"ወንድምሽ...እዚህ መጥቷል"አላት
"ወንድሜ ?እዚህ እንዴት?››ካርሎስ የሚያወራው ነገር ምንም እየገባት አይደለም፡፡
"አላውቅም ግን..እይ ተመልከቺ ዳግላስ እጅ ነው ያለው...ፎቶውን ወደእሷ አቅርቦ እያሳያት"ይሄውልሽ...ይሄንን ቦታ በደንብ አውቀዋለው፡፡ ማንም ሊደርሶበት የማይችለው የዳግላስ ምሽግ የሆነው ሳንቹዋሪ ነው።››
ፎቶውን ተቀበለችና በፍዘት ትመለከተው ጀመር...ዥውውውው አለባትና ቀድሞ ስልኩ ከእጇ ላይ ተንሸራቶ ወደቀባት...ፈጠን ብሎ ሊደግፍት ሲንቀሳቀስ ቀድማ ወደኃላዋ እራሷን ስታ ተዘረረች...በፋጥነት ተነሳና አፋፍሶ አቅፎ አልጋ ላይ አስተኛት።ልብስ ደራርቦ አለበሳትና ከድንጋጤ እስክትወጣ መጠበቅ ጀመረ።
###
ኮሎምቢያ/አማዞ ደን ማህፀን ውስጥ
ካርሎስ በተሰበረ ልብ ምርጫ አልባ ሆኖ በህይወቱ የመጨረሻውን ፍቅር ያፈቀራትን ይቺን ጠይም ኢትዬጵያዊ ሴት ሳይወድ በግድ ከማናአስ ወደ ቲጎና በፕሌን… ከዛ ደግሞ በጀልበ ከብራዚል ድንበር ወደኮሎምቢያ አሻግሯትና ላቲሲያ ከተማ ጫፍ ድረስ ሸኛት፡ከዛ እሱ ከዳግላስ የንፍስ ጠላቶች ጋር ለመደራደር ደቡብ ምእራብ ኮሎምቢያ ድንበር ተጠግታ ወደምትገኘው የቪንዚዎላዋ ሳና-ካርሎስ ከተማ ጉዞ ጀመረ …፡፡
ይህቺን ያፈቀራትን አፍሪካዊ ሴት ማዳን ማለት እራሱን ማዳን ማለት ነው፡፡ሰው እራሱን ለማዳን ደግሞ ምንም ያደርጋል፡፡ዳግላስን ያገኙትን ማንኛውንም አጋጣሚ ተጠቅመው ሊያጠፉት የሚፈልጉ የቢዝነስ ተፎካካሪዎች እንዳሉት ያውቃል..እሱ ደግሞ ስለ ዳግላስ የቢዝነስ ሚስጥሮች ፤ መግቢያ መውጫውን ፤ድክመትና ጥንካሬውን በደንብ ያውቃል…አሁን የሚያገኛቸው ሰዎቹ ደግሞ ሃይልና ብር አላቸው….እነሱ እሱን አምነውት ከተቀበሉትና አብረውት ለመስራት ከወሰኑ ዳግላስን እስከወዲያኛው አስወግዶ ኑሀሚንና ወንድሟን ነፃ ለማውጣት የሰለለችው ቢሆን ተስፋ አለው፡፡ያ ተስፋ ካልተሳካ ነፍሱን እንደሚያስከፍለው ያውቃል…ቢሆንም ግድ የለውም…ያቺ የሰለለች ተስፋ ከመቶ አንድ ፐርሰንት ብትሆንም እንኳን ከመሞከር ወደኃላ አይልም..ለዛ ነው እሷን ወደዳግላስ ልኮ እሱ የዳግላስን ጠላቶች አግኝቶ ለመደራደር ጊዜ ሳያባክን ጉዞ የጀመረው፡፡
ኑሀሚ ካርሎስ እንደነገራት ላቲሲያ ከተማ በተቀመጠችበት ሆቴል ነው አንድ ሰዓት እንኳን ሰትቆይ የዳግላስ ሰዎች በቁጥጥር ስር ያዋሏት፡፡በመጀመሪያ እዛ ላቴሲያ ከከተማው ወጣ ብሎ አማዞን ወንዝ ደር ካለ ወደ አንድ ሰዋራ ቤት ነበር የወሰዷት፡፡ለአራት ቃናት ያህል እዛው አስቀመጧት፡፡በየቀኑ የሚያስፈልጋትን ያህል ምግብ ፤ልብስ እና መጠጥ ያቀርቡላታል፡፡ግን ማንም ሊናግራት የሚደፍር ፤ብታናገራቸውም የሚመልስላት አልነበረም፡፡በየቀኑ ምግብ እና መጠጥ እንዲሁም የሚያስፈልጋትን ነገር የሚያመጡ ሁለት ሰዎች አሉ….መጥተው እቤቱ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠውላት ይሄዳሉ….ብታናግራቸው አይመልስላትም፡፡ጠባቂዎቾ እርስ በርስም ቁጥብ ቃላትን ሲለዋወጡ ብትሰማ እንኳን በማይገባት ቋንቋ ስለሆነ ምንም መረዳት የምትችለው ነገር አልነበረም ፡፡ይበልጥ ልትቆጣጠረው የሚከብዳት ጥልቅ ድባቴ ውስጥ እየገባች መጣች፡፡እሷ ካለችበት ቤት አስር ሜትር እርቃ ባለች ጎጆ አንድ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቀ ጎረምሳ ሁሌ ንቁ ሆኖ ሲጠብቃት ታየዋለች…ወደእሷ መጥቶ ለማውራት አይሞክርም…እሷም ወደእሱ ለመቀረብ ምንም ጥረት ኣላደረገችም፡፡ይህን ጠበቂ ወይ ጥላው ወይ ገድላው በቀላሉ ማምለጥ እንደምትች ታውቃለች…..ግን ያ አይደለም እቅዷ፡፡ አሁን ሂጂ አምልጪ የሚላት አዛኝ ሰው ቢኖር እራሱ እሺ ምትልበት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለችው፡፡አሁን የእሷ ጥረት ወደፊት ስምጥ ወደሆነው የአማዞን ደን ማህፀን ውስጥ ገብቶ ወንድሟን ማግኘት ነው…ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍላት ግድ የላትም፡፡እንደው ወንድሟንና ምስራቅን የማትረፍ እድሉ ባይኖራት እንኳን የዩትን መከራ አብራ አይታ የሚጎነጩትን

👍76❤13👏2
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በማግስቱ የናፈቀው ቢሮ የገባው አራት ሰዓት አካባቢ ነበር….የማታው ስካር አንጎበሩ ሙሉ በሙሉ አለቀቀውም…አሁንም ጭንቅላቱን እየወቀረው ነው፡፡ለፀሀፊው መምጣቱን
ስላልነገራት አልገባችም…ከፍቶ ገባና ቁጭ አለ ..የሚሰራው ስራ ስላልነበረ የሚያደርገው ነገር ግራ ገባው..ስልክ አውጥቶ ደወለ፡፡
‹‹እንዴት ነሽ…ለሊሴ?››
‹‹ደህና ነኝ ሰለሞን…እንዴት ነው ስራ?››
‹‹አሪፍ ነው..አሁን ተመልሼለሁ…ቢሮ ነው ያለሁት››
‹‹ውይ ለምን ሳትነግረኝ..ቀድሜ ገብቼ አፀዳድቼ ጠብቅህ ነበረ እኮ››
‹‹አይ ችግር የለውም..ቢሮው አሁንም ንፅና የተስተካከለ ነው››
‹‹አዎ እሱማ በሶስት ቀን አንዴ ከፍቼ አናፍሰዋለው….እና ስራህን ጨረስክ ማለት ነው?››
‹‹አይ አልጨረስኩም…በመሀል የሶስት ቀን እረፍት ስላለኝ ነው የመጣሁት…ለመሆኑ ያንቺ ነገር እንዴት ሆነ?››
‹‹የቱ?››
‹‹የሁለቱ ፍቅረኞችሽ ነገር?››
ለሊሴ ሰለሞን ባቀረበላት ሀሳብ መሰረት ከሁለት ፍቅረኞቾ መካከል አንዱን ለባልነት ለመምረጥ ምታደርገውን ጥረት ወዲያው ነበር የጀመረችው ….መጀመሪያ ነጋዴውን ለአንድ ወር ላታገኘው እንደማትችል ነግራ ከመንግስት ሰራተኛው ጋር ነበር የቀጠለችው..ሲደውልላት ትሄዳለች..ዝም ሲላት ትደውልለታልች….ከስራ መልስ ሳታገኘው ወደቤት አትገባም…እሁድ ቢያንስ ግማሹን ሰዓት ከእሱ ጋር ነች፡፡ይበልጥ ትኩረቷን ሰብስባ ከእሱ ጋር ባሳለፈች መጠን በፊት ከምታውቀው በላይ እያወቀችው …በፊት ከምታዳምጠው በላይ እያዳመጠችው መጣች፡፡አሁን ያለበትን የኑሮ ደረጃ ብቻ ሳይሆን ..
የወደፊት እቅዶቹንና እነዛን እቅዶች ለማሳካት እያደረገ ያለውን ተጋድሎም እየተረዳችና እየተገነዘበች መጣች…..እሱ ላይ ያላት ቅሬታ ባገባው እኔን አኑሮ ቤተሰቦቼንም እንድረዳ የሚያበቃኝ ህይወት ሊሰጠኝ አይችልም የሚል ነበር…አሁን ስታስበው ግን ያንን ከእሱ ብቻ መጠበቅ እንደሌለባት ነው የገባት…እሱ ባለው ቁርጠኝነት ላይ እሷ ተጨምራበት ካገዘችውና ከጎኑ ሆና አብራው ከታገለች ጎዶሎው ሊሞላ የሚችል አይነት እንደሆነ ተረድታለች…ግን ውሳኔ ላይ ከመድረሷ በፊት ለእሱ የመደበችለት ወር ተገባደደ እና ለዛኛው የሰጠችውን ተመሳሳይ ምክንያት ሰጥታ ..ለአንድ ወር ያህል ልትደውልለትም ሆነ ልታገኘው እንደማትችል ነገራ ወደነጋዴው ሄደች፡፡
በእውነት ነገዴው ጋር ልክ እንደወትሮ ሁሉ ነገር ተሰርቶ ያለቀ ሆኖ ነው የጠበቃት…ቤቱ የተዘጋጀ..እቃዎቹ የተደራጁ ናቸው…አዎ እያንዳንዱን ሀብቱንና አኗኗሩን ተራ በተራ አሳያት፣ቀጥታ እንዳገባችው ሕይወቷን ወደመስራት ሳይሆን የተሰራ ህይወት ውስጥ ገብቶ ለመኖር መሞከር ብቻ እንደሚጠበቅባት ተረዳች ፣ግን ለምን ልቧ ወደኃላ እንደሚጎትታት ግልፅ ሊሆንላት አልቻለም‹‹…ታግዬ ያላሸነፉኩት በሌላ እጅ የተሰራ ህይወት ምን ትርጉም ይኖረዋል?››እራሷን ጠየቀች… መልሱ ቀላል አልነበረም….፡፡
ሁሉንም ሂደት አንድ በአንድ ዘርዝራ አስረዳችው፡፡ ሰለሞንም‹‹እና ምን ተሰማሽ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አሁንም እንደተወዛገብኩ ነው…ግን በአእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሱ ጥያቄዎች በፊት ከሚመላለሱት የተለዩ ናቸው…እንግዲህ እኔ በህይወቴ ጠንከር ያሉ ውሳኔዎችን የማስተላለፍ ከፍተኛ ድክመት እንደለብኝ ነው የተረዳሁት፡፡››
‹‹አይ እንደዛ አይመስለኝም …አንቺ ቀሪ ህይወትሽን አብሮሽ በደስታ የሚዘልቅና ከቤተሰቦችሽም ጋ ተሰስማምቶ የሚያኮራሽ ለፍፅምነት የተጠጋ ባል እየፈለግሽ ነው….በዚህ ምድር ላይ ደግሞ ለፍጽምና የተጠጋ ነገር መምረጥ ቀላል ነገር አይደለም፡፡አንድ ታሪክ ልንገርሽ..
‹‹ደስ ይለኛል››
ደቀ መዝሙሩ መምህሩን ‹‹ፍፁምና በህይወታችን እንዴት አድርገን ነው ፍፅማዊ የሆነ ነገር መጎናፀፍ የምንችለው? ሲል ጠየቀው ፡፡ መምህሩም አሰብ አደረገና ‹‹የዚህን መልስ
እንድነግርህ ከፈለክ በፊት ለፊት በር ወደ ግቢው የአትክልት ስፍራ ቀጥ ብለህ ግባ ።በመንገድህ ከምታገኛቸው አበቦች መካከል በጣም የሚያምረውንና ደስ ያሰኘህን ቀንጥስና በጎሮ በር ውጣ …አንዴ ያለፍከውን አበባ ከእንደገና ወደኃላ ተመልሰህ መቅጠፍ አትችልም አሉት።›› አለው ።እሱም ትዕዛዙን አክብሮ እንዳተባለው ወደ አትክልቱ ስፍራ ገባና እስከመጨረሻው ጥግ ከተጓዘ በኃላ ባዶ እጅን በጓሮ በር ወጣ።
መምህሩ ‹‹ለምንድነው አንድ ቀንበጥ አበባ እንኳን ይዘህ መውጣት ያልቻልከው?››ሲሉ ጠየቁት፡፡
‹‹ምርጥ የተባለውን አበባ ወዲያው እንደገባሁ ነበረ ያገኘሁት... ግን የተሻለ አገኛለሁ ብዬ በማሰብ ሳልቀነጥስ ወደፊት ቀጠልኩ .. መጨረሻው ላይም ደረስኩ.. ወደኃላ የመመለስ እድል ስለሌለኝ ባዶዬን ለመውጣት ተገደድኩ›› ሲል መለሰ።
መምህሩ መልሱን ሲሰሙ ፈገግ አሉና ‹‹አዎ! ትክክል ነህ ፤ህይወት እንደዛ ነው ።ፍፁምናን ለማግኘት ይበልጥ በዳከርን ቁጥር ብኩን እየሆንክ ትሄዳለህ።እውነተኛ ፍፁምናን መቼም የትም አታገኝም።››ሲሉ መለሱለት። ‹‹ገባሽ አይደል?››
‹‹አዎ ገብቶኛል››
‹‹እንግዲያው ፍፅም በምናብ አለም ካስቀመጥሽው ወንድ ጋር የሚስማማ ባል እንደማታገኚ አውቀሽ ለሚማጡት 10 ቀናት ሁለቱንም ሳታገኚ አስቢበት..ከዛ ማንኛቸው ናቸው የበለጠ የሚናፍቁሽ..የትኛው ቢያቅፍሽ ትፈልጊያለሽ ….?ማንኛቸው የልጆችሽ አባት ቢሆኑ ይሻላል..?በህልምሽ እየደጋገመ የሚመጣው የትኛው ነው?፡፡ለ10 ቀን አስቢበት፡፡››
‹‹እሺ እንደዛ አደርገላው..ግን አሁን አሁን እየገባኝ ያለው እኔ ከባሌ ምን እጠብቃለው ብቻ ሳይሆን ለባሌስ ምን ይዤለት ሄዳለው…?የሚለውን በጥልቀት ማሰብና መዘጋጀት እንዳለብኝ ነው፡፡ ››
‹‹ጎበዝ ነሽ…ይሄ ትልቅ መረዳት ነው..በይ ደህና እደሪ››
‹‹ውይ …ከመዝጋትህ በፊት…ድፍረት አይሁንብኝና ዛሬ ቤት ለምን አትመጣም››
‹‹ለምን?››
‹‹እማዬ የማሪያም ድግስ አለባት….ማህበርተኞቹ እስከ10 ሰዓት ነው የሚቆዩት 11 ሰዓት ብትመጣ በጣም ደስ ይለኝ ነበር…››
‹‹አረ ተይ››
‹‹ምን አለበት…ቤተሰቦቼ በጣም ነው ደስ የሚላቸው››
‹‹11 ሰዓት ነው ያልሽኝ?፡፡››
‹‹አዎ 11 ሰዓት››
ብቻውን ሆኖ ስለአስቴር እያሰበ ከሚሰቃይ ከሰው ጋር ተቀላቅሎ የባጥ የቆጡን እያወራ ሊረሳት ቢሞክር እንደሚሻለው አሰበእና ‹‹በቃ እሺ መጣለሁ››አላት፡፡
‹‹በቃ አቃቂ ፖሊስ ጣቢያው ጋር ስትደርስ ደውልልኝ..ወጥቼ እቀበልሀለው››
‹‹እሺ ደውላለው››
ስልኩን ዘጋው፡፡ እሺ ማለቱን ፍጽም አላመነም….ጠበል ለመቅመስ ከሜክሲኮ
አቃቂ….ለመሆኑ በህይወቱ ጠበል የተጠራውና ጥሪውን አክብሮ የሄደው መቼ ነው..?ፍጽም አያስታውስም….
እንዳለችው …..እንደደወለላት ደቂቃ ሳታባክን ነው ወጥታ የተቀበለችው….መኪናውን
እዛው አስፓልት ዳር ፓርክ አደረገና ተከትሏት ይዛው ሄደችው.. ግን ወደሚያስደነግጥ ቦታ ነው ይዛው የሄደችው…ይሄንን ግቢ ትናንትና በዚህን ሰዓት መኪና ውስጥ ሆኖ ከአሰሪዎቹ ጋር በመሆን ሲሰልለው ነበር …‹‹ምን አይነት መገጣጠም ነው?››ለለሊሴ ምንም አይነት የመደነቅና የመገረም ስሜት ሳያሳያት ተከተላት፡፡አሁን ነገሮችን ገጣጥሞ ሲያስብ በፀሎት እሱን እንዴት እንዳገኘችውና ስልኩን ከማን እንደወሰደች ተገለፀለት፡፡

👍73❤5👎2
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
=====================
‹‹እናንተ ደግሞ ጅል አትሁኑ…ሰሎሜ ሰው ነች…ሰው ስለሆነች ታማለች…የተመመ ሰው ደግሞ በትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛውን ህክምና ካላገኘ ይሞታል….ይሄ ሀቅ ለሌላ ሰው ከሰራ ለሰሎሜም ይሰራል፡፡››ሁሴን ነበር የተናገረው፡፡
‹‹አንተ ደግሞ ሁሉን ነገር አውቃለሁ የምትለው ነገር አለ››አለማየሁ በብስጭት መለሰለት፡፡
‹‹ትክክል ነኛ..ከእናንተ በተሻለ ብዙ ነገር አውቃለሁ…ይልቅስ ሰሎሜ ቀዶ-ጥገናዋን እንድታደርግ እኛ ምን ማድረግ አለብን ?የሚለውን መነጋገር ነው የሚጠቅመን፡፡››
‹‹ትክክል ነህ..የመጣልህ ሀሳብ አለ?››አለማየሁ ነው በጉጉት የጠየቀው፡፡
የቀዶ ጥገና እንዲደረግላት የተወሰነበትንና እና የገንዘቡን መጠን የሚገልፅ ደብዳቤ ማግኘት አለብን›› ሁሴን ሀሳብ አቀረበ፡፡
‹‹አግኝተንስ ምን እናደርገዋለን?››አላዛር ጠየቀ፡፡
‹‹በሰፈር ጠቅላላ ዞረን እንለምናለን…በትምህርት ቤታችንም እንለምናለን፡፡››
‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው..ግን ያንን ሁሉ ብር የምናገኝ ይመስልሀል?››በጥርጣሬ ጠየቁት፡፡
‹‹እስከቻልነው እንሞክራለን…ካልሞላልን ደግሞ ሌላ ዘዴ እንፈልጋለን..አሁን ደብዳቤውን እንዴት እንደምናገኝ ማሰብ አለብን››
‹‹ለምን ሀኪም ቤት ሄደን ሰሎሜን የሚያክማትን ሀኪም አንጠይቀውም…››አላዛር ነው ሀሳቡን ያቀረበው፡፡
‹‹አይ አንተ ጅል የሆንክ ልጅ..አሁን ሄደን ብንጠይቀው ለ13 አመት ልጇች እንዲህ አይነት መረጃ ሚሰጠን ይመስልሀል?››
‹‹እኔ እንጃ ግራ ስለገባኝ እኮ ነው፡፡››
‹‹ለምን እቴቴን አንጠይቃትም..እሷ ደብዳቤውን ልታስወጣልን ትችላለች››
‹‹አሌክስ ትክክል ነው..ጊዜ ሳናባክን አቴቴን እናናግራት››ሁሴን በአለማየሁ ሀሳብ ወዲያው ተስማማ፡፡
‹‹ግን እኮ እሷ ሆስፒታል ነው ያለችው››
‹‹እኮ እንሂዳ››
ተስማሙና ቀጥታ ሰሎሜ ወደተኛችበት ሆስፒታል ነበር የሄዱት፡፡ሰሎሜ የተኛችበት ክፍል ገብተው ያለችበትን ሁኔታ ካዩ በኃላ‹‹እቴቴ አንዴ ውጭ ልናናግርሽ ፈልገን ነበር፡፡››ሲሉ ጠየቋት፡፡
‹‹ምነው በሰላም?››
‹‹በሰላም ነው..ሰሎሜ ስለተኛች እዚህ ስናወራ እንዳንቀሰቅሳት ነው››አለ ሁሴን፡፡
‹‹እሺ እንዳላችሁ ››በማለት ተስማምታ ተከትላቸው ወጣች፡፡እዛው ሆስፒታሉ በረንዳ ላይ ካለ አግዳሚ ወንበር ላይ በመደዳ ተቀመጡ፡፡
ለነገሩ ብዙም ትኩረት ባለመስጠት‹‹እሺ ልጆች ..ለምንድነበር የፈለጋችሁኝ?››ስትል ጠየቀቻቸው፡፡
‹‹ሰሎሜ እንዴት ነች?››
ቀዝቀዝ ባለ ስሜት ‹‹ደህና ነች..ምንም አትል››ስትል መለሰችላቸው፡፡
‹‹ማለት ስለቀዶ ጥገናው ነው የምናወራሽ…?እንዴት ነው የሚሆነው…?ያን ያህል ብር ከየት ታመጪያለሽ?››
‹‹ልጇች አትጨነቁ..ከየትም ብዬ ከየትም ይሄንን ብር አግኝቼ ብቸኛ ልጄን ማሳከም አለብኝ….አታስቡ ጓደኛችሁን እንድትድን የተቻለኝን አደርጋለሁ፡፡››ስትል እንባ እየተናነቃት መለሰችላቸው፡፡በእውነት ብሩን ከየት እንደምታመጣው…የትኞቹን ዘመዶቾን እንደምታስቸግር…የትኛውን ንብረቷን ብትሸጥ የተጠየቀችውን ብር ማግኘት እንደምትችል ምንም አይነት ሀሳብም ሆነ ተስፋ አልነበራት፡፡ግን ለልጆቹ ይሄንን ምን ብላ በምን አይነት ቋንቋ ልታስረዳቸው ትችላለች፡፡ለዛ ነው በደፈናው ልታፅናናቸው የወሰነችው፡፡
‹‹እቴቴ…ሰሎሜን ለማዳን የተቻለንን ብቻ ሳይሆን ከምንችለው በላይ ነው ማድረግ ያለብን…ሶስታችንም ልክ እንደአንቺ እሷን ለማጣት ዝግጁ አይደለንም…እና የሆነ ነገር ለማድረግ አስበናል፡››ሁሴን ነበር ተናጋሪው፡፡
አቴቴ ግራ በመጋባት‹‹ምን ማለት ነው …?እናንተ ደግሞ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?››
‹‹ከሀኪም ቤቱ ቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለባት መወሰኑን እና ለዛም የሚያስፈልገውን ብር የሚገልጽ ደብዳቤ እንዲሰጡሽ ጠይቂያቸው››
‹‹ማለት ..ደብዳቤው ምን ያደርግልኛል?››
‹‹አይ ላንቺ አይደለም..ለእኛ ያስፈልገናል››
‹‹ለምን .?.ምን ልታደርጉበት?››
ትምህርት ቤታቸውን ሆነ በሰፈራችን እርዳታ እየዞርን እንጠይቃለን..ከየአንዳንዱ ሰው አንድ ብርም ሆነ አስር ብር እየዞርን እንሰበስባለን…ለዛ ግን ሰው እንዲያምነን እና ስራችን ቀላል እንዲሆንልን መረጃው ያስፈልገናል፡፡››
በወቅቱ የሰሎሜ እናት ስሜቷን መቆጣጠር አልቻለችም ነበር…ሁሉንም አንድ ላይ አቅፋ ጉያዋ ውስጥ በመወሸቅ ስቅስቅ ብላ ነበር ማልቀስ የጀመረች፡፡
አለማየሁ ጉንጮ ላይ ያለውን እንባ በመዳፎቹ እየጠረገላት ‹‹እቴቴ አይዞሽ.. አታልቅሺ …ሰሎሜን እናድናታለን…እሷ የእኛ ንግስት ነች..ንግስታችንን ማጣት አንፈልግም፡፡››ሲል አፅናናት ፡፡
‹‹ያስለቀሰኝ ሀዘን አይደለም ደስታ ነው፡፡ልጄን ወንድም ወይም እህት ሳልወልድላት ብቸኛ አደረኳት ብዬ ብዙ ጊዜ አዝኜና አልቅሼ ነበር፡፡አሁን ግን እንደተሳሳትኩ በደንብ ነው የገባኝ፡፡ወንድሞች ቢኖሯትም እናንተ ከምትወዷትና ከምትንከባከቧት በላይ ሊንከባከቧት አይችሉም ነበር፡፡
በጣም ነው የማመሰግናችሁ፡፡ እናንተ ስላላችኋት ልጄ በጣም እድለኛ ነች››
‹‹አይ እቴቴ….እሷ ስላለችን እኛ ነን እድለኞች…አሁን መላቀሱ አይጠቅመንም…ሂጂና ዶክተሮቹን ጠይቀሽ ደብዳቤውን አግኚልን፡፡››
‹‹እሺ በቃ ውስጥ ገብታችሁ ጠብቁኝ …መጣሁ››ብላ በነጠላዋ ጫፍ በጉንጮቾ የረገፈ እንባዋን እየጠረገች ወደአስተዳደር ቢሮ ሄደች፡፡
ደብዳቤውን በእጃቸው ካስገቡ በኋላ ሰፈራቸው ወደሚገኝ ባነር መታሚያ ቤት ነበር የሄድት፡፡ ደብዳቤውን አሳይተውና ሁኔታውን አስረድተው…የሰሎሜ አሳዛኝ ፎቶ የሚታይበትንና ያለችበትን ሁኔታ እጥር ምጥን ባለ ግልፅ ዓረፍተ ነገር አፅፈው ሁለት ሜትር በአንድ ሜትር በሆነ ባነር አሳተሙ፡፡ ..በማግስቱ ወደትምህርት ቤት ይዘው ሄዱ፡፡ቀጥታ ወደ ዳሪክተሩ ቢሮ ሄዱና ሁኔታውን አስረዱት….፡፡.ተማሪዎች በተሰለፉበት ባነሩ ለሁሉም እንዲታይ ተዘርግቶ ሰሎሜ ያለችበትን ሁኔታና የሚያስፈልጋትን ነገር ለሁለቱም ፈረቃ ተማሪዎች ተነገረ…፡፡በእለቱ በኪሳቸው ያላቸው ተማሪዎች ወዲያውኑ ማዋጣት ጀመሩ…ሁለት ሺ ሶስት መቶ ብር አካባቢ ተሰበሰበ፡፡በማግስቱ ሁሉም ተማሪ ለወላጆቹ በማስረዳት የቻለውን ይዞ እንዲመጣና በስም ጠሪዎች አማካይነት በየክፍሉ እንዲሰበስብ ተደረገ፡፡
በአጠቃላይ በሶስት ቀን ውስጥ ከመላው ተማሪና አስተማሪዎች 23 ሺ ብር ተሰበሰበ፡፡ትምህርት ቤቱ የሰሎሜን እናት ጠርቶ ቀጥታ ብሩን አስረከባት፡፡ የትምህርት ቤቱን ቅፅር ግቢ በእልልታ አናጋችው….ሶስቱን የልጇን ጓደኞች እያገላላበጠች ሳመቻቸው፡፡ከልቧ መረቀቻቸው፡፡ከነፍሷ ወደደቻቸው፡፡
እነአለማየሁ ግን እንደእሷ ባገኙት ነገር ፍፅም ደስታ አልተሰማቸውም ነበር፡፡የእነሱ ግምት ቢያንስ 40 እና 50 ሺ ብር እናገኛለን የሚል ነበር፡፡ወዲያው ጊዜ ሳያባክኑ ባነሩን ለሁለት ጉን ለጉን ይዘው አንደኛው በአጀንዳ ላይ እያንዳዱ ሰው የሚሰጠውን ስምና ብር እየመዘገበ በሰፈር ውስጥ እያንዳንዱን ቤት እያንኳኩ እና የድርጅቶችንም ቢሮ ዘልቀው እየገቡ ጭምር መጠየቅ ጀመሩ፡፡
በአራት ቀን ውስጥ ሌላ 20 ሺ ብር አገኙና ለእናትዬው አስረከቧት..፡፡እሷ በፊት ደብተሯ ላይ የነበራትናን ከቢሮዋ ሰራተኞች ተዋጥቶ የተሰጣት አንድ ላይ ሆኖ እነሱ ከሰበሰቡት ጋር 50 ሺ ብር አካባቢ በእጇ ያዘች፡፡
ሶስቱም በአንድ ላይ ተሰብስበው ሄደው ‹‹እቴቴ..አሁን ስንት ብር ሆነልሽ?››ብለው ጠየቋት፡፡

👍59❤9👏1
#ቋጠሮ_ሲፈታ
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሶስት
፡
፡
#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
///
"ምንድነው የነገረችሽ?"
"እኔ ዲቃላ መሆኔን ."
የጁኒየር ፊት በድንጋጤ ባዶ ሆነ።
"እውነት ነው አይደል?"
ጁኒየር እጆቹን ዘረጋና እቅፉ ውስጥ አስገባት… እንባዋ በመጨረሻ የዐይን ሽፋኖቿን ሞልተው ያለከልካይ ፈሰሰ።
"ሰሎሜ ከኮፈሌ ተመልሳ መጣች። ከገመዶ ጋር ለመታረቅ ተዘጋጅታ ነበር።ፍቅራቸውን ለማደስ ተስማምተው ነበር …የመጋባት እድል ሁሉ ነበራቸው…በመሀል ግን ለማንኛችንም ሳትነግረን መልሳ ጠፋች….በኋላ ነው አንቺን ማረገዟን ስላወቀች እንደጠፋች ያወቅነው፡፡››ሲል አስረዳት፡፡
በእፍረት ፊቷን በእጆቿ ሸፈነች።
" ኦ አምላኬ በጣም ቢጠላኝ አይገርምም።››
ጁኒየር እጆቿን ከፊቷ ላይ አንስቶ በቅን ልቦና የሚወዳቸውን ጥቆቁር አይኖችን እየተመለከተ።
"ገመዶ አንቺን አይጠላሽም አሌክስ። ማናችንም ብንሆን አንጠላሽም…ያ ከአመታት በፊት ተጋፍጠን በይቅርታ ያለፍነው ጉዳይ ነው››
በንግግሩ በምሬት ሳቀች።‹‹ለምን አያቴ ሁሌ እኔ ላይ ጥብቅ እንደምትሆን እያሰብኩ እበሳጭ ነበር …በስንት ሰዓት ከቤት እንደወጣው? በስንት ሰዓት እንደተመለስኩ..?ከማን ጋር እንደነበርኩ ከአግባቡ ያለፈ ቁጥጥር ታደርግብኝ ነበር…ምክንያቷ አሁን ነው የገባኝ
…ለካ እናቴን ያጋጠማት ነገር እንዳያጋጥመኝ ፈርታ ነው፡፡አሁን ነው የገባኝ፡››
"ይሄ ከሃያ አምስት አመታት በፊት የሆነ ድርጊት ነው ፣ አሌክስ አሁን ስለዛ ማሰብ አቁሚ "
"አያቴ በእውነት እኔን ለምን እንደማትወደኝ የሚያብራራልኝ ታሪክ ነው… የሰሎሜን ህይወት አበላሽቻዋለሁ…እና ለዛ ፈጽሞ ይቅር ሳትለኝ ነው የሞተችው…. ሰሎሜ ገመዶን አጥታለች …ፍቅራቸው እንዳይሆን ሆኖ ተሰባብሯል … እና ሁሉም የሆነው በእኔ ምክንያት ነው››.
‹‹ኦህ፣በእግዚአብሔር !ተረጋጊ እንጂ!"
አለም ከእቅፉ ወጣችና ወደ መኪናዋ ሮጠች…መኪና ውስጥ በመግባት አስነሳችና አካባቢውን ለቀቀች።
."ምንድነው ነገሩ?" አለም ወደ መኪናዋ አቅጣጫ ስትሮጥ ያያት አቶ ፍሰሀ ጠየቀው።
"ሁለታችሁም እሷን ተዋት" ሳራ ከውስጥ እየወጣች ለባሏ መለሰች፡፡
ጁኒየር ወደ እናቱ ዞረና።
"እማዬ እንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ? እንዴት ልጅቷን እንዲህ ትጎጂያታለሽ?"
"ልጎዳት አስቤ አይደለም የነገርኳት፡፡››
"ምን ነግራት ነው?" አቶ ፍሰሀ ጠየቀ ፡፡
ጁኒየር “በእርግጥ ጎድተሻታል። ደግሞ አቅደሽበት ነው ያደረግሽው… ለምን ነገርሻት?"
‹‹ምክንያቱም እሷ ማወቅ ስላለባት። አለምን የምትጎዳት እራሱ አለም ብቻ ነች። ሸቅዠቷን እያሳደደች ነው። የምትፈልጋት አይነት ቅድስት የሆነች እናት በሰሎሜ ውስጥ አልነበረችም። ሰሎሜ ምትባል ድንቅ እናት እንደነበረቻት በማይረባ ጭንቅላቷ ደምድማለች። እናቷ ምን ያህል ተንኮለኛ እና ሀጥያተኛ እንደሆነች ልጅቷ ማወቅ አለባት.. እናቷ ስትማግጥ እሷን ዲቃላ እንዳረገዘቻት የማወቅ መብት አላት››
" አንቺ እኮ ጤነኛ አይደለሽም!" አቶ ፍሰሀ ተበሳጨባት፡፡
…
አቶ ፍሰሀ በጸጥታ ወደ መኝታ ቤት ገባና ከኋላው በሩን ዘጋው፡፡ሳራ በአልጋዋ ላይ ያሉትን ትራስ ደራርባ ተደግፋ መፅሃፏን እያነበበች ነበር…እሱን ስታይ መፅሀፉን ከደነችና አጠገቧ ያለው ኮመዲኖ ላይ አስቀመጠች ።
ወደአልጋው ቀረበና " ላናግርሸ እፈልጋለሁ።"አላት፡፡
"ስለ ምን?"
‹‹ዛሬ ከሰአት በኋላ ስለተፈጠረው ነገር።››
"ራስ ምታት እየፈለጠኝ ነው…ለእራት ወደታች ያልመጣሁትም ለዛ ነው"
‹‹የሆነ መድሀኒት አልወሰድሺበትም?"
"አዎ ወስጄለሁ…አሁን በመጠኑ እየተሻለኝ ነው ።"የሳራ የራስ ምታት በትዳራቸው ልክ አብሯት የቆየ ህመም ስለሆነ የተለመደ ነው፡፡
በአልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጠ እና አቀርቅሮ ሀሳብ ውስጥ ገባ፡፡
" ምንድነው ፍሰሀ ?አሁንም የሚያሰጋን ችግር አለ እንዴ?››ጠየቀች፡፡
"አይ..ሁሉም ነገር ሰላም ነው።"
"ታዲያ ለምን ታስባለህ…?እግዚአብሔር ይመስገን ብቸኛው የሞተው ፈረስ የገመዶ ነው
።››
አቶ ፍሰሀ ምንም አስተያየት መስጠት አልፈለገም ። ሳራ ጆ ለገመዶ ያላት ስሜት ፈጽሞ አይለወጥም፤በዚህ ጉዳይ ከእሷ ጋር መነጋገር ጥቅም አልባ እንደሆነ እርግጠኛ ነው፡፡ከእሷ ጋር ሊወያይ የመጣው ስስ ስለሆነ ጉዳይ ነው። ቃላቱን በጥንቃቄ ለመምረጥ ትንሽ ጊዜ ወሰደበት.
"ሳራ ዛሬ ከሰአት በኋላ -……" "በጣም ተበሳጭቼ ነበር" አለችው፣ ፡፡
" ተበሳጭተሽ ነበር?" ፍሰሀ ትዕግሥተኛ ሆኖ ጠየቃት፡፡ወደ ድምዳሜው ከመዝለሉ በፊት ከእሷ ወገን ያለውን የታሪኩን ገጽታ መስማት ፍልጓል።
"የአለምን ስሜትስ የጎዳሽ አይመስልሽም…?"
"ዲቃላ መሆኗን ስላወቀች ብቻ አይደለም የተናደደችው….እሷ በተፈጥሮዋም ብስጩ ነች:: "
"እኔ በእሷ ቦታ ብሆን አይገርመኝም… ወላጆቼ የጋብቻ ሰርተፊኬት እንዳላቸው በጭራሽ አጣርቼ አላውቅም.., እና ባይኖራቸውም ምንም አይመስለኝም ነበር.››
" ሁሉም ሰው ለነገሮች ያለው ምላሽ የተለያየ ነው››
‹‹ አለም ግን ስሜታዊነት የሚያጠቃት ወጣት ሴት ነች።"
"እሷ ይሄን ታሪክ ለመቀበል የሚያስችል ጥንካሬ እንዳላት አምናለው."ስትል መለሰችለት
"በእርግጥ የምትይውን ያህል ጥንካሬ እንዳላት እርግጠኛ አይደለሁም።በረንዳ ላይ ቆሜ እያየችኝ እኔን እንኳን ሀሳትሰናበተኝ ነው ገፍትራኝ ሮጣ የሄደችው፡፡››
የሳራ ፈገግታ ተሰበረ። "ስለነገርኳት ትወቅሰኛለህ? ስህተት የሰራው ይመስልሃል?"ስትል ጠየቀችው፡፡
በዛ ልብን በሚሰረስር የግሏ የሆነ ልዩ እይታ ስታየው፣ ልቡ ቀለጠ። ሁል ጊዜም የዚህ አይነት አስተያየት ስታየው የሚሆነው እንደዚሁ ነው። ፍሰሀ በስሱ ይዳብሳት ጀመር፡፡
‹‹ውዴ ስለነገርሻት አልወቅስሽም። ግን የነገርሽበት መንገድ እንደዚህ ባይሆን ጥሩ ነበር፡፡ እንደዛ ከማድረግሽ በፊት ከጁኒዬር እና ከእኔ ጋር መመካከር ነበረብሽ…በህይወቷ ሙሉ ባታውቀው የሚሻል ታሪክ ነበር፡፡››
"አልስማማም" ስትል ሳራ ተከራከረች።
አቶ ፍሰሀም "እናቷ እና አባቷ አብረው ከተኙ በኃላ አለመጋባታቸው ወይ መጋባታቸው በእሷ ልጅነት ላይ አሁን ምን ለውጥ ያመጣል? ይህ በቡዙ ወጣት ሴቶች ህይወት ላይ የሚያጋጥም በጣም የተለመደ ነገር ነው..››አላት፡፡
"ልጅቷ ስለ ሰሎሜ ያላት አመለካከት ላይ ግን ለውጥ ያመጣል። ››
‹‹እንዴት?››
‹‹ሰሎሜ ልጅቷ የምታስባትን አይነት ቅድስት ሴት አይደለችም…ይሄን ማወቋ የእሷን የግድያ ጉዳይ ለማወቅ የምታደርገውን ልፋትና ጥረት ቆም ብላ እንድታይ ያግዛት ይሆናል….ይልቅ ከአሁን በኃላ ሁላችሁም ከአለም ጋር መገናኘቱን እና መወያየቱን ማቆም አለባችሁ፡፡››
"ለምን?"ግራ ገብቶት ጠየቀው፡፡
"ለምን? ምክንያቱም እሷ እኛን ለማጥፋት እየሞከረች ነው…ለዚህ ነው. እሷን ለመፋለም የወሰንኩ…. ያለኝን ጥይት ነው የተጠቀምኩት….አንተን እና ጁኒየርን ለመጠበቅ እየሞከርኩ ነበር."
በእውነቱ፣ ፍሰሀ እንደ አለም ያለ በራስ መተማመን የነበራትን ሴትን ለመጋፈጥ ለሣራ ትልቅ ድፍረት እንደሆነ አሰበ። ያደረገችው ስህተት ቢሆንም ሳራ ያደረገችውን ነገር ያደረገችው ቤተሰቧን ልትጠብቅ እንደሆነ ተረድቷታል። የጀግንነት ጥረቷ ከትችት የተሻለ ነገር ይገባዋል ብሎ አሰበ እና ጎንበስ ብሎ ግንባሯን ሳመ።
ለስለስ ባለ ንግግር" የትግል መንፈስሽን አደንቃለሁ… ግን ማናችንም ያንቺን ጥበቃ አንፈልግም ።"አላት፡፡

❤46👍3