አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ:
….

‹‹ምነው አልክ..?ፒጃማ የለህም እንዴ?››

‹‹አለኝ ግን በማሳጁ ምን ያህል ብቁ ሆነሻል.ስልጠናውስ እንዴት ነበር? የሚለውን ማወቅ እፈልጋለሁ…››

‹‹ተው… እርግጠኛ ነህ?››

‹‹አዎ ምነው ፈራሽ አንዴ.?ነው ወይስ በብቃትሽ አትተማመኝም? እንዳዛ ከሆነ ይቅር፡› ብሎ ፊቱን ወደቁምሳጥኑ መልሶ ሊራመድ ሲል እጁን ለቀም አደረገችውና‹‹መፍራት ያለብህማ አንተ ነህ…ትዝ ይልሀል ያን ቀን ቤትህ አታለህ አስገብተኸኝ የዋህነቴን ተጠቅመህ እዛ የማሳጅ ጠረጴዛ ላይ አስተኝተህ እንዴት እንደተጫወትክብኝ ያንን መበቀል መቻል አለብኝ፡፡›› ብላ እየጎተተች ወደ ማሳጅ ጠረጴዛው ወሰደችና በጀርባው እንዲተኛ አደረገችው፡፡

ከዛ በቅርብ ካለው ቅባት ወደተኮለኮለበት ጠረጴዛ በመሄድ አንዱን መርጣ አነሳችና ጀርባው ላይ አፈሰሰችበትና ከላይ ከጆሮ ግንዱ ጀምራ እስከታች የእግር ጣቶቹ ድረስ በወሰደችው ሰልጠና መሰረት የተለያዩ ቴክኒኮችን በመጠቀመ እያገለባበጠች ለአርባ ደቂቃ ካሸችው በኃላ እጅግ በሚገርም ሰመመንና መመሰጥ ውስጥ ገብቶ ከተዝለፈለፈ በኃላ እንደምንም ከጠረጴዛው ላይ አስነስታ ወለሉ ላይ ዘረረችው…. ከዛማ ቀሚሷን ወደላይ መዥርጣ አውልቃ ከጎኑ ተኛች…ከዛ በኋላ የነበረውን ለማሰብም ይከብዳታል…ያንን ሰፊ የመኝታ ቤት ወለል እየተንከባለሉበት አንዴ የአልጋው ጠርዝ ሲገጫቸው፤አንዴ ከጠረጴዛው እግር ጋር ሲላተሙ አንዴ ስትገለብጠው….ከዛም ሲገለብጣት ከ30 ደቂቃ ቆይታ በኋላ ነበር መጀመሪያ እሱ ከዛ ከ5 ደቂቃ ያህል ዘግይታ እሷ ጡዘት ላይ የደረሱት…፡፡

ከዛ እንደምንም.ተላቀው ወዲህና ወዲያ የነበሩበት ወለል ላይ የተዘረሩት.. ከ7ደቂቃ እረፍት በኋላ እሷ እንደምንም ከተዘረረችበት ተነስታ እየተሳበች ወደሻወር ቤት ሄደች….ውሀውን በላይዋ ላይ ለቀቀች…በሁሉም ነገር በጣም ረክታለች.. የዚህ ወሲባዊ ተራክቦ መሪ እሷ ነበረች.. እርግጥ ያ በግልፅ ለእሱ እንዲሰማው አላደረገችም ቢሆንም እያንዳንዷን ቅንጣት በንቃት አጣጥማታለች፡፡ ከ10 ደቂቃ በኃላ ፎጣዋን አገልድማ ወደመኝታ ቤቱ ስትመለስ ደምሳሽ ጥላው በሄደችበት ወለል ላይ ተዘርሮ እንደተኛ እንቅልፍ ወስዶታል፡፡ እየሳቀች  ወደእሱ  ቀረበችና በእግሯ ወዘወዘችው..

‹‹ደምሳሽ…እረ ተነስ ሻወር ውሰድና እንተኛ››

‹‹እንዴ... አንቺ ምን አደረግሺኝ?›› እያለ እደምንም ተነሳና ወደ ሻወር ቤት ገባ፡፡

እሷ ሰውነቷን በሎሺን አባበሰችና  አልጋ  ላይ  ወጥታ  ከአንገቷ  ቀና  በማለት ትራስ ተደግፋ ታጥቦ እስኪመጣ በንቃት ትጠብቀው ጀመር….እሱ 5 ደቂቃ አልፈጀበትም፡፡ፎጣውን አገልድሞ ወጣ…

ቁጭ ብላ ሲያያት ‹‹እንዴ ምነው አተኚም እንዴ?››

‹‹ምነው? አንዴ አንደግምም?››አለችው እየሳቀች፡፡

ሰውነቱን የጠቀለለበትን ፎጣ ከላዩ አነሳና የረጠበ ጸገሩን እያደራረቀ‹‹ምነው በቀል ቢሉሽ እንዲህ በአንድ ቀን ሙሉ በሙሉ ማውደም ነው እንዴ.? ቀስ እያልሽ አይሻልም?››አለና እሱም እንደእሷ አልጋ ላይ ወጣ…ከውስጥ ገብቶ ተኛ፡፡
‹‹ችግር  የለም …ዋናው እጅ መስጠትህ ነው››

‹እረ እጅ ሰጥቼያለሁ…በነገራችን ላይ የማሳጅ ችሎታሽ በጣም አስገራሚ ነው የሆነብኝ….ለረጅም አመት በስራው ላይ የቆየሽ እኮ ነው የምትመስይው… በራስሽ ካላበላሸሽው በስተቀር በቀላሉ ውጤታማ እንደምትሆኚ በእርግጠኝነት መናገር እችላለሁ››

‹‹ይሄን ያህል?››

‹‹የምሬን ነው በጣም ነው ያስደመምሺኝ.. ሶስትና  አራት  አመት  በስራው  የቆዩ እንኳን ያንቺን ያህል በጥበብ እና በእውቀት አይሰሩም….አንቺ በዚህ ላይ  ሶስት አራት ወር ልምድ ካከልሺበት በቃ ልዩ ነው የምትሆኚው፡››

‹‹ለአድናቆትህ በጣም ነው የማመሰግነው..ግን ምነው አድናቆትህ ማሳጁ   ላይ ብቻ ሆነ ..ሌላው እስከዚህም ሆነብህ ማለት ነው?፡፡››

‹‹ትቀልጂያለሽ አይደል…? በወሲብ ልምዴ እንዲህ አቅሌን ስቼ ስዘረር የመጀመሪያ ገጠመኜ ነው…ብቻ  ድንቅ ተማሪ ነሽ.. የመጀመሪያ  ጊዜ ወሲብ  ስናደርግ..ትኩስ እና ሞቃት ነበርሸ ቢሆንም አብዛኛውን ነገር ለእኔ ነበር አሳልፈሽ የሰጠሸው…ዛሬ ግን እኔ ባሪያሽ ሆኜ ነበር፡፡ በአጠቃላይ በሁሉም ዘርፍ ነው የተቀየርሽው….ምን አልባት ተሰጥኦሽን ይሆናል ያገኘሽው፡፡

‹አንተ እየሰደብከኝ ነው እንዴ…? የታደሉት በስዕል ችሎታቸውና በሙዚቃ ብቃታቸው የተፈጥሮ ታለንታቸውን አገኙ ይባላል…እኔን በወሲብ?፡፡›

ሁሉን ነገር በጥበብና በእውቀት ከከወንሽው አርት ነው…ተሰጥኦ ነው፡፡ እንዴ ትቀለጂያለሽ እንዴ ለአንድ ሴት አርክቶ በእኩል ሰዓት  መርካት  መቻል  እራሱ ድንቅ መሆንን ይጠይቃል፡፡ ብዙ ጊዜ አንዱ አንዱን ለማስደሰት ምን ይህል እንደሚሰቃይ አታውቂም፡፡ ወንድ ልጅ ደግሞ አንዲትን ሴት ሲቀርብ  እሷም ሴትነቷን በሚፈልገው መጠን እንዲህ እንደ አንቺ በገለጠችለትና ይበልጥ በእሷ እየተደሰተና እየረካ በሄደ መጠን ነው ቀን ከቀን ይበልጥ በእሷ እየተሳበ እና በአካሏ ብቻ ሳይሆን መላ እሷነቷን እየወደዳትና እየተቀበላት የሚሄደው፡፡

‹‹እሺ ለማንኛውም ነገ ወደ ወሳኙ ተግባራዊ ፈተና የምሰማራበት ቀን  ስለሆነ ደክሜ  መገኘት አልፈልግም፤ እንተኛ  ለዚህ  ድንቅ  ልብ  አቅልጥ  አስተያየትህ ግን አልፎ አልፎ ያው እቸገርልሀለሁ›› አለችው፡፡

ተንጠራርቶ መብራቱን እያጠፋ‹‹በነገራችን ላይ የዛሬው አዳራችን ምን አልባት የስንብት ሊሆን ይችላል?››ሲል ነበር ያረዳት፡

የእውነት ከልቧ ደንግጣ ተነስታ ቁጭ አለች‹‹ምን ማለት ነው?››

‹‹ከዚህ በፊት ነግሬሽ የለ…ልጄን ፍለጋ ወደአሜሪካ እንደምሄድ አሁን ፕሮሰሱ ሁሉ.አልቆልኛል...ቪዛም አግኝቼያለሁ….ከአራት ቀን በኋላ እበራለሁ››

‹‹ምን አይነት ጨካኝ ሰው ነህ ግን…? እንዴት አራት ቀን እስኪቀረው ድረስ ሳትነግረኝ?››

‹‹ከባድ ስልጠና ላይ ስለነበርሽ ልረብሽሽ አልፈለኩም ነበር…››አላት፡፡

‹‹በፈጣሪ…ግን  ቶሎ ተመልሰህ ትመጣልህ አይደል?››

‹‹ስለእሱ ምንም የማወራው ነገር የለም….ልጄን ካገኘሁ በኋላ በቀጣይ ባለው ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡››
‹‹ያ ማለት አስከወዲያኛውም ላትመጣ ትችላለህ ማለት ነው?››
       ቁዝዝ ብሎ‹‹አዎ ላልመለስ እችላለሁ››አላት፡፡
ተመልሳ ተኛች…እሱም ተኛ…ተቃቅፈው ….እሷ  ይሄን  የመሰለ  መከታ  የሆነ ወዳጅ እንዲህ በድንገት እብስ ብሎ ከእጇ ሊያመልጥ መሆኑን ስታውቅ ሆዷን ባር  ባር  አላት… በጣም  ከፋት…ሰሰተችው….ገና  ከመሄዱ   በፊት ከአሁኑ ናፈቃት... ግን እርቃኑ ከእርቃኗ ተጣብቆ እቅፉ ወስጥ  ገብታ  ትንፋሿ ሲገርፈው ዝም ብሎ መተኛት አልፈለገም … እሷም  በተመሳሳይ…  ለሁለተኛ  ዙር  ፍልሚያ ገቡ፡፡

ጠዋት 12 ሰዓት ነበር ከእንቅልፉ ነቅቶ መኝታውን በመልቀቅ ወደ ኪችን የገባው፤ጥሩ ቁርስ ሰራና አንድ ሰዓት ሲሆን ቀሰቀሳት…ሶስት ሰዓት ስልጠና የምትወስድበት ቪላ ቤት ጋር አድርሷት አንኳኩታ ወደውስጥ ስትገባ…እሱ ወደሌላ ስራው ሄደ፡፡

ስልጠና ቦታዋ ስትደርስ ማንም አልነበረም።ግራ ገባት...አብረዋት የሚሠለጥኑት ተፎካካሪዎቿን ደውላ መጠየቅ አትችልም። ስልክ ቁጥራቸው  አልነበራትም። አሰልጣኟ  ጋር  ደወለች። አይሰራም። ምን  ተፈጠረ?"ሰገን  ጋር ደወለች። ጎሽ ይጠራል "አለችና ጆሮዋ ላይ ለጠፈች። ዝም ብሎ ይጠራል አይነሳም።

ሊዘጋ ሲል። "ምነው ፈለግሺኝ እዚህ ነኝ" የሚል  ድምፅ  ከጀርባዋ  ሰማች። በፈገግታ ዞር አለች።

"ግቢው ባዶ ሲሆንብኝ ግራ ገብቶኝ ነው"
👍727👏2
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


"አዎ ገብቶኛል....ግን ይቀረፃል ያልሺው?"

"አዎ ይሄንን በከፍተኛ ሚስጥር ነው....ድንገት ተስቶሽ በህልምሽ እንኳን ብታወሪ ህይወትሽን ያስከፍልሻል።ምክንያቱም ደንበኞቻችን እንደሚቀረፁ ቢያውቁ እዚህች ቤት ዳግመኛ ዝር አይሉም።እኛ ግን በጣም ምስጢራዊና ማንም በቀላል ፍተሻ ማግኘት በማይችልበት ቦታዎች ካሜራዎች አሉን።ይሄ በዎናነት ሰራተኞቻችንን ከአደጋ ለመጠበቅ ነው። ማንኛውም ሰው  አጉል  እመል  ኖሮት  ጥቃት  ልፈፅም ቢል በፈጥነን እንደርሳለን፡፡ ከእንደገና ሰውዬው በሂደት ከእኛ ጋር ተቃቅሮ ድርጅታችንን ሊያጠቃ ቢንቀሳቀስ ያ ሚስጥር መከላከያ ጋሻችን ነው።

"አሁን ገባኝ"

"አዎ...ግን ላስጠንቅቅሽ...ስራ ስትጀምሪ ፈፅሞ ስለካሜራው በአእምሮሽ ማሰብ የለብሽም...ልክ አንድ የፊልም ተዋናይ ስትተውን ፊት ለፊቷ ስለተደቀነው ካሜራ ቁብ እንደማይሰጣት ሁሉ አንቺም ተመሳሳዩን ማድረግ አለብሽ፤ ይሄንንን ከመጀመሪያው ቀን ጀምረሽ መልመድ አለብሽ"

"እሺ እንዳልሺኝ አደርጋለሁ።

"እሺ አሁን ጨርሰናል...ክፍልሽን ያሳዩሻል  ግቢና  እረፊ...  ልክ  9.30   ላይ ከክፍልሽ ወደማሳጅ ቤቱ ይወስድሻል። አስር ሰዓት ላይ የመጀመሪያ ደንበኛሽ ይመጣል። ዝግጁ ሆነሽ ጠብቂው ።ከእኔ ጋር ነገ ጠዋት እንገናኛለን ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳችና ጉንጯን ስማት በተቀመጠችበት ጥላት ሄደች።


ሳባ በህይወቷ ዘመኗ የከፋው ፍርሀት ነው  በመላ  ሰውነቷ  ተሰራጭቶ እያንዘፈዘፍት ያለው እርግጥ ይህ ፍራቻ ገና ጠዋት  ስለፕሮግራሙ  ከተነገራት ጀምሮ ነው ሲረብሻት የዋለው ። ሰአቱ ሲቃረብ እንዲያደፋፍራት መድሀኒት ነገር ወይም መጠጥ ጠጣ ጠጣ አድርጋ ለመሄድ ፈልጋ ነበር።ግን ስልጠና ላይ እንደተነገራት ወደስራ መጠጥ ጠጥቶ አይደለም ቀምሶ እንኳን መግባት አይቻልም።ባይሆን በስራ ላይ እያለች ደንበኛው መጠጥ እንዲቀርብለት ካዘዘና ለእሷም ከጋበዛት የዛኔ ነፃ እንደሆነች ነው የተማረችው።በመጀመሪያ ቀን የሙከራ ጊዜዎ ደግሞ ስህተት በመስራት ልትጀምረው አልፈለገችም። ቢያንስ እያወቀች መሳሳት አትፈልግም"ሰገን
ሰገን ነች ማሳጅ መስጫ ክፍል ድረስ ይዛት የሄደችው። እያንዳንዱ ለማሳጅ የምትገለገልበት እቃ የት የት እንዳለ ምን ማድረግ እንዳለባት ምን አለማድረግ እንዳለባት ከ20 ደቂቃ በላይ ክፍል ውስጥ  እየተንጎራደደች  አንድን  ዕቃ እየያዘች መልሳ እያስቀመጠች አብራራችላትና መልካም እድል ተመኘችላትና ተሰናብታት ወጣች።
ጥላት ከሄደች ከ10 ደቂቃ በኃላ በራፍ ተቆረቆረ ከተቀመጠችበት በመበርገግ ቆመች...መልሳ ቁጭ አለች...የኋላ መውጫ በር ቢኖረው በራ ለመውጣት ሁሉ ተመኘች።
ደግሞ በራፍ ተቆረቆረ..እንደምንም መቀመጫዋን ለቃ ወደበሩ ተራመደች ከፈተችው…በድንጋጤ ላይ ድንጋጤ የሚጨምር ሁኔታ ተከሰተ በራፋ ላይ የገጠማት አንድ ግዙፍ አስፈሪ መልክና  ኮስታራ ፊት ያለው ሰው ፊቷ ተጋረጠ" ወይኔ በጌታ አሁን ይሄ ምኑ ይታሻል?"ስትል በቅፅበት ውስጥ አሰበች"አሽቀንጥሮ.ገፈተራትና.ወደውስጥ.ገባ።በድንጋጤ.አይኖቿን.በለጠጠች።
በየክፍሉ  እየገባ ይፈትሽ ጀመር።ቁም ሳጥኖቹን ሁሉ  እያንዳንድን  መሳቢያ  ሳይቀር  እየከፈተ እየዘጋ ማየቱን ቀጠለ
"ይሄ ምን የሚሉት ደንበኛ ነው? "ስትል በውስጧ አሰበች። በሁኔታው ተበሳጨች፤ስትበሳጭ.በመጠኑ.ፍራቻዋ.ቀነስ.አለላት።
  "ጌታዬ ምን ፈልገው ነው?"
መሀል ወለል ላይ ቆመና ዙሪያ ገባውን ኮርኒሱንም ሳይቀር በጥንቃቄ ካየ በኋላ ለእሷ  ጥያቄ   ምንም    መልስ   ሳይሰጥ    እንደ አመጣጡ    መልሶ ወጣ። ይበልጥ ግራ ተገባች፡፡ ይሄ ጠረንገሎና አስቀያሚ እዛ የማሳጅ ጠረጴዛ ላይ ተኝቶ እሺኝ ስላላላት እግዚያብሄር ይመስገን ብላ አመስግና ሳትጨርስ በራፍ ተከፈተና ያው ሰውዬ መልሶ አንገቱን አሰገገ...ሀሞቷ ፍስስ አለ...በራፉን ሙሉ በሙሉ ከፈተው ሌሎች ሰዎች ታያት።ሶስት መሆናቸውን አየች።
"በአንዴ ሶስት ሰው ማሸት ይቻላል እንዴ? እንዲህ አይነት ነገር እንዳለ አልተነገረኝም...ምን ነካቸው ቢያንስ ለተለማማጅ ሰራተኛ እንደዚህ ማድረግ ይገባል?"በውስጧ አጉረምርማ ሳትጨርስ ግራና ቀኝ የነበሩ ሁለት  ወጠምሾች መሀል ያለውን ሰውዬ ወደውስጥ አስገቡትና እነሱ  ወደኋላ  ሸሽተው  ከክፍሉ ወጡ። በራፉ ከውጭ ተዘጋ።
ግድግዳውን ተለጥፋ እንደቆመች ሰውዬው ላይ አፈጠጠችበት። ሰውዬውን ታውቀዋለች..አዎ በደንብ ታውቀዋለች። ሮጣ ሄዳ ልትጠመጠምበት ነበር።ትዝ ሲላት ለካ የምታውቀው በመገናኛ ብዙሀን ነው።ማን ነበር..አዎ አስታወሰችው። እንዴ እዚህ ምን ይሰራል?"
‹‹ጤና ይስጥልኝ ቆንጆ?››አላት በሚያምር ግን አስገምጋሚ በሆነ ድምፅ።

በፍጥነት ወደቀልቧ ለመመለስ ጥረት አደረገች። ፊቷን በፈገግታ አደመቀችና እጇን ለሰላምታ ዘረጋች….በተመሳሳይ ድምቀት ጨበጣት ...
‹‹ጌታዬ ትንሽ አረፍ ትላለህ...ወይስ?››

"ቆይ ትንሽ ትንፋሼን ልሰብስብ... ካንቺም ጋር በደንብ ልተዋወቅ።"አለና ወደሶፋው ሄደና ተቀመጠ፡፡
"ጌታዬ ቀለል እንዲልህ ኮትህን ታወልቀው?"

"አዎ ትክክል ነሽ..››ብሎ በተቀመጠበት  ሶፋ  ሆኖ  ኮቱን  አወለቀ.. በፍጥነት ተቀብላ ወደመስቀያው ሄደችና በጥንቃቄ  ሰቀለችና  ወደ  ሰውዬው ተመለሰችና ፊት ለፊቱ ተቀመጠች።
‹‹ስምሽን ማን ልበል?›› ጠየቃት፡፡
‹‹ቬሮኒካ"አለችው፡፡ ይሄ ስም ድንገት አፏ ላይ የመጣላት ስም ነው…ለዚህ ስራ ትክክለኛ ስምን መጠቀም አግባብ መስሎ ስላልተሰማት ነው እንዲህ ያደረገችው፡፡
‹‹የእኔ ክብሮም››አላት ሰውዬው፡

‹‹ጌታዬ አንተን የማያውቅ ኢትዬጴያዊ ማን አለ?››

‹‹እንደዛ ከሆነ ጥሩ...››አለና ከኪሱ ሞባይሉን አወጣና ደወለ፡፡

"የሚጠጣ አስመጣልን እስቲ"አለና ትዕዛዝ ካስተላለፈ በኃላ ሞባይሉን ዘግቶ ቦታው መለሠና።
"ከነገሩኝ በላይ ቆንጆ ነሽ"አላት
ከት ብላ ሳቀች.‹‹..እንዴ ማነው እንዲህ አይነት ጥብቅ ሚስጥር ያሾለከው?" አለችው፡፡
"የውስጥ ሰላይ አለኝ...ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ ስራው ያንቺን እንቅስቃሴ መከታተል ይሆናል››
"እንግዲህ እኛም ቀዳሚ ስራችን ውስጣችንን ከሰላዬችና ከሰርጎ ገቦች ማፅዳት ይሆናል" ስትለው በራፍ ተቆረቆረ ፡፡ መቀመጫዋን ለቃ ተንቀሳቀሰችና ከፈተች፡፡ ከጋርዶቹ አንዱ ነው። በሰርቪስ ትሪ ሙሉ ጠርሙስ ውስኪ ከሁለት ብርጭቆ ጋር ይዟል። አልፏት ወደ ውስጥ ገባና ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ ወጥቶ ሄደ ...ተከትላው ሄደችና በራፉን ከውስጥ በመቀርቀር ወደ ጠረጴዛው ተመለሰች። ውስኪውን ጠርሙስ ከፈተችና በአንድ ብርጭቆ በመቅዳት አቀረበችለትና   ቦታዋ  ተመልሳ ቁጭ አለች።
"እንዴ ላንቺስ?"

"እኔማ ስራ ላይ ነኝ...ሰክሬ ሰውነትህን ብቦጫጭቅህስ? "

"ነፍሴን አትቦጫጭቂያት እንጂ ለቆዳዬ ችግር የለም...በሰርጀሪ ይድናል "
"አረ ተው ...አንተን ማሳከም አይደለም ከእኔ ከድርጅቴም አቅም በላይ ነው"
"አልገባኝም...ቆዳ ቆዳ ነው?ምኑ ነው የሚከብድ››
‹‹ኸረ ጌታዬ ቆዳ ሁሉማ ቆዳ አይደለም..››
ራሱ ተነሳና ጠርሙሱን አንስቶ በባዶው ብርጭቆ ቀዳና "በይ እንደውም ጠጪና የምታደርጊኝን አድርጊኝና የሚሆነውን አብረን እናያለን....እግረ መንገዴንም የእኔ ቆዳ እንዴት የተለየ እንደሆነ እንዳውቅ ታደርጊያለሽ።

"ጌታዬ በአንድ ምስኪን ላይማ ይሄን ያህል አትጨክንባት››
👍536👏3👎1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

በማሳጅ ስም እየሰራችው ያለችው ስራ ካሰበችው በጣም ውስብስብ ፤ከግምቷ በጣም የረቀ፤ ካደገችበት ስነ-ምግባር ያፈነገጠ፤ የተለየ አይነት አለም ሚያሳይ ቢሆንም ወደ ቦርሳዋ በሚፈስላት ብር ስለሚካካስ አሜን ብለ ተቀብላው ለአመታት ሰትሰራ ነበር፡፡እንጂማ ስራ ሲያስጀምሯት ማሳጅ ቤት ብለው የሰበኳት ስብከት ፌክ መሆኑን የተረዳችው ስራ በጀመረች ሶስት ወርም ሳይሞላት በፊት ነበር፡፡ምክንያቱም ከሚሰጡት አገልግሎቶች ውስጥ ትክክለኛ ያልበተበረዘና ያልተከለሰ ማሳጅ 25 ፐርሰንትም አይሆንም...አሱ ሽፋን ነው፡፡
ወደስራው ጠልቃ ከገባች በኃላ ብዙ ብዙ ገራሚ ገጠመኞችን አስትናግዳለች… አንዳንዶቹ እስከህይወቷ ፍፃሜ የማትዘነጋቸው አይነት ናቸው፡፡
ከበርካታ ያልተለመዱ አይነት ገጠመኞቾ መካከል  አንድን ለምሳሌ ያህል ለማየት ብንችል ነገሮችን ግልፅ ያደርግልናል፡፡ስራ በጀመረች በአራተኛው አመት ነው፡፡ደምበኛ እንዳላት ተነግሯት በሰዓቷ ስራ ቦታዋ ተገኝታ እየጠበቀች ነው፡፡ እንደተባለውም በሰዓቱ በራፍ ተንኳኳ… ከፈተች፡፡በራፍ ላይ በመግባትና ተመልሶ ሮጦ አካባቢውን ለቆ ለመሄድ ውዝግብ ውስጥ የገባ ስሜት ላይ ያለ ጎልማሳ  ሰው  ቆሟል..ሰውዬውን  ታውቀዋለች… በአካል አይደለም..ታዋቂ ሰው ነው..ግን ምንድነው?  ተዋናይ  ነው?  ፖለቲከኛ ነው…? ግልፅ ብሎ ሊታወሳት አልቻለም፡፡‹‹ጌታዬ እንኳን ደህና መጡ ይግቡ.›› አለችና በራፉን በሰፊው ከፈተችለት..የመዝለል ያህል ፍንጥር አለና ወደ ውስጥ ገባ…እሷም በራፉን ዘጋችና  ተከተለችው…እቤቱ  ውስጥ  ከወዲህ  ወዲያ መንጎራደድ ጀመረ‹‹…ጌታይ ችግር አለ? ››ጠየቀችው፡፡

‹‹እዚህ መምጣቴ ትክክል ነው ወይስ ስህተት አላውቅም››

‹‹ጌታዬ ስህትም  ሆነ  ትክክል  አንዴ  መጥተዋል..አረፍ  ይበሉና  ትንሽ ይረጋጉ..እዚህ መምጣቶት ስህተትም ቢሆን የሆነ ጥቅም አይጠፋውም….ደግሞ ነገሮች እንደአጠቃቀማችን ይወሰናሉ…የህይወት ጨለማ ክፍሉ ውስጥ ዳካሮ መውጣት የብርሀኗን ውበት የበለጠ እንድናጣጥም  ግንዛቤያችንን ይጨምርልናል፡፡››
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው፡፡››ብሎ ሶፋው ላይ ቁጭ አለ፡፡ሳባም ወደፍሪጁ ሄደችና የታሸገ ውሀ በማምጣት ከጎኑ ያለ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠችለት..ከፈተና ገርገጭ.ገርገጭ አድርጎ ግማሽ ያህሉን ከጠጣለት በኃላ ከደነና መልሶ አስቀመጠው፡፡ለእኔ እዚህ ቦታ መምጣት ቀላል አይደለም…እዚህ እንድመጣ የጠቆመኝ አንድ ወዳጄ ነው….

‹‹ጥሩ ነው…ምን አይነት አገልግሎት ነው የሚፈልጉት…ሙሉ ማሳጅ ..የእግር ማሳጅ አለ…ከአንገት በላይ ማሳጅ አለን…ሌሎች አገልግሎቶቹም አሉን.መጠጥና
…››
‹‹አይ እንዳዛ አይደለም…የዘረዘርሻቸውንም ሁሉ አንዳቸውንም አልፈልግም…እኔ የምፈልገው እንድታዳምጪኝ ብቻ ነው…ቆይ አሉና እጃቸውን ወደ ኮት ኪሳቸው በመክተት አንድ መለስተኛ ጥራዝ ያለው መፅሀፍ  አወጡና  ዘረጉላት፡፡ግራ በመጋባት ተቀበለችና አነበበችው›

‹‹የኢየሱስ ተአምራዊ የማዳን ስራ››የሚል ርዕስ አለው፡፡ጀርባውን ገልብጣ አየችው ፀሀፊ-ፓስተር ጴጥሮስ ዳንሳ ይላል፡፡ ከፊት ለፊቷ ያለው ሰው ፎቶ ገጭ ብሎበታል…እንደአዲስ ደነገጠች..ሰውዬው በደንብ ታውቀዋለች..በፕሮቴሰታንቱ መንደር በጣም ታዋቂና ዝነኘ ፓስተር ነው…በዛ ላይ የራሱ ሆነ ቴሌቬዥን ጣቢያ ስላለው.በተደጋጋሚ ስብከቱን በቴሌቪዥን መስኮት አዳምጣለች፤አሷ  ጋር መምጣቱ ለምን እንደዚህ እንደከበደው ወዲያው ነበር ግልፅ  የሆነላት..ኸረ መምጣቱ ለእሷ ለራሷ በጣም ገርሟታል..››

‹‹ፓስተር.በእውነት የአርሷ እዚህ  መምጣት  ለእኔ  ትልቅ  ክብር  ነው….እና እንዳሉኝ የሚፈልጉት እንዳዳምጧት ከሆነ በሙሉ ነፍሴ  የለምንም  ፍርድና ትዝብት እንደማዳምጧት እርግጠኛ ይሁኑ››

‹‹እሺ እንደዛ ከሆነ .ማወራሽ ስለመፅሀፉ ነው፡፡በእጅሽ ስለያዝሺው መፅሀፍ ፡፡ መፅሀፉ እውነተኛ የህይወት ገጠመኜ የሰፈረበት ነው፡ይሄ ገጠመኝ ምንም ማጣፈጫ ያልተጨመረበት ንፅህ እውነት ነው ብዬ  አምን  ነበር።ላለፍት  9 ዓመታት ሰፋ ያለ ህዝብ በታደመበት አውደ ምህረት ላይ  ያለመሰልቸት ተርኬዋለሁ። ምዕመኑም አንዳንድ ሶስቴ ሌላውም 13ቴ ደጋግሞ ሰምተውታል። ግን አይ ሰልችቶኛል የሚል የለም፡፡ ከእልልታው ጥቂት ዝንጣፊ የሚቀንስ የለም።በጌታ ሰው አንደበት የሚነገር የጌታ ተአምር እንዴት ሰለቸኝ ማለት ይቻላል...?መታሰብስ።

የዛሬ 14 አመት ለአገልግሎት ደቡብ ኢትዬጰያና ሱዳን ድንበር  አካባቢ  ወደሉ ጎሳዎች እሄዳለሁ።እርግጥ ብቻዬን ሳይሆን ከሁለት ጓደኞቼ ጋር ነበር።እና ጉዞችን ጥቅጥቅ ደን የምናቋርጥበት ከአውሬ ጋር ድብብቆሽ የምንጫወትበት አስደናቂና አስፈሪ ነበር..ግን ደግሞ ጌታ ከእኛ ጋር ስለነበር በዝምታ ሳይሆን በዝማሬ ነበር የተጓዝነው። መንገድ ከሚገኝበት የሁለት ቀን የእግር መንገድ ተሂዶ ነው የሚደረሰው። ጌታ ይመስገን በሰላም ደረስን።ጌታን አገለገልን በሶስት ወር ቆይታችን 10 ብቻ የነበሩትን አማኞች ወደ ሶስት መቶ አሳድገን በመንደሩና በአካባቢው  የጌታ  አገልጋዬች  አድርገን  ጉባኤ  አደራጅተን  ቤተክርስቲያን መስርተን አንደኛውን ጓደኛችንን እዛው  እንዲያገለግል  ትተን  የመልስ  ጉዞ ጀመርን።

በመሀል ደረቀ ጉሮሮውን ለማርጠብ ከጎኑ ካለው ጠረጴዛ ውሀውን አነሳና ላይ የተቀመጠለትን ሀይላደንድ ውሀ በመክፈት እየተጎነጨ በተመስጦና በስሜት ትረካውን ቀጥሏል…፡
…በሁለተኛው ቀን ከጓደኞቼ ነጥለው ጠለፍኝ።አንድ መፅሀፍ ቅድስ ብቻ ነበር በእጄ የያዝኩት፡፡ጌታ ሆይ አንተ ጠብቀኝ አልኩ።የጠለፍኝ ሰዎች ቋንቋቸው የማይገባ እጅግ ከሰው ተነጥለው ጥቅጥቅ ደን ውስጥ የሚኖሩ 2መቶ የማይሞላ ቁጥር ያላቸው አባላት ያላቸው ጎሳዎች ናቸው።
ከወሰዱኝ በኃላ አንድ ጠባብ ጎጆ ውስጥ ጠርቅመውብኝ በራፍን ገንጥዬ እንዳላመልጥ ሁለት ጦር የቀሰሩ ጠባቂዎች በራፍ  ላይ  አስቀመጡ።መፅሀፍ ቁዱሴን ደረቴ ላይ ለጥፌ እኔ ፀልያለሁ...ያለማቆረጥ ከጌታ ጋር አወራለሁ።ሶስታ ቀንና ሶስት ለሊት  እዛች  ጠባብ ጎጆ  ውስጥ  አሳደሩኝ፡፡  በአራተኛው ቀን የተለየ ነገር መታየት ጀመረ፡፡ ውጭ ታላቅ  ክብረ  በዓል  ለማዘጋጀት  ትርምስ  ላይ እንደሆኑ ይታየኛል።‹‹ጌታ ሆይ  ተአምራትህን  በዚህ  ዝግጅት  ላይ  አድርግ›› እያልኩ ፀሎቴን ቀጠልኩ.. ሲጨልም ምቀምሰውን ምግብ አንድ ልጃገረድ ይዛልኝ መጣች፡፡ ጠባቂዎቹ ወደውስጥ እንድታልፍ ፈቀድላት...:: ጎምበስ ብላ ምግብን እያቀረበችልኝ
"አይዞህ"አለችኝ፡፡

‹‹ እንዴ ጌታ ስራውን መስራት ጀመረ ››አልኩ...አማርኛ ትችላለች..

"ለምንድነው የያዙኝ...?ከእኔ ምን ፈልገው ነው ?"ከእሷ ባነሰ ደካማ ድምፅ ጠየቅኳት።
"ለመስዎእትነት..ለአማልዕክቱ ሊያቀርብህ ነው" አለችኝ... ያልጠበቅኩትን መልስ ነበር ያገኘሁት…የጌታ ጥበቃ በዙሪያዬ እንዳለ ባምንም..የልጅቷ በዛን ሰዓት

ከአማርኛ  ችሎታ  ጋር  ስሬ  መከሰት  አንድ  ምልክት  እንደሆነ  ባልጠራጠርም
...ሰውነቴ በፍራቻ መራድ፤አፌም በድንጋጤ መድረቁ አልቀረም ነበር።"
👍795🥰4👏1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ እንደተገለፀው ሳባ እዚህ ስራ ውስጥ የጀመረችውም ጠልቃ ስር ድረስ የገበችውም ለአበቷ ስትል ነው…ከዛ አልፋ ሌላውን የማጥፋትና የማውደም ትግባር ላይም የተሰማራችው በአባቷ ምክንያት ነው፡፡የሚገርመው ደግሞ ያንን በወሰነችበት ጊዜ የዬኒቨርሲቲ ትምህርቷን ላለመቀጠል ወስና ነበር…. እንዴት አድርጋ ምን አይነት ስራ ሰርታ ያን የሚያህል ገንዘብ በማግኘት ልትገዛለት እንደምትች ፍፅም ፍንጭ አልነበራትም፡፡ግን ደግሞ በሙሉ እምነት ነበር ያኔ ፕላን ያደረገችው..ከዛ በአባቷና በስንዱ ጥረት ወደትምህርቷ ተመለሰች ...ተማረች  …ተመረቀች…  ስራ  ያዘች….ሶስት  አመት  በማባከን  እሷ ብዙ ጥረት አድርጋ ትምህርቷን ጨርሳ ዲግሪዋን ጭና ስራ ብትይዝም እንኳን ዘመናዊ ዊልቸር እና መኪና የምትገዛበት ገንዘብ ለማጠራቀም ይቅርና እራሷን ማኖር እራሱ እያቃታት ሲመጣና ከቤተሰቦቾ በተለይ  ሁለት  እግሮቹን  አጥቶ በአሮጌ ዊልቸር እቤት ውስጥ ከቀረ  አባቷ  የድጎማ  ብር  ሲሰጣት  ስትመለከት ተስፋ ወደመቁረጥና ከአመታት በፊት ለአባቷ ለማድረግ ወጥና የነበረው እቅድ የዕብደት ሀሳብ ወይም የልጅ እቅድ ነበር ብላ በመቀበል  ተስፋ  ለመቁረጥ በመዳደት ላይ እያለች ነበር ተአምራዊ በሆነ አጋጣሚ ከትብለጥ ጋር የተገናኘችው..ከዛ ተአምራዊ ስራ አገኘች..በስራ ሂዳቷ የፅድቅ የመሰሉ፤መቅሰፍት ላይ የሚጥሉ፤እብደት የታከለባቸው፤ወንጀል ቀመስ የሆኑ፤ከሞራል ያፈነገጡ ብቻ ውጥንቅጡ የወጣ ስራ በመሰራት በ6 መቶ ሺ ብር እጅግ ዘመና ዊልቸር ገዝታ በአባቷም ሆነ በወዳጅ ዘመድ ለአመታት ተመርቃበት ነበር....ትዝ ይላታል ተአምራዊውን የማሳጅ ስራ ከጀመረች በአንድ አመት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለአባቷ ዘመናዊ ዊልቸር መግዛት የሚያስችላት ብር አግኝታ ነበረ… እርግጥ ዊልቸር ለመግዛት የሚሆናትን ብር ገና ስድስት ወር እንደሰራች ነበር  ያገኘችው  ..ግን በወቅቱ ገበያ ላይ የዋለ በኤሌክትሪክ የሚሰራ እጅግ ዘመናዊና ምቹ ሚባለውን ለመግዛት ፈለገችና ለዛ ሚሆን በቂ ብር ለማግኘት ስትል አንድ አመት መጠበቅ ግድ ሆነባት፡፡ እንደሞላለት ወዲያው ነበር ብሩን  ለካምፓኒው  ገቢ  አድርጋ መጠበቅ የጀመረችው.. .ከዛ ውጭ ባሉ  ወዳጆቾ  አማካይነት  በሁለት  ወር ኢትየጵያ ደርሶ እጇ ገባ፡፡
በህይወቷ እንደዛን ቀን በራሷ ኮርታና ፍፅም የሆነ ደስታ ተስምቷት  አያውቅም ነበር፡፡ ጨረቃ ወለል ላይ በእግሯቾ አርፋ ኮከቦቹን በእጇቸ እየዳሰሳች ምትጫወት ነበር የመሰላት፡፡
ያ ከሆነ ከሁለት አመት በኃላ በአጠቃላይ የማሳጅ ስራዋን ከጀመረች ከሶስት አመት በኃላ ደግሞ ሁለተኛዋን ህልሞን አሳካች፡፡በጣም ተደስታለች….ግን ደግሞ እየተደሰተች ያለችው በበቂ መጠን እንደሆነ እየተሰማት  አልነበረም…የገዛችው መኪና የስድስት ድፍን አመት ህልሟ እና  የሶስት አመት ተአምራዊ ጥረቷ ውጤት ነበር፡፡ይሄን  ህልም  ገና  አባቷ  ሆስፒታል  እግሮቹ  ተቆርጦ  አልጋ  ላይ ተኝቶ ስትመለከት ያሰበችው ሀሳብ ነበር‹‹ለአባቴ መልሼ እግሯቹን ልመልስለት ባልችልም ግን ደግሞ ከቦታ ቦታ  የሚንቀሳቀስበት  አንደ  ዘመናዊ  ዊልቸርና ዘመናዊ መኪና ገዛለታለሁ፡››ብላ የወሰነችው፡፡እና ከአመታት ልፋትና ትጋት በኃላ ሁለቱንም አሳካች፡፡
እጇ የገባውን ልዩና ዘመናዊ መኪና በትዕዘዝ ካስመጣች በኃላ  አዲስ  አበባ ከእንደገና ዊልቸር እንዲያስገባ  ሞዲፋይ  ተደርጎ  እስኪሰራ፤  መቀመጫው ከእንደገና ምቹና  ለማረፍ  እንዲመችም  ተደርጎ ሲስተካከል  ፤አንድ ወር ፈጀበት… ያ ሁሉ ጊዜ ዜናው ቤተሰቦቾ ጋር እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጋ ነበር፡፡
መኪናዋን ተረከበች….የደስ ደስ የሚታረድ ሁለት ሙክት በጎች ገዛችና ጫነች፡፡ ዝግጁ ሆና አደረች፡፡ከዛ እሁድ ለሊት 12 ሰዓት ላይ ነበር እራሷ እየዘወረች ወደ አሳለ ጉዞ የጀመረችው፡፡
ስትሄድ አባቷ ፊት ላይ ምታገኘውን ፈገግታ ለማየት  በመጓጓት  ነበር..ከእሱ አንደበት የሚወጣውን የምርቃት ናዳ ለመስማት ጓጉታ ነበር…አባትዬውም ብቻ ሳይሆን ስንድም በደስታ ስታለቅስና አቅፋት እየወዘወዘቻት ሰታመሰግናት እያሰበች ነበር…. ገና ሳትደርስ ልቧ ሞቆ እንባዋ እየተንጠባጠበባት ነበር ፡፡ የሰፈር
ሽማግሌዎች ሲመርቋትና የሰፈር ወላጆች የእኛስ ልጆች መቼ ነው እንዲህ እንደአንቺ የሚያስቡልን እያሉ እሷን እየመረቁ በልጆቻቸው   ቅር   ሲሰኙ… እያለመች በደስታ ስክራ ነበር፡፡ለሁለት አመት የሰራችውን   ብር አጠራቅማ ይሄው   2.5   ሚሊዬን   ብር   የገዛቻትን   ልዩ   መኪና   በህይወቷ ለሁለተኛ ጊዜ አባቷንም   ሆነ   መላውን   የትውልድ   ቀሄዋን   ኑዋሪዎች ለማስፈንጠዝ በጉዞ ላይ ነበረች፡፡

ዴራ ላይ ስትደርስ ስልኳ ጠራ..አነሳችና አየችው.ስንዱ ነች፡፡
‹ስንድ ልብን ቀጥ ለሚያደርግ ሰርፕራይዝ ተዘጋጂ፡፡ አሁን ስልኬን አንስቼ ሰርፕራይዜን አላበላሽም›› ብላ ስልኩን ሳታነሳ ነበር ወደቦታው  የመለሰችው.. ደግሞ ተደወለ….ዝም አለችው  …አስር  ደቂቃ  ቆየና  ተደገመ.አነሳችና  ሙሉ በሙሉ ዘጋችው፡፡
‹‹…ባይሆን እርቦኛል… ቁርስ ሰርተሸ ብትጠብቂኝ ደስተኛ እሆናለው›› በማለት በውስጧ አጉረመረመችና የመኪናውን ፍጥነት ጨመረች…፡፡.
አሰላ ከተማ ገብታ …ለእቤቷ ከ10 ደቂቃ በታች ነበር የቀራት… መነኸሪያውን ትንሸ አለፈ አለችና ወደሰፈሯ ወደሚወስደው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ከመታጠፏ በፊት የአስፓልቱን ጠርዝ ይዛ መኪናዋን አቆመች…፡፡.
በወቅቱ ለምን እንደዛ እንዳደረገች አልገባትም ነበር….ግን  የሆነ  መግለፅ የማትችለው የተለየ ስሜት እየተሰማት ነበረ….አዎ እያፈናት ነበር…መተንፈስ አልቻለችም ነበር..ገቢናዋን ከፈተችና ወረደች….እርጥበት አዘሉን አየር ወደውስጥ በመሳብ አተነፋፈሷን ለማስተካከል ሞከረች…ወደመኪናዋ ኃላ ሄደችና ኮፈኑን ከፈተች….በጎቹ በጤና እና በንቃት ላይ እንዳሉ በማረጋገጥ መልሳ ዘጋችው፡፡

‹‹ምንድነው የሆንኩት…..?ለምንድነው ቤት ስደርስ እንዲህ ብርክ የያዘኝ? በቀጣይ የሚያጋጥመኝን ደስታ ለማጣጣም ለምን  ፈራሁ?…››በወቅቱ  እራሷን ብትጠይቅም መልስ ማግኘት አልቻለችም ነበር….ወደኃላ  ተመለሺ  ..ተመለሺ የሚል ስሜት ተፈታተናት…
.‹‹እንዴ እየቀወስኩ  ሳይሆን  አይቀርም…?››አለች…እንዲህ  ያስባላት  ትናንት መሽቶ እስኪነጋና ጥዋት ተነስታ ስትወጣ በማይለካ ጉጉት ነበር ስትከንፍ የነበረችው….አዲስአበባ ለቃ ስትወጣ   ምነው መኪናዋ  እንደፕሌን ክንፍ በኖራት አና በርሬ በደቂቃዎች ውስጥ መድረስ በቻልኩ›› ብላ እስከመመኘት ደርሳ ነበር… የዚህ አይነት ስሜት ይሰማት የጀመረው ከሀያ ደቂቃ በፊት  ጀምሮ ነበር ፤.ግን ደግሞ ያፍናት የጀመረችው አሰለ ከተማ ከገባች በኃላ ነበር..ድንገት መንገድ ስታ በሀሩር ንዳድ የተሸፈነ ጭው ያለ ሰው አልባ በረሀ ውስጥ የገባች መስሎ ነው የተሰማት.. እንደምንም እራሷን አጠነከረችና መኪናዋ ውስጥ ተመልሰ ገባች…. መሪውን ተደገፈችና 10 ደቂቃ በፀጥታ አሳለፈች…ከዛ አየር ወደውስጥ እየሳበች ወደውጭ መልሳ እየተነፈሰች ለሶስት ጊዜ ያህል ተመሳሳዩን ካደረገች  በኃላ መኪናዋን አንቀሰቀሰች..
👍548👎1😱1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሳባ ሰገን ላይ የጀመረችውን በቀል ጀምራ እስክትጨርስ አንድ ዓመት ፈጀባት።መጀመሪያ ከትብለጥ ጋር ክፉኛ እንድትጣላና ስራዋን ሙሉ በሙሉ እንድትለቅ አደረገች፡፡ ለአመታት የሠራችበት ከድህነት ማጥ ወጥታ ሚሊዬነር የሆነችበት ክፉውንም ደጉንም ያየችበት ከምትወደው የስራ ቦታ ልታስወግዳት ቻለች፡፡ ትብለጥም የምትወዳት አለቃዋ ብትሆንም በተፈጠረው ጥል እሷም ተበድያለሁ ብላ ስላሰበችና በቂ የሆነ ሀብትና ንብረት ስላፈራች በቀላሉ ለመፅናናት ችላ ነበር፡፡ በወሩ መኪናዋ ነደደች፣ከሁለት ወር በኃላ ደላሎች እስከ መቶ ሚሊዬን ብር የሚያስገኝ ማዕድን አለ ብለው ባላት ብር ሁሉ ድንጋይ  ሸጠውላት  የባንክ ደብተሯን ባዶ እንዲያስደርጉባት ማድረግ ቻለች...ከዛ ጤናዋ ተቃወሰ… ህይወት ስታዘቀዝቅባት የተንጣለለ ቪላ ቤቷን ሸጣ ኮንደሚኒዬም ቤት ገዝታ ገባችና በቀሪው ሚኒባስ ገዝታ በሱ ሹፌር ቀጠራ በማስራት ኑሮዋን መግፋት ጀመረች… ስድስት ወር ሳይቆይ ሙሉ በሙሉ ሚኒባሱን አሰረቀችባት እና እንድትታረድ አደረገች....ከወር በኃላ ሰገን እራሷን በገመድ አንጠልጥላ የመሞቷን ደስታ በዜና አየች።
ከዛ ትብለጥን ሆነ ማንነቷን ያሳጣትን የስራ ቦታዋን ለማውደም ማድባት ጀመረች። ያ  ግን   ቀላል አልሆነላትም። ከሁለት አመት በላይ መጠበቅ   ነበረባት። አሁን ግን ጊዜው ደርሷል፡፡
ሳባ ትብለጥን እና ድርጅቷን በአንድ ጊዜ ለማውደም የዘየደችው ዘዴ የተለየ ነበር፡፡ ታሪኩን በጥልቀትና በዝርዝር በመፅሀፍ ማዘጋጀት፤ከዛ በሌላ ሰው ስም ማሳተምና በሰፊው እንዲሰራጭ ማድረግ ነው።
ደራሲ ጳውሎስ ከሀገር ከመውጣቱ በፊት እሷ እናቱን ልትንከባከብለትና ከመፅሀፉ የሚገኘውን ብር ልትሰጥለት እሱም በሄደበት ሀገር በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆን ሚስጥሩን ሊጠብቅ.. ካልሆነ ግን በእናቱ ላይ ችግር ሊደርስ እንደሚችል ነግራውና በማስፈራራት ሁሉን ነገር ችላ ው ሸኘችው፡፡ከሀገር መውጣቱን ከረጋገጠች ከአንድ ሰዓት በኃላ ለአከፋፋዬች ደውላ መፅሀፉን ማከፋፈል እንዲጀምሩ ነገረቻቸው፡፤
በማግስቱ መፅሀፉ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ውር ውር ማለት ጀመረ...በሶስተኛው ቀን በአንድ የግል ጋዜጣ ላይ "ቤርሙዳ ዘካሳንቺስ" በሚል ርዕስ የከተማዋ ቁጥር አንድ ሀብታሞች፤የመንግስት ሹማምንትና ታዋቂ አርቲስቶቻችን የሚመሽጉበት በማሳጅ ቤት ስም የወሲብ አገልግሎትን ጨምሮ ሀሺሽና ሌሎች ህገወጥ ስራዎች የሚካሄድበት    ቦታን ፀሀፊው ለአመታት ካጠና በኋላ በተጨባጭ መረጃ በማስደገፍ በ220 ገፅ መፅሀፍ  አድርጎ በማሳተም በአሁኑ ወቅት በገበያ ላይ አውሏል። በጣም የሚገርመው ግን በዚህ መፅሀፍ ላይ ታሪካቸው የተገለፁ ሰዎች እስከሚኒስቴር ደረጃ ስልጣን ያላቸው በመሆናቸው ያስገድሉኛል በሚል ፍራቻ ሀገር ለቆ መውጣቱን ማረጋገጥ ችለናል።›› በሚል  የደራሲውንና የመፅሀፉን የሽፋን ስዕል ይዞ ወጣ።
ከዛ ወዲያው ዜናው ከጋዜጣው በመነሳት በፌስቡክ መንደር በሰዓታት ውሰጥ ተሠራጨ...ቲክ ቶክ መንደር ተሸጋገረ... ዪቲዩበሮች ዜናውን እየቆረጡ እየቀጠሉ አባዙት፡፡ በከተማዋ መተረማመስ ተፈጠረ....መፅሀፉ ፓለቲካዊ ይዘት አለው የሚል ወሬ በጎን ተነዛ... የማሳጅ ቤቱ ደንበኞች የነበሩ ቱጃሮች እና ባለስልጣኖች ተበላን በሚል ስሜት በየፊናቸው መፅሀፉን ከያለበት በጅምላ እያስገዙ በማሰብሰብ ከገበያ የማስወጣት ስራ ሰሩ...ሳባ ግን  ለዚህ ተዘጋጅታ ነበር፡፡ከታተመው 5ሺ መፅሀፍ ኮፒ ወደገበያው እንዲለቀቅ ያደረገችው 2 ሺውን ብቻ ነበር።በከፍተኛ ጥንቃቄ በኮንትሮባንድ መልክ ከዋጋው ሁለትና ሦስት እጥፍ ቀሪው 3ሺ. ሞጃዋቹና ኃያሎቹ በማይደርሱበት መንገድ በሳምንት ውስጥ ተሰራጭቶ አለቀ...
ትብለጥ ለሳባ ደወለችላት ‹‹…ልጄ ጉድ ሆነናል››

ምንም እንዳልሰማች…እንዳአዲስ ጮኻ አዳነቀች…ወዲያው እየበረረች ከስሯ ተገኘች፡፡ ዋና አፅናኝና አማካሪዋ ሆነች፡፡
ማሳጅ ቤቱ ለጊዜው ተብሎ የተዘጋው በሶስተኛው ቀን ነበር... ባይዘጋም ወደዛ በስህተት ዝር የሚል ደንበኛ አልነበረም፡፡ እንደውም ከዛ ይልቅ እየደወለ ትብለጥ ላይ የሚጮህባትና የሚፎክርባት ደንበኛ በዛ...ጋዜጠኞችና ዩቲዩበሮች ወሬ ለማነፍነፍ ግቢውን በመክበብ ሰፈሩን አጨናነቁት..በዚህ ጊዜ ታዲያ ሳባ ከትብለጥ ጎን ሆና በዋናነት ሀዘን ላይ ከወደቁና እሷን ከሚያፅናኑ ሠዎች ግንባር ቀደሟ ሆነች... በሳምንቱ ትብለጥ ሙሉ በሙሉ መልሳ እንደማታገግም ገባትና ራሷን ለማትረፍ ወሰነች፡፡ሰራተኞቹን   በጠቅላላ    ከስራ    አሰናብታ    ንብረቷን ለጊዜው በውክልና ለዘመድ አስተላልፋ ወደውጭ ለመውጣት ዝግጅቷን ጨረሰች፡፡ ሁሉም ሰራተኞች ተራ በተራ ከስራ ለቀው ጥለዋት ቢሄዱም ሳባ ግን በውስጧ ደስታዋን እያጣጣመች በውጭ ያዘነች በማስመሰል እስከመጨረሻው ጠብታ አብራት ቆየች ። ለዛውም በእንባ እየታጠበችና በቁጭት የተንገበገበች በማስመስል። ችግሩ ከተከሰተ ከ15 ቀን በኋላ አብራት ውላ ቦሌ ድረስ ሸኘቻትና ወደቤቷ ተመለሰች።
በማግስቱ በግል ጋዜጣ ላይ ሆነ የመንግስት ሚዲያዎች ላይ ‹‹ቤርሙዳ ዘካሳንቺስ›› በሚል ርዕስ አነጋጋሪ መፅሀፍ የተፃፈበት የትብለጥ ማሳጅ ቤት ባለቤት ወ/ሪት ትብለጥ ገ/ኪዳን በግብር ማጭበርበርና ደረሰኝ ባለመቁረጥ ወንጀል ተጠርጥረው ከሀገር ሊወጡ ሲሉ ከቦሌ አየር ማረፊያ ተይዘው በቁጥር ስር ውለዋል።ቤታቸውም ሲፈተሽ ህጋዊ ያልሆኑ ደረሰኞች ከነማሽናቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል…..እያለ የሚቀጥል ዜና ተበተነ።
ሳባ ማታ ትብለጥን  ሸኝታት ከቦሌ ለመመለስ ፊቷን ስታዞር ፓሊሶች ወደ ውስጥ ሲገቡ እየተገፋፉ ነበር የተላለፉት..እንደዛ እንደሚሆን ታውቅ ነበር፡፡ ምክንያቱም ጥቆማውንም መረጃውንም የሠጠችው እሷ ስለሆነች።
ከዛ አዲዮስ
አንደኛውንና ጣፋጩን የህይወት ዓላማዋን ያጨለሙባትን ሁለት ሰዎች በሁለተኛው የህይወት ዓላማዋ ሰባበረቻቸው፣ወጥተው ወጥተው ከተሠቀሉበት አድማስ ሰማይ ሳጥናኤል ባቀበላት ጉልበቷ ጎትታ ሁለቱንም እንጦሮጦስ ጨምራቸዋለች... እሷም አስር አመት ስብዕናዋን ከሸጠችበት፤ማንነቷን ካሳጣት፣ያባቷን ነፍስ ካስነጠቃት ቤርሙዳ  ውስጥ  ልክ  ከአስር አመት ቆይታ በኋላ በታምር ነፃ ወጣች..ወይም የወጣች መሰላት...ለዛውም ቤርሙዳውን ለማንም እንዳይሆን አውድማው...እንደዛ በማድረጓ እስከ 50 የሚጠጉ ሰዎች ስራ እንዳጡ ታውቃለች...ቢሆንም የመቶዎችን ጋብቻ ከመፍረስ ታድጋለች...የሺዎችን ፍቅር ከስብራት ጠግናለች....በህይወት ፍፁም ጥሩ የሚባል ነገር የለም፡፡ያ ማሳጅ ቤትም ጥሩ ተግባር ፈፅሞ አይሰራበትም ብላ አታስብም እዛ ማሳጅ ቤት እሷ ጋር መጥተው ከመንፈስ ስብራታቸው አገግመው ህይወታቸውን ያስተካከሉ......የእሷን ምክር ሰምተው ጋብቻቸውን ከመፍረስ የታደጉ ብዙ ነበሩ፤ግን ከጠቅላላው አንፃር በጣም ጥቂት ናቸው። ስለዚህ እንዲዘጋ በማድረጓ ስህተት እንዳሰራች አታምንም.. ግን ደግሞ በቀሏን  እንዲህ  በስኬት ከተወጣች በኋላ ደስታዋ ለምን የሳምንት እድሜ እንኳን እንዳጣ ነው ግራ የገባት?ለምን ሁሉ ነገር በፍጥነት እንዲህ አስጠላት...? ለምን ከቤቷ መውጣት ከሰው መገናኘት ሆነ መደዋወል አንገሸገሻት...?ቀጣይ ዕቅዷ ምንድነው ራሷን መቅጣት ይሆንን? ይሄንን ስታስብ ዝግንን አላት።ምክንያቱም ለአባቷ ሞት ዋና ተጠያቂ ሰገን፤ትብለጥና፤ ራሷ ነች።
👍724
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ቤት እንደገባች ስልኳን ከፈተችና አሰላ ስንዱ ጋር ደወለች "እንዴት ነሽ ሳባ...? ሀኪሙ ጋር ሄድሽ?" ማውራት ስለማትፈልገው ርዕስ ብታወራላትም እንደምንም እራሷን ተቆጣጥራ መለሰችላት
"አዎ ሄጄ ነበር..መድሀኒት  ቀይሮ  አዞልኛል.. ግን  አሁን  የደወልኩት  አንድ ጓደኛዬ ሱባኤ ልትገባ  ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም  ልትሄድ  ነበር. ለተወሰነ  ጊዜ በፆምና በፀሎት ብናሳልፍ ጥሩ ነው አለቺኝ"
"እና ምን አሰብሽ?"
"እኔ እንጃ ..ውስጤ ግን ሂጂ ሂጂ እያለኝ ነው፡፡"
"ብትሄጂ ጥሩ ነው ብቻ እንዳይከብድሽ ነው የምፈራው"
"ግድ የለሽም ስንድ.. እንደምንም ልሞክረው"
‹‹ታዲያ መች አሰባችሁ?"
‹‹ነገ ጠዋት"
"ስንቅ ምናምን ሳለዘጋጅልሽ?"
"ስንዱ ደግሞ ሁሉ ነገር ሱፐር ማርኬት አለ...›› "ዳቦ ቆሎ፤ኩኪስ፤በሶም እንዳትረሺ.."
"በቃ ስንዱ አታስቢ….ምን አልባት ስልክ ካልተፈቀደ ላልደውልልሽ እችላለሁ"
"እሺ የአባትሽ አምላክ ከአንቺ ጋር ይሁን...እኔም ፀልይልሻለሁ"
"ቻው ስንድ ..ለራጂ ንገሪው" ስልኩን ዘጋችው፡፡ ወዲያው ሙሉ በሙሉ አጥፍታ ኮመዲኖ መሳቢያ ውስጥ ከተተች። ተወዳጅ የእንጀራ እናቷን  ስለዋሸቻት ፀፅቷታል.. ግን ምንም ማድረግ አትችልም።ላልተወሰነ ቀናተሰ ከሰው ጋር በአካል መገናኘትም ሆነ በስልክ ማውራት አትፈልግም፡፡ ለዚህም ዘዴ መዘየድ ነበረባት
..መጥሪያውን አንጣረረች፡፡ታች ምድር ቤት ኪችን ያለችው..ሰራተኛዋ አለም እየሮጠች መጣች
"ምነው ሳባ ፈለግሺኝ?" "አዎ ቁጭ በይ"
በእንደዚህ አይነት ሁኔታ አውርታት ስለማታውቅ ደነገጠች...ሽምቅቅ ብላ በራፋ አጠገብ   ያለው  ወንበር  ላይ  ተቀመጠችና  የምትነግራትን ነገር  ለመስማት ዝግጅ ሆና መጠበቅ ጀመረች።
"አሁን የምነግርሽን..ለልጁም ንገሪው፤ ከዛሬ ጀምሮ ማንም  መጥቶ  በራፍ አንኳኩቶ ቢጠይቃችሁ የለሁም ..ፀበል ሄጃለሁ.. እዚህ መኖሬን ማንም በስህተት እንኳን እንዲያውቅ አልፈልግም።ማንም እንዲረብሸኝ አልፈልግም። ጫጫታ ኳኳታ እንዳልሰማ። ስራሽን እስከአሁን እንደምትሰሪው መስራትሽን ቀጥይ፤ ግን መቶ ፐርሰንት ራስሽን ችለሽ በመሠለሽ መንገድ ነው የምትሰሪው.. በየቀኑ ደግሞ አንድ አንድ ጠርሙስ ውስኪ እዚህ ጠረጴዛ ላይ ታስቀምጪልኛለሽ... ለጊዜው መጋዘን አለ፡፡ እሱ ሲያልቅ ያው  ከተለመደው  ቦታ ታስመጪያለሽ...የምትፈልጊውን ነገር ከደንበኛችን ሱፐር ማርኬት ሄደሽ እያስመዘገብሽ ትወስጂያለሽ... ከእነሡ ጋር  ስለተነጋገርኩ  ሂሳቡን  እኔ  ነኝ  የምዘጋው። እዛ የማይገኝ እቃ የምትፈልጊ ከሆነ እዛ ቁም ሳጥኑ የታችኛው ኪስ ውስጥ ብር አለልሽ፡፡እኔን መጠየቅ አያስፈልግሽም ..ቀጥታ የምትፈልጊውን ያህል ትወስጂያለሽ..ደሞዛችሁ ያው እንደተለመደው ከባንክ ጋር አጀስት ስላደረኩ ቀናችሁ ሲደርስ በደብተራችሁ ይገባል። ልጁ ቁርስ ምሳ ራቱን እንዳታጎይበት፡፡የሚፈልገው ነገር ካለም እንዳትከለክይው። ጨርሻለሁ በቃ   ወደ ስራሽ ተመለሽ።"
"ሳባ ሰላም ነሽ ግን ?አስፈራሺኝ እኮ"
"ጨረስኩ አልኩሽ እኮ" ወደአልጋው ወጣችና ብርድልብሱን ጥቅልል ብላ ተኛች። አለምም ግራ መጋባቷን በልቧ እንደያዘች ሹክክ ብላ ወጥታ ወደ ስራዋ ተመለሠች። ከዛ በማግስቱ ጠዋት ስትመጣ የተለየች ሳባ ነበረች የጠበቀቻት፤
//////
ሳባ ክፍሏ ውስጥ ከተከተተች 35 ቀን ሞላት

ከሆስፒታል የዶክተሯ ምርመራ ክፍል ውስጥ  ድንገት  ከተገናኘችው  ኤፍሬም የተባለ ሰው ጋር አጓጉል ነገር አድርጋ ከተመለሰችበት ቀን አንስቶ ከበፊቱ በባሰ መልኩ መኝታ ቤቷ ውስጥ ራሷን ደበቀች፡፡ ሰራተኛዋ በቀን ሁለት ጊዜ ምግብ ወደ ክፍሏ አስገብታ ከአልጋው ጎን ባለው ኮመዲኖ ላይ ታስቀምጥላትና ሹክክ ብላ ተመልሳ ትወጣለች፡፡እሷም ከቀረበላት ምግብ 20 ፐርሰንቱን ብቻ ስትጠቀም ከመጠጡ ግን እንጥፍጣፊ ጠብታ አታስተርፍም፡፡
ይህ ድባቴ እስከመቼ እንደሚዘልቅ ማብቂያው የት ጋር  እንደሆነ  ማንም አያውቅም፡ እሷም እያስጨነቃት አይደለም፡፡ከአስር አመት በፊት ከአዲስአባ ዩኒቨርሲቲ በአካውንቲንግ  ተመርቃ  ስራ  ፍለጋ  በየቢሮው  የምትንከራተት፤ የታክሲ የሚቸግራት፤ ካፌ ግብቶ ማኪያቶ ለመጠጣት ድፍረት  ያልነበራት፤ ሚስኪን ንፅህና ፤ባለብሩህ ተስፋ ወጣት ነበረች፡ዛሬ ከአስር አመት በኃላ የተንጣለለ ባለ10 ክፍል ቢላ ቤት ያላት፤ ምርጥ የተባለ ሴቶች ሁሉ አይናቸውን  የሚያንከራትቱበት መኪና ምታሽከረክር ፤የባንክ ደብተሯ ላይ አስራ ምናምን ሚሊዬን ብር ያላት የ33 ዓመት አማላይ ግን ደግሞ አባቷን ጨምሮ የአራት ሰዎችን ህይወት ያመከነች ከዚህም በኃላ በአጠቃላይ የህይወት አላማው ትርጉሙም ውሉም የጠፋባት ስብርብረ ያለች ሴት ነች፡፡
በተኛችበት አልጋ ላይ ሳትነሳ እጇን ሰደደችና ኮሚዶኖ ላይ የተቀመጠ ውስኪ ጠርሙስን እንደምንም ጎትታ አነሳች፡፡ገርገጭ ገርገጭ እያደረገች ጠጣችና ክዳኑን በመከራ አሽከርክራ በመዝጋት  እዛው  ቅርቧ  ትራሱ  ስር  አስቀመጠችና ወደድባቴዋ ተመለሰች፡፡
አለም እንደመጣች ወደሳባ ክፍል በመሄድ ሰላም ማደሯን ከተለመለከተች በኃላ ወደኪችን ሄዳ በተቻላት መጣን አጣፍጣ ቁርስ ሰራችና እንደጨረሰች ከዳድና በማስቀመጥ ተመልሳ ወደሳባ ክፍል ሄደች ፤ስትገባ ሳባ ተዘርራ  በተኛችበት አይኖቾን ኮርኒሱ ላይ ሰክታ በሀሳብ ጠፍታ ነው ያገኘቻት ፤ቀጥታ ወደ   ቁም ሳጥኑ ሄደችና  ከፈተች..  ልብስ  መምረጥ  ጀመረች…ፎጣ፤ፓንት…ቢጃማ ከያሉበት መረጠችና አወጣች…..ወደሻወር ቤት ይዛ ገባች.የሻወሩን ሙቅ ውሀ ለኮሰችው…ገንዳውን በውሀ ሞላችው..
ከዛ ተመልሳ ወደመኝታ ቤት ገባችና ወደሳባ ተጠግታ ጎንበስ አለችና ወዝውዛ ከገባችበት ሀሳብ በግድ   መነጭቃ በማውጣት ‹ሳቢ ተነሽ ሰውነትሽን ታጠቢና ልብስ ቀይሪ››አለቻት፡፡
‹‹ምን? ››

‹‹ሰውነትሽን ታጠቢ. ..ውሀውን ለኩሼልሻለሁ….ቀለል ይልሻል››

‹‹ምነው ሰውነቴ ሸተተሸ እንዴ?››
አለም ያላሰበችውን ነገር ስለተናገረቻት ደነገጠች‹‹ኸረ ሳቢ እንደዛ ለማለት ፈልጌ አይደለም››
‹‹በቃ ውጪልኝ››ሰሞኑን ከነበራት ኃይል በመቶ እጥፍ በበለጠ ኃይል አንቧረቀችባት…አለም በጣም ተከፍታ ወደሻወር ቤት ተመልሳ  ገባችና የለኮሰቸችውን ውሀ አጠፋፍታ ያወጣችውን ልብስ ወደቁምሳጥኑ መልሳ ሹክክ ብላ ክፍሉን ለቃ ወጣች፡
ሳባ ልጅቷን እንዲህ ለማበሻቀጥ ምንም ፍላጎት አልነበረትም፡፡እንደዛም ስላደረገች እፍረት ተሰምቷታል..የጮኸችው በእሷ ላይ ይሁን እንጂ እውነታው ግን በራሷ ላይ ነበር ለመጮኸ የፈለገቸው፡፡በገዛ ማንነቷ ነው የተበሳጨችው፡፡
ለመሆኑ እንዲህ ከንቱ ከሆንኩ ቀድሞውንስ ለምን ተፈጠርኩ..?ለምንስ እኖራለሁ? ህይወት ምንድነው? ሞትስ..?በመኖሬ ምን አተርፋለሁ.?.በሞቴስ የማጣው ነገር አለ?ያለፈትን አንድ ወር ሙሉ በእምሮዋ ሚጉላሉ ግን ደግሞ ቁርጥ ያሉ መልሶችን ልታገኝላቸው ያልቸለች ግትልትል በህይወት ትርጉም ላይ ሚያጠነጥኑ ጥያቄዎች ናቸው፡፡
እንዲሁ በድን ሆና ተዝለፍልፋ እንደተኛች..ቀኑ ነጎደ መሸ..አራት ሰዓት ሆነ
👍678👏2🔥1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


እሷ እየተንደረደረች ወደቤቷ ገባችና ፎቁን ወጣች መኝታ ቤት ገባች፡፡ የሆነ ነገር አደናቅፎት እንዳትወድቅ እንኳን  መብራቱን  ማብራት  አልፈለገችም።በዳበሳ ከልጋዋ ላይ ወጣችና ጠርዙን ያዘች፡፡ ወደ ኮመዲኖ ተንጠራራች ቀን በጅምር ያቆመችውን የውስኪ ጠርሙስ አነሳችና ክዳኑን ከፍታ አንደቀደቀችው።

"እስኪ ይሄ ምስኪን ልጅ ምን አደረገኝ?"እራሷን እረገመች። ምነው እግሬን በሠበረው በማለቱ ወደእሱ በመሄዶ እራሷን ወቀሰች፡፡
….////…
ሳባ አሁን በዚህን ሰዓት 80ሺ ብር የተገዛ ባለ 2 ሜትር የተንጣለለ ግዙፍ አልጋ ጠርዝ ላይ ተኝታ  ያቺን ከዛሬ 10 ዓመት በፊት የነበረችዋን  የዋህ  ንፅህ  ጉጉ ተስፈኛ ወጣት አብዝታ እየናፈቀቻት ነው፡፡አሁን ያላትን  ሀብትና  ንብረት  ሁሉ ከፍላ ይቺን ሚስኪን ወጣት ከነሙሉ ክብሯ፤ ንፅህናዋና፤ የዋህነቷ እንዲውም ከሙሉ ተስፋዋ ጋር ቢመልሱላት ዓይኗን ሳታሽ ነበር የምትስማማው፤ ግን ያንን ማድረግ እንደማይቻል ስታውቅት ተስፋ ቆርጣ ይበልጥ አንገት ያስደፋታል፡፡
ደግሞ ይህ ተስፋ መቁረጧ ጫፍ ላይ አድርሶ እርሷን እንድታጠፋ እና ካለችበት ቅዠት እንድትገላገል ቢያግዛት  ደሰተኛ  ትሆን  ነበር፡፡ግን  ህይወትን  በአዲስ መንፈስ አድሳ ከድባቴ እራሷን አላቃ ከሚወቅራት እራስ ምታትና ከሚያኮረማምታት የመንፈስ መሰበር ተላቃ አዲስ ህይወት ለመጀመር የሚያስችላት አቅም ለማግኘት ሆነ እስከዛሬ ባለፈችበት የሀጥያት  መንገድና የተበላሸ የህይወት መስመር የተነሳ እራሷን ተጠይፋ ከህይወት መዝገብ  ላይ በፍቃዷ እራሷን ለማሰናበት የሚያስችል ብቃትና ፅናት ማግኘት አልቻለችም፡፡ያ ደግሞ በአየር ላይ አንገትን በገመድ ታንቆ እንደመንጠንጠል አይነት የሚያቃትት ስሜት ነው እንዲሰማት እያደረጋት ያለው፡፡
አሁን እንደዚህ ምስቅልቅል ባለ ህይወት ላይ ሆና ለሚያያት ሰው ምን ሆነሽ ነው
?ብለው ቢጠይቋት እንዲህ ሆኜ ነው ብላ በድፍረት አንገቷን ቀና አድርጋ የምትመልሰው ለሰሚው ሚዛን የሚደፋና ለእሷም እንዲያዝኑላት የሚያደርግ ምንም ምክንያት የላትም… ምክንያቱም ትክክለኛ ምክንያቷን(ነፍስ ገዳይነተዋን)መናገር አትችልም…ብትናገር ማረፊያዋ እስር ቤት ነው፡፡
እነዛን ሚስጥሮች የማያውቁ  ሰዎች ደግሞ‹‹ባፈቀረችውና ልቧን አሳልፋ በሰጠችው ሰው የመከዳት ችግር አልገጠማትም ..የገንዘብ እጥረት ወይም ኪሳራ ፍፅም የለባትም..የሆነ ወንጀል ሰርታ የተከሰሰችበት ጉዳይ ፈፅሞ የለም..የህክምና ምርመራ አድርጋ እንዲህ አይነት ቋሚ የጤና ችግረ አለብሽ ተብሎ አልተነገራት…ታዲያ ምንድነው እንዲህ የሚሰባብራት?›› ብሎ ቢያስብና ቅብጠት ነው ብሎ ፍርድ ቢሰጥ አይገርምም፡፡
እውነታው ግን አሁን በዚህ ወቅት የሳባ መንፈሶ ተሰብሯል ፤የመኖር ጉጉቷ ተንቆሻቁሾል፤በውስጧ ምንም አይነት  የደስታ  ቅመም  መመረት  ካቆመ ሰነባብቷል፡፡ የመኖርም  ሆነ  የመሞት  ፍላጎቷን  አጥታለች፡፡ማፍቀርም  ሆነ መፈቀር ሳይቀር ትርጉመ ቢስ ሆኖባታል፡፡በአጠቃላይ ስሜተ ቢስ እየሆነች ነው፡፡እንደሚታወቀው ስሜት ማለት የሠው  ልጅ  መንፈሳዊ  ወዝ  ነው።  የሰው ልጅ ህይወትን ጣፍጭና ወዝ ያለው የሚያደርገው የስሜቱ ውጣ  ውረድ ነው ። ሰው ሲከፍው ከላለቀሰና ሲደሰት ካልሳቀ ከፍተኛ የስሜት መሠበር እንዳለበትና ጠንካራ ህክምና እንደሚያስፈልገው በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል።ጠንካራ ስሜት ያላቸው ሰዎች ህይወታቸው ደማቅና ከሩቅ ትኩረት የሚስብ ናቸው።ግን ደግሞ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ሲሰበሩም በትልቁና በቀላሉ ነው፧፡ለዚህ  ነው  የሠውን ስሜት መስበር አስጠሊታ ሀጥያት የሚባለው።
እለቱ ማክሰኞ እኩለቀን አካባቢ ነው።ሰራተኛዋ አለም የምትሰራውን ሰርታ ወደቤት ለመሄድ ስትወጣ ቀናውን በራፍ ላይ ቁጭ ብሎ እንደወትሮው ሲያነብ አገኘችው፡፡ኮቴዋን ሲሰማ ቀና ብሎ ‹‹ልትሂጂ ነው?››አላት፡፡
‹‹አዎ ልሄድ ነው….ግን አንድ ነገር ላማክርህ ነበር፡፡›› ከመቀመጫው ተነሳና ፊት ለፊቷ ቆመ‹‹ምንድነበር?››ጠየቃት፡፡
‹‹የዚህች ልጅ ነገር በጣም አሳስቦኛል…ይሄው መኝታ ቤቷ ከተሸሸገች ሁለት ወር ሊደፍናት ነው..ምግብ አትበላ፤ መጠጣትና ..መተኛት ብቻ ነው ስራዋ…፡፡አሁንማ ሰውነቷ አልቆ አልቆ ስንጥር አክላለች..በዚሁ ከቀጠለች በጥቂት ሳምንታት ውስጥ መሞቷ አይቀርም፡››
‹‹የእሷ ነገር እኔንም አሳስቦኛል…..አንቺ ምን አሰብሽ?››
‹‹እንዴ ግራ ገባኝ ..ከቤት መውጣት እምቢ ካለች፤ ህክምናዋና ካቆረጠች፤ መብላትና መጠጣት ካቆመች..እራሷን ቀስ በቀስ እየገደለች እኮ ነው….አንድ ነገር ከሆነች ደግሞ እኔና አንተ መጠየቃችን አይቀርም.. በተለይ እኔ……በጣም አሳስቦኛል፡፡››
‹‹ቆይ ዘመዶች የሏትም እንዴ?››
‹‹አላት …አሰላ ናቸው እንጂ  ዘመዶች  አሏት  ፡፡እሷ  ግን  ያለችበትን  ሁኔታ ለማንም እንዳንናገር በጥብቅ ነው ያስጠነቀቀችኝ…ግን አሁን አሁን ምርጫ የለኝም..ግፋ ቢል ስራውን መልቀቅ ነው፣ እስር ቤት ከመግባት ስራዬን ባጣ ይሻለኛል…እንደምንም የእንጀራ እናቷን ስልክ አግኝቼያለሁ…ልደወልላት ነው፡፡››
‹‹እኔ የሆነ ነገር አስቤ ነበር››አላት ቀናው፡፡

‹‹ምን?››
‹‹አሁን አልነግርሽም…ግን አንድ ሳምንት ይፈጅብኛል..እንደምንም አንድ ሳምንት ጊዜ ስጪኝና ልሞክር… እስከዛ ምንም ለውጥ ካላሳየች እንዳልሺውም ትደውይላቸዋለሽ፡፡››
ለተወሰነ ደቂቃ እንደማሰብ አለችና‹‹..እሺ  ካልክ…እስከዛሬ  ያልሞተች  መቼስ በአንድ ሳምንት ውስጥ አትሞትም ››ብላ ተሰናበተችውና  ወጥታ  ሄደች፡፡ቀናው ወደ ነበረበት መቀመጫ ተመልሶ ተቀመጠና ማሰላሰል ጀመረ..ምን  አድርጎ ቀጣሪው ከገባችበት የመደበት ስሜት ሊያወጣት እንደሚችል አሰበ …ቢያንስ የተወሰነ ቀና ብላ ወደህክምና ክትትሏ እንድትመለስ ማድረግ እንዳለበት ወሰነና ከተቀመጠበት ተነሳ፡፡ ግቢውን ቆላለፈና   አነስተኛ ምንጣፋና አንድ መፅሀፍ ይዛ ወደ ትልቁ ቤት ገባ።
የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለበት ውስጡ እየገፋፋው ነበር የከረመው ዛሬ  ደግሞ የአለም ንግግር በአፋጣኝ ወደ ተግባር እንዲሸጋገር አስገደደው…እርግጥ ከእሷ የሚያጋጥመውን መልስ ምን እንደሚሆን አያውቅም ግን ምንም ሆነ ምንም ለመጋፈጥ ወስኗል......ሳሎኑን አልፎ ወደፎቅ የሚወስደውን ደረጃ ተያያዘው... መኝታ ቤቷን ቀስ ብሎ ገፍው፡፡ አንገቱን  አሰገገና  ወደ  ውስጥ  ተመለከተ... እንደዚህ ባለ ቅርበት ካያት  ብዙ  ቀናት  አልፈዋል....ፀጉሯ  ተንጨፍርሮና  እርስ በርሱ ተቆጣጥሮ አስፈሪ ሽፍታ አስመስሏታል፡፡ ሆዷ ከጀርባዋ የተጣበቀ ነው የሚመስለው ፤በጣም ከስታለች፤ አይኖቾ ኮርኒሱ ላይ እንደተሰካ ነው ወደ ውስጥ ዘልቆ ገባና መልሶ ዘጋው።በዚህ ጊዜ አይኖቾን አንከባለለችና ወደእሱ ተመለከተች
..የሆነ ነገር እንድትለው ፈልጎ ባለበት ተገትሮ ቆመ...፡፡
ምንም አላለችውም..ወደጥግ ሄደና ግድግዳውን አስጠግቶ ምንጣፉን አነጠፈ... እንደብዲስት መነኩሴ እግሩን አጣምሮ ቁጭ አለ።መፅሀፍን ከፊት ለፊቱ አስቀመጣና እጇቹን አቆላለፈ...ከዛ ልክ እንደእሷ ፀጥ አለ...ልዩነቱ የእሷ ፀጥታ በድንዛዜ ሲሆን የእሱ ፀጥታ በንቃት ነበረ...
👍559🔥1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


የተንታራሰችው ትራስ የሌላ ሰው  ጠረን  ይዞል…ደስ  የሚል  ተፈጥሯዊ ጠረን…እዚህ አልጋ ላይ አብሯት የተኛ ወንድ ፋሲል ብቻ ነበር ፤እሱንም ጨክና አስገድለዋለች….ትናንት ሌላ ወንድ በራሱ ፍቃድ ሰተት  ብሎ  ገብቶ  ከጎኗ በመተኛት አስደምሟታል፡፡ማስደመም ብቻም ሳይሆን ልቧንም ሸርሽሮባታል… ሚኒዬነሩ ዘበኛዋ….ታሪኩ ራሱ   ህልም ነው የሆነባት….ስለእሱ እያሰበች የመኝታ ቤቷ በራፉ ተከፈተ …አለምን ነበር የጠበቀችው….ወደውስጥ እየገባ የነበረው ግን ቀናው ነበር…የሼፎችን አይነት አለባበስ ለብሷል…በእጁ ላይ ባለ ሰፋ ያለ ትሪ ላይ ትናንሽ ሳህኖች ተደርድረው በዛ ያሉ ምግቦችን ይዘዋል፡፡
ምግቡን መኝታ ቤት የምትገኘው አነስተኛ ጠረጴዛው ላይ  አስቀመጠና  መኝታ ክፍል ውስጥ ወዳለ አነስተኛ ፍርጂ በመሄድ ውሀ አወጣ… አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠ…ከዛ ከምግቡ ጠቀለለና በተኛችበት ወደአፏ አስጠጋላት… በጣም ከመደንገጧና ከመደመሟ የተነሳ ያለምንም ተቃውሞ አፏን በጠባቡም ቢሆን ከፈተች…አጎረሳት…፡፡እንደምንም አላምጣ  ስትወጥ  እየጠበቀ  ያጎርሳታል.. በመሀከል ለራሱም አንድ ሁለቴ ይጎርሳል…  እደምንም  ብላ  አንድ  ስምንት የሚሆን ጉርሻ ጎረሰችና ከአቅሟ በላይ  ሲሆንባት  በቃኝ  አለችው፡፡
ያ ምግብ  ትብለጥን ወደ ወህኒ ልካ በክፍሏ ከተከተተች በባለፈው ሁለት  ወር  ውስጥ ወደሆዷ የገባ ብዛት ያለው ምግብ ነው። እሱም ለራሱ የተወሰነ ከጎራረሰ በኃላ ምግብ የተቀመጠበትን ጠረጴዛ ከአልጋው ራቅ አድርጎ  አስቀመጠና  የታሸገ ውሀውን   በማንሳት   ክዳኑን   ከፈተና   አቀበላት።    ከትራሷ    በመጠኑ    ቀና ብላ የተወሰነ ጠጣችለትና መልሳ ሰጠችው።
"ሌላ የምትፈልጊው ነገር ከሌለ መሄዴ ነው? "አላት። "እስኪ ቁጭ በል"አለችው።
ጥያቄዋን ተቀብሎ ከአልጋው ጠርዝ ላይ መልሶ ተቀመጠ"ደህና ነህ አይደል..? ማለቴ ትናንት ህመምህን ለእኔ ስትል ..."
"አታስቢ ሰላም ነኝ"

"ጥሩ..ጥያቄ ብጠይቅህ ቅርይልሀል?"
"የፈለግሽውን"
" ካምፓኒው ማለቴ የባለቤትህ ነበር..አሁን ማን ወረሰው?"

"ማንም ..አሁንም የእኔ ንብረት ነው..አሁንም በጥሩ  ሁኔታ  እየሠራ  ነው..የእሷ ስም የያዘ ካምፓኒ በመሆኑ  የበለጠ እንዲያድግ ነው የምፈልገው.."
"እና የአንተ በቅርብ አለመኖርህ ችግር አይፈጥርም"
"በፍፅም… ያ ካምፓኒ ከቤተሰብ ሲዎረስ የመጣና ከ80 ዓመት በላይ እድሜ ያለው ነው..እዛ ደግሞ እንደእኛ ሀገር አይደለም ..ነገሮች በህግና በስርዓት ስለሚመሩ በተለይ የደረጀ ድርጅት ባለቤቱ ቢኖርም ባይኖርም ልዩነቱ ያን ያህል ነው።ደግሞም እንደእቅዴ ከዛሬ 15 ቀን በፊት ተመልሼ ስራዬ ላይ የመሆን እቅድ ነበረኝ››
‹‹እና ታዲያ ለምን  ሳትሄድ…?ደግሞስ  እንደዛ  ሚኒዬነር  ሆነህ  እዚህ  ዘበኝነት ለምን ?አልገባኝም።››
‹‹እኔም አልገባኝም..በነገራችን ላይ እስከአሁን የካምፓኒው ወስጄ የተጠቀምኩት  ብር የለም… እንደዛ ለማድረግ እቅድ የለኝም..እኔም የራሴ የሆነ የተወሰነ ብር አለኝ።ትናንት እንደነገርኩሽ እዚህ የመጣሁት ለስድስት ወር ነበር… እንደመጣሁ ለሁለት ወር ሆቴል ነበር ያረፍኩት.. ግን  ሰለቸኝ።  አፓርታማ ተከራይቼ ልወጣ አስብኩና ድንገት የእብደት የሚመስል ሀሳብ መጣብኝ።..ለምን መልሼ እንደድሀ አልኖርም..ምን አልባት ያ ሁሉ ቅጣት የመጣብኝ የማይገባኝ የድሎት ቆጥ ላይ ስለተንጠለጠልኩ ይሆናል ..እስኪ ለትንሽ ወራትም  ቢሆን ድህነትን መልሼ ላጣጥመው  ብዬ  አሰብኩና  ከክፍለ  ሀገር  ስራ  ፍለጋ እንደመጣሁ ተናግሬ ቄራ አካባቢ አንድ ክፍል ቤት ተከራይቼ ገባሁ።እና በሰላም አንድ ወር ያህል እንደኖርኩ ከጎኔ ተከራይቶ የሚኖር  አንድ  ደላላ  ነበር  ሲገባ ሲወጣ ሰላም መባባል ጀመርን… ተግባባን በወሬ በወሬ ስራ  አጥ  መሆኔን ነገርኩት። እንደዛ የነገርኩት ስራ እንዲፈልግልኝ አልነበረም።እሱ ግን ዘበኝነት ካላስቀጠርኩህ..አሪፍ ቤት ነው ሴተ-ላጤ  ነች..ካልተመቸህ  ወዲያው  ትለቃለህ ብሎ ድርቅ አለብኝ።ወደአሜሪካ ለመመለስ ከሶስት ወር ያነሰ ጊዜ ቢቀረኝም እንደአድቨንቸር ለምን አልወስደውም አልኩና እሺ አልኩት፡፡ አመጣና ካንቺ ጋር አስተዋወቀኝ..ስራ ጀመርኩ ..ይሄው አራተኛ ወር ልደፍን ነው።
ፈገግ አለችና ‹‹እና እንዴት ነው ስራው ተመቸህ?"ስትል ጠየቀችው፡፡

"አዎ..በጣም እንጂ ...ከመልመዴና  ከመደላደሌ  የተነሳ  የራሴ  ቤት  ሁሉ እየመሠለኝ ተቸግሬለሁ።››
ዝም አለች‹‹...አመሠግናለሁ..እንዲህ እንዳወራ ስላደረከኝ አመሠግናለሁ።››

"አንቺም ዳግመኛ ለሌላ ሰው መጨነቅ እንድጀምርና ...አሁንም እስትንፋሴ ያልተቋረጠ ሰው እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ስላደረግሺኝ በጣም አመሠግናለሁ"
‹እና አሜሪካ መሄዱንስ?›

‹‹በሁለት ወር አራዘምኩት››

‹‹ለምን እንደሆነ መጠየቅ እችላለሁ?››

‹‹ሳይሽ ባለፉት አመታት ያሳለፍኩትን  መከራ  ነው  የምታስታውሺኝ..እንደዚህ ሆነሽ ብሄድ የሆነ ግማሽ ማንነቴን እዚሁ አንቺ መኝታ ቤት ቆልፌበት እንደሄድኩ ነው የምቆጥረው..እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሄጄም ሰላም ማገኝ አይመስለኝም››
‹‹እና መቼም ከዚህ ካልተነሳሁስ?ምን ልታደርግ ነው?››

‹‹ሳባ በዚህች ሶስት ወር ስላንቺ እንደተረዳሁት አንቺ ደጋ ላይ በቅላ ያደገች ..ግን ንፋስ ድንገት አንገዋሎ በረሀ መሀከል የጣላት ...ያንንም  መልመድና  መቀበል አቅቷት የደነገጠች የፅጌረዳ አበባ ነሽ...ያቺ አበባ ባለመደችው የውሀ ጥም ጉሮሮዋ ተሰነጣጥቆ እየሟሸሸች ነው። ...ያቺን ማራኪ ፅጌረዳ አበባ በፀሀይ ንዳድ ስትነድ የህይወት  ፈሳሿ  ከውስጧ  ተሟጦ   ሲያልቅ   እያየሁ   በከፍተኛ   ትዕግስት እና በጥልቅ ሀዘን ስታዘብ ቆይቼያለሁ።ማየት  ብቻም  ሳይሆን  ምን  አልባት ላድናት እችል ይሆን ?በሚል ተስፋ ዙሪያዋን በመኮትኮት በኮዳዬ ለክፍ ቀን ብዬ ያኖርኩትን የውሀ ጠብታ በስሯ ዙሪያ ለማንጠባጠብ በጥቂቱም ቢሆን እየሞከርኩ ነው ፡፡ስሯ ግን በራሱ ሀዘን ጨልሞ መምጠጫ ቀዳዳውን ፅልመት ስለደፈነበት የዕንቁ ያህል ዋጋ ያላቸው ህይወት አድን የውሀ  ጠብታዋቼን በከንቱ  የበረሀው ንዳድ በላቸው።እና እኔ ከንቱው ከዚህ በላይ እዚህ ቆይቼ የፅጌረዳዋ ቅጠሎች ከመወየብና ከመጠውለግ አልፈው እስኪረግፋ ማየት አልችልም፡፡ደግሞ በቅጠል መርገፍ ብቻ የሚያበቃ መስሎ አልታየኝም...የግንድ መሞሸሽና ሙሉ በሙሉ መፍረስ ሊያጋጥም ይችላል...እኔ ታዲያ በየትኛው  ብረት  ልቤ  ይሄንን እስከፍፃሜው ጠብቄ ማየት እችላለሁ..አይ እኔ ለዛ የተሰራሁ አይነት ሰው አይደለሁም..
እና ለእኔ ስትይ ይህቺን  ፅጌረዳ  አድኚያት  ...ወይ  የሚበቃትን  ያህል  የህይወት ውሀ ያለችበት በረሀ ድረስ በመውሰድ ስሯ እስኪረሰርስ፤ሙሽሽ ብሎ  የተኛው ቅጠሏ እስኪነቃና እስኪቃና አጠጪያት… ወይ ደግሞ ቀስ ብለሽ ስሯን ሳትነኪ ዙሪያዋን በመቋፈር ከነስሯ ንቀያትና ቀድሞ ወደበቀለችበትና ወዳደገችበት ስፍራ... ወደለመደችውና ወደምትናፍቀው ቀሄ በመውሰድ መልሰሽ ትከያት።...ለዛ 15 ቀን
👍8211👏2🥰1😁1
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ባለፋ ሶስት ወር ውስጥ ተሰምቷት የማያውቅ ደስ የሚልና የሚያፅናና ስሜት ተሰማት…..እናም ለመጀመሪያ ጊዜ ሰውነቷን ለመታጠብ ወደ ሻወር ቤት ገባች፡፡ግዙፉ መስታወት ፊት ቆማ የለበስችውን ቢጃማ በቁሟ አወለቀችና እዛው ከእግሯ በታች ወለሉ  ላይ  ረገጠችው…መላ  እሷነቷን  በፅሞና  ተመለከተች…. ፀጉሯ በዛ ርዝመቱና ብዛቱ ጭብርር ብሎ ከመንግስት ተሰውሮ ዋሻ ውስጥ ለአመታት ተደብቆ የኖረ ሽፍታ አስመስሏታል፡፡ ….አማላይ  የነበረው  የሠውነቷ ቅርፅ አሁንም እንዳለ ቢሆንም የሰውነቷ ክብደት ግን በተጋነነ ሁኔታ መቀነሱ ወደፊት ወጥተው በጉልህ የሚታዩት አጥንቶቾና  ወደ  ውስጥ  ጎድጉደው  ጭል ጭል የሚሉ አይኖቾ ምስክር ናቸው፡፡ከሁሉም በላይ ያስደነገጣት  ግን  የብልት ፀጉሯ ነው…ከስራዋ ባህሪ አንጻር ለአመታት በሶስት ቀን አንዴ ስትላጭ የኖረች ሴትዬ  ለወራት  ችላ  የተባለው  የብልቷ  ፀጉር  በአስፈሪ  ሁኔታ   አድጎና ተንጨፍርሮ እርስ በርሱ ተቆጣጥሮ በመሀከል ስንጥቅ መኖሩን እራሱ በእጅ ዳብሰው ካልበረበሩት ማወቅ የማይቻልበት ደረጃ ላይ በመድረሱ አስደነገጣት….
….የቀኝ አጇን  ዘረጋችና  አንገቷን  ጠምዝዛ  ብብቷን  ተመለከተች  ..ተመሳሳይ ነው፡፡ በፀጉር ከመሸፈኑም በተጨማሪ ሽታ ከሩቁ ይገፋተራል፡፡ይሄ ሁኔታ ደግሞ ይበልጥ አስገረማት፡፡
‹‹ለምንድነው ግን በቁማችንም እያለን ጭምር ለጥቂት ቀናት ትኩረታችንን ከራሳችን ላይ ስናነሳ እንዲህ በፍጥነት የምንሸተው..?››ስትል ጠየቀች፡፡መልሱን ለመመለስ ግን ብዙም አላስቸገራትም፡፡  ምክንያቱም ከማሳጅ ስራዋ ጋ ተያይዞ ከወሰደቻቸው ኮርሶች አንደኛው የሰው ልጅ አመጋገብ ስርዓት በተመለከተ ነበር ፡፡ ከሺ አመታት በፊት የሞቱ ሰዎች መቃብር ተቆፍሮ ሲገኝና የጥርሳቸው ጤንነትና ጥንካሬ ሲፈተሸ አሁን ካለው የሰው ልጅ ጋር የማይነፃጸር እጅግ ንጹህና ጠንካራ  እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡ምክንያቱም ደግሞ አመጋገባችን ሆኖ ነው የተገኘው፡፡አሁን አብዛኛው ምግቦች ከኬሚካል ጋ ንክኪ ያላቸው… ስኳርነት የበዛባቸውንና  ጤንነትን ሳይሆን ጥፍጥና መሰረት ያደረጉ ናቸው…ስለዚህ እነዚህ ገብተው ተፈጥአዊ ሰውነታችንን በክለዋል….በዛ ላይ ምንቀባቸው ቅባቶች የምንረጫቸው ሽቶዎች፤ የምንታጠብበት ሳሙና በጠቅላላ እንዲህ በቀናት ውስጥ በቁማቸንን እንድንሸት ዋና ምክንያቶች መሆናቸው ለመረዳት ብዙ ምርምርም አያስፈልግም፡፡ ወደመኝታ ቤቷ ተመለሰችና የቁም ሳጥኗን ኪስ ከፈተችና  የፀጉር  መላጫ ማሽኗንና መቀስ አውጥታ በመያዝ ወደ ሻወር ቤት ተመለሰች፡፡ምንም ማሰብ እና መጨነቅ አላስፈለጋትም፡፡ከፀጉሯ ጀመረች…..ከርዝመቱ ወጥራ ወደፊት እየያዘች…..ወገብ ላይ ትጎምደው ጀመር፡፡ ወለሉ በተንጨባረረ እና በተቆጣጠረ
ፀጉር ተሞላ፡፡ ባለከመከም ጎፈሬ ሆነች፡፡በመስታወቱ የተለየች አይነች እስከዛሬ እሷ ራሷ ማታውቃት አይነት ሳባን ተመለከተች፡፡መቀሷን አስቀመጠችና ማሽኗን አመቻቸችና ወደብልቶ ጎንስ ብላ እግሯን ፈርከክ በማድረግ ታጭደው ጀመረ…..ሁሉን ነገር ጨርሳ ሰውነቷን  ታጥባና  ፀድታ ከሻወር ለመውጣት ከ2 ሰዓት በላይ ነው የፈጀባት፡፡
ከዛ ወደመኝታዋ ተመልሳ የተወሰነ እረፍት አደረገች.. ከተኛበት  ብንን  አለችና ስልኳን አነሳች፡፡ እንዲህ አይነት ጥንካሬ እና ፍላጎት በደቂቃ ውስጥ ከየት እንዳመጣች አታወቅም፡፡ደወለች..ከሶስት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡
‹‹ሄሎ ዶክተር››

‹‹ሳባ ለመሆኑ በህይወት አለሽ…?ምን ነካሽ…?ሌላ ሌላው ይቅር እሺ ህክምናሽን ግን እንዴት ታቋርጪያለሽ…ያልተመቸሽ ነገር ካለም እኮ ተነጋግረን ማስተካከል እንችል ነበር..››
‹‹ምን አልተመቻትም ብለህ አሰብክ…ያደረኩት ነገር አግባብ ነበር እንዴ?›ስትል መልሳ ጠየቀችው፡፡
‹‹እሱን ከህክምናሽ ጋር ምን አገናኘው..ምን አልባት በእኔ ህክምናውን መከታተል የሚከብድሽ ከሆነ እኮ በሀገሪቱ ያለሁት የስነ-ልቦና ሀኪም እኔ  ብቻ አይደለሁም
… ተነጋግረን ሁኔታዎችን መስመር ማስያዝ እንችል ነበር››

‹‹ኖኖ ዶክተር እንደዛ አስቤ አይደለም…እኔ እንደውም አንተ ካላከምከኝ ማንም ሊያክመኝ አይችልም››አለችው፡፡
የተናገረችው ትክክል ይሁን አይን እራሷም እርግጠኛ አይደለችም…እርግጥ ከእሱ ውጭ በሌላ ሀኪም መታከም አትፈልም….ደግሞም በእሱም ቢሆን መታከሙን የምትችል መስሎ አልተሰማትም፡፡ህመሟ አካላዊ ቢሆን ችግር የለውም፡፡ ጉበቷ ወይም ኩላሊቷ ቢሆን ወይም ማህፀኗን አሟት ልብሶቾን አወላልቃ እግሮቾን አንፈርክካ መላ ሚስጥሯን ለእሱ  ማሳየት  ቢሆን  ምንም  አይመስላት ነበር፡፡…..እሱ ፊት ስትቀርብ ከኤፍሬም  ጋር  በገዛ  ምርመራ  ክፍሉ  የሰራችው ነውር ነው ትዝ የሚለው የገዛ ወንድሙን ስታማግጥበት…ዝግንን አላት፡፡
‹‹እና ታዲያ ለምን እራስሽን  ሰወርሽ….?እንዴት  እዲህ  ይጠፋል…..?ደግሞ ለህክምና ፋይል ላይ ያስመዘገብሽ መረጃ በጠቅላላ የተሳሳተ ነው….አድራሻሽን ጭምር  ..አንድ ትክክል የሆነው ስልክ ቁጥርሽ ቢሆንም እሱንም ጠርቅመሽው ይሄው ስንት ወር፡፡››

ደስ አላት…ስለእሷ እንዲህ ሲጨነቅና ሲብሰለሰል መክረሙ ደብዝዞ እና ሊከስም ጫፍ ላይ ደርሶ የነበረ ተስፋዋ በጥቂቱም ቢሆን ቢል ቢል እያለ  እንዲነቃቃ ተጨማሪ ነዳጅ ሆኖ ሲያነቃቃት ተሰማት፡፡
‹‹እና አሁን እንዴት ነሽ…?የት ነሽ..?ሀገር ውስጥ ነሽ?››

‹‹አዎ እዚሁ ነኝ፡፡››

‹‹እና እንዴት ነሽ?፡፡››

‹‹እኔ እንጃ ..ምን ላይ እንደሆንኩ አላውቅም…እንዴት እንደሆንኩ አላውቅም….. መኖሬን እራሱ አላውቅም….ለምን አሁን አንተ ጋ እንደደወልኩም አላውቅም….
››አለችው፡፡

ከንግግሯ አሁን ያለችበት ሁኔታ ከወራት በፊት ለመጨረሻ ጊዜ ካገኛት እጅጉኑ የከፋ እንደሆነ ወዲያው ተረዳ….ስለእሷ ሲያስብና   ሲጨነቅ   የከረመው   ግን ከዚህም የከፋ ነገር ላይ እራሷን ትጥላለች ብሎም ጭምር ስለሰጋ ነበር…እራሱን ያጠፋ ሰው ዜና በሶሻል ሚዲያም ሆነ በሜን እስትሪም ሚዲያ ሲሰማ ደንግጦ በንቃት ዜናውን እስከመጨረሻው ለማየት ሲጥር የነበረው እሷን አስቦ ነው፡፡አሁን  ግን በከፋ ሁኔታ ላይም ሆና ቢሆን በህይወት መኖሯ ብቻ አስደሰተው፡፡
‹‹አይዞሽ ይሄ በማንኛውም ሰው ላይ በሆነ ጊዜ ላይ የሚከሰት ነው..አንቺ ደግሞ ከዕድሜሽ በላይ ብዙ ነገር ያየሽና ብዙ ነገር ምታውቂ ጠንካራ ልጅ ነሽ...እኔም ደግሞ በፈለግሽኝ ጊዜና መንገድ ከጎንሽ ነኝ፡፡››
‹‹አንተ ከጎኔ መሆንህን በመስማቴ ተደስቼያለሁ…አመሰግናለሁ፡፡››

‹‹እና መች ብቅ ትያለሽ?›

‹‹እኔ እንጃ››አለችው የምትለው ግራ ገብቷት…

‹‹እኔ  እንጃ  ማለት  ምን  ማለት  ነው…ህክምናው  ቢቀር  አንኳን  ናፍቀሺኝል… ሆስፒታል መምጣት ካስጠላሽ የፈለግሺው ቦታ መገናኘት እንችላለን፡፡››
‹‹ካልክ ነገ ስንት ሰዓት ይመችሀል?››

‹‹እንቺ የሚመችሽን ሰዓት ነገሪኝ እኔ ፕሮግራሜን አሬንጅ ማድረግ እችላለሁ›› እሷን ከማግኘት የሚቀድምበት ምንም ጉዳይ የለውም፡፡
‹‹በቃ 10 ሰዓት እንገናኝ..››

ደስ አለው….‹‹እሺ የት እንገናኝ?›› ነገረችው
‹‹ችግር  የለም….እንገናኛለን…››

‹‹እሺ ዶ/ር ….አመሰግናለሁ››
👍697👏4🥰2
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ለ15 ቀን ያህል በሶስት ቀን አንዴ እየተመላለሰች ህክምናዋን መከታተልና የታዘዘላትን መድሀኒት በመጠቀም ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት ከጀመረች በኃላ... ቀናውና ሳባ እሷ መኝታ ቤት አንድ አልጋ ላይ ጎን ለጎን ተኝተው እያወሩ ነው።

‹‹እንግዲህ አሁን ጥሩ ሁኔታ ላይ ነሽ ...ቀጣይ  እቅድሽ ምንድነው?›› "ቀጣይ እቅዴ አንተን ማግባት"አለችው ፍርጥ ብላ
"እውነቴን እኮ ነው"

""ወደአሰላ እመለሳለሁ...እዛ የእንጀራ እናቴ የጀመረችልኝ በጣም እስፔሻል የሆነ ስራ አለ …እሱን በሰፊው መስራት ነው የምፈልገው።››

"ምንድነው ስራው?"

"ልነግርህ አልችልም...የዛሬ ሳምንት አብረን እንሄዳለን ..የምወዳት እናቴን አስተዋውቅሀለው..ትንሹ      ወንድሜም      እርግጠኛ      ነኝ      ይወድሀል... እናም የምወዳትን እትብቴ የተቀበረባትን ከተማዬን አስጎበኝሀለው...ከዛም የምሰራውን ስራ አሳይሀለው።››

"በጣም ደስ ይለኝ ነበር...ግን እኮ የዛሬ ሳምንት የምበርበት ቀን ነው፡፡"

"ምን?"ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና ቁጭ አለች።
ጭራሽ ትዝ ብሏት አስባበት የማታውቀው ነገር ነው፡፡

ቅዝዝ እና ክፍት ብሏት፡፡"የእውነት ጥለኸኝ ልትሄድ ነው...?."ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹ምን ማድረግ እችላለሁ...?እሺ ብትይኝማ ወደአሜሪካ ብወስድሽ ደስ ይለኛል  "

‹‹እንደዛማ ማድረግ አልችልም...ለስንድ ቃል ገብቼላታለሁ....አባቴን የሚያስደስት ስራ መስራት ነው የምፈልገው፡፡ሀገሬን ለቆ የመሄድ እቅድ የለኝም"

"ይገባኛል....ግን የእኛ ነገርስ?"

"እኳ አትሂድ ምልህ እኮ ለእኛ ብዬ ነው።...አሜሪካ ምን አለህ ?ገንዘብ ብቻ ነው ያለህ። እዚህ ለዛውም አሰላ ለመኖር ያንተ ብር አያስፈልገንም።እኔ ሁሉንም ነገር አስተካክላዎለው።ይሄንን ቤት እንሸጥና ጥሩ  ብር  እናገኛለን፡፡  ከዛ   አሪፍ የሆነ ገቢ ሚያስገባ ድርጅት እናቋቁማለን..፡፡››

"መሄድ እኳ የምፈልገው ለገንዘብ አይደለም...የካትሪንና የሱዛና ስም ከስሞ እንዲጠፋ ስለማልፈልግ ነው።በካምፓኒው አመታዊ ትርፍ የሚንቀሳቀስ ካትሪን ኤንድ ሱዛና ፋውንዴሽን የሚባል የእርዳታ ድርጅት ለማቋቋም አስቤ ነበር።

"የሚገርምና ደስ የሚል ሀሳብ ነው።.....ግን ፍውንዴሽኑ ምን ላይ ነው የሚሰራው..?ሀሳብህ እንዴት ነው?።››

"እሱን  ገና  አልወሰንኩም...ይሄን  አይነት  ሀሳብ   እራሱ   ወደ   አእምሮዬ የመጣው እኮ አሁን በቅርብ እዚሁ አንቺ ቤት ሆኜ ነው።"

"አትለኝም...እየቀለድክ መሆን አለበት?"

"የእውነቴን ነው፡፡ ወደ ኢትዬጰያ ስመጣ የምኖርበት   የህይወት   አላማ   የሚኖር ከሆነ በስክነትና በመረጋጋት ውስጥ ሆኜ ለመፈለግ ነበረ...እና የዛሬ ወር አካባቢ
እዚሁ አንቺ ቤት ሆኜ ሳውጠነጥን ነው ሀሳብ የመጣልኝ። ስለዚህ ዝርዝሩን ገና አሜሪካ ከሄድኩ በኃላ ነው የተወሰኑ ጥናቶችን በማድረግ የምወስነው።"

‹‹እሺ ገባኝ ..ግን ለእኔ ስትል አንድ ነገር አድርግ...››

‹‹ጠይቂኝ".

‹‹ ..ወደአሜሪካ የመሄድ ቀንህን በአንድ ወር አራዝመው..."

የተወሰነ እንደማሰብ አለና‹‹ጥሩ እሺ አራዝመዋለሁ...እና ለአንድ ወር እንዴት አድርገሽ ልትንከባከቢኝ ነው ያሰብሽው?››

‹‹እርግጠኛ ሁን …አሪፍ የሚባል ጊዜ እንድታሳልፍ አደርጋለሁ…››

‹‹እኮ እንዴት እንዴት አድርገሽ..?››

‹‹በመጀመሪያ አሰላ ወስድሀለሁ...ከምወዳት እንጀራ እናቴና ከወንድሜ ጋር አስተዋውቅሀለው...ቀጥሎ ደሴ እንሄዳለን?"

የደሴን ድምፅ ሲሰማ ደነገጠ "ምን  ..?ደሴ? ምን ለመስራት?"

"ቤተሠቦችህን ሳታይ በምንም አይነት  መንገድ  መሄድ  የለብህም..እነሱ  በአሁኑ ጊዜ በምድር ላይ የቀሩህ የቅርብህ  የሆኑ  ሰዎች  ናቸው።እንዳልከው  እነሱን ማግኘት የማትፈልገው የሚጠይቁህን ጥያቄ መመለስ ፈርተህ  ብቻ አይመስለኝም?"

በገረሜታ አፍጥጦ እያያት ‹‹›.እና ለምን ይመስልሻል?"

"ዳግመኛ የእኔ የምትላቸውን ሰዎች ስትነጠቅ ላለማየት ከለህ ፍራቻ ነው። ጨለማውን እየሸሸህ ነው።በጭለማው ሰንጥቀህ ካላለፍክ ደግሞ ብርሀን የሚባል ነገር አታይም…"

"ዋው...የስነ-ልቦና ባለሞያዎችን ታስንቂ የለ እንዴ?"

"አዎ... በበሽታዬ የተነሳ ከእነሡ ጋር አመታትን አሳለፍኩ እኮ ..አሁን  አሁን እንደእነሡ ማሰብ ጀምሬለሁ።"

‹‹..እሱን በደንብ እያየሁ ነው…ግን ነገሩ እንዳልሽው ቀላል አይደለም.."

‹‹ይሄውልህ ቀናው እኔ ካንተ አላውቅም… አንድ ጓደኛዬ ‹ሁሉም ድርጊቶች የአምላክን ፍቃድ ያገኙ  ናቸው::››የሚል እምነት ነበረወ…  ይሄ  ጓደኛዬ  ሀይማኖተኛ አይደለም…ማለቴ ማንኛውንም ሀይማኖት አይከተልም….ግን በእግዚያብሄር ያምናል..መንፈሳዊ ሰው እንደሆነም ይናገራል፡፡እና እሱ እኛ የሰው ልጆች የእግዚያብሄር ህልውና አንድ  ቅንጣት  ሴሎች  ነን፡፡ከመወለዳችን  በፊት  የእግሩ ሴል ከሆንን ከተወለድን በኃላ ምን አልባት የእጆቹ ሴል ሆነን ሊሆን  ይችላል.. ከሞትን በኃላ ደግሞ የጭንቅላቱ ወይም የፀጉሩ አንድ ቅንጣት ሴል ነው የምንሆነው…ስለዚህ ለእግዚያብሄር ከመወለዳችን በፊትም በተወለድን ጊዜም ሆነ ከሞታችን በኃላም ተመሳሳይ ዋጋ  ነው  ያለን…  ቦታችን  እንቅስቃሴ  ላይ መሆናቸን ካልሆነ በስተቀር ምንም የሚቀየር ነገር የለም…››
‹‹ይመስለኛል ጓደኛሽ ለማለት የፈለገው…ሞት   በእግዚያብሄር   ዘንድ   ያለው ትርጉም እኛ እንደምናስበው አይደለም ለማለት መሰለኝ››
‹‹በትክክል….በቃ አሁን እንተኛ"

‹‹እሺ… ከመተኛታችን በፊት ግን አንድ ጥያቄ መልሺልኝ?›› "ምንድነው?"
"እናትሽ..ማለቴ እንጀራ እናትሽ ላንቺ ብላ የጀመረችውን ስራ ምንድነው?እስቲ ንገሪኝ"

"ምነው ሄደህ እስክታየው መጠበቅ አቃተህ..?እኔስ እንደሰርፕራይዝ እንዲታይልኝ ፈልጌ ነበር...ያው ከዚህ በፊት ታሪኬን ስተርክልህ ስለአባቴ አደጋ ነግሬህ ነበረ.. በመኪና አደጋ ሁለቱም እጀግሮቹን አጥቶ በዊልቸር ለአመታት ሲገፍ ኖሮ እንደሞተ...እና ድንቋ እናቴ ስንድ በተለያየ ምክንያት  አደጋ  ደርሷባቸው  አካል ጉዳት ላይ የወደቁ ግን ደግሞ ለመታከምና ለማገገም የፋይናንስ አቅም የሌላቸውን ጉዳተኞች እቤት በመከራየት ተንከባካቢ ቀጥራ ሀኪም ቤት እያመላለሰች ትንከባከባቸዋለች ፡፡ሙሉ በሙሉ ድነው ህክምና የማይፈልጉበት  ደረጃ  ላይ ሲደርሱ የተሻለ ነገር ካገኙ መርቀዋትና  ተሰናብተዋት  ይሄዳሉ። እርግጥ  ካላት አቅም አንፃር ለጊዜው አስር  የሚሆኑ  ሰዎችን  ነው  የያዘችው..እኔ  አቅሜን አጠናክሬ ስሄድ እስከመቶ ሰው መቀበልና መንከባከብ ምችል ይመስለኛል..በሂደት ደግሞ ፈንድ በማፈላለግ…እያስፋፋሁት ሄዳለሁ…..ያን በማድረጌ ምን አልባት ባለፉት አስር አመታት ውስጥ የሰራዋቸውን ቆሻሻ ስራዎች  እግዚያብሄር  ይቅር ይለኝ ይሆናል፡፡በዛ ላይ ደግሞ ከአባቴ የሙት መንፈስ ጋር ያለኝን ቀረቤታ
አጠብቅበታለሁ…እያንዳንዱን አካል ጉዳተኛ ስንከባከብ አባቴን እንደተንከባከቡኩ ነው ሚሰማኝ..እሱም ባለበት ሰማይ ቤት ሆኖ ይደሰትብኝ ይሆናል፡፡››

‹‹የሚገርም ነው..ምን አልባት እኔና አንቺ  መገናኘታችን  እንዲሁ  በዘፈቀደ  የሆነ ነገር አይመስለኝም…የሆነ ታላቅ ህይወት ምስጢራዊ ተልዕኮ ያለው ሊሆን ይችላል፡፡››

‹‹አልገባኝም››
👍1068👎1😁1