አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቆንጅዬ
:
#በሕይወት_እምሻው
:
:
እንደ እህቴ ቆንጆ አደለሁም ። ሕይወቴን ሙሉ በተደጋጋሚ የሰማሁት አንድ ነገር ቢሆን እንደ እህቴ ቆንጆ አለመሆኔን ነው።የሁለት አመት ታላቄ ናት።ትምህርት ቤት እያለን ጀምሮ የአባትና የአያታችንን ስም ሰምቶ እስኪያረጋግጥ ፤ አንድ ቤት ውለን ማደራችንን እስኪያውቅ ድረስ፣ በመልክ መራራቃችንን የሚያውቅ ሰው ሁሉ፣ እህትማማቾች መሆናችንን አያምንም ነበር።

''የሆነ ነገራችሁ ግን ይመሳሰላል....አለ አይደል....ደማችሁ'' እያሉ፣ ሊያፅናኑኝ የሚተጉ ሰዎች አንዳንዴ ይከሰታሉ።እኔና እህቴ በደም እንኳን ብንመሳሰል ከፎቶ ሾፕ በፊትን በኋላ ነው የመንሆነው።በፊቱ እኔ...በኋላዋ እሷ። በዚህ ላይ እህቴ ራሷን መጠበቅ ፣ ውበቷን መጨመር ታውቅበታለች። እኔ አጎፍሬው ስዞር፣ ቅንድቧን መቀንደብ የጀመረችው፣ አስራ አምስት ሳይሞላት ነው።እኔ በቋሚነት በሄር ባንድ አፖሎ አስይዤው ስሄድ፣ ለታክሲ የሚሰጠንን ገንዘብ አጠራቅማ ጸጉሯን መቶከስ የጀመረችው ዘጠነኛ ክፍል እንደገባን ነው።

እንደ እህቴ ቆንጆ አይደለሁም። ግን ጎበዝ ተማሪ ነበርኩ። መደበቅያዬ ትምህርትና መፅሀፍት፣ ብቸኛ የውዳሴ ምንጩ ጉብዝናዬ ስለነበር ፣ ትምህርቴ ላይ ቀልድ አላውቅም ነበር። ገናና ተማሪ ነበርኩ። ከሴክሽን አንደኛ የምወጣ፣ እህቴ ተንጠልጥላ ስታልፍ ፣ ደብል የምመታ።

የእህቴ ምኞት አንዱን ሀብታም በገመዜ አግብታ የድሎት ኑሮ መኖር ነበርና ሃያ ሁለት አመት ሳይሞላት አገባች። የመጀመርያ ድግሪዬን በህግ (ያው በከፍተኛ ማእረግ ተመርቄ)ከእሷ ጋር የመነፃፀር ዘመኔ አበቃ ብዬ እፎይ ባልኩበት ግዜ ግን፣ የእማዬ፣ ''ምናለ እንደሷ ብትሆኚ'' ንዝንዝ ጭራሽ ባሰ።

ለእማ የእኔ በማእረግ ተመርቆ የብዙ መሦርያ ቤቶች፣ ''እኛ ነን የምንቀጥራት'' ሽምያ ብዙ አላኮራትም። በተመረኩ በቀናት ውስጥ ቤት ተቀምጠን እንዲህ አለችኝ፣

''በይ እንደ እህትሽ አንቺም ቶሎ አግቢ።''
''እንዴ! ማስተርሴን ሳልሰራ?'' አልኳት።
''ማግባት በወጣትነት ይሻላል፣ በተለይ እንዳንቺ አይነቱ....''
በተለይ እንዳንቺ አይነቱ ማለት ምን ማለት ነው ? በዚህ ማስጠላትሽ ላይ እድሜ ስትጨምሪበት፣ እንኳን የሚያገባሽ በዕንጨት የሚነካሽ አታገኚም ማለት ነው?

ተውኳት ማስተርሴን ሠራሁ። ኢንተርናሽናል ሎው ነው የተማርኩት። ኤ ደርድሬ ከመመረቄ በፊት ነው ስራ ያገኘሁት። ያውም የኮራ የደራ ኢንተርናሽናል ኤንጂኦ። በዜሮ አመት ልምድ 27050 ብር ስቀጠር በድንጋጤ እንጥሌ ዱብ ሊል ምንም አልቀረው።ለነእማ ስነግራቸው፣ ሌንጬቻቸው እስኪንጠለጠል ድረስ ደነገጡ። አባዬ ጎበዝ አለኝ። እማ ግን ከድንጋጤዋ መልስ ስትል ፣ ''ይሁን...ገንዘብ ብቻውን ምን ይራሰራል ይልቅ ቶሎ አግቢ'' ነበር ያለችኝ።

ኤንጂኦ!

ኤንጂኦ በእህቴ አይነት ሰዎች የተሞላ ነው። በራሳቸው አምረው በገንዘብ ይበልጥ የቆነጁ፣ ፉንጋ ሆነው መተው፣ በገንዘብ ሀይል ደም ግባት ያበጁ ይበዙበታል። ከሚሰሩት በላይ የሚከፈላቸው ሴቶች፣ ቋ ቀጭ ጫማቸውን ሲያንቋቁ ይውላሉ። ውድ ሽቶቸውን በየኮሪደሩ እየረጩ ሲወዛወዙ ያመሻሉ። ሲፎራ ሊፒስቲክ ተለቅልቀው ፣ የ 700 ብር ፓውደር ፊታቸው ላይ ነስንሰው፣ በሳምንት ሁለቴ የሚተኮስ ውድ የብራዚል ጸጉራቸውን ሰክተው፣ በዋክስ ሙልጭ ተደርጎ የተላጨ እግሮቻቸውን በአጭር ቀሚስ አጋልጠው ወዲህ ወዲህ ሲሉ ያረፍዳሉ ይውላሉ

ይሄን ስራ ይዤ ለመቆየት አካባቢዬን መምሰል ነበረብኝ። እንዴት አድርጌ እንደምመስል ግን መንገዱ ጠፋኝ እኔ አሁንም ዩኒቨርስቲ ያለሁ ድክርት ተማሪ ነው የምመስለው። ወፋፍራም እና ቀጭን ሰውነቴ ላይ፣ የሚወዛወዙ ሹራቦቼ ከትልቅ መነፅሬ ቡናጫ (ቡኒና ግራጫ) ሱሪዎቼ ጋር ተደምረው ፣ እድሜ ላይ 20 ዐመተ ይጨምራሉ። ከተማሪዎች ጋር መጨቃጨቅ የሰለቻት የሃይል ስኩል ላይበረርያን እንጂ የኤንጅኦ ሰራተኛ አልመስልም። ሥራ በጀመርኩ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ከሁሉ ጋር የሚግባባው ቄንጠኛው የሥራ ባልደረባዬ ቶማስ ቢሮዬ መጣና፤ ኦፊስ ፓርቲ ጋበዘኝ።

''መቅረት አይቻልም!'' አለኝ ማንነቴን አጢኖ።

''እህ....እስቲ ላስብበት'' (መቀላቀሉን እፈልገዋለሁ ግን ምን ለብሼ ልሄድ ነው ብዬ ተጨንቄ ነው)

''ማሰብ የለም ...መምጣት ብቻ ነው...መምጣት'' ብሎኝ ጥሎኝ ሄደ።ቶማስ በሄደ በደቂቃ ውስጥ አጠገቤ የምትቀመጠውን የዘናጭ ጥግ ጠራኋት።

''ሜሪ...''

''ወዬ..''

''ልብስ የት ነው የምትገዢው?''

''ማርቲስ ኮሌክሽን ሂጂ'' አለችኝ። ከስራ እንደወጣን ሄድኩ። ልብሶቹን ሁሉ እየነካካው በፍርሀት ከቃኘው በኋላ የምትሸጠውን ዘናጭ ልጅ...
''ማታ እራት አለብኝ...ሾፒንግ ሞቴ ነው ....አስቲ አማርጪኝ በናትሽ'' አልኳት። ሰባ ምናምን ነገር ሳልሞክር አልቀረሁም። አላበኝ። በመጨረሻ ከጉልበቴ ትንሽ ከፍ የሚል ፣ በጣም የሚያምር ብሩህ አረንጓዴ ቀሚስ መረጠችልኝ። ''ሲያምርብሽ!'' አለችኝ (የሚከፈላት እንዲህ እንድትል ስለሆነ ከቁብ አልቆጠርኳትም)

''እውነት?'' አልኳት ዝም ላለማለት።

''ውይ በጣም...ሰፊ ነገር ለብሰሽ ስትመጪ ወፍራም ትመስይ ነበር....በጣም ያምራል ሰውነትሽ።'' (ቢከፈላትም ደስ አለኝ....)

''ስንት ነው?'' አልኩኝ።

''950.....ሴል ላይ ነው'' አለችኝ ፈጠን ብላ።

ወይ ሴል እቴ!

ትንሽ አቅማምቼ....

''እሺ በቃ እወስደዋለው....'' አልኩና፣ አንዴ ዞር ብዬ ቂጤን ዐየሁት። ፍጥጥ ብሏል።

''አይዞሽ በጣም አምሮብሻል...ግን....እግርሽን ዋክስ ብታደርጊ ጥሩ ነው....'' አለችኝ።

አስጠቅልዬ ወጣሁ።

''ፐፐፐ ሌላ ሰው መስልሽ የለ እንዴ! ዛሬ ላይብረሪ የምትሄጂ አትመስይም አለኝ ቶማስ፣ ገና ሲያየኝ።

ዐስራ ምናምን ከሚሆኑ የሥራ ልጆች ጋር እንደ ተቀመጥኩ አስተናጋጅ መጣና ፣ ''ምን ልታዘዝ ?'' አለኝ።

''ሁላችንም ቮድካ ይዘናል...ቮድካ አጠጭም..? የሚል ድምፅ ሰማሁና ወደ ቀኝ ዞርኩ። አይቼው የማላውቅ የሚያምር ልጅ ነው።

እኛ ቤሮ ነው የሚሰራው..?
''አይ...መጠጥ ብዙ አደለሁም...ቶሎ እሰክራለዉ...'' አልኩ፣ ትኩር ብዬ ማየቴን ሳላቋርጥ።

''አይዞሽ...ባንዴ እኮ አንድ ብርጭቆ ነው የሚያመጣልሽ...'' አለና ፈገግ አለ። የፈጣሪ ያለ! በእነዚህ ጥርሶቹ እህል አላምጦ ያውቃል?

ነ.....ጭ.....ናቸው።

ትንሽ ተከራክረን ቀይ ወይን፣ ጣፋጭ የአገር ውስጥ ወይን አዘዝኩ። ''የት ዲፖርትመንት ነው የምትሰሪው?'' አለኝ ፣ ወይኑ እንደመጣ። ነገርኩት።

''እኔ ኮሚኒኬሽን ነኝ ግን ልለቅ ነው....'' አለኝ።

''ውይ.... ለምን ?

''የተሻለ ነገር አግኝቼ ነው...ዩ ኤን ዲፒ ልሄድ ነው'' አለኝ።

ከፊቴ ላይ ለምን ? የሚሀውን ቃል አንብቦ ነው?

''አሪፍ.....'' አልኩና ወይኔን ጎንጨት አልኩ።

''ቀሚስሽ በጣም የምራል'' አለኝ በጣም ተጠግቶኝ...

''አመሰግናለው...'' አልኩ፣ ፀጉራም እግሮቼን እንዳያይ ቀሚሱን ያለ አቅሙ ወደ ታች እየጎተትኩ።

''ዋጋውም ያምራ.....'' አለኝ።አሁንም ተጠግቶ ድምፁን ዝቅ አድርጎ። በአንድ ግዜ ፊቴ የምጠጣውን ወይን መሰለ።

ምንም ሳይለኝ እጆቹን ወደ አንገቴ ጀርባ ልኮ ፣ እረስቼው የነበረውን የዋጋ ወረቀት በጠሰው። ሽምቅቅ አልኩ። በሚያምሩ ጥርሶቹ ሣቀና፣ ''አዲስ ነው ማለት ነው....?'' አለ። ዝም ብዬ ያዘዝኩትን ጥብስ በጣቶቼ ማማሰል ቀጠልኩ።

''ምን አይነት ምግብ ነው የምትወጅዉ?'' (ለምንድን ነው ጥርሱ እንዲህ የሚያምረው?)

''አኔ....''

''አዎ...አንቺ
👍61
#ቆንጅዬ
:
#በሕይወት_እምሻው
:
#ክፍል_ሁለት
:
:
... ''ወይኔ... ወይኔ! ኸረ በማርያም ቀስ በይ...ሥጋዬን እንዳትቦጭቂው!'' አልኩ በጩኸት።

ከዚያ ቁንጅናውን ይዞ ከአዲሱ መሥርያ ቤቴ ሊለቅ ለተዘጋጀው፣ ''ቀሚስሽ ያምራል ሽሮ ልጋብዝሽ...'' ምናምን ብሎ ላሽኮረመመኝ፣ የመጀመርያው ወንድ ልጅ እራት እየተዘጋጀው ነው። የእግሮቼን ፀጉሮች በሞቀ ሰም እያስላጨሁ ነው።

ከብስጭት የተሰራ የሚመስል ፊት ያላት ሴትዬ ናት፣ ያለርህራሄ የምትላጨኝ።ሕመሙን መግለፅ አይቻልም። መጀመርያ ለፕላስተርነት ከሚቀርብ ነገር የተሰራውን ፤ በአራት-አራት መአዘን የተቆራረጠ ነገር ታመጣለች። ከዚያ ምድጃ ለይ የተጣደው ሰም ውስጥ ትከተዋለች። ደቂቃ ቆይታ ታወጣዋለች። ጸጉራሙን ቦታ እየመረጠች አንዴ ባቴ፣ አንዴ ቁርጭምጭምቴ አካባቢ፣ ሲላት ጉልበቴ ጋር ትለጥፈዋለች። ይይዛል። ይሄን ግዜ ይሞቃል እንጂ አያምም። ከዛ ግን የጭቃ ጅራፎን ታመጣዋለች። በአንድ ምት ጫፉን ይዛ ላጥ አድርጋ ስታነሳው ፣ ፀጉሬን ይዞ ሲነሳ፣ ከነቆዳዬ፣ ከነስጋዬ የተነሣ ይመስል፣ ነፍሴን ከሥጋዬ የሚያላቅቅ ሕመም ይሰማኛል። ከዛ ይሄንኑ ዐሥሬ አሥራ አንዴ፣ አሥራ ሁለቴ ትደጋግመዋለች። ህመሙን መገለፅ አይቻልም። በትንሹ ሊገልፀው የሚችለው ነገር፣ እሳት በተነከረ አለንጋ እነደመገረፍ ያለ ነው ብላችሁ ነው።

አንዱን የለጠፈችውን ላ...ጥ አድርጋ ባነሳች ቁጥር፣ ወይኔ፣ ወይኔ፣ ኸረ ቀስ ብዬ እጮሀለው።

''የመጀመርያሽ ነው?'' አለችኝ ፊቷን እንዳቀጨመች።

''አዎ...''

ዝም አለች።

''ሥጋዬም አብሮ የተነሳ ያህል ነው የሚያመኝ...'' አልኩ ሰውነቴ እየተንቀጠቀጠ። ቀጥላ የምታነሳው የትኛውን ይሆን በሚል ስጋት ተወጥሬ።

''ሲያጌጡ ይመላለጡ ነው እንግዲህ...'' አለችና ላ...ጥ ! ቀላል እየተላላጥኩ ነው?

ሴቶች ግን ምን ሆነው ራሳቸው ላይ እንዲህ አይነት ሥቃይ የሚያበዙት? ቅንድብ ሲቀነደቡ እዬዬ! ካስክ ሲገቡ መቃጣል፣ ዋክስ ሲደረጉ ስቃይ ....ምን ሆነን ነው?

ቁርጭምጭሚቴ ጋር ላ....ጥ! አደረገችኝ።

''ወይኔ .... አረ ይሄ ነገር ማደንዘዣ ያስፈልገዋል...! አልኩ።
''ሃሃ...'' አለች ፊቷ ሳይፈታ፣ ጥርሷ ሳይታይ። ምን አይነት ሳቅ ነው? መአከላዊ ገራፌ የነበረችና በሰው ስቃይ የምትደሰት ዓይነት ሰው ትመስላለች
ላ....ጥ!

''አይዞሽ ጨርሻለው አሁን...''

ጥርሶቼን እንደበረደው ሰው እያንገጫገጭኩ ፣ ዐይኖቼን ጨፍኜ እንድትጨርስ ተመኘሁ።

''አሁን ይሻላል.... ሌላ ግዜ እንደዚህ አትቆዬ...ባደገ ቁጥር ይባስ ያማል....'' አለችኝ! ፎጣዬን ያለ ፍቃዴ እስከ እንትኔ ድረስ ከፍ አድርጋ። ''ሱሪ አድርገሽ አይመችም'' ብለው አስወልቀውኝ፣ የእነሱን ፎጣ አገልድሜ በውስጥ ሱሪ ነው ያለሁት። ክው ብዬ ፎጣውን በእጆቼ ልመልስ ስል፣

''እንዴ...ምንድነው የሚታየኝ እዛ ጋር....? ደን እያለማሽ ነው እንዴ?'' አለችኝ(ገራፊዋ ቀልድም ትችላለች)። ሣቅኩ።

''እውነት ምንድን ነው እንደዚህ መዝረክረክ...አንድ በይው እንጂ....''አለችኝ እንደተኮሳተረች።

''እህ...'' አልኩ (እሱም አለ ለካ)

''ብራዚሊያን አትፈልጊም? '' አለችኝ በተኛሁበት ቁልቁል እያየችኝ። ''ብራዚሊያን ደሞ ምንድን ነው?'' አልኳት በፍርሃት እያየኋት።

'' ሆ....ያዲስ አበባ ልጅ አደለሽም እንዴ?''

''ነኝ ግን ሰምቼው አላውቅም።''

ነገረችኝ።

''እንዴ! ሴቱ እሱንም ከፍሎ ያስላጫል እንዴ?'' አልኩኝ፣ ከልክ በላይ ደንግጬም፣ ተገርሜም።

''ድብን አርጎ ነዋ...እንኳን ሴቱ ወንዱም ጀምሮል አሁንማ...'' ማመን አልቻልኩም።

(ወንድ ልጅ እዛ ጋር ያለውን ጸጉር ያስለጫል ? ለምን? ታየኝ አንዴ ወደ ግራ...አንዴ ወደ ቀኝ እያደረጉ ሲላጮዋቸው...የፈጣሪ ያለህ)

''እኛ ወንድ አንሰራም...ሴት ግን እንሰራለን...'' አለችኝ።
''እ...'' አልኩ እያቅማማሁ። እግሬን እንዲህ ያመመኝ ፣ ሥሥ ''ብልቴ'' ቢነካ ምን ልሆን እንደምችል አስቤ።
''ከእግር ብዙ አያምም...'' አለችኝ ሐሳቤን የሰማች ይመስል።

''ግን...ለምን ይላጫል ሴቱ...ማለቴ፣ቤታቸው... እራሳቸው በምላጭ ነካ ነካ...ላጨት ላጨት አያደርጉትም?''

በዚያ ፊቷ ፈገግ ማለት የምትችለውን ያህል ፈገግ ብላ፣ ''አይ...በምላጭ ለዛውም ራስሽ ፣ አይመችም እኮ...ሴቱ ደሞ እየወፈረ ቦርጩ ከልሎት እንትናቸውን ካዩ ዘመን ያለፈባቸውም ስንት አሉ እኮ...'' አለች። (ይህቺ ሴትዮ ቀላል ትቀልዳለች እንዴ...) በጣም ሳቅኩ።
''የዛሬ ወንዶች እዛ ጋር ጸጉር ሲበዛ አይወዱም አሉ....እኔ ምን ዐውቃለሁ ...ሴቶቹ እንደዛ ይሉኛል...በወር...በወር እየመጡ ዋክስ የሚያደርጉ ከስተመሮች አሉኝ።

(የዛሬ ወንዶች እዛ ጋር ጸጉር አይወዱም?...እና... ለሽሮ እራት እንትኔን በሞቀ ሰም ላስላጭ?)

''ለምንድን ነው የማይወዱት?'' አልኳት።

''እንጃ...ስንፍና ይሆናላ!...ፈልጎ ላለማግኘት..ሃሃሃ (ሆሆይ ምን ጣጣ ውስጥ ገባሁ...?)

''ስንት ብር ነው?'' አልኩ! በተኛሁበት እያየኋት።
''ከላይ ከላይ ከሆነ 300 ብር...ብራዚሊያን 500 ብር ነው። እንደኔ ግን ብራዚሊያኑ ይሻልሻል። ጥርት ያለ ነው ፣ በዛ ላይ ይቆይልሻል (ከላይ ከላይ የቱ ጋር ነው...?ብራዚሊያንስ ምን ምንን ነው የሚያካትተው ብዬ ለመጠየቅ ፈለኩ )

ቡራዚሊያን ሲሆን አንዲት ፀጉር አትቀርም...በየትም በኩል...''(ሐሳቤን ትሰማለች ልበል?)

''እሺ... ብራዚሊያን ይሁንልኝ...'' አልኩኝ፣ እየፈራሁም ፣ አዲስ ነገር ለማድረግ በመዘጋጀቴም በራሴ እየኮራሁ።

እሷ፣ አዳዳዲስ ፕላስተሮች ሰፋ ያለ ድስት ውስጥ የሚንተከተክ ሰም ውስጥ ስትነክር ፣ እኔ ለመጀመርያ ጊዜ ከፀጉር ነፃ የሆኑ እግሮቼን እርስ በእርስ አነካካሁ። አወይ መለስለሳቸው።ያማርኩ መሰለኝ።

''እሺ....እንጀምር...'' (ከመቼው ሞቀላት?)

''እሺ.... አልኩ ደንበር ብዬ...''?

''እ...ፓንትሽን አውልቅያ ...! አወለቅኩ።

''እግርሽን ወደ ላይ!'' አዘዘችኝ። የፈጣሬ ያለህ!

ከእኔ በቀር ማንም ነክቶት የማያውቅ ጓዳ ጎድጓዳዬን በረብራ አንዲት ፀጉር እንኳን ለወሬ ነገሪነት ሳታስቀር ላጭታ ጨረሰች ።

በረደኝ።

''ዕይ....ው!'' አለችና የፊት መስታወት ሰጠችኝ።

''እ...?'' አልኩ ደንግጬ።

''ዕይው ...ቅር ያለሽ ቦታ ካለ...'' (ወይ ጉድ! ምኑ ቅር ይለኛል?) ዐየሁት ሞልጫኝ የለ እንዴ! ገና ከማህፀን የወጣች አራስ ሴት ልጅ መስያለው።

''አሪፍ ነው?'' አለችኝ፣ መስታወቱን ልትቀበለኝ እየተዘጋጀች።

''አ...አዎ...'' መስታወቱን እየመለስኩላት።

''በሚቀጥለው ስትመጪ ዲዛይን እሰራልሻሀው..''

''እ?..''

''ዲዛይን....የልብ ቅርፅ ምናምን...''

ወይ ጉድ...!

''እሺ...''አልኩ እየተነሳሁ። ገላዬ የኔ አልመስል አለኝ። የተከፋፈትኩ መሰለኝ። መስኮቱም በሩም እንደተከፈተ ቤት ፣ ንፋስ ተመላለሰብኝ...ሱሪዬን ፍለጋ ዞር ስል ፣

''በይ ይልመድብሽ...እርገጠኛ ነኝ ይወደዋል..''

ትታኝ ሄደች።

የሚያየው ወንድ እንደሌለና፣ በምናልባት ከታየ፣ በዚህ ሁሉ ስቃይ እንዳለፍኩ እንደማያውቅ ብታቅ ታዝንልኝ ይሆን።

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍21
#ቆንጅዬ
:
#በሕይወት_እምሻው
:
#ክፍል_ሦስት
:
:

.... ''ውይ ዛሬ ደግሞ ሌላ ሆነሻል....እንዴት እንዳማረብሽ....'' አለኝ፣ ገና እንደተገናኘን።

ቀድሞ ደረሶ እየጠበቀኝ ነበር። ግርግር የበዛበት ምግብ ቤቱ ደንገዝገዝ ያለ ነው ። እንደውም ለጨለማ የቀረበ ነው። ተበሳጨሁ። ይሄን ሁሉ ተሰቃይቼ ውጤቱን ማሳየት የማልችልበት ቤት ይቀጥረኛል ? ስቃዬ የባከነ መሰለኝ።

''እውነት ልዩ ሆነሻል ዛሬ...'' (ህእ! ያለፍኩትን ስቃይ ባየህ!) እንደነገሩ ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳምንና እግሮቼን አነባብሬ ቁጭ አልኩ። አወይ አለሳለስ! አጭር ቀሚሴ ይበልጥ አጥሮ ስንት ያየሁባቸው እግሮቼና ግማሽ ጭኖቼ ተጋለጡ።

''ቤቱን ወደድሽው?'' አለ ፣ ጭኖቼን ያላየ ለመምሰል እየሞከረ። ''አዎ...ደስ ይላል።'' (ግን በጣም ጨለማ ነው...ምን ዋጋ አለው...)

''እሺ.... ስራ እንዴት ነው?''

''ደህና...ነው።''

''እየለመድሽ ነው ?''

''ምንም አልል...''

የተነባበሩት እግሮቼን ስነጣጥላቸው ከየት መጣ ያላልኩት ብርድ ቀጥ ቦሎ ማሕፀኔ ውስጥ የገባ መሰለኝ። መልሼ አነባበርኳቸው።

የተወራለት ሽሮ መጥቶ መብላት ጀመርን።

''ሽሮው እንዴት ነው ?''

''በጣም አሪፍ ነው።''

''አላጋነንኩም አይደል?'' እንጀራ ጠቅልሎ እየጎረሰ

''በጭራሽ በጣም ይጣፍጣል'' አልኩ፣ አንድ ጎርሼ እየተቅለሰለስኩ።

''ከኔ ግን አይበልጥም...''

(ዛሬም ትን ሊለኝ ነበር።ኧረ ፍጥነት ፣ በዚ አይነት እዚያ ጋር መላጨቴ ደግ ኘድርጌለሁ።)

ዝም ብዬ ጉርሻየን ማላመጥ ቀጠልኩ።

''ምነው ?'' አለኝ።

''ምነው?'' መለስኩ።

''አጠፋው እንዴ?'' (ኧረ አላጠፋክም። የኔ ሰፈፍ የሌለው ማር...የኔ ጌታ)

''አይ...''

በልተን ጨርሰን ወጣን።
:::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
ዛሬም እንደወትሮ ተቀጣጥረን ተገናኝተናል። ከተገናኘን ጀምሮ በሳምንት ቢያንስ ሦስት ግዜ እንገናኛለን። ጸጉሬ አልበቀለም። ቀሚሴም አጭር ነው።ጸጉሬም ይተኮሳል።ከንፈሬም ቀለም ይቀባል። ግን ከ ''ዛሬ አምሮብሻል አንዳንድ ገፋ ያሉ ማባበሎች፣ መለጠፎች፣ መነካቶች ውጪ ምንም አልተፈጠረም። ምንም አልሆነም።

እስከዛሬ ለምን አልተሳሳምንም?

አልወደደኝም?

''ምንድን ነው የምታስቢው?'' አለኝ።

''ምንም...''

''ካንቺ በጣም የምወደው ነገር ምን እንደሆነ ታውቂያለሽ? (ምን የኔ ጌታ.....ምን?)

''በጣም ስማርት ነሽ....(ስማርት ፊት.....ካልጠፋ ካልጠፋ ነገር ማንም የሚለኝን ነገር ይለኛል....? ይሄን ሁሉ ሆኜለት ጎበዝ ብቻ ብሎኝ ያልፋል?) መላ ሰውነቴ ኩምሽሽ አለ።

''ታንክስ....'' አልኩ የግዴን።

''ዛሬ ምሽቱ ደስ ይላል...ለምን ትንሽ ወክ አናደርግም?'' አለኝ፣ ብርጭቆው ውስጥ የቀረችውን እንጥፍጣፊ ማክያቶ ጨልጦ። ተነስተን ወጣን።የሚገርም ምሽት ነበር እውነትም ለመሳሳም የተሰራ ምሽት። ትልቅ ጨረቃ፣ ንፋስ የሌለው ግን ቀዝቀዝም፣ ለብም ያለ ውብ አየር። ሰው ያልበዛበት ዛፋም መንገድ። (አረ ሳመኝ በናትህ!)

''ሴት ልጅ ስማርት ስትሆን ደስ ይለኛል....''(እግሬን አላየም ? ቅርፄን አያይም?...ይሄንን ኬክ ወጥቄ ወጥቄ ሆዴ ተንቀርፍፏል እንዴ?)

''ቀስ በል...በሂል መሄድ አልለመድኩም አልኩት።ወሬውን ከስማርትነቴ ለመቀየር...

''ደከመሽ..?''

''እ...ትንሽ....''

''ኡፍ ግን በጣም አምሮብሻል....አለባበስ ደግሞ ስታውቂበት...''(እንዲህ ነው ወሬ....!)

''እውነት?...'' አልኩት ዞር ብዬ እያየሁት።
(ጎበዝ ነሽ ከመባል ውጪ ከወንድ ያገኘሁት የመጀመርያ አድናቆት ነው.....)

''እና ደግሞ ይሄ ቀሚስ....ይቅርታ ግን ሰውነትሽ..''
(ኧረ ይቅርታ አያስፈልግም። አወድሰኝ የኔ ጌታ...እስኪ ነጋ...ክርስቶስ እስኪመጣ አቁመህ አወድሰኝ...አድናቆት የተጠማች የሴት ነፍሴን፣ ደግመህ ደጋግመህ እያወደስክ አረስርሳት...)

''ሰውነትሽ በጣም ያምራል....''(የቱ ጋር የኔ ጌታ? ዘርዘር አድርገዋ...እግሬ ነው....ቂጤ ነው....ዐይኔ ነው... ወይስ ፀጉሬ በትንልኛ የኔ ጌታ...ቅኔ ተቀኝልኝ....!)

''እውነት?'' አልኩኝ።

''በጣም....በተለይ እግሮችሽ....''

''እግሬ ብቻ ነው ደስ የሚልህ ?'' እጁን ጨብጬ ጠየኩት።

አልቦታል።

''ኧረ....ኖ.... ፊትሽ.... ፀጉርሽ... በጣም ቆንጆ ነሽ ...'' ልቤ ምንጃርኛ ጨፈረ።( በጣም ቆንጆ ነሽ ነው ያለው ወይስ ጆሮዬ ነው?)

እጁን የበለጠ አጥብቄ ያዝኩት። (የቅንድቤና የእግሮቼ ውበት እመቤት...ያቺ ባለ ዋክስ ሴትዮ ትመስገን። ደሞዝ ይጨመርላት። ከስተመር ይብዛላት። አሜን።)

''ብዙ ሰው ግን እህቴን ነው ቆንጆ ናት የሚለው..''

''አላምንም...እህትሽ ሰላም ተስፋዬ ምናምን ካልሆነች አላምንም...ብትሆንም አንቺ ጥግ አትደርስም።'' (ሰዎች...ሰከርኩ። በቃላት ብስብስ ብዬ ሰከርኩ....)

''ፎቶዋን ብታይ እንዲህ አትልም....'' እጆቹን ጭምቅ እንዳደረኩ።

''አሳይኛ...''

ቆምኩና ስልኬን ከፈትኩ።

የእህቴን ፎቶዎች አሳየሁት።

''ኧረ በናትሽ ጫፍሽ አትደርስም!'' አለ።

''ባክህ አትፎግረኝ....በጣም ታምራለች....'' ስልኬን ቦርሳዬ እየከተትኩ መለስኩለት።

''በርግጥ ቆንጆ ናት...ማለት ሁሉ ነገሯ ለየብቻው ሲታይ ጥሩ ነው ግን...እንዳነቺ ደም ግባት የላትም....አንቺ እኮ...አንቺ እኮ...በጣም ሴኪሲ ነሽ....''

ፀጉር አልባ እግሮቼ ተንቀጠቀጡ። ሙልጭ ተደርጋ ከተላጨችው የሴትነት ሽንቁሬ ወንዝ ቢጤ መፍሰስ ጀመረ። ቆም አልኩና ተጠጋሁት።

ሳምኩት።

ከንፈሩን ግጥም አድርጌ ሳምኩት።

አንዳንድ ሴቶች በቁርጥ ስጋና ቱርቦ ተደልለው ወደ አልጋ ይሄዳሉ። አንዳንዶቹ ውድ ሽቶ ሲሰጣቸው፤ ገና ሳይቀቡት ልብሳቸውን ለሰጭያቸው ያወልቃሉ። አንዳንዶቹ ለቪትዝ የውስጥ ሱሪያቸውን ያስዘልቃሉ። አንዳንዶቹ ጂ ፕላስ ምናምን ቤት ሲያዩ ጭኖቻቸው ይከፈታሉ። አንዳንዶቹ ላሳቃቸው ወንድ ገላቸውን ይቸራሉ።

የእኔ ምስ ግን አንድ ነው፤ ''ቆንጅዬ'' መባል ''የኔ ቆንጆ'' መባል።....

💫ይቀጥላል💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍31
#ቆንጅዬ
:
#በሕይወት_እምሻው
:
#ክፍል_አራት (የመጨረሻ ክፍል)
:
:

....የእኔ ምስ ግን አንድ ነው ''ቆንጅዬ'' መባል ''የኔ ቆንጆ'' መባል።ከእህትሽ ታምሪያለሽ ብሎኝ አብሬው ያለሁት የመጀመርያ ቦይፍሬንዴ ፣ ለአልጋ ዝግጁ የሚያደርገኝን ቃል ጠንቅቆ ያውቀዋል። ወደ አልጋ ሊያስገባኝ ሲፈልግ ውድ ምሳ፣ ወይ የሻማ እራት አይጋብዘኝም። ወይን አያጠጣኝም። ስጠቶ አሽጎ አያመጣልኝም።

''ቆንጅዬ'' ሲለኝ ፍንክንክ እላለዉ። ''የኔ ውብ'' ሲለኝ ወከክ እላለሁ። ''የኔ ቆንጆ'' ሲለኝ ሙክክ ብዬ እበስላለው። ''ካንቺ በላይ ቆንጆ የለም'' ሲለኝ ሲራገብ እንደዋለ ክሰል ትርክክ እላለሁ። እንኳን ጭኖቼ ሁለንተናዬ ይከፈታል። ብርግድግዴ ይወጣል።

ቆንጆ መባሉ እኔም እንደሴቱ ወግ ደርሶኝ ቦይ ፍሬንድ ኖሮኝ ፤ የአልጋ ላይ ንግስት መሆንን ብቻ አደቸም የሰጠኝ። እሱ ቆንጆ ባለኝ ቁጥር ተጨማሪ የራስ መተማመን በመርፌ እንደተወጋ ሰው ያደርገኛል። እነቃለሁ። እነሳለሁ። ወደ ፊት እራመዳለሁ።

ቆንጅዬ ሲለኝ የደስታ ክትባት እንደተከተብኩ ሁሉ ሁለንተናዬ እየሣቀ፣ እየፈነጠዘ፣ እየተፍነከነከ በኔን ጀምሬ እጨርሰዋለሁ።

ያኔ ነው አለምም በራሳቸው ለሚተማመኑ የምትመች ቦታ መሆኗን ያወኩት።

እንዲህ ያለው ቀን በቦይፍሬንዴ ተስሜ፣ በፍቅር ተሽሞንሙኜ ውዬ ከቤቱ ስወጣ ሰበር ሰካ እል የለ ? ከአንገቴ ቀና ፣ ከትከሻዬ ነቀል ፣ ከእግሮቼ ፈንጠር እያልኩ እሄድ የለ? ይሄን ግዜ የሚያየኝ ወንድ የለም። ይሄን ግዜ የማታየኝ ሴት የለችም። ጸጉሬን በእጆቼ ወደ ግራ ወደ ቀኝ መታ አድርጌ፣ ደረቴን ነፋ አድርጌ በጎዳና ላይ ሽር ብትን ስል፣ የሚያዩኝ ሥራ ፈትተው፣ ''ዛሬ ደግሞ ምን እናድርግ ? ማንን እንልከፍ....?'' ምናምን ብለው ብቻቸውን የቆሙ ቦዘኔ ወንዶች ብቻ አይደሉም። ከሴት ጋር የቆሙ ፣ ከሴት ጋር የተቀመጡ፣ ከሴት ጋር የሚበሉ ፣ ከሴት ጋር የሚጠጡ፣ ከሴት ጋር የሚራመዱ ወንዶች ሁሉ ፣ አፍጥጠው ያዩኛል።

ከሴት ጋር ስል ዝም ብለው ቱታ ወይ ድርይ ለብሰው፣ ሻሽ ሽብ አድርገው የወጡ ሴቶችን አደለም። ቦርጫም ወይ ብጉራም ፣ ቂጣቸው ከጭናቸው ጋር የተቀላቀለ ዓይነት አይስቤ ሴቶችንም አይደለም።

ቂቅ.....ቋ ብለው የወጡ ፣ በከፍተኛ ሂል ጫማ ላይ የቆሙ ፣ በሂውማን ሄር ያበዱ፣ አንጀታቸው ሙትት፣ ቂጣቸው ውጥት ያሉ ቆንጆ ሴቶችን ማለቴ ነው። እንዲህ ዓይነቷ ሴት ጋር ያሉ ወንዶች ናቸው እኔን ለማየት የሚዞሩት። የሚሰርቁት ዐይኖቻቸውን የሚያንከራትቱት። እህቴን የሚመስሉ ሴቶችን ወገብ አቅፈው የሚሄዱ ወንዶች ናቸው፣ አንገታቸውን አዙረው እኔን ዐይተው ከንፈራቸውን እንደ ምግብ የሚልሱት። ነገሮች ፍፁም ተለዋውጠዋል ። የቁንጅና ጣኦት ፣ በየጎዳናው የምመለክ ጣዖት ሆኛለው። ከእነዛ ውብ ሆነው ከተወለዱ የኤንጅኦ ሴቶች ጋር ምሳ ስወጣ ፣ (በ ''ማን ይበለጥ ያምራል'' አደራደር ቃተኛ ተኮልኩለን ተቀምጠን) ምድረ ሀብታም ወንድ ፣ ምግቡና አጠገቡ ያለች ሴቱን ትቶ አይኑን እኔ ላይ ይሰካል ። እጆቼን ልታጠብ ቋ ቀጭ እያልኩ ስነሳ፣ የሠራውን ጉርሻ አፍርሶ እየተደናበረ ይከተለኛል ።

ሰከርኩ። በመፈለግ፣ በፍላጎት በመታየት፣ ብዛት ብስብስ ብዬ ሰከርኩ።በራስ መተማመኔ በዝቶ በዝቶ፣ ወደ ትዕቢትነት ለመቀየር እስኪደርስ ድረስ በወንዶች የአድናቆት ብዛት ሰከርኩ።

አንዱን ቀን ከቢሮ ሴቶች ጋር እራት ልንበላ አንዱ ቤት ተቀምጠናል። ከገባን ጀምሮ በመጥቀስና በማፍጠጥ መሀል ባለ ሁኔታ የሚያየኝ ፣ ብዙም የማያምር ግን ወንዳ ወንድ ልጅ ፣ ከእኛ ቀጥሎ ያለውን ወንበር ዘሎ ያለው ወንበር ተቀምጧል። አላየውም እልና ዐየዋለሁ። ዐይኖቻችን ሲገናኙ ወሬ እንደያዘ ሰው ፣ ወደ ጓደኞቼ እመለሳለሁ። ደግሞ አሁንም እያየኝ ይሆን ብዬ አስብና ቀና ብዬ ዐየዋለሁ።

አሁንም እያየኝ ነው።

ምን ፈልጎ ነው?

ትቼው ጨዋታውን ቀጠልኩ።

''ስሚ'' አለችኝ ከሰባቱ አንዷ ፣ ደጎረሰችውን ጥብስ ፍርፍር ጨርሳ ሳትውጥ።

''እ....'' አልኩ ፣ ሃሳቤ ከወንዳ ወንዱ ልጅ ሳይላቀቅ። አላየውም...አላየውም.... አላየውም.. ዐየሁት።

እንዳፈጠጠ ነው።

ተሽኮረመምኩና ዐይኖቼን ሰበርኩ።

ሆ!

''....እና ስልኳን ካልሰጠሽኝ ብሎ ወጥሮኛል ...ልስጠው?'' አለችኝ ሕይወት።

ልጁን ሳይ፣ ያለችውን ሁሉ አልሰማሁም።

''ምን?'' አልኳት እያየኋት።

''እንዴ ....አልሰማሽኝም እንዴ?''

''አዎ....ሶሪ....ማነው ስልኳን ያለሽ....?''

እንደገና አየሁት። አየኝና ተነሳ። ቁመቱ መዐት ደልዳላ ነገር ነው።

የት ሊሄድ ነው ?

ሕይወት ታወራለች። በዐይኔ ተከተልኩት።

''እና ልስጠው ?'' አለች ሕይወት።

''ስጪው...'' አልኩና ብድግ አልኩ።

የት ሊሄድ ነው ? ዐየሁት ። ወደ መታጠብያ ቤት ነው የሚሄደው ። ተከተልኩት። ኮራደር ጋር ስደርስቆሞ አገኘሁት።

''እምም...በጣም ታምሪያለሽ....'' አለ።ድምፁ ቁመናውን የሚመጥን ነጎድጓድ ነው።በቆምኩበት ፈገግ አልኩ።

''አመሰግናለው አይባልም እንዴ ?'' አለኝ።

''...ይባላል። አመሰግናለሁ። ሽንት ቤት ልገባ ነው. አንዴ....በቆመበት በቄንጥ እየተራመድኩ ጥዬው ሄድኩ። ዐይኖቹ ቂጤ ላይ ተለጥፈው ይሰሙኛል። ድንገት ዞር ብዬ አየሁት። ልክ ነበርኩ።

'' እጠብቅሻለው....'' አለ ጮክ ብሎ። (አዎ ትጠብቀኛለህ።) ያልመጣ ሽንቴን አልሸና ነገር። ሊፒስቲኬን አስተካክዬ እጆቼን ታጥቤ ወጣሁ። እዛው ቆሟል።

''የምር ጠበቅከኝ አይደል...?'' አልኩ፣ አጠገቡ ስደርስ።

''የእኔ ቆንጆ አንቺ ካልተጠበቅሽ ማን ይጠበቃል ታድያ ?'' (እውነት ነው። እኔ ካልተጠበቅኩ ማን ይጠበቃል?)

ስልኬን ሰጥቼው ወደ ወንበሬ ተመለስኩ።

''ስልክሽ ሲጮህ ነበር'' አሉኝ።ዐየሁት። ቦይፍሬንዴ አራት ግዜ ደውሏል። አንድ ቴክስትም አለኝ። ቴክስቱን ከፈትኩት።

''ቆንጅዬ ናፈቅሽኝ...ማታ አትመጪም?''

ለጀመርያ ጊዜ መልስ ሳልሰጠው ስልኬን አስቀመጥኩና ሕይወትን እያየሁ።

''ማነው ስሙ ስልኬን የምትሰጪው ልጅ?'' አልኳት።

''እንዴ...ያን ሁሉ ስለፈልፍ አትሰሚም ነበር እንዴ...እንዴ ቆይ ደግሞ...ማንነቱን ሳታውቂ ነው ስልኬን ስጪው ያልሽኝ እንዴ?'' አለችኝ በመገረም (ከፈለገኝ ማንነቱ ምን ያደርግልኛል? ''ቆኖጆ ናት ፣ ስልኳን አምጡልኝ፣ ከኔ ጋር እንድትሆን ልልፋ፣ ልድከምላት'' ካለ፣ እኔ ምን ቸገረኝ)

''እ....ጫጫታው አልሰማ ብሎኝ ነው...'' አልኩና ዋሸሁ።

''ቢኒያም ነው ...ያ ዶክመንተሪ የሚሰራልን ልጅ...'' አለች ሕይወት።

ቢኒያም ያሚ! ከማማሩ ብዛት ቢሮ ውስጥ በአባቱ ስም የሚጠራው የለም። ሴቶች ሁሉ ቢኒያም ያሚ ነው የምንለው። ቢኒያም ጣፋጭ...

ቢኒያም ያሚ እኔን ፈለገኝ?...ከዛ ሁሉ ዉበት መሀል እኔን መሠጠኝ?

ቦይፍሬንዴ ደወለ። ዘጋሁበት።

ጭካኔ ሊመስል ይችላል ግን ፣ ''ማንም አይወደኝም ፣ አስቀያሚ ነኝ።'' ብላ ታስራ ትሠቃይ የነበረች የሴትነት ነፍሴን ፣ በአንዲት ቃል ከፈታት ወንድ ጋር በውለታ ብቻ ታስሬ መቆየት አልፈልግም። ይህንን አዲስ ቁንጅና ለዓለም ማካፈል ፣ ለብዙ ወንዶች መበተን አለብኝ። አይመስላችሁም? አስቲ አውሩኝ ከበታች ባለው አድራሻ ሀሳባችሁን ላኩ

🔘አለቀ🔘

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍5🔥1