አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ምንትዋብ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_በሕይወት_ተፈራ

....ሰሞኑን ቀለሞቹ ከደረቁለት በኋላ፣ እየተመላለሰ ሲቀባ፣ ሲያስተካክል፣ ሲያበጃጅና ሲሞሽር ቆይቶ ከአምስት ቀናት ድካምና ጥንቃቄ የተሞላው
ሥራ በኋላ፣ ሦስቱን ሥላሤ ሥሎ ጨረሰ። የመጨረሻው ቀን ራቅ
ብሎ ሥዕሉን ሲመለከት ተደነቀ። ሦስቱም በሁሉም አቅጣጫ እኩልና የተመጣጠኑ ናቸው። አንድም የተዛነፈና ከቦታው ውጭ የሆነ ነገር የለም። የፊታቸው ገፅታ ፍፁም ተመሳሳይ ነው። ፊታቸው ሙሉ ለሙሉ ይታያል። በሰማያዊ፣ በቢጫ፣ በነጭና በቀይ ቀለማት አምረዋል።

ተንበርክኮ ምስጋና አቅርቦ ወጣ።

በማግስቱ፣ አለቃ ግዕዛን ከሊቀጠበብት አዳሙ፣ ከአለቃ ተክለየሱስና ከሊቀጠበብት ያሬድ ጋር መጥተው ሥዕሉን ተመለከቱ። ጥላዬ፣ከኋላቸው ቆሞ፣ በእነዚህ ታላላቅ ሠዓሊዎችና የሥዕል መምህራን ላይ ያሳደረውን ስሜት ለማወቅ ተጠባበቀ።

መምህራኑ ፈዘው ተመለከቱ፤ የሚያዩትን ማመን አቃታቸው።

አለቃ ግዕዛን፣ “ጥላዬ፣ ይኸ የፍቅር ውጤት ነው። ፍቅር ብቻ ነው ይኸን የመሰለ ሥራ ሊያሠራ ሚችለው። እስታሁን በሥራህ ደስተኛ ነበርሁ። ዛሬ ግን ይኸን የመሰለ የላቀ ሥራ ስላሳየኸኝ አከብርሃለሁ።

ይኸን የመሰለ የጥበብ ውጤት እንዳይ ዕድሜ ለሰጡኝ ሥላሤ ምስጋናዬን ሳቀርብ፣ ላንተ ደግሞ አድናቆቴን ገልጣለሁ። አንተም ሥላሤን ብቻ ሳይሆን እኔንም ነው ያከበርኸኝ። እኔን እንዳከበርኸኝ አንተን ደሞ ሥላሤ ያክብሩህ። አንተ የሥዕል ንጉሥ ነህ። ከይኸ ቀደም ማንም አልቀደመህም፣ አሁንም ሚደርስብህ የለም ወደፊትም ሚተካህ ዠግና
ሚመጣበት ግዝየ ሩቅ ነው” አሉት፣ ደብቀውና ተጠንቅቀው የያዙትን፣ለማንም ተማሪ አድረገውት የማያውቁትን ምስጋና እያዘነቡለት።

ጥላዬ እግዚሐር ይስጥልኝ ማለት ፈልጎ፣ ልሳኑ ተዘጋበት። በዝምታ
እግራቸው ሥር ተደፋ።

“ተነስ ልዥ ። ንጉሥ እሰው እግር ሥር ኣይወድቅም” አሉት።

ሊቀጠበብት አዳሙም፣ “ውነትም የሥዕል ንጉሥ ነህ። አንተ ዛሬ
ግዕዛንን ብቻ ሳይሆን ሁላችንንም ነው ያከበርኸው፣ ያኮራኸው። ውበት ማለት ይኸ እንጂ ሌላ ምን አለ? አንተ ለብዙ ተማሮች አርአያ
ትሆናለህ። ሚያሳዝነው ሥዕል እንደዝኸ ድንቅ ነገር ሁኖ ሳለ እንደ ቅኔና ዜማ በርካታ ተማሮች የሉትም። ደብረ ወርቅ እንደመጣህና ትምርት እኔጋ እንደዠመርህ፣ ውነትም የሥዕል ንጉሥ እንደምትሆን አውቄ ነበር። የናትህ ማጠን ይለምልም። ዛሬ የአለቃ ሔኖክ ነፍስም በሰማይ ቤት ትዘምራለች። ሥላሤ እጅህን ያለምልሙት” ብለው
ሊስሙት ሲጠጉት፣ ፈጠን ብሎ እግራቸውን ሳመ።

አለቃ ተክለየሱስና ሊቀጠበብት ያሬድም አድናቆትና ምስጋና
አዥጎድጎዱለት፤ ባረኩት፤ እንኳን ደስ ያለህ ብለው ሳሙት። እሱም
እግራቸውን ሳመ።

በምስክር ፊት በሥዕል ትምህርት ተመረቀ።

የመመረቂያውን አነስተኛ ድግስ እንዲቀምሱለት ሁሉንም ወደቤቱ
ይዟቸው ሄደ። እንጎች ያዘጋጀችውን ምግብ በልተው፣ አረቄ ጠጥተው አመስግነውትና መርቀውት ሊሄዱ ሲሉ፣ ሊቀጠበብት ያሬድ በድንገት
ሲቆሙ፣ ሌሎቹም ቆሙ።
ሁሉንም በተራ እየተመለከቱ፣ “በሉ ወንድሞቼ ኸመኼዳችን
በፊት አንድ ቅር ያለኝን ጉዳይ ልናገር ነው” አሉ። “ተማሪ እናታባቱ ያወጡለትን ስም እየተወ ለራሱ ስም ያወጣል። ዜማ ሲማር 'ጥዑመ ልሳን ነኝ ይላል። ቅኔ ሲማር ባሕረ ጥበብ ነኝ... ማንቴስ ነኝ ይላል።አንዳንዴም እሰበሱ ስም ይሸላለማል። ይኸ ልዣችን ግን ትሑትና የሥራ ሰው በመኾኑ ይኸው የባላገር ስሙን እንደያዘ ጥላዬ እንደተባለ
አለ። ምሥጢሩ ደግ ነው፤ ጥላ ከለላ ትኾነኛለኽ ሲሉ ማዶል አባቱ
“ጥላዬ ማለታቸው? ድንቅ ስም ነው። ግና ለእንዳንተ ያለ ጠቢብ
ዛሬ እናንተ ወንድሞቼ ኸፈቀዳችኹልኝ 'ሥሙር' ብዬዋለኹ። ደሞም አይኾንም። ሠዓሊ ተኹኖ ጥላዬ መባል ምሥጢሩ አይገጥምም። ስለዚኸ
ፊቱኑ የነበረ ወግ ነው። መምህራን ለጥበብ ልዦቻቸው ይስማማል
ያሉትን ስም ይሽልማሉ። እና ምን ትላላችኹ? ሥሙር አይዶለም
ጥላዬ?”
ሁለቱም መምህራን በአንድ ድምጽ በደስታ አደነቁት፣ “ቃለ ሕይወት ያሰማዎ ጌታዬ፤ ድንቅ ነው፤ ሥሙር ነው፤ ስሙም አሰያየሙም የተገባ ነው” ብለው አጸኑለት።”

መምህሮቹ በደስታ እያውካኩ ሲሄዱ ሸኝቷቸው እንደተመለሰ መደብ ላይ ጋደም አለ። የተዋጣለት ሥራ እንደሠራ አረጋገጠ። ሕልሙ ሁሉ
እውን ሆነ። ቋራ እያለ ወለቴን ንጉሥ ኸወሰዳት እኔ የሥዕል ንጉሥ ማልሆን? ያለውን አስታወሰ።ምኞቱ ሠመረ።

ዝናው በደብረ ወርቅ ብቻ ሳይሆን፣ አድባራቱን አልፎ መርጡለማርያም ድረስ ዘለቀ። በየደብሩ ያሉት የሥዕል መምህራን እንዲያስተምር
ገፋፉት። ዝናውን የሰሙ የአካባቢው ባላባቶች ደብራቸውን እንዲያስጌጥ ተረባረቡበት።

እሱ ግን አንዴ ለአንዱ ባላባት አድሮ መሥራት ከጀመረ ወደሌላው መሄድ ስለማይችል ለማንም አልታዘዝ አለ። በተጨማሪ፣ ሥዕል ታሪክ
ተናጋሪ፣ አስተማሪ፣ አብራሪ፣ ስሜትንና አእምሮን ቀስቃሽ እንጂ ለስም መጠሪያ ቤተክርስቲያን ማስዋቢያ ብቻ ሆኖ መወሰድ እንደሌለበት ተናገረ። በባላባቱ ዘንድ ቅሬታን አተረፈ።

ጐንደር ተመልሶ መሄድ ፈልጎ ከሀያ ዓመት በላይ በመቆየቱ
ባይተዋር የሚሆን መሰለው። ጐንደርን እንደዛ ወዶ ይህን ያህል
ርቆ መቀመጡ አልገባ አለው። ደብረ ወርቅ ብዙ አስተምራዋለች።
በርግጥም የሥዕል ንጉሥ አድርጋዋለች። ሆኖም ደብረ ወርቅ
የሕዝብ ዓይነት አይታይባትም። ደብረ ወርቅ ነዋሪዎቿን
የጐንደርን ዓይነት ታላቅነትና ግርማ ሞገስ የላትም። እንደ ጐንደር አድርጋ የመቀመጥ ባህርይ ሲኖራት፣ ጐንደር አደባባይ አውጥታ ታሟግታቸዋለች፤ የቤተክርስቲያን ምርጫ ትሰጣቸዋለች፣ ለድሆቿ
የእንፋሎት መታጠቢያ እንኳን አዘጋጅታለች።
ታዲያ ይህችን ጐንደርን እንዴት አድርጎ ለዘላለም ይተዋት? እንደ
ወለቴ የልጅነት ፍቅሩ፣ የጎልማሳ ዘመኑ ትዝታው አይደለችምን?
ጐንደር ለመሄድ ባሰበ ቁጥር፣ “እቴጌ ኸባላቸው እት ልዥ ጋር
ወዳጅነት ያዙ” የሚለውን ወሬ መርሳት ስላልቻለ ልቡ ያመነታል።
ባሏ ከሞቱ ጊዜ የቀድሞው ስሜቱ አንሰራርቶ የነበረው ዜናውን
ሲሰማ ልቡ ተሰርጉዶ ምንትዋብ ላይ ቅሬታ አድሮበታል።

በምንትዋብ ቅር መሰኘቱ ቅር የሚያሰኘው አልፎ አልፎ ደግሞ
የሚያስቀው ነገር ሆኖ አግኝቶታል ቅሬታው የመነጨው እኔ ይህን
ያህል ስለእሷ ሳስብ እሷ እንዴት ሳታስፈልገኝ ቀረች በሚል ነው።
የሚያስበው ሁሉ ተገቢ እንዳልሆነ ቢያውቅም፣ “ውነት ትወደኝ ኸነበረ እንዴት አታስፈልገኝም?” ብሎ ደግሞ በስጨት ይላል። በሌላ በኩል አፄ በካፋ ሲሞቱ ልቡ ውስጥ የተስፋ ጭላንጭል የተቀረፀበትን ጊዜ ያስብና ከት ብሎ ይስቃል። ድጋሚ ሌላ ሥዕል ሊልክላት ወሰነ።ሆኖም እንደመነኩሴው ታማኝ ሰው እንዴትና የት እንደሚያገኝ ማሰብ
አቃተው።

ቀደም ብሎ ስለአብርሃ ወሬ ይሰማ የነበረውን ያህል ባለመስማቱም በሕይወት ይኖር ይሆን እያለ መጨነቁም አልቀረም። ካንድ ሁለት
ጊዜ መልዕክት ልኮበት ሳይደርሰው ቀርቶ ይሁን ወይንም ደርሶት ዝም ብሎት እንደሆነ ለማወቅ ተቸገረ።

አንድ ቀን፣ ደብረ ወርቅ ማርያም ውስጥ የቅኔ መምህር ከሆኑት
ከመጋቤ ሥነ-ጊዮርጊስ ጋር ቤተክርስቲያኗ ግቢ ውስጥ ያለ ጥድ ስር ተቀምጠው ሲጨዋወቱ በቅርቡ ጐንደር ሄደው እንደነበር ነገሩት።

“እደብረብርሃን ሥላሤ ደርሰው ነበር?” አላቸው።

“አዎን።”

“እንዲያው መጋቤ አብርሃ ሚባል ጓደኛ ነበረኝ። መልክትም
ብልክበት አልደረሰው ሁኖ ነው መሰለኝ መልስም አልሰጠኝ።”
“አሉ። መቸም ጐንደር ኻፈራቻቸው ሊቃውንት አንዱ ናቸው ነው ሚሉ።”

ጥላዬ ደስ አለው። ጐንደር የመሄድ ፍላጎቱ ተነሳሳ።

“እንዴት ያለ ጥሩ ነገር ነገሩኝ። እኔማ ተጨንቄ ቆይቻ።”
👍10
#ምንዱባን


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ትርጉም_ከዬሐንስ_ገፃዲቅ

የሁለት ከዋክብት መቀራረብ

አሁን እንግዲህ ማሪየስ አድጎ የሚያስቀና መልከ መልካም ወጣት ሆኖአል፡፡ አፍንጫው ስልክክ ብሉ ከቁመቱ ዘለግ ያለና በሩቁ የሴቶች ዓይን የሚስብ ጎረምሳ ነው፡፡ ረጋ ብሎ ሲራመድ የዋህነቱ ከፊቱ ይነበባል፡፡ ጭምትና አሳቢ ከመሆኑም በላይ ለአዋቂነቱ ወደር የለውም
ማሪየስ አንደበቱ የሚጣፍጥ፣ ከንፈሩ ወለላ፣ ጥርሱ ከወተት የነጣ ፈገግታው ውሃ የሚያደርግ ስለሆነ አሟልቶ የሰጠው ወጣት ነው::

ድኅነት አኮማትሮት የተቀዳደደ ልብስ ይለብስ በነበረበት ጊዜ እንኳ ልጃገረዶች በአጠገቡ ሲያልፉ ሰርቀው እንደሚያዩት ያውቃል፡፡ እርሱ ግን አቀርቅሮ በመሄድ ይሸሻቸዋል፡፡ የለበሰው ልብስ እያዩ የሚሳለቁበት እንጂ
በውበቱ ተስበው እንደሆነ አይገነዘብም ነበር፡፡ እውነታው ግን በውበቱ በቁመናው ተማርከው ነበር የሚያፈጥጡበት::

ከሚያፈጥጡበት ሴቶች መካከል ሁለቱን ግን አይሸሽም፡፡ እነርሱ
ባለጢማምዋ አሮጊት ሠራተኛውና አንዲት መንገድ የሚያያት ልጅ ናቸው ከአንድ ዓመት በፊት ጀምሮ ዘወትር ለሽርሽር በወጣ ቁጥር የሚያያት
አንዲት ልጅ ነበረች፡፡ በየቀኑ በአንድ በተወሰነ መንገድ ሲያልፍ አንድ ጠና ያለ ስልሣ ዓመት ገደማ የሚሆነው ሽማግሌና አንዲት ልጅ ዘወትር ከአንድ ቦታ ጎን ለጎን ቁጭ ብለው ያያቸዋል፡፡ ሰውዬው ኮስተር ያለና ጡረታ የወጣ ወታደር ይመስላል:: ሀዘን ከፊቱ ላይ ይነበባል:: እርሱን ደፍሮ
ለማናገር ያስፈራል::

አብራው የምትቀመጠዋን ልጅ ማሪየስ በመጀመሪያ ያያት እለት
አሥራ ሦስት ወይም አሥራ አራት ዓመት ቢሆናት ነው ብሎ ገምቷል
በመጀመሪያ ሲያያት ይህን ያህል መልክዋ የሚስብ አልመሰለውም ነበር በኋላ ስታድግ ግን በጣም ቆንጆ ሆነችበት:: ልብስዋ የገዳም ተማሪ ዩኒፎርም ነው። ሽማግሌውና ልጅትዋ ጎን ለጎን ቁጭ ብለው ለተመለከተ አባትና ልጅ ለመሆናቸው አያጠራጥርም።

ማሪየስ በአጠገባቸው ሲያልፍ ሁለትና ሦስት ቀን ድረስ እነዚ ሰዎች ምንድን ናቸው ብሎ ራሱን ከመጠየቅ ሌላ ብዙ አልተጨነቀበትም እነርሱ ግን እንዲያውም ያዩት አይመስልም:: ሁለቱ ሲገናኙ የራሳቸው
ጨዋታ ይጫወታሉ እንጂ ለአለፈና ለአገደመ ደንታ አልነበራቸውም ልጅትዋ እየሳቀች ሳታቋርጥ ለረጅም ጊዜ ታወራላች:: ሽማግሌው
በመጠኑ ነው የሚያወራው አስተያየቱ አባት ለልጁ ያለውን ፍቅር ያመለክታል፡:

በዚያ መንገድ በየቀኑ መጓዝ እንደልምድ አድርጎ ወስዶታል፡፡ በየቀኑ በዚያ ሲያልፍ ደግሞ እነዚያን አባትና ልጅ ከተወሰነ ቦታ ተቀምጠው ያያቸዋል፡፡ ማሪየስ በመንገዱ አንድ ጊዜ ብቻ ማለፍ ሳይሆን በቀን አምስት ወይም ስድስት ጊዜም የሚያልፍበት ቀን አለ፡፡ እንግዲህ ሰዎቹን በየቀኑ
አምስት ወይም ስድስት ጊዜ ያያቸዋል ማለት ነው:: ግን ሁለቱም ወገን ሰላምታ አይለዋወጡም፡፡ እርግጥ ነው ሁለቱ ሰዎች በየቀኑ በተወሰነ
ሰዓት ከዚያች ከተወሰነች ሥፍራ ስለሚቀመጡ የማሪየስን ብቻ ሳይሆን የሌሎችም ከዚያ ሥፍራ አየር ለመቀበል የሚወጡ ተማሪዎች ዓይን መማረካቸው አልቀረም፡፡ ከእነዚህ ተማሪዎች መካከል ኩርፌይራክም ይገኛል:: ማሪየስ በልጅትዋ ስለተሳበና ዘወትር የምትለብሰው ልብስ ጥቁር ስለነበር «ወት/ጥቁር»፣ አባትየው ደግሞ ብዙውን ጊዜ ነጭ ልብስ ስለሚለብስ
«ክቡር ነጭ» የሚል ስም አወጣላቸው:: ስሞቹ እየተለመዱ ስለሄዱ ተማሪዎች በዚያ ባለፉ ቁጥር «ክቡር ነጭና ወት/ ጥቁር ሥፍራ ሥፍራቸውን ይዘዋል» እያሉ ይፎትቷቸዋል፡፡

እኛም ለአገላለጽ ስለሚያመች ስለታሪካቸው ስንናገር በዚሁ ስም
እንጠራቸዋለን፡፡ ማሪየስ በየቀኑ ለአንድ ዓመት ሙሉ ሲያያቸው ክቡር ነጭን ይወዳል:: ወ/ት ጥቁርን ግን እስከዚህም አላፈቀራትም፤ ግን አይጠላትም::

በሁለተኛው ዓመት ማሪየስ ለራሱ እንኳን ግልጽ ባልሆነ ምክንያት
በዚያ መንገድ ለስድስት ወር መንሸራሸሩን ያቆማል፡፡ ከስድስት ወር በኋላ አንድ ቀን በዚያ ያልፋል:: አየሩ ጥሩ ስለነበር ማሪየስ ደስ ብሎት ነበር
የሚራመደው:: ከዚያች ከተወሰነች ሥፍራ ሲደርስ አባትና ልጅ አሁንም ከዚያች ከተወሰነች ሥፍራ ተቀምጠው ይጫወታሉ፡፡

ሲቀርባቸው በሰውዬው ላይ ምንም ለውጥ አላየም:: ልጅትዋ ግን በጣም ተለውጣለች:: በጣም ቆንጆ ሆና ታየችው:: በአጠገባቸው ሲያልፍ
አቀርቅራ ስለነበር ዓይኖችዋን ለማየት አልቻለም::

በመጀመሪያ የልጅትዋ ታላቅ እህት እንጂ እርስዋ አልመሰለችውም::
ግን እየተመላለሰ ሲያያት ራስዋ መሆንዋን አረጋገጠ፡፡ በስድስት ወር ጊዜ እጅግ ውስጥ ትልቅ ሴት መሰለች:: የደረሰችበት እድሜ እንደ አበባ የምትፈነዳበትና
አምራና ደምቃ የምትታይበት ነበር፡፡ በድንገት የጽጌረዳ አበባ መሰለች::የትናንትናዋ የዋህ ሕፃን የዛሬዋ አደገኛ ሴት ሆነች::

ቁመትዋ ብቻ አልነበረም ያደገው መልኳም ጭምር ነበር የተለወጠው:: በዝናብ ወራት ዛፎች ብዙ ቅርንጫፎችን እ
አብቅለው በመስከረምና በጥቅምት ወራት በአበቦች ቅርንጫፎቻቸውን እንደሚያጌጡ
ሁሉ ልጅትዋም በአለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በመልክ አበባ አጌጠች፥ ተዋበች::

ጥቁር ልብስዋን አውልቃ ከቀለምዋ ጋር የሚሄድ ያሸበረቀ ልብ ለበሰች:: በአጠገብዋ ሲያልፉ የምትቀባው ሽቶ ያውዳል፤ የልጅነት ጠረንዋ ልብ ይሰነጥቃል::

በሁለተኛው ቀን ማሪየስ በአጠገብዋ ሲያልፍ ቀና ብላ አየችው::የተለየ ስሜት አልሰጣትም:: ማሪየስ ሌላ ነገር እያሰበ መንገዱን ቀጠለ። አራት ወይም አምስት ጊዜ እየተመላለሰ በልጅትዋ አጠገብ አለፈ።
እንደለመደው ለመንሸራሸር ነበር እንጂ ዞር ብሎ እንኳን አላያትም፡፡

በሚቀጥሉት ቀናት የሽርሽር ሰዓቱን ጠብቆ በዚያ አለፈ፡፡ ግን ወደ እነዚያ ሁለት ሰዎች ብዙም አልዞረም:: ልጅትዋ መለዋወጥዋንና ቆንጆ
መሆንዋን ካረጋገጠ በኋላ ከወጥመድዋ እንዳይገባ ቸለል ማለቱን መረጠ።የሚያልፈው ግን እርስዋ ከምትቀመጥበት መቀመጫ በጣም ቀርቦ ነበር፡፡

በጣም ደስ የሚል ቀን ነው:: ማሪየስ ልቡን ገልጦ የተፈጥሮ ውበት ራሱን አበርክቷል፡፡ የተፈጥሮ ውበት መላ ሕሊናውን ስለያዘበት ሌላ ነገር
ከጭንቅላቱ ውስጥ ሊገባ አልቻለም:: የተፈጥሮን ውበት እያሰላሰለ በተለመደው ሥፍራ ሲያልፍ የልጅትዋና የእርሱ ዓይን ግጥም አሉ፡፡ዓይንዋ ውስጥ ምን አለ? ማሪየስ እንዲነግረን ብንጠይቀው እንኳን ሊነግረን
አይችልም:: ልብን የሚሰልብ ነገር አለው:: ግን ዓይንነቱ ያው ዓይን ነው።
ሆኖም አንድ አይነት እንግዳ የሆነ ብልጭታ አለው።

ዓይንዋን መለስ አደረገችው:: እርሱም መንገዱን ቀጠለ፡፡

ዓይንዋን ሲያየው ያ የምናውቀው ገራገሩ የልጅ ዓይን አልነበረም፡፡
ምሥጢራዊ ጥልቀት ነበረው:: ገለጥ አድርጋ ወዲያው ነው የመለሰችው፡፡

እያንዳንድዋ ወጣት ልጃገረድ የዚህ የተለየ አስተያየት የምታይበት ጊዜ አላት:: በዚያች ሰዓት ከዓይንዋ ለሚገባ ወዮለት!

ገና ምንነትዋን የማታውቅ ነፍስ የመጀመሪያ እይታ ከጎሕ መቅደድ
ጋር ይመሳሰላል፡፡ ጎሕ ሲቀድ አንድ የማይታወቅና የሚያበራ ነገር ከእንቅልፉ ሚነቃበት ሰዓት ነው:: ጎሕ ሲቀድ ያልታሰበ ውበት፧ ያልታሰበ ድምቀት ያልተጠበቀ ነገር ያሳያል፡፡ እንዲሁም የፈነዳች አበባ የምትመስል ልጃገረድ እይታ ምንም ሳይታወቅ ካልታሰበ ወጥመድ ውስጥ ልብን አጥምዶና ያልታሰበ ጭንቀት ውስጥ ወዝፎ ካልተጠበቀ መንከራተት ያደርሳል:: ይህ
👍13😁2
#ሳቤላ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_ሚሲስ_ሔንሪ_ውድ

ሳቤላ ከላይኛው ከተማ ምሽጎች ትንሹ ሰፈር እየተባለ ከሚጠራው ቦታ አንድ አግዳሚ ወንበር ላይ ተቀምጣለች - ሚስተር ካርላይል ወደ ቤቱ ከተመለሰ 0ሥር ቀን ያህል አልፎታል በጤናዋ በኩል ጉልህ የሆነ መሻሻል አድርጋለች
በጥንካሬዋ የታየው ለውጥም ለማመን የሚያስቸግር ነበር ከቤቷ ወጥታ የእንግሊዛዊያኑን የመቃብር ጽሑፍ እየተዘዋወረች ስታነብ ቆየችና በመጨረሻ ልትሔድ ስትል ለማሪፍ ተቀመጠች እንደ ሁልጊዜው በእግር ስትንሸራሸር ፍራንሲዝ ሌቪስን አሁንም አብሯት ነበር እሱን አራግፋ መጣል አልሆነላትም። የመውጫ ሰዓቷን ብትለውጥ የምትሔድበትን መንገድ ብትቀይር ዱካዋን ፈልጎ ከች ይልባታል ምናልባት እሷ
እንደጠረጠረችው አስቀድሞ በመምጣት ከምቹ ቦታ እየሆነ ይጠባበቃት ኖሮ ይሆናል እሷም ቁርጥ ያለ ነገር ነግራ ዳግመኛ እንዳይመጣባት ለማድረግ አልቻለችም ቢጠይቀኝ ምን ምክንያት ልሰጠው ነው? የሚል ጭንቀት ይመጣባታል " መሰጠት ያለበትን ምክንያት ደግሞ ልትሰጠው ቀርቶ ልታስበው አትፈልግም ምንአባቱ እንግዲህ የቀረኝ ትንሽ ቀን ነው ወደ ቤቴ የምሔድበት ጊዜ ደርሷል ብላ
በማሰብ ራሷን ታጽናናለች ነገር ግን እሷ ይህን ታስብ እንጂ ከሱ ጋር መገናኘቷ እየቀጠለ •እየረዘመ ሲሔድ የራሱን ፍሬ ማፍራት ጀመረ " ብቅ ባለ ቁጥር ፊቷ
ልውጥ ልቧ ድንግጥ ይልባታል ላለመደንገጥ ላለመሸበር ብዙ ጊዜ ብትሞክርም ነፋስን እንዳይነፍስ ለማድረግ እንደ መሞከር እየሆነባት ተቸገረች።

ጊዜው መሽቷል ቅዝቃዜው የሞቃቱ የሐምሌ ማታ አይመስልም" ከነፍሳት ልዩ ልዬ ጥዝታና ጭርጭርታ በቀር ምንም ድምፅ አይሰማም " ወይዘሮ ሳቤላ አመፀኛው ልቧ በራሱ የደስታ ስሜት እየመታ ከጓዶኛዋ ጋር ጸጥ ብለው ተቀምጠዋል
በውስጧ የጠነከረባት የሕሊና ድምፅ ባያስቸግራት የትክክለኝነትና የጥፋተኝነት
ፍርድ ባይደቀንባት ባጭሩ ሚስት የመሆኗ ነገር ባይከብዳት ኖሮ የነበረው ዝምታ ሳይነካ እሷም ከተቀመጠችበት ንቅንቅ ሳትል እሱም ከጐኗ እንዳለ እስከ ዘለዓለም ቢቀጥል የምታገኘውን የሚያረጋ ደስታ ታስብ ጀመር "

“ትዝ ይልሻል እመቤት ሳቤላ ?” አላት „ “ ልክ እንዶ ዛሬው በመስለ ሁኔታ አባትሽ : ሚስዝ ቬን አንቺ ' እኔና ሌሎችም ሆነን ሪቸመንድ የሔድን ጊዜ ''

“ አዎን ትዝ ይለኛል " ጥሩ ቀን ነበር የዋልነው " ሁለቱ ሚስ ቫሎነሮች አብረውን ነበሩ " አንተ ሚስዝ ቬን በሠረገላ ወደ ቤቷ ወሰድካት እኔ ከአባባ ጋር
ሔድኩ " በኃይል እየነዳህ ሰለ አስደነገጥካት • ሁለተኛ አንተ ሠረገላ ላይ እንደማትሳፈር ከቤት ከተመለስን በኋ ነገረችህ "

“ የማትጨክነውን እኮ ነው በተናገሩት ከማይረጉ ተገለባባጮችና ታይታ ወዳድ ሴቶች ሁሉ ኤማ ማውንት እስቨርንን የሚያህል የለም አሁንም “ ኤማ ማውንት
እስቨርን” ተብላ ማዕረግ ጨምራ እንኳን ያው ነች ከመዳራት በቀር ሌላ ቁም ነገር የላትም እኔም በዚያን ጊዜ በኃይል የነዳሁት ሆነ ብዬ እሷን ለማስደንገጥ ነበር

" ምን አደረገችህ ?

"በጣም አናደደችኝ " እኔ ሌላ ወዳጅ ስፈልግ እሷ የግድ ከላዬ ተጠምጥማ ከላዬ አልለቅም አለችኝ "

"ብላንሽ ሻሎነርን ነበር አንተ የፈለግህ?

“ብላንሽ ሻሎነር ?!” አለና ጮኸ ካፒቴን ሌቪሰን » እሷ ደግሞ ምኔ ናትና? ”

ሳቤላ ያሥራ ስባት ዓመት ቆንጆ ከነበረችው ከመልከ መልካሚቷ ከብላንሽ ሻሎነር ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንደ ነበረው አስታውሳ “ምነው ሚስስ ቬን ከሷ ጋር ብርቱ ፍቅር ይዞሃል ብላ ታማህ አልነበረም ?

“ እሷ እንኳን ከብላንሽ የበለጠ በሌላ ስው ነበር ስሜን የምታነሣው ” አላት ማንን ለማለት እንዶሆነ ለመገመት በሚያመች አነጋገርና አስተያየት "

“ እና ደግሞ የቅናት ግምቷ አለቦታው ያላረፈ አልነበረም " እኔም ልለው የፈለግሁት ብላንሽ ሻሎነርን አልነበረም " አንቺስ በዚያን ወቅት የተሻለ መገመት
አትችይም ነበር ? " አላት ወደሷ ዞር ብሎ "

ምን ለማለት እንደ ፈለገ በድምፁ አነዛዘርም ሆነ በዐይኑ አመለካከት ስለገባት መልኳ ሲለዋወጥ ተስማትና ፊቷን ወደ ሌላ አዞረች "

“የዱሮ ነገር ኣልፏል ተመልሶ ሊመጣ አይችልም በጊዜው ግን ሁለታችንም የየዕድላችንን ተውተን አሳልፈነዋል " ለመፋቀር የተጠሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ ቢባል አንቺና እኔ ነበርን እንዲያውም ያን ጊዜ የልቤን ሐሳብ የምታነቢው ይመስለኝ ነበር "

ለጊዜው ድንግጥ ብላ በዝምታ ከቆየች በኋላ ኮስተር ብላ አቋረጠችው ::

“ ልናገር እንጂ. . .ወይዘሮ ሳቤላ ጥቂት ቃላት ልናገርና ከዚያ በኋላ ለዘላለም ምንም አልተነፍስም - ብችል ኖሮ ያን ጊዜ አሳልፌ አልሰጥሽም ነበር " ነገር ግን
ያልተደላደለው ሁኔታዬና ዕዳዎቼ ሚስት እንዲኖሬኝ አላስቻሉኝም ቁልቁል ..ተጫኑኝ ስለዚህም የሎርድ ማውንት እስቨርንን ልጅ
ለማግባት እንድጠይቅ ከሚያበቃ
ደረጃ እንዲያደርሰኝ ሰር ፒተርን በመለመን ፈንታ ተስፋዎቼን በውስጤ ከለከልኳቸውና ከእጄ አምልጠሽ ስትሔጅ “ዐይኔ እያየ ዝም ብዬ ሰደድኩሽ » ”

“ እኔ ይኸን ነገር ለመስማት አልፈልግም ካፒቴን ሌቪሰን " አለችና ተቆጥታ ከተቀመጠችበት ብድግ አለች "

እንድትቀመጥ ክንዷን ነካ አድርጎ ባክሽን ትንሽ ልንግርሽ " ለምን እንዳመለጥሽኝ እነግርሻለሁ እያልኩ ከተመኘሁ ብዙ ዘመኔ ነው ሌላ ስለ ወሰደሽ እስከ ዛሬ ሆድ ሆዴን ሲያቃጥለኝ ይኖራል የሌላ ሚስት በመሆንሽ ቁርጤን ዐውቄ እስካርፍ ድረስ ምን ያህል እወድሽ እንደ ነበር መግለጽ ያቅተኛል ያ ፍቅር ዛሬም ከልቤ አልጠፋም " ሙሉ በሆነ ልባዊ ስሜት እወድሻለሁ አላት »

" እንዴት እንደዚህ ደፍረህ ትናገረኛለህ ? አለችው "

የትዳር ኃላፊነትና ግዴታ ስለነበረባት ተቆጣች ተጀነነችበት ነገር ግን ቆጣ ጅንን ትበል እንጂ ይህ አነጋገር በሌላ ወቅትና ሁኔታ ሆኖ ቢሆን ኖሮ ለልቧ ታላቅ ሐሴት የሚሰጥ ይሆን እንደ ነበረ በመግንዘቧ ለቁጣው ንግግሯ ተቃራኒ የሆነ ኃይለኛ ስሜት ውስጥ ለውስጥ በሠራ አካላቷ ሲሯሯጥባት ተስማት "

የአሁኑ ንግግሬ እኮ ምንም ጉዳት የለውም ” አለና ካፒቴን ሌቪሰን ንግግሩን በመቀጠል ' ' ነገሩ ጊዜ ያለፈበት ነው » ባለትዳርነትሽን አንችም ሆንሽ እኔ መዝንጋት አንችልም ሁለታችንም የየራሳችንን የኑሮ ጎዳና መርጠናል ስለዚህ አንድ ጊዜ የያዝነውን ፈር አክብረን መያዝ አለብን በመካከላችን ያለው ባሕር ሊያገናኘን አይችልም
በራሴ ጥፋት አምልጠሽኛል እንግዲህ በየትም አልፈ ላገኝሽ
አልችልም ያን ግዜ እንደምወድሽ
እንደምፈልግሽ ልገልጽልሽ ሲገባኝ ራስሽን ከሚስተር ካርላይል እጅ ስትጥይ ዝም ብዬ አየሁሽ

ራስሽን ስትጥይ አልክኝ ? ብላ ቱግ አለች "ሚስተር ካርይል እኮ የምወደውና የማከብረው በራሴ ምርጫ ያገባሁትና እሱን በማግባቴም የምመካበትና
የማልጸጸትበት ባሌ ነው ኧረ ለመሆኑ አንተ ከሱ ጋር ብትወዳደር ከምኑ ትደርሳለህ!
ራስህንም ረስተኽዋል . . . ፍራንሲዝ ሌቪሰን

ከንፈሩን ነከስና “ የለም አልረሳሁም ” አላት

እንዴዚህ ብለህ ልትናገረኝ አትችልም » ከዚሀ ብቸኝቴን አይቶ የሰደበኝ ካንተ ሌላ ማን አለ ? ሚስተር ካርላይል ካጠገቤ ቢኖር እንዲሀ ብለህ ልትናገረኝ አትደፍርም ነበር ? በል ደኅና እደር ጌታዬ !
👍16🔥1
#የጣሪያ_ስር_አበቦች


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ትርጉም_ሀኒም_ኤልያስ


የእናታችን ድንገተኛ ዜና

እናታችን እንደገና ልታየን ከመምጣቷ በፊት ባለፉት በእያንዳንዱ አስር ቀናት
ውስጥ፣ እኔና ክሪስ ለምን አውሮፓ ሄዳ እንደቆየችና ከሁሉም በላይ ደግሞ
ልትነግረን የነበረው ትልቅ ዜና ምን እንደሆነ ለመገመት ለሰአታት እናወራ
ነበር።

አስሩን ቀናት እንደ ሌላ ቅጣት አሰብነው ቅጣትም ነበረ: እዚህ አንድ ቤት
ውስጥ ሆነን ልክ ጣሪያው ስር ያለው ክፍል ያለን አይጦች እንደሆንን ሁሉ
ችላ ልትለንና ልትዘጋን ችላለች:

ስለዚህ ያን ያህል ቆይታ ስትመጣ እኔና ክሪስ በደንብ ስለተቀጣን የጥላቻ
ወይም የመውጣት ጥያቄያችንን ከደገምን ተመልሳ ላትመጣ ትችላለች ብለን በጣም በመፍራት ፀጥ ብለን እጣ ፈንታችንን ተቀበልን፡ ተመልሳ ካልመጣች ምን እናደርጋለን? መንትዮቹ ገና ጣሪያው ላይ ሲደርሱ ብርክ ከያዛቸው ከተተለተለ አንሶላ በሰራነው መሰላል ተጠቅመን ማምለጥ የማይታሰብ ነው።

ስለዚህ ለእናታችን ፈገግ አልንላት አንድም የማማረር ቃል አላሰማንም
ለወራት ጠፍታ ስለምታውቅ አስር ቀናት በመቆየት ለምን እንደቀጣችን
አልጠየቅናትም፡ ልትሰጠን የፈቀደችውን ተቀበልን፡ ከአባቷ ጋር ለመሆን
እንደተማረችው አይነት ታዛዥ የማይቃወሙ ቅን ልጆች ሆንን የሚገርመው እንዲህ መሆናችንን መውደዷ ነው: እንደገና የሷ ጣፋጭ አፍቃሪና ሚስጥራዊ “ውዶች” ሆንን።

አሁን በጣም ጥሩ፣ አስደሳች፣ ለእሷ አድናቆት ያለን፣ አክባሪና በእሷ
የምንተማመን መሆኑን ስታውቅ ጊዜውን ቦምቧን ለመጣል መረጠችው።
“ውዶቼ፣ ለእኔ ደስ ይበላችሁ! በጣም ደስ ብሎኛል!” እየሳቀች እጆቿን ደረቷ ላይ አድርጋ በክብ ተሽከረከረች: “ምን እንደተከሰተ ገምቱ ቀጥሉ… ገምቱ!” አለችን።

እኔና ክሪስ ተያየን “አያታችን ሞተ!” አለ። ልቤ ደስ የሚለውን ዜና ስትነግረን
ለመዝለልና ለመቦረቅ በመዘጋጀት በጣም እየደለቀ ነው።

“አይደለም!” አለች በድንገት ደስታዋ በጥቂቱ የደበዘዘ ይመስላል።

“ወደ ሆስፒታል ተወሰደ?” ብዬ ሁለተኛውን ምርጥ ግምት አቀረብኩ።
“አይደለም: አሁን አልጠላውም፧ ስለዚህ እናንተ ጋ መጥቼ በሞቱ መደሰቴን ልነግራችሁ አልችልም:”

“ታዲያ ለምን መልካም ዜናውን ራስሽ አትነግሪንም? ስለ ህይወትሽ ብዙም
ስለማናውቅም መገመት አልቻልንም” አልኳት።

ማለት የፈለግኩትን ችላ ብላ ቀጠለች፤ “ለረጅም ጊዜ የጠፋሁበትን ለመግለፅ አስቸጋሪ ሆኖብኝ የነበረው ምክንያት ባርት ዊንስሎ የተባለ ሰው ማግባቴ ነው። ጠበቃና በጣም ጥሩ ሰው ነው። ትወዱታላችሁ። እሱም ሁላችሁንም ይወዳችኋል። ጥቁር ፀጉር ያለው፣ በጣም መልከመልካም፣ ረጅምና የሚያምር ሰውነት ያለው ነው። ክሪስቶፈር፣ ልክ እንዳንተ የበረዶ ሸርታቴ ይወዳል፧ ቴኒስ ይጫወታል፤ ልክ እንዳንተ ጎበዝ ነው” ይህንን ስትናገር ወደ ክሪስ
እየተመለከተች ነበር።

በጣም ደስ የሚል ሰው ነው ሁሉም ይወዱታል። አባቴም ሳይቀር ይወደዋል
ወደ አውሮፓ የሄድኩት ለጫጉላ ሽርሽር ነበር። ያመጣሁላችሁ ስጦታዎች
ከእንግሊዝ፣ ከፈረንሳይ፣ ከስፔንና ከጣልያን የተገዙ ናቸው:” እኔና ክሪስ
በፀጥታ ተቀምጠን፡ ስለ አዲሱ ባሏ የምታወራውን እየሰማን ነበር።

እኔና ክሪስ ከገና በአል ግብዣ ምሽት ጀምሮ ብዙ ጊዜ ጥርጣሬዎቻችንን
አውርተናል: ልጆች ብንሆንም፣ እንደ እናታችን ያለች ወንዶች የምትፈልግ
ቆንጆ ወጣት ሴት ለረጅም ጊዜ ካለ ባል እንደማትቆይ እናውቅ ነበር። ሰርግ
ሳይደረግ ሁለት አመት ሲያልፍ ግን ያ ትልቅ ፂም ያለው መልከመልካም
ባለ ጥቁር ፀጉር ሰው ለእናታችን ብዙም አስፈላጊ ነው ብለን አላሰብንም
ነበር። በየዋሁ ልባችን እናታችን ለሞተው አባታችን አሁንም ታማኝ እንደሆነች ራሳችንን አሳምነን ነበር። ባለወርቃማ ፀጉር፣ ሰማያዊ አይኖች ያሉት አማልክትን የመሰለ የቅርብ ዝምድና እያላቸው እንኳን እሱን ለማግባት ከምክንያት ባሻገር ላፈቀረችው አባታችን ታማኝ ናት ብለን እናስብ ነበር::

የአባታችንን ቦታ ስለሚወስድ ሌላ ሰው ስትነግረን በጥላቻ የተሞላ ድምፅዋን ላለመስማት በመሞhር አይኖቼን ጨፍኜ ነበር: አሁን የሌላ ሰው ሚስት ናት ሙሉ በሙሉ የተለየ ሰው ሚስት ሆናለች: አሁን አልጋዋ ውስጥ
ይገባል፣ ከእሷ ጋር ይተኛል: እንግዲህ ከዚህ በኋላ ከምናገኛት ያነሰ ጊዜ
ነው የምትመጣው ማለት ነው: አምላኬ፣ እዚህ የምንቆየው ለምን ያህል ጊዜ ይሆን? ለምን ያህል?

ዜናዋና ድምፅዋ በደረቴ አጥንቶች ውስጥ የተያዘችና ልውጣ ልውጣ የምትል ትንሽ የፍርሀት ወፍ ፈጠረ።

“እባካችሁ…” ለመነችን፡ ፈገግታዋና ሳቋ ሀሴትና ደስታዋ እኛ ዜናውን
ባስተናገድንበት ቀፋፊና የተበላሽ አየር ላይ ለመቆየት እየታገሉ ነው::
“ለመረዳት ሞክሩና ለእኔ ደስ ይበላችሁ አባታችሁን እወደው እንደነበር
ታውቃላችሁ ግን እሱ ሞቷል። ከሞተ ረጅም ጊዜው ነው እና የምወደውና
የሚወደኝ ሰው ያስፈልገኛል።”

ክሪስ እንደሚወዳት፣ ሁላችንም እንደምንወዳት ለመናገር አፉን ከፈተ። ነገር
ግን ይህ ከልጆቿ የምታገኘው ፍቅር፣ እሷ የምታወራው አይነት ፍቅር
እንዳልሆነ ስለገባው ከንፈሮቹን ገጠመ እኔ ከአሁን በኋላ አልወዳትም።
ከዚህ በኋላ ትንሽ የመውደድ ስሜትም ለእሷ እንደሚኖረኝ እንኳን እርግጠኛ አይደለሁም: ግን መንትዮቹ በሁኔታዬ እንዳይደነግጡ መሳቅና ማስመሰል እንዲሁም ከአንገት በላይ መሆን እችላለሁ፡ “አዎ እማዬ፣ ለአንቺ ደስ ብሎኛል እንደገና የሚወድሽ ሰው ማግኘትሽ ጥሩ ነው።”

“ለረጅም ጊዜ ይወደኝ ነበር ካቲ፣” ተበረታታችና እንደገና በራስ በመተማመን
ፈገግ እያለች ቀጠለች “ወንደላጤ ሆኖ ለመቆየት ወስኖ ስለነበር ሚስት
እንደሚያስፈልገው ለማሳመን ቀላል አልነበረም: አያታችሁ ደግሞ በፊት
አባታችሁን በማግባት ለሰራሁት ኃጢአት ቅጣት እንዲሆን ሁለተኛ ጊዜ
እንዳገባ አልፈለገም ነበር። ግን ባርትን ይወደዋል፤ ብዙ ስለምነው ቆይቼ
በመጨረሻ እሺ አለኝ ባርትን ማግባትና ሀብቱንም መውረስ እንድችል
ፈቀደ” ንግግሯን ቆም አደረገችና የታችኛውን ከንፈሯን መብላት ጀመረች።
እንደገና ደግሞ በጭንቀት ተዋጠች ቀለበት ያጠለቀችበት ጣቷ ወደ ጉሮሮዋ ሄደና አንገቷ ላይ ያንጠለጠለችውን ጌጥ በጭንቀት ያፍተለትል ጀመር።“በእርግጥ አባታችሁን የምወደውን ያህል ባርትን አልወደውም” አለች።
የበራው ፊቷ አሁን ያላት ፍቅር በፊት ከምታውቀው እጅግ የበለጠ እንደሆነ
እያጋለጣት ነበር በረጅም ተነፈስኩ: ምስኪን አባቴ!

“ያመጣሽልን ስጦታዎች... ሁሉም ከአውሮፓ፣ ወይም ከእንግሊዝ ደሴቶች
አይደሉም: የስኳር ከረሜላው የመጣው ከቬርሞንት ነው: ቬርሞንትም ሄደሽ ነበር? እሱም ከዚያ ነው የመጣው?”

ልክ ቬርሞንት ብዙ ነገር የሰጣት ይመስል በደስታ ሳቀች። “አይ፣ እሱ የመጣው ከቬርሞንት አይደለም ካቲ፤ ግን እዚያ የምትኖር እህት አለችው ከአውሮፓ ከመጣን በኋላ በሳምንቱ መጨረሻ ልንጠይቃት ሄደን ነበር የስኳር ከረሜላ
ምን ያህል እንደምትወጂ ስለማውቅ ከዛ ነው ያመጣሁልሽ። ደቡብ የሚኖሩ ሌሎች ሁለት እህቶችም አሉት: ደቡብ ካሮላይና ውስጥ ካለች ግሪንግሌና ግሪንግሌና ወይም እንደዚያ አይነት ስም ካላት ከተማ ነው የመጣው: ግን በኒው ኢንግላንድ ብዙ ቆይቷል: የተመረቀው ከሀርቫርድ የህግ ትምህርት
👍393😁2
#ጠላፊዎቹ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በኬንፎሌት


#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ከመሐል አትላንቲክ ወደ ቦትውድ (ካናዳ)


ዳያና ላቭሴይ ባሏ ፎየንስ ላይ አይሮፕላኑን መሳፈሩ በእጅጉ አስቆጥቷታል፡ በመጀመሪያ ዱካዋን እግር በእግር ተከታትሎ በመምጣት መሳቂያ መሳለቂያ ስላደረጋት አፍረት ውስጥ ከቷታል፡ ባሏ እቤታችን እንሂድ ቢላትም ሀሳቧን መለወጥ አትፈልግም ከማርክ ጋር ወደ አሜሪካ ለመሄድ የወሰነች ብትሆንም መርቪን ግን የመጨረሻ ውሳኔዋ ነው ብሎ መቀበል አልቻለም፡፡ ይሄ ደግሞ በቁርጠኝነቷ ላይ ጥላ አጥልቶበታል፡፡እሱም ውሳኔዋን እንደገና እንድታጤነው ደጋግሞ ስላሳሰባት ውሳኔዋን
በተደጋጋሚ ገልጻለታለች፡፡ በመጨረሻ ግን የአየር ጉዞዋ የሰጣትን ደስታ
ነጥቋታል፡፡

በህይወት አንዴ ብቻ የሚገጥም ከፍቅረኛ ጋር የሚደረግ ጉዞ፡፡

ከሳውዝ ሃምፕተን ሲነሱ የነበረው የነጻነትና የደስታ ስሜት አሁን የለም: መርቪን ከመጣ ወዲህ ምቹው አይሮፕላን፣ ከተለያዩ ተሳፋሪዎች ጋር መቀላቀሉና እጅ የሚያስቆረጥመው ምግብ ደስታ እየሰጣት አይደለም፡መርቪን ባጋጣሚ ሲያልፍ ያየኛል ብላ ስለፈራች ከማርክ ጋር መላፋት፣መተሻሸትና መሳሳም አልቻለችም፡፡ መርቪን የት እንደተቀመጠ አታውቅም፡፡ካሁን አሁን ይመጣ ይሆን እያለች ትበረግጋለች። ማርክ ካሊፎርኒያ ስለሚጠብቃቸው ኑሮ በተስፋ ሲያወራና ሲቀልድ ቆይቶ ጣውንቱ ከሰማይ
እንደወደቀ ሁሉ ድንገት አይሮፕላኑ ውስጥ ጥልቅ ካለ ወዲህ ግን ቀልቡ
ግፍፍ ብሏል፡ አሁን የተነፈሰ ፊኛ መስሏል፡፡ ዳያና አጠገብ ቁጭ ብሎ
አንድም ቃል ሳያነብ የመጽሔቱን ገጾች ያገላብጣል፡፡ ስሜቱ መጎዳቱን ዳያና አይታለች፡፡ አንድ ወቅት ላይ ይዟት እንዲጠፋ ከቆረጠች በኋላ ሃሳቧን ለውጣ ነበር፡፡ አሁን ባሏ ስለመጣ ከእሱ ጋር እሄዳለሁ ብላ ሃሳቧን
የማትለውጥ መሆኗን እርግጠኛ መሆን አልቻለም፡፡
የአየሩ ሁኔታ እየከፋ መምጣቱ ደግሞ ሌላ ራስ ምታት ሆኖባታል

አይሮፕላኑ ልክ ኮረኮንች ላይ እንደሚሄድ መኪና ይንገጫገጫል፡፡ በየሰዉ
ፊት ላይ ፍርሃት ይነበባል፡፡ ተሳፋሪው ሁሉ የሚያወራው ይህንኑ ነው፡

ዳያና ባሏ የት እንደተቀመጠ ማወቅ ፈለገች፡፡ እግረ መንገዴን ባየው እየተዘዋወረች ብትቃኝም መርቪንን የበላው ጅብ አልጮህ አለ፡፡ በመጨረሻ የቀራት ክፍል የሙሽሮቹ ክፍል ብቻ ነው፡፡

የሴቶች መዋቢያ ክፍል ገባች። ክፍሉ ውስጥ ሁለት ወምበሮች ያሉ ሲሆን አንዱ ወንበር ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ ትኳኳላለች፡፡ ዳያና በሩን ልትዘጋ ስትል አይሮፕላኑ ዘጭ ሲል ሚዛኗን ስታ ልትወድቅ ምንም አልቀራትም፡፡ እንደምንም ተንገዳግዳ ሄዳ ባዶው ወምበር ላይ ዘፍ አለች።

‹‹ተረፍሽ?›› ስትል ጠየቀች ሴትየዋ፡፡

‹‹አዎ፣ አመሰግናለሁ›› አለች ዳያና ‹‹አይሮፕላን እንዲህ ሲሆን አልወድም››

‹‹እኔም አልወድም፡ ከዚህ በኋላ ጉዟችን የከፋ እንደሚሆን አንድ ሰው
ነግሮኛል፡ ዶፍ ዝናብ ይጠብቀናል›› አለች፡፡

የአይሮፕላኑ ውዝዋዜ ጋብ ሲል ዳያና ጸጉሯን ማበጠር ጀመረች።

‹‹ሚስስ ላቭሴይ ነሽ አይደለም?›› ስትል ጠየቀች

‹‹አዎ ዳያና በይኝ››
‹‹እኔ ናንሲ ሌኔሃን እባላለሁ:: ፎየንስ ላይ ነው የተሳፈርኩት”
ከሊቨርፑል ካንቺ. . . ከሚስተር ላቭሴይ ጋር ነው የመጣሁት››
‹‹ኦ!›› ዳያና ይህን ስትሰማ ፊቷ በእፍረት ቲማቲም መሰለ፡፡ ‹‹ጓደኛ እንዳገኘ አላወቅሁም ነበር›› አለች በምጸት፡፡

‹‹ይህን አይሮፕላን ለመሳፈር ወደ ሳውዝ ሃምፕተን ለመሄድ ፈልጌ
ሊቨርፑል ላይ መውጫ አጥቼ ስጨነቅ ባለቤትሽን አየር ማረፊያ ላይ
አገኘሁትና እንዲወስደኝ ለመንኩት››

‹‹እንኳን ቀናሽ›› አለች ዳያና፡፡ ‹‹የእሱ መምጣት እኔን እፍረት ውስጥ
ከቶኛል፡፡››

‹‹ማፈር የለብሽም፡፡ ሁለት ወንዶችን በፍቅር ማጥመድሽ ደስ የሚል
ነገር ነው፡፡ እኔ አንድ እንኳን ፍቅረኛ የለኝም፡፡››

ዳያና ናንሲን በመስታወት አየቻት፡፡ ሴትየዋ ቆንጆ ባትባልም የደስ ደስ አላት፡ ጸጉረ ጥቁር ስትሆን ከሰውነቷ ጋር የሚሄድ ልብስ ለብሳለች።
ስትታይ በራሷ የምትተማመን ትመስላለች፡ መርቪን ሊፍት ቢሰጥሽ
አያስገርምም፡ እሱ እንዳንቺ ያለች ሴት ነው የሚፈልገው አለች ዳያና በሆዷ፡፡
‹‹እንዴት ነው ያሳየሽ ባህሪ ጥሩ ነበር?›› ስትል ጠየቀቻት ናንሲን፡፡
‹‹ብዙም ጥሩ አልነበረም›› አለች በቅሬታ ፈገግታ፡
‹‹አዝናለሁ፡ ይህ ባህሪው ነው የሚያስጠቃው›› አለችና ሊፒስቲኳን ጨረገች

‹‹ሆኖም በችግሬ ጊዜ ስለደረሰልኝ ባለውለታዬ ነው›› አለችና ናንሲ
ተናፈጠች፡ ናንሲ ቀለበት ማሰሯን ዳያና አጤነች፡፡ ‹‹ትህትና ባይኖረውም
ጥሩ ሰው ይመስላል፡፡ ራትም ጋብዞኛል፡ ጨዋታ ያውቃል፡፡ የሴት ልጅን
ልብ የሚሰርቅ ቁመናና መልክ አለው›› አለች፡፡

ጥሩ ሰው ቢሆንም….... አለች ዳያና ‹‹ሰው ይንቃል፡፡ ትዕግስትም የሚባል ነገር ፈጽሞ አልፈጠረበትም፡፡››
ናንሲ ጥቁር ጥቅጥቅ ያለውን ጸጉሯን ታበጥራለች ሽበቷን ለመደበቅ ቀለም ትቀባ ይሆን?› አለች ዳያና በሆዷ።

አንቺን መልሶ በእጁ ለማስገባት ሲል የሚደርስበትን መከራ ለመቀበል ቆርጧል››

‹‹አይደለም ክብሩ ስለተነካ ነው›› አለች ዳያና ‹‹ሌላ ወንድ ስለወሰደኝ ነው ያንጨረጨረው፡፡ ተጋፊ ስለመጣበት ነው ተከትሎኝ የመጣው፡ ጥዬው
እህቴ ቤት ሄጄ ቢሆን ኖሮ እኔን ለመፈለግ እግሩን አያነሳም ነበር››

ናንሲ ሳቀችና ‹‹እንዳነጋገርሽ አንቺን ለማስመለስ ተስፋ ያለው
አይመስልም›› አለች፡፡

‹‹ምንም ተስፋ የለውም›› አለች ዳያና፡፡ ዳያና ድንገት ስሜቷ ስለተረበሸ ከናንሲ ጋር ከዚህ በላይ ማውራት አልፈለገችም፡፡ ሜክአፕና ማበጠሪያዋን ቦርሳዋ ውስጥ ከታታ ለናንሲ ያላት ጥላቻ እንዳይታወቅባት የውሽት ፈገግታ አሳየቻትና ‹‹ወደ ቦታዬ ልሂድ›› ብላ ተነሳች፡፡

‹‹መልካም ዕድል!››

ከሴቶች መዋቢያ ክፍል ስትወጣ ሉሉ ቤልንና ልዕልት ላቪኒያ የመዋቢያ ዕቃዎቻቸውን ያጨቁበትን ቦርሳዎቻቸውን አንጠልጥለው ገቡ፡፡
ወደ ቦታዋ ስትመለስ አስተናጋጁ ዴቭ መቀመጫቸውን ወደ ታጣፊ አልጋ ሲቀይር አየች፡፡ ዳያና አንድ ተራ ሶፋ እንዴት ወደ ተደራራቢ አልጋ ሊቀየር
እንደሚችል ገርሟታል። ዴቭ ከወምበሩ ስር አንሶላና ብርድ ልብስ አወጣና
አነጠፈ፡፡

ተደራራቢ አልጋዎቹ ምቹ ቢሆኑም ከሰው እይታ ውጭ ባለመሆናቸው
ዴቭ መጋረጃ አመጣና ጋረዳቸው፡ ከዚያም በአልጋዎቹ ጎን ትንሽ ታጣፊ
መሰላል አያያዘባቸው፡፡ ዴቭ ይህን የሰራው በሚያስደንቅ ቅልጥፍና ነው፡፡

ዴቭ ወደ ዳያናና ማርክ ዞሮ ፈገግታ ሳይለየው መኝታችሁ እንዲዘጋጅላችሁ ከፈለጋችሁ ንገሩኝና አዘጋጅላችኋለሁ›› አላቸው፡፡

‹‹ተደራራቢ አልጋዎቹ ውስጥ ሲተኙ ሰዎች አይታፈኑም?››
‹‹እያንዳንዱ አልጋ የራሱ አየር ማስገቢያ አለው›› ሲል መለሰ ‹ቀና ብለሽ ብታዪ ያንቺ አልጋ አየር ማስገቢያ አለው፡›› ዳያና ቀና ስትል መስቀያና መዝጊያና መክፈቻ ያለው በብረት ፍርግርግ የተሰራ አየር ማስገቢያ አየች:: "ከዚህ በተጨማሪ›› ሲል ቀጠለ ዴቭ ‹‹የራስሽ መስኮት፣ መብራት፣ የልብስ መስቀያና የመፀሐፍ ማስቀመጫ አለሽ።ከዚህ በተረፈ የምትፈልጊው ነገር
እንዲመጣልሽ ስትፈልጊረመ ይህን ቁልፍ ብትጫኚው ከተፍ እልልሻለሁ›› አላት።
👍10
#ኢቫንጋዲ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ

ኮንችትና ሶራ በኦሞ ወንዝ ሲጓዙ በኡዱማ መርኩል
ጎዋ ኩረምና ሻንጋሮ ያሉትን የቦዲና የሙርሲ መንደሮች ካዩ በኋላ የደቡብ ሱዳንን አቅጣጫ  ይጓዝ የነበረው
አቅጣጫውን ከደቡብ ወደ ምስራቅ ድንገት እጥፍ በማድረግ መጓዝ ጀመረ

በአለምአቀፍ አቅጣጫ ማስተካከየዋ ጂፒ ኤስ'
ከሳተላይቶች ጋር ግንኙነት ፈጥራ ያለችበትን የኬክሮስና ኬንትሮስ
ዲግሪ ካወቀች በኋላ ማፑን ስትመለከት በጣም ከሚጠማዘዘው የኦሞ
ወንዝ ጉዞ በኋላ የካራ የሙሩሌ ዳሰነች ማህበረሰቦችና ዝቅ ብሎ
የሚታየው የቱርካና ሐይቅ ብቻ የሚቀራቸው መሆኑን ተረዳች በዚህ ጊዜ ኮንችት ትልቅ ሃሣብ ላይ ወደቀች የአያቷን ቀዬ ለማግኘት የቀራት እድል በጣም ውስን ነው  የዳሰነች ማህበረሰብ ያለው  ከቱርካና ሐይቅ ጥግ ሲሆን አያቷ ስለሃይቅ ፈፅሞ አንስቶ ስለማያውቅ የሱ ማህበረሰብ ዳሰነች ሊሆን አይችልም ስለዚህ ጥርጣሬዋ ወደ ሁለት ዝቅ አለ ከካራና ከሙረሌ
ከነዚህ አንዱ ካልሆነ ግን የአያቷን ቀዬ ለማግኘት
የምትወስደው አማራጭ
ጭልምልም ያለና  ምናልባት ሌሎች ተጨማሪ አመታትን የሚወስድ ይሆናል ስለዚህ ኮንችት ጭንቀት አንገቷን ሲያስደፋት ሶራ ችግሯ ምን እንደሆነ ገብቶት፡-

አዞይሽ ካሰብሽው ትደርሻለሽ" አላት::

ያ ሃሳብ አንዳች ውስጣዊ ሃይል ፈጠረላት አመሰግናለሁ ብላው ጉዟቸውን ቀጠሉ።

ትንሿ ድንኳናቸው ከኦሞ ወንዝ ራቅ ካለ ጉብታም ቦታ አግራር ዛፍ አቅራቢያ ተተክላለች።

ኮንችት ሁለት እግሯን እጥፍጥፍ አድርጋ ድንቁን
የተፈጥሮ ውበት የማታዋን ጀንበርና ልዩ መስህብ የተጎናፀፈውን የዳመናውን ቀለም እያየች የተፈጥሮን ሙዚቃ የአዕዋፍ ዝማሬ
የንፋሱን ሽውሽውታ... ታዳምጣለች።

ይህች አንደበት ያጣች ሃገር ምንኛ ታሳዝናለች። የሌላ
ውበት በውሸታም ካሜራ ቀርፀው ሌላውን እየኮረኮሩ ለማዬት ሲያራኮቱት ኢትዮጵያ ግን እንዲህ ትንፋሽ ቆራጭ የሆነውን
ውበቷን ቆንጥሮ ለዓለም ህዝብ የሚያሳይላት አጣች

ከጥሩው የተበላሸው  የሚበዛበት አለማችን ሳታወቅ ከተበላሽው ጥሩው የሚበዛባት አፍሪካ ግን ጨለማ ዳፍንታም
አህጉር ተባለች

“የሚዲያ ልሳን ያልተፈጠረባት ምስኪን ኢትዮጵያ ስለ ውበቷ ማን የራሱን ጥሎ የእሷን ያስተዋውቅላት ታውቃለህ ሶራ ስለ አፍሪካ ዜና በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች ስናይ አንበሳ ሲያገሳ ፏፏቴው ሲንፏፏ... አዕዋፍ ሲበሩ አውሬው ሲተራመስ ይታይና
ኢትዮጵያን የሚመለከት ዜና ሲመጣ ግን ሁሌ ከረጂ ድርጅቶች ዳቦ ሲታደል ማየት ብቻ የሰሃራ በርሃ አገሮች ግመላቸውና አሸዋቸው ሲታይ ኢትዮጵያ ዛፍ አይበቅልባት ፏፏቴም የላት አውሬና አዕዋፍም አይገኙባት የሚባባለው ብዙ ነው።

ለካ ኢትዮጵያ ምንም አላጣች: ሰው ግን ያላት
አይመስለኝም እንደ “ኢብንባቱታ እየዞረ እሚያስተዋውቃት
የላትም..." አለችው እያሸጋገረች አድማሱን አያዬች: ሶራ የሚላት
ጠፋው: ኢትዮጵያውያን በሄዱበት ስላላቸው ነገር ማለት እንኳን አይችሉም። ብዙ ኢትዮጵያውያን በሌላው ዓለም ይኖራሉ ፧ ግን ስለ አገራቸው ትንፍሽ አይሉም በቅኝ ግዛት የማቀቁት ህዝቦች
አንገታቸውን ቀና አድርገው መዘመር ሲጀምሩ ኢትዮጵያውያን ግን
የተውሶ ካባ ከጃማይካ ተበድረው ትዮጵያዊነታቸውን ከውስጥ
ጃማይካነታቸውን ከላይ ደርበው ተደበቁ። hገሃዱ እውነት ማስመሰሉን መረጡ።' ሶራ አዕምሮው ተረበሸ።

“ተፈጥሮን አትወድም? ሶራ
እስኪ እየው ይህን ውበት?
የሰው ኪነታዊ ጥበብ ምን ብሎ ሊገልጸው ይችላል?" አለችው።

“ያምራል ኮንችት... ብቻ ምን ይሆናል እያለን ያጣን
መሆናችን ያሳዝናል። ለቤት ማስዋቢያ በየግድግዳችን የምንለጥፈው የባህር ማዶ ስዕሉችን ነው። የባር ማዶው ህዝብን ደግሞ አንች እንዳልሽው? “ለመሆኑ አገራችሁ ዛፍ ያበቅላል ወይ! ይሉናል።

“ህይወት ሳናይ ገና የናታችንን ጡት ሳንጠግብ በባህር ማዶህይወት ለሃጫችንን እያዝረበረብን እንነሆልላለን።

“ከዚያ ማነህ? ሲሉን  ጸጥ ምን አለህ ሲሉን ቁልጭልጭ በመጨረሻ እነሱም ንቀው እንደ ምራቃቸው ይተፉናል!... የመጣበትን ያላወቀ የደረሰበትን ማን ይጠይቀዋል?.." ብሎ ፀጥ አለ::

ኮንችትና ሶራ እንዲህ በፀጥታ ድባብ ተውጠው ማራኪዋን ተፈጥሮ እየቃኙ የበኩላቸውን ሃሣብ ሲያንሰላስሉ የሆነ ድምፅ
ንፋሱ ይዞ መጣ: እንደገና ድምፁን ጠበቁት  ተመልሶ መጣ የወፍ ዝማሬ የወንዝ ኩሉልታ የእፅዋት ሽዋሽዋቴ
አይደለም።የአራዊት ድምፅ… ከሁሉም የተፈጥሮ ቅላፄዎች የተቀነባበረ የሙዚቃ ቃና ነው: ጥዑም ዜማው ይማርካል!
ይስባል! ከተፈጥሮ ጋር ተዋህዶ ልብ ይሰርቃል። ተያዩ ኮንችትና ሶራ: ድምፁ እንደገና እየተስረቀረቀ መጣ። ተጠቃቅሰው ተነስተው ማራኪውን የሙዚቃ ቃና ወደሰሙበት አቅጣጫ ሄዱ።

“ክላሽንኮቭ” መሳሪያውን ጎኑ ያጋደመ ሰው ወይሳውን'
ይነፋል። አዕዋፍ ነፍሳቱ ፀጥ እረጭ ብለው ያዳምጡታል፤ ሶራና
ኮንችትም ከተደበቁበት ሳይወጡ የዜማው እንቅፋት ሳይሆኑ ያን ጥዑም ዜማ በፀጥታ ማዳመጥ ቀጠሉ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ካርለት ካሎ ጎይቲና አንተህ ይመር ከካሮ ማህበረሰቦች
መንደር አንዷ የሆነችው ቆርጮ ዘግይተው ስለተነሱ ከመሸ በኋላ ደረሱ። ከዚያ ወደ መንደሩ ገብተው ሽማግሌዎች ከፀሐይ ቃጠሎ ከሚጠለሉበትና ከሚወያዩበት ኦሞ ወንዝ ዳር ላይ ካለው ዳስ ሄዱ

ቆርጮ ከፍ ብሎ ሜዳማ ከሆነ ቦታ  ላይ ያለች መንደር በመሆኗ ለጥ ያለውን የኦሞን ወንዝ ግርጌው ሌላውን የካሮ መንደር ዱሰን ከቀኝ የሙሩሌን ሚዳ ከግራ ማዶው ደሞ የማሽላ
አዝርዕቱን በስተ ምስራቅ ለጥ ያለውን የማንጎ ፓርክ አረንጓዴን ደን ማየት ስለሚቻል ቆርጮ ቀለል ያለችና የተፈጥሮ ውብት በትርኢት መልክ የሚቀርብባት መንደር ናት።

ከሎና አንተነህ ሽማግሌዎችን መጀመርያ ተጥሎ ጎረምሶችን የሐመሩን ደልቲ ገልዲን አይተው እንደሆን ጠየቋቸው በእርግጥ ከጎረምሶች ጥቂቶቹ እንጂ ብዙዎቹ አያውቁትም  የሚያውቁት አላየነውም አ
ሲሉ ሌሎቹ ግን ብዙ የሐመር ወንዶች ከከብቶቻቸው ጋር ሙርሌ ያሉ መሆናቸውን ነገሯቸው።

በእርግጥ ይህ ለአንተነህ  እንግዳ አልነበረም ዝናብ ሲቀንስና የግጦሽ ሳር ሲጠፋ የሐመር ከብቶች ፍየሎችና በጎች ወደ ኦሞ ወንዝ  ይመጣሉ ኦሞ ወንዝ አካባቢ ሳሩ ጥሩ ነው። በዚያ ላይ ደግሞ ከብቶች የሚጠጡት በቂ ውሃ ከኦሞ ያገኛሉ ስለዚህ የቆርጮ
መንደር ካሮዎች እንደነገራችው ሐመሮች ከብቶታቸው ጋር በሙርሌ ሜዳና በኦሞ ወንዝ ዳር አሉ::

“ታዲያ ምን ይሻላል? አለች ካርለት ከሎንና ጋልተንቤን

የሚሻለውማ ለአንድ ሶስት አራት ቀን እዚሁ አካባቢ
ማጠያየቅ ነው" አላት አንተነህ ይመር ረጋ ብሎ እያንዳንዱን ቃል
እየረጋገጠ፡

ጎይቲ ጆሮዋን በሁለት እጅዋ ይዛ እግሯን አጣጥፋ መሬት ላይ ቁጭ ብላለች:: ደልቲ ቆርጮ መንደር ነኝ ብሎ እንደነገራት ሁሉ ስትመጣ ባለመኖሩና ያለበትም አለመታወቁ ሆዷን አዋለለው ! ሆድ ባሳት...

“እንግዲህ ለዛሬ እዚሁ እንደር ነገና ተነገ ወዲያ ሙርሌ ወርደን እንፈልገውና ተዚያ ወደ ሌሎች የካሮ መንደሮች ዱስና ለቡክ
እንሄድና እንፈልገዋለን!" አለና ጋልታምቤ አያቸው። ሁሉም ተስማሙ፤ ጎይቲ ግን ተነጫነጨች። እሱን ሳታይ ጎኗን ማሳረፍ
አልፈለገችም: ጀግናው እየተንጓለለ እሷ እንቅልፍ እንዴት ያሸልባት? ግን ከአቅሟ በላይ በድምፅ ብልጫ ተሸነፈችና ሁለት
ድንኳናቸውን ዘርግተው ካርለትና ጎይቲ አንዱ ድንኳን ጋልታምቤና ከሎ ደግሞ ሁለተኛው ድንኳን ሊተኙ ተስማሙ።
👍14
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ልዩ ከመድህኔም ሆነ ከጊፍቲ ጋር በአካልም ሆነ በሰልክ  ከተገናኘች ሁለት ወር ተቆጠረ፡፡ሰሞኑን የምርቃት ሽር ጉድ ላይ ስለሆነች ሀሳቧን ለጊዜውም ቢሆን ከእነሱ ላይ አንስታለች…

የሚቀጥለው እሁድ የምረቃ ፕሮግራም አለባት…ነገሩ በገዛ ሴራዋ ድብልቅልቅ ባታደርገው ኖሮ ቀለበቷም ጭምር የሚደረግበት ቀን ነበር፡፡በዚህ ሀሳብና ሁኔታ ላይ እያለች ነበር ትናንት ማታ ቃል ደውሎ ነገ በስድስት ሰዓት እሱ ቤት እንድትመጣ የነገራት።ምክንያቱን ስትጠይቀው ‹‹ስትመጪ ትደርሺበታለሽ›› አላት። በዚህም የተነሳ ልቧ እንደተንጠለጠለ መሽቶ ነጋ።

ሁል ጊዜ ቃል ፈልግሻለሁ ባላት ቁጥር ለምንድነው ልቧ   የምትቅበዘበዘው? ሁሌ የማይገባት ጉዳይ ነው… አምስት  ተኩል ሲሆን ነው አምራና ተሸቀርቅራ እቤት የደረሰችው....እቤቱ የቀጠራት የፍቅር ጥያቄ ሊጠይቃት እንደሆነ 90 ፐርሰንት እርግጠኛ ነች...እሱ ደፍሮ ባይጠይቃት እንኳን ትንሽ ፍንጭ ካሳያት እሷ ገፍታበት የውስጧን ዘክዝካ ልትነግረውና የዘላለም ፍቅረኛዋ እንዲሆን ልትጠይቀው አስባበትና ተዘጋጅታበት ነው የመጣችው፡፡ ስትደርስ ቤቱ በምግብ ሽታ ታውዷል "ስትገባ በሞቀ ፈገግታና  ሠላምታ ተቀበላት የሚሰራውን ምግብ ገና ስለነበረው ታግዘው ጀመር..እየተዘጋጀ ያለው የምግብ ብዛት ግን ለሁለቱ ብቻ አልመስል አላትና ደባሪ ስጋት በእምሮዋ ሽው አለባት…እሱን ጠይቃ ለማረጋገጥ ግን አልፈለገችም፡፡ስድስት ሰዓት ሲሆን በራፍ ተቆረቆረ..‹‹ ሂጂና ክፈቺ ››አለት፡፡ የቃል የቤት አከራዮ ናቸው በሚል ግምት ቂው ቂው እያለች ሄዳ ስትበረግደው  ፊቷ የተጋረጠው ሰው ያልጠበቀችው ነበር..ልክ እንደናፈቀ ሰው  ተንደርድራ ልትጠመጠምባት ነበር.. ለጥቂት ነው ትውስታው በአዕምሮዋ ብልጭ ሲል  እራሷን የገታችውና..እንደመመናቀር ብላ በራፋን በመልቀቅ ወደውስጥ የተመለሰችው...፡፡እሷ ካለች ቃላ ላሰበችው ነገር እንዳልጠራት አወቀችና በጣም ተከፋች….

"ማነው?"ጠየቃት ቃላ..አልመለሰቸለትም ዝም አለችው   ..ቃል ግን ወዲያው ገባውና  የሚሰራውን ምግብ አቋሞ ወጣ ""ጊፍቲ..እንኳን በሰላም መጣሽ" "ብሎ ተጠመጠመባት ..አገላብጦ ሳማት...ጊፍቲ ቅዝቅዝና ቅዝዝ ባለ ስሜት አፀፋዋን መለሰች ..ወስዶ ምግብ የተደረደረበት ጠረጴዛ አካባቢ አስቀመጣትና ትኩር ብሎ አያት ..ባለፈው ካያትም በላይ ጉስቁልና ጥቁርቁር ብላለች…ውስጡ አዘነ..ፊቱን አዙሮ ወደ ልዩ እየተራመደ ሳለ  በራፉ ዳግመኛ ተቆረቆረ...ልዩ ባለችበት ግራ ተጋባች ‹‹ዛሬ ምንድነው .? ›ስትል አጉረመረመች….ሄዶ ከፈተው።

"ኦ መድሀኔ ...እንኳን በሰላም መጣህ… ግባ›› ሲል ልዩ ሠማች ባለችበት ሽምቅቅ ነው ያለችው፡፡

‹‹ወይ ጉዴ ጭራሽ ያን ሁሉ የለፋሁበትን ነገር ገደል ከተተው..ይሄ ልጅ ምን እየሠራ ነው? ። እንዲህ በድንገት አንድ  ቤት የሠበሰበን ሊያቧቅሰን ነው ወይስ ሊያስታርቀን?ሊያስታርቀን ከሆነ በምን መልኩ።እንደድሮችን እንድንጣመር ወይስ በአዲስ አሰላለፍ...?››በደቂቃ ውስጥ አእምሮዋ ውጥርጥር አለ።
ከዛ የተሰራው ምግብ ሁሉ ጠረጴዛው ላይ ቀረበ...ሁሉም በተኳረፈ ስሜት ቢሆኑም ጠረጴዛውን ከበው ተቀመጡ.የቀረበውን ምግብ በልተው አጠናቀቁና የተበላበትን ሰሀኖች ተገጋዘው በማንሳት መልሰው በጠረጴዛው ዙሪያ ተቀመጡ።በዛ በውጥረት ውስጥ የመናገር  ቅድሜያውን የወሰደው  ቃል ነው።

ያው እንግዲህ  ሁላችንንም  እዚህ  ለምን እንድንገናኝ እንደፈለኩ ታውቃላችሁ።ባታውቁም መገመት አይከብዳችሁም፡፡ በመካከላችን ደስ የማይል ነገር ተፈጥሯል። እንደድሮችን እርስ በርስ አንገናኝም፤አንደዋወልም ይሄ ከዛሬ ጀምሮ በዚህ አይነት ሁኔታ መቀጠል የለበትም።

ልዩ ጣልቃ ገባች"ቃል እነሱ በእኛ ላይ የፈፀሙት በደል እኮ መቼም ይቅርታ የሚያሰጥ አይደለም" ተንዘረዘረች.አዎ በተቻላት አቅም ነገሩን ከመጀመሩ በፊት ልታስቆም እየጣረች ነው፡፡

ቃል ግን ቀድሞውንም ይሄን ገምቶ የተዘጋጀበት ጉዳይ ስለነበር በጥንካሬ ተጋፈጣት‹‹አይ… ይቅርታ የማያሰጥ አንድም በደል  የለም...ደግሞ በግንኙነት ውስጥ አንድ በአንድ ነገር ሲበድል  ሌላው ደግሞ በሌላ መበደሉ አይቀሬ ነው...ስለዚህ እሱ የበደለው ይቅር እንዲባልለት እሱ ቀድሞ  የጓደኛውን በደል  ይቅር ማለት አለበት።ጊፉቲ  አንቺ ለእኔ በጣም አስፈላጊ ሰው እንደሆንሽ ታውቂያለሽ  ።ለሁለታችንም ግንኙነት ብዙ ብዙ መስዋአትነት ከፍለሻል..አንቺ በጣርሺው መጠን እኔ አልጣርኩም.. በዛም በጣም አዝናለሁ...እባክሽ  በውስጥሽ ለፈጠርኩት መጥፎ ስሜት በአጠቃላይ ከልብሽ ይቅር እንድትይኝ እፈልጋለሁ"በማለት ከመቀመጫው ተነሳና በተቀመጠችበት እዛው ይዞ ጉልበቷ ላይ ተደፋ...እሷም እጇን ጭንቅላቱ ላይ አድርጋ ፀጉሩን እያሻሸች ትነፈርቅ ጀመር..

መድሀኔ እንደፈዘዘ ነው። ልዩ ግራ ገብቶታል‹‹ ምንድነበር የተፈጠረው?ማን ነው ማንን ይቅርታ መጠየቅ ያለበት.....?እኔም ተነስቼ መድሀኔ እግር ስር ልደፋ እንዴ?›እያለች ስትብሰለስል በድንገት መድሀኔ ከተቀመጠበት ተነሳና መጥቶ እግሯ ስር ድፍት አለ"እባክሽ ልዩ በተፈጠረው ነገር በጣም አፍሬለሁ።እንዴት እንደዛ እንዳደረኩ አላውቅም ።በእውነት በዛ ስካርና የእብደት ቀን ከተፈጠረው ውጭ እምልልሻለሁ በእኔና በእሷ መካከል ምንም የለም...አንቺ መስለሺኝ እሷንም ያሳሳትኳት እኔ ነኝ።በዚህም ሶስታችሁም ይቅር እንድትሉኝ እፈልጋለሁ።

"በቃ ተነስ ይቅር ብዬሀለው ....ከአሁን ጀምሮ ግን ንፅህ ጓደኛሞች ነን"አለችው ፈርጥም ብላ..ፈጥና ይቅር ያለችው ሆነ ብላ የቃልን ትኩረት ለመሳብ ስለፈለገች ነው፡፡ባለፈው ከቃል ጋር ስለዚህ ጉዳይ ሲያወሩ እንዲ እንድታደርግ ስለነገራት ምን ያህል የእሱን ቃል አክባሪ እንደሆነች እንዲያቅላት ስለፈለገች ነው

መድሀኔ ግን ከፊል በሆነው ይቅርታዋ እርካታ አልተሰማውም.በልመናው ገፈበት"እባክሽ ልዩ እኔ እኮ በጣም ነው የማፈቅርሽ በዛ ላይ የሁለታችንም ቤተሠቦች ለሠርጋችን እየተዘጋጅ እኮ ነው።ይቅር ብለሺኝ እንደበፊቱ ካልሆን ምን ልንላቸው ነው።"

"አይ እንደዛማ ፍፅም አይሆንም...እኔ ለቤተሠቦቼ አንተን እንደማላገባ ነግሬቸው ዝጎጅታቸውን አቋርጠዋል...አንተም ጊዜውና ሳይረፍድ ዛሬውኑ ለቤተሠቦችህ ንገራቸው።

"ምን ብዬ.ቀለበቱን እንኳን እንዲቀር ለማድረግ ስንት ነገር ቀባጥሬ ነው…ከእነጭራሹ ሰርጉም ጭምር ቀርቷል ብላቸው ኸረ በስመአብ?"ዘገነነው

"እሱ ያንተ ችግር ነው..."

"ቃል አረ አንድ ነገር በላት...ቆይ አንተ ጊፍቲን በፍቅረኝነት አትቀበላትም።"ሲል አንጀት በሚበላ ድምፅ ጠየቀው

ልዩ የቃልን መልስ ለመስማት አይኖቾን አፍጥጣበት በጉጉት ትጠብቅ ጀመር..የፈራችውን አይነት መልስ መለሰ"ለምን አልቀበላትም የይቅርታ ግማሽ የለውም እኮ"

በቃል ንግግር ወሽመጧ ብጥስ አለ‹‹...ምን አይነት ሀሞት የሌለው ሰው ነው...የወራት ልፋቴን በጠቅላላ ገደል ሊከተው እኮ ነው.. አሁን እሺ ምን ላድርግ?።›በውስጧ አብሰለሰለች.ሀሞትና ከርቤ ቀላቅላ እንደተጋተ ሰው .አፏን መረራት…፡፡መድህኔ ተፍለቀለቀ...ግን የልዩ ብስጭት ሆነ የመድሀኔ ደስታ ለሽርፍራፊ ሰከንድ ብቻ ነው መቆየት የቻለው።ድንገት የመብረቅ ብልጭታ በሚመስል ክስተት ታአምር መሳይ ዜና ከጊፊቲ አንደበት ዱብ አለ"አርግዤለሁ"አለች...መድህኔ በተንበረከከበት ዝርፍጥ ብ ሎ መሬት ያዘ
👍712😱2😁1
​​#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ኬድሮን ከምሽቱ 11 ሰዓት አካባቢ ሲሆን ደባበራት እና ከቤቷ ወጣች… ቦሌ አካባቢ  ወደሚገኝ ሰሞኑን ወደተከፈተ  አንድ ሆቴል ነው እየሄደች ያለችው ..መኪናዋን ሆቴሉ ግቢ ውስጥ በማስገባት ምቹ ቦታ ፈልጋ አቆመችና የለበስችውን ልብስ እዛው ከመኪናዋ ሳትወርድ አወላልቃ የዋና ልብሷን በመልበስ  ወደ ዋና ጋንዳው አመራች ..ሰውነቷን  ጭፍግግ ስላለት  ዘና ማለት  ነው የፈለገችው….በዋና ሰውነቷን ማፍታታት……
የዋና ገንዳው አካባቢ እንደደረሰች ዘላ ውሀ ውስጥ ገብታ መንቦጫረቅ አልፈለገችም…የመዋኛ ገንዳውን ዙሪያ ከበው ወደ ተዘረጉ ዘመናዊ ወንበሮች ሄደችና ..ባዳውን ከሆነ አንድ ወንበር ላይ ዘና ብላ በመቀመጥ የሚዋኙትን ታዳሚዎች እያየችና  እየታዘበች መዝናናቷን ቀጠለች…..
…..አበሻም ፈረንጆችም…. ሴቶችም ወንዶችም… ህፃናትም፤ ወጣትና አሮጊቶችም በስብጥር  ሲዋኙ እና ሲንቦጫረቁ ይታያሉ….
ስሜቷ አንቀልቅሎ ወደ እዚህ ስፍራ ያመጣት ለምን እንደሆነ እስከአሁን አልተገለፀላትም .. …?…..  ድንገት ግን ሳታስብ አንድ ወጣት ዕድሜው በግምት በ25 30 ዓመት መካከል የሚገኝ  ወንድ ላይ አይኗ አረፈ…ያምራል… በጣም ነው የሚያምረው..፡፡ ከደረቱ በላይ ያለው የሰውነት ቅርጽ ውጥርጥር ያለ እና ሚማርክ ነው…ፀጉሩ በውሀው አቅም ተሸንፎ በሚመስል ሁኔታ ዝልፍልፍ ብሎ ግንባሩ ላይ ተዘናፍሏል፡፡አይኖቹ ከጨረቃ የተዋሳቸው ይመስላሉ…ኪሊማንጀሮ ተራራ ጫፍ ላይ ያገኘችውን አንድሪውን አስታወሳት፡፡.
እሷ ደግሞ ካለ ችግሯ ወይም ድክመት ሊባልም ይችላል   ስድስት ወር ወይም አመት ምንም ወንድ ሳያምራት ወይም ከምንም አይነት ወንድ ጋር ሳትነካካ ትቆይና ድንገት በሰከንድ ውስጥ በእይታዋ ውስጥ የሆነ ወንድ ገብቶ ቀልቧን ከሰረቀት በቃ..ስግብግብ ነው የምትለው..፡፡በዛኑ ቀን ወይም ከተቻለም በዛኑ ደቂቃ ማግኘትና አምሮቷን መወጣት አለባት….(ያው የእሷ ፍቅር ከአንድ ጊዜ የወሲብ ፍላጎት አያልፍም ..ከዛ በላይ ፈልጋ አታውቅም ..ለእሷ በፍቅር መነሁለል እና . ወንድን እየተከተሉ መዞር ወይም ወንድ አፈቀርኩሽ እያለ ለሀጩን እያዝረበረበ በዙሪያዋ እንዲሽከረከርባት በፍፅም አትፈቅድም….)
.የእሷ ችግር ጊዜያዊ ነው ..ጊዜያዊም ብቻ ሳይሆን ቅፅበታዊም ጭምር ነው….በፈለገች ጊዜ ማግኘት አለባት… .ካለበለዛ እራሷን ሁሉ መቆጣጠር ስለሚያቅታት ጥፋት ታጠፋለች....የማይሰራ ስራ ትሰራለች…የወሲብ ጠኔም በቀላሉ አዙሮ እና አጥወልውሎ ሊደፋት ሁሉ ይችላል….እና አሁንም ይሄ ሻንቂላ ወንዳ ወንድ ወጣት እፊቷ ያለው ሰማያዊ መዋኛ  ገንዳ ውስጥ ጥበባዊ በሆነ ስልት እንደ ዓሳ ነባሪ ብቅ ጥልቅ በማለት እየዋኘ ቀልቧን ስልብልብ አድርጎታል..
‹‹ተይ ይቅርብሽ››እራሷን ለመገሰፅ ሞከረች…እራሷን መገደብ እንደማይሳካላት ግን ከልምድ ታውቃለች… …..ከለበሰችው የዋና ልብስ ስር እግሯ እና እግሯ መካከል ያሳክከት ጀመረ.. እጣቷን ወደ ጭኗ መካከል በመስደድ የሚበላትን አካባቢ አከክ…አከ…ክ አድርጋ ተንፈስ ለማለት አሰበችና   ዙሪያዋን በሰዎች መከበቧን  ሳታስተውል መልሳ ተወችው....ከተቀመጠችበት መቀመጫ ተነሳችና ወደዋናው ገንዳ ቀረበች…ምን ማድረግ እንዳለባት እያሰበች ነው…ድንገት በትይዩ አቅጣጫ በሰማዩ ላይ በሶስት መቶ ሜትር  ርቀት ….   ንስራ ሲያንጃብብ ተመለከተችና
‹‹…ወይ ከመቼው ተከትሎኝ መጣ….ግን እንኳን መጣህ.››ስትል በውስጧ አጉረመረመች…. እሱን በአቅራቢያዋ በማየቷ ደስ አላት..አዎ ይሄ ቀልቧ ያረፈበትን ወጣት ከተቻለ አሁን ለመክሰስ..ካልሆነም ለእራት ለማድረስ የእሱ እርዳታ ያስፈልጋታል….ስለደካማ ጎኑ በእነዛ ሰርሳሪ አይኖቹ  በማየት  ካልነገረራትና በምን ሁኔታ ብትቀርበው የሀሳቧ ሊሳካ እንደሚችል መረጃውን ካላቀበላት ባሰበችው ፍጥነት ሊሰካላት አይችልም ፡፡

ደስታዋ ግን ሀሳቡን አስባ ሳትጨርስ ነው ከውስጧ በኖ የጠፋው….የንስሯን እርዳታ መጠቀም አትችልም…ምክንያቱም ይሄ ሰው ምን አልባት የማይሆን ታሪክ ካለው..ወይም አደጋኛ ሰው ከሆነ ንስሯ  የሆነ ተአምር ፈጥሮ ከእሱ ጋር በምንም አይነት ተአምር እንዳትገናኝ ያደርጋታል..በምኞቷ መካከል ጣልቃ ይገባና ያጨናግፍባታል…ያ እንዲሆን ደግሞ አትፈልግም...ስለዚህ እዚህ ታሪክ ውስጥ ንስሯን አታሳትፈውም፡፡እንደዛ ወሰነች፡፡

..እንዳዛ ከሆነ ደግሞ እየበላት ያለውን በገዛ ጣቶቾ  ስታክ ማደራ ነው…ፈርዶባት ደግሞ በአንዱ የተቀሰቀውን ስሜቷ  በሌላ ወንድ አካክሳ ልታበርደው  አትችልም…ይሄ የእሷ የሆነ ልዩ ባህሪ ነው……
ስለዚህ ይሄን ጉዳይ በራሷ መወጣት አለባት….."ንስሯን ምንም እርዳታ አልጠይቀውም….እሱ በሚዋኝበት አካባቢ እስትራቴጂካል ቦታ መርጣ   ገንዳው ዳር ተቀመጠችና እግራን ብቻ ውሀ ውስጥ በማስገባት ልክ መዋኘት እንደሚፈልግ … ግን ዋና ስለማይችል መግባቱን እንደፈራ ሰው በመምሰል ማንቦጫረቅ እና በእጇ እየጨለፈች በውሀው መጫወት  ጀመረች….
አዎ  ልጁ እየዋኘ ወደስሯ ተጠጋ…ተመልሶ ሄደ ..ሶስት አራቴ በሰሯ ተመላለሰ…በአምስተኛው በአጠገቧ ሲያልፍና በጣም ሲጠጋት…

‹‹ታድለህ ››አለችው

‹‹ምን አልሺኝ…?››

‹‹ እንደ ዓሳ ነው የምትዋኘው…ታስቀናለህ…!!!  ››  

‹‹አመሰግናለሁ…››ብሏት ዋናውን ሊቀጥል ካለ በኃላ መልሶ ወደ እሷ  በመዞር..‹‹ለምን አትገቢም…? ››ሲል ጠየቀት

‹‹መግባት እፈልጋለሁ ..ግን ዋና አልችልም፤ ብሰምጥስ…?››

‹‹አይዞሽ እኔ እጠብቅሻለው ግቢ››

‹‹ኸረ ተው ይቅርብኝ››ተግደረደረች

‹‹ግቢ. በእኔ ተማመኚ››

የምትፈልገው  ሀሳብ ስለሆነ ቀሰ ብላ ገባችና ልክ እንደጀማሪ ዋናተኛ ተንደፋደፈች..በቅርቧ ስለነበረ ቶሎ ብሎ ከስር ገባና  ሰቅስቆ በክንዶቹ
መሀል አድርጎ ወደ ላይ አወጣት …
  

ይቀጥላል
👍10912👏1
#ትንግርት


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹እኔ ከቤት ወጥቼ ስለጠፋሁበት ያን ያህል የሚያዝን ይመስልሀል?››

‹‹ልጠፊ ቢሆንማ ምን አልባት አንድ ቀን ተመልሳ ትመጣለች በሚል ተስፋ አንቺን ለመጠበቅ ሲሉ ብቻ ህይወታቸውን በጥንካሬ ያቆዮታል፤ከሞትሽ ግን ለመኖር ምን ምክንያት ይኖራቸዋል?፡፡››

‹‹እንዴ!!!... ሞታለሁ መች አልኩህ?››

‹‹ባትይኝም ዕቅድሽ እራስሽን ለማጥፋት እንደነበረ አውቃለሁ፡፡››

‹‹እንዴ በምን አወቅክ…?ይሄ እኮ በውስጤ ብቻ ያቀድኩት የብቻ ሚስጥሬ ነበር፡፡›› በገረሜታና ግራ በመጋባት ጠየቀችው፡፡

‹‹እንዴት እንዳወቅኩ አትጠይቂኝ ..ግን እርግጠኛ ነበርኩ፡››

‹‹ለማንኛውም በጣም አስደንቀኸኛል፤ደግሞም በጣም አመሰግናለሁ፤ ለእኔ መልዓኬ ነህ፡፡ሁል ጊዜ ስላንተ ሳስብ የተቋጠረ ፊትህና የተዘጋ አንደበትህ ሳይሆን የውስጥህ ቅንነት ነበር የሚታየኝ፤በትክክል ነበርኩ ...ልዩ ሰው ነህ ››አለችው፡፡

ፊቷን ወደ እሱ አዙራ በማቀፍ ብትስመውና ብትውጠው ደስ ይላት ነበር ፤ግን አልቻለችም ፡፡ …ሊረዳት እንጂ ሊያፈቅራት እንዳልፈለገ ትዝ ስላላት..ፈራች፡፡ ቢሆንም የሆነች ብጣቂ የህይወት ተስፋ በልቧ ሲበቅል ይታወቃታል፡፡

ከሦስት ወር በኃላ ታዲዬስና መርጊቱ ቀለል ባለ ዝግጅት በስርአቱ 8ዐ ተፈራርመው ተጋቡ፡፡አባትዬው የግል ዕቃቸውን ጠቅልለው ታዲዬስ ተከራይቶበት የነበረበት ቤት ሲገቡ፤ በተቃራኒው ደግሞ ታዲዬስ ዕቃውን ሸክፎ አባ ወራ ሆኖ ትልቁ ቤት ገባ፡፡
አንድ ቤት መኖር ከጀመሩ ሁለት ወራቶች እየተገባደዱ ነው፡፡በዚህ ጋብቻ እንደ አቶ ቂጤሳ ደስተኛ የሆነ የለም፡፡መርጊቱ እርግዝና እየገፋ ሲመጣ የታዲዬስ እንክብካቤ እየጨመረ መጣ፡፡ አንድ ባል ለሚስቱ ማድረግ የሚገባውን ማንኛውንም ነገር ያለስስት ያደርግላታል፤ከአንድ ነገር በስተቀር፡፡ታዲዬስና መርጊቱ እስከአሁን አንድ መኝታ ቤት ውስጥ ቢያድሩም አልጋ ላይ እና መሬት ተለያይተው ነው የሚተኙት፡፡

ይሄ ሁኔታ ደግሞ ለመርጊቱ ይበልጥ ከብዷታል፡፡እንዴት ወንድ ልጅ ያለምንም ጥቅም አንዲት ምኑም ያልሆነችን ሴት ለዛውም ለማያፈቅራት ሴት እንዲህ መስዋዕት ይከፍላል?››

ፍራሹን ከተጣጠፈበት ፈታና ወለሉ ላይ ዘረጋው፤አንሶላና ብርድልብስ አቀበለችው፡፡ አነጠፈና ከጨረሰ በኃላ ተጋደመ..፡፡እሷም ከበላዮ ካለው አልጋ ወጥታ ከውስጥ ገብታ ከተኛች በኃላ ‹‹መብራቱን ላጥፋው?››

አለችው፡፡

‹‹አጥፊው፡፡››

አጠፋችው፡፡

‹‹...ውይ ፌናን ሳልነግርሽ፤ነገ አዲስአባ መሄድ ፈልጌያለሁ..ነገና እሁድን እዛ ውዬ ሰኞ እመለሳለሁ፡፡››

‹‹እሺ››አለችው፡፡

ቅር ያላት ስለመሰለው‹‹አትፈሪም አይደል?››አላት፡፡

‹‹ምን ያስፈራኛል..ካልሆነ አባዬ እዚህ እንዲተኛ አደርጋለሁ..ግን በሰላም ነው?››

‹‹አይ ሰላም ነው…ጓደኛዬ ናፍቀኸኛል ስላለችኝ ነው፡፡››

«...ማ ርብቃ?>>

‹‹አዎ..በዛ ላይ እኔም አምሮኛል..ሁለት ወር ሊሞላኝ እኮ ነው፡፡››ታዲዬስ ስለ እሱና ርብቃ ግንኙነት ከዚህ ቀደም ነግሯታል ፡፡

‹‹ርብቃ ማለት የታዲዬስ ጓደኛም፤ፍቅረኛም ነች፡፡በወቅቱ ሶስት ዓመት ያስቆጠረ የፍቅር ታሪክ ነበራቸው፤ሲነፋፈቁ ይደዋወሉና ይገናኛሉ፡፡ ለሁለት ሶስት ቀን ጣፋጭ የፍቅር ጊዜ ያሳልፉና መልሰው ይለያያሉ፡፡ሁለቱን የሚያቆራኛቸው የጋራ ነገር ፍቅራቸው እና ጓደኝነታቸው ነው፡፡

በጭለማው ውስጥ ለረጅም ደቂቃ ስለእሱና ስለርብቃ በዝምታ ስታሰላስል ከቆየች በኃላ‹‹ታዲ.... >> አለችው፡፡

<<አቤት>>

‹‹መሬት ልተኛ?››

‹‹አልተመቸሽም? ምነው ልቀይርሽ እንዴ?››

‹‹አይ!! ካንተ ጋር ለመተኛት ፈልጌ ነው፡፡››

‹‹ነይ ..ምን ችግር አለው፡፡››አላት…..ማብራቱን ሳታበራ ተንሸራታ ወረደችና ከጎኑ ተጋደመች፡፡

<<ታዴ...::>>

<<አቤት>>

‹‹ከርብቃ ጋር ግን የምትጋቡ ይመስልሀል?››

‹‹አይመስለኝም፡፡››

<< ከተፋቀራችሁ ለምን አትጋቡም?››

‹‹የተፋቀረ ሰው ሁሉ ይጋባል እንዴ..…?››

‹‹አዎ ሰው ከተፋቀረ ምን ይፈልጋል…?በአሁኑ ጊዜ የጠፋው እኮ በሁለት ወገን ሚከሰት ተመጣጣኝ ፍቅር ነው፡፡››

‹‹ችግሩ ሁለታችንም ለጋብቻ ጉጉት የለንም፡፡ ርዕሱንም አንስተን አውርተንበት አናውቅም፡፡ እኔ እንጃ ብቻ እንደዛ ሚሆን አይመስለኝም ››ወደ እሱ ዞረችና አቀፈችው፡፡እሱም አቀፋትና ተኛ ፤ቀድሞ እንቅልፍ ወሰደው .. እሷ ግን መአት ግትልትል ሀሳብ ስታስብ ለሊቱ ከተጋመሰ በኃላ ነበር እንቅልፍ ያሸነፋት፡፡ .

ታዲዬስ እንደተለመደው ከአንድ ወር ቆይታ በኃላ ጓደኛውን ርብቃን ጥየቃ ወደ አዲስአበባ ሄደ፡፡ ናፍቃው፡፡ ኮልፌ የሚገኛው ቤቷ ሲደርስ እሷ አልነበረችም፡፡ግን አልተመለሰም የሳሎኑን በራፍ ተጠጋና ዙሪያውን በዓይኑ ቃኘ፡፡የእግር መጥረጊያ ምንጣፉን ገለጥ በማድረግ ቁልፉን አገኘው፡፡ከፍቶ ገባ፡፡በሩን መልሶ ዘጋውና ያነገበውን መለስተኛ ሻንጣ ጠረጴዛ ላይ አኑሮ ወደ ሶፋው በመሄድ ጋደም አለ፡፡ ርብቃን ለምን እንደሚያፈቅራት ዘወትር ሲያስብ ግራ ይገባዋል፡፡ምን አልባት እንደ እሱ ሚስጥራዊ፣እንደእሱ በፀጥታ የተሞላች፣እንደእሱ ገለልተኛ ስላልሆነች ይሆናል፡፡ክፍተቱም ከእሷ ጋር ሲሆን ተደፍኖ ስለሚያገኘውም ሊሆን ይችላል፡፡ግን ለምንድነው እንደሌሎች ሴቶች ለጋብቻ ፍቅር የሌላት?ለምንድነው እስከዛሬ አግባኝ ብላ ያልጠየቀችው? ይሄም ይገርመዋል፡፡
መገረሙ ሳያበቃ እንቅልፍ ይዞት ጭልጥ አለ፡፡ መርጊቱ ነጭ ቀለም ያለው እስከ እግር ጥፍሯ የሸፈናትን ቀሚስ ለብሳ ከብዙ ሰው መካከል እየተሹለከለከች ወደ እሱ ትመጣለች፤ አባቷንም ትጠጋለች፡፡ አልፋ ፡፡ ወደእሱ ትጠጋለች።

‹‹ምነው መርጊቱ፤ ፈለግሺኝ?>>ይጠይቃታል፡፡

‹‹አዎ..እዚህ ካንተ እና ከአባዬ ጋር መኖር ከብዶኛል...እናቴ ጋር ብሄድ ይሻለኛል፡፡.››ትለዋለች፡፡

<እና?>>

‹‹እናማ እሷ ጋር ሄጄ ልኖር ነው፡፡››

‹‹እናትሽ የት ነው ያለችው?››

‹‹እሱን አላውቅም..ግን ልትወስደኝ መጥታለች፡፡…ያችዋትና እየጠበቀችኝ ነው››ብላ እናቷ ወዳለችበት አቅጣጫ ትጠቁመዋለች፡፡እይታውን ወደ ጠቆመችው
አቅጣጫ መልሶ ሲያይ እናትዪዋን ይመለከታታል፡፡ግርም ይለዋል፡፡እናትና ልጅ ምንም ልዩነት የላቸውም፡፡ በመልክ፣በአለባበስ፣ በቁመት፣ በሰውነት መጠን፣ብቻ የእናትዬው ፀጉር ድፍን ነጭ ሲሆን አጠገቡ የቆመችው መርጊቱ ፀጉር ደግሞ ከጥቁርነት ገና ወደ ነጭነት ለመቀየር የጀመረ ዓይነት ነው፡፡

‹‹እና ምን ልርዳሽ?›› ይላታል፡፡

አዲስ የሰው እጅ ያልነካው እስር መቶ መቶ ብር አንድ ላይ አስር ሺ ብር ይመስለዋል ወደ እሱ እየዘረጋችለት ‹‹ይሄንን በአደራ አስቀምጥልኝ፤ ይውልህ ይሄን ብር ለማግኘት ብዙ መከራ አሳልፌያለሁ፤ብዙ ተሰቃይቼያለሁ፡፡በካዝናህ ውስጥ ካንተ ወርቅ እና ዕንቁዎች ጋር አስቀምጥልኝ፡፡አንድ ቀን ተመልሼ ከመጣሁ ትመልስልኛለህ፡፡ ካልሆነም እኔን ፍለጋ መምጣትህ ስለማይቀር ያን ጊዜ ታስረክበኛለህ፡፡››

‹‹እንዴ!! ይሄን ሁሉ ብር ለምን ለአባትሽ አትሰጪያቸውም?እሷቸው ከእኔ በተሻለ በእምነት ያስቀምጡልሻል..በፈለግሽ ጊዜም መልሰው ይሰጡሻል፡፡››.

‹‹አይ አባዬ እኮ አሁን አርጅቷል፤ይሄንን ብር በሌባ እንዳይዘረፋ ነቅቶ መጠበቅና ማቆየት የሚችል ይመስልሀል..?ተው ተው ይሄንን አድርግልኝ ብዬማ ጭንቅ ውስጥ አልከተውም…አንተው ትሻለኛለህ፡፡››

‹‹ካልሽ እሺ..››በማለት ይቀበላታል፡፡

‹‹ግን ከባድ አደራ ነው ፡፡ የጣልሺብኝ ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ብር ቤቴ ገብቶ አያውቅም፡፡››
👍7817👏3🤔2
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ሳባ ሰገን ላይ የጀመረችውን በቀል ጀምራ እስክትጨርስ አንድ ዓመት ፈጀባት።መጀመሪያ ከትብለጥ ጋር ክፉኛ እንድትጣላና ስራዋን ሙሉ በሙሉ እንድትለቅ አደረገች፡፡ ለአመታት የሠራችበት ከድህነት ማጥ ወጥታ ሚሊዬነር የሆነችበት ክፉውንም ደጉንም ያየችበት ከምትወደው የስራ ቦታ ልታስወግዳት ቻለች፡፡ ትብለጥም የምትወዳት አለቃዋ ብትሆንም በተፈጠረው ጥል እሷም ተበድያለሁ ብላ ስላሰበችና በቂ የሆነ ሀብትና ንብረት ስላፈራች በቀላሉ ለመፅናናት ችላ ነበር፡፡ በወሩ መኪናዋ ነደደች፣ከሁለት ወር በኃላ ደላሎች እስከ መቶ ሚሊዬን ብር የሚያስገኝ ማዕድን አለ ብለው ባላት ብር ሁሉ ድንጋይ  ሸጠውላት  የባንክ ደብተሯን ባዶ እንዲያስደርጉባት ማድረግ ቻለች...ከዛ ጤናዋ ተቃወሰ… ህይወት ስታዘቀዝቅባት የተንጣለለ ቪላ ቤቷን ሸጣ ኮንደሚኒዬም ቤት ገዝታ ገባችና በቀሪው ሚኒባስ ገዝታ በሱ ሹፌር ቀጠራ በማስራት ኑሮዋን መግፋት ጀመረች… ስድስት ወር ሳይቆይ ሙሉ በሙሉ ሚኒባሱን አሰረቀችባት እና እንድትታረድ አደረገች....ከወር በኃላ ሰገን እራሷን በገመድ አንጠልጥላ የመሞቷን ደስታ በዜና አየች።
ከዛ ትብለጥን ሆነ ማንነቷን ያሳጣትን የስራ ቦታዋን ለማውደም ማድባት ጀመረች። ያ  ግን   ቀላል አልሆነላትም። ከሁለት አመት በላይ መጠበቅ   ነበረባት። አሁን ግን ጊዜው ደርሷል፡፡
ሳባ ትብለጥን እና ድርጅቷን በአንድ ጊዜ ለማውደም የዘየደችው ዘዴ የተለየ ነበር፡፡ ታሪኩን በጥልቀትና በዝርዝር በመፅሀፍ ማዘጋጀት፤ከዛ በሌላ ሰው ስም ማሳተምና በሰፊው እንዲሰራጭ ማድረግ ነው።
ደራሲ ጳውሎስ ከሀገር ከመውጣቱ በፊት እሷ እናቱን ልትንከባከብለትና ከመፅሀፉ የሚገኘውን ብር ልትሰጥለት እሱም በሄደበት ሀገር በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆን ሚስጥሩን ሊጠብቅ.. ካልሆነ ግን በእናቱ ላይ ችግር ሊደርስ እንደሚችል ነግራውና በማስፈራራት ሁሉን ነገር ችላ ው ሸኘችው፡፡ከሀገር መውጣቱን ከረጋገጠች ከአንድ ሰዓት በኃላ ለአከፋፋዬች ደውላ መፅሀፉን ማከፋፈል እንዲጀምሩ ነገረቻቸው፡፤
በማግስቱ መፅሀፉ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ውር ውር ማለት ጀመረ...በሶስተኛው ቀን በአንድ የግል ጋዜጣ ላይ "ቤርሙዳ ዘካሳንቺስ" በሚል ርዕስ የከተማዋ ቁጥር አንድ ሀብታሞች፤የመንግስት ሹማምንትና ታዋቂ አርቲስቶቻችን የሚመሽጉበት በማሳጅ ቤት ስም የወሲብ አገልግሎትን ጨምሮ ሀሺሽና ሌሎች ህገወጥ ስራዎች የሚካሄድበት    ቦታን ፀሀፊው ለአመታት ካጠና በኋላ በተጨባጭ መረጃ በማስደገፍ በ220 ገፅ መፅሀፍ  አድርጎ በማሳተም በአሁኑ ወቅት በገበያ ላይ አውሏል። በጣም የሚገርመው ግን በዚህ መፅሀፍ ላይ ታሪካቸው የተገለፁ ሰዎች እስከሚኒስቴር ደረጃ ስልጣን ያላቸው በመሆናቸው ያስገድሉኛል በሚል ፍራቻ ሀገር ለቆ መውጣቱን ማረጋገጥ ችለናል።›› በሚል  የደራሲውንና የመፅሀፉን የሽፋን ስዕል ይዞ ወጣ።
ከዛ ወዲያው ዜናው ከጋዜጣው በመነሳት በፌስቡክ መንደር በሰዓታት ውሰጥ ተሠራጨ...ቲክ ቶክ መንደር ተሸጋገረ... ዪቲዩበሮች ዜናውን እየቆረጡ እየቀጠሉ አባዙት፡፡ በከተማዋ መተረማመስ ተፈጠረ....መፅሀፉ ፓለቲካዊ ይዘት አለው የሚል ወሬ በጎን ተነዛ... የማሳጅ ቤቱ ደንበኞች የነበሩ ቱጃሮች እና ባለስልጣኖች ተበላን በሚል ስሜት በየፊናቸው መፅሀፉን ከያለበት በጅምላ እያስገዙ በማሰብሰብ ከገበያ የማስወጣት ስራ ሰሩ...ሳባ ግን  ለዚህ ተዘጋጅታ ነበር፡፡ከታተመው 5ሺ መፅሀፍ ኮፒ ወደገበያው እንዲለቀቅ ያደረገችው 2 ሺውን ብቻ ነበር።በከፍተኛ ጥንቃቄ በኮንትሮባንድ መልክ ከዋጋው ሁለትና ሦስት እጥፍ ቀሪው 3ሺ. ሞጃዋቹና ኃያሎቹ በማይደርሱበት መንገድ በሳምንት ውስጥ ተሰራጭቶ አለቀ...
ትብለጥ ለሳባ ደወለችላት ‹‹…ልጄ ጉድ ሆነናል››

ምንም እንዳልሰማች…እንዳአዲስ ጮኻ አዳነቀች…ወዲያው እየበረረች ከስሯ ተገኘች፡፡ ዋና አፅናኝና አማካሪዋ ሆነች፡፡
ማሳጅ ቤቱ ለጊዜው ተብሎ የተዘጋው በሶስተኛው ቀን ነበር... ባይዘጋም ወደዛ በስህተት ዝር የሚል ደንበኛ አልነበረም፡፡ እንደውም ከዛ ይልቅ እየደወለ ትብለጥ ላይ የሚጮህባትና የሚፎክርባት ደንበኛ በዛ...ጋዜጠኞችና ዩቲዩበሮች ወሬ ለማነፍነፍ ግቢውን በመክበብ ሰፈሩን አጨናነቁት..በዚህ ጊዜ ታዲያ ሳባ ከትብለጥ ጎን ሆና በዋናነት ሀዘን ላይ ከወደቁና እሷን ከሚያፅናኑ ሠዎች ግንባር ቀደሟ ሆነች... በሳምንቱ ትብለጥ ሙሉ በሙሉ መልሳ እንደማታገግም ገባትና ራሷን ለማትረፍ ወሰነች፡፡ሰራተኞቹን   በጠቅላላ    ከስራ    አሰናብታ    ንብረቷን ለጊዜው በውክልና ለዘመድ አስተላልፋ ወደውጭ ለመውጣት ዝግጅቷን ጨረሰች፡፡ ሁሉም ሰራተኞች ተራ በተራ ከስራ ለቀው ጥለዋት ቢሄዱም ሳባ ግን በውስጧ ደስታዋን እያጣጣመች በውጭ ያዘነች በማስመሰል እስከመጨረሻው ጠብታ አብራት ቆየች ። ለዛውም በእንባ እየታጠበችና በቁጭት የተንገበገበች በማስመስል። ችግሩ ከተከሰተ ከ15 ቀን በኋላ አብራት ውላ ቦሌ ድረስ ሸኘቻትና ወደቤቷ ተመለሰች።
በማግስቱ በግል ጋዜጣ ላይ ሆነ የመንግስት ሚዲያዎች ላይ ‹‹ቤርሙዳ ዘካሳንቺስ›› በሚል ርዕስ አነጋጋሪ መፅሀፍ የተፃፈበት የትብለጥ ማሳጅ ቤት ባለቤት ወ/ሪት ትብለጥ ገ/ኪዳን በግብር ማጭበርበርና ደረሰኝ ባለመቁረጥ ወንጀል ተጠርጥረው ከሀገር ሊወጡ ሲሉ ከቦሌ አየር ማረፊያ ተይዘው በቁጥር ስር ውለዋል።ቤታቸውም ሲፈተሽ ህጋዊ ያልሆኑ ደረሰኞች ከነማሽናቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል…..እያለ የሚቀጥል ዜና ተበተነ።
ሳባ ማታ ትብለጥን  ሸኝታት ከቦሌ ለመመለስ ፊቷን ስታዞር ፓሊሶች ወደ ውስጥ ሲገቡ እየተገፋፉ ነበር የተላለፉት..እንደዛ እንደሚሆን ታውቅ ነበር፡፡ ምክንያቱም ጥቆማውንም መረጃውንም የሠጠችው እሷ ስለሆነች።
ከዛ አዲዮስ
አንደኛውንና ጣፋጩን የህይወት ዓላማዋን ያጨለሙባትን ሁለት ሰዎች በሁለተኛው የህይወት ዓላማዋ ሰባበረቻቸው፣ወጥተው ወጥተው ከተሠቀሉበት አድማስ ሰማይ ሳጥናኤል ባቀበላት ጉልበቷ ጎትታ ሁለቱንም እንጦሮጦስ ጨምራቸዋለች... እሷም አስር አመት ስብዕናዋን ከሸጠችበት፤ማንነቷን ካሳጣት፣ያባቷን ነፍስ ካስነጠቃት ቤርሙዳ  ውስጥ  ልክ  ከአስር አመት ቆይታ በኋላ በታምር ነፃ ወጣች..ወይም የወጣች መሰላት...ለዛውም ቤርሙዳውን ለማንም እንዳይሆን አውድማው...እንደዛ በማድረጓ እስከ 50 የሚጠጉ ሰዎች ስራ እንዳጡ ታውቃለች...ቢሆንም የመቶዎችን ጋብቻ ከመፍረስ ታድጋለች...የሺዎችን ፍቅር ከስብራት ጠግናለች....በህይወት ፍፁም ጥሩ የሚባል ነገር የለም፡፡ያ ማሳጅ ቤትም ጥሩ ተግባር ፈፅሞ አይሰራበትም ብላ አታስብም እዛ ማሳጅ ቤት እሷ ጋር መጥተው ከመንፈስ ስብራታቸው አገግመው ህይወታቸውን ያስተካከሉ......የእሷን ምክር ሰምተው ጋብቻቸውን ከመፍረስ የታደጉ ብዙ ነበሩ፤ግን ከጠቅላላው አንፃር በጣም ጥቂት ናቸው። ስለዚህ እንዲዘጋ በማድረጓ ስህተት እንዳሰራች አታምንም.. ግን ደግሞ በቀሏን  እንዲህ  በስኬት ከተወጣች በኋላ ደስታዋ ለምን የሳምንት እድሜ እንኳን እንዳጣ ነው ግራ የገባት?ለምን ሁሉ ነገር በፍጥነት እንዲህ አስጠላት...? ለምን ከቤቷ መውጣት ከሰው መገናኘት ሆነ መደዋወል አንገሸገሻት...?ቀጣይ ዕቅዷ ምንድነው ራሷን መቅጣት ይሆንን? ይሄንን ስታስብ ዝግንን አላት።ምክንያቱም ለአባቷ ሞት ዋና ተጠያቂ ሰገን፤ትብለጥና፤ ራሷ ነች።
👍724
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሰላሳ_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
==================

....‹‹አሁንማ ያንቺ እንዳልሆነ አውቄያለሁ…በወቅቱ ግን የእሷ ነው ብሎ ስለላከልኝ ..ያንቺ በመሆኑ ምንም ጥርጣሬ አልነበረኝም..እናም በየጊዜው ደብዳቤ እፅፍልሽ ነበር፡፡ከአንቺም መልስ ለማግኘት አመታትን በናፍቆት ጠብቄያለሁ፡፡

‹‹ታዲያ ኢሜሉ የእኔ እንዳልሆነ እና ምትፅፍልኝ ደብዳቤዎች እንዳልደረሱኝ እንዴት ልታውቅ ቻልክ፡፡››

‹‹ከአላዛር ጋር ከተጋባችሁ ከአንድ ወር በኃላ በዚሁ ኢሜል መልስ ፃፈልኝ..መጀመሪያ ያንቺ መስሎኝ ፈንጥዤ ነበር …ሳነበው ግን የእሱ ነበር .. እንቺ አንብቢው››አለና ከፍቶ ሰጣት ፡፡

በጣም በመገረምና ምን ብሎ እንደፃፈለት ለማወቅ በመጎጎት ላፕቶፑን ተቀበለችውና ጭኗ ላይ አስቀምጣ ማንበብ ጀመረች፡፡

የልጅነት ጎደኛዬ ሁሴን እንዴት ነህ…?.የሰው ሀገር ኑሮ እንዴት ይዞኸል?እኔ በጣም ደህና ነኝ፡፡
ይሄንን ደብዳቤ ልፅፍልህ የተነሳሁት ይቅርታ እንድታደርግልኝ ለመጠየቅ ስለፈለኩ ነው፡፡የሰራሁት ነገር አግባብ ይሁን አይሁን አላውቅም፡፡ግን ደግሞ ደጋግሜ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ብገባ ተመሳሳዩን ነው የማደርገው፡እሰክዛሬ ለሰሎሜ እንዲደርሳት ስትልካቸው የነበሩ ኢሜሎች በአጠቃላይ ለእሷ አልደረሷትም….ምክንያቱም የምትልክበት አድራሻ የእሷ ነው ብዬ ብልክልህም እውነታው ግን በእሷ ስም የከፈትኩት እኔ ነኝ..እሷ ስለዚህ የኢሜል አድራሻ ምንም የምታውቀው ነገር  የለም ፡፡ወንድሜ የምትፅፍላትን  ደብዳቤ እንድታነበው ኢሜሉን  ልሰጣት ያልቻልኩት ላወዛግባት ስላልፈለኩ ነው፡፡አየህ አንተም ሆንክ አሌክስ እዚህ አጠገቧ የላችሁም፡፡ስለዚህ እሷን በተመለከተ ከአመታት በፊት እርስ በርስ የገባነው ቃልኪዳን ተፈፃሚ ሊሆን አይችም…ከህፃንነታችን እስከዚህን ቀን ድረስ አብሬያት በብቸኝነት መዝለቅ የቻልኩት እኔ ብቻ  ነኝ..የዚህንም ፍሬ አሁን ልቆርጥ ነው፡፡በቀደም እቴቴ ጋር እሷን ለማግባት ሽማግሌ ልኬ እሺ ተብያለሁ…ምን አልባትም ይሄ የኢሜል መልዕክት  በምታነብበት ጊዜ እኔና እሷ ታጋብተን ባልና ሚስት በመባል አንድ ቤት ገብተን ይሆናል፡፡ለዛ ነው አሁን እውነታውን ልነግርህ የፈለኩት፡፡ይሄንን ጉዳይ ሰሎሜ አታውቅም፡፡ከፈለክ ግን ደስ ባልህ ጊዜ ልትነግራት ትችላለህ፡፡ከአሁን በኋላ የእኔ ስለሆነችም እንዳታገኛት እንቅፋት ልሆንህ እልፈልግም…ቢያንስ ጓደኛዋ ሆኖ የመቀጠል መብት አለህ፡፡ለዛ ነው ቀጥታ ስልክ ቁጥሯን በዚህ የኢሜል መልዕክት ላይ የላኩልህ፡፡

በል ወንድሜ ቅር በተሰኘህብኝ ነገር ሁሉ ይቅርታህን ጠይቃለው….የዘላለም ጓደኛህ አላዛር ነኝ፡፡››ይላል፡፡

የምታነበውን ማመን ነው ያቃታት፡፡ምን አይነት ምላሽ ሁሉ መስጠት እንዳለባት ማወቅ አልቻለችም፡፡

‹‹እነዚህ በዚህ የኢሜል አድራሻ ላንቺ የላኳቸው መልዕክቶች አሁን ጥቅም የሌላቸው ና ጊዜያቸውም ያለፈባቸው ቢሆኑም ያንቺው ናቸው…ቢያንስ በወቅቱ ስለአንቺ ምን አስብ እንደነበረና ምን ብዬሽም እንደነበረ ያስረዳሉ….ላፕቶፑን ውሰጄና  ለማንበብ ዝግጁ በምትሆኚበት ጊዜ አንብቢያቸው››› አላት፡፡
ዝም ብላ እጇ ላይ ያለውን የተከፈተ ላፕቶፕ አጥፋ ዘጋችና  ከተቀመጠችበት ተነሳች….‹‹አራት ሰዓት አካባቢ ወጣ እንላለን….እስከዛ አረፍ በል….››ብላው ከእሱ መልስ ሳትጠብቅ ላፕቶፑን ይዛ ቀጥታ ክፍሉን ለቃ ወጥታ ወደ ራሷ መኝታ ክፍል አመራች…ክፍሉን ከፍታ በቁሟ ነው አልጋዋ ላይ  የተዘረረችው፡፡ኢሜሎቹን  አሁን ከፍታ ለማንበብ እና ሌላ አይነት ውዥንብር ውስጥ እራሷን ለመሰንቀር አልፈለገችም…ተንጠራራችና ላፕቶፑን  ኮመዲኖ ላይ አስቀመጠችው፡፡
‹‹በወቅቱ ሶስትም እንደሚያፈቅሩኝ ባውቅ ኖሮ ማንኛቸውን መርጥ ነበር?››እስከዛሬ አስባ የማታውቀውን ጥያቄ እራሷን ጠየቀች፡፡

‹‹ሶስቱንም በወጣትእናታቸው ምን እንደሚመስሉ …አቋማቸውን፤ ፀባያቸውን ፣የወደፊት ተስፋቸውንና ጉድለታቸውን መዘነች…..ልቧ አልማየሁ ላይ ተንጠልጥሎ ቀረባት…ግን ያ የሆነው በምክንያት ተመዘዝኖ በልጦ ስለተገኘ አይደለም….ብቻ በማታውቀው ምክንያት አንጀቷ በተለየ ሁኔታ ከልጅነታቸው ጀምሮ ለእሱ እንደሚንሰፈሰፍ ታውቃለች…ከሶስቱም ጋር ስትሆን ደስታና ምቾት እንደሚሰማት ታውቃላች ከእሱ ጋር ስትሆን ግን የበለጠ ድልቅቅ ያለ የመዝናናት ስሜት ነው የሚሰማት፡፡በሌላ ቋንቋ ለመግለፅ…ሶስቱም ጓደኞቾ ለእሷ ቤቷ ናቸው፡፡ግን ደግሞ አላዛርና ሁሴን ሳሎኗ ሲሆኑ..አላዛር ግን ጋደም ብላ እራሷን የምታድስበት….እርቃኑዋን ሆና ልብሷን የምትቀይርበትና የምትዋዋብበት የምቾቷ መጨረሻ ምሽግ የሆነው መኝታ ቤቷ ማለት ነው…እሱን እንደዛ ነው የምታስበው….ለዛም ነው እንደሚያፈቅራት እንኳን ሳታውቅ ጥሏት በመሄዱና ለስድስት አመት ከእሷ ጋር ያለውን ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ስላቆረጠ..ክፉኛ ተቀይማው ነበረው….፡፡

አላዛር 12 ሰዓት ሲሆን ለአሌክስ ደወለለት›

‹‹ሄሎ ኮማንደር›››

‹‹ሄሎ አላዛር››

‹‹የት ነህ..ስራ ቦታ ነህ ወይስ ወጣህ?››

‹‹አይ ስራ ቦታ ነኝ….ምነው በሰላም?››

‹‹አይ ስራ ከጨረስክ መጥቼ ልውሰድህ ልልህ ነው፡፡››

‹‹ወደ የት?››

‹‹እንዴ ጥዋት ተነጋገርን አልነበር እንዴ..?ወደቤት ነዋ››

‹‹ዛሬ ቢያልፈኝ አይሻልም…?››

‹‹ኖኖ…እንደዛማ አይሆንም..አሁን ሰሎሜ ደውላልኝ አብረን እየመጣን ነው ብያታለው…ዲያስፖራውም ይጠብቀናል::››

‹‹በቃ እሺ…በቢሮ መኪና እራሴ መጣለሁ››

        ‹‹ለምን ..ሜክሲኮ አካባቢ ነው እኮ ያለሁት..ልምጣና አብረን እያወራን እንሄዳለን…..››

‹‹እሺ በቃ ና››አለና ስልኩን ዘጋው፡፡

‹‹ይሄ ሰውዬ ለምንድነው እንዲህ ሙጭጭ ያለብኝ?››ሢል ጠየቀ፡፡ነገረ ስራው ሁሉ ግራ እያጋባው ነው..መቼስ እንደዚህ የሚያደርገው የድሮ ጓደኛሞችን በአንድ ላይ በመሰብሰብ የድሮ ፍቅራችውን እንዲያገኙ ለማድረግ አይደለም..የሆነማ የተደበቀ ተልዕኮ አለው››ሲል አብሰለሰለ፡፡‹‹ይሄንንማ ፈልፍዬ  እቅዱን ማግኘት ካልቻልኩ ምኑን ፖሊስ ሆንኩ?›› ሲል ፎከረ፡፡ከተቀመጠበት ተነሳና ከመስቀያ ላይ ጃኬቱን በማንሰት ለብሶ ከቢሮው ወጣ…የፖሊስ ጣቢያው ግቢ ውስጥ ወዲህ ወዲያ እየተንቀሳቀሰ አላዛርን መጠበቅ ጀመረ…ብዙ አላስጠበቀውም ..እንደደወለለት ፈጠን ብሎ ሄደና ገቢና ከጎኑ ተቀመጠ   …ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ መንዳት ጀመረ….

‹‹ውሎ እንዴት ነበር?››አለማየሁ ነበር የጠየቀው፡፡

‹‹ያው እንደተለመደው ነው..አንተ ጋስ?››

‹‹እኔ ጋርም እንደዛው…››
ለተወሰነ ደቂቃ በሁለቱ መካከል ጥልቅ የሆነ ዝምታ ሰፈነ..በኋላ ግን ኩማንደሩ ዝምታው  ሰበረው

‹‹ዛሬ ቤቴ ለማደር ነበር እቅዴ››

‹‹ቤት ብቻህን ምን ትሰራለህ…?አብረን ተሰብስበን ስንጫወት እናመሻለን››

‹‹እሺ እንዲህ ተሰብስበን መጫወት ለምደን በኃላስ…?

ማለት ስንበታተን…?አንተ ሚስትህን አቅፈህ በሞቀ ቤትህ ትቀራለህ..እኔ ሚስኪኑ ወደወንደላጤ ቤቴ ስመለስ በፊት ከማውቀው በተለየ ሁኔታ ቀዝቅዞ ደባሪ ሆኖ እንደሚጠብቀኝ አታውቅም?››

‹‹ሚስትህን አቅፈህ በሞቀ ቤትህ ነው ያልከው?››

‹‹አዎ …ምነው››

‹‹አሽሙር አይደለም አይደል?››

‹‹እንተ ሰው ከመቼ ወዲህ ነው እንዲህ ተጠራጣሪና የሰው ንግግር መንዛሪ የሆንከው?››

‹‹እኔን እኮ የቆሰለ ነበር በለኝ…ማንኛውም ኮሽታ ያስደነብረኛል….››

‹‹አይዞኝ….ቁስልህ በቅርብ እንደሚጠግ እርግጠኛ ነኝ፡፡››

‹‹ልሄድ ነው››
👍565