አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እህቴ_ባትሆኚ_አገባሽ_ ነበረ


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


#ክፍል_ሁለት

///
    እሁድ ነው በዛ ላይ ክረምት፡፡አየሩ ጨላማና ጭጋጋማ ነበር፤በዛም የተነሳ ከመኝታዬ መውጣት አልቻልኩም..ሞቆኛል ብርድልብሴን ተከናንቤ የሀሳብ ድር እያደራሁ የምኞት ሸማ እየሸመንኩ ነው፡፡እኔ እየብ ነኘ፤ማለት ስሜ እዬብ ነው፤ ህይወቴም ልክ እንደመፅሀፍ ቅዱሱ እዬብ ከምቾትና ከድሎት ህይወት በተአምራዊ ሁኔታ የተፋታ  ወደ ድህነት አዘቅት ተሸቀንጥሮ የተጣለ ነው፡፡

ልዩነቱ የዛኛው እዬብ መከራ የመጣበት በሰይጣንና በእግዚያብሄር መካከል በተፈጠረ ቁማረ መሰለ ክርክር በማያውቀው ጉዳይና የእሱ ባልሆነ ስህትት የአለምን ቅጣት ሁሉ እንዲቀጣ የተደረገ ነው..በእኔ ምልከታ እሱ ላይ የተደረገበት ግፍ ነው፤ አረ እንደውም ቤተ ሙከራ ውስጥ ሳይንቲስቶች እንደሚጠቀሙበት ሚስኪን አይጥ ነው ያደረጉት፡፡

   የእኔ ጉዳይ ግን እንደዛ አይደለም...እያንዳንዷን ያሳልፍኳት መከራ እያንዳንዷ የገጠመኝ ጨለማ ችግርና የብቸኝነት ስቃይ ከገዛ ራሴ ጥፋት የተመዘዙ ፤ወድጄና ፈቅጄ በምርጫዬ ወደ ህይወቴ ያመጣኋቸው የድክመቶቼ ውጤቶች ናቸው…እንደውም ሳስበው ከሚገባኝ በታች የተቀጣው ሰው ነኝ፡፡ስለዚህ ታላቄ እዮብ በማይገባው ስቃይ ተሰቃይቶ እንኳን እግዜሐብሄርን ሲያመሰግን ከኖረ እኔ ግን ከሚገባኝ በታች  እየተቀጣሁ እያለሁ እንኳን ሁሉ ግዜ ከምስጋና ይልቅ ንጭንጬ ለምን  አንደበቴን እንደሚቆጣጠረው ግራ ይገባኛል፡፡

ለአለፉት ሁለት አመት   የዘወትር ጸሎቴ፤ ስነሰና ስተኛ  መፅሀፍ ቅዱሴን ገልጬ መፅሀፈ-እዮብ ላይ ሄደና የእዬብን ምሬት ልክ ከራሴ ምናብ እንደመነጨ በመቁጠር  አንበለብል  ነበር ፡፡

..ያ የተወለድኩበት ቀን ይጥፋ...ያም ወንድ ልጅ ተፀነሰ የተባለበት ለሊት።ያ  ቀን ጨለማ ይሁን፣ እግዚሐብሄር ከላይ አይመልከተው፣ብርሀንም አይብራበት።ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው ገንዘብ ያድርጉት፣ደመናም ይረፍበት።የቀን ጨለማ ሁሉ ያስፈራው።ያን ሌሊት ጪለማ ይያዘው።በአመቶች ቀኖች መካከል ደስ አይበለው።በወሮች ውስጥ ገብቶ አይቆጠር።እንሆ ያ ሌሊት መካን ይሁን።እልልታ አይግባበት።...........ቀኑን የሚረግሙ ይርገሙት። አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፣........በመሀፀን ሳለሁ ለምን አልምትሁም?ከሆድስ በወጣሁ ጊዜ ፈጥኜ ስለ ምን አልጠፋሁም?ጉልበቾች ስለምን ተቀበሉኝ? ጡትስ ስለምን ጠባሁ።አሁን ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፣አንቀላፍቼ ባረፋሁ ነበር።

     አሁን ግን ይህንን የምሬት እንጉርጉሮ ማላዘን ካቆምኩ ሰነባበትኩ፤ ምክንያቱም በጥቂቱም ቢሆን ጭል ጭል የምትል ሻማ በህይወቴ የሆነ ጫፍ ላይ ተለኩሳ ማብራት የጀመረች ይመስለኛል.. ፡፡እንደነገርኳችሁ አቶ ሰሎሞን   ሆቴል ስራ ካገኘሁ ከአንድ ወር በኃላ የምኖርበትንም ቤት አገኘሁ፡፡የምኖርበት ግቢ ከሆቴሉ ተያያዥ ወይም ቀጥሎ የሚገኝ ሲሆን ሰፊና በዛፎች የተሞላ ነው፡፡በግቢው ውስጥ አንድ ኪችን፤ አንድ ሳሎን እና አንድ ሻወር ቤት ያለው መለስተኛ ቢላ አለ፡፡ይሄ ቤት የፊት ለፊቱ ሳሎን ከሌሎቹ ክፍሎች ጋር የሚያገናኘው በራፍ ታሸጎል፡፡ እኔ ሳሎኑ ውስጥ እኖራለሁ፤የተቀረውን ክፍል ነጋሽ’ዩ ሙሉአለም ይኖሩበታል፡፡ለዚህ ለምኖርበት ቤት በቀጥታ ኪራይ አልከፍልም፤ በምትኩ ግን የተወሰኑ አገልግሎቶችን ለቤቱ ባለቤት እሰጣለሁ፡፡
እኚህ እቤት የሚጋሩኝ ሰውዬ ማለቴ አቶ ሙሉአለም የአለቃዬ ማለት የሆቴሉ ባለቤት የአቶ ሰሎሞን አባት ናቸው፡፡

አዛውንቱ አቶ ሙሉዓለም የሚገርም ባህሪ አላቸው ፡፡ከቤት መውጣት ካቆሙ ሶስተኛ አመታቸውን ሊጨርሱ ነው፡፡በኮሮና ሰሞን በጣም የሚወዷት የእድሜ ዘመን ባለቤታቸው በዚህ በሽታ ተይዛ ሞተችባቸው...ከዛ እሳቸውም በፍራቻ እራሳቸውን ኳረንቲን አስገቡ፡፡ ይሄ በዛን ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃም ሆነ በሀገር ደረጃ በአዎጅ ሁሉም ዜጋ ባለበት እንቅስቃሴውን ገቶ እንዲቀመጥ ታዞ ስለነበር የእሳቸውም የተለየ አልነበረም…፡፡ግን ከወራት በኃላ አዎጁም ተነሳ ሁሉም ሰው ቀስ በቀስ ማስክ እያደረገ ከቤት መውጣት ፤ከዛም በሂደት ያለማስክስ ልክ እንደበፊቱ መተረማመስ ጀመረ፤ እሳቸው ግን ከቤታቸው ደጃፍ መውጣት አምቢኝ አሉ..፡፡ፀሀዮም ትቅርብኝ ጨረቃም አትናፍቀኝም አሉ፡፡ልክ እድሜ ልክ ተፈርዶበት ከርቸሌ እንደገባ ሰው በክፍላቸው ተከተቱ፡፡
ልጃቸው እራሱ በሳምንት አንድ ቀን መስኮታቸውን ይከፍቱና ከመስታወት ወዲያ ማዶ ሆኖ ያያቸዋል .እዛው በሶስት ሜትር ርቀት ሆነው አይን አይኑን  እያዩት  የሚያወሩትን ያወሩትና ይለያያሉ..ከቤታቸው ደጃፍ ለመሻገር ፍቃደኛ አይደሉም…ከማንም ሰው ጋር ለመነካካት አይፈልጉም፡፡

እና አኔ አንደኛ በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ከሆቴል አሰራና አምጥቼ  በራፍ  ስር  በማስቀመጥ …‹‹አያቴ ምግብ አምጠቻለሁ ያስገቡት፡፡›› እላቸዋለሁ፡

‹እሺ ዞረ በል›› ይሉኛል፡፡

‹‹እሺ ››ብዬ ዞሬ ወደ ክፍሌ ገባለሁ..እሳቸው ቀስ ብለው በራፉን ከፈት አድርገው መጋኛ እንዳያጠናግራቸው የፈሩ ይመስል ግራና ቀኛቸውን ገልመጥ ገልመጥ ያደርጉና የመመንጨቅ ያህል የምግብ ሰሀኑን በማንሳት ወደ ውስጥ ተመልሰው በመግባት በራፉን መልሰው ጠርቅመው ይዘጉታል፡፡
እና ሌላ የሚፈልጉት   ነገር ካለ ይነግሩኛል…ብዙውን ጊዜ በሳምንት አንድ ጠርሙስ ውሰኪና  መፅሀፍ ነው የሚጠይቁት፤ አልፎ አልፎ የራስ ምታት መድሀኒት ያዙኛል፡፡በአጠቃላይ ከውጭ የሚፈልጉት ነገር በጣም ጥቂት ቢሆንም ያንኑ ጥቂቱን  ካለበት ፈልጌ  የማቅረብ ኃላፊነቱ የእኔ ነው፡፡

በተጨማሪ  ከስራ ሰዓት ውጭ  እቤት ስሆን እኔም ሳሎኔ አልጋዬ ላይ ተኝቼ ፤እሳቸውም ወይ ተቀምጠው ውስኪቸውን እየተጎነጩ ወይ አልጋቸው ላይ ተጋድመው ይደሰኩሩልኛል ፡፡እኔም የጣሙኝንም ያላጣሙኝንም ወሬዎች በማዳነቅ እና በተመስጦ አዳምጣቸዋለሁ፡፡ አልፎ አልፎም ስለውጩ ዓለም ወቅታዊ ሁኔታ የተወሰነ ወሬዎች እነግራቸዋለሁ..ያው ድምፅን ትንሽ ከፍ አድርጎ ማውራት ይጠይቃል እንጂ ከግድግዳ ወዲህ ማዶና ወዲያ ማዶ በደንብ ለመደማመጥ ተቸግረን አናውቅም፡፡
ከእኔ በፊት ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት መአት ሴትና ወንዶች እዚህ ቤት ገብተው ነበር፡፡ ብዙዎቹ ግን ከአንድ እና ሁለት ወር በላይ መቆየት አልቻሉም ነበር..አብዛኞቹን አቶ ሙሉ አለም አልፈላጓቸውምና እንዲለቁ ተደረጉ ፤ የተወሰኑት ደግሞ ጠቅላላ ሁኔታውና የእሳቸውን ዲስኩርና ወሬ  በግድ ማድመጥ ሰልችቶቸው በራሳቸው ለቀው ይሄው ዛሬ እኔ ጋር ደረሰ..ለእኔ ግን ይሄው 11 ወር ሆኖኛል.እሳቸውም እስከዛሬ ከምስጋና ውጭ ስሞታ አቅርበውብኝ አያቀውቁም፤ እኔም ከቀን ወደቀን ከእሳቸው ጋር ያለኝ ትስስር እየጠነከረ እና እንደውም አያቴ እየመሰሉኝ መቸገሬን ስገልፅ እየተገረምኩ ነው፡፡አሁን ስገምት እንደውም ባሉካው እራሱ እየወደደኝ እና እያመነኝ የመጣበት ዋናው ምክንያት ከእሳቸው በሚያገኘው ተደራራቢ ሙገሳና ምሳጋና የተነሳ ይመስለኛል፡፡

ይሄ ሁሉ ሆኖ ግን እስከአሁን ጋሽ ሙሉአለም በአካል አይቻቸው አላውቅም…ልጃቸው እንኳን እንደሚያደርጉት በመስታወት አሻግሬ በሩቅ ለማየት እኔም ሞክሬ አላውቅም እሳቸውም አበረታተውኝ አያውቁም አንድ ቀን ጋሼ ‹‹መልኮት እኮ ናፈቀኝ ››አልኳቸው፡፡

‹‹ምነው ሳታውቀው እንዴት ሊናፍቅህ ቻለ….?

«የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም ሲሉ አልሰማህም?››

‹‹እኔ ግን እኮ በደንብ  አውቆታለሁ….እንደውም የማላውቀውን አያቴን ነው የሚመስሉኝ…..››
👍764🔥1🥰1😁1🎉1
#የዘርሲዎች_ፍቅር


#በፍቅረማርቆስ_ደስታ


#ክፍል_ሁለት


የወሮ መንደር ሽማግሎች ከሁለቱ መንደሮች መሃል ካለችው ትንሽ ሜዳ ግማሽ ክብ ሰርተው በርኮታቸው ላይ ተቀምጠዋል" ባለ
ጴሮው፥ ሹልሹላው፥ የሰጎን ላባ ፀጉሩ ላይ የሰካው ሁሉም በተመስጦ ስብሰባው እስኪጀምር ለውይይቱ ህሊናቸውን ይሳስላሉ  ህፃናት ከሽማግሎች ርቀው
እንቧይ እየተቀባበሉ
ይጫወታሉ ጋልታምቤ ከቤቱ ወደ ሜዳው በምትወስደው ቀጭን ጎዳና ሄዶ ከሽማግሎች ጋር ተቀላቀለ ሌሎችም ከያቅጣጫው እየመጡ
ተደባለቁ„

ረጅም ጦር የያዙት የመንደሩ አለቃ (ዘርሲ) ከተቀመጡበት
ተነሱና ከወገባቸው ከታጠቁት ዝናር ጩቤ አውጥተው ጎረምሶች
የያዙትን ለፍላፊ ፍየል በቁሙ ጉሮሮው ላይ ወጉትና ፍየሉ ሲወድቅ
ከደሙ ጦራቸው ላይ ከፈርሱ ደግሞ ባታቸውን ቀባ-ቀባ አድርገው
ሄድ መለስ: ሄድ መለስ ብለው ንግግር ጀመሩ

"ጥሩ ነው! ዝናቡ መጥቷል መሬቷ ሳር አብቅላለች፥
ተራሮች እንደ ልጃገረድ አጊጠዋል ድንጉላ ቢራቢሮዎች፥ ወፎች
ይበራሉ" ንቦች አበባቸውን እየቀሰሙ ወደ ቀፎቻችን ይተማሉ፥ ውሃ የጠማት ምድር እምትጠጣው አግኝታለች እኛም የምንጠጣውን  ከስኬ ይሰጠናል አሸዋውን ስንጭረው ውሃ መሬቷን በጧር  ስንወጋት ማሽላ እናገኛለን ዳመናውን ሰርስራ
በምትወጣው ጨረቃም ልጆቻችን ይደሰታሉ
እንግዲህ ተቀያችን: ከዚች
አባቶቻችን ካቆዩን ምድር ምን ጎደለ!" ብለው ዝም አሉ የሽማግሎች
አለቃ" እንደገና ሄድ መለስ እያሉ ሁሉንም በዐይናቸው እየቃኙ

ብዙዎቹ ተሰብሳቢዎች ዐይናቸው ያለው ሌላ ቦታ ነው ሐመር ላይ ነገር በዐይን አይገባም' ነገር የሚደመጠው በልቦና ነው፤
ልቦና ያያል ልቦና ይሰማል
ልቦና ይመራመራል ልቦና
ይወስናል" በልቦና ለማየትና ለመስማት ግን ፀጥታ ያስፈልጋል ውስጣዊ እርጋታ የሃሳብ ማዕበል የሌለበት መተራመስ የተረጋጋበት ሊሆን ይገባል" ሐመር ላይ ሽበት ብቻ
ለሽምግልና አያበቃም፤
ጀግንነት ብቻ አያስከብርም
ማህበራዊ ችግርን ለመፍታት በጥንቃቄ ውሉን ፈልጎ አግኝቶ ትብትቡን
የሚፈታ ህሊናው ቀልጣፋ ከጀግንነቱም ከፍርድ አዋቂነቱም ሁለገብ ችሎታ ያለው መሆን ያሻል  ለሽምግልና ለመታጨት

"ጥሩ ነው! የአባቶቻችን መንፈስ ከእኛ ጋር አለ እንዳንራብ መከራ እንዳይበዛብን ዝንጉ እንዳንሆን የነሱ መንፈስ እንደ ዛፍ ጥላ ከለላ ይሆነናል ይሁን እንጂ በአባቶቻችን የነበረው ችግር አሁንም
አለ አሁንም የአባት ጠላት አለን አሁንም የአባት ጠላቶች እያዘናጉ የከብቶቻችንን ጅራት ሊጎትቱ የሚስቶቻችንን እጅ ሊስቡ፥ የላሞቻችንን ጡት ሊያልቡ ይፈልጋሉ ተናጋሪው  ንግግራቸውን ገተው ዙሪያ ገቡን እያዩ ፀጥ አሉ የኦሞ ወንዝ ቆሞ ያውቃል? ውሃ ታግዶ ይቆማል? ያባት
ደንብም እንዲሁ ነው፤ ሁሌም ከልጅ ወደ ልጅ ግድቡ በሽማግሎች
እየተከፈተ ከላይ እየወረደ የመጣው ወደሚቀጥለው
ትውልድ እየቶንዶለዶለ
ይፈሳል" ለዚህ ነው ከስኬ ሲጫር ውሃ: የእኛ ልብ
ሲቆፈር ደግሞ ያባት ደንብና ባህል የሚፈልቀው፤ ከእኛ መሃል ልቡ ሲቆፈር የአባት ደንብና ባህል የማያፈልቅ ደረቅ ካለ ግን ከጠላት
የተወረወረብን ድንጋይ ስለሆነ አምዘግዝገን መወርወር፥ ካካባቢያችን
ማጥፋት ይኖርብናል" ተናጋሪው ሽማግሌ ንግግራቸውን ገትተው
የተናገሩትን እንደገና በህሊናቸው አጣጣሙት።

"ወንድሞቼ የአባቶቻችን መንፈስ ከእኛ ጋር ነው
የምንሰራውን እነሱ ካቆዩን ደንብ ጋር ካላመዛዘነው እንደ ዱር ጉንዳን ማን እንደቆመብን ሳይታወቅ፤ ምንነታችንም ሳይጠየቅ አውራ እንደሌለው የሚያስተባብረው እንዳጣ ንብ በየጢሻው እንበተናለን
እንጨት ቆርጠን ሳር አጭደን ለንብ ቀፎ እየሰራን: እኛ ግን ተሰርቶ የቆየንን የአባት ደንብ ደህንነቱን
በመጠበቅ ለልጅ ልጆቻችን ማስተላለፍን ዘንግተናል" ከጉንዳን: ከንብ አንሰን የአባት ደንብ እየሻርን ነው: ትብብራችን እየላላ ነው፥ ወኔያችን ተሸንቁሮ
ንፋስ እየገባው ነው." እንደገና ቃኙት ተሰብሳቢውን  በዝምታ።

"አውሬ ይሁን ወፍ የማይታወቅ ጉድ በአራት እግሩ መንደራችን እየመጣ ሲቆም በሰፊው ሆዱ  ሴቶቻችንን እየሸፋፈኑ
እያቀፈ ሲወስድና ሲመልስ
ሴት ልጅ ወንድ የዘራውን ማብቀል  ሲሳናት እኛ አልተቃወምንም! ኧረ ተው! የተቀበልነውን የማናቀብል ጅብ አንሁን ጅብ የሚኖረውና የሚሞተውም ለሆዱ ነው የአባት ደንብ የለው ለልጄ ማለት አያውቅ አፍንጫው ጥንብ እንዳሸተተ: ሆዱ ለመብላት እንደተስገበገበ
ኖሮ ይሞታል ለልጄ ሳይል ደንብ ሳይኖረው ጥንብ እንደ አማተረ ይሞታል ለሆዱ! የተናጋሪውን ሃሳብ ከሚያዳምጡት መካከል አንዱ ሽማግሌ
የዘርሲዎች አለቃ በተናገሩ ቁጥር "ህም ህም… "አሉ በሐመር የስብሰባ ደንብ አንዱ ሲናገር ሌላው ህም ህም ካለ ልቀጥል ልናገር ማለት ስለሆነ የሽማግሎች አለቃ የንግግር እድሉንና
ተናጋሪው የሚይዘውን ጦር አቀበሉ  ተረኛው ሽማግሌ ጦሩን በቀኛቸው ይዘው ከፍየሉ ፈርስ ባታቸውንና ግንባራቸው ቀባ አድርገው እየተንቀሳቀሱ ሽማግሎችን: ህፃናትን: መንደሩን: ዙሪያ
ገቡን ቃኙት ጦሩ እጃቸውን ነዘረው ስሜታቸውን በሙቀቱ አጋጋለው፤ ወኔያቸውን እንደ ብረቱ ጫፍ አጠነከረው  የአያት
የአባቶቻቸው መንፈስ ከጦሩ ተነስቶ ወደ ልቦናቸው ተስለከለከ

ጥሩ ነው! የቀጋ ፍሬ ከሾላ ዛፍ የለቀመ ማነው ሾላና
ቀጋን ደባልቆ የሚበላ ግን አስተዋይ ነው ይህ ሰው የተፈጠረው ደግሞ እዚሁ እኛ ዘንድ ቡስካ ተራራ ላይ ነው ያ ሰው እሳት
አንድዶ የሚፈልጋቸውን መልካም መልካም ሰዎች በእሳት ብርሃን
ከያካባቢው ጠራቸው
እንግዲህ አያቶቻችን የባንኪሞሮን እሳት
እያዩ ከያቅጣጫው የተሰባሰቡ ናቸው እኒያን ፍሬዎች  ቀጋና ሾላዎች ባንኪሞሮ ደባልቆ በሐመር ምድር በተናቸው"
አያቶቻችንና አባቶቻችን በቀሉ ከእኒያ ብሩክ ፍሬዎች ደግሞ እኛ በቅለን እህ! በተራችን እንድናፈራ ላደረጉን አባቶቻችን ውለታችን ምንድነው?" ብለው ዝም አሉ ሽማግሌው በጠየቁት ጥያቄ አንጀታቸው እየተላወሰ መልሱን ግን ፀጥታው ዋጠው"

"ወንድሞቼ የአባቶቻችን መልካም ሥራ የሚመለሰው ባህልና.ደንባቸውን በመጠበቅ ነው" ተዚህ ታፈነገጥን የሚያድነው እንሰሳ ላይ ማነጣጠር እንዳልቻለ አነር መሮጥ እንጂ የምንይዘው አይኖርም ሁሉም ያምረናል፤ አረንጓዴ ሁሉ ይበላል? ኮሽም: ዶቅማ ይሆናል?- የእኛ ህይወት የአባቶቻችንን ፈለግ በመከተል የሚመራ
ነው፤ እነሱ ያዩትን ዓለምና ደስታ ለማግኘት ከዱካቸው ዝንፍ ማለት የለብንም ተዚያ ታፈነገጥን ግን እሾህ አለ እንቅፋት አለ… ዳመና
ከሰማዩ ላይ ይጠፋል ከብትና ምድሯ ይነጥፋሉ በሽታ ይበዛል ከዚያ ያኔ ቀያችን አጥንት ሰላማችን ቆምጭሮ ሁከት
ይከመርበታል እፅዋት መብቀል ያቆማሉ፤  ባንኪሞሮ  የአነደደው
እሳት ይጠፋና ጥንት እንደነበረው ቀያችንን ዳፍንት ይውጠዋል
ባዶ ይሆናል! እና ተልባችን እንምከር ወንድሞቼ!" ብለው እጃቸውን
አወራጭተው ጦሩን ስመው ዝም አሉ ሌሎች ሽማግሎችም እንዲሁ
የሚሰማቸውን ሲናገሩ ቆዩና ጥፋቶች በመጀመሪያው
ተናጋሪ ተዘረዘሩ።

በአካል ለዘለዓለም
ለተለዩን በርቲና ቃላ መደረግ የሚገባው ደንብ አልተሰራላቸውም "አሉ” እንዳንል የሉም የሉም
እንዳንል ደግሞ ደንቡን የምትጠብቀው ነፍሳቸው አንዴ በወፍ ሌላ ጊዜ በአሞራ ወይንም በንፋስ … መልክ እየመጣች ከእኛ ጋር ናት ንግግራቸውን ገተው የሽማግሎችን የመንደሯን የአካባቢውን ትንፋሽ አዳመጡና

ነጯ ሐመር ይዛው የመጣችብን ስም የለሽ: ጢስ ተፊ አውሬም እዚሁ ከእኛ ጋር እየኖረ ነው ሲበላ ባናየውም ሲጋት ግን
በዐይናችን በብረቱ አይተነዋል ከዚያ እንደ ጅብ አጉረምርሞ ዐይናችን እያዬ ግማቱን ለቆብን ይሄዳል "
👍18
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

///

ክሊኒክ ደረሱ.. ።ከባለላዳው የወሬ ዝባዝንኬ ስለተገላገለች ደስ አለት ..።ወረዱ.. 100 ብር ከፈለው። ወደ ውስጥ ገቡና ካርድ ቆርጠው በድንገተኛ ስም ተራ ሳይጠብቁ ወደህክምና መስጫው ክፍል ገቡ።የሚፈሰው ደም እንዲቆም ተደረገ ፤ያበጠውና የተጫጫረውም የሚደረገው ተደርጎ በፍሻ ተጠቅልሎ በፕላስተር ተለባበደላት.፡፡.አምስት ቀን የሚዋጥ ኪኒኒ አሸከሟት..፡፡ዝም ብላ ፈዛ እያየችው 850 ብር ከፈለ..።ጥዋት ከቤት ስትወጣ እንደቀልድ ኪሷ ውስጥ ሸጎጥ ያደረገችው ከ2ሺ ብር በላይ አላት...ግን ለመክፈልም ሆነ ለመግደርደር ምንም አይነት ሙከራ አላደረገችም….ለምን እንዳልተግደረደረች ደግሞ እሷም መልሱን አታውቅም ፡፡ለብር ቁጠባ ወይም በስስት ምክንያት እንዳልሆነ ግን እርግጠኛ ነች፡፡

እስከአሁን ባደረገው ነገር በውስጡ እርካታ ተሰምቷታል….አዎ አሁን ቢለያት ምንም የሚፀፅተው ነገር እንደሌለ ያውቃል...ግን ይህቺን ልጅ በተመለከተ የሚሰማው ሰሜት አሁንም የተለየ ነው…‹‹ይህቺ ልጅ ሌባ አይደለችም…››ሲል አሰበ..ግን ደግሞ ስትሰርቅ እጅ ከፍንጅ ተይዛለች ለዛውም የገዛ ስልኩን… ቢሆንም ልቡ እውነት ነው ብሎ ሊቀበልለት አልቻለም…ታዲያ እውነታው ከአይኖቹ ምስክርነት ያገኘው ሀቅ ነው ወይስ ልቡ ሹክ የሚለው ትንቢት?….ይሄንን ሳያረጋግጥ እንዴት ይለያታል..?ጨነቀው…፡፡ ‹‹አሁን ስልክሽን ስጪኝ ብላት ሌላ አላማ ያለኝ ነው የሚመስላት››ከውስጡ ጋር የጀመረውን ሙግት ሳያቋርጥ."አሁን እንሂድ..."አላት፡፡

"ከተቀመጠችበት ተነሳችና በዝምታ ተከተለችው” ..ጎን ለጎን እየሄዱ ነው።በሁለቱም ፊት ላይ ጭንቀት ይነበባል.እንዲህ እንደቀልድ በአጋጣሚ እንደተገናኙ በአጋጣሚ መለያየቱን ሁለቱም የፈለጉት አይመስልም፡፡

‹‹...እንዴት ነው የምንለያየው...? ደግመንስ እንገናኛለን? ›በእሷ እምሮ ውስጥ የሚጉላሉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

‹‹ያወጣኸውን ብር እንድከፍልህ አድራሻህን ስጠኝ ››ልበለው እንዴ? በነዚህና መሠል ጥያቄዎች በውስጧ ስትብሰለሰል ስልኩ አንቧረቀ...ቅድም እዛ ታክሲ ውስጥ የሠማችው ምን አልባትም መቼም ልትረሳው የማትችለው አስቀያሚ ያለችውን ጥሪ ነው እየሰማች ያለችው..እሱ በዝምታ አንገቱን አቀርቅሯል፡፡

.."ምን አንገቱን ይደፍል ስልኩን አንስቶ ይሄንን ጥሪ በመስማቴ እያተቀሰቀሰብኝ ካለው የእፍረት ስሜት አይታደገኝም እንዴ?""በማለት በሆዷ እያጉረመረመች ሳለ በተመሳሳይ አቅጣጫ እየተጓዘች ያለች አንድ ወጣት.."እህት ስልክሽ እኮ እየጠራ ነው"አለቻት ወደ ጃኬት ኪሴ እየጠቆመች።

"ምን እያለች ነው?"በሚል ስሜት በርግጋ እጇን ወደኪሷ ከተተችና መዠርጣ ሳታወጣ የልጁ ስልክ ነው።እስከአሁን እሷ ጋር ምን ይሰራል?እንዴት አልመለስችለትም?...እሱስ እስከአሁን እንዴት ስልኬን መልሺ አላላትም...? በመሀከላቸው የሆነ የሚያደነዝዝ አይነት አዚም ተረጭቷል ማለት ነው፡፡ከዝምታዋ ሳትላቀቅ እጇ ላይ ያለውን የሚጠራ ስልክ ወደእሱ ዘረጋችለት... በትህትና ተቀበላትና ወደጆሮው ለጥፎ ሄሎ ከማለቱ በፊት ተዘጋበት።

ደዋዩን ማንነት ተመለከተና "ጓደኛዬ ነች በኃላ መልሼ ደውልላታለሁ..."ብሎ መልሶ ስልኩን ወደእሷ ዘረጋው፡፡

"ይሄ ልጅ ያመዋል እንዴ?"በውስጧ ነው ያማችው ፡፡

"ያንተ እኮ ነው..ምን ላድርገው?"

"እ ይቅርታ የእኔ ነው ለካ" ብሎ ኪሱ ከተተ፡፡ ሳቋ አመለጣት.... አብሯት ሳቀ...‹‹.ጥርሶቹ ያምራሉ። ›ስትል በውስጧ አሰበች፡፡
ከሆስፒታሉ ግቢ ወጥተው በአንድ አቅጣጫ እየተጓዙ ነው።ታክሲ ወደሚገኝበት እና ላዳዎች ወደሚቆሙበት ስፍራ።ሁለቱም በምን ሁኔታ ተለያይተው ወደየመዳረሻቸው እንደሚሄድ ግራ እንደገባቸው ነው፡

ምን አድርጋ እንዴት አይነት ዘዴ ፈጥራ ከእሱ ጋር ያላትን ቆይታ እንደምታራዝም እያሰበችበት ቢሆንም ምንም አይነት ዘዴ ወደምናቧ አልመጣላትም…እሱም እደዛ እያሰበ እንደሆነ ግን ተሰምቷታል..ወይንም እንዳዛ እንዲያስብ ፈልጋ ይሆናል ፡፡:

"ቤቴ ድረስ ሸኘኝ ልበለው እንዴ ?..ይሄ ደግሞ ምን አይነት ቅብጠት ነው?››ቢለኝስ፡፡

ድንገት የንዴት በሚመስል ቃና ቆጣና ኮስተር ብላ‹‹በቃ እንለያያ ..በጣም አመሰግናለሁ"አለችው..

ካቀረቀረበት ቀና አለና

"እንለያይ.. እሺ ደህና ሁኚ..." አላት፡፡

ክፈት አላት፡፡እሷ ያልገባት እሱም እንደዛ አይነት መልስ የመለሰላት አስቦበት ወይም እንደዛ ማለት ፈልጎ ሳይሆን ድንገት ከእሱ ፍቃድ ውጭ ከከንፈሩ አዳልጦት ነው፡፡ዘመናትን በሚመስል የተጎተተ ድምፅ"ደህና ሁን ...››አለችው፡

ስህተቱን ለማስተከከል ያደረገው በሚመስል ሁኔታ"ግን እኮ ላዳ ላሳፍርሽ ነበር..."አላት….አሁንም ድንገት አፉ ላይ የመጣለትን ቃል እንደወረወረ ያስታውቅበታል..ቢሆንም የምትፈልገውን ነገር ነው የተናረው..ነገር ግን ያው ሴት ነችና..እሷም እንደቢጤዎቾ መግደርደር አማረት..በመሀል ጣቷ ግንባሯን አሽት አሸት እያደረገች"አይ በታክሲ ሄዳለሁ..አንተ አትቸገር"አለችው፡፡

"ታክሲውንም ቢሆን ላሳፍርሻ ...ሰፈርሽ የት ነው?።››ሲል ጠየቃት፡፡

"ሳሪስ"

"በድንግል ማሪያም … እንዲህ ቆስለሽ ምንም ሳታርፊ ከመገናኛ ሳሪስ...?አይ እንዲማ አይሆንም..የእኔ ቤት እዚ ካሳንቺስ ነው..እንሂድና አንድ ሁለት ሰዓት አርፈሽና ተረጋግተሽ ትሄጂያለሽ።››አላት፡፡

እቤቱ ድረስ ሴት ሲጋብዝ ይሄ የመጀመሪያ ቀን ገጠመኙ ነው፡፡እቤቱ ከአንድ ሴት በስተቀር ገብታበት አታውቅም…እነድትገባበትም ፍላጎት አድሮበት ፍፅም አያውቅም …ምክንያቱም ያቺ ሴት የዘላለሙ ነች…ልዋጭም ሆነ ቅያሪ የማያስፈልጋት ብቸኛ ምርጫው….ዛሬ ግን የሚሰራቸው ነገሮች ሁሉ ከቁጥጥሩ ውጭ ናቸው..እና ከውስጡ መታገል አልፈለገም..ሊሆን ያለው ነገር እንዲሆን መፍቀድ አለብኝ››አለና ከራሱ ጋር ተማክሮ ወሰነ፡፡ግን ሁኔታውን በትዝብት ለሚከታተል ሰው ሴትን አዳኝ ብሎ እንደሚፈርጀው እርግጠኛ ነው..አረ ልጅቷ እራሷ እንደዛ ማሰቧ አይቀርም››አለ በውስጡ፡፡

እሷም ያልተጠበቀ ግብዣውን ስትሰማ ዘለሽ ሂጂና ተጠምጠሚበት የሚል ስሜት ተፈታተናት ...ግን እንዴት ብላ..?የልቧን መሻት ከግንባሯ እያነበበ የሚያወራ ነው የመሰላት...እንደዛም ሆኖ ግን አንደበቷ እንደልቧ በቀላሉ እጅ የሚሰጥ አይነት አይደለም።

"አረ አይሆንም...ከዚህ በላይ ላስቸግርህ አልፈልግም...አንተም ወደምትሄድበት ብትሄድ ነው የሚሻለው፡"

"የምሄድበትማ ለስራ ነበረ …አሁን ሰዓት አልፎል.. ብሄድም መስራት አልችልም...እኔ ቀጥታ ወደቤት ነው የምሄደው ..ካልደበረሽ አብረሺኝ ብትሄጂና እንዳልኩሽ የታዘዘልሽን ኪኒንም ውጠሽ አረፍ ብለሽ ስትረጋጊ ወደ ቤትሽ ብትሄጂ ደስ ይለኛል።››አላት፡፡

ከአሁን በኃላ ብትግደረደር ሌለ እድል እንደማይሰጣት እርግጠኛ ሰልሆነች "አረ አይደብረኝም..እሺ እንሂድ"አለችው፡፡

እየተከታተለን ያለ ሠው ቢኖር ሁለቱም ፊት ላይ የደስታ ካፊያ እንደተርከፈባቸው የፊታቸው በድንገት ማብረቅረቅ በመመልከት በቀላሉ ይረዳ ነበር፡፡ላዳ አስቆሙና ይዟት ገባ...በስድስት ደቂቃ ውስጥ እቤቱ ደረሱ።

ይቀጥላል
👍14236🥰3😁2🔥1👏1
#ህያብ


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_ኤርሚ

"አቤት ህያብ" አለኝ ዶክተሩ ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ካየኝ በኋላ

'ማስወረድ እፈልጋለሁ' አልኩት

"ምን" የሚል ድምፅ ሰምቼ ስዞር እናቴ ከኋላዬ ቆማለች።

"ምንድነው የምታወሪው እ... ማን ፈቅዶልሽ ነው የምታስወርጂው.... ምን ስልጣንስ ኖሮሽ ነው የእግዜርን ፍጡር የምትገይው......" ወደኔ የበለጠ እየተጠጋች የቁጣ ናዳ አወረደችብኝ። እናቴ በአካባቢው እያለች ከአንደበቴ ይህንን ቃል ማውጣት አልነበረብኝም።
.......
ከውርጃ ጋር ተያይዞ በጣም መጥፎ ትዝታ አለባት። ልጅ እያለሁ ትርሲት የምትባል የዘመዳችን ልጅ አብራን ትኖር ነበር። ታናሽም ታላቅም ስለሌለኝ እንደ እህቴ ነበር የማያት እሷም ሲበዛ ታቀብጠኝ ነበር። በትምህርቷ በጣም ጎበዝ ነበረች። ታዲያ ከጊዜ በኋላ ውጤቷ እያሽቆለቆለ መጣ። መምህሮቿ ቤታችን ድረስ መጥተው እናቴን አናገሯት እማዬ ደነገጠች..... ትርሱ ከሄደችበት ስትመለስ ቁጭ አድርጋ አወራቻት መከረቻት ግን ለውጥ አልነበረውም የባሰ ትምህርት ቤት እያለች ሌላ ቦታ እንደምትውል ተደረሰባት.... እናቴ ይህን ስትሰማ በጣም ተቆጣቻት።
......
የሆነኛው ቀን ላይ መልዕክተኛ መጥቶ ትርሲት ታማ ሆስፒታል መግባቷን ነገሩን እናቴ እየሮጠች ሄደች። ወደቤት ይዛ የተመለሰችው ግን አስከሬን ነበር።
.......
ትንሽ ካደኩ በኋላ እናቴን ጠይቄ እንደተረዳሁት ከሆነ ትርሲት ከአንድ የከተማችን ነጋዴ ጋር የፍቅር ግንኙነት ትጀምራለች። ሁሉ ነገሯን ትታ ነበር ክንፍ ያለችለት .... ግንኙነታቸው በሱ ጎትጓችነት ወደ አልጋ ላይ ጨዋታ ይሸጋገራል.... በዚህ መሀልም ትርሲት አረገዘች። ማርገዟን ስታውቅ ሁሉንም ነገር ዘርዝራ ለጓደኛዋ ከነገረቻት በኋላ ምክሯን ጠየቀቻት
"ስለሚወድሽ ያገባሻል እንዳረገዝሽለት ንገሪው" አለቻት።

በማግስቱ ወደ ፊት የሚኖራቸውን የደስታ ህይወት እያሰበች በፈገግታ የደመቀ ፊቷን ይዛ ወደ ነጋዴው ፍቅረኛዋ ጋ ሄደች። እንዳረገዘችለት ስትነግረው

" ከማናባሽ አርግዘሽ መጥተሽ ነው አረገዝኩልህ የምትይው" አላት።
ከሱ ውጪ ወንድ እንደማታውቅ ያውቃል ግን ሊሰማት አልፈለገም። ትርሲት ለሱ የሆነ ሰዓት ላይ ተጠቅሞባት እንደሚጥላት እቃ ነበረች።
አይንሽን ማዬት አልፈልግም ከነ ዲቃላሽ ገደል ግቢ ብሎ አባረራት..... ለሳምንታት ተስፋ ሳይቆርጡ እሷም ጓደኛዋም ለመኑት.... ጭራሽ አይኑን ወደ ጓደኛዋ ማዞር ጀመረ ነገሩ ሲገባቸው እሱን እርግፍ አድርገው ትተው ሌላ መፍትሄ መፈለግ ጀመሩ እናም ማስወረድ በሚለው ተስማሙ። የትርሲት ጓደኛ ቤተሰቦቿ ወደገጠሩ ስለሚርቁ ቤት ተከራይተውላት ነው ትምህርቷን የምትማረው.... እናም ለእቅዳቸው ተስማሚ የሷ ቤት ስለሆነ ትርሲት እማዬን ለፈተና ለማጥናት ጓደኛዬ ጋር ልደር ብላ አስፈቀደቻት። እማዬም ምናልባት አብረው ሲያጠኑ ውጤቷ ይሻሻላል ብላ ስላሰበች አልተቃወመቻትም።
.......
ጓደኛዋ ቤተሰቦቿ ካሉበት ገጠር ለውርጃ ይጠቀሙታል ያለችውን መድኃኒት ሰጠቻት እናም ግጥም አድርጋ ጠጣችው። ለትንሽ ጊዜ ሁሉም ሰላም ነበር ሌሊት ላይ ግን ከበድ ባለ ሁኔታ ደም ይፈሳት ጀመር። ልጁ እየወረደ ነው ብለው ስላሰቡ የሚሆነውን በዝምታ ጠበቁ..... ከሰአታት በኋላ ግን ትርሲት እየደከመች መጣች። ጓደኛዋ የአከራዮቿን ቤት አንኳኩታ እርዳታ ጠየቀች እናም ወደ ሆስፒታል ተወሰደች ግን አርፍደው ነበር። ትርሲት ብዙም ሳትቆይ አሸለበች ።

አይደለም እኔ ልጇ ማንም ላሶርድ ቢላት ኡ ኡ እንደምትል አላጣሁትም ግን.......

"እማዬ በዘመናዊ መንገድ እኮ ነው በሀኪም" አልኳት

"አይሆንም ብያለሁ አይሆንም..." ጮኸችብኝ.... ንግግራችንን ሲሰማ የነበረው ዶክተር ተነስቶ አጠገባችን መጣና አረጋግቶ ወንበር ላይ ካስቀመጠን በኋላ

"ህያብ ከማስወረድ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም ብለሽ ታስቢያለሽ" አለኝ።

"አዎ ዶክተር መማር እፈልጋለሁ በዛ ላይ የሰው መሳቂያ ነው የምሆነው.... ማንም ተደፍራ ወለደች የሚለኝ የለም...." ንግግሬን ሳግ አቋረጠኝ

"እርሶስ ወይዘሮ ወይንሸት ምን ይላሉ"

"እኔ ቆሜ እያለሁ ልጄን ለሞት አሳልፌ አልሰጣትም በፍፁም አይሆንም" እርግጠኝነት በተሞላበት መንፈስ ተናገረች።
......
"እኔም የእናንተን ሀሳብ ልስማ ብዬ እንጂ ፅንሱ ሶስት ወር አልፎታል በዛ ላይ ልጅ ነሽ ከማስወረዱ ብትወልጂው ይሻላል ለሱም ቢሆን እድሜሽ ገና ስለሆነ ያላቋረጠ የህክምና ድጋፍ ያስፈልግሻል......" ይሄን እና የመሳሰሉትን ሲያወራ እናቴ 'እህ' እያለች አንገቷን እየነቀነቀች ትሰማዋለች።

ትቻቸው በሀሳብ ነጎድኩ ከዛስ አልኩ ለራሴ...... ከዛስ ትምህርቴ ሊቀር..... የሰፈር ሰው መጠቋቆሚያ ልሆን...... ከዛስ እ...... የወደፊት እጣ ፋንታዬስ.... እዚሁ የተወለድኩበት ሀገር በናቴ እግር ተተክቼ ፓስቲ እና ጠላ ስሸጥ ልጄን ለማሳደግ ደፋ ቀና ስል በህሊናዬ ሳልኩ።
....
"አይሆንም" አልኩ ቃል አውጥቼ.... ያልኩት መልሶ አስደነገጠኝ

"ምኑ ነው የማይሆነው ሚጣዬ.... ዶክተር ያለውን ሰምተሻል አይደል እንደዛ እናደርጋ...." ዶክተር! ዶክተር ምንድነው ያለው?...... ምንም ይበል ምን አገባኝ። ዶክተር እኮ ህልሙ ይሁንም አይሁንም ዶክተር ሆኗል አይደል.... ደግሞ እሱ ምን አለበት በሰው ቁስል ላይ እንጨት መስደድ ለሱ ቀላል ነው.... "ውለጂው" አለ አይደል? መውለዴ የሚያሳጣኝ ነገር ግን ግድም አይሰጠው.... ይቺ የአስራ ሶስት አመት ልጅ ከምታስወርድ ትውለድ ሲል ይቺ የአስራ ሶስት አመቷ ህያብ ህልሟን ትቅበረው ማለቱ እንደሆነ አልገባውም።

''ወለድኩ ማለት ህልሜ ሁላ ይቀበራል" አልኩት የመጨረሻ እድሌን ልሞክር ብዬ

"አንቺ ከምትቀበሪ ህልምሽ ቢቀበር አይሻልም" አለችኝ እናቴ.... ምንም ሳልናገር ቢሮውን ለቅቄ ወጣሁና ወደቤት መንገድ ጀመርኩ እማዬ ከኋላዬ ደረሰችብኝ። ምንም ሳንነጋገር ጎን ለጎን ትንሽ ከሄድን በኋላ

"እስኪ ሚጣዬ ሆድሽን ሸፈን አድርጊው" ብላ የለበስኩትን ፎጣ ስባ ሆዴን አለበሰችው.....
..........
እና ሁሉም ነገር እንደዚህ ሊቀጥል ነው? አይሆንም! እናቴም እኔም አንገታችንን ከምንደፋ የሆነ ሀሳብ በውስጤ መጣልኝ። እንደማደርገው እርግጠኛ ሆንኩ.....

ይቀጥላል
👍577👎3🥰2
#ተአምራተ_ኬድሮን


#ክፍል_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///



እቤት ስትደርስ ሰዓቱ ገና ለአስራ ሁለት ሰዓት እሩብ ጉዳይ ነበር‹‹ሁለተኛ ሰዓት ሳላይ እና መንጋቱን ሳላረጋግጥ ንቅንቅ አልልም ..ቅዱስ ሚካኤል ነው ከመአት ያወጣኝ ፡፡››ብላ ስህተቷን ዳግመኛ ለለመድገም  ለራሷ ቃል ገባች፡፡ግን ደግሞ ያለማቋረጥ ስለእሱ ከማሰብ እራሷን ማቀብ አልቻለችም‹‹ይሄ ሰው የሆነ ነገር አድረጎኝ ቢሆንስ ?››ስትል አሰበችና በፍርሀት ራደች፡፡ደግሞ የደሎ መና ኑዋሪ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነች፡፡ምክንያቱም ከተማዋ በሁለት ቀበሌ ብቻ የተዋቀረች በመሆኗ  ኑዋሪዎቹ ቢያንስ በመልክ እርስ በርሱ ይተዋወቃሉ፡፡ ያንን ወንዝ ውስጥ በግማሽ እርቃን ሆኖ ያየችውን ሰው ግን ከዚህ በፊት የትም ቦታ አይታው እንደማታውቅ እርግጠኛ ነች፡፡ የደሎ ህዝብ እርስ በርስ ከመተዋወቁ የተነሳ ለምሳሌ የጉልት ነጋዴዎች በመደዳ አስር ሆነው ቢቀመጡ ምሳ ሰዓት ሲሆን አንዱ ይቀርና ዘጠኙ ምሳ ለመብላት ወደየቤታቸው ይሄዳሉ፡፡አንዱ የሁሉንም ደንበኛ   በታማኝነት ያስተናግዳል፤በታታሪነት ይሸጣል፤ የተቀበለውን ገንዘብ በተገቢው ቦታ ያስቀምጣል፡፡
ቀኑ ተገባዶ መሽቶ ወደ መኝታዋ ስትሄድ እንኳን  ሀሳቧ ያዶት ወንዝ ላይ  እንደተጣበቀ ነበር …ጀርባዋን የጥጥ ፍራሽ ላይ አሳርፋ በተለመደው ሰዓት ብትተኛም እንቅልፏ ሁሉ የተቆራረጠ ..ለሊቱ የረዘመና የተንቀራፈፈ ሆነባት፡፡ክፋቱ ደግሞ አያቷ በኢጣሊያንን ወረራ ለመፋለም አድዋ ዘምተው በድል ሲመለሱ ከጠላት ማርከው ለግላቸው ካስቀሩት አንዱ ብርቅዬ  የእጅ ሰዓት ነበር…ይህ ሰዓት ማሰሪያው ቢበላሽም ዋና ሰዓት ቆጣሪው ግን በትክክል ያለዝንፈት ይሰራል፡፡ይህን የዘመኑ ተአምራዊ ዕቃ አያትዬው ከሞቱ በኋላም ቤተሰቡ ግድግዳ ላይ አንጠልጥለው ይጠቀሙበታል…በሬዱም ማታ ሰዓቱን ከወላጆቾ ክፍል ወደራሷ ክፍል በማዘዋወር ከራስጌዋ ሰቅላው ስለነበር በየሆነ የጊዜ ክፍት አየተነሳች ሰዓቱን ትመለከት ነበር፡፡በወቅቱ ሰዓት ሚባል ተአምራዊ ማሽን በከተማዋ ብርቅ ነበር፡፡ምን አልባትም ይህ ሰዓት በግለሰብ ደረጃ በከተማውም ያለው ብቸኛው ቅርስ  ሳይሆን አይቀርም፡፡ያው በወቅቱ ማህበረሰቡ የጊዜ ልኬትን በተወሳሰበ ማሽን ሳይሆን ሲወርድ ሲዋረድ በመጣ የሰዓት አቆጣጠር ጥበብ ነበር በራስ መንገድ በመስፈር የሚገለገለው፡፡
በሬዱ ግን ዕድሜ ለጀግናው አያቴ እያለች በመሀል ከእንቅልፏ ተነስታ ሰዓቷን ታያለች…ገና 8፡20….መልሳ ለመተኛት ትሞክራለች..ብዙ ከመሰላት ቆይታ በኃላ ሰመመን ከመሰለ እንቅልፏ ትባንንና ብድግ ብላ ፋኖሷን ለኩሳ ሰዓቷን ታያለች 9፡35…‹‹ሰዓቱ ተሳስቶ ይሆን እንዴ?›› የሚል ስጋት በውስጧ ይሰነቀርና በቤታቸው ሽንቁር አጮልቃ ውጩን ትመለከታለች፡፡ ግማሿ ጨረቃ ሰማዮ አናት ላይ በስሱ ስትጓዝ ፤ ከዋክብቶች ደግሞ ሰፊው ሰማይ ላይ ተበትነው ሲደንሱ ታያለች… ወደምድር ስታይ ሁሉ ነገር ጨለማና በፀጥታ የታጠረ ይሆንባታል…ሰዓቱ እንዳልተበላሸ ውስጧን ታሳምንና መልሳ ትተኛለች..
ቆይታ ቆይታ ስትነቃ ምንም የተቀየረ ነገር አይኖረም….ከቤታቸው በአቅራቢ ካለው መስኪድ የመጀመሪያ አዛን  ትሰማለች…በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ የዶሮ ማራኪ ድምፅ እና የወፎች ጥዑም ዝማሬ ይናፍቃታል….ግን ምንም የሚሰማ ነገር የለም…መልሳ ለመተኛት ትሞክራለች‹‹ሰውዬው ምን አይነት አዚም ነው ያስነካኝ?›በራሷ ጥያቄ ውስጧ ራዳ..…ተኝታ ተኝታ ስትባንን የወፎች ብስራት ዜማ ሰማች… በርግጋ ከመኝታዋ ወረደችና ሰዓቷን ተመለከተች 11፡40 ይላል.. ከዛ በላይ ታግሳ መጠበቅ አልፈለገችም..ቀስ ብላ ተነሳችና ቤተሰቦቾን እንዳትቀሰቅስ እየሰጋች ሹክክ ብላ   ጄሪካኗንና ማዘያ ጨርቋን  ይዛ በቀስታ በራፉን ከፍታ ወጣች…

.ያስፈራል፤ከጭለማው ጋር አይኗን እስክታለማምድ ደቂቃዎች ወስደውባት ነበር….በጭራሮ ታጥሮ በጭራሮ በር የተዘጋውን የጊቢያችውን  አጥር መሸንጎሪያ አውጥታ ከፈተችና ወጣች… ግን መቀጠል አልቻለችም… ልቧ ለሁለት ተከፈለ..‹‹ሂጂ ችግር የለውም፡፡››እሯሷን ለማበረታታት ሞከረች፡፡
‹‹..አረ ተይ ሰው አግኝቶ ባይተናኮልሽ እንኳን አውሬስ ቢዘነጥልሽስ…?›ሌላ የፍራቻ ስብከት ከውስጧ በመመንጨት ይረብሻት ጀመር፡፡ ከግቢያችው መሀል ተጋድሞ የነበረው መቻል በጩኸት ያንቧርቀው ጀመር…አንድ ሀሳብ መጣላት፤ተመልሳ ወደ ጊቢ ገባችና ወደ እሱ ሄደች፡፡ቀስ ብላ በሹክሹክታ ልክ እንደልብ አውቃ ጎዳኛ መጮሁን ተወና እግሯ ስር ሽብልል ብሎ ተኛ፡፡
.‹‹አብረን እንሂድ ተነሳ…››አለችውና መንገዷን ይዛ ወደ መውጫው እርምጃዋን  ቀጠለች ..ተከተላት..::
አዎ አሁን ቀለል አላት‹‹…ቢያንስ ካንተ ጋር መሄድ ይሻላል……››ብላ ውሻዋን አስከትላ ጉዞዋን ቀጠለች...ወንዙ ጋር ስትደርስ ገና ጭለማው እንደመግፈፍ እያለ   ነበር፡፡መቻል ከኃላ ከኃላዋ ኩስ ኩስ እያለ ነው፡፡በዛፎቹ ላይ ያሉት ወፎች የለሊት ዝማሬያቸውን ያሰማሉ..እንደደረስች ጄሪካኗን አንከርፍፋ ለአስር የሚሆን ደቂቃ ፈዛ ወዲህና ወዲያ አይኖቾን በማንከራተት የሆነ ነገር ትፈልግ ነበር..፡፡

‹‹እንዴ ምንድነው የምፈልገው….?ጄሪካኑን ይዤያለሁ… የወንዙም ውሀ በእግሬ ላይ እያለፈ ወደ ፊት እየተመመ ነው..እና ለምን ጎንበስ ብዬ  አልቀዳም ..?ለምን በብርድ እንዘፈዘፋለሁ….?›› እያለች ከራሷ ጋር ሙግት በገጠመችበት ቅፅበት ውሻዋ ማንቧረቅ ጀመረ….. ግረ ገብቷት አይኖቾን ስታቁለጨልጭ ከወንዙ መሀል ብልቅ ብሎ ወጣ…፡፡
‹‹የፈጣሪ ያለህ.!!›› ጩኸቷን ለቀቀችው...ደግነቱ  የእሷ ጩኸት ከመቻል ጩኸት ስለማይበልጥ ተውጦ ቀረ…፡፡

"ዛሬም ደነገጥሽ?››
‹‹ምን አይነት ሰው ነህ…..?ቤትህ  ወንዙ ውስጥ ነው እንዴ?››በመገረም ጠየቀችው፡፡
ፈገግታ የተርከፈከፈበትን አንፀባራቂ ፊቱን ወደእሷ አቅጣጫ አዙሮ‹‹አዎ …ከፈለግሽ ነይ ልብስሽን አውልቂና ግቢ ….በዛውም ቤቴን አሳይሻለሁ››አላት፡፡

‹‹ቤትህን ባየው ደስ ይለኝ ነበር… ግን ዋና  አልችልም››አለችውና ለቀልድ ምላሽ ሰጠች፡፡
‹‹የደሎ ልጅ ሆነሽማ ዋና አልችልም ብትይ አላምንም…ደሎዎች እንኳን ሰዎቹ እንስሳቱም ዋናተኛ ናቸው፡፡››

‹‹ቢሆንም ይቅርብኝ ..ባይሆን ሌላ ጊዜ›› እለችና ጎንበስ ብላ ጄሪካኗን ወደ ውኃ ውስጥ ከተተቸው…መቻልም ድምፅን አጥፍቶ በሜትሮች ርቀት መሬት ላይ ለጥ ብሎ ሁለቱንም እየታዘበ ነው፡፡
‹‹እንግዲያው ቀረብሽ ››ብሎ መልሶ ወደ ውሀ ውስጥ እራሱን ደፈቀና ሙሉ በሙሉ በመስመጥ እራሱን ከእይታ ሰወረ…የሆነ ነገሯን ይዞ የሄደ ነው የመሰላት…፡፡
እንዳላት ልብሷን አወላልቃ ወንዙ ውስጥ መግባት እና አብራው መዋኘት በጣም አሰኝቷት ነበር..ግን ፈርታ ነው እምቢ ያለችው፤በዚህ ሰዓት እርቃኗን ወንዝ ውስጥ ከማታውቀው ሰው ጋር…‹‹ግን ምን ችግር አለው…?ባደረግኩት ኖሮ››ስትል ቁጭት ውስጥ ገባች…አንድን ነገር እኩል መፈለግ እና እኩል አለመፈለግ እንዴት ነው የሚቻለው፡፡በዚህ ደቂቃ በእሷ ላይ እየታየ ያለው ስሜት እንደዛ አይነት ነው...በሁለት ጫፍ ወደግራና ቀኝ በእኩል ኃይል መወጣጠር፡
👍1175😁4
#ትንግርት


#ክፍል_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

...ሁሴን ፊቱ የተቀመጠውን የውስኪ ብርጭቆ በማንሳት አንዴ ጠቀም አድርጎ ከተጎነጨለት በኃላ መልስ መስጠት ቀጠለ፡፡...

‹‹እርግጥ እኔ በእግዚአብሔር አምናለሁ፡፡ የእኔ እግዚአብሔር ግን በየትኛውም ሀይማኖት ውስጥ እስካሁን አላገኘሁትም፡፡ የእኔ እግዚአብሔር ፍፁም የተለየ ነው፡፡››!

«ለምሳሌ...?>>

‹‹ለምሳሌ ሁሉም ሀይማኖቶች ማለት በሚቻልበት ደረጃ በሲኦልና ገነት ያምናሉ፡፡ ይሄንን ፅንሰ ሀሳብ የእኔ አዕምሮ ደግሞ ፈፅሞ ሊቀበለው አይችልም፡፡እግዚአብሔር ፈጥሮናል ብለን የምናስብ ከሆነ እኛ በዚህች ምድር ላይ ለምንፈፅመው ሥህተት ኃላፊነቱን ብቻችንን መውሰድ ያለብን አይመስለኝም፡፡
የሥህተታችን ዋና ምንጩ አፈጣጠራችን (የተሠራንበት ንጥረ ነገር) ነው ብዬ አምናለሁ....እኛ አሁን የሆነውን የሆነው በእግዚአብሔር ፍቃድና ምርጫ ነው፡፡ ስለዚህ አፈጣጠራችን ለስህተቶች ተጋላጭ እንደሚያደርገን ገና ከመፈጠራችን በፊት ዲዛይኑን የሠራው እግዚአብሔር በደምብ ያውቃል ብዬ አስባለሁ፡፡ ይሄ እውነት ከሆነ ደግሞ የተሳሳተውን ለማጥቃት ሲኦልን መገንባት ለምን አስፈለገ? አለዚያማ እግዚአብሔር የእነ ሂትለር ግልባጭ ነው ማለት ይሆናል፡፡ ሂትለር አይሁዶችን አይሁድ ስለሆኑ ብቻ እየሠበሠበ ጨፈጨፋቸው፣ ቆራረጣቸው፣ አቃጠላቸው፡የሚገርመው ግን እውነታውን ማንም እንደሚገነዘበው አንድም ሰው በፍቃዱ አይሁዳዊ ወይም ጀርመናዊ ሆኖ መወለድ አይችልም፡፡

ሌላው አንድ ምሳሌ ልጨምርልህ ወሲብን ሁሉም ሀይማኖቶች በደቦ ያወግዙታል፤ከጥንት ባህላዊ ሀይማኖቶች በስተቀር ማለቴ ነው፡፡ እስቲ ተመልከት እያንዳንዳችን እኮ የወሲብ ውጤቶች ነን፡፡ አንዲት ሴት አሥር ዓመት ገዳም ሲሞላት ጡቶቿ እንዲያጎጠጉጡላት፣ብልቷ ላይ ፀጉር እንዲበቅልላት፣ የወር አበባዋ ምንጭ እንዲፈልቅላት በየእለቱ በናፍቆትና በጉጉት ታልማለች፡፡ ለምን ይመስልሃል ?በቶሎ ደርሳ እንደ እናቷና እንደ ታላላቅ እህቶቿ አንድ ጎረምሳ አፍቅራ ወሲብ የሚባለውን ተዓምር ለማየት ነው... ወንድዬውም እንደዛው፡፡

የምንበላው ቆንጆ ለመሆን፣ለማደግ፣ብሎም ለመኖር ነው፤የምንማረው በህብረተሠብ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኝት፣ የተሻለ ተመራጭ ሠው ለመሆን ነው፤የዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ የመጨረሻ ግብ ግን በተቃራኒ ፆታ ተመራጭ ሆኖ ፣በወሲብ እርካታ ተደስቶ፣ የዝርያችንን ቀጣይነት አረጋግጦ ፣ በህይወት ውስጥ የድርሻን ለመወጣት ነው... እና ይሄ የህይወት አንኳር ቅመም የሆነው ወሲብ ሀይማኖት መሆን ሲገባው እንዴት ሀጥያት ነው ተብሎ ይፈረጃል?››

‹‹ወዴት..…? ወዴት ...?የትኛውም ሀይማኖት እኮ ወሲብን ስርአት ይበጅለት ይላል እንጂ አያወግዝም፡፡ሚስት አግብተህ ከሚስትህ ጋር እንደፈለክ ወሲብ ማድረግ የሚከለክልህ ሀይማኖት ያለ አይመስለኝም››

‹‹እሱ ነው ማይገባኝ፡፡ድሮ አንድ ወጣት 17 እና 18 ዓመት ሲሞላው አባትዬው ሁለት ጥማድ መሬት ከሁለት በሬ ጋር ይሸልመውና የ13 ወይም የ14 ዓመት እንጭጭ ልጃገረድ ፈልጎ በመዳር ከጣጣው ይገላግለው ነበር፡፡ ወደዚህ ዘመን ነገሩን አምጥተን ስንመለከተው
ግን አንድ ወጣት ሚስት ለማግባት ከማሰቡ በፊት ቀድሞ ኑሮውን በራሱ ተጣጥሮ ማሸነፍ አለበት፡፡ ምክንያቱም አይደለም በከተማ በገጠር እንኳን አባት ከእሱ ተርፎት ለልጁ ቆርሶ የሚሰጠው መሬት ስለማይኖር በቀላሉ ጎጆ መቀለስ የማይታሰብበት ዘመን ላይ ነው ያለነው፡፡ ስለዚህ ለማግባት የግድ ከእሱ አልፎ ለሚስቱ የሚበቃ የገቢ ምንጭ ሊኖረው ያስፈልጋል፡፡ያንን እስኪያሟላ ዕድሜው ቢያንስ በቀላሉ ከ3ዐ በላይ ይሆናል፡፡ይሄ ልጅ እንግዲህ ለአቅመ ወሲብ ከደረሰ ስንት ዓመት አለፈው ብለህ ስታሰላ 14 እና 15 ዓመት ይሆናል ፡፡ ታዲያ ይሄን ሁሉ ዓመት በዘመኑ እንዲህ የተበተኑትን ቆነጃጅት እየተመለከተና እየጎመዠ እስከ ጋብቻ ታቅቦ ለመቆየት የሚያስችል ጥንካሬ በውስጡ የሚኖረው ይመስልሀል? ተፈጥሮስ ትፈቅድለታለች

‹‹እንዴ !!ፍቅረኛ እኮ መያዝ ይችላል፡፡››

‹‹ይችላል... ግን እኮ ብዙዎቹ ሀይማኖቶች ከጋብቻ በፊት ወሲብ ክልክል ነው ይላሉ ፡፡››

‹‹ባክህ አንተ የምትለው አታጣም .. በቃ.. በቃ አሁን ጨዋታ ቀይር፤ሙሽሮቹ እየገቡ ነው፡፡››በማለት የጫወታውን አቅጣጫ ቀየረው፡፡

የሠሎሞንን ንግግር ተከትሎ ሁሴን ፊቱን ወደ
ጓሮ በር አሽከረከረ፡፡ ፀጉረ ረጅም፣ባጭሩ የከረከመች፣ ዊግ የከመረች፣ሱሪ ያረገች፣ቀሚስ የለበሰች፣ ሊፒስቲክ የተለቀለቀች ፣ቅንድቧን የመለጠች፣ ቀጭን፣ወፍራም፤ከየዓይነቱ ለናሙና ተመርጠው የቀረቡ ይመስል በሠልፍ ተንጋግተው ገቡ…ከአስር ይበልጣሉ፤ከመሀከላቸው አንዷ ትንግርት ነች፡፡

የቁመቷ መመዘዝና የመልኳ ቅላት ከሌሎቹ ጎልታ እንድትታይ አድርጓታል፡፡ ትንግርት የሁሴን ቋሚ ደንበኛ ነች፡፡ ከሁለት ዓመት በላይ እውቂያ አላቸው፡፡ ስታሰኘው እቤቱ ይዟት በመሄድ ሲኖረው ይከፍላታል... ከሌለውም ደግሞ ትዘለዋለች፡፡ ትመቸዋለች... ይመቻታል፡፡

‹‹ሥጋዋ ነው እንጂ ነፍሷ ንፁህ ነው፡፡›› ይላል፡፡ ጠንካራ ንግግሯና የአስተሳሰብ ብስለቷ ዘወትር ያስደምመዋል፡፡ በወሲብ ችሎታዋ የዛለ ስጋውንም ሆነ የተጨናነቀች ነፍሱን እኩል ስለምታረግብለት እስከአሁን እንዳይለያት አስሮ ያቆየው ተጨማሪ ሠንሠለት ሆኖበታል... እየተውረገረገች የተቀመጡበት ድረስ መጥታ ሁለቱንም ሠላም አለቻቸው ፡፡

ሠሎሞን በተቀመጠበት አንጋጦ እያየ‹‹ዛሬ ደግሞ ይበልጥ አምሮብሻል፡፡›› ሲል አስተያየቱን ሠነዘረ፡፡

‹‹የእናንተ የባለትዳሮች አስተያየት እኮ ከወንደላጤው በላይ ውስጥ ድረስ ዘልቆ ልብን ይሰረስራል፡፡››

<እንዴት?>>

‹‹እያንዳንዷ ፊት ለፊታችሁ የተከሠተችን ሴት የምታወዳድሩት እቤታችሁ ውስጥ ከምትገኘው ሚስታችሁ ጋር ስለሆነ በጥልቀት ነው የምትመረምሩት፡፡ ወንደላጤው ደግሞ በአእምሮው ውስጥ ከቀበራት ሴት ጋር ነው የሚያወዳድረው፤ በአእምሮው ውስጥ የሳላትን ደግሞ እንደአስፈላጊነቱ ሊያስተካክላት ስለሚችል መመርመሩ ላይ ብዙም ጊዜውን አያባክንም፤ገረፍ ገረፍ አርጎ ውሳኔውን ይወስናል... ወይ ይከተላታል ካልሆነም አልፏት ይጓዛል፤እናንተ ግን ውይ! ..ደም ትመጣላችሁ…ለማንኛውም መጣሁ፡፡›› ብላቸው እንደአመጣጧ እየተውረገረገች ጥላቸው ሄደች፡፡

‹‹ይህቺ ልጅን ግን ደህንነቶች አንተን ለመሠለል እዚህ ያስቀመጧት ሠላይ ትመስለኛለች፡፡››

‹‹ደህንነቶች ለምንድነው እኔን የሚሠልሉት?›› ሁሴን ጠይም ፊቱን ይበልጥ በማጥቆር ሠፊ ግንባሩን አጨማዶ ጠየቀው፡፡

‹‹ምን አውቃለሁ፤እዛ ጋዜጣህ ላይ ፖለቲካ ነገር ፅፈህ ጀርባህን ሊያጠኑህ ይሆናላ፡፡››

‹‹ሠውዬ እኔ የጥበብ አምድ አዘጋጅ እንጂ የፖለቲካ አምድ አዘጋጅ አይደለሁም፡፡››

‹‹እሱን እንኳን ተወው፡፡ ፖለቲካ አምድ ላይ እንደውም ደረቅ ትችትና የሚሻክር ተቃውሞ ነው የሚፃፈው…ማለት ሁሉ ነገር በግልፅ ነው የሚቀመጠው፡፡ ይሄ ደግሞ የደህንነቶችን ሥራ ያቀልላቸዋል፡፡ የፀሀፊው እምነትና አመለካከት ምን እንደሚመስልና የየትኛው ፖለቲካ ድርጅት ደጋፊ ወይም አባል እንደሆን ? ለመለየት ብር ከስክሶ ሠላይ መመደብ አያስፈልጋቸውም፡፡ በቃ አንዱ የፖለቲካ ኤክስፐርታቸው ቢሮው ቁጭ ብሎ ይተነትንላቸዋል፡፡ ያንተ አምድ ግን በቅኔያዊ አሽሙር የተጀቦነ፣በሰምና ወርቅ የሚተነተን ፍቺ ያለው ሚስጥራው መርዝ ነው፡፡በዛች ባንተ ደንበኛ ስም የሚታተሙ አጫጭር ልብ ወለዶችና ግጥሞች እንኳን ብንመለከት ለዚህ ማስረጃ ይሆናል፡፡››

ሁሴን ተንገሸገሸ‹‹ተወኝ ባክህ ስለ እሷ አታንሳብኝ፡፡››
👍11215👏3🔥2🤔2
#ቤርሙዳ_ዘ_ካሳንቺስ


#ክፍል_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ስልኳን ዘግታ ወደጳውሎስ ተመለሰችና ቁጭ አለች‹‹ወደቢሾፍቱ መቼ መንቀሳቀስ ትችላለህ?››
‹‹በቃ… ነገም ቢሆን መሄድ እችላለሁ…እናቴን መሰናበት ካልሆነ ሌላ የሚያቆየኝ ጉዳይ የለኝም፡፡››

‹‹ጥሩ …ነገ ጠዋት ሁሉ ነገር ዝግጁ አድርጎ የሆነ ሰው ይደውልልሀል ፡፡ መኪና ይይዛል…እሱም አብሮህ ነው እዛ የሚቀመጠው…የሚያስፈልግህን ነገር ሁሉ የሚያመቻቸው እሱ ነው….አንተ መቶ ፐርሰንት ትኩረትህን ስራህ ላይ ብቻ እንድታደርግ ነው የምፈልገው፡፡ ማንኛውም የምትፈልገው ነገር ሲኖር ለእሱ መንገር ብቻ ነው የሚጠበቅብህ..እሱ ያሟላልሀል፡፡ ….እንደቅድሚያ ክፍያ 50 ሺ ብር ጠዋት በእሱ በኩል እልክልሀለው፡፡የተወሰነውን ቀንሰህ ለእናትህ መስጠትና ምርቃት ማግኘት ትችላለህ፡፡እዛ ያለው ሙሉ ወጪህ የሚሸፈነው በእኔ ነው፡፡››

‹‹ከሁለት ወር ቀድሜ ከጨረስኩስ..?››

‹‹ተጫማሪ ቦነስ ይኖርሀል ማለት ነው፡፡››

‹‹ተስማምቼያለሁ.. አሁን መሄድ እችላለሁ…?፡፡››

‹‹አዎ …ምስጢራዊነቱ  ላይ  ግን ተጠንቀቅ…  ህይወትህን  ሊያሳጣህ ከዛም አልፎ…ጦሱም ለእናትህ ሊተርፍ ይችላል›› ብላ ጨብጣ ሸኘችውና..ጋርደኑን ለቃ ወደቤት ገባች፡፡ቀጥታ ፎቅ ላይ ወደሚገኘው የተንጣለለ መኝታ ክፍሏ ነው ያመራችው፡፡ በጣም ደስ  ብሏታል፡፡ይህ  ጉዳይ  ሀሳብ  ሆኗት  ለወራት ሲያስጨንቃት ነበር ፤ እንዲህ መስመር በመያዙ ፈነጠዘች..ይህ መፅሀፍ ለእሷ የኒኩሊየር ቦንብን ያህል  ዋጋ  አለው፡፡እናም  አሁን  የተደሰተችው  መደሰት  ልክ አንድ የአሸባሪ ቡድን መሪ የኒኩሊየር አረር በእጁ ሲገባ የሚሰማውን አይነት ስሜት ነው የተሰማት፡፡
ቀጥታ ወደ ሻወር ቤት ሄደችና ፈጣን  የሆነ  ሻወር  ወሰደች፡፡  ወደቁም  ሳጥኗ ሄደችና ፓንቷንና ጡት ማሳያዣዋን ብቻ  ለበሰችና  ጋዋኗን  ደርባበት  አልጋዋ ጠርዝ ላይ በመቀመጥ ፋሲልን መጠበቅ ጀመረች..አሁን ለዚህ በውስጧ ለሚፈሰው ደስታ ቺርስ ብላ የምትጋብዘው አንድ ነገር አስፈልጓታል፡፡

ፋሲል  ስለእቅዱ  እያሰላሰለ  ተንደርድሮ  ቤቷ  ሲደርስ  ሳሎኑ  ባዶ  ነው፡፡ ተንደርድሮ ወደፎቅ ወጣ፡፡መኝታ ቤት  ገባ፡፡በጋዋን  ግማሽ  እርቃኗን  ሸፍና ግማሹን አጋልጣ  አልጋው  ጠርዝ    ላይ  ቁጭ  ብላለች፡፡ገና  አልፎ  ወደ ውስጥ እንደገባ ነው ከጭኗ የተነሳው ነፀብራቅ አይኖቹ ላይ የተመሰገው፡፡
ሁኔታዋን ሲያይ ፈራት…የመጣበትን እቅድ ማሳካት እንደማይችል ውስጡ ጠረጠረ.. እሷ ለወሬ ሳይሆን ለወሲብ ዝግጁ ሆና ነበር የጠበቀችው ፡፡ከረሜላ እንዲገዛለት እናትዬውን በልምምጥ እንደሚጠይቅ ህጻን ልጅ ለንቦጩን ጥሎ‹‹አንድ ነገር ላስቸግርሽ ነበር››አላት፡፡
‹‹የእኔ ማር ያንተ ወሬ ይደርሳል….እንደምታየው አሁን ተርቤያለሁ..ቅድሚያ መቅደም ያለበትን ነገር ብናስቀድም..››

‹‹ችግር የለውም..ግን ያልኩሽን እሺ እንደምትይኝ ቃል ግቢልኝ›› ለነገሩ ብዙም ትኩረት ባለመስጠት‹‹ቃል ገብቼልሀለሁ››አለችው..፡፡

ግንባሩን በማነቃነቅ እሱም መስማማቱን አረጋገጠላት…
‹‹ግን ቁጥር 5 ነው የምፈልገው››አለችው፡፡

ገባው…ሁለቱ የሚግባቡበት ኮድ ነው ፡፡12 ዓይነት በመሰቃየት የምትረካበት ዘዴዎች አሉ፡፡እያንዳንዱን ዘዴ በቁጥር ስያሜያቸው ለይታ አስጠንታዋለች.. አሳውቃዋለች፡፡
እጇን ይዞ ከተቀመጠችበት የአልጋው ጠርዝ አነሳት፡የለበሰችውን ጋዋን በቀላሉ ካላዯ ላይ አነሳና  እዛው  ወለል  ላይ  ተዋት፡፡፡ከፊት  ለፊቱ  ግድግዳ  የላይኛው ኮርነር ላይ ግድግዳው ውስጥ ከተቀበረ ብረት አንድ  ላይ  በተያያዘ  ጠንካራ ሰንሰለት እጆቿን ለየብቻ አሰራቸው፡፡በተመሳሳይ መልኩ ከወለሉ ጋር አንድ ላይ ተጣብቆ ከተሰራ ሰንሰለት ጋር እግሮቾን አለያይቶ አሰራቸው፡፡በአጠቃላይ ስትታይ ወዲህና ወዲያ ተበለቃቅጣ የ x ምልክት ሰራች፡፡ከወደ ጥግ የሚገኝ ኮመዲኖውን ከፈተና አብረቅራቂ  ሳንጃ  እና የተወለወለ  የፈረስ መግረፊያ አለንጋ አወጣ፡፡ ቀረባትና ሳንጃውን በቅርብ ርቀት ከሚገኘው ደረቅ ወንበር ላይ አስቀመጠው፡፡አለንጋውን አስተካከለና ባለ በሌለ ኃይሉ መቀመጫዋን ለመጠጣት..ደገማት..በጀርባዋ ዞረ..ፍጥነቱም ኃይሉም እየጨመረ ሲመጣ ፊቷ እየተቀያየረ..ድምፅ እያወጣች መጣች፡፡
ይሄንን የወሲብ አይነት ልክ እንደጥሩ ነገር የወረሰችው በምትሰራው የማሳጅ ስራዋ ደንበኛዋ ከሆነ ከአመታት በፊት የሀገሪቱ ትልቅ ባለስልጣን ከነበረ አንድ ሰው ነው፡፡ይሄ ባለስልጣን ለሶስት አመት ያህል የምትሰራበት ማሳጅ ቤት ደንበኛ ሆኖ በወር ሁለት ቀን ይጎበኛት ነበር፡፡

በሚመጣበት ጊዜ በሁለት ጋርዶች ተከቦ አንድ ሻንጣ የማሰቃያ ብረታ ብረቶችንና መግረፊያ  አለንጋዎችን በመያዝ ነበር፡፡ከዛ በሚሰቀጥጥ አይነት ሁኔታ  እንድታሰቃየው፤ እንድትገርፈውና አንዳንዴም በስለት ቆዳውን እንድትሰነጣጥቀው ያስገድዳት ነበር..ማስገደዱ ግን በማሳፈራራት ሳይሆን በገንዘብ ኃይል የሚከወን ነበር፡፡ለአገልግሎቷ በአንድ ቀን ሀያና ሰላሳ ሺ ብር ነበር የሚከፍላት፡፡ከዛም በላይ አሁን የምትኖርበትን ባለአንድ ፎቅ የተንጣለለ ቪላ ቤት የሰራችበትን 250 ካሬ መሬት በነፃ ከማዘጋጃ ያሰጣት

እሱ ነው፡፡በዛ የተነሳ በሚፈልገው መጠን መጨረሻ ጠብታ ድረስ በስቃዩ ደስታ አግኝቶ እንዲረካ የተቻላትን ጥረት ታደርግ ነበር..በሂደት  ግን ለራሷ  ቆይ ልሞክረው ብላ በመጠኑ ስትሞክረው .ከዛ ትንሽ ስትጨምርበት….ሙሉ በሙሉ የባህሪው ተጋሪ ሆነች፡፡ልክ እንደ ሀሺሽ ሱስ ተፀናወታት፡፡እሱ በመሰቃየቱ ብቻ የሚረካ ግለሰብ ነበር.እሷ ደግሞ በማሰቃየትም. በመሰቃየትም የምትረካ ሴት ሆና እርፍ አለች..ከመምህሩ  ደቀመዝሙሩ  ይባል  የለ….እንግዲህ  ይሄ  ሰው  በአሁኑ ጊዜ በፖለቲካ ልዩነት ምክንያት ስልጣኑንም ለቆ ከሀገርም  ስለተሰደደ  ሙሉ በሙሉ ግንኙነታቸው ቢቋረጥም ውርሱን ግን አጠንክራ አስቀጥላለች፡፡ከእሱ ጋር ያላት ግንኙነት ከተቋረጠ በኋላ ሁለት ወንዶችን በማደን  የስሜቷ አገልጋይ እንዲሆኑ አሰልጥና ልትጠቀምባቸው ሞክራ ነበር ግን ብዙም ሳይዘልቅ ከሽፎባታል… በመጨረሻ በሆነ  አጋጣሚ  ፋሲልን  አገኘችና  ተሳካላት.ይሄው አመት አለፋቸው፡
ፋሲል ስራውን ቀጥሏል፡፡

‹‹ኸረ የእኔ ጌታ ይቅር በለኝ..››

‹‹ይቅርታ አይገባሽም››

‹‹ተው እንጂ አትጨክንብኝ››

‹‹ከጥፋትሽ መማር አለብሽ..ሀጥያትሽ እንዲሰረይልሽ መቀጣት ይገባሻል››

‹‹እሺ የእኔ ፍቅር…እንዳልክ››

የተቆራረጠና በጣር የተሞላው ምልልስ  በግርፊያው  እንደታጀበ ቀጥሏል..ግርፊያው ከመብዛቱ የተነሳ ክንዶቹ እየዛሉ መጡበት፡፡
‹‹እሺ የእኔ ጌታ ሁለተኛ አልመለስበትም…አይለመደኝም››

‹‹ሁል ጊዜ እንዲሁ ነሽ..አትታረሚም››

‹‹በቃኝ አልኩ እኮ..   አይለመደኝም..   ተቃጠልኩልህ…   ሞትኩልህ… ተንገበገብኩልህ›› በዚህ ጊዜ አለንጋውን ወደ ወለል ወረወረና ሳንጃውን አነሳ..በደንብ ተጠጋት.. ሳንጃውን በደረቷ   አሻግሮ   በሁለት   ጡቶቾ   መካከል ሰቅስቆ አስገባው
‹‹ከዚህ ከፍ ያለ ቅጣት ነው ሚያስፈልግሽ››

‹‹ኸረ ይቅር በለኝ የእኔ ጌታ››

ሳንጃውን አጠነከረ …በፍራቻ ተርበተበተች፡፡ወደ ታች ገፋው የለበሰችው የጡት ማስያዣ ማንገቻን ተራ በተራ ሸርክቶ በተነው....የጡት ማስያዣ ከገላዋ ተፋቶ ወደ ወለሉ ወደቀ፡፡መቃተቷን ቀጥላለች..በወጥመድ የተያዘች አይጥ መስላለች፡፡
👍778🤔8🔥1
#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


በፀሎት በእንባዋ እና ሜካፕ ቅልቅል የተበላሸውን ፊቷን በሳሙና ታጠበችና አፀዳችው….መልሶ ሜካፕ መጠቀም ሳያስፈልጋት ቀጥታ ወደሳሎን ሄደች፡፡ከላይ ከአንደኛ ፎቅ እስቴሩን ተጠቅማ ወደታች ስትወርድ በመጀመሪያ አይኗ የገቡት እናትና አባቷ ነበሩ… ጎን ለጎን ተጣብቀውና እጅ ለእጅ ተቆላልፈው…በየመቀመጫው እየተዞዞሩ እንግዶቹን ያዋራሉ፡፡‹‹እንኳን ሰላም መጣችሁ›› እያሉ የውሸት የተጠና ሳቅ ይስቃሉ፡፡ከአስር ደቂቃ በፊት እንደዛ በፀያፍ ቃላት ሲጠዛጠዙ ላያቸው ሰው አሁን በእንደዚህ አይነት ቅርበት መጣበቅ ይችላል ብሎ ማንም ሊያስብ አይችልም፡፡

‹‹ሰላም ተስፋዬ እና ሰላሞን ቦጋለ እንኳን የእናንተን ገፀ ባህሪ ቢሰጣቸው በዚህ ልክ አስመስለው መጫወት መቻላቸውን በጣም እጠራጠራለሁ፡፡››እያለች ወደታች ወርዳ መድረኩ ላይ ወደተዘጋጀላት የክብር ቦታ ሄዳ ተቀመጠች፡፡ወዲያው እሷን ብለው የመጡ የሰፈርና የዩኒቨርሲቲ ጓደኞቾ ዙሪያዋን ከበቧት..እሷም ወላጆቾን እንደአርአያ ወስዳ የውስጧን ብስጭትና ንዴት በሆዷ ቀብራ አንድ ልደቷ እየተከበራላት እንዳለ ደስተኛ ቀበጥ የሞጃ ልጅ በፈንጠዝያና በፌሽታ ልደቷን ማክበሩ ላይ ትኩረቷን አደረገች….፡፡

ከመቀመጫዋ ተነሳችና ከእናቷ ጋር ደነሰች…ከዛ ከአባቷም ጋር ደነሰች…እናም በሁለቱ መሀከል ሆና ለሶስት ሆነው እንዲደነስ አደረገች….ይሄ እንቅስቃሴያቸው እያንዳንዱ ዳንሳቸውና የእርስ በርስ መተቃቀፋቸው በፕሮፌሽናል ቪዲዬ ማን እየተቀረፀና ፎቶም እየተነሳ መሆኑን ታውቃለች….ለዛም ነው እንደዛ እያደረገች ያለችው‹‹ልጄ እስከዛሬ ከነበረው ልደትሽ ሁሉ ይሄ ልዩ ነው…ይሄው ሀያ አንድ አመት ሙሉ ያንቺን ልደት ሳከብር አንድ ቀን አብሬሽ እንድደንስ ጋብዘሺን አታውቂም ነበር….ዛሬ ግን…››ለሶስት ሆነው እጅ ለእጅ ተያይዘው በመደነስ ላይ ሳሉ ነበር አባቷ ስሜታዊ ሆኖ የተናገረው፡፡

እናትዬውም ወዲያው ነበር የራሷን ሀሳብ ያስቀመጠችው‹‹አባትሽ እውነቱን ነው….እኔም ብሆን ከልጄ ጋር የመደነሱን እድል ሳገኝ ይሄ የመጀመሪያ ቀኔ ነው…በጣም ደስ ብሎኛል፡፡››

‹‹እርስ በርሳችሁስ?››ስትል ሁለቱንም ያስደነገጠ ጥያቄ ጠየቀቻችው፡፡

‹‹ማለ…ት?››እናትዬው በተለጠጠ ንግግር ጠየቀቻት፡፡

‹‹አንቺና አባዬ እንዲህ እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ ከደነሳችሁ ምን ያህል አመት ሆናችሁ?››ጥያቄውን አፍታታ ደገመችው፡፡

‹‹እኔ እንጃ ልጄ እኔ አላስታውሰውም…..ምን አልባት አንቺ ከመወለድሽ በፊት ይመስለኛል››አባትዬው መለሰ፡፡

‹‹አያችሁ..ልጅ ወላጆቹ የሚያወሩትን ሳይሆን የሚያደርጉትን ነው ኮርጆ ደግሞ የሚያደርገው..እናንተ በዚህ መልክ ስትደንሱ አይቼ ስለማላውቅ ነው እኔም ላደርገው ያልቻልኩት…ፍቅርን በተመለከተ ጥሩ አርአያዎቼ አልነበራችሁም ማለት ነው..አዎ እውነቱ እንደዛ መሰለኝ፡፡››

‹‹አይ ያ እውነት አይደለም፡፡ልጄ እኛ በጣም እኮ ነው የምንወድሽ፡፡››

‹‹እሱ አይደለም ጥያቄው..እናንተስ እርስ በርስ እንዴት ናችሁ…..?ከመሀከላችሁ ማንኛችሁ ናችሁ የታመማችሁት….?ምናችሁን ነው የሚያማችሁ….?እንዴት ነው ይሄን ሁሉ አመታት እርስ በርስ መጠላላት የማይደክማችሁ…..?እንዴት አንዳችሁ እንኳን አትሸነፉም….?ለማንኛውም እኔ ማውራቱ ደከመኝ …ይብቃን…..ከአሁን ወዲህ ልደት ብዬ ስለማልደግስ የዛሬው የመጨረሻችን ነው፡፡››

‹‹የመጨረሻ ማለት?››አሁንም ልጃቸሁን እንደአምስት አመት ህጻን የሚያዩት አባቷ ኮስተር ብለው ጠየቁ፡፡

‹‹አባዬ አትኮሳተር ፡፡አሁን ሀያ አንድ አመት ሞላኝ…እራሴን ችዬ ከቤት መውጪያ ጊዜዬ ከመድረሱም በላይ እያለፈብኝ ነው…በእናነተ ላይ መንጠልጠልና መደገፍ ይበቃኛል…ከነገ ጀምሮ ጋርዶችህ እንዲከተሉኝ አልፈልግም….በሹፌርም አልንቀሳቀስም…..በአጠቃላይ እንደምርኮኛ ወፍ ለዘመናት ካስቀመጥከኝ ጎጆ በሩን ሰብሬ ወጣላሁ ..ክንፌን በሰፊው ዘርግቼ በሰፊው ሰማይ ላይ ባሻኝ አቅጣጫ በራለሁ..አንተም ልታስቆመኝ ያለህ ኃይል በሙሉ በቂ አይሆንም፡፡››.

ይሄ ንግግር በሁለቱም ወላጆች ላይ መብረቃዊ ድንጋጤ ነው ያስከተለው‹‹ልጄ እንዲህ አይነት ቀልድ ከመቼ ወዲህ ነው መቃላለድ የጀመርነው..?ይሄ እቤት ዘመንሽን ሁሉ የምትኖሪበት ያንቺ የእድሜ ልክ ቤተመንግስት ነው…እዚሁ አግብተሸ እዚሁ ወልደሽ እዚሁ ነው የምታረጂው..ይሄን ምን ጊዜም ከአእምሮሽ እንዳታወጪው፡፡››

‹‹አባዬ… እናንተም መቼም ቢሆን ይህቺን ቀን ከአእምሮችሁ አታውጧት….››

‹‹እሺ ልጄ አሁን ለእንዲህ አይነት ጭቅጭቅ ጊዜው አይደለም… በድጋሚ መልካም ልደት..››

‹‹አመሰግናለው ..››ብላ

ሁለቱንም በየተራ ጉንጫቸውን ሳመችና ልርገፍ እያለ የሚታናነቃትን እንባዋን እንደምንም ከትራ ወደመቀመጫዋ ተመሰችና ከጓደኞቾ ጋር ተቀላቀለች፡፡፡

የልደት ዝግጅቱ ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ የጀመረ ሲሆን እሰከአራት ሰዓት ያለው ዝግጅት ለሁሉም የሚሆን ሰከን ያለ ሙዚቃ ያለበት የምግብና የመጠት መስተንግዶ ጨምሮ… የተረጋጋ የእርስ በርስ ጫወታ… የኬክ ቆረሳና.. የሻማ ማጥፋት ስርአት …የስጦታ ዝግጅት የተደረገበትና የተለመደ አይነት ነበር…ከአራት ሰዓት በኃላ ግን ጠና ጠና ያሉት ሰዎች አባትና እናቷንም ጨምሮ ግዙፍንና የተንጣለለውን ሳሎን ለወጣቶቹ ለቀው በመሰናበት ሄዱ፡፡የዝግጅቱ አጠቃላይ ሁኔታ ተቀየረ..ሙዚቃዎቹ የፈጠኑና የሚያስጨፍሩ ሆኑ፤ መጠጡ የጠነከረና አስካሪ እየሆነ ሄደ….ይሄም ሆኖ ግን በፀሎትን የሚጠብቁ ሁለት ጋርዶች የሳሎንን የግራና ቀኝ በራፍ ይዘው በተጠንቀቅ እንደቆሙ ነው፡፡እሷም በአይነ ቁራኛ እያየቻቸው ነው…በየሆነ ደቂቃ ልዩነት መጠጥ እንዲወስዱላቸው ለአስተናጋጆቹ መልዕክት ማስተላፏን ፈፅሞ አትረሳም…..መጀመሪያ ስራ ላይ ስለሆኑ መጠጥ እንደማይጠጡ በመናገር መልሰው ነበር..በኃላ ግን እራሷ ሄዳ ‹‹በልደቴ ቀንማ ቢያንስ አንድ ጠርሙስ መጠጣት አለባችሁ ››ብላ እንዲቀበል አስገደደቻቸውና  ተቀበሏት…በአንድ ብቻ ግን አላቆሙም፤ አራትና አምስት መደጋገም ቻሉ..፡፡ሰዓቱ እኩለ ለሊት አልፎ ሰባት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ሰክሮ ሚለፋደደው በዛ….በፀሎት ግን ከመጀመሪያም ጀምሮ እየጠጣች አልነበረም ….ዛሬ የምትጠጣበት ቀን እንዳልሆነ ከመጀመሪያውኑ ነው የወሰነችው…እንደምንም ጋርዶቹን በጥንቃቄ እያየች…እየተሹለከለከች የፎቁን ደረጃ ተያያዘችውና ወደላይ ወደመኝታ ቤቷ አመራች…ከፍታ ገባች እና መልሳ ከውስጥ ቆለፈችው፡፡

የለበሰችውን ቀሚስ በፍጥነት አወለቀችና ቅድም አዘጋጅታ የነበረውን ጅንስ ሱሪ ለበሰች…፡፡ወርቃማ አርቴፊሻል ፀጉሯን አወለቀችና ጥቁር ሆኖ ከኃላ ረጅም ከፊት አጭር ሆኖ ከፊል ግንባሯን ሚሸፍን ሌላ ፀጉር አጠለቀችና ከላይ ኮፍያ ያለው ጥቁር ጃኬት ደረበችበት፡፡ አይኗ ላይ ጥቁር መነፅር ሰካችና መስኮቱን ከፈተች…፡፡

…መለስተኛ የቆዳ ሻንጣዋን ከአልጋዋ ላይ አነሳችና በጀርባዋ አንጠለጠለችው… አዎ በጀርባ የሚገኘውን የአደጋ ጊዜ መውጫ ተጠቅማ ወደ ምድር መውረድ ጀመረች፡፡ይሄንን መወጣጫ ልጅ እያለች ጀምሮ በጣም ትፈራዋለች፡፡ መጀመሪያ ቀኝ እግሯን አስቀደመች
👍8513🤔2🥰1
#ወይ_አጋጣሚ(አጭር ልብወለድ)


#ክፍል_ሁለት


#ድርስት_በዘሪሁን
==========================
ቢሆንም ቅንዝሬ ያው ቅንዝር ነውና ጆሮው የተደፈነ ነው፤የእኔ እና የእሷን ምክንያት አያዳምጥም ፡፡ስለዚህ እመክረው እመክረውና…ከዛም ደግሞ እለምነው እለምነው እና በቃ ከአቅሜ በላይ ሲሆን  እንደነርኳችሁ በወር አንዴ በደሞዝ ሰሞን ወደ አብረቅራቂ መብራት ወደሚንቦገባግባቸው የለሊት ቤቶች ጐራ እላለሁ ፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን ልቤ ለሀይሚ እንዳላዘነ ነው፡፡ዛሬ ግን እፎይ ልገላገል ነው ፡፡ሀይሚ እቤት ለመምጣት ከስድስት አታካች ወራቶች ጭቅጭቅ በኋላ ተስማምታለች፡፡ከቀኑ 8 ሰዓት ነው የምትመጣው፡፡እኔ ግን ከእንቅልፍ የባነንኩት ከለሊቱ 8 ሰዓት ነው፡፡ለዝግጅት፡፡እውነቴን ነው እኮ ፡፡ገና እቤት ማዘጋጀት አለ፣ዕቃ ማጣጠብ አለ፣አልጋ በስርአት ማንጠፍ አለ፣ለፍቅራችን ማጀቢያ ሙዚቃ መምረጥ አለ፣ደግሞ እኔም እንድደፍራት እሷም እንድትደፈርልኝ የሚያግዝ መጠጥ ማዘጋጀት አለ፣አረ ስንቱ….፡፡

ደግሞ አይገርማችሁም ዛሬ ሀይሚ ቤት ልትመጣ ትናንትና ቂጣሟን ማግኘቴ….፡፡ ማግኘቴ ብቻ ሳይሆን እቤቷ ድረስ መከተሌ..ከዛም አልፎ ስልክ ቁጥሯን መቀበሌ..፡፡አሁን ልደውልላት እንዴ….? የሚል ሀሳብ መጣብኝ ፡፡መልሼ ሀሳቤን ውድቅ አደረግኩት ::ለሀይሚ ያለኝን ታማኝነት ዝቅ ማድረግ ነው:: አይደለም መደወል …ቢቻል በምናቤ ተንጠልጥሎ አልወርድ ያለኝን የቂጧን ምስል አሽቀንጥሬ መጣል ብችል ደስ ይለኝ ነበር፡፡እንደቀጠሯችን ምንም ሳታረፍድ ከቀኑ 9 ሰዓት ሀይሚ መጣች..ያው አንድ ሰዓት ዘገየች ማለት አረፈደች ተብሎ መደምደም የለባትም ብዬ ነው፡፡ አለባበሷን ልግለጽላችሁ፣ቡትስ ጫማ፣ጥብቅ ያለ ጅንስ ሱሪ፣በሱሪው ላይ ቁርጭምጭሚቷ ጋር የሚጠጋ ቀሚስ፣በቀሚሱ ውስጥ ደግሞ ሱሪዋ በቀበቶ የተጠፈረ መሆኑን በሚታየው የቀበቶ ቅርፅ ማወቅ ይቻላል፣ከላይ ደግሞ ግብዳ ሹራብ ደርባለች፡፡
ጉንጯን እያገላበጥኩ እየሳምኩ ቢሆንም አይኖቼን ግን ሰማዩ ላይ አንጋጥጬ እያንከራተትኩ ነው፡፡ሀሞቴ ፍስስ ነው ያለው፡፡አሁን እሺ ብላ እንድናደርግ ፍቃዱን ብትሰጠኝ ..ይሄን ጫማዋን ፈትቼ እስካወልቅ አንድ ሰዓት፣ሱሪዋን እስካወልቅ ሌላ አንድ ሰዓት፣ምን አልባት ከሱሪዋ ስር ታይት፣ከታይቱ ስር ደግሞ ሁለት ወይም ሶስት ፓንት ታጥቃ ሊሆን ይችላል..? ታዲያ መሽቶ ነጋ ማለት አይደል?፡፡

ወደ ቤት ዘልቃ ቁጭ አለች፡፡ቁጭ አባባሏ እራሱ ሲያበሳጭ፡፡ ከጓዲያ ወጥቶ ማጅራቷን አንቆ የሚውጣት ዳይኖሰር ያለ ይመስል በራፉ ጥግ የሚገኝ ኩርሲ ላይ ተቀመጠች፡፡ፈርጥጣ ለመውጣት እንዲያመቻት ይመስለኛል፡፡ ደግሞ እሷ ብቻ ሳትሆን እኔም አበሳጫለሁ ፤ ምን አለበት ከመምጣቷ በፊት እቤቴ ያሉትን መቀመጫቸው ሁሉ ሰብስቤ ጓዲያ አስገብቼ ቢሆን ኖሮ ምርጫ ስታጣ አልጋ ላይ መቀመጧ አይቀርም ነበር፡፡

‹‹ሀይሚ ..ምነው በራፍ ላይ….. ?አልጋው አይሻልሽም…?››

‹‹አይ መጣለሁ  ብዬህ እንዳልቀር ነው እንጂ …እሄዳለሁ፡፡››

‹‹ወዴት?››

‹‹ወደቤት ነዋ…እናቴ ስራ አዛኝ ነበር ….ተደብቄ ነው የመጣሁት››ብላኝ እርፍ፡፡

ይታያችሁ ሰው አሁን ይህቺን ያፈቅራል...?ከለሊቱ 8 ሰዓት እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ፍዳዬን ስበላ ቆይቼ እሷ ግን ገና መጥታ ሳትጨርስ ልሄድ ነው ትላለች፡፡ቀኑን ሙሉ እሷን እያሰበ ሲወጣጠር የዋለውን እንትኔ ወዲያው ልፍስፍስ ብሎ ሲሸበለል ይታወቀኛል፡፡ችላ አልኳት እና ወደ ጓዲያ ገብቼ የሰራሁትን ምግብ በማምጣት ጠረጴዛ ላይ ደረደርኩት፡፡ ወይኑንም አወጣሁ..አሁን የምግብ ጠረጰዛው አልጋውን ተጠግቶ ስለሚገኝ ምርጫ የላትም መጥታ አልጋው ላይ ከጐኔ መቀመጧ አይቀርም ፡፡

‹‹ሀይሚ ነይ ምሳ እንብላ ፣እርቦኛል..እስከአሁን እኮ አንቺን ስጠብቅ አልበላሁም፡፡››

‹‹እኔ እኮ በልቼያለሁ፡፡››አቤት ወሽመጥ ስትቆርጥ፡፡

‹‹ባክሽ አታበሳጪኝ..በስንት ጣጣ  መጥተሸ ደግሞ..?›› ተኮሳተርኩ፡፡ እንደመደንገጥ አለችና መጣች፡፡ እንዴት መጣች አትሉኝም…? ኩርሲዋን ይዛ በመምጣት ከአልጋው ራቅ ብላ ተቀመጠች፡፡ ምርጫ አልነበረኝም፤ እጇን አስታጠብኳት ፤ወይኑን ስቀዳ‹‹ለእኔ እንዳትቀዳልኝ››አለችኝ እየተንዘረዘረች፡፡ መርዝ ልቀዳላት የተዘጋጀው አስመሰለችው፡፡

‹‹አንድ ብርጭቆ ብቻ››ተለማመጥኳት፡፡
‹‹አንድ መለኪያም አልጠጣም..እንድበላ ከፈለክ በውሃ ቀይርልኝ…›› ለወራት ተጨንቆ የቀየሰው የጦርነት እስትራቴጂ ፍርክስክሱ እንደወጣበት የጦር ጄኔራል ሞራሌ ድቅቅ አለበኝ፡፡ለንቦጬን ጣልኩ …ያለችውን አደርግኩ፡፡

እየተጐራረስን በፀጥታ በልተን ጨረስን፡፡እኔ የእሷንም ፋንታ የምጠጣ ይመስል እንደውሃ እጋተው ጀመር ፡፡ እንደጨረስን የተበላበትን ዕቃ አነሳሳሁ..እጇን አስታጠብኳት እና እኔም ታጥቤ  ወደ ቦታዬ ተመለስኩ፡፡

ልክ ምሳዋን ለመብላት የመጣች ይመስል…‹‹ልሂድ በቃ፡፡›› አለችኝ፡፡

‹‹ቆይ ማውራት አለብን፡፡››

‹‹ምንድነው የምናወራው?››

‹‹ስለፍቅራችን ነዋ፡፡ ››

እንደመደንገጥ ብላ‹‹ፍቅራችን ምን ሆነ ?››አለችኝ፡፡

‹‹እስከአሁን ምንም አልሆነ …ካላወራንበት እና መፍትሄ ካላበጀንለት ግን መሆኑ አይቀርም.››ወይኑን በደረቁ እየለጋሁት ስለሆነ በድፍረት የመናገር ወኔዬ ሙሉ ነው፡፡

‹‹እሺ ፈጠን በልና እናውራበት››

‹‹ታፈቅሪኛለሽ?››

ግራ በመጋባት‹‹ምን ማለት ነው?››

‹‹ታፈቅሪኛለሽ ወይ?››ደግሜ ጠየቅኳት፡፡  

‹‹በጣም አፈቅርሀለሁ፡፡››
  ‹‹ካፈቀርሺኝ …ዛሬ ፍቅር እንድንሰራ እፈልጋለሁ፡፡››

‹‹ፍቅር እየሰራን አይደል እንዴ?››

‹‹እንደ እሱ አይደለም..ልብስሽን አወላልቀሽ..እኔም ልብሴን አውልቄ… እዚህ አልጋ ላይ ወጥተን ምናምን ማለቴ ነው… በጣም አምሮኛል…ስንት ወር ነው የምሰቃየው…?››ብሶቴን ተረተርኩት፡፡

‹‹እሱማ አይሆንም፡፡››

‹‹ለምን አይሆንም?››

‹‹አፈቅርሀለሁ… ግን ጊዜው አሁን አይደለም…ገና 18 ዓመት እኮ አልሞላኝም፡፡ በዛ ላይ የሃይእስኩል ትምህርቴንም አልጨረስኩም፡፡››

‹‹ስንት ዓመትሽ ነው?››

‹‹17 ዓመት ከ11 ወር…››

‹‹እና ታዲያ ሰው ለሚወደው እንኳን አንድ ወር ይቅርና አንድ ዓመትስ ቢያጭበረብር ምን አለበት?››

‹‹እንደ እናቴ መሆን አልፈልግም፡፡››

‹‹እንዴት እንደ እናትሽ?››

‹‹እሷም 10ኛ ክፍል እያለች ነው እኔን ያረገዘችው፡፡በዛ የተነሳ ትምህርቷን አቋርጣ ብዙ ስቃይ ተሰቃይታለች፡፡ ብዙ ብዙ መከራ ካሳለፍን በኋላ ነው በቅርቡ ህይወታችን የተስተካከለው፡፡››

‹‹እኔ እኮ ብታረግዢም አፈቅርሻለሁ..ማለቴ አገባሻለሁ፡፡››

‹‹አባቴም እሷን እንደዛ ነበር የሚላት…፡፡የእውነት እንዳረገዘች ስትነግረው ግን የራስሽ ጉዳይ ነበር ያላት፡፡››

‹‹እሺ በቃ በኮንዶም እንጠቀም..ህይወት ትረስት፣ሴንሴሽን፣ሜምበርስ ኦንሊ… የፈለግሽው አይነት አለ፡፡››

‹‹እንዴ ዲኬት ነው እንዴ የምትሰራው…? ይሄ ሁሉ ኮንደም ምን ልታደርግ ሰበሰብከው…?››ያላሰብኩትን መስቀለኛ ጥያቄ ጠየቀችኝ፡፡

‹‹ባክሽ አንድ ዲኬት የሚሰራ ጓደኛዬ ነው አምጥቶ ለማንኛውም እያለ ቤቴ የሚያስቀምጠው፡፡››

‹‹ጥሩ…. ግን ድንግል ነኝ… ድንግልናዬን ደግሞ በኮንደም አላስወስደውም፡፡››

‹‹እኔ እኮ ድንግልናውን አልፈልገውም..፡፡››
‹‹……እና አውልቄ ላስቀምጠውና ተጠቅመህ ከጨረስክ በኃላ መልሼ ላጥልቀው?››ንግግሯ ከማበሳጨትም አልፎ አሳቀኝ፡፡

‹‹እና ምንድነው መፍትሄው?››

‹‹ምታፈቅርኝ ከሆነ ጠብቀኝ?››
‹‹እሱማ አፈቅርሻለሁ፡፡››
👍865👏2👎1
#የጣት_ቁስል


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

ቄስ አሻግሬ

ሔደውልኝ ይሆን? ዛሬ ደግሞ ማርያም ናት፡፡ ቅዳሴ ይኖርባቸው ይሆን? ለነገሩ ቅዳሴ እንኳን ከሰዓት ነው፡፡ ቀኑ ዕሮብ አይደለም ምናልባት ጠዋት ሄደውልኝ ይሆናል፡፡ ለማንኛውም እኔም ማህበር ስላለኝ እዛው ቤተ ክርስቲያን አገኛቸዋለሁ፡፡ ከማህበር ስንወጣ እጠይቃቸዋለሁ፡፡ ብሎ ከሰው ጋር ባይይሆንም ከራሱ ሃሳብ ጋር የተናገረው ነበር፡፡ አቶ ለማ ሽፈራው፡፡

ከቅዳሴ የመውጫ ሰዓት ስለደረሰ ጋቢውን ለባብሶ ተነሳ፡፡ ወደ ጉራንባ ማርያም ቤተክርስቲያን ጉዞውን ቀጠለ፡፡

ቄስ አሻግሬ አማላጅነቱ ሙሉ በሙሉ ተሳክቷል ባይባልም በተወሰነ መልኩ ተስፋ የሚሰጥ መልስ በማግኘታቸው ተደስተዋል፡፡ ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ከሰዓት ቅዳሴ ስለነበረባቸው ብዙም ሳይቆዩ ተነስተው ወደ ጉራንባ ማርያም ቤተክርስቲያን ጉዞዋቸውን አቀኑ፡፡

አቶ ለማ ከቅዳሴ ሲወጡ ደረሰ፡፡ ቄስ አሻግሬን ለማናገር ከማህበር በኋላ ሊመሽ ስለሚችል ዛቲ እንደቀመሱ ማናገር እንዳለበት አሰበ፡፡ ከዛቲ እንደተበተኑ ካህናት ከቅዳሴ ወጥተው ወደ ተቀመጡበት ቦታ ሔደ፡፡

"ሰላም ዋሉ ቄስ አሻግሬ” ፡፡

"እግዚአብሔር ይመስገን ሰላም ዋልህ?፡፡ ለማ" ብለው አጠፌታ መልስ ሰጥተውት መስቀል አሳለሙት፡፡ "ዛሬ ማርያም መጥተህ ኖሯል፡፡ መሃበር አለህ ለካስ" አሉ፡፡

"አዎ፤ ማህበር አለኝ"፡፡ ብሎ በቀጥታ ለማናገር ወደ ፈለገው ጉዳይ ገባ፡፡ "እንዴው እዛ ጉዳይ ጋር ሔደውልኝ ነበር ?"፡፡

"አዎ፤ ሔጀ ነበር፡፡ ያው! መቼም በአንዴ እሽ እንደማይባል አንተም ታውቃለህ፡፡ ለማንኛውም ለዛሬ አስራ አምስት ቀን ቀጥረውኛል፡፡ ቁርጡ ያኔ ይታወቃል" ::

"ቀጠሮ መስጠታቸውም ጥሩ ተስፋ ነው፡፡ እና እርሶንም በጣም አመሰግናለሁ"፡፡ ብሎ የማህበር ሰዓት ስለደረሰባቸው ወደየ ማህበራቸው ገቡ፡፡

አቶ ለማ ከማህበሩ እንደወጣ ወደ ቤቱ እየሔደ ፤ እንዴው እሽ ባለኝ፡፡ ልጅቷ ጎበዝ ተማሪ እና ጨዋ እንደሆነች መቼም አገር ነው የሚያወራላት፡፡ ፀባይዋም ቢሆን ምንም አይወጣላትም ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ እንዴው በተሳካልኝ፡፡ ሰዎች ስለእድላዊት መልካምነት ሲያወሩ የሰማውን ሁሉ በሃሳቡ እየደጋገመ እና እያወራ ሳይታወቀው እቤቱ ደረሰ፡፡

"ምነው ዛሬ ደግሞ አመሸህ? ማህበሩ ቶሎ አላለቀም እንዴ?" አለ አበበ ላባቱ፡፡

"አዎ፤ ዛሬ ደግሞ ቶሎ ወደ ማህበር አልገቡም ነበር፡፡ ማህበረተኛውም የት እንደ ሄደ እንጃ ፤ጠላውም አላልቅ ብሎን እኔም ይመሽብኛል ብየነው ፤ ሳያልቅ ትቸው ነው የመጣሁት"፡፡

ከዛቲ መልስ ቄስ አሻግሬንም አግኝቻቸው ነበር፡፡ እቄስ መልካሙ ጋር እንደ ሔዱልኝ እና የድጋሜ ቀጠሮውም ለዛሬ አስራ አምስት ቀን እንደቀጠሯቸው ነገሩኝ" አለው፡፡

አበበ ለእድላዊት አማላጅ እንደላከለት ሲነግረው በጣም ወደር የሌለው ደስታ ተሰማው፡፡ ለማግባት የሚያስፈልገውን ነገር ማሟላት እንዳለበት በመወሰን የጀመረውን የቤት ስራ ለመጨረስ እየተጣደፈ ነው፡፡

እድላዊት ግን እሽ ትበለውም አትበለውም ባያውቅም ማድረግ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ባለበት ሰዓት በህሊናው አንድ ሃሳብ ያቃጭልበታል ?

ተመስገን

ሊነጋጋ ሲል የወሰደው እንቅልፍ ተጫጭኖት ቶሎ አልተነሳም፡፡ ለትምህርት ከሚነሳበት ሰዓት አርፍዶ ነው የተነሳው፡፡ የእድላዊት ባል ማግባት እና ከትምህርት መቅረት እውነት ሆኖ ቀረ ማለት ነው?፡፡ እውነት ባይሆንማ ኖሮ ሳትቀሰቅሰኝ ባልቀረች ነበር፡፡ ከራሱ ጋር እያወራ ከመኝታው ተነሳ፡፡ ሽንት ቤት ተፀዳድቶ ተመለሰ፡፡

እናቱን ከቤት ሲወጡ እበር ላይ አገኛቸው፡፡ እንደማይተዋወቅ ሰው የእግዚአብሔር ሰላምታ ሳይለዋወጡ ተላለፉ፡፡ የቤተሰቦቹ ድርጊት እና እርህራሔ የሌለው ውሳኔ ያስከፋው ተመስገን ለማነጋገር አይደለም የሚጨክን አንጀት እና አቅም ቢኖረው ቤተሰቦቹን በደበደባቸው ነበር፡፡

ወደ እድላዊት መኝታ ቤት አመራ፡፡ የቤቱ በር ከውስጥ የተዘጋ መስሎ ገርበብ ብሏል፡፡ እስካሁን ያልተነሳችው አሟት ቢሆን ነው፡፡ የቤቱን በር አንኳኳው፡፡ መልስ የሚሰጥ አላገኘም፡፡ ደጋግሞ በሩን ተመለከተ፡፡ ከነጋ የተከፈተ አይመስልም፡፡
ደግሞ ለማንኳኳት ሰውነቱን ከነከነው፡፡ ውስጡ ፍራት ፍራት ተሰማው፡፡ እጆቹም ተንቀጠቀጡ፡፡ የሚሆነው ሁሉ ጠፋበት፡፡ ከውስጥ አልተዘጋ ይሆን እንዴ? ተጠራጠረ፡፡ በሩን ማንኳኳቱን ትቶ የሞት ሞቱን ገፋው፡፡ መዝጊያው ከውስጥ ምንም የያዘው ነገር ባለመኖሩ ተከፈተ፡፡ በፍርሃት ወደ ውስጥ ገባ፡፡

ከአልጋ በስተቀር እድላዊት አይደለችም ፤ የእድላዊት ልብስ እንኳን አላገኘም ነበር፡፡ የህሊና ፀሎት እንደሚያደርስ ሰው ቆሞ የስልክ እንጨት መሰለ፡፡ ደቂቃዎች አልፈው ከወሰደው የድንጋጤ ሰመመን ባነነ፡፡ በቀጥታ ወደ እናት አባቱ ቤት ሄደ፡፡ እድላዊትን የት ሄደች ? ብሎ እናቱን ጠየቀ፡፡

ወ/ሮ አሰገደች የሚናገሩት ፣ የሚያነሱት ፣ የሚቧጥጡት አጡ፡፡ የት ሔደች? የለችም መኝታዋ ላይ ፤ እንደፎከረችው አደረገችው ማለት ነው፡፡ ወይ ጉዴ! እያሉ ከተመስገን መልስ ሳይጠብቁ ኡኡታቸውን አቀለጡት፡፡

የአካባቢው ሰውና ጎረቤቱ ምን ደረሰባቸው? ምን አጋጥሟቸው ይሆን?፡፡ እየተሯሯጡ ግቢው ሰው በሰው አጥለቀለቁት፡፡ታዲያ የሰው መዓት ቢሰበሰብ እና እሪ እየተባለ ቢጮህም እድላዊት ልትገኝ አልቻለችም፡፡ ኡኡታ
ሰምተው ከመጡት ሰዎች መካከል ወ/ሮ ስንዱ "የት ትሔዳለች ፤ ከዚህ በፊት ከቤት ወጥታ አታውቅም፡፡

ወደ ዘመዶቿ ሔዳ ይሆናል፡፡ ሰው ልኮ ማጠያየቅ ነው" አሉ፡፡

ወ/ሮ አሰገደችን ለማረጋጋት ቢሞክሩም ወ/ሮ አሰገደች ግን የሚረጋጉ አይደለም፤ ጨርቃቸውን ጥለው የሚያብዱ ነበር የሚመስሉት፡፡

ቄስ መልካሙ በድንጋጤ የተነሳ የሚጮኸውን ጩኸት የራሳቸው ችግር አይደለም፤ ለተመለከታቸው ሰው ከነጭራሹም ጩኸቱን የሰሙት አይመስልም ነበር፡፡

ጎረቤት የሆኑት አቶ ማን ችሎት ማን ያዝልሃል፡፡ ቄስ መልካሙን ለማነጋገር እና የተፈጠረውን ለመጠየቅ ቢሞክሩም ቄስ መልካሙ አይናቸውን ከማቁለጭለጭ ውጭ መልስ የሚባል ለመመለስ አይደለም ከነጭራሹም ለመናገር አቅቷቸው ነበር፡፡ ተመስገን ከእናት አባቱ የተሻለ ቢሆንም ሰው የሚጠይቀውን ጥያቄ ግን እሱም መመለስ አልቻለም፡፡

የተሰባሰቡት ሰዎች ሁሉ የሚያደርጉት ጠፋቸው፡፡ ከመካከላቸው አንድ ሰው መኮንን ሃይሌ የሚባል ተነሳ

"አሁን ሁላችንም አብሮ ማጃበሩን እና ማልቀሱ ዋጋ ያለው አይመስለኝም፡፡ እነሱን አረጋግተን መላ ብንፈልግ የሚሻል ይመስለኛል፡፡ ብሎ ሃሳብ ሰነዘረ፡፡ የተሰበሰበው ሰው በሃሳቡ ተስማምቶ ወሮ አሰገደችንና ባለቤታቸውን አረጋግተው እድላዊትን ፍለጋ በየ አቅጣጫው ሁሉም ሰው ተበታተነ፡፡

እድላዊት ግን በዘመዶቿ ቤት አይደለም በዱር በገደሉም ልትገኝ አልቻለችም፡፡ ከጠፋችበት ቀን አንስቶ አየናት፡፡ በዚህ አልፋለች የሚል አይደለም የበላት ጅብ እንኳን ሊጮህ አልቻለም፡፡

ቄስ መልካሙ በልጃቸው መጥፋት ጥልቅ ሃዘን ተሰማቸው፡፡ እድላዊት ትሙት ትኑር ሳያውቁ "አይ! አንተ ሰማይ እና ምድርን የፈጠርህ ጌታ እንደዚህ በቁሜ እንዳዋረደችኝ እና እንዳሰቃየችኝ በቁሟ የሚያዋርድ ይስጣት፡፡ የፈጠሯትን ልጅ አምርረው ረገሟት፡፡
👍736👏3
#የድንግሊቷ_አፍቃሪዎች


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
================

አላዛር አስራሁለተኛ ክፍል ተማሪና ነጋዴ እያለ ነው፡፡ በቀኑ በድካም የዛለ ሰውነቱን ለማሳረፍ ወደአልጋው የሚሄድበት ሰዓት ነው፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት  ሆኗል፡፡ቢሆንም ግን ከመተኛቱ በፊት የእለቱን ሂሳብ ቆጥሮና ወጪና ገቢውን መዝግቦ ማጠናቀቅ አለበት..ይሄ ሁል ጊዜ ወደአልጋው ከመሄዱ በፊት  መስራት ያለበት የግዴታ  ስራው ነው..ግን መዝግቦ ከመጨረሱ በፊት ስልኩ ጠራ፡፡የማያውቀው ቁጥር ቢሆንም ከስራ ጋር የተገናኘ ይሆናል በሚል ግምት አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ›

‹‹ሄሎ …አላዛርን ፈልጌ ነበር››ሳግ የተናነቀው የሴት ድምፅ ነው፡፡ግራ ገባው…፡፡በዛ ሰዓት እያለቀሰች እሱ ጋር የምትደውል  ሴት ማን ነች..ለመገመት አንኳን አልቻለም፡፡

‹‹አዎ አላዛር ነኝ፡፡ ማን ልበል?››

‹‹በዚህ ምሽት ስለደወልኩልህ ይቅርታ፡፡አስካለ እባላለሁ፡፡››

አስካለ የሚባል ስም ያላት ሴት ቢያስብ ሊመጣለት አልቻለም፡‹‹ይቅርታ አስካለ… አላወቅኩሽም፡፡››

‹‹አታውቀኝም..የአባትህ  ባለቤት ነኝ፡፡ ›

‹‹የአባትህ ባለቤት?››

‹‹አዎ ››

ሊገባው አልቻለም፡፡በመጀመሪያ ስለአባቱ ምንም ነገር መስማት አይፈልግም፡፡.ከዛም አልፎ አባቱ ባለቤት እንዳለው አሁን ገና መስማቱ ነው፡፡ከሁሉም በላይ ደግሞ ይህቺ የአባትህ ባለቤት ነኝ የምትል ሴት ለምን እንደደወለችለት መገመት አለመቻሉ ነው፡፡

‹‹እና በሰላም ነው?››

‹‹እኔ እንጃ፣አባት ምን ጠጥተው እንደመጡ አልውቅም…. እራሳቸውን ስተው                         አረፋ እየደፈቁ ነው፡፡እኔ ለአካባቢውም ለሀገሩም እንግዳ ነኝ፡፡ምን እንደማደርጋቸው አላወቅኩም፡፡ እጄ ላይ እንዳይሞቱ ፈርቼለሁ፡፡እባክህ አንድ ነገር አድርግ››አለችው፡፡

‹‹ለመሆኑ ቁጥሬን እንዴት አገኘሽው?››

‹‹ከአባትህ ማስታወሻ ደብተር ላይ ነው ፡፡ልጄ አላዛር ተብሎ ተመዝግቧል፡፡ ከዛ ላይ ነው ያገኘሁት፡፡››

ግርም አለው…አንደኛ አባቱ አላዛር የሚባል ልጅ እንዳለው የሚያውቅ አይመስለውም ነበር…ቢያውቅ እንኳን በቁም ነገር የእሱን ስልክ ቁጥር በማፈላለግ  በማሳታወሻው መዝግቦ ያስቀምጣል የሚል ቅንጣት ጥርጠሬ እንኳን አልነበረውም፡፡

‹‹እሺ ምን አልከኝ…?በፈጣሪ..ቢያንስ ለእኔ ስትል እርዳኝ፡፡›› ልስልስ እና እንስፍስፍ በሆነ የድምፅ ቃና ተማጸነችው፡፡
አረፋ እየደፈቁ ነው ከተባሉት አባቱ በላይ በሲቃ የምትንሰቀሰቀው የማያውቃት እንጀራ እናቱ  አሳዘነችው፡፡ ‹‹እሺ በቃ መጣሁ….እቤቱ ከጠፋኝ ደውልልሻለው… ወጥተሸ ትቀበይኛለሽ፡፡››

‹‹እሺ አመሰግናለው..እባክህ ቶሎ በል፡፡››

ስልኩን ዘጋና ጃኬት ደርቦ ከመሳቢያ ውስጥ ብር አንስቶ ወደኪሱ ጨምሮ ወጣ….መጀመሪያ ጓደኞቹ  ጋር ደወለ፡፡

‹‹አሌክስ ተኝተሀል እንዴ?››
በሻከረና በተዳከመ ድምፅ‹‹አዎ!! ምነው በሰላም ነው?››ሲል መለሰለት፡፡

‹የሆነ ችግር አጋጥሞኛል…አንድ ቦታ አብረኸኝ እንድትሄድ ነበር..፡፡››

አለማየሁ ከመኝታ ተነስቶ  ልብሱን እየለበሰ‹‹ምነው በሰላም?››ሲል ጠየቀው፡፡

‹‹ፍጠን …ስትመጣ ነግርሀለው…››ብሎ ስልኩን ዘጋና የሚያውቀው ባለ ላዳ ጋር ደወለ..፡፡ላዳው መጥቶ ውስጥ ገብቶ ሲጠብቅ አለማየሁ ሰሎሜን አስከትሎ መጣ፡፡

‹‹እንዴ !!አንተን  ና አልኩህ እንጂ እሷን ይዘህ ና ብየሀለው?››
‹‹ምንድነው ችግርችሁ? የሴት ጉዳይ ነው እንዴ…? ልመለስላችሁ?››አለች ሰሎሜ… በኩርፊያ፡፡
‹‹አረ አይደለም..በዚህ ለሊት  በመንገላታትሽ አሳዝነሺኝ ነው››አላት፡፡
‹‹እንደዛ ከሆነ እሱም ጓደኛህ እኔም ጓደኛህ…..እሱ ካስፈለገህ እኔም አስፈልግሀለው ማለት ነው፡፡››

‹‹እሺ ግቡ››

ከኃላ ከፍተው ገቡ..ላዳዋ ልትንቀሳቀስ ስትል አለማየሁ‹‹ቆይ ሁሴንም ደውዬለት መጣሁ ብሏል.. ትንሽ እንጠብቀው››
አላዛር በሰማው ነገር ተበሳጨ‹‹እንዴ ማን ንገረው አለህ…?አሁን ሳምንቱን ሙሉ እንዳላጠና አዘናጋችሁኝ እያለ ሲነጫነች ነው የሚከርመው፡፡››

‹‹ባንነገርው ደግሞ‹እኔስ ጓደኛችሁ አይደለሁም ወይ?› ብሎ ሳምንት ያኮርፈናል››ሲል አለማየሁ መለሰለት፡፡

ሰሎሜ ‹‹እሱ እኮ….››ብላ ሀሳቧን ልትናገር ስትል ሁሴን ደርሶ የኃላዋን የላዳ በራፍ ከፍቶ ተቀላቀላቸው….ላዳዋ ተንቀሳቀሰች፡፡

እነዚህ አራት ጓደኛሞች ከአንድ መሀፀን እንደወጡ መንታ ልጆች ናቸው፡፡በክፉውም ቀን ሆነ በደጉ አብረው ናቸው፡፡
የአራቱ ጓደኝነት መነሻ ምክንያቱ አንድ ሰፈር ውስጥ ተፋፍጎ ከተሰራ ቤት ስለተወለዱ ብቻ አልነበረም፡፡የአራቱም እናቶች  ቡና የሚጠራሩ የአንድ ክለብ ተጫዋች አይነት ስለሆኑ ነበር…አንዳችው ቤት ቡና ተፈልቶ ሁሉም እናቶች ሲጠሩ ሁሉም የየራሳቸውን ልጆች ይዘው ይመጣሉ…ከዛ ሁሉም  ከእናታቸው  እቅፍ ውስጥ እየሾለኩ እርስ በርስ የመጫወት  ሙከራ ያደርጋሉ…ያ ደግሞ በተለየ መልኩ ከጮርቃነታችው ጀምሮ በተለየ ሁኔታ እንዲቀራረብ አደረጋቸው፡፡ የእናቶቻቸውን ጡት ሳይጥሉ የጀመረ ጓደኝነት …የእናቶቻችውን መሰባሰብ ሳይጠብቁ በራሳቸው ተጠራርተው በአንዳቸው ቤት በረንዳ ወይም  በሆነ ብጣቂ ሜደ መጫወት ተጀመረ…፡፡
ከዛ ትምህርት ቤት የገቡትም አንድ ላይ በአንድ ወቅት ነበር፡፡ሌላው ይቅር አንዳንድ የማይዳረሱ መፅሀፎች አንድ ለሶስት ወይም ለአራት ሲሰጥ ሳይነናጋገሩ ነው የሚቧደኑት፡፡ከመሀከላችን አንድ ሰው ሲጠቃም አንድ ላይ ድንገት አጥቂውን ይወሩታል፡፡ማንም ቢሆን በቁመትም ሆነ በውፍረት ከእነሱ  ቢበልጥ እንኳን አራት ሆነው አንደአንድ ለመፋለም ሲከቡት  ይፈራል፡፡በዚህም ምክንያት  ማንም እነሱን ለመጋፈጥ ድፈረቱ አይኖረውም፡፡
እንዳዛም ሆኖ  በህብረት ከሌላው ሰው ጋር ከሚጣሉበት  ይልቅ እርስ በርሳችው የሚጣሉበት ጊዜ በብዙ እጥፍ ይበልጥ እንደነበረ ትዝ ይለዋል፡፡የጥላችው  90 ፐርሰንት ምክንያት ግን ሰሎሜ ነች፡፡በመሀከላቸው ያላችው አንድ ብቸኛ ሴት ሁላችውም በሆነ መንገድ ከሌላቸው የተሻሉ  ሆነው  በሆነ መጠን ወደእራሳቸው የበለጠ እንድታጋድል ስለሚፈልጉ ሁሉ ጊዜ የጥቅም ግጭት በመሀከላችው  ይፈጠር ነበር፤እና ሁሉንም እኩል በመቆጣት ጥላችውን  አቁመው  በስምምነት እንዲከቧት  የምታስገድዳቸው እሷው ነች፡፡ሰሎሜ በዛ የጓደኝነት ክበብ ውስጥ ልክ እንደንግስት ንብ አይነት ነበረች፡፡
ንግስት ንብ ትውልድ ከማስቀጠል በተጨማሪ ፌርሞን የተባለ ኬሚካል ታመነጫለች፡፡ፌርሞን ሚስጥራዊ ኃይል ያለው ንጥረ ነገር ሲሆን  በአንድ ቀፎ ውስጥ በጋራ የሚኖሩ ንቦችን የውል እና የጋራ ባህሪን  በበላይነት ለመቆጣጠር የሚረዳ ረቂቅ ኬሚካል ነው፡በዛ ኬሚካል አማካይነት ንግስቲቱ በዙሪያዋ ያሉትን እሰከ60 ሺ የሚቆጠሩ የንብ መንጋዎችን ሰጥ ለጥ አድርጋ  ትመራለች ፤ ትቆጣጠራለች፡፡ፌርሞን ለንግስቲቱ የአገዘዛ እና  የኃይል ምንጭ ከመሆኑም በተጨማሪ  በመስክ ስራ ላይ ካሉ ንቦች ጋር መልዕክት የምትለዋወጥበት የመገናኛ አውታር ጭምርም ነው፡፡በተጨማሪ ፌርሞን በአንድ ቀፎ ውስጥ  በህብረት ለሚኖሩ  ንቦች እንደመታወቂያ ወረቀት ሆኖም ያገለግላል፡፡በአንዷ ንግስት የሚተዳደረው የንብ መንጋ ከሌላው ጋር ይለያል..ያ ማለት አንድ ንብ ከሌላ ቀፎ መጥቶ የተሳሳተ ቀፎ ውስትጥ ገብቶ ከሌሎች 60 ሺ   ንቦች ጋር ቢቀላቀል  ሰርጎ ገብ መሆኑን በቀላሉ ይለያል ማለት ነው፡፡
እንግዴህ ሰሎሜም ልክ እንደንግስቲቱ ንብ ሶስቱንም የምትቆጣጠርበት እና እንደፈለገች የምታዝበት የራሷ የሆነ ሚስጥራዊ መንገድ ነበራት፡፡
👍6120🥰2
#አላገባህም


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ


////
ፀአዳ የ21 ዓመት አዋቂ ሴት ነች፡፡አገላለጹ ይጋጫል አይደል?የ22 አመት ወጣት ሆኖ አወቂ ሴት ነች ሲባል  ፡፡አዎ እሷ የ15 አመት እና የ9 ኛ ክፍል ተማሪ እያለች ድብን ያለ ፍቅር ያዟት ነበር፡፡በ16 ዓመት የልደት በአሏ በሚከበርት ቀን በወቅቱ የ19 ዓመት ጎረምሳና የ11 ክፍል ተማሪ ለነበረው የልቧ ሰው በፍደኝነት ድንግልናዋን አስረከበች፡፡ከሁለት ወር በኃላ ማርገዟን አወቀች… ነገረችው፡፡ከሳምንት በኃላ እሷን ሳይሰነበታት.. ደግሞ ሳይስማት…ደግሞ ቀሚስሽን ላውልቅ ፤ ጡትሽን ልጥባ ሳይላት  እሷንም ሆነ ከተማዋን ጥሎ ውትድርና ተቀጥሮ ሄደ…ያንን የመሰለ አስቀያሚ ዜና የሰሚ ሰሚ ከሰው ነው የሰማችው፡፡ያንን የሰማች ቀን ሰማይ ምድሩ ነበር የዞረባት፡ያልጠና ጮርቃ ልቧ ስንጥቅጥቅ አለ….ደነዘዘች…… ፡፡በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ  ማርገዞን አወቀች…ሰማይ ምድሩ ዞረባት…እና በወቅቱ ሁለት ምርጫ ነበር የታያት ..አንድም በሆነ ዘዴ መርዝ በመጠጠት ወይም በገመድ ተንጠልጥሎ ብቻ በሆነ ዘዴ እራሷን ማጥፋት ሲሆን ፤ ሁለተኛው ደግሞ ብን ብላ ሀገሯን ጥላ ወደማታውቀው ሀገር ሄዳ ህይወት እንዳደረጋቻት መሆን፡፡

….በምን አሳማኝ ምክንያት እንደሆነ ባታውቅም ሁለተኛውን መረጠችና ከተወለደችበትና ቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ከሚኖርበት ዶዶላ ከተማ በአንድ አነስተኛ ሻንጣ ልብሷና እና ይጠቅሙኛል ያለችውን  ዶክመንት ይዛ ወደአዳማ የሚሄድ መኪና ውስጥ ተሳፈረች፡፡እንግዲህ የህይወት ዘመን ባለውለታዋን የሆነውን ሚካኤልን የተዋወቀችው እዛ መኪና ላይ ነበር፡፡በወቅቱ አጋጣሚ ሆኖ ጎን ለጎን ነበር የተቀመጡት፡፡የተወሰኑ ቃላቶች እየተለዋወጡ ከተግባቡ በኃላ ድንገት ወዳልታሰበ ቁምነገር ያለው ውይይት ውስጥ ገቡ፡፡

‹‹አዳማ ነው የምትሄጂው  ወይስ ወደአዲስ አበባ ታልፊያለሽ?
››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹አላውቅም…››ስትል በደፈናው መለሰችለት፡፡

‹‹አልገባኝም››

‹‹እኔ እንጃ ..ከተመቸኝ አዳማ እቀራለው…ከለበለዚያ ወደአዲስ አበባ ሄዳለው…እድል እንዳደረገቺኝ ነው የምሆነው››

‹‹ማለት …ቤተሰብ ጋር ነው የምትሄጂው?››ጥያቄውን አሻሽሎ ጠየቃት፡፡

‹‹አይደለም…ስራ ፍለጋ ነው የምሄደው››

‹‹ስራ ፍለጋ….ምን አይነት ስራ?››

‹‹የተገኘውን ስራ፡፡››

‹‹ምነው… ቤተሰቦችሽ የት  ናቸው?››

‹‹ዶዶላ ነበር የሚኖሩት  …ማለት እናቴ ና እኔ ብቻ ነበር..አሁን እናቴ ስለሞተች ብቻዬን ቀረው…እናቴ የሞተችበት ሀገር ደግሞ ተረጋግቼ መኖር አልቻልኩም..ስለዚህ የእድሌን ልሞክር ብዬ ዝም ብዬ ነው እየተጓዝኩ ያለሁት….››ንግግሯን ተከትሎ ከአይኖቾ እንባዋ እየተንከባለለ ፊቷን በማጠብ ወደታች ይወርድ ጀመር፡

የሚካኤል አይኖቸ እንባ አቀረሩ‹‹በጣም አዝናለሁ….አይዞሽ እሺ››

‹‹አረ ችግር የለውም…መኖር ካቃተኝ መሞት አያቅተኝም››ስትል የበለጠ አስደንገጭ ነገር ነገረችው፡፡እሱ ደግሞ እራስን ማጥፋትን በተመለከት እህቱንና እናቱን በቅርብ ያጣ ሰው ስለነበር በቀላሉ ነው ስሜቱ የተነካው፡፡እና በተቻለው መጠን ሊረዳት ወዲያው ነው በውስጡ ውሳኔውን የወሰነው፡፡

‹ኸረ በፍጽም እንደዛ አታስቢ…ቆይ ትምህርት ተምረሻል?››

‹‹አዎ ግን.. ገና ዘጠነኛ ክፍል ነኝ››

‹‹እንግዲያው ለአንቺ የሚሆን ስራ አለኝ››በማለት ያልጠበቀችውን የሚያስፈነጥዝ የምስራች አበሰራት፡፡ማመን አልቻለችም‹‹እየቀለድክብኝ አይደለም አይደል?››

‹‹አይ እውነቴን ነው…አዳማ ላይ ቡቲክ አለኝ…ፍቅረኛዬ ነች የምትሰራው..ግን በቅርብ ትምህርት ስለምትጀምር የሚረዳት ሰው ያስፈልጋታል…እና ሰው ለመቅጠር እያፈላለግን ነበር››

‹‹በጣም ደስ ይለኝ ነበር…ግን ምንም አይነት ተያዥ እኮ የለኝም..ያለኝ መታወቂያ እንኳን የትምህርት ቤት ብቻ ነው››ስትል ስጋቷን ያለምንም መሸፋፈን በግልፅ ነገረችው፡፡

‹‹ችግር የለውም..እኔ ዋስ እሆንሻለው››ሲል ከስጋቷ ገላገላት፡፡

እንባዋን መገደብ ስላልቻለች ለሁለተኛ ጊዜ ማለቀስ ጀመረች..ያሁኑ ለቅሶ ግን የደስታ ነበር፡፡

‹‹ኸረ አታልቅሺ..በፈጣሪ እኔ ሰው ሲያለቅስ ማየት አልፈልግም››ብሎ  ከኪሱ ሶፍት አወጣና አቀበላት…..ተቀበለችና ፊቷን ጠረረገችበት፡፡

እንዳለው አዳማ እንደወረዱ ቀጥታ ይዟት ወደ ቤት ሄደ… ወስዶ ከፍቅረኛው ጋር አስተዋወቃት፡፡በመሰራት ላይ ካለው ጅምር ቤቱ አንድ ክፍል ቤት አስተካከለና ዕቃ አሟልቶ አስረከባት፡፡ሰው ሳይሆን መላአክ መስሎ ተሰማት፡፡እሱም ብቻ ሳይሆን ፍቅረኛው አዲስ አለምም በልዩ ሁኔታ እንደጓደኛ ብቻ ሳይሆን እንደታናሽ እህት ተቀብላ ወደደቻት….በዚህም ፀአዳ ለረጅም ወራቷች ስታማርረው የነበረውን ፈጣሪዋን ይቅርታ ጠይቃ ማመስገን ጀመረች፡፡

በዚህ ሁኔታ ነው ሚካኤል እና ፀአዳ የተዋወቁት..፣ከዛ ብዙም ሳትቆይ ከቤተሰብ ጠፍታ የመጣችበትን ትክክለኛ ምክንያት ለሚካኤል እና  ለፍቅረኛው ለአዲስአለም  ነገረቻቸው…እንደዛ ያደረገችው ሆዷ እየገፋ ሲሄድ የግድ መጋለጧ የማይቀር መሆኑን ስለተገነዘበች ነው፡፡
ከዛ ልጇን በእጇቸው ላይ ወልዳ ከእሷ እኩል እየተንከባከቡ አሳድጉላት፡፡ዛሬ ላይ እነሱም አንድ ቤት ተጠቃለው መኖር ከጀመሩ አራት አመት ያለፋቸውና የሶስት አመት ልጅ ያላቸው ሲሆን በተለያየ ምክንያት በዚህ ወር ይሁን… በሚቀጥለው አመት እያሉ ሲያዘዋወሩት የነበረው ሰርጋቸውን  ለመደገስ አሁን ቀን ተቆርጦ በጀት ተመድቦለት እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፡፡ 

እና  ፀአዳም ይሄንን የወዳጆቾን ሰርግ ልዩ እና በህይወት ዘመናቸው ሙሉ የሚያስታውሱት እንዲሆን ትፈልጋለች፡፡ለዛ ነው ምንም ነገር እንዳይጎድል ለወራት ቀንና ለሊት እንቅልፍ አጥታ ስትለፋ የሰነበተችው ፡አሁን አንድ ነገር ብቻ ይቀራታል፡፡በዚህ ሰርግ ላይ ለሚካኤል ብቸኛ ዘመድ የሆነውን አንድ ወንድሙን እንደምንም አሳምና ሰርጉ ላይ እንዲገኝ በማድረግ  ሰርፕራይዝ  በማድረግ  ደስታውን ሙሉ ልታደርግለት እቅድ አውጥታለች፡፡ሚካኤል  ለረጅም ጊዜ አውርቶትና አግኝቶት የማያውቀው  ወንድሙ ዘሚካኤል  በሆነ ተአምር በሠርጋቸው ላይ እንዲገኝ  ለማድረግ  ከልቧ ቆርጣ ተነስታለች።

ይህንን ሀሳብ በአእምሮዋ ስታሰላስልና ስትዘጋጅበት ከወር በላይ ነው የቆየችው፡፡በጣም በብዙ ጥረትና በብዙ ድካም መውጫ መግቢያውን ፕሮግራሞቹንና ልምዶቹን ስታጠና ነበር ሰነበተችው፡፡በቋሚነት በሚኖርበት አዲስአበባ እሱን ለማግኘት ፈተና ነው፡፡ በትክክል እንዴት እሱ በሀሳቧ እንዲስማማ ለማድረግ እንደምትችል እስካአሁን ድረስ በትክክል አላወቀችም።ምክንያቱም ዘሚካኤል እንደማንኛውም ሰው በቀላሉ አግኝተውት  የሚያናግሩትና የሚያሳምኑት አይነት ሰው አይደለም፡፡እሱ ሚሊዬኖች የሚያብዱለት ከሀገሪቱ ዝነኛ ድምጻዊያን መካከል ከዋናዎቹ አንደኛው ነው፡፡በዛው ልክ ፕሮግራሞቹ የተጣበቡ..አጃቢዎች የበዙ ሰው ነው፡ቢሆንም ይሄንን ማድረግ አለባት፡፡ይሄ ለምትወዳቸው ና የእድሜ ዘመን ባለውለታዋ ለሆኑት ባልና ሚስቶች እንደስጦታ አድርጋ ልታቀርብላቸው ያሳበችው ትልቅ ስጦታ ነው፡፡፡
👍7613👏3🔥2👎1
#የእግዜር_የአደራ_ልጅ


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
 
ፀጋ አባቷ  እቅፍ ላይ እንዳለች   ፈገግ በማለት የራሄልን ትኩረት ለመያዝ ሞከረች፣ በዚህ ጊዜ እናቷ ጣልቃ ገብታ መናገር ጀመሩ ፡፡

‹‹ራሄል፣ ከዶክተር ኤሊያስን  ጋር እንድትተዋወቂ  እፈልጋለሁ። እሱ የፀጋ  ሐኪም ነው…ዔሊ ይህች ልጃችን ራሄል ናት።››

ዶ/ሩ በስሱ ፈገግ በማለት ‹‹ሰለአንቺ ብዙ ሰምቼያለው ..አንድ ቀን እንደምንገናኝ አምን ነበር›› በማለት እጁን ወደ እሷ ዘረጋ

ጨዋነት ያልጎደለው ፈገግታ ፈገግ አለችለት እና የዘረጋውን እጅን ጨበጠች፡፡ወላጆቿ ከእሱ ጋር አማች ለመሆን እያሴሩ እና እሱንም እያደፋፈሩት እንደሆነ ታውቃለች…ቢሆንም  የሱ ጥፋት አልነበረም።

‹‹የሞተር ሳይክሉ  ሰው ነህ አይደል?››

‹‹አዎ… ነኝ›› አላት፡፡

እጁ ሞቃታማ፣ ጣቶቹ ረዣዥም ነበሩ፣ እና ሲነካት ለረጅም ጊዜ በእንቅልፍ የመወሰድ አይነት የግንዛቤ ብልጭታ በአእምሯዋ ተንፀባረቆ ነበር….ስሜቱን አልወደደችውም። ‹‹በዛ ፍጥነት   ስታበር  ገርሞኝ ነበር››አለችው፣ትንፋሽ ወሰደችና  ‹‹ደግሞ ዶክተር መሆን እና …..››

‹‹እና  ምን?›› ከአንደበቷ ቀልቦ ጠየቃት።

‹‹ከተሸከምከው ሃላፊነት  አንፃር  ሞተር ማሽከርከር….አንድ ነገር ቢደርስብህስ?››

‹‹ለጊዜው አቅሜ የሚፈቅደው ርካሹ እና ፈጣኑ  መጓጓዣ ሞተር ነው. እና  ደግሞ አስፈላጊውን ጥንቃቄ አደርጋለሁ.››ሲል መለሰላት፡፡

ቀዝቀዝ ባለ ድምፅ‹‹ሁሉም የሚያቀነቅናቸው ታዋቂ የመጨረሻ ቃላቶች ናቸው…ጥንቃቄ አደርጋለው..››አለች በንዴት፡፡

በመጠኑ ደፍረስ ባሉት አይኖቹ በትኩረት ተመለከታት…ከመተዋወቃቸው እየሰጠችው ያለው ጠንከር ያለ አስተያየት ግራ አጋብቷታል…

እናትዬው  ፀጋን  ከአቶ ቸርነት  እቅፍ  ወሰድና፡፡‹‹በሉ ወደምግብ ጠረጴዛው እንሄድ….ምሳ ዝግጁ ነው››ሲሉ አወጁ፡፡

ሁሉም ወደምግብ ጠረጴዛው ተከታትለው ሄዱ፡፡ራሄል፣ የተለመደውን ቦታዋ ላይ ተቀምጣለች፣ ዔሊያስ ከእሷ ፊት ለፊት ተቀምጠ።››
አቶ ቸርነት በቀኝ  እጇቸው  የሴት  ልጇቸውን እጅ ግራ እጇቸው ደግሞ  በዔሊያስ ትከሻ  ላይ ዘረጉና። ‹‹ብዙውን ጊዜ ከምግብ በፊት እንፀልያለን››ሲሉ ለዔሊያስ ገለጹለት።

‹‹እኔ ደስተኛ ነኝ. በቤተሰቦቼ ቤትም ስርዓቱ እንዲሁ  ነው.››ሲል መለሰ፡፡አባቷ እጇን ጨምቀው ነበር፣መጸለይ ሲጀምሩ አንገቷን ዝቅ አደረገች።አባቷ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገሩ ማዳመጥ ብትጀምርም  ከጸሎቱ ጋር በልቧ መቀላቀል አልቻለችም። እሷ በሀይማኖት ስርዓት ውስጥ ተወልዳ ያደገች ቢሆንም፣ ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ ከመስመር ወጥታለች። አምላክ  በህይወቷ ጣልቃ እንዲገባ አትፈልግም ወይም  ደግሞም እሱ ራሱም ለእሷ ደንታ እንደሌለው ታምናለች።ስለዚህ ለምን ትጨቀጭቀዋለች፡፡ ወላጆቿ በዚህ መሳኔዋ  ደስተኛ እንዳልሆኑ በደንብ ታውቃለች ቢሆንም ግን ርቀታቸውን በመጠበቃቸው ታመሰግናቸዋለች። እና ምናልባት ወደቀልቧ እንድትመለስ ዘወትር ለእሷ በድብቅ ይፀልዩላት ይሆናል፡፡

ፀሎቱ ተገባዶ በ‹‹አሜን›› እንደተዘጋ እናትዬው ‹‹በሉ እራሳችሁን አስተናግዱ ››አለቻቸው፡፡ሁሉም ፊት ለፊቱ ባለው ሳህን ላይ ፊለፊታቸው ከተደረደሩት በርካታ የምግብ  ዓይነቶች የሚፈልጉትን  መጠን መውሰድ ጀመሩ፡፡ተ

‹‹ከቻልክ ክትፎውን  አቀብለኝ››ስትል ራሄል ወደኤልያስ እያየች አጉተመተመች፣
እናትዬው የራሄልን አስተያየት ውድቅ በማድረግ እጆቿን እያወዛወዘ ‹‹እስኪ እንደአንበሳ ስጋ ማሳደድሽን አቁሚ።››በማለት ገሰፃት፡፡  ቀጠል አደረጉና ‹‹ለሚያገባሽ ሰው አዝንለታለው።››ሲሉ  አከሉበት፡፡

‹‹ደህና፣ ደስ ሚለው ነገር ፍቅረኛ  የለኝም ››አለች ራሄል፡፡
‹‹እነዚህማ የተለመዱ ቃላቷችሽ ናቸው››

እናቷ በራሄል ንግግር ተከፍተው ‹‹አንድ ቀን ያንን በብቸኝነት  የቀዘቀዘ አፓርታማሽን እርግፍ አድርገሽ ጥለሽ  እንደ ዶ/ር ኤሊያስ ቤት አይነት  ግቢ  ወዳለው ቤት ትቀይሪ ይሆናል።››ሲሉ  ምኞታቸውን ተናገሩ፡፡

እናትዬው  ወደ ዶ/ሩ  ዘወር አሉን‹‹ቤትህን በማስተካከል ላይ እንዳለህ ሰምቼያለው?››

‹‹በእውነቱ ወንድሜ ቢንያም ነው እየተከታተለው ያለው። እሱ አናጺ  ነው። ስለ ኩሽና አሰራር አንዳንድ ውሳኔዎችን እንድወስን እየጨቀጨቀኝ  ነበር, ነገር ግን ዘመናዊ ይሁን ወይም ባህላዊ ጭብጥ ይኑረው  የሚለውን ለመወሰን  እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም››

አቶ ቸርነት‹‹ራሄልን  ይዘሀት ብትሄድ ልትረዳህ ትችል ይሆናል››የሚል ሀሳብ አቀረቡለት። ዔሊያስ የራሔልን መኮሳተር ችላ በማለት እንደ ተወደደ ልጅ ፊቱ እያበራ ነው።
አንቷም ‹‹አዎ የእኔ ልጅ …በኢንቴርዬር ዲዛይን  ላይ በጣም ጎበዝ ነች።››ሲሉ  የአባትዬውን ሀሳብ ደገፉ፡፡

ራሄል ስለእሷ የተሰጠ ያለው  አስተያየት ከየት እንደመጣ አታውቅም። ወላጆቿ አፓርታማዋን  በሚጎበኙበት ጊዜ  በዕቃዎቾ፤በምንጣፎች እና በመኝታ ቤቷ ቀለም ..ብዙ ብዙ ኔጌቲቨ  የሆነ አስተያየት ሲሰጧት እንደነበር ታስታውሳለች፡፡ እንደውም እናቷ ‹ጥቂት እንኳን ለስሜቷ ሳይጨነቁ ቤቷን መኖሪያ ቤት ሳይሆን ሙዚየም እንዳስመሰለችው ነግረዋት  ነበር፡፡

‹‹የምፈልገውን በትክክል  አውቃለሁ። ትልቁ ችግሬ ግን ውሳኔዎችን ለመወሰን  ጊዜ ማግኘት አለመቻሌ ነው ›› ሲል ኤሊያስ መለሰ።

ራሄል የሆነውን ነገር የተረዳች መስላ‹‹እንድትጨርሰው  የምትገፋፋህ  ሴት የለችም?››ስትል ጠየቀችው፡፡
አባቷ  ራሄልን በግንባራቸው ገፆት ፡፡
ዶ/ሩ ‹‹ለጊዜው አቋሜ ልክ እንደአንቺው ነው….ለሴት ዝግጁ አይደለሁም››ሲል መለሰ።
ራሄል ውይይቱ ወደ መሃል ከተማ የትራፊክ ፍሰት፣ የኑሮው ውድነትና   ፣ እና የፖለቲካ ውዥንብር.እና የሰላም እጦት  የመሳሰሉት ጉዳዬች ላይ ሲያተኩር እፎይ አለች፡፡
በመሀል ወደ ዶ/ሩ አትኩራ እየተመለከተች ‹‹በቅርቡ የኖብል ፋውንዴሽን አመታዊ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት  አለ።በዝግጅቱ ላይ መገኘትህን ማረጋገጥ አለብህ››አለችው፡፡

‹አረ ችግር የለውም..አታስቢ እገኛለው››ሲል ቃል ገባላት፡፡
እናትዬው‹‹ቀኑ ደረሰ እንዴ..?እንግዲህ በስራ ጫና ድራሽሽ ሊጠፋ ነው››ሲሉ ስጋታቸውን ገለፁላት፡፡

ራሄል  ‹‹እማዬ ደግሞ ….እኔ ብቻዬን የማደርገውን አስመሰልሺው ። አብዛኛውን ስራ የሚሰሩልኝ  ትላልቅ ሰራተኞች አሉኝ እኮ››

‹‹ነገር ግን ለሰራተኞችሽ  በቂ ውክልና አትሰጪም።ቅድስትን ለመተካት እነዚያን ሁለቱን ረዳቶች መቅጠርሽን ስሰማ  ብዙ  የስራ ጫናሽን ያቃልሉልሻል ብዬ አስቤ ነበር። ነገር ግን አሁን እንደማየው ከሆነ የበለጠ ስራ ነው ያበዛብሽ፡፡››

‹‹ሰራተኞቹ  በጣም አዲስ ናቸው ። ፋይሎቹን ብቻ ሰጥቻቸው ሁሉንም ነገር በራሳቸው እንዲቋቋሙት  መጠበቅ አልችልም።››

‹‹ዬኒቨርሲቲ ዲግሪ ያላቸውና …በደንብ የሰለጠኑ ናቸው እኮ።››

‹‹አዎ ትክክል ነሽ..ግን የፋውንዴሽኑን ስራ በተመለከተ ትንሽ ተጨማሪ ልምድ ያስፈልጋቸዋል፣ሁሉም ሰው ወደሆነ አዲስ ስራ ሲሄድ ለተወሰነ ጊዜ ከአሰራሩ ጋር እስኪለማመድ አዲስ ሆኖ መገኘት አይቀርም››ለእናቷ ሌላ የማስጠንቀቂያ እይታ ሰጠቻት። ይህን ጉዳይ ሙሉ በሙሉ በማያውቁት ሰው ፊት መወያየታቸውን አልወደደችውም ።
‹‹ውዴ እወድሻለሁ፣ ግን ደግሞ አውቅሻለሁ።››ሲሉ  እናትዬው በአቋማቸው መፅናታቸውን አረጋገጡላት፡፡

የራሄልን ማስጠንቀቂያ ችላ በማለት ‹‹እና ሁሉንም ነገር መቆጣጠር እንደምትችይ  ማሰብ ማቆም አለብሽ። አንዳንድ ነገሮችን ለእግዚአብሔርን መልቀቅ አለብሽ።››ሲሉ ንግግራቸውን ደመደሙ፡፡
59👍7
#ቋጠሮ_ሲፈታ


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በዘሪሁን_ገመቹ
/////

ጤና ይስጥልኝ..ከዞኑ ዋና አቃቢ ህግ ቢሮ ክብሩ አቃቢ ህግ አቶ ግርማን ወክዬ ነው የመጣሁት ….ስብሰባው በእኔና እና በእናንተ መካከል ይደረጋል ማለት ነው፡፡››የሚል ያልተጠበቀ አይነት አጭር ማብራሪያ ሰጠች፡፡

ከመሀከለኛው ወንበር የተቀመጡት በእድሜያቸው መጨረሻ ላይ ሚገኙት አዛውንቱ ሰው"ምንም ችግር የለውም ለአንቺ እና ለሀለቃሽ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት ፍቃደኞች ነን…እኔ ዳኛ ዋልልኝ እባላለው፡፡እሱ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኩማንደር ገመዶ ይባላል፡፡ሁለት ሰዎች ተራ በተራ እየጠቆመ። "እሳቸው አቶ ፍሰሀ ይትባረክ ይባላሉ እሱ ደግሞ ልጃቸው ጁኒየር ይባላል።የሶሌ ኢንተርፕራይዝ ዋና እና ምክትል ስራአስኪያጅና ባለቤት ናቸው፡፡የሶሌ ኢንተርፕራይ ማለት ከተማዋ የጀርባ አጥንት የሆኑትን በጣም
በርካታ ድርጅቶችን በጥምረት የሚያስተዳድር ግዙፍ ድርጅት ነው፡፡አቶ ፍሰሀ እና ልጃቸው በከተማዋ እጅግ የተከበሩ እና የተመሰገኑ ግለሰቦች ናቸው፡፡››ሲሉ የማስተዋወቅና የመግቢያ ንግግር አድርገው ከጨረሱ በኃላ ራሷን እንድታስተዋውቅ አይን አይኗን ይመለከቷት ጀመር፡፡

አለምም የዳኛውን ማብራሪያ በፅሞና ስታዳምጥ ከቆየች በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ እነዚህ ከፊት ለፊቷ ያሉትን ዳኛው የዘረዘሯቸውን ሶስት ሰዎች በማየቷ እንግዳ እና ሀይለኛ የማወቅ ጉጉት በውስጧ ሲንተገተግ ተሰማት፡፡በውስጧ ለእነሱ ያዳበረችው ጥላቻም ሲገለባበጥ ይታወቃታል፡፡ እነሱ ስለእሷ እና ስለ ስብሰባው አለማ ለማወቅ እንደጓጉ ሁሉ እሷም እነሱን ለማወቅ ፈልጋለች፣
አለም መጀመሪያ አቶ ፍሰሀን ነው የተመለከተችው….በእድሜ ከዳኛው ብዙም የሚያንስ አይመስልም…ግን እንደዳኛው ግርጅፍጅፍ አላለም፡፡ሰውነቱን በትኩረት ላየ‹‹አሁንም ገና እጅ አልሰጥም ››እያለ የሚፎክር ይመስላል፡፡ፊቱን በትኩረት ስትመለከት መሰላቸቱን ታዘበች፡፡የበጋው የከረረ ጸሀይ እና ፀሀይን ተከትሎ ያለው ሙቀት ያደከመው ይመስላል፣ የማሰብ ችሎታ ያላቸው የሚመስሉ ደማቅ ጥቋቁር አይኖቹ አፈጠጡባት።

አለም ከእሱ አይኗን ነቀለችና ቀጥሎ ወደተቀመጠው ኩማንደር አዘዋወረች፡፡ሙሉ የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ነው፡፡ጭንቅላቱ ላይ ያጠለቀው የፖሊስ ኮፍያ ወደታች አዘቅዝቆ ብድር እንዳለበት ሰው ከፊል ፊቱን እንዲሸፍን አድርጎታል፡፡ እድሜው አርባዎቹ አጋማሽ ላይ እንዳለ ብትገምትም ሰውነቱ ግን አሁንም የጎረምሳ ነው…ከፊቱ ላይ ምንም ማንበብ አልቻለችም ፡፡ቀዝቃዛና ስሜታ አልባ ሆኖ ነው ያገኘችው፡፡ አካሉ ብቃት ያለው እና ጠንካራ ይመስላል። ማንም ሰው ከእሱ ጋር አካላዊ ፀብ ውስጥ ገብቶ መጣላትን ይጸየፋል። በዛ ላይ ጨካኝና ተንኰለኛ መሆኑን በእይታ እንኳን መገመት ያን ያህል ከባድ አይደለም፡፡ በመጨረሻ ጁኒዬርን ተመለከተች፤በእድሜ ከኩማደሩ ጋር እኩያ መሆኑ ያስታውቃል፡፡ በሌሎች ነገሮች ግን ተቃራኒ ናቸው፡፡ጁኒዬር ከሁለቱም በተለየ ገራገር ሰው ይመስላል፡፡ፈገግ ሲል ልዩ አይነት መስህብ አለው ። ቀጥ ያሉ ነጭ ጥርሶቹ ብልጭ ድርግም ሲያደርጋቸው ቀልብን ይገዛሉ፡፡ ጥቁር ደማቅ አይኖቹ ከአባቱ በተለየ የጠለቀ ሀዘን ይነበብባቸዋል፡፡ ደግሞ ውብ ነው፡፡የወንድ ቆንጆ፡፡

በሽርፍራፊ ሰከንዶች ሁሉንም ገምግማ ካጠናቀቀች በኃላ ጉሮሮዋን አሟሸችና ስሟን ለመስማት በጉጉት እየጠበቁ ወዳሉት አራት ጥንድ አይኖች እየተመለከተች ።

"እኔ አለም ጎበና እባላለሁ፣ ጎደኞቼ አሌክስ ይሉኛል፡፡የሶሎሜ ሴት ልጅ ነኝ።"አለች

ንግግሯን ተከትሎ በቤቱ ኒዩክሌር ቦንብ የፈንዳ ይመስል በሶስትም ሰዎች ላይ የታየው ድንጋጤ የተለየ አይነት ነበር፡፡ዳኛው ግን ምኑም ስላልገባቸው የሌሎቹ መደንገጥ ድንግርግራቸው እንዲወጣ ነው ያደረገው…ለተወሰኑ ደቂቃዎች በክፍሉ ፍፁም አይነት ዝምታ ተንሰራፋ።

ዳኛው ግራ በመጋባት "ሰሎሜ  ማን ናት?"ሲሉ ጠየቁ።

አቶ ፍሰሀ ወንበሩ ላይ እንደ ተሰባበረ አሻንጉሊት ወደ ኋላ ተንሸራተተና
"አንቺ…የሰሎሜ ሴት ልጅ….?
አምላኬ..እኔ አላምንም." አለ፡፡

ጁኒየር በሹክሹክታ" የማይታመን ተአምር።አንድ ሰው ህልም ነው ቢለኝ ደስ ይለኛል?" ሲል ተሰማ፡፡

በጡረታ መውጫው በር ላይ ሚገኙት አዛውንቱ ዳኛ አሁንም ግራ እንደተጋቡ ነው። ሁሉም ድንጋጤ ውስጥ ስላሉ ለእሳቸው ማንም ትኩረት አልሰጠም።አባትና ልጅ ፊቷን በደንብ ለማጥናት አፈጠጡባት …አይኖቾ ከዘመናት በፊት ከሚያውቋት እናቷ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለቸው በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል።በደንብ ልብሱ ላይ የወታደር ኮፍያ ያጠለቀው ኩማንደር አሁን በትካዜ እግሯቹን እያወዛወዘ እንደሆነ አስተዋለች፡፡

"ከዚህ ሁሉ አመት በኋላ እዚህ ምን ልትሰሪ መጣሽ ?" አቶ ፍሰሀ ነው ያለይሉኝታ የጠየቋት።

‹‹ምን ልትሰሪ መጣሽ ነው..?ወይስ እንኳን ደህና መጣሽ?››በማሽሞጠጥ መልስ ሰጠች፡፡

"ስንት አመት ሆነሽ?" ጁኒየር የጠየቀው የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር፡፡

"ሃያ አምስት." አለም ትክክለኛ እድሜዋን ነገረችው፡፡

"አያትሽ እንዴት ነች?"

"በአሁኑ ጊዜ አርጅታለች..በሜቅዶኒያ የአረጋዊያን መንከባከቢያ ተቋም ውስጥ ነው የምትገኘው…የጡረታ ደሞዟን ይዛ እዛ ገብታለች..በካንሰር በሽታ ተይዛ የመሞቻ ጊዜዋን እየተጠባበቀች ነው።
ማለቴ ኮማ ውስጥ ነች።››

"ይህን በመስማቴ አዝናለሁ."አለ ጁኒዬር፡፡

"አመሰግናለሁ።"ስትል በትህትና መለሰችለት፡፡

"ይህን ሁሉ ጊዜ የት ነበር የምትኖሪው?"አቶ ፍሰሀ ነው ጠያቂው፡፡

ህይወቴን በሙሉ አዲስ አበባ ነው የኖርኩት፡፡ቢያንስ እኔ እስከማስታውሰው ድረስ። እዚያው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን አጠናቅቄ ወደ አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍልን ተቀላቀልኩ።ከአራት አመት በፊት ነው ግራጅዌት ያረኩት..እና ሶስት አመት እዛው አዲስአበባ አንድ የውጭ ካምፓኑ ውስጥ ተቀጥሬ ስሰራ ነበር..እና አሁን ለዞኑ ምክትል አቃቢ ህግ ሆኜ ከተመደብኩ አንድ ሳምንት ሆነኝ ።"

"የህግ ትምህርት ቤት ተመርቀሽ….እዚ የእኛ ዞን አቃቢ ህግ ። ደስ የሚል ነው››ጁኒየር በፈገግታ ተውጦ ተናገረ ፡፡
በዋናው አቃቢ ህግ ጥያቄ አቅራቢነት ይህንን ስብሰባ እንዲያዘጋጁ የጠየቁትና ያዘጋጁት አዛውንቱ ዳኛ ሁኔታው ምንም አላመራቸውም… ፡፡

"እንደዚህ አይነት ልብ የሚነካ አይነት መገናኘትን እጠላለሁ፣ ግን አሁንም በጨለማ ውስጥ ነኝ..ስለሚካሄደው ነገር ምንም የገባኝ ነገር የለም፡፡››ሲሉ ብሶታቸውን ተናገሩ፡፡

‹‹ሶሎሜ ማለት የእሷ እናት ነች፡፡እሷ ከመወለዷ በፊት የጁኒዬርና የኩማንደሩ የቅርብ ጓደኛ ነበረች፡፡ከዛም አልፏ ቤተሰብ ነበርን….ነፍሷን ይማርና ፈፅሞ የማይለያዩ የልብ ጓደኛሞች ነበሩ…. ››ከዚያም ጥቋቁር አይኖቹ ደመና አጠላባቸውና በሀዘን ራሱን ነቀነቀ..እና ንግግሩን ካቆመበት ቀጠለ "ሞቷ ለሁለችንም ከፍተኛ ሀዘን ያስከተለ ነበር….ክብር ዳኛ … የገዳዩን ችሎት እኮ እርሶ ነበር ያስቻሉት…የእኔ የእርባታ ግቢ ውስጥ አንድ እብድ በቢላዎ ወግቶ ከገደላት በኋላ ራሱን እስር ቤት ውስጥ ያጠፋው…፡፡››

የዳኛው ፊት ሲጠቁር በግልፅ ተመለከተች‹‹እኔ እንጃ ትዝ አላለኝም…የሽማግሌ ነገር ስንትና ስንት ችሎት አስታውሳለው ብለህ ነው?››በማለት ሸፋፍነው ለማለፍ ሞከሩ፡፡

አቶ ፍሰሀ ራሱን ለመቆጣጠር የተወሰነ ጊዜ በፀጥታ አሳለፈና። " ለማንኛውም ስለ አለም ሆነ ስለ አያቷ የሆነ ነገር ስንሰማ ይህ የመጀመሪያ ጊዜያችን ነው።

ለማናኛውም እንኳን ወደእናትሽ የትውልድ ከተማ በሰላም መጣሽ››አላት፡፡
53👍3😢2🔥1