አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ፍቅር_አለማማጁ!


እኔና ቤቲን ያገናኘን እንጀራ ነው እህል ውሃ። Destiny ወይም እጣፈንታ ልትሉት ትችላላችሁ፡፡ እኔ የድርጅቱ የሂሳብ ሹም ሆኜ በተቀጠርኩ በመንፈቄ፣ ቤቲ ፀሐፊዬ ሆና ተቀጠረች፡፡
የሚያስደነግጥ መልክና ቁመና የላትም፡ ግን ከዚያ የማይተናነስ ቀልድና ጨዋታ አዋቂ ናት፡፡
ወንዶችንም ሴቶችንም እኩል መማረክ የሚችል አንደበት ተችሯታል እኔንም የማረከችኝ በዚሁ
አንደበቷ ነበር ቤቲ ሲበዛ ቀልደኛ ናት የዕድል ጉዳይ ሆኖ ነው እንጂ ቦታዋ የእኔ ቢሮ ሳይሆን የኮሜዲ መድረክ ነበር እሷ ከመጣች በኋላ
መ/ቤታችን የሳቅ አዝመራ ሆኗል በእርግጥ አንዳንድ አስደንጋጭ ቀልዶች ተናገራለች፤ አጥንት ከሥጋ የሚለያዩ በቀልዶቿ ደንግጠው
የሸሹ ግን አላየሁም ከልጅነት ባልንጀራዬ ከቢኒ በቀር እኔና ቢኒ እንደወንድማማቾች ነው
ያደግነው። አንድ ሰፈር ብይ ተጫውተን፣ አንድ ት/ቤት ተምረናል ዩኒቨርስቲ ስንገባ
ተለያየን፡፡ እሱ ኢንጂነሪንግ ሲያጠና፣ እኔ አካውንቲንግ አጠናሁ። እሱ ባህርዳር ሥራ
አግኝቶ ሲሄድ፣ እኔ አዲስ አበባ ቀረሁ፡፡ እሱ ከሥራ ባልደረባው ጋር ፍቅር ሲጀማምር፣ እኔ የፍቅር ጓደኛዬን አለምኩ በሁለተኛ ወሬም፣ ቤቲን ጣለልኝ ቢኒ በዓመቱ ነው ዳጎስ ያለ ደሞዝ የሚያስከፍለውን የባህርዳር
ሥራውን ጥሎ ሸገር የመጣው ምን ሥራውን ብቻ! ፍቅረኛ ያላትንም ጭምር እንጂ የድሮ ሸጋ ባህርዩንም ባህርዳር ጥሎት የመጣ ይመስለኛል ተግባቢና ተጫዋች የነበረው ቢኒ፤ በዓመት
ጊዜ ውስጥ እልም ያለ ተጠራጣሪ ሆኖ ነው የመጣው፡፡ ብዙ የእሱ ያልነበሩ እንግዳ ጠባዮችም አምጥቷል መቆጣት
መነጫነጭ፣ ማማረር እና ሌሎችም
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሆኖ ሆኖ ግን አዲስ አበባ መምጣቱን ከሰማሁ ጊዜ ጀምሮ ፍቅረኛዬን ላስተዋውቀው ብዙ
ለፋሁ። ለእኔ የበኩር ፍቅረኛዬን ለልጅነት ባልንጀራዬ ማስተዋወቅ ትልቅ ትርጉም ነበረው፡፡ ሸጋ የህይወት ጓደኛ መምረጤን እየነገረኝ፣ ቢያደንቅልኝ ደስታዬ ነበር፡፡ድሮ የማውቀው ቢኒ ደግሞ የአድናቆት ስስት የለበትም፡፡ አሁን
እሱ ራሱ መች ጭራው ተይዞ! ከስንት ጊዜ በኋላ እንደምንም እሺ አሰኘሁት፡፡
የተቀጣጠርንበት ሆቴል ቀድመን የደረስነው እኔና ቤቲ ነበርን፡፡ ከ20 ደቂቃ በኋላ ቢኒ መጣ። ከወደፊቷ የትዳር አጋሬ ጋር አስተዋወቅሁት፡፡
እሱቴ! አልሞቀውም አልበረደውም፡፡ ቤቲ ከፍቅር ጋር የተገናኙ ቀልዶችን በተከታታይ አዘነበችልን። ብዙዎቹን እኔ ራሴ ሰምቻቸው አላውቅም ይሄን ሁሉ ያደረገችው የልጅነት ባልንጀራዬ ዘና እንዲልና የመግባባት ስሜት ለመፍጠር ነበር ግን
አልተሳካላትም፡፡ በቀልዶቿ የምንስቀው እኔና እሷ ብቻ ነበርን ቢኒ ተሳስቶ እንኳን ጥርሱን ብልጭ አላደረገም፡፡ እሷ ግን ተስፋ ሳትቆርጥ በኩመካዋ
ገፋችበት “ምነው…የተደበርክ ትመስላለህ? እኔ እኮ መቼ ተዋውቄው ስል ነው
የከረምኩት”አለችው፤ ዓይን ዓይኑን እያየችው፡፡
ደንገጥ አለና ተመለከታት፤ ኮስተር
ብሎ፡፡“የምሬን ነው… ትላንት ሳሚ እንደቀጠረህ ሲነግረኝ ጉጉቴ ጨመረ፤ የቀጠሮ ሰዓቱ አልደርስ
አለኝ” ስትል አከለችለት፡፡ ይኼኔ የተለጎመው አፉ ተፈታ “ምነው በደህና?” ጠየቃት፤
በጥርጣሬና በጉጉት ስሜት ተሞልቶ “ምን መሰለህ… ሳሚ፤ ፎቶህን ሲያሳየኝ በአካልም እንዲህ ከሆነ ወደ እሱ እቀየሳለሁ ብዬው ነበር…” አለች ቤቲ - በዓይኗ እየጠቀሰችኝ፡፡ እንዲህ አይነት ኩምክና ለእኔ የተለመደ ስለሆነ ምንም አልመሰለኝም ቢኒ ግን
እንደአራስ ነብር ቱግ አለ የባሰ አታምጣ ማለት ይሄኔ ነው “የሴት ቀልደኛ ደሜን ነው የምታፈላው!” እያለ ከተቀመጠበት ተነሳ “ሳሚ፣ ህይወቴን ያበላሸችብኝ እንደዚህች ያለችው ፎጋሪ ነኝ ባይ ናት…እቺም ጉድ እንዳታደርግህ!”
አለና ከሆቴሉ የማምለጥ ያህል ተጣድፎ ወጣ፡፡ እኔ ብቻ ሳልሆን እምብዛም ድንጋጤ የማይጐበኛት ቤቲ፤ ለአፍታ በዝምታ ተውጣ
ቀረች፡፡ ለማጫወት ያደረገችው
ሙከራ እንዲህ በጠብ ይጠናቀቃል
ብላ አላሰበችም ነበር “ሳሚዬ ፈተናውን ወድቋል…
አንተው ትሻለኛለህ!” ስትል እየቀለደች፣ ከንፈሬ ላይ ከንፈሯን አሳረፈች፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ከወር በኋላ ቢኒ ጋ ደውዬለት እንድንገናኝ ጠየቅሁት “የሴት ቀልደኞች እጣ ክፍሌ
አይደሉም … ካለች ግን ከበር ነው የምመለሰው!” ሲል አስጠነቀቀኝ ባህርዳር በመሃንዲስነት
በተቀጠረበት የግል ኮንስትራክሽን ድርጅት ውስጥ ለጥቂት ወራት እንደሰራ ነበር አንዲት ልጅ እግር መሃንዲስ ከሌላ ቅርንጫፍ
ተዛውራ፣ ወደ እነቢኒ ክፍል የመጣችው ማህሌት ትባላለች፡፡አለቃው እንደቀልድ
“አለማምዳት” ብለው ለእሱ
አስረከቡት እሱ ግን የምር አደረገው፡፡
የኪስ ቦርሳውን አውጥቶ ሁለት ፎቶዎቿን አሳየኝ፡፡ ውበቷ እንደሰማይ ክዋክብት ይንቦገቦጋል።
በዚያ ላይ ሽቅርቅር ናት! ቢኒ እሷን ማለማመድ ዋናው ስራው አድርጐት ቁጭ አለ ጠዋት ከቤት
ወደ ቢሮ ይዟት ይመጣል- በኮንትራት ታክሲ፡፡ በሻይ ሰዓት አብሯት ነው ማታ በውድ ሆቴሎችና
ሬስቶራንቶች እየጋበዘ ህልሟን፣ ተስፋዋንና ቅዠቷን ሰምቶ ወደ ቤቷ ይሸኟታል፡፡ የማታ ማታም
አለማምዳለሁ ብሎ ተለማመዳት በልቡ ፍቅር አረገዘ፡፡ እሷ ደግሞ ቀልዷና ቁምነገሯ አይለይም፡እንደልጅነት ዘመኑ “ባሌ” እያለች
ልታሳፍረው ትሞክራለች። ፍቅረኛ
ይኑራት አይኑራት የሚያውቅበት
ፍንጭ አልነበረውም “አለማምዳት” ያለው አለቃ “ራት ልጋብዝሽ” ሲላት “ቢኒ
ቦይፍሬንዴ ነው” ብላ እንዳስደነገጠችው ነግራዋለች ለቢኒ ነግራዋለች አንድ ቀን
ያረገዘውን እንደምንም አምጦ ተገላገለው። ለማህሌት እውነቱን ነገራት የሚገርመው ግን
ነገርየው ዱብዕዳ አልሆነባትም ቢኒ…“ጊዜ ስጠኝ፤ ላስብበት” ለቢኒ ይሄም ቢሆን አስፈንጥዞታል ምላሿ አዎንታዊ ይሆን ዘንድም
ነፍስ ካወቀ ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ
ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ስለት ተሳለ ወራት እንደዘበት ነጎዱ፡፡ በእርግጥ የተለመደው ግንኙነታቸው
አልተቋረጠም፡፡ ግን ምላሽ የለም ቢኒያም ፍቅሩን
ልታረሳሳው የሁሉ ፈለገች መሰለው ከራሱ ጋር ብዙ ከተማከረ በኋላ ፍቅሩ አስታወሳት
“ቢኒዬ… አልወሰንኩም እኮ!” አለችው፤ በሚንቆረቆር ድምጿ“እስካሁን?” አላት፤ ተገርሞ፡፡
“ያጣደፉት ፍቅር…” የሚለውን ዘፈን በሚወድላት ድምጿ አቀነቀነችለት (አትቸኩል ለማለት!)
ቢኒ ራሱን ታዘበ “እውነቷን እኮ ነው … ምን አጣደፈኝ?” አለ፡፡ ግን ምን ያህል ጊዜ እንደሚስፈልጋት ቢያውቅ አይጠላም ነበር፡፡
የዛን እለት እንደወትሮው ወደ ቤቷ ከሸኛት በኋላ ወደ ቤቱ አልሄደም ቢመሽም ቤተክርስቲያን ሄዶ
ፈጣሪውን ተለማመነ ጠዋት ከእንቅልፉ የቀሰቀሰው የሞባይሉ ቴክስት ሜሴጅ (SMS)
ነበር፡፡ እየተጨናበሰ ሞባይሉን ከኮመዲኖው ላይ አንስቶ መልሶ
አስቀመጠው። ትንሽ ቆይቶ ግን
ከአልጋው ላይ ተስፈንጥሮ ተነሳና
ሞባይሉን አፈፍ አደረገ፡፡ የሜሴጅ
ሳጥኑን የሚከፍተውን ቁልፍ ተጫነ፡፡ ዓይኑን አላመነም ጽሑፉን ትክ ብሎ ተመለከተው፡፡ ያው ነው። “ቢኒዬ… የህይወት ዘመን ሽልማት ትፈልጋለህ?
አሸንፈሃል! እኔን!!” ይላል - የማህሌት መልእክት። ስሜቱ ድብልቅልቅ አለበት፡፡ ደስታ…ድንጋጤ..ጭንቀት… ብዙ
ስሜቶች አፈኑት፡፡ ሁሉንም አስተናግዶ ሲጨርስ ወደ አቅሉ ተመለሰ፡፡ ስልክ ሊደውልላት ወይም መልእክት ሊልክላት አሰበ። ከዚያ በፊት ግን አንድ ነገር ትዝ አለው - ስለቱ! ከመቅፅበት ከአልጋው ወርዶ ልብሱን መለባበስ ጀመረ “ስለቴ
ሰመረልኝ”ን በልቡ እያዜመ፡፡ በቀጥታ ያመራው ወደ ቤተክርስቲያን ነበር፡፡ ስለቱን የቤተክርስቲያኑ ሳጥን ውስጥ
ለማስገባት ሲታገል፣ ሌላ ቴክስት

ሜሴጅ አንቃጨለ፡፡ ስለቱን ታግሎ
አስገባና ሞባይሉን ከኪሱ አወጣ
👍2
እንዴት ናቹ #የአትሮኖስ ቻናል ቤተሰቦች እንደሚታወቀው #ሁቱትሲ የተሰኘው ድርሰት በትላንትናው እለት ተጠናቋል ያላችሁንም አስተያየት በውስጥ መስመር እየገለፃችሁልኝ ነው ለዚህም ከብዛቱ የተነሳ ለሁሉም መልስ መስጠት ስላልቻልኩ ይቅርታ እየጠየኩ ባጠቃላይ ግን ሁላችሁንም ከልቤ ማመስገን እፈልጋለሁ። 🙏

ሌላው በቅርብ ቀን ልንጀምረው ያሰብነው
ረጅም ታሪክ አለ ከነዚህም ውስጥ ለጊዜው 3 አሉ ከነዚህ ውስጥ አንዱን መርጦ ለመጀመር የናተ ከፍተኛ ትብብር ያስፈልጋል

መጀመርያ ከታች ከማስቀምጣቻው ምርጫዎች ውስጥ በናተ በከፍተኛ መጠን የተመረጠውን ቅድምያ አቀርባለው

ሌላው #MUTE አድርጋችሁ የምትጠቀሙ የቻናሉ ቤተሰቦች ፅሁፍ ማዘጋጀት በጣም ከባድ ነው አንዳንድ ቻናሎች ላይ እንደምታዩት ሌላ ቻናል ላይ ያሉትን ታሪኮች Cope paste አደለም የማደርገው በተቻለ መጠን አዳዲስ ታሪኮችን ይዤ ለመምጣት እሞክራለሁ ለዚህም ደሞ ለናተ በሚመች መልኩ ለማቅረብ ከፍተኛ ልፋት አለው እንዲህ የተዘጋጀውን ደሞ እናተ ካላያችሁት ልፋት ብቻ ነው የሚሆነው እናም እባካችሁ #UNMUTE አድርጋችሁ ተጠቀሙ እኔም ሳልሰለች ለናተ ምርጥ ምርጥ ታሪኮችን ይዤ እመጣለሁ

ከታች ካሉት ምርጫዎች ቅድምያ ይቅረብ የምትሉትን በመምረጥ ተሳተፉ

💚 #ፍቅር_እስከ_መቃብር

💛 #ሮዛ

❤️ #የአና_ማስታወሻ
#ፍቅር_ሲሸሽ

አንድም ፍጡር ላይኖር ከስ'ተት የጸዳ
ሆድሽ እጅግ ጠቦ ልብሽ እጅግ ከብዳ
ጠርጥረሽ ላትበይው
አኝከሽ ላትውጪው
በማላመጥ ብዛት ኮስሶ አኮሰስሽው
ጓዴ የሆነውን ዘርዝሬ ብነግርሽ
በጉዳቱ አዝነሽ
እጅግ ተቆጭተሽ
እምዬ ማሪያምን አብረሽው በቆረብሽ
የጨረቃ ወጋገን ፈክቶ በሰማይ ላይ
አንቀላፍታ ሳለች ምድሪቷ በአንድ ላይ
ፍቅርን ሲለግስሽ ስትሰጪው ፍቅርን
ድንገት አውሬ አይቶ በቁም ሲባንን
ነግረሽው ነበረ ውሻ መሆኑን
ነገር ግን . . . ነገር ግን . . .
ሽሽትን መረጠ ከነፈ ከቤቱ
አንድያ ነውና ለናትና አባቱ
አንቺ ግን . . . አንቺ ግን .
ደብቀሽ ሳትይዥ ይሄ ሚስጥሩን
ሃገር እንዲያውቅ አርገሽ ትንሹ ልቡን
“ ጥንቸሊቱ ” አስባልሽው መጠሪያ ስሙን
ውቢት . . .ውቢት .
ሊሳሳት ይችላል ማንም በቀን ውሎ
ቢሮጥ ምን ነበረ እኔን አስከትሎ
ብለሽ ተቀይመሽ ልብሽን አትዝጊው
ለበጎ ነው ብለሽ ሁሉንም አስቢው
ደ'ሞም ዱብ እዳ ነው አስጨናቂ ብርቱ
አውሬ ሲያጋጥመው ሳያስብ ከፊቱ
ሊሆን ደ'ሞ ይችላል የደፈጣ ስልቱ
ይህን አውሬ ፍጡር ሊያቆስለው በብርቱ
ብለሽ አስቢና አፍቅሪው ካ'ንጀትሽ
ታድያ ምኑ ላይ ነው ሩሩ ሴትነትሽ
ውቢት........
ምን አልባት . . .ምን አልባት . . .
የወሬ ነጋሪ ጭራሽ እንዳይጠፋ
ይሆናል መሮጡ ሳይነግር ከፊትሽ
ሲያወራው ለመኖር ዝነኛውን ፍቅርሽ፡

🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘
#ፍቅር_እንደ ...

የሻማ መብራት ነው
ፍቅር እያልኩሽ
አንቺ ግን የአምፖል ነው
ብለሽ ተቆጣሽ
ቁጣሽን በመፍራት
ድንገት ተጨንቄ
ከመቅረዝ ላየሁት
እኔስ ምን አውቄ
አፍታ እንኳ ሳንቆይ
ሳይጠፋ መብራት
ጨለማ ተዋጥን
አላፊው አግዳሚው እፍ እፍ እንዳሉት፡፡

🔘ፋሲል ሃይሉ🔘
#ፍቅር_አያሸንፍም

ህፃን
ልጅ
አዋቂው
ወጣት ሽማግሌው ፥ ረጋሚ መራቂው
በአንደበቱ ማህፀን
ፍቅር ያሸንፋል”
የሚል ጥቅስ አርግዞ ፥ በምላስ ይወልዳል
ፍቅር ግን ሁል ጊዜ
እየተሸነፈ ፣ መሸነፍ ይወዳል።

አቅመ ቢስ ነው አቅሙ ፥ ወዋረድ ነው ልኩ
ሁሌም መሽነፍ ነው
ሁልጊዜ መውደቅ ነው ፥ የፍቅር ታሪኩ።
ርሐብተኛ ነው
አይበላም አይጠጣም ፣ ንብረት አያፈራም
አይደፍርም አይፈራም
አይጠፋም አይሰራም
ፎቅ አይደረድርም ፥ ቪላ ቤት አይሰራም
ማደሪያው በረት ነው ፥ ሲታይ ስጋ ለብሶ
ባሪያ ነው አንግሶ
ሁሌም ዝቅ ያለ ነው ፥ ከፍታ ላይ ደርሶ።

ፍቅር ይሸነፋል!
መንገድ ምራን ላሉት ፥ መንገድ ሆኖ ያርፋል
ሁሉ ይረግጠዋል
መልኮት ኋይል አለው ፥ በሰው ይገረፋል
በሰማይ ሲሾሙት ፥ ወደምድር ይጠፋል
አንድ ሀገር የለውም
የትም ቦታ አለ ፥ እየተሰደደ
ሁሌ እንደተገፋ ፥ እንደተዋረደ
ዝቅ ይሎ ይኖራል
ዝቅ ብሎ ያድራል
ቃል አይናገርም ፥ ስንጥለው ጠልፈን
እርቃን ስናስቀረው
ልብሱን ከአደባባይ ፥ ከገላው ላይ ገፍፈን
ፀሐይ ላይ ተጥደን
ውርጭ ስናስመታው ፥ ስናለብሰው ቆፈን
ከሀገር ስናስወጣው ፥ ካንጀት ተፀይፈን
ጥለነው ስንሔድ ፥ ስናገኘው አልፈን
ትንፋሽ አይወጣውም
ለሁሉ መንገድ ነው ፥ መሔጃ የለውም።
ሁሉን ይከተላል
ለሁሉ ዝቅ ይላል
እረኛ ሲያደርጉት ፥ በግ መሆን ይመርጣል
ዘጠና ዘጠኝ በግ
ሜዳ ላይ በትኖ
አንድ የጠፋ በጉን ፥ ፍለጋ ይወጣል
አይቀድም ይሮጣል
አይሸሽም ያመልጣል
አይተኛም ያደፍጣል
ሲሰድቡት ቃል ያጣል
ቃል ሆኖ ይመጣል
ህያው ነው ስንለው
መቃብር ይወርዳል ፥ በሙታን ተገድሎ
ይነሳል ሲቀብሩት ፥ ከሞት ተነጥሎ
ባሪያ ነው ለሁሉ
መንግስቱን የሚያወርስ ፥ ከምንዱባን ውሎ።

አቅሙ አቅመ ቢስ ነው ፥ ሽንፈት ነው እድሉ
ወርዶ መገኘት ነው
ማጎንበስ ነው እጣው ፥ መረታት ነው ውሉ
ዝቅ ብሎ መኖር ነው ፥ እቅድና አቅሉ
ዝም ነው ስንገርፈው
ዝም ነው ስንዘልፈው
ጭጭ ነው ስንጠልፈው
ቃላት አይወጣም
ራሱ ግን ቃል ነው ፥ የቃሉ እስረኛ
ፍቅር ሲሸነፍ ነው
ፍቅር ያሸነፈ ፥ የሚመስለን ለኛ!

ያንሳል ስናገዝፈው
ቀድሞ ይጠብቃል ፥ ትተነው ስናልፈው
እየተሸነፈ
በመሸነፉ ነው ፣ ፍቅር ያሸነፈው።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘
#ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር

ያሳለፍነዉ ሁሉ
አሁን ትዝታ እንጂ
ዉስጡ ህይወት የለም እያልሽ ላገሩ
ታወሪያለሽ አሉ


(እኔ ግን ልንገርሽ)
የሁለታችን ፍቅር
ምን እንደሚመስል. . .
እንዴት እንደነበር
በሶስት ምስክር
1
አሁን በቀደም ለት
የሆነ ቦታ ላይ
ድምጻችን ከፍ አርገን የሳቅንበት ቦታ
ፒያሳ አደባባይ
ድንገት
በቀደም ለት
በዛ ቦታ ስሄድ
ከሰባት ወር በፊት
ስቀሽ የነበረዉ
ያንቺ ሳቅ ተሰማኝ
መራመድ አቃተኝ
የሚገርምሽ ነገር
ያለፈ ነዉ ያልሺዉ
ትዝታ ነዉ ያልሽዉ
ፍቅርሽና ሳቅሽ
ከሰባት ወር ኋላ እንደ ወንዝ ፍሳሽ
ይሰማል ልንገርሽ

(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
የወንዝ ዉሀ ሳቅሽ
ያለፈ ትዝታ ምናምን ነዉ ብሎ
ማንም ተራ ዘፋኝ የሚሸነግልሽ
(ይልቅ እኔን ስሚኝ)

ወደየትም ሳይሆን
ወዴትም ተመለሽ
የትም ሳትደርሺ
ጊዜን እንዳቆምነዉ
እንኳን ጊዜ ቀርቶ ሰዓት እንዳልሄደ
ደቂቃ እንዳልሄደ
አስረጂ ሊሆንሽ
ምስክር ሊሆንሽ
ከምንም አቅጣጫ. . . የትም ሳትመለሽ
አደባባይ መሀል
ከቡና ጠረን ጋር
እንደወንዝ የሚፈስ
ሳቅሽን ትሰሚያለሽ

2
ትዝ ይልሽ እንደሆን
ካንቺ መኖሪያ ቤት
(የመጣሁኝ ጊዜ)
የመራራቅ ናፍቆት
አስክሮን ቸኩለን
ሰማያት ለመዝለቅ
ከመሬት ላይ ወድቀን
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ከሴት ወዝሽ ጋራ
የጡትሽ ስር ሽቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ምወደዉን ሸሚዝ
ለመልበስ እርም አልኩኝ
ለብሼዉ እንዳልሄድ
ከበደኝ ጨነቀኝ
ያንቺን ጠረን ማጠብ. . .
ነፍስ የማጥፋት ያህል
ሀጥያት መስሎ ታየኝ
(የሚገርምሽ ነገር)
እስከ ዛሬ ድረስ
በመስኮቱ ዘልቆ. . .በበሬ
የሚወጣዉ የማለዳዉ ነፋስ
በሽቶሽ ጠረን ነዉ መንደሩን የሚብስ

3
ታስታዉሽ እንደሆን
የሆነ ቅዳሜ
የሆነ ዉብ ሆቴል
ደግሞም አትረሺዉም. . .ፍጻሜ ምሳ ነዉ
ይኼ እንኳን ትዝ ይላል
እና. . .
እኔና አንቺ ብቻ
የተቀመጥንበት ወንበር ጠረጴዛዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ. . .
እዛዉ ቤት ዳግመኛ ተመልሼ ባየዉ
የሚገርምሽ ነገር
ጻፊዉን ባላዉቅም
#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር
የሚል ጽሁፍ ሰቅለዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ
አንድ ለብቻዬ ካንድ አንቺ ናፍቆት ጋር
ነበር ለምትይዉ ለሁለታችን ፍቅር
(ምስክር ሊሆኑን)
ያኔ ሁለታችን የጠጣነዉ ወይን
ከወይንም. . . Two Ocean
እኔ የጨለጥኩት
አንቺ ያጋመስሽዉ
እኛ ያስተረፍነዉ
እስከዛሬ ድረስ
ያተረፍነዉ ማዕድ. . .
ጠርሙስና ጽዋዉ
በክብር ተቀምጧል
ማንም ሳያነሳዉ. . .ያኔ እንደነበረዉ
(ታዲያ ምን ማለት ነዉ)



ፒያሳ አደባባይ
የወንዝ ዉሃ ሳቅሽ
ከቡና ጠረን ጋ
ከኔ መኖሪያ ቤት. . .
የምወደዉ ሸሚዝ ላይ
የሽቶ መአዛሽ
ከሴት ላቦትሽ ጋር
ደግሞም
እዚያ ዉብ ሆቴል ስር
ያስተረፍነዉ . . .
ማዕድ ጠርሙስና ጽዋ
አንጀት ከሚበላ
ከቆንጆ ጥቅስ ጋር
‘’#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር::’’

ነበርን እስካሁን
በመሆን እያየሽ
ሳቅሽ ፈሶ ሳያልቅ
ከምወደዉ ሸሚዝ
የሽቶ መዓዛሽ ዉብ ጠረኑ ሳይለቅ
ማዕድ ሳይነሳ ጽዋዉ ሳይታጠብ
ሦሥቱን ምስክሮች በዓይንሽ ፊት እያየሽ
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
ያሳለፍነዉ ሁሉ
"አሁን ትዝታ እንጂ .....
ዉስጡ ህይወት የለም"
ብለሽ ለመንደሩ
ላገሩ ማዉራትሽ
እዉነት ለምንድን ነዉ?




ኤፍሬም ስዩም
(ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር)
😱1
#ፍቅር_ይዞኝ_እንጂ

መች አስቤው እንደ ሥራ
መች ቆጥሬው እንደ እንጀራ
ጭው ባለው በረሃ ውስጥ
መንከራተቴ ያለ እፎይታ
ቀጥ ባለው ተራራ ላይ
ላቤን ማፍሰሴ ጠዋት ማታ
መች አስቤው እንደ ስራ
መች ቆጥሬው እንደ እንጀራ
የልጆቼ ዓይን በዓይኔ ላይ
ያለ እረፍት ሲመላለስ
ልቻለው ከሃገሬ አይበልጡም
እያልኩኝ የምንከላወስ
ዘመን በዘመን ሲቀየር
በዓል አውድ ዓመት ሲመጣ
ለእንጀራዬ ብዬ ነው እንዴ
ከበረሃ የማልወጣ?
ከዘመድ አዝማድ የማልበላ
ከአብሮ አደጎቼ የማልጠጣ
የያዘ ይዞኝ እንጂ
የሀገር
ፍቅር----- የሚሉት ልክፍት
እኔ ሁለት ሆድ የለኝ
እስክሞት የሚንከራትት
መች አስቤው እንደ ሥራ
መች ቆጥሬው እንደ እንጀራ
ላቤ በጀርባዬ ላይ
የጨው አምድ መስሎ እስኪታይ
ከእረፍት ከእንቅልፍ ተፋትቼ
የማጣው የቅጽበት ፋታ
ቀናትን በእግሬ የምኳትን
ጫማዬን ከእግሬ ሳልፈታ
ለእንጀራዬ ብዬ ነው እንዴ
ቀዝቃዛ ውሃ እየናፈቀኝ
ትኩስ መመገብ እያማረኝ
ጨዋማ ውሃ እየጠጣሁ
በድካም ጨው የሚያልበኝ
ለእጀራዬ ብዬ አይደለም
ርቄ ከመሃል ማዶ
በቀበሮ ጉድጓድ ሆኜ
ምሰማው የናቴን መርዶ
ለእንጀራዬ ብዬ አይደለም
በእህቴ ሰርግ የማልገኝ
በወንድሜ ህመም የማልመጣ
ከሃገሬ አስተሳስሮኝ እንጂ
ወታደር የመሆኔ እጣ
ለእንጀራዬ ብዬ አይደለም
የምቃጠል በበረሃ
የሚያነደኝ ቦምብ ፈንጂ
ቃልኪዳኔ ከሆነችው
ከሀገሬ
ፍቅር ይዞኝ እንጂ

🔘ሻለቃ ወይን ሐረግ በቀለ🔘
#ፍቅር_ከራስ_ያልፋል

በሕይወት ጎዳና ዕጣ ሲደለደል
ላንዱ ሜዳ ሆኖ ለሌላኛው ገደል
ግማሽ ግራ ገብቶት የቀረው ሲበደል
እኔ ዝምተኛው ካንቺ ሆንኩኝ አይደል?
ምርቃቱ ደርሶ ፍቅር ያጠመቀኝ
በየትኛው ዘመን ማነው የመረቀኝ?
በሚሆነው ሁሉ
ግራ ለተጋባው ለዚህ #ላገሬም_ሰው
ከማይሆነው መንገድ ይዞ እንዲመልሰው
መርቆ ሰምሮለት ፍቅር እንዲዳብሰው
ባወኩት ባወኩት ባወኩት ያንን ሰው።

🔘ሰለሞን ሀይሌ🔘
👍13
#ፍቅር_ከራስ_ያልፋል

በሕይወት ጎዳና ዕጣ ሲደለደል
ላንዱ ሜዳ ሆኖ ለሌላኛው ገደል
ግማሽ ግራ ገብቶት የቀረው ሲበደል
እኔ ዝምተኛው ካንቺ ሆንኩኝ አይደል?
ምርቃቱ ደርሶ ፍቅር ያጠመቀኝ
በየትኛው ዘመን ማነው የመረቀኝ?
በሚሆነው ሁሉ
ግራ ለተጋባው ለዚህ ላገሬም ሰው
ከማይሆነው መንገድ ይዞ እንዲመልሰው
መርቆ ሰምሮለት ፍቅር እንዲዳብሰው
ባወኩት ባወኩት ባወኩት ያንን ሰው

🔘ሰለሞን ሳህለ🔘
👍96👏2
#ፍቅር_የመሸባት_ሀገር


እዛ ሰው ይሞታል፣ እዛ ደም ይፈሳል
እዚህ ይጨፈራል ፣ እዚህ ይደነሳል
እዛ ሰው ያለቅሳል፣እዚህ ሳቅ ይነግሳል።
፨፨፨
እዛም እኛዎች ነን፣አዚም እኛ ባዮች
የደላን እኛው ነን ፣ እኛው ተበዳዮች
አንድነትን ሰብከን፣የምንሆን ብዙዎች፡፡
እኛው ነን የሞትነው፣እኛው ነን ቀባሪ
እኛው ነን ሙሾ አውራጅ፣እኛው ነን ጨፋሪ
አንድ ነን እያልን ፣ ልዩነት ፈጣሪ፡፡
፨፨
እዛ እኛ ስንሞት፣ እዚ እኛ ስንጨፍር
እዛ እኛን ስንቀንስ፣እዚ እኛን ስንደምር
ሙሾን ከደስታ ጋር የምንደባልቀው
እኛው እያነባን ፣ እኛው የምንስቀው
እኛው ለነፃነት ፣ ታግለን የምናልቀው
እኛው ባርነትን፣ፈቅደን የምንሞቀው
እዚ እየረሳን ፣ እዛ ም'ናፍቀው
ፍቅር መሽቶብን ነው፡፡
፨፨
እንዲህ ነው ሚኖረው....
ፍቅር የመሸበት፣ሀቅ ያልገባው ሀገር
እዛ እኛ ሙሾ አውራጅ ፣ እኛ አዚ ምንጨፍር፡፡

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
😢20👍11👏43🔥2
#ፍቅር_ሙጀሌ

እየነዘነዘ እንቅልፍ ቢነሳም ፣
ንክሻ ፣ ስቃዩ ፣ረብሻው ይጥማል፣
ፍቅር ሙጀሌ ነው፣
በትዝታ ጥፍር ሲያኩት ደስ ደስ ይላል።

🔘ኑረዲን ዒሳ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose
👍84😁4