አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሠላሳ_ሁለት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ቃል ቤት የተፈጠረው ድራማ ወር አልፎታል….በዚህ የጊዜ ክፍት ውስጥ መአት ነገሮች ተከስተዋል.ልዩ ትምህርቷን ተመርቃ ዲገግሪዋን ይዛለች…በምረቃት ፕሮግራሟ ላይ ቃል መድሀኔና ጊፍቲም ጭምር ተገኝተው ደስታዋ ተካፋይ ሆነዋል.እርግጥ ነገሩ ቀላል አልነበረም፤ በተለይ የልዩ እናት መድሀኔን ዝግጅቱ ላይ ሲመለከቱት ንዴታቸውን መቆጣጠር አቅቶቸው እንዴት ተደርጎ በማለት ሂድልኝ ሊሉት ፈልገው ነበር ፤በልዩ ግሳፄ ነው እንደምንም እራሳቸውን ተቆጣጥረው ሊያልፉት የቻሉት…፡፡በወቅቱ ልዩ ቃልን ከእናቷ ጋር ማስተዋወቅ ስለቻለች ከፍተኛ ደስታ ተስምቶታል…፡፡ሌላው ልዩና ቃል አንድ ላይ በመተጋገዝ    መድህኔ እና ጊፍቲ አብረው እንዲቀጥሉ ማድረግ ችለዋል፡፡መድሀኔም እንደምንም እቤተሰቦቹን በማሳመን የጊፍቲ ሆድ ከመግፋቱ በፊት በቅርብ ለመጋባት ወስነው ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ለእነልዩ ነግረዋቸዋል፡፡እንደውም የጊፍቲ አንደኛ ሚዜ ልዩ የመድሀኔ ደግሞ ቃል ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጥተዋቸዋል፡፡ ያው ጓደኝነታቸውም ቃል በሚፈልገው መሰረት እንደድሮ ቀጥሏል‹‹..አሁን ይሄ ታሪክ ሙሉ ሊሆን የቀረው አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡የእኔና የቃል ጉዳይ..እሱንም ጠብቁኝ በቅርብ ይሆናል….እስከአሁን እኔ አስቤ ያላሳከሁት ነገር የለም፡፡››ስትል ዛተች
ቀኑ ቅዳሜ  ነው...ከቃል  ጋር   ለመገናኘት ተቀጣጥረው ነበር።
እሱ ወደሚገኝበት ቦታ እየነዳች ስለእሱ በማሰብ ትለፈልፋለች…ብቻዋን ስትለፈልፍ ለሚመለካተታ እግረኛ ከኃላ የመኪናው ወንበር ላይ  ተኝቶ የሚያዳምጣት ሰው አለ ብሎ ነው የሚያስበው
‹‹ቆንጆ ነው።ቆንጆ የሚጠላ ሰው የለም። ግን ከስጋው ቁንጅና ይልቅ በነፍስ ቁንጅና ነው ቀድሜ እጅ ሰጠሁት ።እርግጥ የነፍስ ውበትን ልክ እንደስጋ ውበት በቀላሉ  ለመለየት አይቻልም። ድብቅና ስውር ነው።መረጋጋትና በአስተውሎት መገምገምን ይጠይቃል። ውስጣዊ ስለሆነ በውስጣዊ አይን ብቻ ነው ሊታይና  ሊረጋገጥ የሚችለው።እሱን በተመለከተ ግን የውጭ ውበቱን ዘግይቼ ና ተረጋግቼ ነው ያየሁት።ቀድሞ ውስጤ የሠረገው የነፍሱ ውበት ነው። ያሽመደመደኝ ሰባአዊነቱና የተሞረደ አስተሳሰብ ነው።እንደእሱ አይነት ሰው ይኖራል ብዬ አስቤ አላውቅም።መኖሩን ካወቅኩም በኃላ የእኔ ሰው መሆን አለበት ብዬ ቀን ከሌት ከመቃዠት ውጭ ሌላ ምንም አይነት የስጋም ሆነ የነፍስ ስራ የለኝም፡፡ ››
የተቃጠሩበት ቦታ ለመድረስ ከአንድ ፌርማታ በታች ሲቀራት መኪናዋ ድንገት  ተበለሸባት፡፡እቤት ደወለችና ነገረቻቸው..ሌላ መኪና አምጥተው እስኪቀይሩላት መኪዋን ቆላለፈችና .በእግር ቃል ወደሚገኝበት ቦታ በእግሯ ወክ በማድረግ ሄዳ አገኘችው‹‹ ምሳ  ልጋብዝህ ብላው እዛው አካባቢ አንድ ሬስቶራንት ይዛው ገባች..።እሷ ቁርስ ስላልበላች በጣም እርቧታል..እሱ ይራበው አይራበው አታውቅም።ግን ከረሀቡም በላይ የእሷ ዋና አላማ ከእሱ ጋር የምታሳልፈው ጊዜ በሰበብ አስባብ ማስረዘም ነው።
ፊት ለፊት ተፋጠው ተቀመጠዋል ..የየምርጫችውን አዘዙ ።  ሰዓቱ ስድስት ሰዓት ያልሞላ ቢሆንም በሬስቶራንቱ ውስጥ ያሉት ተስተናጋጆች እነሱ ብቻ አይደለሉም።ቢያንስ 30 ፐርሰንት የሚሆነው ወንበር በጥንድም ነጠላም ሆነው በተቀመጡ ሰዎች ተይዞል።
ከተወሰነ ጥበቃ በኃላ ምግባቸው ቀርበ፡፡
እሷ ለመገብ እጇን ወደምግቧ በመዘርጋ ላይ እያለች ቃል  አንገቱን ለፀሎት ሲያቀረቅር አየችና በእፍረት በአየር ላይ ያንከረፈችውን እጆን ቀስ ብላ ወደሃላ ሳበችውና እሷም በተመሳሳይ አንገቷን ደፋች፡፡
እሱ ፀሎቱን ለእሷ በሚሰማ ነገር ግን ሌሎችን በማይረብሽ የተለሳለሰ ድምፅ ቀጠለ
‹‹እነዚህን የምግብ ግብአቶች ዘርተው ያበቀሉ ተንከባክበው ለፍሬ ያበቁ የገበሬ እጆች የተባረኩ ይሁኑ።የተመረቱትን ግብአቶች ከገበሬው በመግዛት ያለንበት ድረስ በማምጣት የሸጡልን ነጋዴዎች ምስጋናችን ይድረሳቸው።ይሄን እንጀራ ለማስገኘት ጤፍን ወደ ድቄትነት የቀየሩልን የወፍጮ ቤት ባለቤቶችና ሰራተኞች ባሉበት ምስጋናችን ይድረሳቸው ፤ ድቄቱን አብኩታና  ጋግራ ይሄን የመሠለ ማራኪ እንጀራ እንድንቆርስ ላደረገችን እንጀራ ጋጋሪዎ እመቤት እናመሠግናለን።ይሄንን መአዳችን ላይ የቀረበልንን ሚስጥራዊ ውሀ  እንድናገኝ  ኃላፊነታቸውን በበጎነት ለተወጡ የውሀ ልማት ባለሞያዎች እናመሠግናለን።ይሄንን ምግብ በግሩም ሁኔታ እንዲበስል የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲኖር ላደረጋችሁልን የማብራት ሀይል ሰራተኛች እናመሠግናለን።በቀን ውስጥ ስለተደረገልን ሁሉ አናመሰግናለን፡፡››
ብሎ የተለመደ ገራሚ አይነት ፀሎቱን ካንበለበለ በኃላ የቀረበላቸውን መመገብ ጀመሩ

አልፎ አልፎ እያወሩ በመሀልም እየተጓራረሱ በመብላት ላይ ናቸው ።የእሷ አይኖቸ ግን በመሀል ሳትፈልግ ከጎናችው አንድ ወንበር ተሻግሮ ከሴት ጋር ካለው ጎልማሳ ሰው ላይ ይንከራተት ጀመር ‹‹..አሁን ፊት ለፊቴ ያለው ሰው ቃል ባይሆን  ግንባሬን ብሎ በተቀመጥኩበት ጎልቶኝ ይሄድ ነበር?››ስትል አሰበች፡፡
ቢሆንም ግን እራሷን መግታት አልቻለችም፡፡እርግጥ ችግሯ ሰውዬው አይደለም  …፡፡ከጣቱ ወርቅ አውልቆ ኪስ ወስጥ ሲከት አይታ ነው...፡፡ሰውዬው እንደዛ  ያደረገው አብራው ያለችው  ሴት ወደ ጠረጰዛው መጥታ ከፊት ለፊቱ ከመቀመጧ በፊት ነው።ወርቁን ከእጣቱ በችኮላ መንጭቆ በማውለቅ ጃኬት ኪስ ውስጥ  እንደነገሩ    ሻጥ ስላደረገው  በተንቀሳቀሰ ቁጥር  አይኗ ላይ በማብረቅረቅ  እየተፈታተናት ስለሆነ ነው...አስሬ   አይኗ ወደእሱ አየቀባዠረ  የምትቅበጠበጠው።ለጥንዶቹ ምግብ ሲቀርብላቸው ሰውዬው  ሊታጠብ ቀድሞ  ከተቀመጠበት ተነሳና ወደ መታጠቢያ ቤት አመራ..
ልዩም ምንም ሳትናገር ድንገት ከተቀመጠችበት ተነሳችና ምግብ ስትበላበት የነበረ እጇን እንዳንከረፈፈች ከኃላው ተከተለችው... መታጠቢያ ቤት ገብቶ እጅን ሲታጠብ ከአጠገብ ያለው መታጠቢያ ስር ቆመችና ለመታጠብ እጇን ዘረጋች...ታጥቦ ጨርሷ ለመውጣት ሲራመድ እሷም መታጠቧን አቁማ ለመዞር የፈለገች መስላ ተጋጨችው...ቀድሞ ይቅርታ ጠየቃት‹‹...ችግር የለውም› ብላ አሳለፈችው...አንድ አስር እርምጃ ከተራመደ በኃላ ጠበቃችና ከኃላ ተከተለችው።ስትደርስ ወንበሩ ላይ ተደላድሎ ተቀምጦ አብራው ያላቸውን ሴት ለማጉረስ እጅን እየዘረጋ ነበር ...በፊት ለፊታቸው አልፋ ወደ ወንበሯ ሄደችና  ተቀመጠች...ምግብና ሳትጠግብ ያቆመች ቢሆንም መልሳ መብላት መጀመር አልቻለችም ..እጇን ከታጠበቸ በኃላ እንዴት ብላ እጇን ትዘርጋ?

ቃል በዝምታ አቀርቅሮ ምግብን እየተመገበ ነው...ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ሳያያት"ምነው ብይ እንጂ ››አላት፡
"አረ ጠገብኩ እኳ ...ታጥቤ ስመጣ እያየሀኝ"
"ከጠገብሽ ጥሩ ነው...እስከአሁን በልተሽ የጠገብሽው ለራስሽ ነው..ቀጥሎ ደግሞ ለእኔ ብይልኝ"አላት፡፡
አባባሉ ግራ አጋባት"እውነትህን ነው?"
"አዎ እውነቴን ነው"አለ ኮስተር ብሎ።
"እንዲህ ብለኸኝማ  እምቢ አልልህም"አለችና እንደአዲስ መብላት ጀመረች።
ምግባቸውን ጨርሰው፤ እጃቸውን ታጥበው ፤  ብና አዘው እየጠጡ ነው። ምንም እያወራት አይደለም ።ሁለቱም የራሳቸው ሀሳብ እያመነዠጉ ነው።ከጎናቸው ያሉት ጥንዶች የሚበሉትን ጨረሱና ለመታጠብ ሴቲቱ ቀድማ ወደመታጠቢያ ቤት ሄደች ...እሱ ቁጭ ካለበት ሳይነሳ ፊቱ ያለውን የቢራ ጠርሙስ እያነሳ እየተጎነጨ ነው...
👍786😁4
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
///

ቀለበቱን ከቀረቀረችበት ኪሷ አወጣችና ቀጥታ በድፍረት ወደሰውዬው ጠረጰዛ በመሄድ ፊቱ ቅጭልጭል አድርጌ ስታስቀምጥለት አንዴ ቀለበቱን አንዴ ደግሞ እሷን አንዴ ደግሞ ሴትዬዋ ወደሄደችበት መታጠቢያ ቤት እያፈራረቀ ሲያይ ቆየና እጅን ወደ ኪሱ ሰዶ ፈተሸ..
"አልገባኝም ከየት አገኘሽው?"ሲል ጠየቃት፡፡
"ቅድም መታጠቢያ ቤት ስንጋጭ መሠለኝ ከኪስህ የወደቀው...ከወለሉ ላይ ነው ያገኘሁት...ወዲያው አምጥቼ እንዳልሰጥህ ሴትዬህን ፈራሁ…አልተሳሳትኩም ያንተ ነው አይደል?።››
"አዎ የእኔ ነው ..አመሠግናለሁ..ሲወድቅ ግን እንዴት ድምፅ ሳልሰማ?"
"ምን አልባት ቀልብህ ሴትዬህ ላይ ስለሆነ ይሆናል"አለችውና የእሱን መልስ ሳትጠብቅ ወደ ወንበራ ተመለሰች።
ልዩ በእፍረት እንደተሸማቀቀች ከእዛ ሆቴል ተያይዘው ወጡ …ከቤት ሌላ መኪና ተልኳላት ስለነበረ ቀጥታ ምንም ሳይነጋገሩ በራሷ ፍቃድ ወደእራሱ ቤት ይዛው ሄደች፡፡ ….ከዛ ሁለቱም እሱ አልጋ ላይ በመሀከላቸው መተው ያለበትን ክፍተት አስጠብቀው ጋደም በማለት ማውራት ጀመሩ….እርግጥ እራሷ ነች እንዲያወሩ የመጀመሪያውን የመነሻ ጥያቄ የጠየቀችው….
‹‹ግን ከሌባ ጋር ጎደኛ መሆን አልደበረህም?››ዝም ብላ በውስጧ ስታብሰለስል የቆየችውን ጥያቄ ድንገት የጠየቀችው፡፡
"ሰው ሁሉ እኮ ሌባ ነው"አለት

ገርሟት"እንዴት ማለት?"ስትል ጠየቀችው፡፡

"በየቀኑ አንዳችን የአንዳችንን የህይወት ኃይል ስንዘርፍ ወይንም አስገድደን ስንቀማ ነው የምንውለው"

"አሁንም አልገባኝም"

"እኔ አሁን ብጮህብሽ ባመናጭቅሽ አንቺ መላ አካልሽ ሽምቅቅ ይላል ፤ ሰውነትሽ ይንቀጠቀጣል፤እኔ ጩኸቴንና ስድቤን እየቀጠልኩ ስመጣ አንቺ እየተሸማቀቅሽ በራስ የመተማመንሽ እየወረደ ይመጣል ..ያ ማለት ኃይልሽን እየመጠጥኩና አንቺን ባዶ እያደረኩሽ ነው ማለት ነው…ከዛ ደካማና ሽቁጥቁጥ በማድረግ እኔ በራስ መተማመኔን አሳድጋለሁ ማለት ነው..አየሽ ታዲያ ይሄ እንደውም ረቂቅ ሌብነት ነው፡፡ ››
‹‹እና እቤት ሰራተኞች ላይ ስጮህና ሳንቧርቅባቸው….ሲሸማቀቁና ሲሽቆጠቆጡ..ኃይላቸውን እየሰረቅኩባቸው መሆኑ ነው፡፡››

‹‹አዎ ለዛውም የህይወት ኃይላቸውን…ሰው ተበሳጭቶ ተበሳጭቶ በመጨረሻ ምንድነው የሚሆነው..?ለመኖር ያለውን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ያጣል…፡፡ ያ ማለት ምን ማለት መሰለሽ...ለመኖር የሚያስፈልገው ኃይል ውስጡ የለም ማለት ነው….የት ሄደ…. በዙሪያው ባሉ በተለያዩ ሰዎች ቀስ በቀስ እየተዘረፈ እንዲሞጠጥ ተደርጎል ማለት ነው….እና ትልቁ ሌብነት የሰውን የውስጥ ሰላም ማሳጣት ነው፡፡››

‹‹እና አንተ ለዛ ነው…ለሰው አስተያየት በምትሰጥበት ጊዜ ስሜትህን አብዝተህ ለመቆጣጠር የምትጥረው…?››

‹‹አዎ በተቻለኝ መጠን ከማንም ጋር ቢሆን ሰላማዊ የሆነ፤ከጭቀቅጭቅ የፀዳ፤በቁጣ ያልታጀበ ..በእኩልነት ላይ የተመሰረት ንግግር ማድረግ ነው ምፈልገው..እንደዛ ሲሆን ማለቴ አሁን እኔና አንቺ በጓደኝነት መንፈስ ጎን ለጎን ተቀምጠን ፍትሀዊ በሆነ በእኩልነት ሚዛን ሀሳብ ስንለዋወጥ ኃይልም እንደዛው ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ እየተለዋወጥን ነው....ማለት ከእኔ ኃይል ወደአንቺ ይሄዳልም መልሶ ወደእኔ ይመጣልም …..የሁለታችንም ኃይል በእኩልነት እያደገ ደስተኛና ጤነኛ እየሆንን እንመጣለን..እና አንቺም ሁል ጊዜ ከሰዎች ጋር ያለሽ ግንኙነት እንደዛ እንዲሆን እንድታደርጊ ነው የምፈልገው፡፡››

‹‹እሞክራለሁ..ብቻ በውስጤ ያለውን ክፉ አመል በሆነ አስማታዊ ጨረር የሚያጠፋልኝ የሆነ መላአክ ቢኖር በህይወቴ የተከማቸውን ሀጥያት አንዴ ጥርግርግ አድርጌ በማፅዳት ንጽህ የሆነ ኑሮ ነበር መኖር ምኜቴ ››አለችው…የተናገረቸው ከአንጀቷ ነው…ልክ እንደእሱ አይነት ሰው መሆን ነው የምትፈልገው…

‹‹አይዞሽ.አንቺ ብቻ ከዚህ በፊትም እንደነገርኩሽ እራስሽን ለማከም ዝግጁ ሁኚ.. የልጅነትሽ ወይም የታዳጊነት የህይወት ክፍልሽ ላይ መድሀኒቱ ቁጭ ብሎ እንደሚጠብቅሽ ይሰማኛል….ከአባትሽ ጋር ያለሽ ግንኙነት እሱን በማጣትሽ የተፈጠረብሽ የስነልቦና ክፍተት፤ከእናትሽ ጋር የነበረሽ ግንኙነት…ብቻ በደንብ አስተውለሽ አሰላስይ….ከታሪክሽ የሆነ ጥግ ለምን የስርቆት ልክፍት እንደተፀናወተሸ የሚያስረዳ ምክንያት ይገለፅልሽ ይሆናል...ከዛ ዟምክንያቱን ባወቅሽ ቀን የበሸታሽ መርዝም በራሱ ይከስማል..ትድኛለሽ፡
አይን አይኑን በስስትና በአድናቆት እያየችው፡‹‹እንደቃልህ ይሁንልኝ››አለችው ፡፡
እና በሀሳብ ቁዝዝ አለች‹‹.አሁን እኔ ቃልዬ አንተን በጣም አፈቅርሀለሁ..ካየሁህ ቀንና ሰዓት ጀምሮ አንተን ከማለም ውጭ ሌላ ሀሳብ የለኝም ..ስለዚህ ምንም እንኳን ሴት ብሆንም በድፈረት እንድታገባኝ እየጠየቅኩህ ነውሪ’ዩ ››ልትለው ነው የምትፈልገው …ግን እነዛን ቃላቶች ከአንደበቷ አላቃ ማውጣት በድፍረት ለመጠየቅ ትልቅ እንቅፋት የሆናት እሱ በግልፅ ሚያውቀውን ድክመቷና ደግሞም በየሰው ቤት ካሜራ እየተከለች የሰው ሚስጥር የማነፍነፍ ክፍ በሽታዋ ምክንያት ነው፡፡

ቃል ‹‹.ትንሽ እንተኛ እንቅልፌ መጣ›አለና ወደእሷ በመዞር እጁን ተከሻዋ ላይ ጣል አድርጎ በማቀፍ አይኑን ጨፈነ…..እሷም በተመሳሳይ ወደእሱ ዞረችና እጅን በትከሻው ላይ አዙራ አቀፈችውና ልክ እሱ እንዳደረገው አይኖቾን ጨፈነች…..ለመተኛት ፈልጋ ወይም እንቅልፍ ተጫጭኗት አይደለም…ፈፅሞ የእንቅልፍ ስሜት የለባትም…እፍረቱ እስከአሁን በደም ስራ እየተሰራጨ ነው..እና ደግሞ የመከራትም ነገር እያብሰለሰለችበትም ነው…

አባቷን ፍለጋ መንቀሳቀስ እንዳለባት ሰሞኑን ወስናለች፡፡ከዚህ በሽታዋ ለመፈወስ ምትችለው ሁለት ነገር ሳታደርግ እንደሆነ ሰሞንኑ ባደረገችው ማሰላለሰል ውሳኔ ላይ ደርሳለች፣..እንደኛው ከቃል ጋር ያለላትን ግንኙነት የሆነ መስመር ማስያዝ ስትችል..ከዛ ቀጥሎ አባቷን ፍለጋ መሰማራት ..ከዛ አባቷን በህይወት ካገኘችት ጥሩ ነው ፤ብዙ ጥያቄዎቼን ይመልስላታል..ቃል እንደሚለውም ምን አልባት የበሽታዋ መድሀኒት ከአባቷ መገኘት ጋር የተሳሰረ ሊሆን ይችላል……ስትል እምነት አድሮባታል..ሞቶም ከሆን የተንጠለጠለች ነፍሷ እርፍ ትልና ስለእሱ ማሰብ ታቆማለች፡፡

የቃልን ጉዳይ በቅርብ መቋጫ ልታበጅለት እንደሚገባ ተሰማት ‹‹….እንደውም ዝም ብዬ ከዛሬ ነገ እያልኩ ባንዛዛሁት ቁጥር ዛሬ እንደሰራሁት አይነት ሌላ ስህተት ፊቱ እሰራና ምንም ነገር ሳይል ከእጄ ሊሾልክብኝና እስከወዲያኛው ላጣው እችላለሁ…እንደውም ነገ ለምን አላደርገውም..አዎ ነገ..››ወሰነች ፡፡ውስጧ የሚጥለቀለቅ ደስታ መሰቃየት ጀመረ….ቃል ነቅቶ እጁን ከላዮ ላይ አነሳ፡፡ ከእንቅልፉ በመባነኑ በጣም ነው ደስ ያላት፡፡ውሳኔ ላይ ከደረሰችበት ደቂቃ ጀምሮ ወደቤት እስክትሄድ ቸኩላለች….ለምን ?ለነገ ለመዘጋጀት….ከአንድ ሰዓት እንቅልፍ በኃላ ሲነሳ ፈጠን ብላ ከአልጋዋ ወረደች፡፡
‹‹ልትሄጂ ነው እንዴ?››
‹‹አዎ እቤት የምሰራው ስራ አለኝ፡፡››
‹‹ልሸኝሽ ታድያ?››አላት.. አልጋውን ለቆ እየተነሳ..
‹‹አይ አልፈልግም…ቃልዬ ነገ ከሰዓት የምትሄድበት ቦታ አለ እንዴ?››ልስልስ ባለ አሳዘኝ ድምፅ ጠየቀችው፡
‹‹አይ ..ምንም ፕሮግራም የለኝም››
‹‹በቃ በጣም ለጥብቅ ጉዳይ እፈልግሀለሁ…ስድስት ሰዓት እዚህ እቤት እመጣለሁ…››
‹‹ከዛ የት ልትወስጂኝ ነው?››
‹‹የትም እዚሁ ነው ምናመሸው..ማለቴ ውለን ምናመሸው…. ነግሬሀለሁ…ስድስትሰ ሰዓት እመጣለሁ..ደግሞ እኔና አንተ ብቻ..ለጥብቅ ጉዳይ ነው የምልግህ››
👍8911🔥1🤩1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

እቤት እንደገባች መኝታ ቤቷን ዘጋችና ትንሽ እረፍት ልትወስድ ፈልጋ ጋደም አለች፡፡ነገ ቃልን እንደምታፈቅረው ልትነግረው በመወሰኗ በውስጧ የተፈጠረባት መረበሽን ተከትሎ ኃይለኛ እራስ ምታት እያንገላታት ነው..እራሷን ለሁለት ከፍሎ ይፈልጣት ጀመር .ከመኝታዋ እንደምንም እየተንገዳደገደች ተነስታ ኮመዲኖዋን ከፈተችና የህመም መስታገሻ መድሀኒት አወጣች ሁለት ፍሬ ወስዳ ወጠች.እንዲሁ መድሀኒቱ የህመም ማስታገሻ ይባላል እንጂ ድንዛዜ ውስጥ የሚከትና የሚያንሳፍፍ  ሀሺሽነት ባህሪ ያለው መድሀኒት ነው..ለአሷ ግን ይመቻታል፡፡መኝታዋ ላይ ተመቻችታ ተኛች፡፡ቀስ በቀስ ደስ የሚል ስሜት እየተሰማት መጣ..ደስ የሚሉ ሀሳቦች የአምሮዋን የፊተኛ ስፍረ መቆጣጠር ጀመሩ…እሷም በደስታ ፈቀደችላቸው..ድንገት የሆነ ቅፅበታዊ መገለጥ አይነት ነገር ሲከሰተ እየታወቃተ ነው...በአእምሮዋ የፊተኛው ሰሌዳ ላይ ብልጭ ድርግም...ብልጭ ድሮግም  ማለት የጀመረው ...አባቷን በአይኖቾ ያየችበት የመጨረሻ ቀን   ጓሮ ከትክልቶች መካለል ገብታ ተደብቃ ነበር..እንደዛ ያደረገችው የሚያማምር ቀለም ያላቸው አበቧች ቀልቧን ስለሳቧት ነበር...አበባ ትወዳለች...ማንም ሳያያት ሹክክ ብላ ገብታ ከየአይነቱ አንዳአንድ አበባ በመቀንጠስ ወደ ክፍሏ ይዛ በመሄድ በዛ እየተጫወቱ መደሰት ተደጋጋሚ ተግባሯ ነበር...የጊቢያቸውን አትክልተኛ የነበሩት አዛውንት ግን በስራዋ አይደሰቱም.. ሁሌ እንደተነጫነጩና ለእናቷ ስሞታ እንዳሰሙ ነበር...እናቷም ልታስቀይማቸው ስለማትፈልግ ፊታቸው ይቆጧትና ዞር ሲሉ ደግሞ የፍላጎቷን እንድታደርግ ያበረታቶት  ነበር...ይህ  የአበባ ፍቅሯ ዛሬም ድረስ ህያው ነው...ከመጨረሻ ጠላቷም ቢሆን የአበባ ስጦታ ከመቀበል ወደኃላ አትልም።

አዎ የመጨረሻዋ ቀን አሁን ጥርት ብሎ እየታያት ነው።ግን ውስጧ ከነበረ ለምንድነው እስከዛሬ ትዝ ሳይላት የቆየው ...?በየትኛው የአእምሮዋ ጎዳ ውስጥ ደብቃው ብትቆይ ነው?በጣም ያስገረማት ጉዳይ ነበር..በእለቱ ልክ እንደወትሯዋ እዛ የጓሮ  አበባ ውስጥ ተወሽቃ አባተዋና አያቷ ከውጭ  እየተጨቃጨቁ  መጡና እሷ ያለችበት አካባቢ ሲደርሱ ...ቆሙ።

"ከልጄ እንድትርቅ እፈልጋለሁ…. ሁሉን ነገር ጥለህ ይሄን ሀገር እንድትለቅና ዳግመኛም ተመልሰህ እንዳትመጣ አስጠነቅቅሀለሁ"አያተዋ ናቸው በቁጣ አበቷ ላይ የሚጮሁበት፡፡

"ምን እያሉ ነው ...ልጅ አለቺኝ ኦኮ...እንዲህ እንዲያደርጉኝ አልፈቅድም››አባቷ ነው ተቃውሞውን የሚያሰማው፡፡

"እሱን ከመስረቅህ በፊት ማሰብ ነበረብህ..."

‹ስርቆት› ምትለው ቃል በደማቅ ቀለም ነበር በእምሮዋ ላይ የፃፈችው፡፡

""በቃ አንዴ ተሳስቼያለሁ...ሁለተኛ አልደግምም...ከልጄ መለየት አልፈልግም"

"የልጅ ልጄ  በሌባ እጅ እንድታድግ አልፈልግም...ከአንተ ጋር አንድ ጊቢ ውስጥ ሆና በአንድ ከተማ አብሬህ መኖር አልፈልግም..አንድ ቀን ሰጥቼሀለሁ...ካለበለዚያ በማደርገው ነገር ታዝናለህ .."ብለውት ከዘራቸውን እየወዘወዙ ወደ ትልቁ ቤት ሲገብ ትዝ ይላታል።

አባቷ እዛው እቆመበት አካባቢ ያለ ጠፍጣፋ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ ልክ እሷ አሻንጉሊቶቾ ሲጠፍባት እንደምታደርገው እንባውን ሲያንጠባብ አይታለች...ከዛ ከተደበቀችበት ሹክክ ብላ ወጥታ ወደአባቷ ነበር ያመራችው...ተደብቃ የቀነጠሰችውን አበቦች ምንሞ ሳትሰስት እንዳለ ለአባቷ መስጠቷ ትዝ ይላታል። እሱም ጉያው ውስጥ ሸጉጦ በማቀፍ ጉንጮቾን  አንገቷን ትናንሽ እጆቾን እየቀያየረ እና እየደጋገመ ለሳዕታት ደክሞት እዛው ክንድ ላይ እስክተኛ ሲስማት እንደነበረ ትዝ ይላታል...ስለአባቷ  የተገለፀላት ትዝታ ይሄ ነው።ከእዛን ቀን በኃላ አላየችውም ...ከእንቅልፏ ስትነቃ እራሷን ያገኘችው መኝታ ቤቷ  ውስጥ በስርዓት ተኝታ  ነበር።ተነሳችና ‹ አባዬ› ብትል ለስራ ወጥቶል አሏት...በማግስቱ ብትጠይቅ ሩቅ መንገድ ሄዷል ተባለች...ጥያቄዋን ለወራት ብትደጋግምም ታገኝ የነበረው መልስ ግን በጣም አሰልቺ እና ተደጋጋሚ ነበር...ከዛ በህፃን አእምሮዋ አያቷ ላይ ቂም ያዘችበት...‹ሌባ ሌባ› የሚለው ከአያቷ አንደበት ወደ አባቷ የተሰነዘረው ቃል  በጨቅላ አእምሮዋ እየተመላለሰ  አስቸገራት ተሰቃየች? አዎ አሁን የዘመናት ችግሯ መነሻ ምክንያት ተገልፃላታል...በዛ የአባት ናፍቆት ያንገላታት በነበረበት ጨቅላ ዕድሜዋ እንደአባቷ መሆን በጣም መፈለጓ  ትዝ ይላታል፤ ...እንደ አባቷ ‹‹ሌባ..››ይሄንን ደግሞ ተግባራዊ ማድረግ የጀመረችው አባቷን ለመጀመሪያ ጊዜ ሌባ እያለ ሲያወግዘው የሰማችውን አያቷ በመስረቅና ለአባቷ በመበቀል ነው።

"የነገሮች እንዲህ መገጣጠምና መቆላለፍ በጣም  አስገራሚ ነው የሆነባት።ለዚህ ቃል ትልቅ ምስጋና ይገባዋል ፡፡መዳን ከፈለገች ወደ ልጅነት ጊዜዋ ተመልሳ ትዝታዎቾን እንድትቆፍር ባያሳስባት ..ምን አልባትም እኚ ነገሮች በውስጧ እንደተዳፈኑ እዛው ከስመው ይቀሩ ነበር...ግን አሁንም ያልገባት አባቷ ምን ቢሰርቅ ነው አያቷ እንደዛ ሊያስፈራሩት  የቻሉት..?ደግሞስ እንደ እሷ ልክፍት  ይዟት ካልሆነ የገንዘብ   ችግር እንደማይኖርበት እርግጠኛ ነች?ታዲያ ለምን?የእዚህ መልስ እናቷ ጋር ነው ያለው...ግን አሁን እሷ ያልገባት እሺ ለችግሯ መነሻ የሆነ ሰበበ ምክንያቱን አወቀች፡ ግን እንዴት ነው  ፈውስ እንዲሆናት ሊያግዛት የሚችለው?አልገባትም።ቢሆንም ደስ ብሏታል። ነገ ተነገ ወዲያ ደግሞ የሚገለፁላት  ከፈውሷ ጋር የተገናኙ ተጨማሪ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። አዎ እናቷንና ቃልን  ማናገር እንዳለባት ወሰነች፡፡ ከዛ የሚሆነውን ለማየትድምዳሜ ላይ ደረሰች።
አይገርምም ግን የአንድ ቀን  ብጣቂ ገጠመኝ  የረጂሙ  የህይወታችንን  ጉዞ ላይ ጠንካራ ተፅእኖ ማሳረፍ ይችላል።አሁን ይሄን ታሪክ እንዲ አቆላልፍና አዋስቧ ሌላ ሰው ቢነግራት ስቃ ከማለፍ ውጭ እንደቁም ነገር ወስዳ ቦታ አትሰጠውም ነበር...አሁን ግን ዋጋ የከፈለችበት የራሷ ታሪክ ስለሆነ  ችላ ልትለው ፈፅሞ አትችልም። እናቷ ክፍል ገባች...ቁምሳጥናቸው አጠገብ ቁጭ ብለው በመስታወት እራሷቸውን እያዩ ፀጉሯቸውን እያበጠሩ ነበር፡፡በራፋን ከውስጥ ቆለፍችና ወንበር ይዛ ወደእሷቸው በመጠጋት  ከጎነናቸው ቁጭ አለች፡፡
"እማዬ አያቴና አባቴ በምን ጉዳይ ነበር የተጣሉት?"
እናቷ ጠያቄዋን እንደሰሙ ማበጠራቸውን አቁመው ፊታቸውን የሸፈነውን ፀጉሯቸውን ሰብስበው ወደኃላዋ ወረወሩና
‹‹  ምን አልሺኝ ?››አሏት በመኮሳተር
‹‹ ...አያቴ አባቴን ሌባ ነህ ብሎነው ከዚህ ቤት ያባረረው ...አባቴ ምን ሰርቆ ነው?››
"በሰማዕቱ ጊዬርጊስ ይሄን ጉድ ደግሞ ማነው የነገረሽ?
"ማንም አልነገረኝ እማዬ አስታውሼ ነው"
"አስታውሼ ማለት?"አይኖቾን አፍጥጣ፡፡
"አባዬ ከመጥፋቱ በፊት ከአያቴ ጋር ሲጨቃጨቁት ፊት ለፊት አበባ ውስጥ ተደብቄ ሰምቼያቸዋለሁ...አባቴ ከልጄ አይነጥሉኝ እያለ አባትሽን እያለቀሰ ሲለምን  ነበር..አያቴ ግን ከሌባ ጋር አንድ ቤትም አንድ ከተማም አብሬ አልኖርም..ሀገር ጥለህ ጥፋልኝ ሲለው በጆሮዬ ሰምቼለሁ?እና አባቴን ያባረራችሁት ብር ስለሠረቃችሁ ነው ወይስ ወርቅ?"
👍6810🔥2
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

በቀጠሯችን መሰረት ወደቃል ቤት እየሄደች ነው።ይህ ቀጠሮ ለእሷ ልክ እንደከዚ ቀደሞቹ ቀጠሮዎች አይነት አይደለም።ቀጠሮውን ሳታሲዘው እንኳን "ለብቻህ ለረጂም ሰዓት ነው የምፈልግህ..በምንም አይነት የማይሰረዝ የሞት ቀጠሮ ነው"ነበር ያለችው።ልክ ስድስት ሰዓት እሱ ቤት ለመገናኘት ነው የተቀጣጠሩት። ሁለት ሰዓት ከቤት ወጣች፤ የውበት ሳሎን ደንበኞቾ ጋር ሄደች ...ከጥፍሯ አንስቶ ቅንድቧን ፀጉሯን እስክታስተካክልላት አራት ተኩል ሆነ...እቤት ሄዳ በሀገሪቱ አለ በተባለች ዲዛይነር በልዩ ሁኔታ ያሰፋችውን የሀገር በሀል ቀሚስ ለብሳ እሱን ደስ ያሰኘዋል ብላ ባሰችው አለባበስ ዘንጣ መኪናዋን እሱ የሚኖርበት ግቢ አስገብታ ስታቆም ሰዓቱ 6.03 ይል ነበር።የመኪናዋን ሞተር ከጠፋችና ለእለቱ ልዪ ዝግጅት ማድመቂያ ይሆን ዘንድ ይዛ የመጣችውን ቶርታ ኬክ፤ውስኪ፤ሻማዎች እና ቸኮሌቶችን ከእነ ዘንቢሉ እየተንገዳገደችም ቢሆን ይዛ ወረደችና ወደ ቃል ቤት ልትታጠፍ ስትል አሮጊቷ የቤት አከራይ ከእቤታቸው ሲወጡ ተገጣጠሙ ።
"ውይ በጌታ መጣሽ?"አሉ ከሞት የተነሳ ዘመዳቸውን ድንገት እንዳዩ አይነት ደንግጠው። የአሮጊቷ መደንገጥ ብቻ ሳይሆን እንባቸውም እየረገፈ ነው ።
" ማዘር ምን ሆኑ?"
‹‹አረ ምንም አልሆንኩ..ምነው ጠየቅሺኝ?"
"አይ እያለቀሱ ነው ብዬ ነዋ"
"እ አይ ልጄ ጭስ ነገር ነበር ..እቤት ያው ያሮጊት ነገር ታውቂ የለ"
"በሉ እሺ"ብላ መንገዷን ስትቀጥል
"ቆይ ልጄ ቁልፍ ልስጥሸ"አሏትና አስቆሟት፡፡
ውስጧን ክፍት አለው"ምነው ቃል የለም እንዴ?››ለስለስ ባለ ድምፀት ጠየቀቻቸው ።
"ቃል ነው ያልሽው ?"አሉና ወደውስጥ መግባቱን እረስተው ፍዝዝ ብለው ቆሙ፡
"እንዴ እማማ ..ችግር አለ እንዴ?"
"አረ የለም..ማለቴ ቃል ወጣ ብሎ ነው አልቆይም ብሎል"ብለዋት ወደ ውስጥ ገቡ ።
"ቃል ደግሞ በዚህ ቀን?ለዛውም እንዲህ አስጠንቅቄህ"ቃል ስሯ ሆኖ ባይሰማትም ተነጫነጨችበት ።
አሮጊቷ አምጥተው ቁልፍን ሰጧት... ነገረ ስራቸው አላማራትም‹..አይናቸውን ከዓይኔ ለምንድነው የሚያሸሹት?›ቁልፉን ተቀብላ እያልጎመጎመች ወደጓሮ ዞረችና የቃልን ቤት ከፍታ ገባች።እንደወትሮ ፅድት እንዳለ ነው።እሷ ግን ከወትሮ የተለየ የደመቀና የፈካ እንዲሆን ነበር የፈለገችው።ልቧ ላይ እንደሚንቦገቦገው አይነት የደስታ ብርሀን እቤቱም እንደዛው ይሆናል ብላ ጠብቃ ነበር.. በሚገርም ሁኔታ ግን ምን እንኳን እቤቱ በውስጧ በፈለገችው ሆኔታ ባይሸበርቅም ጠረጰዛው ግን በምትወዳቸው የምግብ አይነቶች ተሞልቶል። ሞባይሏን አወጣችና ከተለያየ አቅጣጫ አንድ ሶስት ፎቶዎች አነሳችና።‹‹እንደውም ጥሩ አጋጣሚ ነው ።እስኪመለስ አንዳንድ ነገሮችን አስተካክላለሁ› ብላ አሰበችና ወደውስጥ ዘለቀች።የቤቱን መብራት አበራችው...ሌላ አነስ ያለች ጠረጰዛ የክፍሉን አንድ ግድግዳ ተጠግታ ትታያለች።የጠረጰዛውን አቅጣጫ አስተካከለችና ያመጣችውን ኬክ መሀከል ላይ አስቀመጠችው.. የውሰኪ ጠርሙሱን አወጣችና ከጎኑ አደረገችው...ዝርግ ሰሀኖችን ፈለገችና ቸኮሌቶቾን በመዘርገፍ ቦታ ሰጠዋቸው ።
‹‹አዎ አሁን የጎደለው ሙዚቃና ቃልዬ ብቻ ነው።››አለችና ሙዚቃ ለመክፈት ወደመኝታ ቤት ገባች።ወደጂፓሱ ሄደችና ሶኬቱን ሰካችው.. እላዩ ላይ ፍላሽ ስለነበረ ከፈተችውና ድምፅን መጥና ወደሳሎን ልትመልስ ስትል አይኗ የቃልን አልጋ ላይ አረፈ..ከተነጠፈው ሰማያዊ የአልጋ ልብስ ላይ ሁለት ነጫጭ ፓስታዎች ተደራርበው ተቀምጠዎል።ለምን እንደሆነ ባይገባትም አልፋቸው መሄድ አልፈለገችም።ወደኃላ ተመለሰችና የአልጋው ጠርዝ ላይ በመቀመጥ አነሳቻቸው፡፡ ሁለቱንም በሁለት እጆቾ ይዛ ከላይ የተፃፈባቸውን አድራሻ አነበበች፡፡
አንደኛው‹‹ከቃል ለጊፋቲ የተፃፈ የስንብት ደብዳቤ ››ይላል።
‹‹የስንብት› ማለት ምን ማለት ነው?።አዎ ገባኝ መድህኔን ልታገባ ስለሆነ እየተሰናታት ነው…።በዚህ መጠን ተበሳጭቶብሻል ማለት ነው..ደግ አደረገ›› አለችና በውስጧ በስኬቶ በመኩራራት ፈነጠዘች፡፡
"እሱን ወደነበረበት አልጋ ላይ ወርወር በማድረግ ሁለተኛውን ገልብጣ፡፡ አድራሻውን ማየት ጀመረች፡፡ በተመሳሳይ ቀለም በአንዳ አይነት የፊደል አጣጣል የተፃፈ ነው፡፡ከቃል ለልዩ የተፃፈ የስንብት ደብዳቤ ይላል፡፡በዚህ ወቅት የቤቱ አየር ተበከለ ፤መተንፈስ ብቻ ሳይሆን አይኖቾን ከፍታ አካባቢዋን ሁሉ ማየት ነው ያቃታት.. ፖስታውን በሚንቀጠቀጡ እጇቾ ቀዳዳ ከፈተችው፡፡
‹ልዩ እንዲህ ያደረኩት አንቺን በአካል አግኝቶ መሰናበት ቀላል ሆኖ ስላላገኘሁት ነው።አንቺና ጊፍቲ ከአባቴ ቀጥሎ በዚህች ምድር ያላችሁኝ የቅርቤም የልቤም ሰዎች ናችሁ።ልዩ እኔ ከአሁን ወዲህ የለውም...እንደምታውቂው ነፍሴ በዚህ አለም ኳኳታና ትርምስ ደስተኛ አይደለችም።ከዚህ በላይ በውስጧ መኳተን ለእኔም ሆነ በዙሪያዬ ላሉ ሰዎች መልካም መስሎ አልታየኝም።ወደእዚህች ምድር የመጣሁበትን ምክንያት ለመመርመር ፀጥታ ወደአረበበትና በፅሞና ማሰላሰል ወደምችልበት ቦታ ማለቴ ወደገዳም አምርቼያለሁ።ነግሬሽ ባላውቅም ወደእዛ መሄድ የረጅም ጊዜ ውጥኔ ነበር...ግን ያው ይህቺ አለም የራሷ የሆነ ወጥመድ አላትና እስከአሁን ሊሳካልኝ አልቻለም ነበር።
ለማንኛውም እግዚያብሄር ነገሮች እንዲከወኑ የሚፈቅድበት የራሱ የሆነ ጊዜ አለው ...እናም ዛሬ ቀኗ ሆነችና ህልሜ ተሳካ።ካዛሬ ጀምሮ እኔ የመንፈሳዊው አለም ምልምል ወታደር ሆኜ ተመርጬለሁ።ጮርቃ የሆነውን መንፈሳዊ ህይወቴንም ጥልቀት ያለው የበሰለና ለሌላው የሚተርፍ እስኪሆን ድረስ በልምምድ ተጋለሁ ሁለት አመትም ፈጀብኝ ሀያ አመት ካልሆነም እድሜ ልክ አያስጨንቀኝም...በመንፈሳዊ ልምምድ ውስጥ ወደ ሰማያዊ ንቃት ለማደግ ምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ።እግዚያብሄርም እንደሚያግዘኝ እተማመናለሁ። አንቺም እንደምትፀልይልኝ ጥርጥር የለኝም።እንግዲህ ልዩ የህይወት አላማዬ አስገድዶኝ በመንፈሳዊ ተልዕኮ ተገድጄ ካልሆነ በስተቀር ከምሄድበት የፅሞናና የፀጥታ ቦታ ወጥቼ ወደእናንተ የምመጣ ስለማይመስለኝ ይህ ስንብት የመጨረሻችን ነው።ግን ደግሞ በሚቀጥለው አለም በተለየ ሁኔታ እንገናኛለን የሚል የፀና እምነት አለኝ።
በስተመጨረሻ ሁለት ነገሮችን እንድታደርጊልኝ እጠይቅሻለሁ ..የመጀመሪያው ለጊፍቲ ጥሩ ጓደኛ እንድትሆኚያትና ሁለተኛው ደግሞ በተቻለሽ መጠን አባቴን እንድትጠይቂው ነው።ያው አንቺም አባት የለሽም አይደል... አባቴን ሸልሜሻለሁ።የቤቱን ዕቃ ከጊፍቲ ጋር ተማክራችሁ እንደሚሆን አድርጉት ወይ ለተቸገረ ስጡት...ብቻ እንደመሠላችሁ። በስተመጨረሻ በእጆቼ ጣቶች በጥልቅ ምስጋናና በፍፅም ፍቅር የመጨረሻ ምሳ አዘጋጅቼልሻለሁ...ጣፍጦሽ እንደምትበይው እርግጠኛ ነኝ።በይ ቻው..እስከአሁን አብረን በቆየንባቸው ጊዜያቶች ስላሳየሽኝ ደግነት፤ስለ ሰጠሸኝ ፍቅር፡ስለአጎናፀፍሽኝ ደስታ ከልቤ አመሰግናለሁ!! አመስገናለሁ!!! አመሰግናለሁ... የእግዜያብሄር መንፈስ በልብሽ ይንገስ.. .አሜን
...እራሷን ተቆጣጥራ ፌንት በልታ ወደኃላዋ ተዘርራ ሳትወድቅ ደብዳቤውን አንብባ ጨረስችው.የዛ አይነት ፅናትና ብርታት ከየት እንዳመጣቸ ለራሷም ደነቃት...ምን እየተሠማት እንደሆነ ማወቅ አልቻለችም።

ይቀጥላል
👍14321🤔11👎8🥰2😁1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


"እግዜር ይስጥህ እንኳን እቤትህ ቁጭ ብለህ ጠብቀህ ልዩ ጥዬሽ ገዳም ልገባ ነው አላልከኝ...ድፍረት ኖሮህ አይን አይኖቼን እያየህ እንደዛ ብትለኝ …የሆነ ቢላዎ ፈልጌ ልብህ ላይ ሽጪ እዚሁ ነበር የማስቀርህ...›ስትል ዛተች..ዛቻዋ ከልቧ ነበር.አድራሻው የማይታወቅ ገዳም ገብቶ ለዘላለም ከምታጣው እዚሁ በገዛ እጇ ገድላው አልቅሳ ከቀበርረችው በኃላ ምርጥ በተባለ እምነ በረድ ሀውልት አሰርታለት በየቀኑ መቃብሩ ጋር እየሄደች ሰታወራው መዋል  ይሻላት ነበር፤

አእምሮውን ሳት እንዳደረገው ትኩስ እብድ በቤቱ ወዲህ ወዲያ በመዟዟር ነበር ቀበጣጥረው

ፓስታውን በእጇ ይዛ እጆቾን ከደቡብ ወደሰሜን እያወናጨፈች አንዴ መኝታ ቤት ደግሞም ሳሎን እየተመላለስች ነው‹‹....አረ እያበድኩ ነው መሰለኝ...››አለችና የሳሎኑን በራፍ በርገዳ ወጣች…

...ሮጣ አሮጌቷ ቤት በረንዳ ላይ እራሷን አገኘችው ።ለማንኳኳት እንኳን ትእግስቱ አልነበራም፡፡ በራፍን በርግዳ ገባች፡፡ አሮጊቷ ተቀምጠውበት ከነበረው ግዙፍ ሶፋ  ቀልጠፍ ብለው ተነስተው ቆሙ..ልክ የሆነ ወንጀል ሰርተው በተደበቁት ድንገት ፓሊስ ቤታቸውን ከፍቶ ፊት ለፊታቸው እንደቆመ ነው ሁኔታቸው..

"ቃልዬ የት ነው?እንዴት እንዲህ ይሰራኛል?እርሶ እንደማፈቅረው አያውቁም?"
ቀስ ብለው ካሉበት ተንቀሳቅሰው ቀረቧት ፤ክንዷን ያዙና ወደራሳቸው በመጎተት እቅፋቸው ውስጥ አስገቧት። የምትፈልገው ይሄንን ነበር..መንሰቅሰቅ ጀመረች..እምባዋ ከጀርባቸው ላይ እያረፈ ወደታች ሲንኳለል ይታያታል…ቢያንስ ለ10 ደቂቃ በቆሙበት ተቃቅፈው እየተላቀሱ ቆዩ ።ከዛ አሮጊቷ ቀድሞ ደከማቸው.. እየጎተቱ ወስደው ሶፋ ላይ አስቀመጧትና  ከጎኗ ተቀመጡ።


‹‹እማማ ልጆት አይደለ እንዴት ዝም ይሉታል?››

"ልጄ ወደእግዚያብሄር ቤት ልሄድ ነው ሲለኝ እንዴት ብዬ አትሂድ አይሆንም እለዎለሁ?"

"እኔስ ፍቅር አሲይዞኝ እንዴት ይሄዳል?  ...እሺ አሁን ምንድነው የማደርገው ?ዛሬ እኮ አይኔን በጨው ታጦቤ ልነግረው ነበር  ..እጮኛዬ እንዲሆነኝ ቀለበት ላስርለት ነበር እኮ... በመዳፏ ጨምድዳ የያዘቻቸውን ሁለት ቀለበቶች ወደ ፊትለፊት ዘርግታ እርስ በርስ በማቅጨልጨል አሳየቻቸው

"ልጄ አልሆነማ ምን ይደረግ...?እሱ የእግዚያብሄር ሙሽራ ብሆን ይሻለኛል አለ?በውሳኔው ጣልቃ መግባት ከእግዜሩም መቀያየም ነው።"አሏት ልስልስ እና ድክም ባለ ድምፀ፡፡

‹‹አልገባዎትም ...በጣም እኳ ነው ያፈቀርኩት...እንሂድ ቢለኝ ምን አለበት..?ያለምንም ማቅማማት አብሬው ሄድ ነበርእኮ"

በእንባ የተዳረሰ ፊታቸውን በከፊል ፈገግ አድሮገው"አይ ልጄ ቢጨንቅሽ እኮ ነው... ገዳም   ፊልም ቤት አይደል አብረን እንግባ የሚልሽ።"

ትከሻዋ ላይ ጣል ያደረጉትን እጃቸውን መንጭቃ ወረወረችና ከተቀመጠችበት ተነሳች..."ይሄ እውነት አይደለም..ቃል አሁን መጥቶ እቤት ይጠብቀኛል ..አዎ እየጠበቀኝ ነው...›በማት ወደውጭ መራመድ ጀመረች....

‹‹አይ ልጄ እግዚያብሄር ይሁንሽ ከማለት ውጭ ምን አረጋለሁ? "አሉ አልመለሰችላቸውም.. ተንደርድራ ቃል ቤት ደረስች …ሙሉ በሙሉ ተበርግዶ እንደተከፈተ ነበር።

‹‹አዎ ቃል ተመልሶ መጥቶል..ቃልዬ አልጋው ላይ ጋደም ብሎ እየጠበቀኝ ነው።አዎ እኔሞ አብሬው ከጎኑ እተኛለሁ...እቅፍ አድርጌው ከንፈሩን ስማለሁ ...እና የፈለገውን ነገር ቢጠይቀኝ በደስታ እሺ እለዋለሁ ...እናም ደግሞ ይሄንን ቀለበት ጣቱ ላይ አጠልቅለትና የዘላለም ባሌ እንዲሆን እጠይቀዋለሁ..እርግጠኛ ነኝ እሱም እሺ ብሎ ሌለኛውን ቀለበት ጣቴ ላይ ያጠልቅልኛል።›› ...ይሄን ሁሉ እየለፈለፈች የሳሎኑ በራፍ ጋር ቆማ የሚብረከረከውን ጉልበቷን ባለመተማመን ጉበኑን ጨምድዳ ይዛ ወደ ውስጥ ባዶውንና ኦናውን ሳሎን አያየች ነው...መቀባጠሯን ሳታቋርጥ ወደ ውሰጥ ገባችሁ ልብን በሚቆራርጥ ፍራቻና አጥንትን በሚከታትፍ ሰቃይ የመኝታ ቤቱን በራፍ ገፋ አደርጋ በመክፈት አይኖቾን ወደውስጥ ላከች  ..ሁሉ ነገር ጥላው እንደወጣችው ነው ...ቃል የለም...ወደ ሳሎን ተመለሰች...ቃል ሰርቶላት የደረደራቸው ምግቦች አጠገብ ተቀመጠች።እጆን ወደምግብ ዘረጋች...ልክ ምግብ ለሳምንት በልቶ እንደማያውቅ ሰው (እርግጥ ቃልን ለማግኘት ስትቆነጃጅ ጊዜ ስላላገኘች ከነጋ ምግብ አልበላችም።)እየተስገበገበች መብላት ጀመረች።ሲበቃት ደረቷ ጠቅላላ በወጥ አጨመላልቃዋለችሁ ...የሀገር ባህል ቀሚስ ላይ ወጥ  ነክትቶ... ይባስ ብላ በወጥ የተጨማለቀ አጇን ጠረገችበት 27 ሺ ብር የወጣበት ልብስ ግማሽ ቀን እንኳን ሳይለበስ ድራሹ ጠፋ...‹‹የት አባቱ ቃልዬም ጠፋቶል እንኳን ልብስ ›አለችና የውስኪ ጠርሙሱንና አንድ ብርጭቆ ይዛ መሬት ያዘች።እዛው ሳሎን የቀኝ ግድግዳውን  ተደግፋ በላይ በላይ እየቀዳች መጋት ቀጠለች...ሩብ ያህሉን እንዳጋመሰች ጊፍቲ ትዝ አለቻት።ተንበርክካ በእንፉቅቅ እየሄደች ስልኳን ካስቀመተችበት አነሳችና ከፈተችው …በርከት ያሉ የተደወሉ ስልኮችና ሚሴጆች አሉ...ምን ያህል እንደደነዘዘቸ ማስረጃው   ይሄ ሁሉ ተደውሎ ስልኩ ሲንጫረር አለመስማቷ ነው...ከሙዚቃው ጋር ደርባ ስትሰማ የቆየችው  ሙዚቃ መስሏት ይሆናል..አሁንም ቢሆን  ማን እንደደወለላት ለማየት  ደንታ አልነበራም።ስልኳን ፈለገችና ደወለችላት… አነሳችው፡፡

"ሄሎ ልዩ "
‹‹አቤት››
‹‹ እቤተ እንድትመጪ እፈልጋለሁ›

‹‹የት ቤት  ነው የምመጣው..?ምን ሆነሻል?››
‹‹ቃል እቤት ነይ..…አሁኑኑ››
‹ልዩ ምን ሆነሻል ቃል ሰላም አይደለም?››
‹‹አለም ተገለባብጧል ..የገሀነም በሮች ተከፍተዋል….ምትመጪ እንደሆነ ነይ››ጆሮዋ ላይ ጠረቀመችባ፡፡ሰከንድ  ሳትቆይ ጊፍቲ መልሳ ደወለችላት.. ስልኳን ሙሉ በሙሉ አጠፋችው፡፡ ውስኪዬን እየተጋተች ሀሳቦን ወደመቃዠቱ ገባች …..

ገዳም ገባ አሉኝ -ደብረሊባኖስ
ነፍስ እየገደሉ- ይማራል ወይ ነፍስ?
ነፍስ እየገደሉ -ከተማረ ነፍስ
እኔም ያው ሞትኩልህ....አንተም ተቀደስ።

የትና መቼ  እንደሰማችው የማታውቀው ዘፈን ግጠም ከነዜማው በአእምሮዋ እያንቃጨለ አስቸገራት፡፡

የሠው ልጅ 70 ትሪሊዬን ከሚሆኑ ህውሶች ተዋቅሮ የተገነባ ፍጡር ነው ።በአሁኑ ጊዜ የአለም ህዝብ ቁጥር 7ቢሊዬን ገደማ ነው። .ይሄ ሁሉ ህዝብ አንድ ላይ ተጨፍልቆ ከአጥናፍ አለም አንፃር ከህዋስ ያለፈ ቦታ የለውም።ግን ደግሞ ታአምር የሚያሰኘው አንድ ነጠላ ሰው አጥናፍ አለምን የሚያስስ ሰፊና ጥልቅ የሆነ  ከመጠኑ ቢሊዬን ጊዜ በላይ የሚገዝፍ  በአዕምሮው ማሽንነት የሚፈጠረ ተስፍፊና ተስፈንጣሪ ምናብ ባለቤት ነው።ሰው...ገራሚ ፍጡር ነው።ለዚህም ነው መሠለኝ ሩሚ "አፅናፍ አለም በሙሉ በውስጥህ ስላለ ብቸኝነት ፈፅሞ አይሰማህ "ያለው።ከዝንት አለም ውስጥ ተመዘን ወጥተን ወደህይወት ለመምጣት በእናትህ ቅድስ ማህፀን ውስጥ ገብተን ተብላልተንና በቅርፅና በመጠን ተስተካክለን መውጣት የግድ ይላል።ይሄ ብቸኛው መንገድ ነው።እንደ ሙሀመድ ነብይ..እንደ እየሱስ የእግዚያብሄር ልጅ ፤እንደ ቡድሀ ታላቅ መንፈሳዊ መገለጥ ላይ የደረስንና  የበራልን ብንሆንም እንኳን ሌላ መንገድ የለም። ሌላው ደግም በዚህ ምድር ቆይታ ላይ ሳለን አነዳንዶቻችን በእግዜያብሄር መንግስት እናምናለን?በዛም አሻግረን ወደ ገነትስ መግባት እንሻለን?ከዚህ በሚቃረን መልኩ ግን ከሞት መዳፍ ለማምለጥ ሰንጥርና ስንለፋ ይታያል?ሞት ማለት እኮ በሚመጣው አለም ወደሚጠብቀህ የዘላለም መኖሪያ ሾልከህ ምትሄድበት ብቸኛው በራፍ
👍8011👏4🤔2🥰1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹ከምን ያህል የጊዜ ደንዛዜ ውስጥ እንደቆየች አታውቅም .የሳሎኑ በራፍ ተበርግዶ ሲከፈት ነው ከሀሳቧ ውስጥ በመከራ የወጣችው…ጊፍቲ ከፊት መድህኔ ከኋላ እያለከለኩ ተከታትለው ገቡ
በመጠጥ ተዳክሞ በተቆላለፈ አንደበቷ ‹‹ነይ እንጂ ኑ ብያለሁ››አለቻት..ያልጠበቀችን እና ከነመፈጠሩም ጭሩሱኑ ረስታው የነበረውን መድሀኔን ስታየው ብሶቷ በእጥፍ ጨመረባት፡

ጊፊቲም በራሷ ድንጋጤ ላይ ስለሆነች እሷ የምትለውን እየሰማቻት አይደለም..ጥያቄዋን አዥጎደጎደችው‹‹እንዴ ምን ተፈጥሮ ነው…?ቃልዬ የት አለ….?አመመው እንዴ….?››ተንደርድራ አልፋ የመኝታ ቤቱን በራፍ ከፈተችና ወደ ውስጥ አየች… ባዶ መሆኑን ስታይ ወደ ልዩ ተመለሰችና‹‹…ልዩ ንገሪኝ እንጂ…ተጣልታችሁ ነው….?አሁን እሱ የት ሄደ?››
ዝም ብላ አየቻት..ሆዷ ወደፊት እየገፋ ነው…በሶስት ወር ፣‹‹እንዲህ ያስታውቃል እንዴ…?››ስትል አሰበች ግራ ከመጋባቷ የተነሳ የማያሳስበው እያሳሰበት ነው፡፡መድህኔ እጁን በደረቱ ላይ አጣጥፎ ግራ በማጋባት ዝምብሎ ቁልቁል እያየት ነው፡፡አሳዝናዋለች.በጣም ነው ያሳዘነችው..ስሯ ተንበርክኮ ወደደረቱ አስጠግቶ እቅፍ አድርጎ ቢያፅናናት ደስ ይለዋል.ግን እንደዛ ማድረግ አይችልም…
‹‹ልዩ አረ በፈጠረሽ …አናግሪኝ በጭንቀት ልፈነዳልሽ ነው?››አለች ጊፊቲ
‹‹ቃል ከዛሬ ጀምሮ የለም››
‹‹የለም ማለት ምን ማለት ነው?››
‹‹መልሱ መኝታ ቤት ግቢና አልጋው ላይ አለልሽ››
ከተንበረከከችበት ተነስታ ተንደርድራ ወደመኝታ ቤት ስትገባ መድህኔ ‹‹ልጄን…›› አለ .አንድ ነገር እንዳይሆንበት የተሳቀቀ በሚመስል ሰውነቱን አሸማቆና ፊቱን አጨማዶ‹‹አረ ማሬ ቀስ በይ..ቀስ…..››
ፖስታውን በእጇ እያገላበጠች ተመልሳ መጣች፡፡‹‹የመጨረሻ ስንብት ማለት ምን ማለት ነው? ››ተንዘረዘረችባት
‹‹ወይዘሮ ጊፍቲ ብታነቢው እኮ የምትፈልጊውን  መልስ  ከውስጡ ታገኚያለሽ..››
ከፈተችውና ማንበብ እንደጀመረች እንደማዞር አደረጋት ፡፡ ተንገዳገደች….ተንደርድሮ ሄደና ክንዷን ያዛት …መድህኔ የልዩ የድሮ ፍቅር …ቃልን የማታገኝ መስሏት ለሌላ ሴት አሳልፋ የሸለመችው የልጅነት ጓደኛዋ …የረጅም ዘመን ፍቅረኛዋ… እየጎተተ ወሰዳትና  ወንበር ላይ አስቀመጣት፡፡ ለማንኛውም ብሎ ልክ እንደባለስልጣን ጋርድ ከጎኗ በተጠንቀቅ ቆመ ..እንደምንም ብላ ማንበቧን ቀጠለች…ልዩም መጠጧን እየሳበች እየተከታተለቻት ነው፡፡ ጨረሰችና ደብዳቤውን ወደመሬት ጣለችው›
‹‹አንብቤያለሁ ግን ምንም አልገባኝም››
‹‹እኔም እኮ አልገባኝ ብሎ ነው የጠራሁሽ..አንቺ ምን አልባት የልጅነት ጓደኛው ስለሆንሽ ጠባዩንና ድርጊቱን ከኔ በተሻላ ትረጂያለሽ ብዬ ስለማስብ  እንድታስረጂኝ ነበረ  …አንቺ ግን መልሰሽ እኔን እየጠየቅሽ ነው፡፡››
‹‹ቀስ ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳችና እየተጎተተች ሄዳ ከልዩ  ጎን ተዘረፈጠች…..የውስኪውን ጠርሙስ አንስታ ልትጋተው ወደላይ ስታነሳ..ልክ አንደ እግር ኳስ በረኛ ካለበት ተንደረድሮ ሸርተቴ በመግባት ከእጇ ላይ ቀለበው…
‹‹ምን ነካሽ..?እርጉዝ እኮ ነሸ››
‹‹ይቅርታ መድህኔ …ግራ ስለተጋባሁ ነው..እንዴት ነው ቃል ህይወቱን ጥሎ፤ ስራውን ጥሎ፤ አባቱን ጥሎ፤ እኛን ጥሎ ገዳም  የገባው…ገዳም መግባት ማለት ምን ማለት ነው…?››የመለሰላት የለም…..
መድህኔ ከሁለቱም ፊት ለፊት ቆሞ በጭንቀት እያፈራረቀ እያየቸው ነው..ምን እየተሰማው እንደሆን ልቡ ውስጥ ገብታ ማንበብ ብትችል ደስ ይለታል ..የድሮ ፍቅረኛውና የአሁኑ እጮኛው ሌላ ወንድ ጥሎን ገዳም ገባ በሚል ሰበብ ስብብርብር ብለው እንዲህ ሲነፈርቁ….በጣም ከባድ ነው……፡፡
‹‹የእኔ ፍቅር በቃ አንተ ወደስራህ ሂድ…..››
‹‹እንዴ እንዲህ ጥያችሁ እንዴት…..››
‹‹ግድ የለህም ..ሂድ ..እኛ ምንም አንሆንም…››
‹‹እውነቷን ነው እንደውም ብቻችንን ብትተወን ውለታ እንደዋልክልን ነው የምቆጥረው…›.አለችው
‹‹በቃ..የሆነች አጭር ስብሰባ አለቺብኝ..እሷን እንደጨረስኩ ተመልሼ እመጣና ወሰድችሓለው…፡፡
‹‹ሚስትህን መጥተህ መውሰድ ትችላለህ ..እኔ ግን የማድረው እዚህ ነው….ባይሆን ለእማዬ ደውለህ የሆነ ምክንያት ስጣትና እንደማድር ንገርልኝ››
እኔም እሷን ጥያት ስለማልሄድ ..ለዛሬ ተወን..ከፈለግንህ እንደውልልሀለን…› አለችው…››ጊፍቲ
‹‹ካላችሁ እሺ…ስልክሽ ግን እንዳይዘጋ….ቻው››   ቅር እያለው ወጥቶ ሄደ
የእግሩ ኮቴ መራቁን አረጋግጠው ሁለቱም የተነጋሩ ይመስል   እርስ በርስ ተቃቀፍና እየነፈረቁ ማልቀስ ቀጠሉ….ልክ የጋራ ቅርብ ዘመዳችው ሞቶ  ተረድተው ነው የሚመስለው….
‹‹በጣም አፍቅሬው ነበር እኮ……››አለቻት
‹‹አዎ ጠርጥሬ ነበር…በጣም አዝናለሁ››
‹‹እሺ አሁንም ምን ይሻለኛል….?እንዴት ነው የማደርገው?››
‹‹እኔ አላውቅም የእኔ ማር..እኔም ያለእሱ ምክርና ማበረታቻ ህይወትን መኖር አለመድኩበትም…እንዴትም እንደሚዘለቅ አላውቅም….››>
ማኒቲሱ የሚባል ነፍሳት አለ፡፡ የፌንጣ ዝርያ ነው፡፡የፍቅር ታሪካቸው በጣም ልብ ሰባሪ ነወ፡፡ ሴቷ ወንድ ዙሪያውን በመሽከርከር ስትደንስና ክንፎቾን እያማታች ስታማልልው  የወንዱ ስሜቱ ቀስ በቀስ ተነቃቅቶ በፈቅር ቅልጥልጥ ይላል..ከዛ እራሱን ከግንድና ካገኘው ጠንካራ ነገር ጋር ደጋግሞ ባማጋጨት ከሌላው ሰውነቱ በመለየት ቀንጥሶ ይጥለዋል..ምክንያም እንደዛ ሲያደርግ ብቻ ነው ከእሷ ጋር ወሲባዊ ተራክቦ በማድረግ ከውጥረቱ መርካት ሚችለው…..እና እንዳሰበው ከፍቅር መቅደስ ገብቶ ወሲባዊ መዝምር ዘምሮ …ፍፅማዊ እርካታ ይረካል..ግን ወደህይወት መመለስ አይችልም….ዳግመኛ የተቀነጠሰ አንገቱን ለብቻው ከተዘረረ ሰውነቱ ጋ የማጣበቅ ምንም አይነት ተፈጥሮአዊ ችሎታ የለውም..በዚህም ምክንያት የህይወት ፍፃሜው ይሆናል፡፡
‹‹እና ምን ማለት ነው?››
እኔም እንደዛ ሆኜለሁ…እንደሴቷ ሳይሆን እንደወንዱ…ቃልን አገኛለሁ ብዬ በክንዱ እቅፍ ውስጥ ለአንድ ቀን እንኳን ለመግባትን በፍቅር ትንፋሹን ለመማግ ቋምጬ አንገቴን ከሌላው ሰውነቴ ቀንጥሼ ጥያለሁ..ግን የሚገርመው እንደ ፌንጣው እንኳን የአንድ ቅፅበት እድል አላገኘሁም…ከእነ ፍቅር አምሮቴ ሕይወቴ አከተመላት…ይህ ከበደል ሁሉ የከረፋ በደል ነው፡፡ይቅርታ ማያሰጥ  ሀጥያት  ነው  የፈፀመብኝ››
‹‹ተይ ተይ ከእግዚያብሄር ጋር ለምን ታላትሚዋለሽ..››አለቻት ለቃል በመቆርቆር
‹‹እና ከሰይጣን ጋር ላድርገው..የሄደው እግዚያብሄርን ብሎ አይደል…?ታዲያ እግዚያብሄር ከእኔ ጋር የጀመረውን ጉዳይ አያውቅም ..እሱን ለማግኘት በመቋመጥ አንገቴን ከአከላቴ ቀንጥሼ መጣሌን አላየም..ተው    ግዴለህም እዛው ቆይላት አይለውም ነበር፡፡››

ይቀጥላል
👍103😢36😁95👎3🥰3
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_ሰላሳ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

..ይገርማል እሱ በማንኛውም አእምሮዋ በሚያመርታቸው ሀሳቦች ውስጥ የሆነ ቦታ ፈልጎ ተሸንቅሮ ሲወጣ ነው የምታየው....ስለሰማይም ታስብ ስለምድር…ስለእግዚያብሄር ይሁን ስለሰይጣን እሱ አለበት….፡፡.ደግሞ በሀሳቧ ብቻ አይደለም በህልሟም ጭምር እንጂ…..ህልሟ እኮ ስለ ምንም ሊሆን ይችላል ብቻ እሱ አለበት…ለምሳሌ እሷ እናቷ  መኝታ ቤት አልጋዋ ላይ ወጥታ ፀጉሯን ስትዳብሳት በህልሟ ብታይ እሱም ወይ በመስኮት ተደብቆ ሲያያት..ወይ ደግሞ እራሱን ወደቢራቢሮ ቀይሮ ክንፉን እያማታ መጥቶ ግንባራ ላይ ሲያርፍ ታየዋለች፡፡ይሄ ሁሌ ለራሷም ሳታስበው ግርም ይላታል፡፡እንዴት የሆነ ቦታ ላይ አትረሳውም…እንዴት የሆነ ሀሳብ አሰናድታ አጣጥፋ ስትጨርስ ድንገት ከሆነ ቦታ ተስፈንጥሮ መጥቶ ከላይ በቀላሉ ይደረባል…?ይሄ እንግዲህ በዚህ ከተማ በዚህ ቤት ውስጥ ሲኖር ነበር..አሁንስ ሁሉን ነገር ጣጥሎ ከሄደ በኃላ…….ምንድነው የምትሆነው?የቀንም ሆነ የሌት ህልሟ እንደሆነ ይቀጥላል? ከቀጠለስ እንዴት ልትቋቋመው ትችላለች?
እጇን ዘረጋችና አጠገቧ የተኛችውን የጊፊቲ ሆድ ላይ በቀስታ አሳረፈች…ጊፍቲም ከትራሷ ገልበጥ አለችና ፊቷን ወደእሷ ዞራ በሀዘኔታ አየቻት፡፡
‹‹ምን አለ እኔም እንደአንቺ ለቃልዬ አርግዤ ቢሆን…ማለት ልጅ አስረግዞኝ  ጥሎልኝ ቢሄድ?››
‹‹እኔም አንድ ነገር ልንገርሽ…››
‹‹ምንድነው ንገሪኝ››
‹የቃልዬን እስከ ወዲያኛው ጥሎኝ መሄድን ስሰማ ወደውስጤ ከመጣው የፀፀት ሀሳብ አንዱ ምን አለ ይሄ የፀነስኩት ልጅ የቃልዬ በሆነ የሚል ነበር..እርግጥ መድህኔ በጣም ጥሩ ኃላፊነት የሚሰማው መልካም አባት እንደሚሆን አውቃለሁ…እሱን ስላገኘሁም እራሴን እንደእድለኛ ነው የምቆጥረው…የልጅነት ህልሜንና  የዘመናት ፍላጎቴን ሁሉ ሊያሞላልኝ የሚችል ሰው ነው…ግን መድህኔን የማፈቅርበት ጥልቀት የኩሬ ያህል ሲሆን የቃልዬ ግን ውቅያኖስ አይነት ነው..እና ለዛ ነው እንደዛ ልመኝ የቻልኩት››
ዝም ብዬ ፈዛ አየቻት..ይሄን የተናገረችው ከቀናቶች በፊት በሰላሙ ጊዜ ቢሆን ኖሮ በርግጠኝነት ልዩ አንገቷን ፈጥርቃት ልትገላት ሁሉ  ትችል ነበር..አሁን ግን ያንን ማድረጉም ብቻ ሳይሆን እንደዛ አይነት ስሜት ማስተናገዱም ጥቅም አልባ እንደሆነ ተረድታለች....በዛ ለይ በመንፈስም ሆነ በስጋዋ ደንዝዛለች…
‹‹ግን ከቃልዬ ይሄን ሁሉ አመት ሳታረግዤ እንዴት በዚህች በጥቂት ወራት ከመድህኔ ልታረግዢ ቻልሽ?፡፡››
‹‹ከቀል ጋር በትንፋሽ ነው ማረግዘው?…››
‹‹ማለት….?››
‹‹እኔና ቃል እኮ  ወሲብ ፈፅመን አናውቅም››
‹‹ማለት…ብዙ ቀን እኮ እሱ ጋር አድረሽ እንደወጣሽ… ሲያደክመኝ እንዳደረ ምናምን እያልሽ ስትጎሪርብኝ ነበር››
‹‹ፈርቼሽ ነዋ…..ቃልዬን እንዳትመኚውና እንዳትቀሚኝ ..ተስፋ ላስቆርጥሽ ብዬ ነው…ማለት ከአመታት በፊት  አብሬው ብዙ ጊዜ አድር ነበር..በኃላ ግን ዝም ብሎ ማደሩ ስቃይ ስለሆነብኝ ወስኜ አቆምኩ…..››
‹‹አረ የምን ጉድ ነው..ቆይ ለምን…..?››
‹‹ምነው ገረመሽ..አንቺስ ከመድህኔ ጋር ለምን;?››
‹‹እኔ እንጃ ብቻ የእናንተን በጣም ደጋግሜ ስላመነዠግኩት ነው መሰለኝ አልተዋጠልኝም…››
‹‹መድህኔን ስለወደድኩት..ወይም ቃልዬ ሀብታም ስላልሆነ ይመስልሻል ከቃልዬ ጋር አቋርጬ ከመድህኔ ጋር የሆንኩት ነው  ወይስ አንቺ ስላለስፈራራሺኝ…?››
‹‹እና ለምንድነው?››
‹‹ሳላውቅ ድንገት ከመድህኔ ጋር ተሳሳትኩና ወሲብ ፈፀምኩ..ድንግልናዬን አስረከብኩት ….ወደቃልዬ ጋር እንዴት ልመሰለስ .. ?ሌላ ሰው ቢሆን ችግር የለውም ቃልዬ ግን?
‹‹ቃል ምን ይልሻል..?ምንም አይልሽም እኮ ነበር አንደውም በግልፅ ነበር ይቅርታ የጠየቀሽ፡››
‹‹አውቃለሁ ..ችግሩም እሱ ነው….እኔ በአእምሮው ካለሁበት ቦታ ተንሸራትቼ ወርጄያለሁ.ቃልዬ...የወርቅ ካባ አድርጎ  በብር የተለበጠ  ጫማ ተጫምቶ ወደቤቴ ሲመጣ ውስጤ በሀሤት ትደንሳለች ...ድንግልናዬን በክብር ልሰጠው ለዘመናት ጎጉቼያለሁ ።.እሱ ፍጽም ድንግል እንደሆነ አውቃለሁ.....ማወራሽ ስለስጋዊ ድንግልና አይደለም….ለዛ ግድ የለኝም...ልብ ከቆሻሻ ሀሳብ ጋር ያልተዋሰበ ንፅህ ፤ከክደትና ከማጭበርበር ጋር ያልተጋደመ  ክብር  ነው ።ለዚህም ማረጋገጫው እስሬ ሆኖ ሲያወራኝ  ልቤ ውስጥ ብርሀን ሲፍለቀለቅ ይታወቅኛል….የሆነ አካሉ የሰውነቴን ጫፍ ሲነካው ነፍሴ ድረስ የሚዘልቅ ደስታ ይሰማኛል……ድንገት አግኝቼው  ሰላም ሊለኝ  ከንፈሩ ጉንጬን በስሱ ሲነካው እንኳን .....ከልቤ  የፍቅር ደም ሲንጠባጠብ ይሰማኛል ...
‹‹ከዚህ በፊት ስለእሱ ምን እንደሚሰማኝ ነግሬሽ ነበር …? የእኔን ስሜት እኮ ነው እየነገርሺኝ ያለሽው…››
‹‹አየሽልኝ..ቃልዬ ማለት እንዲህ ነው..ሁለት ሴቶችን ጫፋቸውን ሳይነካ በተመሳሳይ የእብደት በሚመስል ስሜት አንዲያፈቅሩት ማድረግ የሚችል የተለየ ሰው ነው፡፡እሱ ለእኔ መስታወቴ ነው.. ፊት ለፊቴ ተቀምጦ በተመስጦ  ሳየው በጥልቀት ርቄ ሄዳለሁ…. እያንዳንዷን የልጅነት ጊዜዬን በምልስት አስታውሳለሁ… ሀዘኔንና ደስታዬን መልሼ አጣጥማለሁ…. እንዴት እንደተሰራው…? የት ጋር  ማደግ እንደጀመርኩና? የት ጋር ደግሞ እንደተሰበርኩ? ሁሉ እንዳስታውስ ያደርገኛል…እናም በዛ ምክንያት ቃልዬን ሳገኝ  ነፍሴ ሀሴት ታርጋለች…ውስጤ ይፍነከነካል..፡፡ግን ይሄ ስሜት ሁሌ አይደለም የሚያስደስተኝ ..አንዳንዴ ትናንቴ ፈፅሞ የሚያስጠላኝ ጊዜ አለ..አንገቴን ወደኃላ አዙሬ አይኖቼን ትናንቴ ላይ ተክዬ ማሰላሰል የሚያስከትልብኝን ህመም መቋቋም አቅም በማጣበት ጊዜ እሱን ለማግኘት ከራሴ ጋር ትግል እገባለሁ  …ምክንያት ፈጥሬ እሸሸዋለሁ….
ግን የሰዓታ ክፍተት እንኳን መቆየት ተስኖኝ  ግራ ይሁን ቀኝ ልቤ ላይ ብቻ በማለውቀው ቦታ በሆነ የልቤ ክፍል ብቸኝነት  ይለበልበኛል…መለብለብ ብቻም ሳይሆን እብጠትና ጥዝጣዜም አለው…ግን ደግሞ መቻል እስከምችል ደረስ እችለዋለሁ…ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን..ከዛ መተንፈስ ሲያቅተኝና ከአቅሜ በላይ ሲሆን ያለምን ማቅማማት ወደ አለበት በርሬ እሄዳለሁ ፡፡ፊቱ እገተራለሁ…የተጨማደደ ፊቱ በደስታ ፀደል ሲፈካ…ተከርችሞ የነበረ ጥርሶቹ ተፈልቅቀው  መሳቅ ሲጀምሩ አይና እደሰታለሁ....ተንደርድሬ ሄጄ እንጠለጠልበታለሁ….ያለምንም ቅሬታና ወቀሳ ወደላይ አንጠልጥሎ ልክ እንደእርግብ በአየር ላይ ያንሳፍፈኛል…..እና አሁን ያ የልጅነተ መስታወቴ ነው የተሰነጣጠቀዉ… የትዝታ ድልድዬ ነው ተንዶ የተሰበረው…..ወደትናንቴ ለመሻገር በጣም ይከብደኛል….ግማሽ  ሆኜያለሁ
‹እውነትሽን  ነው…..አሁን ሳስበው ቢነካንስ ኖሮ…ማለቴ ያው ነካክቶን ጥሎን ሂዶ ቢሆንስ..?››
‹‹እሰከ መጨረሻ ያበቃልን ነበራ…››ብላ መለሰችላት፡፡
‹‹እኔ እኮ አሁንም እስከመጨረሻው ነው ያበቃልኝ…›
‹‹ቆይ ግን ወደ ወሬሽ ልመልስሽና..ቃልዬንም እኮ ከዚህ በፊት ማለቴ አንቺ ከመድሀኔ ጋር ተገናኝተሸ ከመጀመርሽ በፊት ስለሁለታችሁ ግንኙነት ጠይቄው ነበር…››
👍8910😁1
#ባል_አስይዞ_ቁማር››


#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ክረምቱ ሲመጣ ሰውነቷ ይሸማቀቃል።ዝናብ ትወዳለች ግን ነጎድጓድና መብረቅ ያስፈራታል። በሰማዩ ላይ ቀስተደመና ሲነጠፍ ልቧ ላይ የተጠመጠመ ኒሻን ይመስለትና ትፈነጥዛለች፡፡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለሙ ከኢትዬጰያ መቀነት ጋር መመሳሰሉ ሁሌ እንዳስደመማት ነው።እርግጥ ሳታድግ የቀሰት ደመና የተሸመነባቸው ቀለሞች ሶስት ብቻ ሳይሆኑ ሰባት እንደሆኑ ማወቅ ችላለች።ግን ደግሞ ማወቅና ማመን ይለያያል...ዛሬም አይኖቾን አንጋጣ ቀስተደመናውን ሳታይ በትክክል ወደውስጧ ደምቀው በመግባት የሚውለበለብት እነዛው በልጅነቷ የምታውቃቸው ሶስቱ ቀለማት ብቻ ናቸው።አረንጓዴ ቢጫ ቀይ..."አንዴ አትለከፍ"ትላለች አክስቴ አዎ ልክፍት ነው።››አለች
በማግስቱ ጥዋት መድህኔ መጥቶ ጊፍቲን ወሰዳት….ስራ ስለምትገባ ቅያሪ ልብስና ለሁለቱም የሚሆን ቆንጆ ቁርስ አሰርቶ ነበር  ይዞ የመጣው….ልክ የእሷ እንዳልነበረና ከዚህ በፊት እንደማታውቀው ወንድ አይነት ትክ ብላ አየችው…አሳዛኝና እንስፍስፍ ወንድ ሆኖ ነው ያገኘችው...እንስፍስፍ ያለችው አፍቃሪ ላለማለት ጎርብጦት ነው….‹‹አሁን ጊፊቲን ካገኘ በኃላ ተቀይሮ ነው ወይስ በፊትም ከእኔ ጋር እያለ እንዲህ ነበር ..?››በወፍ በረር ወደኃላ መለስ ብላ ለእሷ የሚያደርግላትን እንክብካቤዎች ለማስታወስ ሞከረችና ሽምቅቅ ብላ ቶሎ ተመለሰች‹‹…ከእሱ ምንም የተለወጠ ነገር የለም ልዩነቱ እኔ መሆኔና ጊፊት መሆኗ ላይ ነው…እሷ ከእሱ የሚሰጣትን ፍቅርና እንክብካቤ በትህትና እና በምስጋና ተቀብላ በፈገግታ ምላሽ ስትሰጥ እኔ ግን በወቅቱ አደርግ የነበረው በብስጭት በመግፋትና በተቃውሞ ነበር ሞራሉን የምሰብረው….እንደውም አሁን መጠየቅ ያለብኝ ያን ሁሉ ጊዜ እንዴት ታግሶኝ ኖረ….?. ›ስትል ድምዳሜ ላይ ደረሰች፡፡
ልብሷን ቀየረችና ካመጣው ቁርስ አንድ ሁለቴ ጎርሳ ጉንጩን ሳመችውና ስትወጣ መድህኔ ደግሞ ወደልዩ ዞሮ‹‹…እንዴት ነው ግፍቲን ቢሮ ካደረስኮት በኃላ መጥቼ ወደቤት ልውሰድሽ እንዴ.?.››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ አልፈልግም..አላየህም እንዴ .?.መኪናዬ እኮ እዚህ ግቢ ውስጥ ነች…››
‹‹እንዴ..ለመንዳትም አቅም የለሽ ..መጥቶ ይውሰድሽ››ጊፍቲ መሀከል ገባች…‹‹.ይቺ ልጅ በፊት ሳገኛት እንደገመትኮት አይነት አይደለችም..ቀናና ጥሩ ሰው ነች..አሁን ሌላ ሴት ብትሆን እኮ ጭራሽ እንዲህ ስላለ ፍቅረኛዋን በግልምጫ ነበር የምታደባየው..መልሳ ብትወስድብኝስ በሚል ስጋት እራሷ ደንብራ አካባቢዋ ያለውን ሰዎች ሁሉ ታስደነብር  ነበር…››ስትል አብሰለሰለች
አይ ..አልፈለግም..እኔ በአሰኘኝ  ሰዓት መንዳት እችላለሁ..ደግሞ ብሔድም ከሰዓት ነው››
‹‹እሺ በቃ ቁረሱን  ተነሺና ብይ..እና ከፈለግሺኝ ደውይልኝ››አለና  ቤቱን ዘግተውላት ተያይዘው ሄዱ ፡እሷም መልሳ እራሷን ትራስ ውስጥ ቀበረችና ወደትካዜዋ ገባች..እራሷን ትራስ ውስጥ ስትከት የቃልን ጠረን በአፍንጫዋ እየተሹለከለከ ወደመላ ሰውነቷ በደምስሯ አማካይነት ተሰራጨና የንዝረት ስሜት በሰውነቷ ለቀቀባት፣
//
በሶስተኛ ቀን እናቷ መድሀኔ እየመራት ያለችበት ድረስ መጣች....ስታያት እንባዎን መቆጣጠር ነው ያቃታት....፡፡

"ምነው መድህኔ ..ምነው ልጄ እንዲህ እስክትሆን እንደው ሁሉ ነገር ቢቀር እህትህ አይደለች?"በማለት ወቀሰችው፡

"እትይ...ከገባችበት ነገር እንድትወጣ በተቻለኝ አቅም ያልጣርኩ ይመስልሻል...?..ሰሞኑን ስራ እንኳን በቅጡ መስራት አልቻልኩም...በቀን ከሶስት ጊዜ በላይ እየተመላለስኩ ለምናታለሁ..ግን ያው እንደምታይው ነች"አለ ..ጥረቱና ልፋቱ መና ስለቀረበት ቅር እንዳለው በሚያሳብቅ የምሬት ንግግር

የልዩ እናትም ከጠንካራ ንግግሯ መለስ አለችና"ልጄ የቻልከውን እንደምትሞክር አውቃለሁ ..የምናገረውን አትይብኝ ደንግጬ ነው"አለችው

"ችግር የለም ይገባኛል....አሁን እናንተ አውሩ ...እዚሁ አካባቢ ነኝ… ስትጨርሺ ደውይልኝ።"ብሎ እናትና ልጅን አፋጦ ወጥቶ ሄደ...እንደዚህ ያደረገው በነፃነት እንዲያወሩ በማሰብ እንደሆነ ሁለቱም ገብቷቸዋል ።ልዩ ግን ምንም የምታወራበት ጉልበት የላትም...ለዛውም ከእናቷ ጋር"

"ልጄ በራሴ አፍሬያለሁ...እኔ እኮ እራሴን እንደዘመናዊና ግልፅ እናት ነበር  የምቆጥረው ..ግን ተመልከቺ ልጄ በዚህ ልክ የምታፈቅረው ሰው ኖሮ እንኳን አላውቅም...."

"እማዬ እሱ የእኔ ጥፍት ስለሆነ አትዘኚ..."አለቻት።

‹‹አይ ልጄ ...ለነገሩ ተይው አሁን ነገሮች ከተበለሻሹ በኃላ ብናወራው ምን ፋይዳ አለው....?..አሁን ይበቃሻል ማልቀሱም ማዘኑም በገዛ ቤት ያምራል...ልጄ ወደ ቤታችን እንሂድ"አለቻት ፈራ ተባ እያለች...ልዩ ምንም አላለቻትም… የውስጧን ጥንካሬ አሰባስባ ቀስ ብላ ተነሳችና እግሯን እየጎተተች ወደ መኝታ ቤት ስትራመድ ውስጥ ገብታ በራሷ ላይ ልትቆልፍ መስሏት የሰጋችው እናት"ወዴት እየሄድሽ ነው ልጄ?"ስትል ጠየቀቻት፡፡

"መጣሁ… የማሳይሽ ነገር አለ›› በማለት ወደ ውስጥ ገባችና  ማንጠልጠያ ላይ ከተንጠለጠለው ቦርሳዋ ውስጥ እጇን ሰዳ  የምትፈልገውን እቃ ያዘችና ወደሳሎን ተመለሰች..."
እናቷ ፊት ለፊት አስቀመጠቻት ...እናቷ ደንግጣ አንዴ እሷን አንዴ ጠረጰዛው ላይ ያለውን ዕቃ በማፈራረቅ ታየው ጀመር… ‹እማ ..በቀደም ለት  ዝግጅት አለብኝ ብዬ እንደዛ ለግማሽ ቀን አምሬና ተሽቀርቅሬ እነዚህን ሁለት ቀለበቶች  ገዝቼ  ወደ እዚህ ቤት የመጣሁት ለቃልዬ ቀለበት ላስርለት ነበር..፡፡.በድፍረት እንዳፈቀርኩት ነግሬው እንዲያገባኝ ልጠይቀው ነበር...ስደርስ ግን ሁሉን ነገር ጣጥሎ ገዳም እንደገባ  የሚገልፅ ደብዳቤ ጥሎልኝ ሄዷል...ይሄ ሁሉ የእኔ ጥፍት ነው ። አረባም ፡፡››

"ምን አጠፋሽ የእኔ ማር....?.."

‹‹ምን ይሄን ሁሉ ጊዜ አዘገየሸ...ከ15 ቀን በፊት ላደርገው እችል ነበር እኮ...ከወር በፊትም ባደርገው ጥሩ  ነበር"

"ልጄ እንደው ቢጨንቅሽ ነው...ይሄ እንደሚመጣ በምን ልታውቂ ትቺያለሽ....?.."

"ደግሞ የዛሬ ሳምንት በጣም አበሳጭቼዋለሁ..››

"ምን አድርገሽ ልታበሳጪው ትቺያለሽ?"

‹‹ሰርቄ ነዋ...ሆቴል ልጋብዝህ ብዬ ወስጄ ሰረቅኩ...በእፍረት አንገቱን ደፍቶ የሠረቅሽውን መልሺ አለኝ .....እኔም መለስኩ ..ከዛ ሲመክረኝ ዋለ ..በማግስቱ  ይቅርታም ልጠይቀው እንደማፈቅረውም ልነግረው ቀጥሬው በሰዓቱ  ብገኝ  እንዳልኩሽ ሆነ...ዳሩ ሌባን ማን ማፍቀር ይፈልጋል?"
"ልጄ አሁን እኮ ባለፈ ነገር ዝም ብለሽ ነው የምትጨናነቂው... እንዳልኩሽ ተነሽና ወደቤታችን እንሂድ፤ከዛ  በእርጋታ እንደ እናትና ልጅ አናውራ። የሚስተካከለውን እናስተካክላለን"

"የምለውን አልሰማሽም እንዴ እማዬ?"

"ምን አልሽ?"

"እሱ ሸሽቶ ቢሄድም እኔ እኳ አግብቼዋለሁ ....ከተቀመችበት ተንጠራራችና ቀለበቶቹን አነሳች የራሷን ቀለበት አጠለቀች
"...እማዬ ደግሰሽ ባትድሪኝም እኔ አግብቼያለሁ...እና እዚሁ ሆኜ መጥቶ ይሄን ቀለበት እስኪያጠልቅ እጠብቀዋለሁ።"

"ምን ነካሽ...?በግልፅ እኳ መቼም ላይመለስ አንደኛውን ወደ ገዳም እንደገባ ነግሮሻል?..እና ምንድነው የምትጠብቂው ?እስከመቼስ ነው የምትጠብቂው?"

"እማዬ ልቤ ተመልሶ እንደሚመጣ እየነገረኝ ነው...ከሁለት አመትም ሆነ ከሀያ አመት በኃላ አንድ ቀን ተመልሷ ይመጣል...እና እዚሁ ቤት ሆኜ እጠብቀዋለሁ።››
👍827🥰5😁5
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አርባ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ያልተኖረበት የአንድ ወር ቅድመ ክፍያ ቃል ከፍሎ የሄደ ቢሆንም እሷ የስድስት ወር ተጨማሪ ቅድመ ክፍያ ከፈለች...ይሄንን ቅድመ ክፍያ ቃል ሲኖርበት ለነበረ ክፍል ብቻ ሳይሆን ከዛ ቀጥሎ  ለነበረች አንድ ክፍል ቤትም ጭምር ነው የከፈለችው። ክፍሏን እንደአዲስ ቀለም አስቀባችው.....ሙሉ እቃ ፤ አልጋ፤አነስተኛ ፍሪጅ፤ቴሌቪዠን አንድ ጠረጰዛና ሁለት ወንበሮች አስገባችበት ...እንዲህ ያደረገችው የቃልን አባት ከመቄዶንያ አስወጥታ እቤት በማምጣት እራሷ  ልትንከባከባቸው ስለወሰነች ነው።አዎ ይሄንን ዕቅድ ካቀደችበት እለት አንስቶ  በውስጧ ደስታ እየተሠማትና ከድብርቷም በመጠኑም ቢሆን እየተላቀቀች ነው።

አሁን ሙሉ በሙሉ ዝግጅቷን ስላጠናቀቀች ወደሜቅዶኒያ ሄዳ አባትዬውን   የምታመጣበት ቀን ነው።ከመውጣቷ በፊት በሞባይሏ ያዘጋጀችውን ቤት ፎቶ ደጋግማ አነሳችው...ለመምጣት  አሻፈረኝ እንዳይሏት ምን ያህል ተጨንቃ እንዳዘጋጀችላቸው   በምን ያህል መጠን ቁርጠኛ መሆኗን  እሳቸውን ለማሳመን እንዲያግዛት አስባ ነው።በዛ ላይ በማሳመኑ ስራ ቀላል እንዲሆንላት ከእሷ በላይ የሚያውቋትንና ከልጃቸው ባልተናነሰ ያሳደጓትን ጊፍቲን ይዛ ነው የምትሄደው።

የራሷን መኪና እየነዳች እግረ መንገዷን ጊፍቲን ካለችበት አንስታ መቂዶኒያ ደረስን.... መኪናዋን አቁማ ከጊፍቲ ጋር ጎን ለጎን በዝግታ እርምጃ(ያው እርጉዝ ስለሆነች)ወደ ቃል አባት ያሉበት አካባቢ ሲደርስ ያልተለመደ ግርግር ነገር ገጠማቸው...ጊፍቲን ወደኃላ ተወችና ፈጠን ፈጠን እያለች ወደፊት ተጓዘች.... ደረሰች፡፡ ከአስር የሚበልጡ ሰዎች በቦታው ይተረማመሳሉ...አንዳንዶቹ ከንፈራቸውን ይመጣሉ...የሆነ ቀፋፊ ስሜት ሳትፈልግ በግድ ወደ ሰውነቷ ሲሰርግ ታወቃት..ወደ አንድን አዛውንት ተጠጋችና"አባባ ምን ተፈጥሮ ነው?"ስትል  ጠየቀቻቸው፡፡

"ያው ሰው ከንቱ አይደል?አንድ ጓደኛችን ሞቶ ነው"

"ወይ እግዚያብሄር ነፋሱን ይማር."አልኩኝ፡፡

‹‹ወዬኔ ጋሽ ሞገስ...በቃ ሞተ "እያለች አንድ ሴት በስሯ አለፈች፡፡

"ጋሽ ሞገስ?  ይሄን ስም የት ነው የማውቀው? ስትል እራሷን ጠየቀች ተምታባት..በዚህ ጊዜ ከኃላዋ ቀርታ የነበረችው ጊፈቲ ስሯ ደርሳ ነበር.."

"ምን ተፈጠረ ?"ስትል ጠየቀቻት፡

"ሰው ሞቶ ነው?ጋሽ ሞገስ የሚባሉ ሰውዬ ናቸው አሉ"ነገረቻት

"ሞገስ?ሞገስ ማን?"አደነጋገጧ አስፈሪ ነበር፡፡

‹‹ምነው ታውቂያቸዋለሽ እንዴ?››

"የቃልዬ አባት...."
ዠው አለባት...‹‹የተምታታብኝ ለካ ለዛ ነው?"አለች፡፡

‹‹ምንድነው እየሆነ ያለው? ማነው የነካሽው ሁሉ ወድያው ይብነን ወይ ይክሰም ብሎ የረገመኝ?።ስትል አማረረች
""""
ከጊፍቲ ጋር ሆነው የቃልና አባት ቀብር በተገቢው መንገድ አስፈፀሙ....ቅልብጭ ያለች የእብነበረድ ሀውልትም አሰራችላቸው። እሳቸው ከሞቱ በኋላ በፊት የሚሰማት  ሀዘን ብቻ አይደለም እየተሰማት ያለው ።ጉልበት የማጣትና ተስፋ የመቁረጥ ሰሜት ጭምር ውስጧን እያወደመው ነው። አሁን በዚህ ሰአት እሳቸው ሀውልት ጋር ቁጭ ብላ እየተከዘች ነው፡፡

ፊት ለፊቷ ዝርፍፍ ያለች የብሳና ዛፍ ትታታለች ...የበጋው ንዳድ እሷን ብቻ ሳይሆን ዛፏንም የጎዳት መሰላት።ቅርንጫፎቾ የተሸከሞቸው አብዛኛው ቅጠሎች ወይበዎል።አረንጎዴ ቀለማቸው ተመጦ ወደ ቢጫነት እያዘገሙ ነው።ድንገት ከወደ ምዕራብ በኩል ብዛት ያላቸውና ከእሷና ከዛፉ በተቃራኒው በውበት ያሸበረቁ ወፎች ተንጋግተው  መጥተው ሰፈሩበት ...ግማሽ የሚሆነው ቅጠሉ እየተቀነጠሰ ወደ መሬት ረገፈ...፡፡አዘነች ውስጧ እስኪሰበር ድረስ አዘነች..፡፡ያዘነችው ለዛፉ በማዘን አይደለም ለራሷ እንጂ...የእሷም ለዘመናት የገነባችው ተስፋዋ ድንገት መጥቶ ህይወቷን በነቀነቀው መከራ ልክ እንደዚህች ዛፍ ቅጠሎች ነው እርግፍ ያለው።እርግጥ ዛፍ ከጥቂጥ ሳምንታት በኃላ ክረምት ገብቶ ዝናብን ሲያርከፈክፍለት በደስታ ከድርቀቱ አገግሞ እንደሚለመልም መወየብ ታሪክ ሆኖ አረንጓዴ እንደሚለብስ ታውቃለች .‹‹.የእኔስ  ዝናብ መቼ ይሆን አስገምግሞ መጥቶ የሚያርሰኝ እና ከድርቀቴ የሚፈውሰኝ።›ስትል ጠየቀች…

ሰው ግን  በሚሊዬን ህያዋን መካከል እየኖረ ሚሊዬን ህያዋንን በመንገድ ላይ እየገፈተሩና እየገላመጡ መጥቶ እንዲህ  በድን ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ ከበድን ጋር ማውራት.?››ስትል በራሷ  ድርጊት ተደመመች፡፡

"ያው የቃል አባት ስለሆኑ የእኔም አባት ኗት...ደግሞ ያው አባትም የለኝም። ምን አልባትም እንደእርሶ የሞተ ይመስለኛል..እንደዛ ከሆነም  የሁለታችሁንም ነፍስ አምላክ ይማራት።››ትንፋሽ  ወስዳ ጉሮሮዋን በምራቋ ካረጠበች በኃላ ንግግሯን አራዘመች፡፡

<<እና ይሄውሏት ቃል ጥሎኝ ከጠፍ በኃላ ለቀናት ሳዝንና ስጨነቅ ከርሜ ነበር እና ድንገት ስለእርሶ ትዝ ሲለኝ ውስጤ ተስፋ ሰነቀ...የፈለገ በእኔም ሆነ በጠቅላላ አለሙ ቢጨክን በአባቱ አይጨክንም ስል አሰበኩ፡፡በእርሶ ላጠምደው ወሰንኩ። ያው ያውቁ የለ እኛ ሴቶች ያፈቀርነውን ወንድ የራሳችን ለማድረግ የተለያዩ ስውር ዘዴዎችን እንጠቀማለን...ለምሳሌ የምናፈቅረው ወንድ አልጨበጥ ብሎ ካስቸገረን ሌሎች ወንዶች እየፈለጉንና እየተከተሉን እንደሆነ እንዲያውቅ እናደርጋለን...ቅናት ውስጥ ገብቶ ከመቀደሜ በፊት ልቅደም እንዲል እኮ ነው ።ወይም ደግሞ የተሳሳትን በማስመሰል  ልጅ እናረግዝና ውሳኔው ከባድ እንዲሆንበት እናደርጋለን ….አዎ በፍቅር ጉዳይ ሴቶች ቁማርተኞች ነን፡፡

እንደሚያውቁት እኔ ደግሞ ቃልዬ አብሮኝ ስለሌለና  የት እንዳለም ስለማላውቅ እንደዛ ማድረግ አልችልም..ስለዚህ የነበሩኝ ብቸኛ የመጫወቻ ካርዴ እርሶ ነበሩ  ። ወደቤታችን ማለቴ ወደቃል ቤት ልወስዶት ለቀናት ለፍቼ ብዙ ብዙ ነገር አዘጋጅቼ  ያማረች ክፍል አዘጋጅቼሎት ነበር...የምትንከባከቦትም ወጣት ነርስ ቀጥሬሎት ነበር..እናም ደግሞ እስከመጨረሻው ድረስ ልንከባከቧት አልሜና ወስኜ ነበር...ከአሁን በኃላ አስርና ሀያ አመት ይኖራሉ የሚል ግምት ነበረኝ...እና በዛ የጊዜ ርዝመት ውስጥ ቃል አንድ ቀን እርሷን ለማየት ሲል ብቻ  ተመልሰሶ ሊመጣ ስለሚችል አንድ ላይ ሲያገኘን ይደሰታል..እናም ምን አልባት ዳግመኛ ጥሎኝ ለመሄድ  ልቡ አሻፈረኝ ትላለች የሚል ምኞት ሰንቄ ነበር ...እንደው ያ ባይሆን እንኳን  አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል እያልኩ ነፍሴን በተስፋ ሞልቼ ህይወቴን በጥበቃ ለማስቀጠል  ወስኜ ነበረ...ግን ምን አልባት የልቤን ሀሳብ አማልዕክቱ ሰምተው መጥተው ሹክ ብለዎት መሠለኝ የሀሳቤ ተባባሪ ላለመሆን ሞተው ጠበቁኝ። ግድ የለም አሁን በሁሉ ነገር ተስፋ ቆርጬያለሁ...እሱን ለመጠበቅ ያለኝን እቅድም እርግፍ አድርጌ ትቼዋለሁ..ግን ህይወቴን እንዴት እንደምቀጥል ምንም አላውቅም..?መቼ መሳቅና መቼ ደግሞ ማልቀስ እንዳለብኝ ግራ ገብቶኛል...በሉ ደህና ይሁኑ...አልፎ አልፎ ብቅ ብዬ አዬዎታለሁ።ቃልዬ አደራ ብሎኛል።

ልፍለፍዋን  ጨርሳ ከመቃብሩ ድንጋይ ላይ ተነሳች፡፡

ይቀጥላል
👍11417👎1🔥1
#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አርባ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ጎነኛው መቃብር ስር አንድ ሰው  እንደሀውልት ተገትሮ   ቆሟል...እዛ ያለ ይመስላል እንጂ በድኑ ብቻ እንዳለ ያስታውቃል። ሀዘኑ ሀዘኗን ቀሰበሰባት። ምኑ ይሆን የሞተበት"የማወቅ ጉጉት አደረባት።አንገቷን አሰገገችና ሀውልቱ ላይ የተፃፈውን ፁሁፍ አነበበች ወ/ሮ ቅድስት ሀምሳሉ 1980 ፡፡ 2015ዓ.ም ይላል።እድሜዋን በአእምሮዋ አሰላችው ።የሰውዬው  እድሜ ገመተች ..አርባ አመት ቢሆነው ነው በቃ ፍቅረኛው ወይም ሚስቱ ነች ስትል አሰበች።እንዲህ ካሠበች በኋላ ለሰውዬው  ያላት ሀዘኔታ ጨመረ፡፡

ለማታውቀው ሰው በዚህ መጠን ሰታዝን ይሄ የመጀመሪያ ገጠመኞ ነው። ምን አልባት እሷ  ገና ለገና ፍቅረኛ እንዲሆናት  የፈለገችው ሰው  ጥሏት ስለተሠወረ  እንዲህ እንቅሽቅሽ ካለች እሱ ደግሞ ፍቅረኛው ወይም ሚስቱ ለዘላለም ጥላው ሞታ ከምድር በታች አፈር ለብሳ ስትቀበር እንዴት ሊያዝን እንደሚችል አሰላችና ሰቀጠጣት...?ያው ለእሱ እያዘነች ቢመስላትም  በተዘዋዋሪ ለራሷ እያዘነች ነው። ወደኋላ  ተመለሰችና ለቃል አባት አምጥታ ሀውልቱ ላይ ካስቀመጥቻቸው አምስት የፅጌረዳ ዝንጣፊዎች መካከል ሁለቱን አነሳች ‹‹ይቅርታ በሚቀጥለው ስመጣ የእነዚህንም ፋንታ ይዤ መጣለሁ... ብድር ነው›› በማለት...ወደሰውዬው ሄደች.. አጠገቡ ቆመች...ከደቂቃዋች በኃላ ዞር ብሎ አያት አየችው.  ።

ጎንበስ አለችና አበባውን በሀውልቱ መሀከል ላይ አስቀመጠችው...፡፡ይደሰታል  ..ያመሰግነኛል ብላ ስትጠብቅ  በቅፅበታዊ ንዴት አይኖቹን አጉረጠረጠባት... ፊቱ በአንዴ ደም ለበሰ...አይኑ ውስጥ የሚንቀለቀል ከገሀነም እሳት የረገፈ ፍም ነው ያየችው..በዚህ መጠን ሰው አስፈርቷትም አስደንግጧትም አያወቅም....፡፡ጎንበስ አለና ያስቀመጠችውን አበባች አነሳና ብጥቅጥቅ አድርጓ ቆራረጣቸው፤ ተበታትነው መሬት ከመርገፍ የዳኑትን ወደ አፍ ከቶ  እያኘከና እየበጣጠቀ መትፍት ጀመረ…፡፡አንድ አምስት እርምጃ ወደ ኃላ ሸሸት አለችው...

‹‹እሷ አበባ ፈፅሞ አይገባትም.››."አሁን ይሄን መቃብር ብንከፍተው ስጋዋን እንዳለነው የምናገኘው..አፈር አይበላትም߹ ከበላትም ለአፈሩ አውዳሚ  አሲድ ነው የምትሆንበት ፤ምስጦችም አይበሏትም ከበሏትም ሰውነታቸው ተመርዞ ያልቃሉ"አላትና ጥሏት ሄደ...በህይወቷ በሞተ ሰው ላይ ሲሰነዘር የሰማችው በጣም መራርና አስከፊው  ወቀሳ ነው ፡፡በመሄዱ እፎይ አለች ..እዛ ከእሷና እሱ ውጭ  ሰው በሌለበት የቀብር ስፍራ  ሲጥ አድርጎ የሚገላግላት መስሏት በፍራቻ መንቀጥቀጥ ጀምራ ነበር ።አይ የሠው ልጅ ከደቂቃዎች በፊት   ለመኖር ያላት ጉጉት ተሟጦ አልቋል ስትል ነበር ..አሁን ደግሞ ህይወቷ ላይ ጥቃት እንዳይደርስ እየሠጋች ነው።እራሷን አረጋጋችና ኩስ ኩስ እያለች ከኋላ  ተከተለችው፡፡

ከመቃብር ቅጥር ጊቢ  ወጥቶ አስፓልት ጠርዝ ላይ ሲደርስ  እርምጃዋን ከእሱ እርምጃ ጋር ማስተካከል ቻለች....ዝም ብሎ መራመድን ቀጥሏል"ማኪያቶ ልጋብዝህ›› አለችው ..ሀሳብ ድንገት ነው የመጣላት፡፡

"አይ  ማኪያቶ አልወድም...አሁን  ጂን  ነው ምጠጣው"

‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው.. እንደውም እኔም እሱን ብጠጣ ጥሩ ይመስለኛል።››

"ጥሩ"
"መኪናዬን ግን  ፊታችን ያለው ሆቴል ነው ያቆምኩት… እዛ ብንጠጣ ቅር ይልሀል..?."ዝም ብሎ አቅጣጫውን ወደነገረችው ሆቴል አስተካከለ።ያ ማለት በሀሳቧ መስማማቱን ማሳያ አድራጋ ወሰደችውና ተከተለችው፡፡እንደዛው ጎን ለጎን እየተራመዱ ምንም ሳያነጋገሩ  ሆቴል ደረሱ..  በፅድ ተክሎች የተከበች ከለል ያለች ቦታ መርጠው ተቀመጡ የሚቀመጡበትንም ቦታ የመረጠችው እሷ ነች..)እሱ ለመጠጡ እንጂ ለቦታው ግድም ያለው አይመስልም፡፡

"ስለደረሰብህ ሀዘን በጣም አዝናለሁ››አለችው ፈራ ተባ እያለች፡፡

የእሷን አስተያየት ችላ አለና"አባትሽ ናቸው?"ሲል ጠየቃት…ደነገጠች

"ምን? ማን?"

"ቀብሩን ነው ያልኩሽ"

"እ...የእጮኛዬ አባት ናቸው...ማለቴ የፍቅረኛዬ...   ማለቴ የማፈቀረው ልጅ አባት"

"በአንድ ፅኚ እንጂ..የምን መወነባበድ ነው?"

"ወድጄ ይመስልሀል"

"የት ነው"

"ማ ?"
"እሱ...የምታፈቅሪው ልጅ"

"ገዳም ገባ"

መልሷን ከሰማ በኃላ ያዝንልኝና  ያፅናናኛል ብላ ስትጠብቅ

‹‹ተገላገለ" ብሎ እርፍ።

"እንዴት እንደዛ ልትል ቻልክ?"

"ያው አንድ ቀን ልቡን ሰብረሺው  ስቃይ ውስጥ ከሚገባ እንዲ በደህናው ጊዜ ገዳም መግባቱ ይሻለዋል"

"እንዴት ልቡን ልሰበር እችላለሁ ከራሴ በላይ እኮ ነው የማፈቅረው"

"እዛ የተኛችው ማለት ቅድም አበባ  የሠጠሻት ሴትም ከአመታት በፊት እንዲሁ አንቺ ያልሺውን ቃል  መቁጠር ከምችለው ጊዜ በላይ ብላኝ ነበር"

"ታዲያ ምን ተፈጠረ?"

"ያው እንዳልኩሽ ነዋ የልብ መሠበር"

"ሁሉም ታሪኮች ፍፃሜያቸው እንደምታስበው አይደሉም"

"ናቸው..ቆይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ?"

"ጠይቀኝ"

"አሁን ጥሎሽ ገዳም ከገባው ልጅ በፊት ፍቅረኛ ነበረሽ"

"አዎ ነበረኝ"

"ታፈቅሪው ነበር?"

"በወቅቱ አዎ አፈቅረው ነበር"

"ጥሩ ...እንደምታፈቅሪውስ ነግረሽው አታውቂም"

"በወቅቱማ እንዴት አልነግረው ...ፍቅረኛዬ ነበር...እንደማፈቅረው ብዙ ጊዜ ነግሬው አውቃለሁ።"

"በቃ መልሴ ተመልሶልኛል"

ድንግርግሯ ወጣ ።ምን ለማለት እንደፈለገ ምንም አልገባትም።

‹‹የምኑ መልስ?"

"ያው መጨረሻውን አየሽው߹ ከዛ ፍቅረኛሽ ጋር አሁን አብረሽ የለሽም...የሌላ ወንድ ፍቅር ፍለጋ በየመቃብር ሀውልቱ ትዞሪያለሽ ߹ያ ፍቅረኛሽ ግን ምን እየተሠማው እንደሆነ ምን ያህል እንዳዘነ ?በምን ያህል መጠን እየናፈቅሽው እንደሆነ ?ምንም ትዝ ብሎሽ አያውቅም አይደል?።"

ለወንዶች ያለው ውግንናና ለሴቶች ያለው ጥላቻ ጠርዝ የወጣ ነው ብላ ስላሰበች አበሳጫት።

"ምን እያልክ ነው..?ቺት ስላረገብኝ እኮ ነው  የተለያየነው"

"እ እንደዛ ነው?" አለና  ጅኑን አንስቶ ተጋተው
‹‹ምነው?  በቂ ምክንያት አይደለም?"

"ለወንድ አዎ .ለሴት ግን አይደለም"

"አልገባኝም?

"ሴት  መጀመሪያውኑ  ለመለየት  አቀባብለ እየጠበቀች ካልሆነ በስተቀር ፍቅረኛዋ ችት ስላደረገባት ብቻ አታባርረውም"

ዝም አለች። ይሄ  የአስፈሪው እንግዳ ሰው ንግግር ለሌሎች ሴቶች ይስራ አይስራ ባታውቅም  እሷን በተመለከተ ዝንፈት የለበትም...እናም ገፍታ ልትከራከረው አቅም  አላገኘችም።ለተወሰነ ደቂቆች በዝምታ እያሰላሠለች ጅኑን መሳብ ጀመረች።ድንዝዝ እንዲላት ፈልጋለች። ለዛሬም ቢሆን እንኳን  ሁሉን ነገር መርሳት።

"እስቲ ስለራስህ ንገረኝ...ስለእሷ...አበሳጭታህ  ስለሞተችው ሴት"

‹‹እርግጠኛ ነሽ መስማት ትፈልጊያሽ?››

‹‹አዎ በደንብ›› አለችና ለመስማት አቆብቆበች….አቀማመጧን አስተካከለች…ማውራት ጀመረ

‹‹የሶስት አመት ፍቅረኛና የአራት አመት ባለቤቴ ነች፡፡ከባለጉዳይ ጋር ስዳረቅ እና ከሀለቃዬ ጋር ስጨቃጨቅ ቆይቼ በድካም ውልቅልቅ ብዬ ወደ ቤቴ ስመጣ  በገዛ አልጋዬ ላይ ከገዛ ጓደኛዬ ጋር ተኝታ ደረስኩ።ከመተኛቷ በላይ ያበሳጨኝ ከእኔ ጋር ስትተኛ ሰምቼው የማላውቀውን በደስታ የመቃተት ድምፅ መስማቴ ነው። የወሲብ ፊልም አክተሮች እራሱ እሷ እያለከለከች እንዳለው አያለከልኩም። ለማንኛውም በአፍላ ስሜት ነቅናቂ ሙዚቃ በታጀበ ተራክቦ ላይ እያሉ ደረስኩባቸው።

እሱ በመስኮት ዘሎ ፈረጠጠ..እሷን ያዝኳት..።
👍846😁2👏1