#ግማሽ_ስኒ_ማክያቶ
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
፡
፡
እንዴት ብዬ እንደምነግረው ባሰብኩ ቁጥር ክፉኛ እያላበኝ ነው።
ከቀጠሯችን ሰዓት አንድ ሰዓት ቀድሜ የደረስኩት ሐሳቤን ሰብስቤ የምናገረውን አስቤ፣ መንፈሴን አረጋግቼ እንድጠብቀው ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ከምን ጀመሬ ምን ላይ እንደምጨርስ፣ ምን ስለው ምን እንደሚለኝ እያሰብኩ፣ ጭንቀቴ ናረ። ከሦስት ዓመታት በላይ አብረው በጓደኝነት የከረሙትን ወንድ፣
ካንተ ፍቅር ይዞኛል!” የሚባለው እንዴት ነው?
ከምንድነው የሚጀመረው?
በምን ቃላት ነው የሚወራው?
ካፌ ውስጥ ይሻላል ወይስ መናፈሻ?
ቁጭ ብሎ ይሻላል እየሄዱ?
ዐይን፣ ዐይኑን እያዩ ወይስ ጣራ ጣራ እያሉ?
መናገሩንስ ነገርኩት እንበል፡፡ ተነስቶ ጥሎኝ ቢሄድስ? ሰው ፊት
ከት ብሎ ቢስቅብኝስ? የሚናገረው ጠፍቶበት ዝም ብሎ ቢያየኝስ?
ከዚህ ሁሉ ብሶ ደግሞ፣ “ኧረ... ይደብራል... እኔ እኮ ልክ እንደ
እህቴ ነው የማይሽ” ብሎ ቢያሸማቅቀኝስ?
እንዴት ብዬ እንደምነግረው ባሰብኩ ቁጥር፤ እጄን፣ ግንባሬን
መቀመጫዬን እያላበኝ ነው፡፡
ግማሾቹ ጓደኞቼ ፣ ለመንገር ስለዘገየሽ፣ አሁን የሚያይሽ እንደወንድ
ጓደኛው ወይ እንደ እህቱ ስለሆነ አፍሽን አታበላሺ” አሉኝ፡፡ ሌሎቹ
ደግሞ፣ ካለመናገር ማርቆስን የመሰለ ሸበላ ይቀራል፡፡ ንገሪውና ያበጠው ይፈንዳ” ብለው መከሩኝ፡፡
ምን ዋጋ አለው ከነገሩ በፊት እኔ በጭንቀት አብጄ መፈንዳቴ ሳይሆን አይቀርም፡፡
ኡ....ፍፍፍ......
ሳልጠጣው የቀዘቀዘውን ሻይ ለመቅመስ ጆሮ የሌለውን ስኒ አነሳሁ፡፡
ያለልክ ያላበው እጄ ፣ ልይዘው ስላልቻለ አዳልጦት ቀጥ ብሎ
መሬት ላይ ከ......ሽ!
ደነገጥኩ፡፡ ስኒ ስለሰበርኩ አልነበረም የደነገጥኩት፡፡
ገና ሳይመጣ፣ ገና ሳልነግረው፣ ገና አልፈልግሽም ሳይለኝ፤ እንዲህ እቃ መፍጀት ከጀመርኩ ይህ ቀን እንዴት ነው የሚያልፈው?
አስተናጋጇ እየሮጠች መጣችና፣ “ውይ... አይዞሽ... አይዞሽ ፈሰሰብሽ እንዴ?” አለችኝ፡፡
ጭንቅላቴን በአልፈሰሰብኝም ነቀነቅኩና የተሰባሰረውን ብርጭቆ
በፕላስቲክ አካፋ ታግዛ ስትጠርግ፣ ፈዝዤ ዐየኋት፡፡
አይዞሽ እዚህ ቤት ለእቃ አናስከፍልም...” አለችኝ፡፡
ትካዜዬ፣ ያስከፍሉኛል ከሚል ጭንቀት የመጣ መስሏት ነው፡፡
ኣይ... እከፍላለሁ... ችግር የለም...” አልኳት፡፡
“አናስከፍልም... ሌሳ ሻይ ላምጣልሽ?” አለችኝ፣ መጥረጎን ጨርሳ እያየችኝ፡፡
ማርክ መጥቶ ፣ እወድሃለሁ ስለው ፣ እኔ አልወድሽም ሕይወቴ ሲበላሽ ከማይ ፤ የአይጥ መርዝ ወይ በረኪና አምጪልኝ
ድፍት ብዬ ልረፍ፡፡” ልላት እየፈለግኩ፤
“እሺ... አምጪልኝ... አመሰግናለሁ” አልኳት፣ ፊቴ ላይ የውሸት ፈገግታ ለመሥራት እየታገልኩ፡፡
“ያመመሽ ትመስያለሽ... ደህና አይደለሽም እንዴ?”
እንዴት አይነት መልካም ልጅ ናት?
“አሞኛል እናቴ... ካመመኝ ቆየሁ... መድኀኒቱ ግን በሽታዬ ነው” ልላት እየፈለግኩ፤
“አይ ደህና ነኝ... ትንሽ... ትንሽ ደክሞኝ ነው...” አልኳት፡፡
“ለማንኛውም ውሃ ላምጣልሽ... አይሻልም?”
“እሺ.. ጥሩ ሐሳብ ነው... አምጪልኝ...”
ሄደች፡፡
ሰዐቴን ዐየሁ፡፡ ዐሥራ አንድ ሰዐት ከሃያ፡፡ ማርክ አለወትሮው
አርፍዷል፡፡ ያውም ሙሉ ሃያ ደቂቃ፡፡
እግዜር ሐሳቤን እንድቀይር ዕድል እየሰጠኝ ነው? እግዜር ተናግሬ
አፌን እንዳላበላሽ ማሰላሰያ ጊዜ እያዘጋጀልኝ ነው?
ልጅቱ ሻዩን እና ውሃውን ስታመጣልኝ ማርክም ወደ ካፌው ሲገባ ዐየሁ፡፡
አርዝሜ ተነፈስኩ፡፡
ኡ....ፍ.....
“መርከብዬ.... ሶሪ የኔ ቆንጆ... ብዙ አስጠበቅኩሽ አይደል?” አለ፣ጉንጬን ስሞኝ ሲቀመጥ፡፡
“አይ... ገና አሁን መድረሴ ነው እኔም..." አልኩ፣ ዐይኖቹን እየሸሸሁ፡፡
ለምን እንደዋሸሁ አልገባኝም፡፡
“ውይ አሪፍ... ጃሙ ናይትሜር ነበር ሜክሲኮ ጋር ... ! ለነገሩ እኔም አርፍጄ ተነስቼ ነው...”
“የት ነበርክ?” አልኩት፣ ደፈር ብዬ እያየሁት፡፡
አዘውትሮ የሚለበስውን ግራጫ ጃኬት፣ በጥቁር ቲ-ሸርት ከጂንስ ሱሪ ጋር ለብሷል፡፡
መረጋጋት አለብኝ፡፡ መረጋጋት አለብኝ፡፡
“ፒያሳ ነበርኩ... የመኪና ኢንሹራንስ ልከፍል...”
እና ቆይ እዚህ ካፌ ነው የምነግረው? ለነገሩ ብዙ ግርግር የለውም፡፡ከእኛ ሌላ ሦስት ሰዎች ከርቀት ተቀምጠው ሞባይላቸውን ይጎረጉራሉ፡፡ ሌላው ቦታ እረጭ ብሏል፡፡ ሙዚቃ እንኳን አልተከፈተም፡፡
" እ.. እሺ...” አልኩና ውሃዬን ሳብኩ፡፡
“ምን ሆነሻል ዛሬ... ፊትሽ ጥሩ አይደለም...” አለና ቀኝ እጁን ትኩሳት በመለካት አይነት ግንባሬ ላይ አሳረፈ፡፡
በቅርብ ርቀት ያለው ረጅም አፍንጫዬ ጠረኑን ከእጆቹ ቀሰመ።
ይሄ... ይሄ ንጹህ ንጹህ ... ፤ እሱን እሱን... ፤ ማርክ ማርክ፤
የሚለው ችግር ውስጥ የሚከተኝ ጠረኑ....
“መርከብ...”
“ወዬ ማርክ...”
“አሞሻል? ታተኩሻለሽ እኮ...” እጁን ከፊቴ ሳይ አንስቶ እጄን ያዘ፡፡
“ደህና ነኝ... ጉንፋን ሊይዘኝ ይሆናል... እሺ... ታዲያ ኢንሹራሱን
ጨረስክ?” አልኩት ወሬ ቅየራ፡፡
እና ቆይ ይሄን የመኪና ኢንሹራንስ ወሬ ቀይሬ ነው፣ “እወድሃለሁ፤
ላገባህ... ልወልድልህ እፈልጋለሁ” የምለው? መስፈንጠሪያ ወሬዬ
ይሄ ነው?
“አዎ... ግን ዋናው ጉዳይ እሱ አይደለም...” ብሎ ሲጀምር፣
አስተናጋጇ መጥታ የሚፈልገውን ጠየቀችው፡፡
“ጥቁር ማኪያቶ...” አለና ልጅቱ ስትሄድ....
“ፋሲል ጋር ነበርኩ... እና መርከብዬ... የሠራችልን ልጅ... እንዴት እንደምታምር? . .
እህ? ምንድነው የሚለኝ?
"ማናት የምታምረው?” አልኩ፣ ውሃውን አንስቼ መጠጣት እየፈለግኩ፣ እጄን እና አንጎሌን ማስተባበር አቅቶኝ ዝም ብዬ በደመነፍስ እያየሁት፡፡
"ሆሳዕና የምትባል ልጅ... የገረመኝ ፋሲል ከእሱና ካንቺ ጋር እንደተማረች አይነግረኝም? ይህችን የመሰለች ፅጌረዳ የት ደብቀሽብኝ ነው በናትሽ?”
ሆሳዕና ሆሳዕና....? የኮሌጅ የክፈል ጓደኞቼን በፍጥነት በአእምሮዬ
አመላለስኩ፡፡ አልመጣችልኝም፡፡
“ሆሳዕና ሆሳዕና? ...አላውቃትም.. ይልቅ ማርክዬ. ዛሬ ለቁም ነገር
ነው የፈለግኩህ...” አልኩ፣ ማርሹን አሁን ካልቀየርኩ ነገሮች አቅጣጫቸውን እየሳቱ መሆኑ ስለገባኝ ቆፍጠን ብዬ፡፡
“ኧረ በናትሽ... ሆሳዕና ጌታነህ... በጣም ቀይ... መሠረት መብራቴን የምትመስል፤ ግን ከእሷ የምትበልጥ... በጣም ቆንጆ... ፍዝዝ የምታደርግ.... እሷ ወዲያው...አውቃሻለች እንዴት ትዝ
አትልሽም?”
ወይ ጉድ... ይሄ ነገር ምንም እንዳሰብኩት እየሄደ አይደለም፡፡
"የእኛ ባች ካልሆነች ረስቻት ይሆናል...
እና ማርክ... ወደ ጉዳዬ
ልግባ... ተረጋግተህ ስማኝ...”
ያንቺ ባች አይደለችም...” አለ፣ ቶሎ ብሎ፡፡
ለምንድን ነው የማይሰማኝ? ይህቺ በድንገት ሕይወቴ ውስጥ ገብታ
የምትበጠብጠኝ መሠረት መብራቴን መሳይ ሆሳዕና ማናት?
“ምን ዲፓርትመንት ነበረች?” አልኩት፣ ስልችት እያለኝ::
“ኤፍ ቢ ነበረች... ባስኬት ቦል ሁሉ ትጫወት ነበር
ረጅም ናት... የሚገርም ሰውነት..”
ይሄን ሁሉ መረጃ ከምኔው ቃርሞ መጣ ማናት?
ጠንከር አድርጌ አሰብኩ ፤ ሆሳዕና ጌታነህ ... ሆሳዕና ጌታነህ ....
እንዴ! መጣችልኝ፡፡
የቁንጅና ውድድር አሽንፋ ሚስ ኤኤዩ የሆነችው ባልሆነች... ናት መሰለኝ...
“ሚስ ኤኤዩ ነበረች መሰለኝ..እሷ ናት..?” አልኩኝ በማመንታት፡፡
“የስ! ፋሲል ስንመጣ እየነገረኝ ነበር... ለነገሩ ባትሆን ነበር የሚገርመኝ..."

👍1