አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#እንደምነሽ #ሸገር

በውቀቱ ስዩም ከአሜሩካ

እንደምነሽ ሸገር የቤት አከራዬ የጋሽ ጣሰው አገር የምትተከዪ የምትነቀዬ የዘመቻ ድንኳን
ብጉርና ችግር ከአባቴ ወርሼ ብኖርብሽ እንኳን
የማልቀያምሽ ሁሌ የማልምሽ
ኦ ማይ ጎድ ይመስገን እኔ እንዳለሁ አለው
ግማሽ እሩዝና ግማሽ ጤፍ በልቼ
አዋጅ እና ዜና ከአደባባይ ሳይሆን ከአይፎኔ ሰምቼ
ሀሜት ሲናፍቀኝ በስካይፒ አምቼ
ጥቃት ሲሰማኝ ፊስቡክ ላይ ሸፍቼ
በኮመንት እሩምታ ጠላቴን ደፍቼ
እኔ እንዳለው አለው
እንደምነሽ ሸገር እንደምነሽ ሸገር
የማይበገረው ወር እየጠበቀ የሚያገራግረው
የቤት አከራዬ የጋሽ ጣሰው አገር
የከሰመው ወንዝሽ የሚታየው ነጥፎ
እንደምነው ጣፎ እንዴት ነው ቀበና
እስቲ ድንጋይ ላጥምድ መረብ ልጣልና
ልክ እንደነ ፓሪስ እንደለንደን ሁላ
ፋፋቴም ባይኖርሽ ሽቅብ የሚፈላ
ምንጭሽ ከማን ያንሳል
ከፈነዳ ትቦ የወጣ ሰገራ ሰንጥቆሽ ይፈሳል
እንደምነሽ ሸገር የቅጠላቅጠል የፍራፍሬ አገር
አንድ ዘለላ ሙዝ ልጠሽ ባታበይኝ
በሙዝ ልጣች ጠልፈሽ የምታከባልይኝ
አሳድገሽኛል አሳድገሽኛል በማርና ወተት
የተሞላ ተረት እየተረክሽልኝ
ጥማቴን በጥማት እያረካሽልኝ
እንደምነሽ ሸገር ኦ ማይ ጎድ ይመስገን
እኔ እንዳለው አለው ሰርቼ ቀፍዬ
ሲነጋ ቀፍዬ ሲመሽም ከፍዬ
ስጋ ምታወፍር ነብስ የምታሳሳ
ዘናጭ አልጋ ሰታ እንቅልፍ የምትነሳ
አገር ላይ ተጥዬ
#እንደምነሽ_ሸገር

እንደምነሽ ሸገር
እንደምነሽ ሸገር
የቤት አከራየ፥ የጋሽ ጣሰው አገር
እንዱ የሚተከልሽ
ሌላው የሚነቅልሽ
የዘመቻ ድንኳን፤

ቡግርና ችግር፥ ካባቴ ወርሼ
ብኖርብሽ እንኳን
የማልቀየምሽ
ሁሌ የማልምሽ፣

Oh, my God ይመስገን
እኔ እንዳለሁ አለሁ፤

ከፊል ሩዝና፥ ከፊል ጤፍ እቡክቼ
እንጀራ ሚመሰል፥ ሰጋጃ በልቼ
አዋጅና ዜና፥ ባይፎኔ ሰምቼ
ሐሜት ሲናፍቀኝ፥ በፓልቶክ አምቼ
ጥቃት ሲበዛብኝቱ ፌስቡከ ላይ ሸፍቼ
በኮመንት ሩምታ፥ ጠላቴን ደፍቼ
እኔ እንዳለሁ አለሁ፤
እንደምነሽ ሸገር
እንደምነሽ ሸገር
የማይበገረው
ወር እየጠበቀ፥ የሚያንገራግረው
የቤት አከራየ፥ የጋሽ ጣሰው አገር፤
የከሰመው ወንዝሽ
የነጠፈው ወዝሽ
የሚታየው ነጥፎ
እንደምነው ጣፎ
እንዴት ነው ቀበና
እስቲ ድንጋይ ላጥምድ፥ መረብ ልጣልና፤

ልከ እንደነ ፓሪሰ
እንደ ለንደን ሁላ
ፏፏቴም ባይኖርሽ፥ ሽቅብ የሚፈላ
ምንጭሽ ከማን ያንሳል
ከፈነዳ ቱቦ፥ የወጣ ሰገራ፥ ሰንጥቆሽ ይፈሳል፤

እንደምነሽ ሸገር
የቅጠላቅጠል፥ የፍራፍሬ አገር
አንድ ዘለላ ሙዝ፥ ልጠሽ ባታበይኝ
በሙዝ ልጣጭ ጠልፈሽ፥ ምታንከባልይኝ
አሳድገሽኛል፥ በማርና ወተት
የተሞላ ተረት
እየተረከሽልኝ
ጥማቴን በጥማት እያረካሽልኝ፤

እንደምነሽ ሸገር
Oh my God ይመስገን
እኔ እንዳለሁ አለሁ፤

ሰርቼ ቀፍየ
ሲነጋም ከፍየ
ሲመሽም ከፍየ
ሥጋ ምታወፍር፥ ነፍሶ የምታሳሳ
ዘናጭ አልጋ ሰጥታ፥ እንቅልፍ የምትነሳ
አገር ላይ ተጥየ።

🔘በውቀቱ ስዩም🔘